በተጠባቂው ጨዋታ እንግሊዝ ክሮሺያን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ እንግሊዝ ክሮሺያን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ 12 መርሐ ግብር እንግሊዝ ክሮሺያን 4 ለ 2 አሸንፋለች።
በዳላስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃሪ ኬን በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጁድ ቤሊንግሃም እና ማርከስ ራሽፎርድ ቀሪዎቹን ጎሎች ለእንግሊዝ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ማርቲን ባቱሪና እና ፔታር ሙሳ የክሮሺያን ግቦች አስቆጥረዋል።
ሀሪ ኬን በዓለም ዋንጫው ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 10 ከፍ አድርጓል።
115ኛ ጨዋታውን ለእንግሊዝ ያደረገው የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኬን የጎል ብዛቱን 81 አድርሷል።
በጨዋታው እንግሊዝ የተሻለ ብልጫ ወስዳለች።
ውጤቱን ተከትሎ እንግሊዝ ምድብ 12ትን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።
ክሮሺያ ያለ ምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች።