ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ምድረገነት ሽሬ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ምድረገነት ሽሬ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሽመክት ጉግሳ በ54ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል ምድረገነት ሽሬን መሪ አድርጓል።

አዛርያስ አቤል በ88ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ወላይታ ድቻ አንድ ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል።


 

ውጤቱን ተከትሎ ምድረገነት ሽሬ በ13 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

ወላይታ ድቻ በሰባት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም