ቀጥታ፡

የዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2018 (ኢዜአ):- በ23ኛ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የስምንተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በምድብ ሁለት ቼክ ሪፐብሊክ ከደቡብ አፍሪካ ምሸት አንድ ሰዓት ላይ በአትላንታ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በምድቡ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቼክ ሪፐብሊክ በደቡብ ኮሪያ 2 ለ 1፣ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግደዋል።

ሀገራቱ ከሽንፈታቸው ለማገገም እና ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋቸውን ለማለምለም ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

በዚሁ ምድብ ሜክሲኮ ከኮሪያ ሪፐብሊክ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በጓድላሃራ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ከአዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሜክሲኮ በመክፈቻው ጨዋታ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

ኮሪያ ሪፐብሊክ ቼክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 ማሸነፏ ይታወሳል።

አሸናፊው ሀገር ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቱን ያረጋግጣል።

በምድብ ሁለት ስዊዘርላንድ ከቦስኒያ ሄርዞጎቪና ከምሽቱ አራት ሰዓት በሎስ አንጀለስ ስታዲየም፣ ካናዳ ከኳታር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በቢሲ ፕሌስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ከኳታር፣ ካናዳ ከቦስኒያ ሄርዞጎቪና በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ሀገራቱ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም