ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ ዘመቻ በይፋ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት
የክረምቱ ወቅት ሲደርስ፣ እኛም ለወገኖቻችን የምንዘረጋው የደግነት እጅ አብሮ ይጀግናል ሲሉ ገልጸዋል።



‎በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ጎሮ ወረዳ የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ዛሬ በይፋ ማስጀመራቸውን ጠቁመዋል።

የገጠር ኮሪደር ልማት መርሃ-ግብር አካል በሆነው ዲዛይን መሠረት 20 ቤቶች በአካባቢው እንደሚገነቡ አመልክተዋል።



‎ሀገራችንን በጋራ ማንሳት የምንችለው አንዳችን ለሌላችን እጃችንን ስንዘረጋ ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በዚህ ሥራ እንዲሳተፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም