ጋና ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች - ኢዜአ አማርኛ
ጋና ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጋና ፓናማን 1 ለ ዐ አሸንፋለች።
ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቶሮንቶ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ 12 ሁለተኛ ጨዋታ የ20 ዓመቱ የአማካይ ተጫዋች ካሌብ ይሬንኪ በ95ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ጋና የጨዋታ ብልጫ ቢወሰድባትም ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝታለች።
ተጋጣሚዋ ፓናማ በኳስ ቁጥጥር እና ግልጽ የግብ እድሎችን በመፍጠር ተሽላ ብትገኝም ጎል ማስቆጠር ተስኗታል።
የጋናው አንቶዋን ሴሜኒዮ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል።
ውጤቱን ተከትሎ የምዕራብ አፍሪካዋ ጋና ውድድሩን በድል ጀምራለች።
ፓናማ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ነጥቧን የማግኘት ህልሟ ሳይሳካ ቀርቷል።
በምድብ 12 ትናንት ማምሻውን በተካሄደ የመጀመሪያ ጨዋታ እንግሊዝ ክሮሺያን 4 ለ 2 አሸንፋለች።
በምድቡ ሁለተኛ መርሐ ግብር ጋና ከእንግሊዝ የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።
ፓናማ ከክሮሺያ ሌላኛው የሚደረግ ጨዋታ ነው።