ምርጫ ቦርድ የ723 የምርጫ ክልሎች ውጤት መጽደቁን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
ምርጫ ቦርድ የ723 የምርጫ ክልሎች ውጤት መጽደቁን ገለጸ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 10/2018 (ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከተካሄደባቸው የምርጫ 1 ሺህ 139 የምርጫ ክልሎች መካከል የ723ቱ ውጤት መጽደቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫውን አስመልክቶ መግለጫ እየሰጠ ነው።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በመግለጫው ላይ እንዳሉት፤ በአጠቃላይ ካሉት 1ሺህ 139 የምርጫ ክልሎች መካከል የ723ቱ የምርጫ ክልሎች ውጤቶች በቦርዱ ፀድቀዋል።
ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ አብዛኛዎቹ ቅሬታዎችም በህግ አካል ታይተው እልባት ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።