በሲዳማ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሲዳማ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
ሀዋሳ፤ ሰኔ 11/2018(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል 49 ሺህ ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ነው።
የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ በሀዋሳ ከተማ ሐይቅ ዳር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ክልላዊ ፈተናውን አስጀምረዋል፡፡
አቶ በየነ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለፈተናው ለማዘጋጀት ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ለፈተናው አስፈላጊው ዘግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው፣ በዛሬው እለትም 49 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን በ232 ልዩ የፈተና ማዕከላት እየወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ፈተናው በልዩ ማዕከላት መሰጠቱ ጤናማ የፈተና ሂደት እንዲኖር፣ ኩረጃን ለማስቀረት እና ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግረዋል።