ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በአማራ ክልል ፋይዳ መታወቂያን ለሁሉም የመሬት ባለይዞታዎች ተደራሽ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው
Jan 17, 2026 14
ባሕር ዳር፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም የመሬት ባለይዞታዎች ተደራሽ በማድረግ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ግብ መያዙን በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር) ገለፁ። "የፋይዳ መታወቂያ ለሁሉም የክልላችን መሬት ባለይዞታዎች" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል። ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ስኬታማ ለማድረግ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል። በክልሉ ፋይዳ መታወቂያን ተደራሽ ለማድረግ በተሠራው ሥራ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም በገጠሩ አካባቢ ለሚኖረው የገጠር መሬት ባለይዞታ አርሶ አደር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በአጭር ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ ግብ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ይህም የመሬት ዘርፉን በማዘመን፣ ፍትሐዊ አሠራርን በማስፈንና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስችላል ነው ያሉት። አርሶ አደሩ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆንና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ግብ መሳካት በየደረጃው የሚገኘው አመራር ተቀናጅቶ በመሥራት የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል። የክልሉ መሬት ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ በበኩላቸው፤ እየተገነባ ያለውን ዲጂታል የመረጃ አሥተዳደር ሥርዓት ውጤታማ ለማድረግ የመሬት አሥተዳደር ሥርዓቱን ከዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር እየተሠራ ነው ብለዋል። በዚህም በክልሉ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ለገጠር መሬት ባለይዞታዎች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም የገጠር መሬት ባለይዞታ አርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ የተያዘው ግብ እንዲሳካም በየደረጃው አመራሩ ተቀናጅቶ በመሥራት የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በክልሉ የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጓል - የክልሉ ፖሊስ
Jan 17, 2026 17
ወላይታ ሶዶ ፤ጥር 09/2018 (ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተራ እና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ደግፌ ደበላ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተራ እና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጓል። ለበዓሉ ስኬታማነት በየመዋቅሩ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነሩ ከጸጥታ መዋቅሩና ከመላው ህዝቡ ጋር በመወያየት ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል። የትራፊክ ፖሊሶችም የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን በሚገባ መቆጣጠርና ለተሽከርካሪ ዝግ በሆኑ መንገዶች ተለዋጭ መንገዶችን በተገቢው እንዲያሳልጡ ስምሪት መሰጠቱን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ በዓሉ በሚከበርባቸው እና ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ላይ ከመደበኛ እንቅስቃሴ የተለየ ነገር ሲመለከት እና የወንጀል ስጋቶችን ሲያጋጥም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር እንደሚገባም ገልጸዋል።
በዞኑ የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Jan 17, 2026 16
ገንዳውኃ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- በምዕራብ ጎንደር ዞን የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ የተለያዩ ተግባራት እያከናወኑ መሆኑን ወጣቶች ተናገሩ። በምእራብ ጎንደር ዞን በዘንድሮው የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ23 ሺህ በላይ ወጣቶች በልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የዞኑ የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል። በዚሁ ተግባር ላይ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል በረከት ዳኘ እና ታያቸው ጥላሁን፤ በአገልግሎታቸው ከተለያዩ አካላት የተገኙ ድጋፎችን በመሰብሰብ ለአቅመ ደካሞች ምግብና አልባሳት ማድረሳቸውን አንስተው የቤት እድሳትና ሌሎችም ተግባራት ላይ በመሳተፍ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በአጠቃላይ ማህበረሰቡን በተለይም አቅመ ደካሞችን በነፃ በማገልገላቸው ደስተኞች መሆናቸውን አንስተዋል። በበጋው ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን የተናገሩት ወጣቶቹ አጠናከረው የሚቀጥሉ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በገንዳውኃ ከተማ የሚኖሩት አቶ መኮንን ረታ፤ በአቅም ማነስ ምክንያት ቤታቸውን ለማደስ ተቸግረው መኖራቸውን አስታውሰዋል። በዘንድሮው የበጋ ወራት ወጣቶች ቤታቸውን አድሰው ያስረከቧቸው በመሆኑ በእጅጉ መደሰታቸውን ተናግረዋል። በወጣቶች እየተከናወኑ ያሉ መሰል ተግባራት የእርሳቸውን ጨምሮ የብዙዎችን ችግር በመፍታቱ ምስጋናቸውን አቅርበው ስራው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። በምእራብ ጎንደር ዞን የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የወጣቶች ማካተት ቡድን መሪ ሀይለየሱስ መኮንን፤ በዞኑ በበጋው የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ከ23 ሺህ በላይ ወጣቶች በልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል። የወጣቶቹ አገልግሎት በቤት እድሳት፣ በጤና አገልግሎት ድጋፍ፣ በግብርና፣ በድጋፍ ስራዎችና ሌሎችም ተግባራት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ እስካሁን የ10 አቅመ ደካሞችን ቤቶች በአዲስ የመገንባትና የመጠገን ስራ መከናወኑን ጠቅሰው በሰብል መሰብሰብ፣ የደም ልገሳ፣ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃና ሌሎችም ስራዎች ላይ በስፋት እየተሳተፉ ነው ብለዋል። በዚህም እስካሁን ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው ስራው ቀጣይነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ራሳቸውን እንዲችሉ እየተደረገ ነው
Jan 17, 2026 25
ጅማ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በከተማ ማስዋብ ዘርፍ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ራሳቸውን እንዲችሉ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ገለጸ። በጅማ ከተማ በልማታዊ ሴፍቲኔት ታቅፈው በከተማ ማስዋብ ሥራ ተሰማርተው የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ አባዎራዎች እና እማዎራዎች ራሳቸውን ችለው ወደ ሥራ ተሸጋግረዋል። በዚሁ ወቅት የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ በቀለ፤ የክልሉ ከተሞች መኖሪያ ብቻ ሳይሆኑ የማምረቻ ስፍራ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት በዝቀተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በልማታዊ ሴፍቲ ኔት ታቅፈው በተለያዩ የከተማ ጽዳት እና ውበት ሥራዎች ተሰማርተው ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ እየተደረገ ነው ብለዋል። እነዚህ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ በመቆጠብ በሚፈልጉት የሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ዛሬ በጅማ ከተማ የተሸጋገሩት የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በከተሞች ያለውን የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ችግሮች ከከተማ ልማት ጋር በማስተሳሰር መፍትሔ ለመስጠት የተጀመረው ሥራ እንደሚጠናከርም አረጋግጠዋል። የጅማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አሥራት እሸቴ በበኩላቸው፤ በልማታዊ ሴፍቲኔት አማካኝነት በከተማ ውበት ሥራዎች ተሰማርተው የቆዩ 3 ሺህ 90 አባዎራዎች ወደ አምራችነት ተሸጋግረዋል ብለዋል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖች የሥራ እና የቁጠባ ባህልን በማጎልበት አምራችነታቸውን የማሳደግ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወንም አመላክተዋል። በመርሐ-ግብሩ ታቅፈው ዛሬ ከተሸጋገሩት መካከል አስረስ መንግሥቱ፤ ከገቢያቸው በመቆጠብ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመለወጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በተመቻቸላቸው ዕድል ከትንሽ ንግድ ጀምረው አሁን ጥሩ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን የተናገሩት ደግሞ አስናቀች በቀለ ናቸው።
የከተማው ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት 17 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ
Jan 17, 2026 38
ነቀምቴ፤ ጥር 9/2018(ኢዜአ)፡-የነቀምቴ ከተማ ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ባለፉት ስድስት ወራት በራሱ አቅም 17 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ወገኖች ማድረጉን ገለጸ። ቡሳ ጎኖፋ ከገዳ ስርዓት የመነጨ እና ችግሮች ሲያጋጥሙ በራስ አቅም እንዲሁም እርስበርስ በመረዳዳት ችግሮችን ለማለፍ ታልሞ እየተተገበረ መሆኑ ይታወቃል። በኦሮሚያ ክልል የቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ተቋቁሞ በየጊዜው የሚያጋጥሙ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች በራስ አቅም ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ ነው። የነቀምቴ ከተማ ቡሳ ጎኖፍ ቅርንጫ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ምስጋኑ ወጋሪ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ በከተማው በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያት ለሚከሰቱ ችግሮች በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት እየሰራ ነው። ጽህፈት ቤቱ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የቅድመ ጥንቃቄ ስራ መስራት፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ ማገዝ እና መልሶ የማቋቋም ስራ እየሰራ ነውም ብለዋል። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት የመንግስት እና የግል ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በጎርፍ እና በሌሎች ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ 15 ሺህ ዜጎች የቁሳቁስ እና የምግብ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች 17 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን 5 ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎችም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ቤት ምገባም በጽህፈት ቤቱ አማካኝነት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህልን በማጠናከር በከተማዋ የሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችን የማገዝ ስራ የሚጠናከር መሆኑንም ገልጸዋል። በነቀምቴ ከተማ በጽህፈት ቤቱ ከሚደረግላቸው ድጋፍ ባሻገር የመኖሪያ ቤት የተገነባላቸው ወይዘሮ ብርቄ ኢረና፣ ቤታቸው በእርጅና ምክንያት በመፈራረሱ ክረምት ከበጋ በብርድና በጸሃይ ሲቸገሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል። በጽህፈት ቤቱ የገነባላቸው ቤት ህይወታቸው ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸው አሁን ችግራቸውም እንደተቃለለላቸውም ተናግረዋል።
ፖለቲካ
የምክክር ሂደቱ ችግሮችን በዘላቂነት መፍቻ በመሆኑ ዕድሉን በአግባቡ መጠቀም ይገባል
Jan 17, 2026 69
ሚዛን አማን፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- የምክክር ሂደቱ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍቻና የሰላም ዕሴት መሰረት ስለሆነ ዕድሉን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የሚዛን አማን ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች አስገነዘቡ። ከሀገር ሽማግሌዎቹ መካከል ሙሴ አይነታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የጥፋት አዙሪትን በመቋጨት ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ሀገር ለመገንባት በምክክር ችግሮቻችንን መፍታት ይገባል። የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ እንዳሚባለው የራሳችንን ችግሮች በራሳችን መፍታት ይኖርብናል ብለዋል። የትኛውንም የግጭትና የልዩነት ዕሳቤ በምክክር፣ ዕርቅና ይቅርታ ከመፍታት የሚሻል አማራጭ የለም ያሉት ደግሞ ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ ምትኩ ሾሻ ናቸው። በሀገር ጉዳይ በመምከር መፍትሔ እናምጣ ብሎ መገናኘት መልካም ሐሳብ በመሆኑ ውጤት የሚያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ ተስፋዬ ዘካርያስ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ አንድነትን፣ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ የሚቻለው ልዩነቶችን በምክክር እየፈቱ ለሰላም መትጋት ሲቻል መሆኑን ጠቁመዋል። ያልተጠቀምንባቸው የካበቱ ዕሴቶች ስላሉ ለሀገር ሰላምና ልማት እንጠቀምባቸው ብለዋል። ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካትም የሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለብን ተገንዝበን በዚህ ልክ መትጋት ይጠበቅብናል ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌዎቹ።
ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት ያጠናክራል - አቶ አደም ፋራህ
Jan 16, 2026 95
ሆሳዕና፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፡- ብልጽግና ፓርቲ በየዘርፉ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት እንደሚያጠናክር የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ። በሆሳዕና ከተማ ሲካሄድ የቆየው የፓርቲው የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም መድረክ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ገበያን ለማረጋጋት የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም ተጠናቋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ እንደገለጹት፣ የብዝሀ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል። ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማስፋት በተከናወኑ ተግባራት ባለፋት 6 ወራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ የተገኙ ድሎችን ለማላቅ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግና የሥራ ዕድል የሚያስገኙ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ የሥራ አጥ ልየታን፣ ነባር ኢንተርፕራይዞችን የማጠናከርና የብቃት ምዘና ተቋማት ሥራ በጥራት እንዲከናወን በልዩ ትኩረት መምራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ገበያን ለማረጋጋት በተሰሩ ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እንዳሉ ገልጸው ይህን ለማጠናከር የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ ለዚህም የግብይት ማዕከላትን የማስፋት፣ የምርት ጥራትን የማስጠበቅ፣ ህብረት ስራ ማህበራትን የመደገፍና የፓርቲው የአንድ ግብ የሆነውን ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የግብይት ማዕከል በአንድ ከተማ ግንባታ ስራን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ ብልጽግና ፓርቲ በተለያዩ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት ያጠናክራል ሲሉም ገልጸዋል። ለዚህም በየዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት የተገኙ ስኬቶችን በማላቅና ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ የአመራሩ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ኃላፊዎችና የወጣቶች ክንፍ አመራሮች ተሳትፈዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
አሰባሳቢና ገዢ ትርክት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚና መጎልበት አለበት
Jan 16, 2026 78
ሐረር ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል አሰባሳቢና ገዢ ትርክት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚናቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተመለከተ። በሐረሪ ክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሚናቸውን ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄዷል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ፣ መልካም እሴቶች እንዲጎለብቱ እና ህዝቡ በክልሉ በሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያስቻሉ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል። በተለይም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ፅንፈኛ ሀይሎች በማህበረሰቡ መካከል የሚነዙትን የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃዎችን በመከላከል አሰባሳቢና ገዢ ትርክቶች እንዲሰርጹ በማድረግ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም አፍራሽ የሆኑ ፕሮፓጋንዳዎችን ቀድሞ በመከላከል የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅና ሕብረ ብሄራዊነት እንዲሰርፅና እንዲፀና በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች እና ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ለተመዘገቡ ውጤቶች አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም አንስተዋል። በተጨማሪም የህዝብ ሰላምና አንድነት እንዲጎለብትና የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አዎንታዊ ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በበኩላቸው፤ የክልሉ ህዝብ የሚታወቅበት የሰላም፣ መቻቻልና አብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በተለይም የጋራ የሚያደርጉ ሀገራዊ እሴቶችን በማጠናከርና ገዢ ትርክትን በመገንባት ሰላምና ልማት እንዲጠናከር እያበረከቱ የሚገኘው ተግባር ይበልጥ መጎልበት አለበት ብለዋል። የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችም የሚያስተላለፉት መልዕክት ሀገርን የሚገነባ፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን የሚሰብክ እንዲሁም ህብረተሰቡ በልማት እንቅስቃሴው ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።
ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንሰራለን -አምባሳደሮች
Jan 15, 2026 116
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፡ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ 14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያቀረቡትም የኪርጊስታን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ ላቲቪያ ሀገራት አምባሳደሮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ማብራሪያ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደሮቹ ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። በውይይቱ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው ለውጥ አድናቆት መስጠታቸውን ጠቁመው፥ ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ልምድና ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የጣልያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በትምህርት፣ በክህሎት፣ በሳይንሳዊ እና በባህል ትብብር ዙሪያ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በሚኖራቸው ቆይታ ጣልያን ለኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ መሆን የምትችልባቸውን መንገዶች ለማየት እንደሚጥሩ ጠቁመዋል። አዲስ የተሾሙት የዛምቢያ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ በበኩላቸው በግብርና ማለትም በተሻሻሉ የሰብል ዝሪያዎች ላይ ልምድ በመለዋወጥ እና በስፋት በመተግበር ምርታማነትን ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልፀዋል። የኬንያ አምባሳደር ጋልማ ሙክሄ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ እና በሌሎች በርካታ ዘርፎች ላይ ይህን ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ባክ ቫለንቲኖ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ይህንንም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሌሎች አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አመላክተዋል:: የፊሊፒንስ አምባሳደር ማሬ ቻርሎቴ በቀጣዩ አመት ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን የምስረታ በአላቸውን እንደሚያከብሩም ተናግረዋል። በሁለቱ አገራት መካከል በፖለቲካ፣በኢኮኖሚ እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር እንደሚሰራ አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ
Jan 15, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፡- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ታዬ ያቀረቡት፤ የደቡብ ሱዳን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ ኪርጊስታን እና የላቲቪያ አምባሳደሮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ማብራሪያም፤ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ መሆኑን አስታውቀዋል። ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም ሀገሮቻቸው በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ አምባሳደሮቹ ከፕሬዚዳንት ታዬ ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። በውይይቱ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ማድነቃቸውንም አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት።
የአውሮፓ ሕብረት እና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች ናቸው - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)
Jan 15, 2026 101
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የአውሮፓ ሕብረትና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ኡሎፍ ስኩጊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ በውይይታቸውም የአውሮፓ ሕብረትና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግንኙነቱ በጋራ ዕሴቶች እና ተስፋዎች ላይ የተመሰረተ ወሳኝ አጋርነት መሆኑንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደት የምታደርገውን ጥረት ያነሱት ሚኒስትሩ እንቅስቃሴው ከአውሮፓ ህብረት ግሎባል ጌትዌይ ኢኒሼቲቭ(Global Gateway initiative) ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸው በቀጣናው ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነትም ተናግረዋል። እየተከናወነ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የአውሮፓ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የበለጠ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ኡሎፍ ስኩጊን በበኩላቸው ህብረቱ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሚያደርገውን ድጋፍና ስትራቴጂያዊ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሆና በመመረጧ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያን የልማት ውጥኖች ከግብ ለማድረስ ህብረቱ አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እደሚያመለክተው በውይይታቸው ሁለቱም ወገኖች በጋራ ጥቅም ላይ በሚያተኩሩ ጉዳዮች አብረው ለመስራት ተስማምተዋል።
የክልሉን የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር ነው
Jan 15, 2026 79
አዲስ አበባ፤ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ያለውን ሰፊ የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) ገለፁ። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ትብብር የተዘጋጀው የፓናል ውይይት "ሰላምን ማጽናት፤ፀጋን ለማልማት"በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) በክልሉ የተከናወኑ "የሰላምና ፀጥታ ስራዎችና እምርታዎች" በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጽሁፋቸው በክልሉ ሰላምን ለማጽናት የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተገኙ የሰላም እመርታዎችን ጠብቆ ማስቀጠል ለልማት ስራዎች መሳካት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የህዝቡን ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች በክልሉ ልማትን ለማፋጠን ወሳኝ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ ያለውን ሰፊ የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው፤ "የክልሉ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች” በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጽሁፋቸውም ክልሉ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑና ያልተነኩ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፀጋዎች ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ለማዕድን፣ ለቱሪዝም፣ ለእንስሳት ሀብት ልማት፣ ለውሃ እና ለመሬት ልማት ምቹ የሆኑ በርካታ ዕድሎች መኖራቸውን አብራርተዋል። የክልሉ የሥነ-ምህዳር አወቃቀርና ምቹ የአየር ንብረት ለግብርና ዘርፍ ዕድገት እምቅ አቅም እንዳለው ጠቁመዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርስነት የተመዘገቡ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ተፈጥሯዊ መስህቦች እና የማይዳሰሱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች የክልሉ የቱሪዝም ሀብት መገለጫ ናቸው ብለዋል። እነዚህን ሀብቶች በተገቢው መንገድ በማልማት የቱሪዝም ዘርፉን የኢኮኖሚ ምሰሶ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል። በክልሉ የሚገኙ የከበሩ ማዕድናት፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና ለኢንዱስትሪ ልማት አመቺ ሁኔታዎች ለኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እነዚህን የተፈጥሮ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች በአግባቡ በመጠቀም የክልሉን አልፎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ የግል ባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት የክልሉ መንግስት ለባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው "የአማራ ክልል የልማት ተስፋዎችና የህዝብ ተጠቃሚነት" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ክልሉ የረጅም፣ የመካከለኛ እና የአጭር ዘመን እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል። በዚህም በ2027 የአማራ ክልል በመሠረታዊ ኢንዱስትሪ ምርቶች የራሱን ፍላጎት የሸፈነ እና የተሳካ የመዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ የክልሉን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በማቀድ እየተሰራ ነው ብለዋል። በ2042 ክልሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ የሆነ የዘመናዊ ኢኮኖሚ ባለቤት እና የበለጸገ ማሕበረሰብ ሆኖ ማየት የዕቅዱ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የክልሉን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፤ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም መገንባት ስትራቴጂክ ጉዳይ ነው ብለዋል። ክልላዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራትንም እንዲሁ። በተጨማሪ ሣይንሳዊ ዕውቀትን የማሕበረሰብ እሴት እና የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ማድረግ፤ ምርታማነትንና ቅልጥፍናን በማሳደግ ጥራት ያለው ኢኮኖሚ መገንባት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው ነው- አቶ አደም ፋራህ
Jan 15, 2026 103
ሆሳዕና፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች በሁሉም አካባቢዎች እየተተገበሩ ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። የፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የቀረበው የፓርቲው ሥራ አፈፃፀም የሚያመለክተው የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች በሁሉም አካባቢዎች የህዝብ ቅቡልነት በማግኘት እየተተገበሩ ናቸው ብለዋል፡፡ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለፓርቲው ስራዎች ውጤታማነት የሚረዳ የተናበበ እቅድ የማዘጋጀት እንዲሁም የፓርቲውን እሳቤ በመረዳት በስነ ምግባር የሚፈፅም ጠንካራ አመራር ለማብቃት በተሰራው ስራ መሻሻሎች መታየታቸውንም ገልጸዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ከህዝቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ውጤት እየተገኘ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራ እና የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲውን እሳቤዎች በመተግበር ህዝቡ ተባባሪ ሆኖ በመስራቱ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። በሁሉም አካባቢዎች ልማትን የማፋጠን እና መልካም አስተዳደር የማስፈን ስራዎች አሁንም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ገልጸው የህዝቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በፓርቲው የተያዙ ሁሉን አቀፍ የእድገትና ትራንፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለማሳካት አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎችና የወጣት ክንፍ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡
ፖለቲካ
የምክክር ሂደቱ ችግሮችን በዘላቂነት መፍቻ በመሆኑ ዕድሉን በአግባቡ መጠቀም ይገባል
Jan 17, 2026 69
ሚዛን አማን፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- የምክክር ሂደቱ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍቻና የሰላም ዕሴት መሰረት ስለሆነ ዕድሉን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የሚዛን አማን ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች አስገነዘቡ። ከሀገር ሽማግሌዎቹ መካከል ሙሴ አይነታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የጥፋት አዙሪትን በመቋጨት ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ሀገር ለመገንባት በምክክር ችግሮቻችንን መፍታት ይገባል። የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ እንዳሚባለው የራሳችንን ችግሮች በራሳችን መፍታት ይኖርብናል ብለዋል። የትኛውንም የግጭትና የልዩነት ዕሳቤ በምክክር፣ ዕርቅና ይቅርታ ከመፍታት የሚሻል አማራጭ የለም ያሉት ደግሞ ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ ምትኩ ሾሻ ናቸው። በሀገር ጉዳይ በመምከር መፍትሔ እናምጣ ብሎ መገናኘት መልካም ሐሳብ በመሆኑ ውጤት የሚያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ ተስፋዬ ዘካርያስ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ አንድነትን፣ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ የሚቻለው ልዩነቶችን በምክክር እየፈቱ ለሰላም መትጋት ሲቻል መሆኑን ጠቁመዋል። ያልተጠቀምንባቸው የካበቱ ዕሴቶች ስላሉ ለሀገር ሰላምና ልማት እንጠቀምባቸው ብለዋል። ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካትም የሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለብን ተገንዝበን በዚህ ልክ መትጋት ይጠበቅብናል ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌዎቹ።
ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት ያጠናክራል - አቶ አደም ፋራህ
Jan 16, 2026 95
ሆሳዕና፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፡- ብልጽግና ፓርቲ በየዘርፉ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት እንደሚያጠናክር የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ። በሆሳዕና ከተማ ሲካሄድ የቆየው የፓርቲው የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም መድረክ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ገበያን ለማረጋጋት የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም ተጠናቋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ እንደገለጹት፣ የብዝሀ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል። ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማስፋት በተከናወኑ ተግባራት ባለፋት 6 ወራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ የተገኙ ድሎችን ለማላቅ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግና የሥራ ዕድል የሚያስገኙ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ የሥራ አጥ ልየታን፣ ነባር ኢንተርፕራይዞችን የማጠናከርና የብቃት ምዘና ተቋማት ሥራ በጥራት እንዲከናወን በልዩ ትኩረት መምራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ገበያን ለማረጋጋት በተሰሩ ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እንዳሉ ገልጸው ይህን ለማጠናከር የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ ለዚህም የግብይት ማዕከላትን የማስፋት፣ የምርት ጥራትን የማስጠበቅ፣ ህብረት ስራ ማህበራትን የመደገፍና የፓርቲው የአንድ ግብ የሆነውን ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የግብይት ማዕከል በአንድ ከተማ ግንባታ ስራን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ ብልጽግና ፓርቲ በተለያዩ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት ያጠናክራል ሲሉም ገልጸዋል። ለዚህም በየዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት የተገኙ ስኬቶችን በማላቅና ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ የአመራሩ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ኃላፊዎችና የወጣቶች ክንፍ አመራሮች ተሳትፈዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
አሰባሳቢና ገዢ ትርክት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚና መጎልበት አለበት
Jan 16, 2026 78
ሐረር ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል አሰባሳቢና ገዢ ትርክት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚናቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተመለከተ። በሐረሪ ክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሚናቸውን ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄዷል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ፣ መልካም እሴቶች እንዲጎለብቱ እና ህዝቡ በክልሉ በሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያስቻሉ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል። በተለይም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ፅንፈኛ ሀይሎች በማህበረሰቡ መካከል የሚነዙትን የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃዎችን በመከላከል አሰባሳቢና ገዢ ትርክቶች እንዲሰርጹ በማድረግ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም አፍራሽ የሆኑ ፕሮፓጋንዳዎችን ቀድሞ በመከላከል የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅና ሕብረ ብሄራዊነት እንዲሰርፅና እንዲፀና በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች እና ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ለተመዘገቡ ውጤቶች አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም አንስተዋል። በተጨማሪም የህዝብ ሰላምና አንድነት እንዲጎለብትና የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አዎንታዊ ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በበኩላቸው፤ የክልሉ ህዝብ የሚታወቅበት የሰላም፣ መቻቻልና አብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በተለይም የጋራ የሚያደርጉ ሀገራዊ እሴቶችን በማጠናከርና ገዢ ትርክትን በመገንባት ሰላምና ልማት እንዲጠናከር እያበረከቱ የሚገኘው ተግባር ይበልጥ መጎልበት አለበት ብለዋል። የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችም የሚያስተላለፉት መልዕክት ሀገርን የሚገነባ፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን የሚሰብክ እንዲሁም ህብረተሰቡ በልማት እንቅስቃሴው ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።
ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንሰራለን -አምባሳደሮች
Jan 15, 2026 116
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፡ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ 14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያቀረቡትም የኪርጊስታን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ ላቲቪያ ሀገራት አምባሳደሮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ማብራሪያ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደሮቹ ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። በውይይቱ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው ለውጥ አድናቆት መስጠታቸውን ጠቁመው፥ ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ልምድና ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የጣልያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በትምህርት፣ በክህሎት፣ በሳይንሳዊ እና በባህል ትብብር ዙሪያ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በሚኖራቸው ቆይታ ጣልያን ለኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ መሆን የምትችልባቸውን መንገዶች ለማየት እንደሚጥሩ ጠቁመዋል። አዲስ የተሾሙት የዛምቢያ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ በበኩላቸው በግብርና ማለትም በተሻሻሉ የሰብል ዝሪያዎች ላይ ልምድ በመለዋወጥ እና በስፋት በመተግበር ምርታማነትን ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልፀዋል። የኬንያ አምባሳደር ጋልማ ሙክሄ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ እና በሌሎች በርካታ ዘርፎች ላይ ይህን ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ባክ ቫለንቲኖ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ይህንንም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሌሎች አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አመላክተዋል:: የፊሊፒንስ አምባሳደር ማሬ ቻርሎቴ በቀጣዩ አመት ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን የምስረታ በአላቸውን እንደሚያከብሩም ተናግረዋል። በሁለቱ አገራት መካከል በፖለቲካ፣በኢኮኖሚ እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር እንደሚሰራ አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ
Jan 15, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፡- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ታዬ ያቀረቡት፤ የደቡብ ሱዳን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ ኪርጊስታን እና የላቲቪያ አምባሳደሮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ማብራሪያም፤ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ መሆኑን አስታውቀዋል። ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም ሀገሮቻቸው በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ አምባሳደሮቹ ከፕሬዚዳንት ታዬ ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። በውይይቱ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ማድነቃቸውንም አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት።
የአውሮፓ ሕብረት እና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች ናቸው - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)
Jan 15, 2026 101
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የአውሮፓ ሕብረትና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ኡሎፍ ስኩጊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ በውይይታቸውም የአውሮፓ ሕብረትና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግንኙነቱ በጋራ ዕሴቶች እና ተስፋዎች ላይ የተመሰረተ ወሳኝ አጋርነት መሆኑንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደት የምታደርገውን ጥረት ያነሱት ሚኒስትሩ እንቅስቃሴው ከአውሮፓ ህብረት ግሎባል ጌትዌይ ኢኒሼቲቭ(Global Gateway initiative) ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸው በቀጣናው ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነትም ተናግረዋል። እየተከናወነ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የአውሮፓ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የበለጠ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ኡሎፍ ስኩጊን በበኩላቸው ህብረቱ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሚያደርገውን ድጋፍና ስትራቴጂያዊ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሆና በመመረጧ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያን የልማት ውጥኖች ከግብ ለማድረስ ህብረቱ አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እደሚያመለክተው በውይይታቸው ሁለቱም ወገኖች በጋራ ጥቅም ላይ በሚያተኩሩ ጉዳዮች አብረው ለመስራት ተስማምተዋል።
የክልሉን የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር ነው
Jan 15, 2026 79
አዲስ አበባ፤ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ያለውን ሰፊ የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) ገለፁ። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ትብብር የተዘጋጀው የፓናል ውይይት "ሰላምን ማጽናት፤ፀጋን ለማልማት"በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) በክልሉ የተከናወኑ "የሰላምና ፀጥታ ስራዎችና እምርታዎች" በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጽሁፋቸው በክልሉ ሰላምን ለማጽናት የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተገኙ የሰላም እመርታዎችን ጠብቆ ማስቀጠል ለልማት ስራዎች መሳካት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የህዝቡን ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች በክልሉ ልማትን ለማፋጠን ወሳኝ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ ያለውን ሰፊ የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው፤ "የክልሉ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች” በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጽሁፋቸውም ክልሉ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑና ያልተነኩ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፀጋዎች ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ለማዕድን፣ ለቱሪዝም፣ ለእንስሳት ሀብት ልማት፣ ለውሃ እና ለመሬት ልማት ምቹ የሆኑ በርካታ ዕድሎች መኖራቸውን አብራርተዋል። የክልሉ የሥነ-ምህዳር አወቃቀርና ምቹ የአየር ንብረት ለግብርና ዘርፍ ዕድገት እምቅ አቅም እንዳለው ጠቁመዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርስነት የተመዘገቡ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ተፈጥሯዊ መስህቦች እና የማይዳሰሱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች የክልሉ የቱሪዝም ሀብት መገለጫ ናቸው ብለዋል። እነዚህን ሀብቶች በተገቢው መንገድ በማልማት የቱሪዝም ዘርፉን የኢኮኖሚ ምሰሶ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል። በክልሉ የሚገኙ የከበሩ ማዕድናት፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና ለኢንዱስትሪ ልማት አመቺ ሁኔታዎች ለኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እነዚህን የተፈጥሮ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች በአግባቡ በመጠቀም የክልሉን አልፎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ የግል ባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት የክልሉ መንግስት ለባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው "የአማራ ክልል የልማት ተስፋዎችና የህዝብ ተጠቃሚነት" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ክልሉ የረጅም፣ የመካከለኛ እና የአጭር ዘመን እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል። በዚህም በ2027 የአማራ ክልል በመሠረታዊ ኢንዱስትሪ ምርቶች የራሱን ፍላጎት የሸፈነ እና የተሳካ የመዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ የክልሉን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በማቀድ እየተሰራ ነው ብለዋል። በ2042 ክልሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ የሆነ የዘመናዊ ኢኮኖሚ ባለቤት እና የበለጸገ ማሕበረሰብ ሆኖ ማየት የዕቅዱ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የክልሉን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፤ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም መገንባት ስትራቴጂክ ጉዳይ ነው ብለዋል። ክልላዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራትንም እንዲሁ። በተጨማሪ ሣይንሳዊ ዕውቀትን የማሕበረሰብ እሴት እና የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ማድረግ፤ ምርታማነትንና ቅልጥፍናን በማሳደግ ጥራት ያለው ኢኮኖሚ መገንባት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው ነው- አቶ አደም ፋራህ
Jan 15, 2026 103
ሆሳዕና፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች በሁሉም አካባቢዎች እየተተገበሩ ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። የፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የቀረበው የፓርቲው ሥራ አፈፃፀም የሚያመለክተው የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች በሁሉም አካባቢዎች የህዝብ ቅቡልነት በማግኘት እየተተገበሩ ናቸው ብለዋል፡፡ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለፓርቲው ስራዎች ውጤታማነት የሚረዳ የተናበበ እቅድ የማዘጋጀት እንዲሁም የፓርቲውን እሳቤ በመረዳት በስነ ምግባር የሚፈፅም ጠንካራ አመራር ለማብቃት በተሰራው ስራ መሻሻሎች መታየታቸውንም ገልጸዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ከህዝቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ውጤት እየተገኘ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራ እና የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲውን እሳቤዎች በመተግበር ህዝቡ ተባባሪ ሆኖ በመስራቱ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። በሁሉም አካባቢዎች ልማትን የማፋጠን እና መልካም አስተዳደር የማስፈን ስራዎች አሁንም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ገልጸው የህዝቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በፓርቲው የተያዙ ሁሉን አቀፍ የእድገትና ትራንፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለማሳካት አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎችና የወጣት ክንፍ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡
ማህበራዊ
በአማራ ክልል ፋይዳ መታወቂያን ለሁሉም የመሬት ባለይዞታዎች ተደራሽ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው
Jan 17, 2026 14
ባሕር ዳር፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም የመሬት ባለይዞታዎች ተደራሽ በማድረግ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ግብ መያዙን በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር) ገለፁ። "የፋይዳ መታወቂያ ለሁሉም የክልላችን መሬት ባለይዞታዎች" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል። ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ስኬታማ ለማድረግ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል። በክልሉ ፋይዳ መታወቂያን ተደራሽ ለማድረግ በተሠራው ሥራ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም በገጠሩ አካባቢ ለሚኖረው የገጠር መሬት ባለይዞታ አርሶ አደር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በአጭር ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ ግብ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ይህም የመሬት ዘርፉን በማዘመን፣ ፍትሐዊ አሠራርን በማስፈንና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስችላል ነው ያሉት። አርሶ አደሩ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆንና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ግብ መሳካት በየደረጃው የሚገኘው አመራር ተቀናጅቶ በመሥራት የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል። የክልሉ መሬት ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ በበኩላቸው፤ እየተገነባ ያለውን ዲጂታል የመረጃ አሥተዳደር ሥርዓት ውጤታማ ለማድረግ የመሬት አሥተዳደር ሥርዓቱን ከዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር እየተሠራ ነው ብለዋል። በዚህም በክልሉ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ለገጠር መሬት ባለይዞታዎች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም የገጠር መሬት ባለይዞታ አርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ የተያዘው ግብ እንዲሳካም በየደረጃው አመራሩ ተቀናጅቶ በመሥራት የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በክልሉ የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጓል - የክልሉ ፖሊስ
Jan 17, 2026 17
ወላይታ ሶዶ ፤ጥር 09/2018 (ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተራ እና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ደግፌ ደበላ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተራ እና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጓል። ለበዓሉ ስኬታማነት በየመዋቅሩ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነሩ ከጸጥታ መዋቅሩና ከመላው ህዝቡ ጋር በመወያየት ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል። የትራፊክ ፖሊሶችም የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን በሚገባ መቆጣጠርና ለተሽከርካሪ ዝግ በሆኑ መንገዶች ተለዋጭ መንገዶችን በተገቢው እንዲያሳልጡ ስምሪት መሰጠቱን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ በዓሉ በሚከበርባቸው እና ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ላይ ከመደበኛ እንቅስቃሴ የተለየ ነገር ሲመለከት እና የወንጀል ስጋቶችን ሲያጋጥም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር እንደሚገባም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት መረቁ
Jan 17, 2026 49
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ዛሬ መርቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ ሥነሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል። ይህም በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል። ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን እንደሚያገለግል ጠቁመዋል። ግቢው ማደሪያ ክፍሎችን፣መማሪያ ክፍሎችን፣ በፀሃይ ኃይል የሚሰሩ በቂ ኮምፒውተሮች ያሉት የኮምፒውተር ላብራቶሪ፣ የንፁህ ውሃ ጉድጓድ፣ የተሟላ የምግብ ማብሰያ ክፍል፣ ቤተ መፃሕፍት እና የአስተዳደር ሕንፃን አካትቶ የተገነባ መሆኑን ነው ያብራሩት። ይኽ ምሉዕነት ያለው የትምህርት ከባቢ የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ልህቀት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተሰራ፣ ለወጣት ተማሪ ልጆቻችን ሁሉን አቀፍ እድገት አዲስ እድል የፈጠረ ተቋም ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የጥቅምት በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው
Jan 17, 2026 72
ጋምቤላ፤ ጥር 9/2018(ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የጥቅምት በዓልን በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረጉ መሆናቸውን በከተማው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰማሩ ወጣቶች ገለጹ። የጥምቅት በዓል በልዩ ድምቅትና ድባብ ከሚከበርባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ጋምቤላ ነው። ዘንድሮም በዓሉ በተለመደው ድምቀት እንዲከበር የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ወጣቶች በዓሉ የሚከበርባቸውን ቦታዎች የማስዋብና የማስተካከል ሥራዎች እያከናወኑ መሆናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ሲሳተፉ ካገኘናቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ተስፋዬ ድልነሳው በሰጠው አስተያየት የጥምቀት በዓል በልዩ ድምቀትና ድባብ እንዲከበር በጋምቤላ ከተማ የተለያዩ የበጎ ፋቃድ አገልግሎት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግሯል። በተለይም ታቦታቱ የሚያልፉባቸው መንገዶችን የማጽዳትና ማስተካከልን ጨምሮ ከተማውን በሰንደቅ ዓላማ የማስዋብና የማሸብረቅ ሥራዎች እያከናወኑ መሆናቸው ገልፅዋል። በአሉ በድቀምትና በስኬት እንዲከበር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ሌላው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተሳታፊ ወጣት ሚስጥር ኢስጢፋኖስ ነው። ታቦታቱ የሚያልፉባቸውን መንገዶችን የማስተካከልና አካባቢውን የማጽዳት ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውንና በቀጣይ በበዓሉ ወቅትም ሁለንተናዊ ድጋፋ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጿል። ሌላው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣት አሸናፊ ገብረማሪያም በሰጠው አስተያየት ከጥር 1 ቀን 2018 ጀምሮ የአካባቢው ወጣቶች የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ተናግሯል። በተለይም የጥምቀት በዓል የሚከበረበትን ቦታ በአፈር የመደልደል፣ በሰንደቅ ዓላማዎች የማስዋብና የማሸብረቅ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልጿል። የጋምቤላ ከተማ የመድኃኒያለም ቤተክርስቲያን አስተዳደር መላከ ፀሐይ ቄስ እሸቴ አስማረ እንዳሉት የከተራና ጥምቀት በዓልን በድምቅት ለማክበር ከጥር 1 ቀን 2018 ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ራሳቸውን እንዲችሉ እየተደረገ ነው
Jan 17, 2026 25
ጅማ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በከተማ ማስዋብ ዘርፍ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ራሳቸውን እንዲችሉ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ገለጸ። በጅማ ከተማ በልማታዊ ሴፍቲኔት ታቅፈው በከተማ ማስዋብ ሥራ ተሰማርተው የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ አባዎራዎች እና እማዎራዎች ራሳቸውን ችለው ወደ ሥራ ተሸጋግረዋል። በዚሁ ወቅት የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ በቀለ፤ የክልሉ ከተሞች መኖሪያ ብቻ ሳይሆኑ የማምረቻ ስፍራ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት በዝቀተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በልማታዊ ሴፍቲ ኔት ታቅፈው በተለያዩ የከተማ ጽዳት እና ውበት ሥራዎች ተሰማርተው ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ እየተደረገ ነው ብለዋል። እነዚህ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ በመቆጠብ በሚፈልጉት የሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ዛሬ በጅማ ከተማ የተሸጋገሩት የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በከተሞች ያለውን የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ችግሮች ከከተማ ልማት ጋር በማስተሳሰር መፍትሔ ለመስጠት የተጀመረው ሥራ እንደሚጠናከርም አረጋግጠዋል። የጅማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አሥራት እሸቴ በበኩላቸው፤ በልማታዊ ሴፍቲኔት አማካኝነት በከተማ ውበት ሥራዎች ተሰማርተው የቆዩ 3 ሺህ 90 አባዎራዎች ወደ አምራችነት ተሸጋግረዋል ብለዋል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖች የሥራ እና የቁጠባ ባህልን በማጎልበት አምራችነታቸውን የማሳደግ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወንም አመላክተዋል። በመርሐ-ግብሩ ታቅፈው ዛሬ ከተሸጋገሩት መካከል አስረስ መንግሥቱ፤ ከገቢያቸው በመቆጠብ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመለወጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በተመቻቸላቸው ዕድል ከትንሽ ንግድ ጀምረው አሁን ጥሩ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን የተናገሩት ደግሞ አስናቀች በቀለ ናቸው።
የጥምቀት በዓልን የሚያደምቁ ባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች ለገበያ ቀርበዋል-ነጋዴዎችና ሸማቾች
Jan 17, 2026 46
አዲስ አበባ፤ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፡- የከተራ እና የጥምቀት በዓል አስመልክቶ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክና እሴት የሚያንጸባርቁ የባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች ለገበያ መቅረባቸውን ነጋዴዎችና ሸማቾች ገለጹ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባለፈ የሀገር በቀል የዕደ-ጥበብ ውጤቶች የሚያስተዋውቁበትና ለዘርፉ ነጋዴዎች ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሚገኝበት አጋጣሚ ሆኗል። ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩ በርካታ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ያሏት ሀገር ስትሆን፤ ከነዚህም መካከል በአደባባይ በድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያውያን የአብሮነትና የማንነት መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል። የጥምቀት በዓል የሀገርን ባህልና ታሪክ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ ሲሆን በከተማዋ የታየው የባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች የንግድ እንቅስቃሴ ለሀገራዊ ኢኮኖሚውና ለዘርፉ ነጋዴዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተመላክቷል። የሀገር ባህል ልብሶች ዲዛይነርና አቅራቢ ወይዘሮ ፋናዬ ነጋ እንደገለጹት፤ የጥምቀት በዓልን በድምቀት ለማክበር በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ባህላዊ አልባሳትን በመግዛት ላይ ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያ ባህላዊ አልባሳት ዘመናዊ ዲዛይኖችን ተላብሰው እየተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ይህም ለበዓሉ ድምቀት ከመስጠት ባለፈ የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ውጤቶች የገበያ ተፈላጊነት እንዲጨምር እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የጥምቀት በዓል ለጌጣጌጥና አልባሳት ነጋዴዎች ትልቅ የኢኮኖሚ መነቃቃትን መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡ ወይዘሪት ሰላም ከድር በበኩሏ፤በዓሉን ለማድመቅ የሚቀርቡት አልባሳትና ጌጣጌጦች የኢትዮጵያን ታሪክና የጥበብ ጥራትን ለዓለም የሚያስተዋውቁ መሆናቸውን ገልጻለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ጌጣጌጦችና አልባሳቱ ለገበያ መቅረባቸው አዲሱ ትውልድ ማንነቱን እንዲያውቅና በባህሉ እንዲኮራ የሚያስችለው መሆኑንም ጠቅሳለች፡፡ የተለያዩ ባህላዊ ጌጣጌጦችን ለገበያ ያቀረበችው ወጣት ቃልኪዳን ሲሳይ፤ በተለይም የውጭ ሀገር ዜጎች የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያንጸባርቁ ቅርጻ ቅርጾችንና ጌጣጌጦችን በብዛት በመሸጥ ላይ መሆኗን ተናግራለች፡፡ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ሙሉጌታ ተካ በበኩላቸው፤ በዓሉን የሚያደምቁ የመዋቢያ ጌጦችንና አልባሳትን ቀድሞ ማዘጋጀት ዓመታዊ ተግባራቸው መሆኑን ገልጸዋል። የሚቀርቡት ውጤቶችም ወቅቱን ያማከሉና የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ በመሆናቸው ገበያው ንቁ መሆኑን ገልጸዋል። የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በየዓመቱ ጥር 11 ቀን በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሲሆን፣ በዓሉ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (UNESCO) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የፋሲል እግር ኳስ ክለብ የጎዳና ላይ የቤተሰብ የሩጫ ውድድር መካሄድ ጀመረ
Jan 17, 2026 39
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜ)፡- 7ኛው ዙር የፋሲል እግር ኳስ ክለብ የጎዳና ላይ የቤተሰብ የሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። ውድድሩን ያስጀመሩት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እና የፋሲል እግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ቻላቸው ዳኘው ናቸው። በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋ መኮንን፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አሥራት አፀደ ወይን (ዶ/ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፋሲል ከነማ የስፖርት ደጋፊ ማኅበር የሥራ ኃላፊዎችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። በሩጫ ውድድሩ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ እና በክለቡ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርም 6 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተጠቁሟል።
ውጤታማ የሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገው ይገኛል
Jan 17, 2026 48
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥር የሚተዳደሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ የሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም በመከተላቸው ገቢያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የሆልዲንጉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገሪቱን ቁልፍ የመንግሥትና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትን ያሰባሰበው “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በመድረኩም በ2014 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 41 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ አንድ በመሰብሰብ ሃብት የማወቅ፣ተበታትኖ የቆየውን ሃብት በተደራጀ መንገድ የማስተዳደር ስራ ተግባራዊ እየሆነ እንደሚገኝ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ኢንቨትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች የነበረባቸውን የፋይናንስ፣ የኦዲት፣የካፒታል፣የብድር ጫና እና የኮርፖሬት አስተዳደር ችግር በመቅረፍ ዘመናዊ የባለቤትነት፣ የአስተዳደር ስርዓት እና ዓለም አቀፍ የኮርፖሬት አስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶላቸዋል። በተጨማሪም ዘመናዊ የኦዲት ስርዓት እንዲከተሉ የተደረገ ሲሆን ይህም ተቋማቱ ከኪሳራ ወጥተው ወደ ትርፋማነት እንዲሸጋገሩ ማስቻሉ ተገልጿል። ከሀገራዊ ለውጡ በፊት አብዛኞቹ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የኢኮኖሚ ስብራት አጋጥሟቸው የነበረ ሲሆን በሆልዲንጉ ስር መተዳደር ከጀመሩ በኋላ ግን የአመራርና አስተዳደር ለውጦችን በማድረግ ወደ ትርፋማነት መሸጋገር ችለዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል በተቋሙ ሥር ያሉ ኩባንያዎችን ትርፋማነትና የሥራ ውጤታማነት ለማረጋገጥ በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህም ተቋማቱ ውጤታማ የሃብት አስተዳደርና አጠቃቀም በመከተል ከጊዜ ወደ ጊዜ ገቢያቸው እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል። በዚህም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ከሚተዳደሩ ተቋማት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል። ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ51 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ጠቅሰዋል። በሆልዲንጉ ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች እንደየሃብት መጠናቸው ገቢ ማስገባታቸውንም ገልጸው፥ለተገኘው ገቢ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ያሉ ተቋማት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ኢትዮ-ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንዲሁም የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከተገኘው ገቢ 80 በመቶውን እንደሚሸፍኑ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ውስጥ የ12 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን ከፍተኛ ታክስ ከፋዮችም ናቸው። ድርጅቶቹ በ2017 በጀት ዓመት ከ228 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ታክስ መክፈላቸውም ታውቋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ፈጠራ በወሳኝ ጥቂት የሕክምና ዘርፎች የሚታየውን የሰው ኃይል እጥረት ለመሙላት ከፍተኛ ሚና አለው
Jan 17, 2026 68
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የቴክኖሎጂ ፈጠራ በወሳኝ ጥቂት የሕክምና ዘርፎች የሚታየውን የሰው ሃይል እጥረት ለመሙላት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ገለፁ። የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በጉብኝታቸው በኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን መመልከታቸውን ገልጸዋል። በተለይም በጤናው ዘርፍ ለተግባራዊ አገልግሎት የሚውሉ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል። የጤና እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ባለሙያዎች በቅንጅት መስራት የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። ይህም በሀገሪቱ የሰው ኃይል እጥረት ባለባቸው የሕክምና ዘርፎች ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ሰፊ ዓለም አቀፍ የትብብር ዕድሎች መኖራቸውን ዶክተር ከሰተብርሃን ጠቁመዋል፡፡ በቦርድ አባልነት የሚያገለግሉበት ሴፒ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ወረርሽኝ ሊያስከትሉ የሚችሉ ቫይረሶችን ቀድሞ በመለየት በ100 ቀናት ውስጥ ክትባቶችን ለማምረት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ተቋሙ በአፍሪካ ውስጥ አብረውት ሊሰሩ የሚችሉ ማዕከሎችን በመፈለግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጉብኝታቸው በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በሴፒ መካከል ጠንካራ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር ዕድል እንደሚኖረው ገልጸዋል። ይህም የኢትዮጵያ የጤና ምርምር ተቋማት ሴፒ የሚያዘጋጃቸውን የኤ አይ ኢንጂኖች (AI Engines) በስፋት መጠቀም የሚችሉበትን መንገድ እንደሚያመቻች አመልክተዋል።
የግብርና ምርምር ውጤቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የጎላ ሚና እያበረከቱ ነው
Jan 16, 2026 56
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ በምርምር የታገዙ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ሁኔታን ማሻሻል መቻሉን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ (ፎረም) ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ ተቋሙ የምርት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት በሽታን የሚቋቋሙና ምርታማነትን የሚጨምሩ ዝርያዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅና የማስተዋወቅ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ይህም ከምግብ ዋስትና ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ እንዲሁም የገቢ ምርቶችን ለመተካት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ ምርምሮችን ከሥነ-ምህዳርና ከማህበራዊ ተቀባይነት ጋር በማጣጣም የአፈር ለምነትን፣ የውኃ አጠቃቀምንና የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረጉንም ኃላፊው አብራርተዋል። በስዊዘርላንድ የበርን ዩኒቨርሲቲ ቡድን መሪ የሆኑት ዘሪሁን ታደለ (ፕ/ር)፤ በጤፍ ምርምር ዘርፍ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመሆን ለአርሶ አደሩ ያቀረቧቸው የተሻሻሉ ዝርያዎች በተለያዩ ሥነ-ምህዳሮች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሜሪካ የሄልዝ ሜድና ፋርም ቢዝ ሥራ አስኪያጅ ሙሉ አየለ (ዶ/ር)፤ ግብርናውን ለማዘመን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ያለውን ፋይዳ በመጥቀስ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። በናይጄሪያ ዓለም አቀፍ የትሮፒካል ግብርና ተመራማሪ መላኩ አየለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በባዮቴክኖሎጂና በሥራስር ተክሎች ላይ የሚከናወኑ ምርምሮችን በኢትዮጵያ ለመተግበር ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ በስንዴ ምርት የታየው ስኬታማ ሥራ በሌሎችም ሰብሎች ሊደገም እንደሚገባ ጠቁመዋል። የሶር አፍሪካ ፋርም ሥራ አስኪያጅ ወጣት አንገፉ ባናታ፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከተረፈ ምርቶች የዶሮ ምግብና የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማምረት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ተናግሯል፡፡ ሌሎች ወጣቶችን በማሰልጠን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆኑን አክሏል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የግብርና ተዋናዮች በቅንጅት በመሥራትና የመረጃ ልውውጥን በማሳለጥ ለዘርፉ እመርታዊ ለውጥ እንዲመጣ መሥራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ማዕከሉ የኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሳካት ጉልህ ሚና ይኖረዋል
Jan 16, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ ትብብር እውን የሆነው የኢንፎርሜሽን ተደራሽነት ማዕከል ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሳካት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ። በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ካንግ ጁንግ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውጤታማ እንዲሆን ኮሪያ ሪፐብሊክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኮሪያ ሪፐብሊክ የቴክኖሎጂና አይ ሲ ቲ ሚኒስቴር እንዲሁም ከኮሪያ ሪፐብሊክ ብሄራዊ የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ያቋቋመውን የኢንፎርሜሽን ተደራሽነት ማዕከል በይፋ አስመርቋል። ማዕከሉ ዲጂታል ክህሎትን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን መስጠት እና በኮምፒውተር ሳይንስና አይ ሲቲ ዙሪያ የሚማሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ እንደሚያስችልም ተመላክቷል። ማዕከሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት ማዕከልን ያካተተ ሲሆን በዘርፉ ጥናትና ምርምር የሚያካሄዱ የደህረ ምረቃ ተማሪዎች ምርምራቸውን እንዲያካሂዱ ምቹ አውድ የፈጠረ መሆኑም ተጠቅሷል። ማዕከሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያሉ ስታርታፖች የፈጠራ ሀሳባቸውን ወደ መሬት ማውረድ የሚችሉበት ድጋፍ የሚያገኙበት ሲሆን ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም ፈጠራን ማበረታታት ማዕከሉ ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል ይገኙበታል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ስርዓት ለመገንባት ሀገራዊ ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው። ግቡን ለማሳካት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰው፥ ለስትራቴጂው ስኬት በዘርፉ የአቅም ግንባታ፣ ፈጠራና የዲጂታል ክህሎቱ ያደገ የሰው ኃይል ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። ለዚህ ደግሞ በኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ ትብብር ዛሬ ለምረቃ የበቃው ማዕከል ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መሳካት የላቀ ሚና አለው ብለዋል። ማዕከሉ ኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ ያላቸው ጠንካራ ትብብር መገለጫ መሆኑንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ካንግ ጁንግ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ የጀመረው ጉዞ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሪያ ሪፐብሊክ በዲጂታል ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ ናት ያሉት አምባሳደሩ በመስኩ ያለንን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ ነን ብለዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ቤተልሔም ላቀው(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ውስጥ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህ ረገድ የማዕከሉ ወደ ስራ መግባት የዲጂታል ክህሎቱ የዳበረ ትውልድ ለማፍራት አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። በመስኩ የሚከናወኑ ተግበራት ውጤት እንዲያመጡ በሕግ የማስደገፉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አብራርተዋል። የኮሪያ ሪፐብሊክ የብሔራዊ ኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ጆንግ ሱንግ ህዋንግ በበኩላቸው፤ ኤጀንሲው በተለይ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአፍሪካ እንዲስፋፋ የአቅም ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ ወጥኖ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ተመራጭ ከሆኑ የቴክኖሎጂ መዳረሻዎች መካከል አንዷ ናት ያሉት ፕሬዝዳንቱ ኤጀንሲው በዚህ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በፍርድ ቤቶቹ የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ መደረጉ መሰረታዊ የስራ ለውጥ ማምጣት አስችሏል
Jan 16, 2026 80
ሰቆጣ ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሚገኙ ፍርድ ቤቶች የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ መደረጉ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን የአስተዳደሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል። የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታነህ ጥጋቡ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ፍርድ ቤቶች ካሁን ቀደም የነበራቸው አሰራር በወረቀት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ ነበር። በፋይል የተቀመጠ የባለጉዳዮች መዝገብ ለመጥፋት፣ በዝናብና በተባይ ለመበላሸትና ለሌሎች ችግሮች ይጋለጥ እንደነበርም አውስተዋል። ዘንድሮ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ጨምሮ የወረዳ ፍርድ ቤቶች የዲጂታል አሰራርን በመተግበራቸው ቀደም ሲል ይከሰት የነበረውን ችግር ሙሉ በሙሉ ማስቀረት መቻሉን ገልጸዋል። የመረጃ ልውውጡም ሆነ የውሳኔ አሰጣጡ በዲጂታል የታገዘ በመሆኑ የስራ ቅልጥፍናን፣ ፍትሃዊነትንና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ማስቻሉን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ባለጉዳዮች በይግባኝ ምክንያት ወደ ደሴና ባህር ዳር በመመላለስ ያገኙ የነበረውን አገልግሎት አሁን ላይ የዲጂታል ስርአቱ ባሉበት ወረዳ ሆነው ተገቢውን ፍትህ የሚያገኙበት እድል ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም የተዘረጋው የዲጂታል ስርዓት በድምጽ የሚሰጠውን ፍርድ ወደ ፅሁፍ በፍጥነት የሚቀይር በመሆኑ የዳኞችን ጫና ጭምር ያቃለለ መሆኑን ተናግረዋል። ፍርዱ ቤቱ የራሱ የሆነ ድረ ገፅ በማልማትም ባለጉዳዮች ከቀጠሮ ጀምሮ እስከ ፍርድ ያለውን ጉዳያቸውን ባሉበት ሆነው እንዲከታተሉና እንዲያውቁ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል። የዋግ ኸምራ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የወንጀል ዳኛ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ መሰለ በበኩላቸው፤ የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ ፈጣን የዳኝነት አገልግሎት እንድንሰጥ አስችሏል ብለዋል። በተለይም ግልፀኝነት የተላበሰ የፍርድ ሂደት እንዲፈጠር በማስቻሉ የውሳኔ ጥራትና ተአማኒነት ላይ አበረታች ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን አስረድተዋል። በወረቀት በነበረበት ወቅት የፍርድ ሂደት የድምፅ ቅጅ በእጅ እንደገና ስለሚፃፍ አንድን ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት እስከ ሶስት ወር ይፈጅ እንደነበር ጠቅሰው አሁን በሳምንት ውሳኔ መስጠት ተችሏል ብለዋል። በሰቆጣ ከተማ የግል ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ እዝራ ደረጀ፤ ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን አሰራር ስርዓትን መከተላቸው ፍትህን ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው ነው ብለዋል። በተለይም የግል ጠበቆች ተወዳዳሪና ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ ከማስቻሉም ባለፈ ደንበኞቻቸውን ካላስፈላጊ ወጭ በማላቀቅ ካሉበት ቦታ ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ማስቻሉን አስረድተዋል።
ስፖርት
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር ይጫወታል
Jan 17, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በሚደረጉ አራት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። ምሽት 12 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አዳማ ከተማ በሊጉ 14 ጨዋታዎችን አድርጎ በአምስቱ ድል ሲቀናው በሁለቱ ተሸንፏል። በቀሪ ሰባት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ ዘጠኝ ግቦችን ሲያስቆጥር ሰባት ግቦች ተቆጥረውበታል። ቡድኑ በ22 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ሲዳማ ቡና በሊጉ ካከናወናቸው 14 ጨዋታዎች መካከል ስምንቱን ሲያሸንፍ የተሸነፈው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በቀሪ አምስት ጨዋታዎች ነጥብ ጥሏል። 18 ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ ስድስት ግቦች ተቆጥረውበታል። ሊጉን በ29 ነጥብ እየመራ ነው። ሁለቱ ቡድኖች በ14ኛ ሳምንት አቻ ከተለያዩባቸው መርሐ-ግብሮች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ሲዳማ ቡና ካሸነፈ የሊጉን መሪነት ያጠናክራል። አዳማ ከተማ ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። በሌላኛው መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ። በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው 14 ጨዋታዎች መካከል አምስቱን ያሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና በስድስቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። በ14ቱ ጨዋታዎች ላይ 13 ግቦችን ሲያስቆጥር 14 ጎሎችን አስተናግዷል። ኢትዮጵያ ቡና በ18 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ሃዋሳ ከተማ በበኩሉ በ14 ጨዋታዎች ሰባቱን አሸንፎ በአራቱ ሽንፈት አስተናግዶ በሶስቱ አቻ ወጥቷል። 15 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ዘጠኝ ጎሎች ተቆጥረውበታል። ሃዋሳ ከተማ በ24 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱም ቡድኖች በአሸናፊነት ለመቀጠል የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ። የ16 ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ19 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። ድሬዳዋ ከተማ በ18 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት ስድስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ተጋጣሚው ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ከድል ርቋል። ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል። ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከመቻል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ20 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባምንጭ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ብቸኛው ክለብ ነው። መቻል ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። ጨዋታው አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ፣ መቻል ወደ ድል መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።
በአፍሪካ ዋንጫ ግብጽ እና ናይጄሪያ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ይጫወታሉ
Jan 17, 2026 59
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ ዛሬ በግብጽ እና ናይጄሪያ መካከል ይደረጋል። ጨዋታው ምሽት አንድ ሰዓት ላይ በመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ይካሄዳል። በግማሽ ፍጻሜው ግብጽ በሴኔጋል፣ ናይጄሪያ በሞሮኮ ሽንፈት አስተናግደዋል። የዓለም አይኖች ያረፉበት ተጠባቂው የማንችስተር ደርቢ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር ይጫወታል ግብጽ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ እስከ አሁን ባደረገቻቸው ስድስት ጨዋታዎች አራቱን ስታሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፋለች። በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይታለች። በጨዋታዎቹ ላይ ስምንት ግቦችን ስታስቆጥር አምስት ጎሎችን አስተናግዳለች። ተጋጣሚዋ ናይጄሪያ ከስድስት ጨዋታዎች መካከል አምስቱን ስታሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፋለች። 14 ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ አራት ጎሎች ተቆጥሮባታል። ናይጄሪያው በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በርካታ ግቦችን ያስቆጠረች ሀገር ናት። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ዋንጫ ሲገናኙ የአሁኑ ለ10ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ናይጄሪያ በአምስቱ ድል ሲቀናት ግብጽ ሁለት ጊዜ አሸንፋለች። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታዎቹ ላይ ሁለቱም ሀገራት በተመሳሳይ 11 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ሀገራቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊው መድረክ የተገናኙት ጋና እ.አ.አ በ1963 ባዘጋጀችው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ነው። በወቅቱ በምድብ ሁለት ተገናኝተው ግብጽ 6 ለ 3 አሸንፋለች። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ካሜሮን እ.አ.አ በ2022 ባስተናገደችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በምድብ አራት ባደረጉት ጨዋታ ናይጄሪያ በኬሌቺ ኢናቺዮ ግብ ግብጽን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ናይጄሪያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ ስታሸነፍ ግብጽ ሰባት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት የውድድሩ ስኬታማ ሀገር ናት። የአፍሪካ እግር ኳስ ኃያላን የሆኑት ሁለቱ ሀገራት በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ለፍጻሜ ባይደርሱም ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በአዎንታዊ መልኩ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ይፋለማሉ። የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ነገ በሴኔጋል እና አዘጋጇ ሞሮኮ መካከል ይደረጋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የዓለም አይኖች ያረፉበት ተጠባቂው የማንችስተር ደርቢ
Jan 17, 2026 80
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል። ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚያደርጉት የደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ማንችስተር ዩናይትድ በ32 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ማንችስተር ሲቲ በ43 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ክለቦች በሁሉም ውድድሮች ሲገናኙ የአሁኑ ለ198ኛ ጊዜ ነው። ቡድኖቹ ከዚህ በፊት ባደረጓቸው 197 ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ 80 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ 63 ጊዜ ሲያሸንፍ 54 ጊዜ ነጥብ ተጋርተዋል። በፕሪሚየር ሊጉ 57 ጊዜ ተገናኝተው ማንችስተር ዩናይትድ 26 ጊዜ ሲያሸንፍ ሲቲ በ21ዱ ድል ቀንቶታል። በቀሪ 10 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ሶስቱን ሲያሸንፍ ማንችስተር ዩናይትድ አንድ ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ የአንድ ከተማ ባላንጣ ቡድኖች ናቸው። ክለቦቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ በ1881 ነበር። በዚህ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 አሸንፏል። ቡድኖቹ ከመጀመሪያ ጨዋታቸው አንስቶ ለ145 ዓመታት የቆየ ፉክክር በእንግሊዝ እና በአውሮፓ መድረክ አድርገዋል። ማንችስተር ዩናይትድ የሊጉን ዋንጫ 20 ጊዜ በማንሳት የበላይነቱን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ 10 ጊዜ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። ማንችስተር ዩናይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኙ ማይክል ካሪክ እየተመራ ወደ ሜዳ ይገባል። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ በመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ክለቦቹ በተመሳሳይ ባለፉት ሶስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። የ47 ዓመቱ የማንችስተር ከተማ ተወላጅ አንቶኒ ቴይለር ተጠባቂውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራሉ። በሌላ በኩል የሊጉ መሪ አርሰናል ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። ሊቨርፑል ከበርንሌይ፣ ቼልሲ ከብሬንትፎርድ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ ሰንደርላንድ ከክሪስታል ፓላስ እና ሊድስ ዩናይትድ ከፉልሃም በተመሳሳይ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ
Jan 16, 2026 64
አዲስ አበባ፤ ጥር 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እዮብ ገብረማርያም እና ሀሰን ሁሴን የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ቢኒያም ካሳሁን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ17 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
አካባቢ ጥበቃ
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በሞዴል መንደሮች የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ይከናወናል
Jan 16, 2026 71
ሰቆጣ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰባት ሞዴል መንደሮች የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ። በአሥተዳደሩ የገጠር ኮሪደር ልማትን ለማሳካት ያለመ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል። የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የመንገድ መምሪያ ኃላፊ ፀጋው እሸቴ በዚሁ ወቅት፤ ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባው የገጠር ኮሪደር ልማት በሕዝብ ተሳትፎ ታጅቦ ይከናወናል ብለዋል። በሁሉም ወረዳዎች ሰባት ሞዴል መንደሮችን በመለየት የገጠር ኮሪደር ልማት እንደሚከናወን የገለጹት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አዲስ ወልዴ ናቸው። በገጠር ኮሪደር ልማት ቅንጅታዊ አሠራርን በመከተል የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
በአስተዳደሩ የተከናወነው የተፋሰስ ልማት ስራ አርሶ አደሮች ከተረጂነት እንዲወጡ አስችሏል
Jan 16, 2026 67
ድሬዳዋ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ከተረጂነት ለመውጣት እንዳስቻላቸው አርሶአደሮች ተናገሩ። በተፋሰሱ እና በሌሎች የገጠር ልማቶች በተከናወነው ስራ በመታገዝ ዘንድሮ ከ38 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ከተረጂነት ወደ አምራችነት እንደሚሸጋገሩ አስተዳደሩ አስታውቋል ። ባለፉት ዓመታት የተሰሩት ልማቶች የተፈጥሮ ሃብት ይዞታን በመመለስ፣ የጎርፍ ችግርን በመከላከልና ምንጮችን በመመለስ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉን ዘንድሮ በተጀመረው የተፋሰስ ልማት እየተሳተፉ የሚገኙ አርሶአደሮች ለኢዜአ ገልጸዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል የገንደ ሪጌ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሱልጣን ፈጃል እንደገለፁት፤ ተፋሰሱ ተጨማሪ የእርሻ መሬትና ውሃን እንዲጠቀሙ በማስቻሉ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተው ህይወታቸውን ለመለወጥ አስችሏቸዋል። ቀደም ብለው ዓልምተው የነበረው ብርቱካን ባለፈው ሳምንት ተሰብስቦ ከ900 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን እንደአብነት አንስተዋል። ከብርቱካን በተጨማሪ ሽንኩርት፣ ሃባብና ሎሚ እያመረቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። .የኡሉል ሞጆ ቀበሌ አርሶአደር ወይዘሮ ሐሊማ መሐመድ በበኩላቸው፣የተፋሰስ ልማቱ ለግብርና ስራ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ አርሶአደሩ በምንጭና በዝናብ ውሃ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ እያመረተ መሆኑን ተናግረዋል። ይሄን የመሰለ የተፈጥሮ ፀጋና ጉልበት እያለን ለልመና እጅ አንዘረጋም ያሉት አርሶአደር ሐሊማ፤ ከራሳችን አልፈን ለተቸገሩ ለመርዳት ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በተፋሰስ ልማትና በሌማት ትሩፋት በተፈጠሩላቸው እድሎችና ድጋፎች በመታገዝ ከተረጂነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር ከልማታዊ ሴፍትኔት መውጣታቸውን የገለፁት ደግሞ ሌላው የኡሉል ሞጆ ቀበሌ አርሶአደር ኡስማን መሐመድ ናቸው። የቀበሌው ህብረተሰብ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የመሸጋገርን መርህ ለማሳካት በተፋሰስ ልማትንም ሆነ በሌሎች ስራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ፤ ባለፉት ዓመታት በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች በሚገኙ 57 ሺህ ሄክታር የተራቆቱ ተፋሰሶች ላይ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በተከናወኑት ተግባራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአነስተኛ መስኖ ልማት በመሰማራት አበረታች ውጤት መገኘቱን የገንደ ሪጌ ገጠርን በአብነት ጠቅሰው አስረድተዋል። እንደ ኃላፊው አቶ ኑረዲን ገለፃ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች የገጠር ልማቶች ከተረጂነት ወደ አምራችነት የመሸጋገሩን ጉዞ ስኬታማ ያደርጉታል። በዘንድሮ በጀት አመት 38 ሺህ በልማታዊ ሴፍትኔት የታቀፉ አርሶአደሮችና አርብቶአደሮች ወደ አምራችነት ይሸጋገራሉ ብለዋል።
በዞኑ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በ631 ተፋሰሶች ላይ እየተካሄደ ነው
Jan 16, 2026 67
ወልዲያ ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በሰሜን ወሎ ዞን የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በ631 ተፋሰሶች ላይ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የተፈጥሮ ሃብት ባለሙያ አቶ ጋሻው አለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ባለፉት አመታት የተከናወነው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ደርቀው የነበሩ ምንጮች እንደገና በመፍለቃቸውና የከርሰ ምድርና ገጸ-ምድር የውሃ አቅም በመጨመሩ አርሶ አደሩ በስራው በንቃት እንዲሳተፍ አድርጓል። የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የአፈር ለምነትን በማሳደጉና የውሀ አማራጮች መስፋታቸው ለመስኖ ልማት ስራው ስኬት ተጨማሪ አቅም መፍጠራቸውን ገልጸዋል። ስራዎቹ ተራቁተው የነበሩ ተራሮችን ወደ ልምላሜ በመመለሳቸው አርሶ አደሩ በመኖ ልማትና በንብ ማነብ ስራ በመሰማራት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዳስቻለው ተናግረዋል። በዘንድሮው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ 380 ሺህ 493 አርሶ አደሮች 631 ተፋሰሶችን እያለሙ መሆኑን አስረድተዋል። በዘንድሮው የአፈርና ውሃ እቀባ ልማት ስራም 443 ሺህ 77 ሄክታር መሬት ላይ የማሳና የተራራ ላይ እርከንና ሌሎች ስነ አካላዊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዞኑ የመቄት ወረዳ የ029 ቀበሌ ነዋሪ አቶ አባቡ ዋለልኝ፣ ባለፉት ዓመታት ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ያገኘናቸውን ጥቅሞች ዘንድሮም ለማስቀጠል በትጋት እየሠራን ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች አካባቢዎች አገግመው ለእንስሳት መኖ፣ ንብ ማነብና ሌሎች ስራዎች ጥቅም በመስጠታቸው ዘንድሮ በራሳቸው ተነሳሽነት ለስራ መውጣታቸውን ተናግረዋል። ባለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት ባከናወኗቸው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን አግኝተንበታል ያሉን ደግሞ በላስታ ወረዳ የጠልፈጢት ቀበሌ ነዋሪ አቶ ታደሰ ዳምጤ ናቸው። በዚህም በጓሮአቸው በአነስተኛ መስኖ አትክልት በማልማት፣ መኖ በማጨድ በእንስሳት እርባታና ማድለብ ስራ በመሰማራት ተጨማሪ ሃብት ለማፍራት እንዳስቻላቸው አስረድተዋል። በዞኑ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተሰራው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ የዞኑን የደን ሽፋን ከ20 በመቶ በላይ ማድረሱን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአካባቢ ጥበቃ ልማት የተሠሩ ሥራዎች ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው
Jan 16, 2026 70
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት የተሠሩ ሥራዎች ጤናማ ትውልድ ለማፍራት የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው በዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ የሕጻናት ሄማቶሎጂና ኦንኮሎጂ ማኅበር የምሥረታ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሐ-ግብሩ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ጤናን ለመጠበቅ፣ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። በአውስትራሊያ የጤና ባለሙያ የሆኑት ብሮንዊን ማክናማራ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ በአካባቢ ንጽህና፣ አረንጓዴ ቦታዎችና ፓርኮችን በማስፋፋት ረገድ ከዚህ ቀደም ከሚያውቁት የተለየ ለውጥ ማየታቸውን ተናግረዋል። የፕላስቲክና የኬሚካል ውጤቶች የጤና ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆኑ ብክለትን ለመከላከል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችንም አድንቀዋል። የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ለጤና አጠባበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ያስረዱት ደግሞ የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሺላ ዋይትዝማን ናቸው። አረንጓዴና ንጹህ አካባቢ ጤናን ለመጠበቅ ከሚያስችሉ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ በሽታን አስቀድሞ መከላከል ከማከም የተሻለ ነው ብለዋል። በ’ፒውር ኧርዝ’ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ፍሬው ከፍያለው በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋችነትና ወጣቶችን በማሳተፍ የጽዳት ሥራዎች ላይ ለበርካታ ዓመታት እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ትብብራቸውን ለማጽናት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Jan 14, 2026 113
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ጋር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ትብብር እንዳላቸው አውስተው በጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) ማዕቀፍ ያላቸውን ግንኙነት አንስተዋል። በዮካሃማ በነሃሔ ወር 2017 ዓ.ም የተካሄደው ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም(ቲካድ) በሁለቱ ወገኖች አጋርነት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አመልክተዋል። ውይይቱ የሁለትዮሽ ትብብሩን የበለጠ ማጠናከርን ያለመ ነው። ጃፓን ለአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (African CDC) እያደረገች ያለው ድጋፍ እንዲሁም የአፍሪካ ዘላቂ እድገት እና ትስስር ለሚደግፉ የመሰረተ ልማት ስራዎች እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል። የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) በስኬት መካሄዱን አድንቀዋል። 10ኛው ቲካድ በአፍሪካ እንዲካሄድ ጃፓን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል። ሀገራቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እና የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ፒዳ) ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቁልፍ ኢኒሼቲቮች መደገፏን እንደምትቀጥል ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ በዓለም አስተዳደር ውስጥ እያደገ የመጣውን የአፍሪካ ሚና በማንሳት የአፍሪካ ህብረት በቡድን 20 ቋሚ አባል መሆኗ ትልቅ ሽግግር መሆኑን ተነግረዋል። ባለስልጣናቱ በአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን የከፍተኛ ደረጃ የምክክር መድረክ እና ቲካድ አማካኝነት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና የባለብዙወገን ዲፕሎማሲ እንዲጸና በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን እ.አ.አ በ1993 አጋርነት መመስረታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰላም እና ደህንነት፣ ኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ንግድ፣ ጤና ፣ ግብርና፣ ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ከሁለቱ ወገኖች የትብብር መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ።
ውኃ ለአፍሪካ የኅልውና ጉዳይ ነው - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Jan 12, 2026 202
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ ውኃ ሁሉንም ዘርፍ የሚነካ አህጉራዊ የኅልውና ጉዳይ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የሕብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው"ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሐሳብ የሚደረግ ነው። በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት ትኩረቱን ያደረገው በውኃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ውኃ በሁሉም አይነት እጅጉን ወሳኝ የሆነ ሀብት እና የኅልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል። በብራዚል ቤለም የተካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) ትኩረት ከተሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ውኃ አንዱ አጀንዳ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማዘጋጀት በመመረጧ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ያሉ ሲሆን፤ ለጉባኤው ስኬታማነት ሕብረቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ሰላም እና ደኅንነት የአፍሪካ አንገብጋቢ አጀንዳ መሆኑን የገለጹት ሊቀ መንበሩ ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሊቢያን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ኢ-ሕገመንግሥታዊ ለውጦች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቅሰው፤ ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንዲያከብሩ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ሪፎርም እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥርን ጨምሮ ለአህጉራዊ አጀንዳዎች እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። አህጉራችን ፈተናዎች ቢኖሩባትም በጋራ ከቆምን እናልፋቸዋለን ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የዛሬው ስብስባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል ሀገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ መሆኑ ይታወቃል።
51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል
Jan 12, 2026 240
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የህብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። ስብሰባው "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ህብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሃሳብ የሚደረግ ነው። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ ጭብጥ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣የሕብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንደሚሳተፉበት ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ስብስባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን የአፈጻጸም እንዲሁም ሕብረቱ እ.አ.አ በ2025 ያካሄዳቸውን ስብሰባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል። ሰላም እና ደህንነት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ የኢኮኖሚ ትስስር፣ የተቋማዊ ሪፎርሞች እና የበጀት እቅዶችን የተመለከቱ የቴክኒክ ሰነዶችንም ያዘጋጃል። ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል አገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ ነው።
የቻይና አፍሪካ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል
Jan 8, 2026 213
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ውይይት አካሄዱ። ውይይቱ እያደገ የመጣው የቻይና አፍሪካ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያለመ ነው ተብሏል። ቻይና የአፍሪካ እውነተኛ አጋር መሆኗን የገለፁት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ፖሊሲ ጠንካራ ወዳጅነት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልፀዋል። የቻይና አፍሪካ ግንኙነት በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል። ከውይይቱ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ ሁለቱ ወገኖች የዓለም ደቡባዊ ቀጣና (Global South) ሀገራትን መብትና ጥቅም ለማስከበር፣ የሉዓላዊነትን ክብር ለመጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በጋራ ለመሥራት መስማታቸውን አስታውቀዋል። በውይይቱ ወቅት የቻይናን የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ከአፍሪካ ኅብረት የ2063 አጀንዳ ሁለተኛው የዐሥር ዓመት ትግበራ ጋር በማጣጣም ዘመናዊነትን ለማምጣት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ምክክር መደረጉ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነቶችን ጨምሮ፣ ቻይና ያቀረበቻቸውን ዓለም አቀፍ የደኅንነትና የልማት ተነሳሽነቶች በጋራ ለመደገፍ ከስምምነት መድረሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። በተጨማሪም የተፈረሙ የትብብር ስምምነቶችን በተግባር በመተርጎም እና የንግድ ልውውጥን በማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል።
ሐተታዎች
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 569
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 504
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 724
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 878
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል። ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ። ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 537
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 477
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1127
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3456
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3094
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1967
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7786
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6271
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት
Jan 14, 2026 162
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት ብርቱዎች ነገን በማሰብ ሁሌም ታትረው ይሰራሉ፤ ይደክማሉ፤ ይጥራሉ…ለቀጣዩ ትውልድም ጥሪት በማስቀመጥ አሻራቸውን ያኖራሉ። አገር የምትገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው። “አባት ያበጀው፤ ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ልጆች ከአባቶቻቸው ያገኙትን ጥሪት በአዲስ እውቀትና አሰራር ለአገር እድገት በሚበጅ መልኩ አጠናክረው መጠቀማቸው አይቀርም። “ዕድሜ ጸጋ ነው” የሚለው አባባል አንዳንዴ በዕድሜ ብንገፋም ጠንክረን ከሰራን ብዙ ነገር እናያለን ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። በሰቆጣ ከተማም እድሜ ሳይገድባቸው በልማት ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ለዚህ ማሳያ ናቸው። የከተማዋ ነዋሪ የ67 ዓመቱ አቶ ብርሃኑ አወቀ እና የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ዕድሜያቸው ቢገፋም ጠንክሮ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልና ዕድሜ ጸጋ ሆኖ ብዙ ለውጥ ማየት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው። ግለሰቦቹ ከዕድሜ ብዛት ጉልበቴ ደከመ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ እጄም ተሳሰረ…ሳይሉ ጊዜያቸውን በደን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በማሳለፍ ለወጣቶች የልማት አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው። አቶ ብርሃኑ አወቀ በሰቆጣ ከተማ ዳርቻ የሚገኝ አለቱ ያገጠጠና የተራቆተ አካባቢን ከሌላ አካባቢ ለም አፈር በማምጣትና በመደልደል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ደን በማልማት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ነው። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከወጣሁ ጀምሮ ጠንክሬ በመስራት የምለወጥበትን ሥራ ማሰብ ስነበረብኝ፤ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ለዘመናት የቆየን ጭንጫ መሬት ጠርጌና ደልድዬ ማልማት ችያለሁ ይላሉ ወደኋላ መልስ ብለው የተነሱበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ። ግማሽ ሄክታር በማይሞላ መሬት ላይ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ዘይቱና፣ ጌሾ፣ ቡና፣ ማንጎና አቮካዶ አልምተዋል። በተጨማሪም ቆስጣ፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመንና ሽንኩርት በማምረት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ጥሪት አፍርተዋል። ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ተግቶ መስራት ከተቻለ ሀብት ማፍራትና ህይወትንም መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወጣቱም ከእሳቸው የሥራ ትጋት በመማር በአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ በማልማት ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሌላው የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ባለፉት 18 ዓመታት በተሰማሩበት የአትክልትና ደን ልማት ሥራ የአካባቢያቸውን ገጽታ ቀይረዋል። የዕድሜ ዘመናቸውን በውትድርናና በመንግስት ሠራተኝነት በማገልገል ሃገራዊ ግዳጃቸውን ሲወጡ ነው የቆዩት። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከተገለሉ በኋላም ቤት ውስጥ መቀመጥን አልመረጡት። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ ጌሾ፣ ዘይቱና እና ማንጎ በማልማት ምርቱን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። በአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ለይተን ማልማት ከቻልን ድህነትን ማስወገድ የሚከብድ አይሆንም ያሉት አቶ ታደሰ፣ የተራቆተና በጎርፍ የተጎዳን መሬት በማልማት አካባቢውን ሳቢና ማራኪ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት። ወጣቱም ከእሳቸው አርአያነት ያለው ተግባር በመማር በአካባቢው እጁ ላይ ባለ ሀብት ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ማሳየት እንዳለበት መክረዋል። የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ እንደገለጹት፤ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 24ሺህ 847 አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል ዕድሜ ሳይገድባቸው ወደ ልማት የገቡ አረጋዊያን እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ሥራ ለወጣቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ከእነሱ ልምድ በመውሰድ በዞኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን በጓሮና ባላቸው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም በዞኑ የሚስተዋለውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።
ከማላጋ እስከ አፍሪካ ዋንጫ፤ የሞሮኮው አዲስ እንቁ ብራሂም ዲያዝ
Jan 13, 2026 176
የግል ክህሎት፣ ፈጣን አስተሳሰቡ እና በጠባብ ክፍተቶች ውስጥ ሰብሮ የመግባት አቅሙ ሙገሳ እንዲጎርፍለት አድርጓል። አንድ ለአንድ ሲገናኝ ተከላካዮችን በፈጣን አካላዊ ቅልጥፍና እና በድንገት አቅጣጫ በመቀየር የሚያልፍበት መንገድ እንዲሁም የመፍጠር አቅሙ የተመልካቾችን ቀልብ የሚይዝ ነው። የአማካይ እና የአጥቂ መስመርን በማገናኘት እና በአስገራሚ ሁኔታ አጭር ኳሶችን በማቀበልም የተዋጣለት ተጫዋች ነው ማለት ይቻላል። በቦታ አያያዙ የእግር ኳስ ልኅቀቱ ከፍተኛ ነው የሚል አድናቆት ከእግር ኳስ ባለሙያዎች አግኝቷል። ኳስን ሲያንከባልልም ለዐይን ይስባል። ከክህሎቱ እና ከማራኪ እንቅስቃሴው ባለፈ ወደ ኋላ እየመለሰ ተከላካዮችን ያግዛል፣ ኳስ ይነጥቃል። ይህ ተጫዋች የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተት የሆነው የሞሮኮው ብራሂም ዲያዝ ነው። የ26 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዲያዝ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው። አዘጋጇ ሞሮኮ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ኮሞሮስን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አስቆጥሯል። ብራሂም አብዱልቃድር ዲያዝ የተወለደው እ.አ.አ ኦገስት 3 ቀን 1999 በስፔን ማላጋ ግዛት ነው። እናቱ ስፔናዊ አባቱ ሞሮኳዊ ናቸው። ዲያዝ ያደገው በማላጋ ነው። እግር ኳስንም በአንዳሉሺያዊቷ ከተማ ሲጫወት ቆይቷል። በ16 ዓመቱ ካደገበት ማላጋ በመውጣት እ.አ.አ በ2015 ወደ ማንችስተር ሲቲ ወጣት አካዳሚ በ200 ሺህ ፓውንድ ወጪ ተዘዋወረ። ዲያዝ እ.አ.አ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2016 በካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ ሊግ ካፕ) ማንችስተር ሲቲ ከስዋንሲ ሲቲ ባደረገው ጨዋታ በ80ኛው ደቂቃ በኬሌቺ ኢናቺዩ ተቀይሮ በመግባት ለውኃ ሰማያዊዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያውን ጨዋታ ካደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ተፈራርሟል። እ.አ.አ ኖቬምበር 21 ቀን 2017 ማንችስተር ሲቲ ከፌይኖርድ ሮተርዳም ጋር ባደረገው የሻምፒዮናስ ሊግ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል። በወቅቱ ብራሂም ስተርሊን መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት ላይ ነበር ተቀይሮ የገባው። ዲያዝ በውኃ ሰማያዊዎቹ ማልያ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ የተጫወተው እ.አ.አ ዲሴምበር 19 ቀን 2017 ነው። ማንችስተር ሲቲ ከሌስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ ለ88 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል። እ.አ.አ ጃንዋሪ 20 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። በወቅቱ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን፤ በውድድር ዓመቱ አራት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሳትፎ ያደረገው ብራሂም ዲይዝ የሜዳሊያ ሽልማት አግኝቷል። እ.አ.አ ኦገስት 5 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 2 ለ 0 ባሸነፈበት የኮሙዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ ላይ በፊል ፎደን ተቀይሮ በመግባት ለ15 ደቂቃዎች ተጫውቷል። ዲያዝ እ.አ.አ 2018/19 ማብቂያ ላይ ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የመጀመሪያ ግቦቹን ለሲቲ አስቆጥሯል። በማንችስተር ሲቲ ያለው ውል እ.አ.አ 2019 ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ስሙ ከዝውውር ጋር በስፋት ይነሳ ነበር። ዲያዝ እ.አ.አ ጥር 2019 በ17 ሚሊዮን ዩሮ ከማንችስተር ሲቲ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዘዋወረ። ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን ውልም ፈርሟል። የክንፍ ተጫዋቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን በነጮቹ ማልያ ያደረገው እ.አ.አ ጥር 9 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ ሌጋኔን በስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ 3 ለ 0 ባሸነፈበት ወቅት ነው። ከአራት ቀናት በኋላ በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ሪያል ቤቲስን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያ ግቡን ለማስቆጠር ሶስት ወራትን ጠብቋል። እ.አ.አ ግንቦት 12 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ በላሊጋው በሪያል ሶሲዬዳድ 3 ለ 1 ሲሸነፍ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በወቅቱ ዲያዝ ስድስት ጨዋታዎች ላይ በላሊጋው የተጫወተ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዓመቱ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ሪያል ማድሪድ እ.አ.አ በ2021/21 የውድድር ዓመት ብራሂም ዲያዝ ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት ማምራቱን ይፋ አደረገ። ዲያዝ ሚላን እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2020 ክሮቶኔን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ ግንቦት 2021 ኤሲ ሚላን ጁቬንቱስን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ያስቆጠረው ግብም ተጠቃሽ ነው። ዲያዝ በኤሲ ሚላን የውሰት ውሉ ሲያበቃ በድጋሚ ለሁለት ዓመታት በውሰት የሚቆይበት ስምምነት ሪያል ማድሪድ ከጣልያኑ ክለብ ጋር የተፈራረመ ሲሆን፤ ውሉ ሚላን ተጫዋቹን የማቆየት መብት ሰጥቶታል። እ.አ.አ መስከረም 15 ቀን 2021 ኤሲ ሚላን በሻምፒዮንስ ሊጉ የ3 ለ 2 ሽንፈት ሲያስተናግድ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ግቡን አስቆጥሯል። በ2023 ኤሲ ሚላን ቶተንሃም ሆትስፐርስን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ 1 ለ 0 ሲያሽንፍ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ በ2023 ሰኔ ወር ላይ ሪያል ማድሪድ ዲያዝ ከኤሲ ሚላን የሶስት ዓመታት የውሰት ቆይታ በኋላ ወደ ክለቡ መመለሱን አሳውቋል። ተጫዋቹ በኤሲ ሚላን ቆይታው 91 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ግቦችን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ዲያዝ ወደ ሪያል ማድሪድ ከተመለሰ በኋላ ኮንትራቱን እስከ 2027 አራዝሟል። እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2023 ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ሪያል ማድሪድ ላስ ፓልማስን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥ እና በአውሮፓ መድረክ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር እና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ዲያዝ እስከ አሁን ለሪያል ማድሪድ ባደረጋቸው 129 ጨዋታዎች 20 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከነዚህም ውስጥ 13ቱ በላሊጋው ያስቆጠራቸው ናቸው። ከክለብ ወጣ ስንል የተጫዋቹን የብሔራዊ ቡድን ቆይታ እናገኛለን። ዲያዝ በታዳጊነቱ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ለስፔን ወጣት ቡድኖች ተጫውቷል። እ.አ.አ በ2016/17 የውድድር ዘመን ለስፔን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ16 ዓመቱ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። በተለይም አዘርባጃን እ.አ.አ በ2017 ባዘጋጀችው 15ኛው የአውሮፓ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ያሳየው ድንቅ ብቃት አድናቆት አስችሮታል። በዚያ ቀጥለው በነበሩ ዓመታትም ለስፔን ከ19 እና ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ተጫውቷል። ብራሂም ዲያዝ በስፔን ታዳጊና ወጣት ቡድኖች ላይ በአጠቃላይ 28 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል። የስፔን ታዋቂ የስፖርት ጋዜጣ ማርካ እ.አ.አ ጥር 23 ቀን 2023 ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ማቀዱን የሚመለከት ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ከዜግነቱ ጋር በተያያዘ ያሉ አንዳንድ የአስተደዳር ጉዳዮች በወቅቱ መፍትሄ አግኝተዋል። ይሁንና ኮትዲቯር እ.አ.አ በ2023 ባዘጋጀችው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሞሮኮው አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከተጫዋቹ ጋር በተደረገ የቅድሚያ ስምምነት ለተጫዋቹ ጥሪ አልተደረገለትም። ዲያዝ እ.አ.አ መጋቢት 10 ቀን 2024 ለሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሀገሪቷ ብሔራዊ መጫወት እንደሚፈልግ በይፋ ማሳወቁን ማርካ በወቅቱ ዘግቧል። ጥያቄውም ተቀባይነት አገኘ። በወቅቱ የሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ብሔራዊ ቡድኑ ከአንጎላ እና ሞሪታኒያ ጋር ለነበረበት የወዳጅነት ጨዋታ ለዲያዝ ጥሪ አድርገውለታል። እ.አ.አ መጋቢት 22 ቀን 2024 ሞሮኮ አንጎላን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። እ.አ.አ ጥቅምት 6 ቀን 2024 ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከጋቦን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 4 ለ 1 ስታሸንፍ የመጀመሪያ ግቡን ለሞሮኮ ማስቆጠር ቻለ። እ.አ.አ ሕዳር 15 ቀን 2024 ሞሮኮ በማጣሪያው ጋቦንን 5 ለ 1 ስትረታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። ከሶስት ቀናት በኋላ ሞሮኮ ከሌሴቶ ጋር ባደረገችው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ 7 ለ 0 ስታሸንፍ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር በሀገሩ ማልያ የመጀመሪያ ሀትሪኩን ሰርቷል። እ.አ.አ ጥቅምት 2025 ሞሮኮ ራባት ላይ ኮንጎ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 በማሸነፍ በስፔን ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተይዞ የነበረውን 15 ተከታታይ ጨዋታዎችን የማሸነፍ ክብረ ወሰን በመስበር ወደ 16 ማድረስ ችላለች። በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ ዲያዝ ተሰልፎ ተጫውቷል። የሞሮኮ ተከታታይ የማሸነፍ ጉዞ 19 ጨዋታዎች ደርሶ የነበረ ሲሆን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከማሊ ጋር አንድ አቻ ስትለያይ አብቅቷል። ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በማጣሪያ ብታልፍም አስቀድማ ውድድሩን እንድታዘጋጅ እድል አግኝታ የነበረው ጊኒ በዝግጅት ማነስ ምክንያት በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለሞሮኮ ተሰጥቷል። ሞሮኮ የዘንድሮውን ውድድር በደማቅ ሁኔታ እያካሄደች ትገኛለች። በውድድሩ ላይ ጎልተው ከታዩ ተጫዋቾች መካከል ብራሂም ዲያዝ ተጠቃሽ ነው። በአፍሪካ ዋንጫው እስከ አሁን ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። በተሰለፈባቸው በእያንዳዱ ጨዋታዎች ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በአምስት የአፍሪካ ዋንጫ ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል። ሞሮኮ በሩብ ፍጻሜው ማሊን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል። ሀገሩ ወደ ግማሽ ፍጻሜ እንድታልፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱንም እየመራ ይገኛል። ሞሮኮ በዚሁ ግስጋሴዋ ከቀጠለች ዲያዝ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ሞሮኮ በግማሽ ፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ታደርጋለች። ዲያዝ በዚህ ጨዋታ ላይ ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ የእግር ኳስ ተንታኞች ብራሂም ዲያዝ እ.አ.አ በ2026 ወጥነት ያለው ብቃት ማሳየት ከቻለ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማቱን የሚወስድበት የለም እያሉ ይገኛሉ። ሞሮኳውያን በተጫዋቹ ፍቅር ልባቸው ከንፏል። በየጨዋታው ዲያዝ ዲያዝ እያሉ ከፍተኛ ድጋፍ እና ሙገሳ እየሰጡት ይገኛሉ። እሱም በድንቅ ብቃቱ ምላሽ እየሰጣቸው ነው። በተወለደበት ማላጋ ከተማ የጀመረው የእግር ኳስ ሕይወት በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የበለጠ አብቧል። የሞሮኮው አዲሱ ኮከብ ብራሂም ዲያዝ ቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወት በስኬት እና በድል የደመቀ እንደሚሆን ከአሁኑ ድንቅ ብቃቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።