ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ኮፕ-32 ጉባኤን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ባለሃብቶች ሚናቸውን መወጣት አለባቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Dec 12, 2025 101
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት (ኮፕ-32) ጉባኤን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ባለሃብቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ /ኮፕ-32/ በተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአራዳ ፓርክ ተካሂዷል።   በመርሀ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን፣ የመዲናዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለብቶች እንዲሁም አልሚዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት ነው። ይህም ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር፣ በከተሞች ልማትና ውበት የተመዘገቡ ውጤቶች ዓለም አቀፉን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ብሎም አዲስ አበባ የዓለም የስበት ማዕከል መሆናቸውን በመጥቀስ፣ መዲናዋ ባለፈው ዓመት በርካታ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏን ገልጸዋል። ኮፕ-32 የዓለማችን ትልቁ የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ነው የተናገሩት። ጉባኤው ለኢትዮጵያውያን ብዙ ዕድል ይዞ ይመጣል ያሉት ከንቲባዋ፤ ለዚህ ደግሞ መንግሥት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ጉባኤው ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማዘጋጀት ዕድል እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየትና የስራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሀብቶች አልሚዎችና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ጉባኤውን በስኬት ለማካሄድ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስረድተዋል። ጉባኤውን በብቃት በማስተናገድ ለኢትዮጵያ ለውጥ መሰረት መጣል አለብን ያሉት ከንቲባዋ፤ ዛሬ የስራ ክፍፍል በማድረግና ዝግጅት በመጀመር ግባችንን ማሳካት አለብን ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ገልጸው፤ ውጤቱም በጋራ ትብብር የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው ስኬቶች ለቀጣይ ስራዎቻችን መስፈንጠሪያ እንደሚሆኑ በመጥቀስ፤ ኮፕ-32 እንዲሁ የተገኘ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤ አዘጋጅነትን ለማግኘት ዓለም አቀፋዊ ውድድር ማድረግ ነበረባት ያሉት ኃላፊዋ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌሎችም አረንጓዴ ልማት ስራዎች በተገኙ ውጤቶች መመረጧን በመግለጽ። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ105 በላይ ሁነቶችን ማዘጋጀቷን ገልጸው፤ እነዚህ ስኬቶች የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅትን በድል እንደምንወጣ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።   በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ባለሃብቶችና አልሚዎች በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ኮፕ-32 ለማስተናገድ መመረጧ ትልቅ ዕድል ይዞ ይመጣል ብለዋል፡፡ በጉባኤው የሚሳተፉ አካላት የውጭ ምንዛሪ ይዘው እንደሚመጡ በማንሳት፤ በቆይታቸው የአገልግሎት ዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ገንቢ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡ ኮፕ-32 የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያ ስኬት ማሳያ እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ጉባኤውን በስኬት ማስተናገድ እንድትችል ከመንግስት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡ በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛ ጉባኤ ላይ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን 32ኛ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (COP-32) ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወቃል።
ስምምነቱ ድንበር ዘለል ሽብርተኝነትንና ሌሎች ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል ከፍ ያለ ፋይዳ አለው
Dec 12, 2025 127
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እና በኮንጎ ሪፐብሊክ(ብራዛቢል) መካከል የተፈረመው ስምምነት ድንበር ዘለልና ሽብርተኝነት የመሳሰሉ ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል ከፍ ያለ ሚና እንዳለው የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ገለጹ። በኢትዮጵያ እና በኮንጎ ሪፐብሊክ(ብራዛቢል) መካከል በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል። የኢትዮጵያ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ የተመሰረተው ኮንጎ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ መሆኑ ተመላክቷል።   ኢትዮጵያ በወቅቱ በአፍሪካ የነፃነት ንቅናቄ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራት በመሆኗ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ ነፃነቷን ባገኘችበት በ1960ዎቹ መጀመሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በይፋ መሥርታለች። ግንኙነቱ በዋናነት የተጀመረው በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በአዲስ አበባ በተመሠረተው በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) እና በአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት (AU) ማዕቀፍ ውስጥ ነበር። የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው በፊርማ መርሃ ግብሩ ወቅት ገልፀዋል። ሚኒስትሯ ከኮንጎ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ጋር በዋናነት በወታደራዊ ኢንዱስትሪ ውጤቶች፣ በጦር መሳሪያ ጥገና፣ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተናግረዋል። ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ አቅም በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል እድል ይፈጥራልም ነው ያሉት።   አሁን ያለንበት አለም በትብብር መስራትን ይጠይቃል ያሉት ኢንጂነር አይሻ ድንበር ዘለልና ሽብርተኝነት የመሳሰሉ ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከልም ከፍ ያለ በጎ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚኖረን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል። የኮንጎ ብራዛቢል መከላከያ ሚኒስትር ቻርለስ ሪቻርድ ሞንጆ በበኩላቸው ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማጎልበት የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል። የመግባቢያ ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመቀየር በቅርቡ ወደ ተጨባጭ ስራ እንገባለን ነው ያሉት። ሚኒስትሩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ኮንጎ ብራዛቢልን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመላክቷል።
የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደግፍ ነው
Dec 12, 2025 106
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደግፍና የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ ገለጹ፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር በበኩሉ፤ በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡   በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛ ምስራቅ፣ ኤዥያና ፓስፊክ አገሮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዳዋኖ ከድር፣ በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጂንግ ካንግ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ እንዳሉት፤ ኮሪያ ሪፐብሊክ በአምራች፣ በመሰረተ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በአይ ሲ ቲ፣ በዲጂታል ሥርዓትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የኢትዮጵያ ጠንካራ አጋር ናት፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በግንባታ፣ በኢንጂነሪንግና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሰማራት ጥራታቸውን የጠበቁ ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ ፎረሙ የኢትዮጵያና ኮሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክር ከመሆኑም ባለፈ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደግፍና የሥራ ዕድሎችን ይዞ የሚመጣ ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያና ኮርያ መካከል ጠንካራ ወዳጅነት አለ። የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ የሥራ ተቋራጮች ማህበር በግንባታ፣ በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንትና በኢንጂነሪንግ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ማህበሩ በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ባሉት የመሠረተ ልማት እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም እንዲሁ፡፡   በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛ ምስራቅ፣ ኤዥያና ፓስፊክ ሀገራት ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ዳዋኖ ከድር እንደገለጹት፤ የኮሪያ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዘርፍ መሰማራቱ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ሃክ ሶ ዮን በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ማህበሩ ለሁለቱ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ትብብር መጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በስር ያሉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ደረጃውን ጠብቆ መታደሱ የአካባቢውን ታሪክ የተሟላ ያደርገዋል
Dec 12, 2025 87
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ የአካባቢውን ታሪክ የተሟላ እንደሚያደርገው ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ የሚገኘውን እና 129 ዓመታትን ያስቆጠረውን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተክርስቲያን የሕንጻ እድሳት ሥራ ጎብኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ ቤተ ክርስቲያኑ ከዓድዋ ድል ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሣሠረ ነው። በፋሽስት ወረራ ጊዜ በእሳት መቃጠልና ጥቁር ቀለም እስከ መቀባት ዋጋ ከፍሏል ብለዋል። የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ደረጃውን በጠበቀና ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ እየታደሰ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።   የህንጻው የአሠራር ጥበብ፣ የሥዕሎቹ ጥበባዊ ከፍታ፣ የብረት ሥራዎች የጥበበ ዕድና የጥራት ደረጃ እንዲሁም የቅርሶቹ የላቀ ዋጋ እጅግ አስደናቂ መሆናቸውን አድንቀዋል። የዓድዋ ድል መታሰቢያ መገንባቱ፣ የዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ጥገና እና የመመልከቻ አምፊ መሠራቱ የአካባቢውን የቱሪዝም ፍሰት ከፍ አድርጎታል ነው ያሉት። የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ ደግሞ የአካባቢውን ታሪክ የተሟላ እንደሚያደርገው አንስተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ የቤተ ክርስቲያኑን እድሳት ሥራው ከከተማዋ የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አጠባበቅ ደረጃዎች ጋር እንዲጣጣም ሁሉም አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መላከ ገነት ክብሩ ገብረጻድቅ፤ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም ከቀለም ቅብና ጥቃቅን ጥገናዎች ያለፈ እድሳት እንዳልተደረገለት ጠቅሰዋል። ሆኖም ከዕድሜው ብዛትና በተለያዩ ምክንያቶች በጉልላቱ፣ በእሳት መከላከያ ጣሪያው እና በዙሪያው ጉዳቶች በመከሰታቸው የባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተሟላ ዕድሳት መገባቱን ገልጸዋል። የዕድሳት ሥራው በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ መጀመሩን ጠቅሰዋል።   የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ አክለውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቤተ ክርስቲያን እድሳት ሥራውን በአካል ተገኝተው በመመልከታቸው ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል። ጉብኝታቸው ቤተ ክርስቲያኑ የሀገር ታሪክና ቅርስ በመሆኑ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ መንግሥት የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል። የቅርስ ሥራዎች ከፍተኛ የኪነ ህንጻ ባለሙያ አርክቴክት ኤፍሬም ንጉሤ እንዳሉት፤ እድሳቱ ከመጀመሩ በፊት ለስድስት ወራት ዝርዝር ጥናት ተደርጓል። በጥናቱ ቤተ ክርስቲያኑ በታሪኩ ከቀለም ቅብና መሰል ቀላል ሥራዎች ያለፈ ዋና ጥገና ተደርጎለት እንደማያውቅ ተረጋግጧል ነው ያሉት። ጉልላቱ፣ በዓይነቱ ልዩ የሆነው የቤተ ክርስቲያኑ እሳተ ከላ እና ሌሎችም ክፍሎች በእርጅና ምክንያት ዝናብ እስከማስገባት ስለደረሱ ወደ ስር ነቀል ጥገና መገባቱን ገልጸዋል። የቅድሳት ሥዕላቱን የማደስ፣ የመስታወት ጌጦችን በነበሩበት ይዞታ የማስተካከል እና ሌሎች የእጅ ጥበብ የሚሹ ውድ ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል። ቤተ ክርስቲያኑ መጀመሪያ ሲሰራበት የነበረውን ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ኖራ እና ሲሚንቶ ያለመቀየር መርህን በመከተል በከፍተኛ ሙያዊ ጥንቃቄ እየታደሰ እንደሚገኝ አስረድተዋል። መምህር ግሩም ጌታቸው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የህንጻ እድሳት አሰባሳቢ ዐቢይ ኮሚቴ የገቢና ቅስቀሳ ክፍል ሰብሳቢ ናቸው። የእድሳት ሥራው አጠቃላይ 157 ሚሊዮን ብር የሚወስድ ሲሆን፤ በሕዝብ ድጋፍ እየታደሰ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሀገር ቅርስና ሀብት በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የዕድሣት ሥራው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሚታይ

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ስምምነቱ ድንበር ዘለል ሽብርተኝነትንና ሌሎች ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል ከፍ ያለ ፋይዳ አለው
Dec 12, 2025 127
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እና በኮንጎ ሪፐብሊክ(ብራዛቢል) መካከል የተፈረመው ስምምነት ድንበር ዘለልና ሽብርተኝነት የመሳሰሉ ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል ከፍ ያለ ሚና እንዳለው የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ገለጹ። በኢትዮጵያ እና በኮንጎ ሪፐብሊክ(ብራዛቢል) መካከል በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል። የኢትዮጵያ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ የተመሰረተው ኮንጎ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ መሆኑ ተመላክቷል።   ኢትዮጵያ በወቅቱ በአፍሪካ የነፃነት ንቅናቄ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራት በመሆኗ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ ነፃነቷን ባገኘችበት በ1960ዎቹ መጀመሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በይፋ መሥርታለች። ግንኙነቱ በዋናነት የተጀመረው በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በአዲስ አበባ በተመሠረተው በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) እና በአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት (AU) ማዕቀፍ ውስጥ ነበር። የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው በፊርማ መርሃ ግብሩ ወቅት ገልፀዋል። ሚኒስትሯ ከኮንጎ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ጋር በዋናነት በወታደራዊ ኢንዱስትሪ ውጤቶች፣ በጦር መሳሪያ ጥገና፣ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተናግረዋል። ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ አቅም በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል እድል ይፈጥራልም ነው ያሉት።   አሁን ያለንበት አለም በትብብር መስራትን ይጠይቃል ያሉት ኢንጂነር አይሻ ድንበር ዘለልና ሽብርተኝነት የመሳሰሉ ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከልም ከፍ ያለ በጎ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚኖረን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል። የኮንጎ ብራዛቢል መከላከያ ሚኒስትር ቻርለስ ሪቻርድ ሞንጆ በበኩላቸው ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማጎልበት የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል። የመግባቢያ ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመቀየር በቅርቡ ወደ ተጨባጭ ስራ እንገባለን ነው ያሉት። ሚኒስትሩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ኮንጎ ብራዛቢልን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመላክቷል።
በክልሉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቷል - ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ
Dec 12, 2025 95
ጋምቤላ፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል ሰላምን ዘላቂ በማድረግ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ። በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።   ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ በወቅቱ እንዳሉት የክልሉን ሰላም በማጽናት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ማጠናከር ይገባል። በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የሰላም ግንባታና የልማት ስራዎችን ወደኋላ ለመመለስ እኩይ ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች መኖራቸውን ጠቁመዋል። በመሆኑም የፀረ-ሰላም ሃይሎችን እንቅስቃሴ በመግታት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል። በዚህ ረገድ በህዝብና በፀጥታ መዋቅሩ እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም የክልሉን ሰላም በማጽናትና የተጀመሩ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን በማስቀጠል ረገድ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።   የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው በአመራሩ ዘንድ ያለውን የሃሳብና የተግባር አንድነት በማጠናከር ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ ልንተጋ ይገባል ብለዋል። በተለይም በቅርቡ ለአመራሩ የተሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ለክልሉ ሁለንተናዊ እድገትና ዘላቂ ሰላም በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ሰላምን ለማደፍረስና ልማቱን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎችን ተከታትሎ ለህግ ለማቅረብ የተጀመሩ ጥረቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።   በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሺኔ አስቲን በበኩላቸው አመራሩ የጋራ የሆኑ ትርክቶችን መገንባት ከቻለ የማይፈቱ ችግሮች አይኖሩም ብለዋል። በመሆኑም አመራሩ አንድነቱን በማጠናከር የፀረ ሰላም ሃይሎችን እንቅስቃሴ በጋራ መግታት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ዘላቂ የሰላም ስምምነቱ የፈጠረውን አስቻይ ሁኔታ በመጠቀም ለህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ መስራት ይገባል
Dec 12, 2025 101
ጎንደር ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ዘላቂ የሰላም ስምምነቱ የፈጠረውን አስቻይ ሁኔታ በመጠቀም አመራሩ ለህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ መስራት እንደሚገባው ተመላከተ። "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በጎንደር ከተማ ለመካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡   የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ እንደተናገሩት፤ በክልሉ መንግስትና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋሃድ) መካከል በቅርቡ የተደረገው ዘላቂ የሰላም ስምምነት መንግስት ችግሮች በውይይትና በንግግር እንዲፈቱ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት ትልቅ እርምጃ ነው። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በዞኑ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መርጠው ሰሞኑን መመለሳቸውን ጠቁመው፣ ይህም ለአካባቢው ዘላቂ ሰላምና ልማት አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል፡፡ በመሆኑም አመራሩ በስልጠና ባገኘው እውቀትና ግንዛቤ ታግዞ የመደመር መንግስት እሳቤዎችን ወደ ተግባር በማሸጋገር ለህዝቡ የልማት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት በትጋት መስራት አለበት ሲሉ አሳስበዋል። ግብርና፣ ቱሪዝም፣ የከተማ ልማት ሥራ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፍ ስልጠናው በዋናነት ያተኮረባቸው አቅጣጫዎች እንደሆኑ ጠቁመው፣ አመራሩ እነዚህን ዋነኛ የልማት ውጥኖች ለማሳካት በጊዜ የለኝም መንፈስ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡   ገቢ አሰባሰብ፣ ከተማ ግብርና፣ ትምህርት፣ የሥራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ ህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና ገበያ ማረጋጋት ስራዎች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል። የዞኑ ሰላም ጸንቶ እንዲቀጥል ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሆን የጀመረውን ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስተዳዳሪው አንስተዋል። ስልጠናው በአመራሩ መካከል የሀሳብና የተግባር አንድነት እንዲኖር በማድረግ በኩል ትልቅ አቅም ሆኖናል ያሉት ደግሞ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የስልጠናው ተሳታፊ አቶ መንግስቱ ቻላቸው ናቸው፡፡ የመደመር መንግስት እሳቤ ሀገር የማሻገር ትልቅ ርዕይ የሰነቀ ሀገር በቀል እውቀት በመሆኑ ለተግባራዊነቱ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡   ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የመጡት ወይዘሮ ሰላማዊት መሳፍንት በበኩላቸው፤ በዞኑ ተስፋ ሰጪ የሰላም ሁኔታ በመፈጠሩ ለህዝቡ የልማት ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።   ስልጠናው ሀገራዊና ክልላዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በቀጣይ አመራሩ ሊያከናውናቸው የሚገቡ የተግባራት አቅጣጫዎችን ያመላከተ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በስልጠናው ጎንደር ከተማን ጨምሮ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተውጣጡ መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት በሀገራዊ ምክክሩ መሳተፍ ይኖርባቸዋል
Dec 12, 2025 101
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ለምክክርና ንግግር ራሳቸውን በማዘጋጀት በሀገራዊ ምክክሩ መሳተፍ እንደሚኖርባቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ። በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍና አካታች ምክክር በማድረግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ኮሚሽኑ ከተመሰረተበት ዓላማ መካከልም ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የሚያስችል የፖለቲካ ባህል ለማዳበር እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር አንዱ ነው። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ክልላዊም ሆነ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማካሔድ በታሰበው ሃገራዊ ምክክር ላይ ተሳትፎ በማድረግ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታት የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር እየሰራ ሲሆን፤ በአብዛኛው በሚባል ደረጃ በስሩ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን አጀንዳ በመሰብሰብ ለኮሚሽኑ ማስረከቡን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም ከመነሻው ጀምሮ በምክክር ሂደቱ ያልተሳተፉና ከተሳተፉ በኋላም ያቆሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግም ውይይቶችና ኮንፈረንስ እየተደረገ መግባባት ላይም እየተደረሰ መሆኑን ገልፀዋል። ከፖለቲካ ፓርቲዎችም በተጨማሪ ጫካ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ወደ ምክክሩ በመምጣት ቀጣዩን ትውልድ የሚጠቅሙ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ነው የተናገሩት። እንደ ሀገር የሚነሱትን ችግሮች ለመፍታት ከምክክር ውጭ አማራጭ የለም የሚሉት ዋና ሰብሳቢው፤ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ሰፊ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው ብለዋል። ከፖለቲካ ፓርቲዎችም ባሻገር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገራዊ ምክክር ሒደቱ ውስጥ በመሳተፍ ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስከበር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን ማበርከት እንዳለበትም አሳስበዋል። ኢትየጵያ ብዝሃ ሀገር ነች ያሉት አቶ ሰለሞን፤ በመደማመጥና በሀሳብ የበላይነት በመመራት የሀገርን ሰላም ማጽናትና የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት። በሀገሪቱ የዲሞክራሲ ስርዓትን የመገንባት ስራ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው አለመሆኑን የተናገሩት ሰብሳቢው፤ በየደረጃው ርብርብ በማድረግ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት። ሀገራዊ ምክክሩ በሀገሪቷ ያሉትን ችግሮች ከመፍታት አኳያ ትልቅ እፎይታን የሚሰጥና ችግሮችን የሚያቃልል መሆኑንም ነው ያነሱት። በቅርቡም በትጥቅ ትግል ላይ የቆዩ ወገኖች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ለማህበረሰቡና ለሀገር ሰላም በማሰብ ወደ ሰላም መምጣታቸው የሚመሰገን ነው ብለዋል። በተመሳሳይም ሌሎችም ይህንኑ አርአያ በመከተል ለውይይትና ለንግግር ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚገባቸውም ነው ያነሱት። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከ60 በላይ የሚሆኑ ክልላዊና ሀገራዊ ፓርቲዎችን ያቀፈ ነው።
ኢትዮጵያ በምትሳተፍባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ተደማጭነቷ እያደገ መጥቷል
Dec 12, 2025 161
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምትሳትፍባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ተደማጭነቷ እያደገ መምጣቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ - ጆሃንስበርግ በተካሄደው የቡድን 20 አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ በአፍሪካና ኢትዮጵያ ተስፋዎች እና በመደመር እሳቤ ዙሪያ ንግግር ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ በግልፅ ታይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ወቅት ያደረጉት ንግግርና ውይይቶች የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ ከፍታና ተደማጭነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በምትሳተፍባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ተደማጭነቷ እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ ከቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ፍሬያማ የጎንዮሽ ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡ በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤና የሁለትዮሽ ውይይቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ የአፍሪካ የጋራ ጉዳዮችን የተመለከቱ መልዕክቶች መተላለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ያስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አጀንዳ ሰጪ መሆኗን በግልጽ አሳይቷል ብለዋል፡፡   የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እንዳለ ንጉሴ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከሀገር በቀል እሳቤ የተቀዳ ለአፍሪካ ሞዴል እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ማድረጓን ገልጸው፤ ከለውጡ በኋላ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገቡ ውጤታማ ተግባራትን አንጸባርቃለች ብለዋል፡፡ የመደመር እሳቤ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካውያን የሚበጅ መሆኑን በመጥቀስ፤ አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት እሳቤ ለመውጣት መነሻ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ነው
Dec 12, 2025 103
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ አስታወቀ። የጋራ ምክር ቤቱ ከክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች ጋር የ2017 ሪፖርትና የ2018 ዕቅድ ማዕቀፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለሰ ዓለሙ፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ፣ የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች ሰብሳቢዎች ተገኝተዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ በሀገሪቱ የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው። ሁሉም ፓርቲዎች በእኩልነት የሚሳተፉበትና ሃሳባቸውን በነጻነት የሚገልጹበት ምህዳር ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ምክር ቤቱ ሀገራዊ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን አጀንዳ አሰባስቦ ከማቅረብ ጀምሮ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ገለልተኛ እና ግልጽ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የብልፅግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ በፓርቲዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አበረታች ተግባር እያከናወነ ነው ብለዋል። ፓርቲዎች በብሔራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም በመያዝ በሰላም፣ በልማትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እያደረጉት ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። የጋራ ምክር ቤቱ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት፣ መቻቻልን ለማጎልበትና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲኖር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
ዘላቂ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች የበደሉትን ሕዝብ በልማት እንዲክሱ የማመቻቸት ተግባር እየተከናወነ ነው
Dec 12, 2025 93
ጎንደር፤ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የዘላቂ ሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን የተሃድሶ ስልጠና ወስደው የበደሉትን ሕዝብ በልማት ለመካስና ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ የማመቻቸት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ። ቀደም ሲልም የሰላም አማራጭን ተከትለው የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው እራሳቸውን እንዲችሉ ሰፊ ጥረትና ድጋፍ መደረጉም ተመልክቷል። የክልሉ መንግስት እና የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት መካከል ዘላቂ የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወቃል፡፡ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ አንተነህ ታደሰ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ ስምምነቱን ተከትሎ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች ሰላምን አማራጭ በማድረግ ሙሉ ትጥቃቸውን ለመንግስት በማስረከብ ተመልሰዋል። የተመለሱትም በተሳሳተ መንገድ በሕዝቡ ላይ በደል በመፈጸማቸው በመፀፀት የሰላምን አማራጭ በመከተላቸው እንደሆነ ገልጸዋል። በወገራ፣ በኪንፋዝ በገላ፣ በአለፋ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በጭልጋና በታች አርማጭሆ ወረዳዎች የተመለሱት የቀድሞ ታጣቂዎቹ የተሃድሶ ስልጠና ወስደው የበደሉትን ሕዝብ በልማት በመካስ ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ የማመቻቸት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ውስጥ በወገራ ወረዳ ለቀድሞ ታጣቂዎቹ የተሃድሶ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ጠቅሰው፤ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። መንግስት የሰላም አማራጭን በመከተል የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ በማቋቋም በኩል ባለፈው ዓመት ወደ ቀደመ ስራቸው የተመለሱ እንዳሉም አውስተዋል። የቀድሞ ታጣቂዎቹ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው እራሳቸውን እንዲችሉና ህይወታቸውንም እንዲመሩ መንግስት ሰፊ ጥረትና ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል። ሕብረተሰቡ ሰላሙን ለማፅናት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል አመልክተው፤ የሰላምን አማራጭ በማይቀበሉ የሽፍታ ሰብስቦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ያለ ልዩነት መረባረብ ይገባል 
Dec 12, 2025 177
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ በዘመናት መካከል አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ዕድል በመሆኑ ለስኬቱ ያለ ልዩነት ልንረባረብ ይገባል ሲል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ (National Plenary) ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት እያጠናቀቀ እንደሚገኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገው ውይይት ተገልጿል።   በውይይቱ የትግራይ ክልልን ጨምሮ አንዳንድ ቀሪ ተግባራትን ፈጥኖ በማጠናቀቅ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። በትግራይ ክልል ወደ ምክክር ለመግባት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በተደራጀ መንገድ መከናወናቸው፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፉ የተለያዩ የቅድመ አጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች መካሄዳቸውና ከመድረኮቹም ጠቃሚ ግብዓቶች መገኘታቸው ተነስቷል። በክልሉ አጀንዳ በማሰባሰብ እና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን በማስመረጥ ምክክሩን ምሉዕ ለማድረግ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባ ሥነ-ዘዴን በመጠቀም ቀሪ ሥራዎችን ማጠናቀቅ እንዲቻል በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመግባባት ላይ መደረሱም ተገልጿል። ለዚህም መላው የትግራይ ህዝብ፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ለሚያከናውነው አጀንዳ የማሰባሰብ እና የጉባኤ ተሳታፊዎችን የማስመረጥ ሥራ የበኩላቸውን ቀና ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።   የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ታሪካዊ፣ ከአንድ ትውልድ የተሻገረ፣ ከአንድ ፓርቲና ከአንድ ሥርዓት በላይ ከፍ ያለ፣ በዘመናት መካከል አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ዕድል እና ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የገለጸው ምክር ቤቱ፤ መላው ኢትዮጵያውያን ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ያለልዩነት እንዲረባረቡ መልዕክት አስተላልፏል። የሰላም በሩ ዛሬም ክፍት እንደሆነ በመግለጽም፣ ማንኛውም የፖለቲካ ጥያቄ አለኝ የሚል አካል እና በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ውስጥ የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች ጭምር በሰላማዊ መልኩ ጥያቄያቸውን በአጀንዳነት ለምክክር ኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል። የቆየውን ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህላችንን ከመሠረቱ ለመቀየር የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ጥሪ በማስተላለፍ ምክር ቤቱ ውይይቱን አጠናቅቋል። በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ፣ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና እና ምክትልን ጨምሮ ሁሉም ኮሚሽነሮች፣ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ማህበራዊ
የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ደረጃውን ጠብቆ መታደሱ የአካባቢውን ታሪክ የተሟላ ያደርገዋል
Dec 12, 2025 87
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ የአካባቢውን ታሪክ የተሟላ እንደሚያደርገው ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ የሚገኘውን እና 129 ዓመታትን ያስቆጠረውን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተክርስቲያን የሕንጻ እድሳት ሥራ ጎብኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ ቤተ ክርስቲያኑ ከዓድዋ ድል ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሣሠረ ነው። በፋሽስት ወረራ ጊዜ በእሳት መቃጠልና ጥቁር ቀለም እስከ መቀባት ዋጋ ከፍሏል ብለዋል። የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ደረጃውን በጠበቀና ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ እየታደሰ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።   የህንጻው የአሠራር ጥበብ፣ የሥዕሎቹ ጥበባዊ ከፍታ፣ የብረት ሥራዎች የጥበበ ዕድና የጥራት ደረጃ እንዲሁም የቅርሶቹ የላቀ ዋጋ እጅግ አስደናቂ መሆናቸውን አድንቀዋል። የዓድዋ ድል መታሰቢያ መገንባቱ፣ የዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ጥገና እና የመመልከቻ አምፊ መሠራቱ የአካባቢውን የቱሪዝም ፍሰት ከፍ አድርጎታል ነው ያሉት። የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ ደግሞ የአካባቢውን ታሪክ የተሟላ እንደሚያደርገው አንስተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ የቤተ ክርስቲያኑን እድሳት ሥራው ከከተማዋ የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አጠባበቅ ደረጃዎች ጋር እንዲጣጣም ሁሉም አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መላከ ገነት ክብሩ ገብረጻድቅ፤ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም ከቀለም ቅብና ጥቃቅን ጥገናዎች ያለፈ እድሳት እንዳልተደረገለት ጠቅሰዋል። ሆኖም ከዕድሜው ብዛትና በተለያዩ ምክንያቶች በጉልላቱ፣ በእሳት መከላከያ ጣሪያው እና በዙሪያው ጉዳቶች በመከሰታቸው የባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተሟላ ዕድሳት መገባቱን ገልጸዋል። የዕድሳት ሥራው በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ መጀመሩን ጠቅሰዋል።   የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ አክለውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቤተ ክርስቲያን እድሳት ሥራውን በአካል ተገኝተው በመመልከታቸው ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል። ጉብኝታቸው ቤተ ክርስቲያኑ የሀገር ታሪክና ቅርስ በመሆኑ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ መንግሥት የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል። የቅርስ ሥራዎች ከፍተኛ የኪነ ህንጻ ባለሙያ አርክቴክት ኤፍሬም ንጉሤ እንዳሉት፤ እድሳቱ ከመጀመሩ በፊት ለስድስት ወራት ዝርዝር ጥናት ተደርጓል። በጥናቱ ቤተ ክርስቲያኑ በታሪኩ ከቀለም ቅብና መሰል ቀላል ሥራዎች ያለፈ ዋና ጥገና ተደርጎለት እንደማያውቅ ተረጋግጧል ነው ያሉት። ጉልላቱ፣ በዓይነቱ ልዩ የሆነው የቤተ ክርስቲያኑ እሳተ ከላ እና ሌሎችም ክፍሎች በእርጅና ምክንያት ዝናብ እስከማስገባት ስለደረሱ ወደ ስር ነቀል ጥገና መገባቱን ገልጸዋል። የቅድሳት ሥዕላቱን የማደስ፣ የመስታወት ጌጦችን በነበሩበት ይዞታ የማስተካከል እና ሌሎች የእጅ ጥበብ የሚሹ ውድ ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል። ቤተ ክርስቲያኑ መጀመሪያ ሲሰራበት የነበረውን ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ኖራ እና ሲሚንቶ ያለመቀየር መርህን በመከተል በከፍተኛ ሙያዊ ጥንቃቄ እየታደሰ እንደሚገኝ አስረድተዋል። መምህር ግሩም ጌታቸው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የህንጻ እድሳት አሰባሳቢ ዐቢይ ኮሚቴ የገቢና ቅስቀሳ ክፍል ሰብሳቢ ናቸው። የእድሳት ሥራው አጠቃላይ 157 ሚሊዮን ብር የሚወስድ ሲሆን፤ በሕዝብ ድጋፍ እየታደሰ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሀገር ቅርስና ሀብት በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የዕድሣት ሥራው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል
Dec 12, 2025 58
ባሕርዳር፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለማስወገድ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ሊጠናከር እንደሚገባ ተመላከተ። "ጥቃትን የማይታገስ ማህሕበረሰብ ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ሃሳብ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል።   በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ፤ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለማስወገድ የሁላችንንም ርብርብና ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል። ልማትም ሆነ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሴቶች ተሳትፎ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን በመጠበቅ ፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ የሚደረገውን ሂደት ለማጠናከርም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለማስቆም የሕብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በኩል የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ በበኩላቸው፤ ፆታዊ ጥቃትንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል በተደረገው ጥረት አበረታች ለውጥ መታየቱን ተናግረዋል። ችግሩን ከመከላከል ጎን ለጎን በክልሉ 17 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተቋቁመው ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የስነ-ልቦና ምክር፣ የጤናና የሕግ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል። በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ ፍትህ ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ሊጠናከሩ ይገባልም ነው ያሉት። ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና የሕብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ያሉት ደግሞ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ብርሃኑ ጎሽም ናቸው። ፆታዊ ጥቃት ፈፅመው በተገኙ 289 ግለሰቦች ላይ ከ3 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል። ከአንድ ሺህ 400 ለሚበልጡ ሴቶች ደግሞ ነፃ የሕግ አገልግሎት ድጋፍ መስጠት መቻሉን ጠቅሰው፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከልና ለማስቆም ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናከሮ ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
ወንጀልን በመከላከልና ሰላም በማስጠበቅ የፖሊስና ሕብረተሰቡ ትብብር ጎልብቶ ሊቀጥል ይገባል
Dec 12, 2025 64
ደብረ ብርሃን፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፡- ወንጀልን በመከላከልና የሰላም በማስጠበቅ ስራ የፖሊስና ሕብረተሰቡ ጠንካራ ትብብር ጎልብቶ ሊቀጥል እንደሚገባ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ። በደብረ ብርሃን ከተማ በወንጀል መከላከል እና በዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የስልጠና እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዋና ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ዓባይ ሙሉጌታ፤ ለወንጀል መከላከልና የሰላም ማስጠበቅ ስራ የፖሊስና ሕብረተሰቡ ጠንካራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።   በመሆኑም በደብረ ብርሃንና አካባቢው ያለውን ሰላም በዘላቂነት በማስጠበቅ የልማትና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በጋራ መስራት አለብን ብለዋል። በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሰው የሽፍታው ስብሰብ ላይ ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አንስተው፤ ለሰላም አማራጭ ዝግጁ የሆኑትንም አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የሰላም ግንባታ የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።   የሰሜን ሸዋ ዞን የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አባይ ኢሌ፤ በዞኑ የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በየዕለቱ እየገቡና አቀባበልም እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በዞኑ ያለው ሰላምና መረጋጋት በአስተማማኝ መልኩ መቀጠሉን አንስተው፤ የጸጥታ ኃይሉ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር የሰላም ግንባታ ስራው ይቀጥላል ብለዋል።
ኢኮኖሚ
የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደግፍ ነው
Dec 12, 2025 106
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደግፍና የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ ገለጹ፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር በበኩሉ፤ በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡   በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛ ምስራቅ፣ ኤዥያና ፓስፊክ አገሮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዳዋኖ ከድር፣ በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጂንግ ካንግ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ እንዳሉት፤ ኮሪያ ሪፐብሊክ በአምራች፣ በመሰረተ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በአይ ሲ ቲ፣ በዲጂታል ሥርዓትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የኢትዮጵያ ጠንካራ አጋር ናት፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በግንባታ፣ በኢንጂነሪንግና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሰማራት ጥራታቸውን የጠበቁ ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ ፎረሙ የኢትዮጵያና ኮሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክር ከመሆኑም ባለፈ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደግፍና የሥራ ዕድሎችን ይዞ የሚመጣ ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያና ኮርያ መካከል ጠንካራ ወዳጅነት አለ። የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ የሥራ ተቋራጮች ማህበር በግንባታ፣ በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንትና በኢንጂነሪንግ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ማህበሩ በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ባሉት የመሠረተ ልማት እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም እንዲሁ፡፡   በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛ ምስራቅ፣ ኤዥያና ፓስፊክ ሀገራት ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ዳዋኖ ከድር እንደገለጹት፤ የኮሪያ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዘርፍ መሰማራቱ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ልዩ ሥራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ሃክ ሶ ዮን በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ማህበሩ ለሁለቱ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ትብብር መጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በስር ያሉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሰላምን በማስጠበቅ የሕዝብን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ስልጠናው የተሻለ አቅም ፈጥሮልናል - አመራሮች
Dec 12, 2025 58
ገንዳ ውኃ፣ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ):- በመደመር መንግስት ዕይታና እሳቤዎች ላይ የተሰጣቸው ስልጠና ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ተረድተው ሰላምን በማስጠበቅ የሕዝብን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተሻለ አቅም እንደፈጠረላቸው በምዕራብ ጎንደር ዞን ሰልጣኝ አመራሮች ገለጹ። በገንዳ ውኃ ከተማ ለዞኑ ለመካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል። የስልጠናው ተሳታፊ ኑርሁሴን ሙሃመድ ፤ በስልጠናው የመደመርን መንግስት ዕይታ በመረዳት የተሻለ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። መዋቅራዊ ሽግግር፣ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ከተማ ልማት እና ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ የተሰጣቸው ስልጠና በቂ እውቀት ያስጨበጠ ነው ብለዋል። ስልጠናው ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን መረዳት እንዲችሉ ማድረጉን ጠቅሰው፤ በዚህም ቀጣይ ሁሉን አቀፍ የሰላም ግንባታና የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ልማቶችን በቁጭትና በተነሳሽነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ሌላው ተሳታፊ አቶ ሀብቴ አዲሱ፤ የከተማ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግና ሆቴል ቱሪዝም ያልተሰራበትና በርካታ ወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ከስልጠናው የተገኘውን አቅም ወደ መሬት በማውረድ የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ልማቶችን በቁጭት ለማከናወን የተሻለ አቅም ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ስልጠናው እያንዳንዱ ዘርፍ የሚፈልገውን እውቀትና ክህሎት ያገኘንበት በመሆኑ ለቀጣይ ስራችን አቅም ፈጥሮልናል ያሉት ደግሞ ሌላኛው ሰልጣኝ ፍሬ ህይወት ምስጋናው ናቸው። በስልጠናው ባገኙት እውቀት ሕዝብን ያሳተፈ የሰላም ግንባታና ልማትን ለማጠናከር ካለፉት ጊዜያት በተለየ ክትትልና ቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ እያሱ ይላቅ በበኩላቸው፤ ስልጠናው የአመራሩን የመምራትና የማደራጀት አቅም ከፍ ያደረገና ትልቅ ተነሳሽነትና ቁጭት የፈጠረ ነው ብለዋል። በተለይም እንደ ሃገር የተቀመጡ ኢኒሸቲቮችን በትክክል ለመተግበርና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ስልጠናው አቅም ፈጥሯል ሲሉ አብራርተዋል። በተለይም የከተማ ትራንስፎርሜሽን፣ የሌማት ቱሩፋት፣ የገጠር ኮሪደር፣ ቱሪዝም ልማትና ኢንዱስትሪ ማስፋፋት የአመራሩ ልዩ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በስልጠናው በየደረጃው የሚገኙ መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጎንደር ከተማ ማሳያ ናት - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
Dec 12, 2025 70
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጎንደር ከተማ ማሳያ መሆኗን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። በጎንደር ከተማ በአምራች ኢንዱስትሪና በሌማት ትሩፋት የተመዘገቡ ውጤቶች የበርካታ ዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ እንደሚገኙም ተናግረዋል። የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጎንደር ከተማ በሌማት ትሩፋት፣ በኢንዱስትሪ ልማትና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።   በጉብኝቱ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፥ በጎንደር ከተማ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸው የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። በጎንደር ከተማ በሁሉም መስክ የሚታየው ትርጉም ያለው የልማት እንቅስቃሴ የከተማዋን ለውጥ ከማፋጠን ባለፈ በርካታ ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የተሰማሩ ማኅበራትና ኢንተርፕራይዞችም የምግብ ዋስትናን እያረጋገጡ መሆናቸውን አንስተዋል። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሀገር በቀል የክህሎት ልማት ትኩረት መስጠቱ ብቁ የሰው ኃይልን በማፍራት የኢንዱስትሪ ሽግግርን እያሳለጠ ወጣቶችንም ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ስኬቶች በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገቡ መሆኑን ጎንደር ከተማ ማሳያ መሆኗንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል። በጎንደር በአመራር ትጋት በአጭር ጊዜ የተመዘገቡ ለውጦች ታሪካዊቷን ከተማ እንደገና በመውለድ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በጎንደር ከተማ ለሚከናወኑ የክህሎት ልማትና ስልጠና ተግባራት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።   የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፥ በከተማዋ በኢንዱስትሪና በሌማት ትሩፋት የተመዘገቡ የልማት ውጤቶች የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዶሮ እርባታ፣ በእንቁላል፣ ወተትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት የተገኙ ውጤቶች በቂ ምርት ለገበያ በማቅረብ ፍላጎትን በማሟላት ረገድ ሚናቸው የላቀ መሆኑንም አንስተዋል። በቀጣይም የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።
በክልሉ በሌማት ትሩፋት መርሀግብር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ውጤት እየተመዘገበ ነው
Dec 12, 2025 57
ቦንጋ፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሌማት ትሩፋት መርሀግብር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በመደመር መንግስት እይታ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸውና ባለሁለት አሀዝ እድገት ለማስመዝገብ ግብ ከተጣለባቸው መካከል የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ተጠቃሽ ነው። በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታመነ በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት በሌማት ትሩፋት መርሀግብር በተለያዩ ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡ መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ወዲህ በወተት፣ በማር፣ በዶሮ፣ በሥጋና በዓሣ 2ሺህ 650 መንደሮች መደራጀታቸውን ገልጸው፣ በዚህም በየዘርፉ ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የአመጋገብ ሥርዓት ከመቀየር ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብልዋል። እንደ አቶ ታመነ ገለጻ በክልሉ የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ከመጀመሩ በፊት ዓመታዊ የማር ምርት 56 ሺህ 275 ቶን ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት ይህ ቁጥር ወደ 71 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በተያዘው በጀት ዓመትም ምርቱን 80 ሺህ ቶን ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ሲሆን ባለፉት አምስት ወራትም 15 ሺህ ቶን ማር ለማምረት መቻሉን ጠቁመዋል። የዓሣ መንደሮችን ለማደራጀት በተከናወኑ ተግባራትም ለውጥ መመዝገቡን የጠቀሱት አቶ ታመነ በበጀት ዓመቱ 9 ሺህ ቶን ዓሣ ለማምረት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። የሺሾ-እንዴ ወረዳ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አዱኛ አለሙ በበኩላቸው እንዳሉት የአካባቢውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በወረዳው 233 የማር፣ የወተት፣ የዓሣና የዶሮ መንደሮች ተደራጅተዋል። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አርሶ አደሩ ከዚህ ቀደም በተበታተነና በባህላዊ መንገድ ሲያከናውን የነበረውን ሥራ በማዘመን ተጠቃሚ እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡ በወረዳው በዋናቦላ ቀበሌ በንብ ማነብ ሥራ የተሰማሩት አርሶ አደር አክሊሉ ወልደሚካኤል እና ታምራት ተክሌ በተደረገላቸው የባለሙያና የግብዓት ድጋፍ ውጤታማ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት እያንዳንዳቸው ሀምሳ ዘመናዊና ባህላዊ ቀፎዎች እንዳላቸው የተናገሩት አርሶ አደሮቹ ከአንዱ ቀፎ ከ35 እስከ 40 ኪሎ ግራም ማር እንደሚያገኙ ተናግረዋል። ሁለት የዓሣ ገንዳዎችን በማዘጋጀት በዓሣ እርባታ ሥራ የተሰማሩት አርሶ አደር ደምሴ ወልደሚካኤል በበኩላቸው የአሣ ምርታቸውን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የገለጹት። የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ከዚህ ቀደም በአካባቢው ያልተለመደውን የዓሣ እርባታ ሥራ በማስጀመር ለህብረተሰቡ የገቢና የምግብ አማራጭ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዓለም አቀፍ ሁኔታን ያገናዘበ የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Dec 12, 2025 78
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ ሁኔታን ያገናዘበ የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሒ ገለፁ። ጤና ሚኒስቴር "የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴሌ ጤና ቴክኖሎጂ ለጤናው ዘርፍ የሚኖራቸው የወደፊት ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት ውይይት አካሒዷል።   የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሒ እንደገለፁት መንግስት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። የጤና አገልግሎትን ከሰው ሰራሽ አስተውሎትና ቴሌ-ጤና ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። ለህክምና አገልግሎት የሚሰበሰቡ መረጃዎች ላይ በመመስረት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን መጠቀም ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል። በተለይም በወረርሽኝና በተፈጥሮ አደጋዎች ቅድመ ትንበያና የተቀናጀ ምላሽ አሰጣጥ ላይ አይነተኛ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል። የጤና ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው ቴክኖሎጂዎች በተገቢው መልኩ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም አንስተዋል። በ2016 ዓ.ም የተሻሻለው አዲሱ የጤና ፖሊሲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በተገቢው መልኩ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚደግፍ መሆኑ ለአተገባበሩ አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የጠቀሱት። በተለይም ለጤና ምርመራ፣ በታካሚዎች መረጃና የህክምና ታሪክ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ለመስጠትና በርቀት ለሚሰሩ የቴሌ ጤና አገልግሎት መጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል። ዓለም አቀፍ ሁኔታን ያገናዘበ የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።   በጤና ሚኒስቴር የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አባስ ሃሰን በበኩላቸው፤ የጤና አገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ ሒደት ባለድርሻ አካላት ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። የጤናውን ዘርፍ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ጋር አጣጥሞ ተግባራዊ ለማድረግ ለተጀመረው ጥረት በዘርፉ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። በኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርፕራይዝ ሶሉዩሽን ቺፍ ኦማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።   በዚህም የጤና ስርዓቱን የሚያዘምኑ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በጤና ተቋማት ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸውን ነው የጠቀሱት። የጤና ተቋማትን በአንድ ቋት በማስተሳሰር መረጃን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በጋራ ትብብር መልማቱን አንስተዋል።
አገልግሎቱ አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረጉ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል
Dec 12, 2025 77
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረጉ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ተገልጋዮች ገለጹ። የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቶፊክ ሻፊ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት አገልግሎቱ አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረጉ ደንበኞች ቀልጣፋና አስተማማኝ መስተንግዶ እያገኙ ነው። አገልግሎቱ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር የቴክኖሎጂ ትስስር መፍጠር በመቻሉና የፋይዳ መታወቂያን በአስገዳጅነት በመጠቀሙ ችግሩን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ስራ ማከናወኑን ገልጸዋል። የመረጃ ቋት ስርዓት በመዘርጋት ሀገራዊ ሰነድ የማረጋገጥና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በማጠናከርና ተደራሽነትን በማስፋት ተገልጋዮች ያለ ወረፋ እንዲስተናገዱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል። በዚህም አገልግሎቱ ባሉት ቅርንጫፎች ለተገልጋዮች ፍላጎት ፈጣን ምላሽ በመስጠት ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋሙ በአጠቃላይ ከወረቀት ወደ ዲጂታላይዜሽን የሚያደርገው ሽግግር በተሳካ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች እንዲሳለጡና የማህበራዊ መስተጋብር ጤናማነት እንዲረጋገጥ አገልግሎቱ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ተገልጋዮች በበኩላቸው በተቋሙ ባገኙት አገልገሎት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል አቶ ከበደ ወልደጊዮርጊስ እንዳሉት ተቋሙ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ እየሰጠ ባለው ቀልጣፋ አገልግሎት በመታገዝ በአጭር ጊዜ ጉዳያቸውን አጠናቀው መመለስ ችለዋል። በተቋሙ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር መሻሻሉንም ነው የተናገሩት። ወይዘሮ ዘሃራ መሀመድ በበኩላቸው ባገኙት አገልግሎት መደሰታቸውን ገልጸው የሚሰጠው አገልግሎት ከነበረው በእጅጉ መሻሻሉን ገልጸዋል። በዚህም በምቹ የአገልግሎት መስጫ ቦታ በአጠረ ጊዜ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘታቸውን ነው የጠቆሙት። የተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ቀልጣፋ በመሆኑ ጥሩ አገልግሎት ማግኘታቸውን የገለጹት ደግሞ አቶ አንዋር አህመድ ናቸው። ቀደም ሲል ከወረፋ ጋር በተያያዘ ይታዩ የነበሩ ችግሮች አሁን ላይ መቀረፋቸውን ተናግረዋል።
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትን በማዘመን ህብረተሰቡ ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ ነው
Dec 12, 2025 72
አሶሳ፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትን በማዘመን ህብረተሰቡ ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሀሚድ ኪኒሶ ተናገሩ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍትህ ቢሮ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባን በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።   በዕለቱ የተገኙት የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሀሚድ ኪኒሶ እንደተናገሩት፤ ዜጎች በሁሉም ዘርፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት እየተሰራ ነው። የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በርካታ ተገልጋዮችን የሚያስተናግድ በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመን ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ሀረሪ፣ ሲዳማና አማራ ክልሎች ዲጂታል የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እያከናወኑ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍትህ ቢሮም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመዋል። አገልግሎቱ ዲጂታል መሆኑ ተዓማኒነት ያለው አሰራርን ከመፍጠር ባለፈ የመረጃ ደህንነትን በመጠበቅ አበርክቶው የጎላ ነው ብለዋል።   የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የክልሉ ፍትህ ትራንስፎርሜሽን ሰብሳቢ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ በበኩላቸው፤ አገልግሎቱ የዜጎችን እንግልት የሚያስቀር እና በተገልጋዩና በመንግስት ተቋማት መካከል ያለውን መተማመን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል። በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ ተቋማት በራሳቸው አቅም አሰራራቸውን በማዘመን የዲጂታል አገልግሎት እንዲስፋፋ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። በክልሉ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎትም በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ በቢሮው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚቀርፍ ነው ያሉት ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ሀሚድ ናቸው።   በቀጣይም የዲጂታል አሰራሩን እስከታችኛው መዋቅር በማውረድ ዘርፉን የማዘመን እና አገልግሎት አሰጣጡን የተሳለጠ ለማድረግ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
የኮደርስ ስልጠና የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን አግዟል
Dec 12, 2025 86
አዶላ ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የኮደርስ ስልጠና የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን እንዳገዛቸው የጉጂ ዞን የመንግስት ሰራተኞች ገለጹ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከወሰዱ የአዶላ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች መካከል ወጣት ጉደታ ገመዳ አንዱ ነው፡፡ ስልጠናው ራስን በቴክኖሎጂ በማብቃት ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎትን ለመስጠት ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ወጣት ገመዳ ተናግሯል።   ከስልጠናው የኮምፒውተር ሳይንስና የሰው ሰራሽ አስተውሎት እውቀትን ማግኘቱ ለስራው ስኬት እንዳገዘው ገልጿል። የወጣት ገመዳን ሀሳብ የሚጋራው ሌላው የከተማው የመንግስት ሰራተኛ ወጣት ደስታ ሀለኬ በበኩሉ ስልጠናው እውቀትና ቴክኖሎጂን በማቀናጀት ተወዳዳሪነቱን እንዳሳደገው ተናግሯል። ስልጠናውን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት መውሰዱን ገልፆ ስልጠናው የዜጎችን ብቃትና ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለተሻለ ስራ የሚያነሳሳ ነው ብሏል፡፡   ይህን እድል በመጠቀም የዘመነ አሰራር ለመተግበር በእውቀትና ክህሎት ለማበልጸግ ሁሉም ሰው ስልጠናውን በመውሰድ ለሀገር ልማት የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ልምዱን አካፍሏል፡፡ የዞኑ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት የሰው ሀብት ልማትና ስምሪት ቡድን መሪ አቶ ቢሉ ሶርሳ፤ የመንግስት ሰራተኞችን እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ 25 ሺህ ሰራተኞች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ መታቀዱን ገልጸዋል።   ስልጠናው የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው በእስካሁኑም 23 ሺህ 456 ሰራተኞች ስልጠናውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡ ስልጠናው የመንግስት ሰራተኞችን ከቴክኖሎጂው ዓለም ጋር በማስተዋወቅ ብቁና ተወዳዳሪ የሚያደርግ አሰራርን እንዲከተሉ ማለሙን አክለዋል፡፡ ይህም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና መንግስታዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
ስፖርት
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
Dec 12, 2025 73
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በአንጎላ ሉዋንዳ እየተካሄደ የሚገኘው አራተኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። የሴቶች ብስክሌት የግል ሰዓት ሙከራ ውድድር ማህደር ደስታ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። ከሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ወጣቶች ጨዋታዎች የተገኘችው ማህደር ያገኘችው ወርቅ በውድድሩ ለኢትዮጵያ ሶስተኛ የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ መመዝገቡን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ በ3000 ሜትር ሴቶች እና በሴቶች ብስክሌት የቡድን የሰዓት ሙከራ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ በሁለቱም ጾታዎች በሰባት የስፖርት አይነቶች 70 ስፖርተኞችን እያሳተፈች ይገኛል።   አትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ ካራቴ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ ውሃ ዋና እና ክብደት ማንሳት ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የስፖርት አይነቶች ናቸው። በአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ስፖርተኞች በቅርቡ በተካሄደው ሁለተኛው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ ባስመዘገቡት ውጤት የተመረጡ መሆናቸው ይታወቃል። በውድድሩ ላይ 54 ሀገራት በ33 የስፖርት አይነቶች እየተሳተፉ ነው። አህጉራዊው የስፖርት ሁነት እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች በ2019 ዓ.ም በሴኔጋል ዳካር ለሚካሄደው አራተኛው የወጣቶች የክረምት ኦሊምፒክ እንደ ማጣሪያ እና መዘጋጃ የሚያገለገል ውድድር ነው።
አካባቢ ጥበቃ
ኮፕ-32 ጉባኤን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ባለሃብቶች ሚናቸውን መወጣት አለባቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Dec 12, 2025 101
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት (ኮፕ-32) ጉባኤን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ባለሃብቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ /ኮፕ-32/ በተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአራዳ ፓርክ ተካሂዷል።   በመርሀ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን፣ የመዲናዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለብቶች እንዲሁም አልሚዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት ነው። ይህም ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር፣ በከተሞች ልማትና ውበት የተመዘገቡ ውጤቶች ዓለም አቀፉን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ብሎም አዲስ አበባ የዓለም የስበት ማዕከል መሆናቸውን በመጥቀስ፣ መዲናዋ ባለፈው ዓመት በርካታ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏን ገልጸዋል። ኮፕ-32 የዓለማችን ትልቁ የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ነው የተናገሩት። ጉባኤው ለኢትዮጵያውያን ብዙ ዕድል ይዞ ይመጣል ያሉት ከንቲባዋ፤ ለዚህ ደግሞ መንግሥት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ጉባኤው ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማዘጋጀት ዕድል እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየትና የስራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሀብቶች አልሚዎችና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ጉባኤውን በስኬት ለማካሄድ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስረድተዋል። ጉባኤውን በብቃት በማስተናገድ ለኢትዮጵያ ለውጥ መሰረት መጣል አለብን ያሉት ከንቲባዋ፤ ዛሬ የስራ ክፍፍል በማድረግና ዝግጅት በመጀመር ግባችንን ማሳካት አለብን ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ገልጸው፤ ውጤቱም በጋራ ትብብር የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው ስኬቶች ለቀጣይ ስራዎቻችን መስፈንጠሪያ እንደሚሆኑ በመጥቀስ፤ ኮፕ-32 እንዲሁ የተገኘ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤ አዘጋጅነትን ለማግኘት ዓለም አቀፋዊ ውድድር ማድረግ ነበረባት ያሉት ኃላፊዋ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌሎችም አረንጓዴ ልማት ስራዎች በተገኙ ውጤቶች መመረጧን በመግለጽ። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ105 በላይ ሁነቶችን ማዘጋጀቷን ገልጸው፤ እነዚህ ስኬቶች የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅትን በድል እንደምንወጣ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።   በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ባለሃብቶችና አልሚዎች በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ኮፕ-32 ለማስተናገድ መመረጧ ትልቅ ዕድል ይዞ ይመጣል ብለዋል፡፡ በጉባኤው የሚሳተፉ አካላት የውጭ ምንዛሪ ይዘው እንደሚመጡ በማንሳት፤ በቆይታቸው የአገልግሎት ዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ገንቢ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡ ኮፕ-32 የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያ ስኬት ማሳያ እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ጉባኤውን በስኬት ማስተናገድ እንድትችል ከመንግስት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡ በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛ ጉባኤ ላይ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን 32ኛ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (COP-32) ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ነው
Dec 12, 2025 77
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት(ኮፕ-32) ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ /ኮፕ-32/ በተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአራዳ ፓርክ ተካሂዷል።   በመርሀ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን፣ የመዲናዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለሃብቶች እንዲሁም አልሚዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት ነው። ይህም ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር፣ በከተሞች ልማትና ውበት የተመዘገቡ ውጤቶች ዓለም አቀፉን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ብሎም አዲስ አበባ የዓለም የስበት ማዕከል መሆናቸውን በመጥቀስ፣ መዲናዋ ባለፈው ዓመት በርካታ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏን ገልጸዋል። ኮፕ-32 የዓለማችን ትልቁ የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ነው የተናገሩት።   ጉባኤው ለኢትዮጵያውያን ብዙ ዕድል ይዞ ይመጣል ያሉት ከንቲባዋ፤ ለዚህ ደግሞ መንግሥት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ጉባኤው ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማዘጋጀት ዕድል እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየትና የስራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሀብቶች አልሚዎችና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ጉባኤውን በስኬት ለማካሄድ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስረድተዋል። ጉባኤውን በብቃት በማስተናገድ ለኢትዮጵያ ለውጥ መሰረት መጣል አለብን ያሉት ከንቲባዋ፤ ዛሬ የስራ ክፍፍል በማድረግና ዝግጅት በመጀመር ግባችንን ማሳካት አለብን ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ገልጸው፤ ውጤቱም በጋራ ትብብር የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው ስኬቶች ለቀጣይ ስራዎቻችን መስፈንጠሪያ እንደሚሆኑ በመጥቀስ፤ ኮፕ-32 እንዲሁ የተገኘ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤ አዘጋጅነትን ለማግኘት ዓለም አቀፋዊ ውድድር ማድረግ ነበረባት ያሉት ኃላፊዋ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌሎችም አረንጓዴ ልማት ስራዎች በተገኙ ውጤቶች መመረጧን በመግለጽ። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ105 በላይ ሁነቶችን ማዘጋጀቷን ገልጸው፤ እነዚህ ስኬቶች የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅትን በድል እንደምንወጣ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛው ጉባኤ ላይ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን 32ኛ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ(COP-32) ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወቃል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አንጻራዊ ጥንካሬ ይኖረዋል -የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Dec 12, 2025 63
አዲስ አበባ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ ደጋማ የአገሪቱ ክፍሎች የሌሌቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው መግለጫ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ እንደሚስተዋል አስታውቋል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት በመነሳት ወደ አገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል። በአንዳንድ አካባቢዎች ቅዝቃዜው ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየሽ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ አስታውቋል። በዚህም በሰሜን ፣ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ ደጋማ የአገሪቱ ክፍሎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖረው ገልጿል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ውርጭ የማስከተል ጥንካሬ እንደሚኖረውም ጠቁሟል። በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ጥቂት ቦታዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ገልጿል። በዚሁ ወቅት አብዛኛው ተፋሰሶች ደረቅ የአየር ሁኔታ እንደሚስተዋል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።  
በክልሉ በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ እየተዘጋጀ ነው
Dec 12, 2025 80
ባህርዳር ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑ ተመላከተ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ እንደሀገር በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተራቁቱ መሬትን መልሶ በደን በመሸፈን እና የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውሀ ሀብትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እያተመዘገበ ይገኛል። ባለፉት አመታት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በትኩረት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የክልሉን የደን ሽፋን ወደ 18 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለም የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል። በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በተለያየ ምክንያት የተራቆተውን መሬት በደን መልሶ ለማልበስና የአየር ንብረት ሚዛኑን ለማስተካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል።   ተግባሩን ለማስቀጠልም በመጪው ክረምት ለሚተከሉ‎ ችግኞች በመንግስት፣ በተቋማት፣ በማህበራትና በግል ተቋማት እንዲሁም ከ75 ሺህ በሚበልጡ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞችን ለማዘጋጀት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል። ‎እስካሁንም በ65 ሺህ 694 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፣ ሀገር በቀልና የውጭ ዝርያ ችግኞችን ለማዘጋጀት የችግኝ መደቦችን በማዘጋጀት ዘር ማፍሰስ መቻሉን ገልጸዋል። ‎ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተዘጋጁ ካሉት ችግኞችም 1 ነጥብ 7 ቢሊዮኑ በተራቆቱ፣ ለደን ተከላ በሚለዩና በበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በሚከናወንባቸው ተፋሰሶች እንደሚተከሉም አስረድተዋል። ‎በክልሉ ባለፈው የክረምት ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከለው ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መካከል በመጀመሪያ ዙር በተካሄደ ቆጠራ 86 ነጥብ 3 በመቶው ፀድቆ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል
Dec 4, 2025 472
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተከናውኗል።   በዕውቅና መርሃ ገብሩ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ ሚኒስትሮችና ተወካዮች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሽልማቱ ለአፍሪካ ጋዜጠኝነት፣ ብሮድካስት ሚዲያ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ዘገባዎች እውቅና የሰጠ ነው። በአፍሪካ ሚዲያ ምህዳርን በመቅረጽ ሚናቸውን የተወጡ ጋዜጠኞች ተሸልመዋል። ምርጥ የዜና ዘገባ፣ ምርጥ ቃለ መጠይቅ፣ ምርጥ ዶክመንተሪ፣ ምርጥ ወቅታዊ ፕሮግራም፣ ምርጥ አፍሪካ ተኮር የመዝናኛ ፕሮግራምና ምርጥ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እና ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው።   አፍሪካ ተኮር ምርጥ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ምርጥ የወቅታዊ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ እና ምርጥ አጭር የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል የማህበራዊ ሚዲያ ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው። ሁሉም እጩዎች 2000 ዶላር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በእያንዳንዱ ዘርፍ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች የስድስት ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝተዋል። የምርጦች ምርጥ የይዘት ፈጣሪዎች አሸናፊም "The Golden Alkebulan" የተሰኘ ልዩ በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። በሽልማቱ ላይ ከ40 ሀገራት በላይ የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ከ800 በላይ ስራዎችን ማቅረባቸውን ተገልጿል። የአፍሪካ ሕብረት ብሮድካስቲንግ፣ የፓትሪስ ሉሙምባ ፋውንዴሽን፣ የክዋሜ ንክሩማህ ፋውንዴሽን፣ የምዋሊሙ ኒዬሬሬ ፋውንዴሽን፣ የኬኔት ካውንዳ ሌጋሲ ፋውንዴሽን፣ የሲሱሉ ፋውንዴሽን ለማኅበራዊ ፍትህ፣ የፒኤልኦ ሉሙምባ ፋውንዴሽንና የሩስያው አር ቲ ሚዲያ የሽልማቱ አጋር ናቸው።
ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው - የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች
Dec 1, 2025 430
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ሲሉየምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ገለጹ። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን ትርክት በመቀየር ትልቅ ሚና የሚወጣ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ይታወቃል። የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በሴት ጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ ከሆኑት መካከል ዩጋንዳዊቷ ጋዜጠኛ አይባሬ ሲንደሬላ ኢትዮጵያ በዜጎቿ አስተዋጽኦ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቃለች። በበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሚከፍሉት ታክስ ተጨባጭ ውጤቶችን እምብዛም ሲያዩ አይስተዋልም ያለችው ጋዜጠኛዋ ኢትዮጵያ በግልጽነትና በጠንካራ ራዕይ የህዝብን ሀብቶች አሻጋሪ ብሄራዊ ፕሮጀክት መቀየሯን ተናግራለች። የአፍሪካ መሪዎች ከሕዳሴ ግድብ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ሊወስዱ ይገባል ብላለች። የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አዘጋጅ አሻ ሃሚሲ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው ገልጻለች። ሕዳሴ ግድብ ዜጎች ለሀገራቸው መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው ያለችው አሻ ይህም በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ መተማመንና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ላይ መስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላከት ነው ብላለች። ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ እንደሆነም ተናግራለች። በኢጋድ ሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ካሸነፉት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ሱዳናዊው የፊልም ባለሙያ እና ተራኪ ጋብርኤል ጋትሉዋክ ዋል ኬት በበኩሉ ህዳሴ ግድብ አፍሪካ ያላትን አቅም በተግባር ያሳየ ነው ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ካሳካች ሌሎች ሀገራትም ይህን ፈለግ ተከትለው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይችላሉ ብሏል። አፍሪካውያን ሀገራቸውን በራሳቸው መገንባት እንደሚችሉ ማመን አለባቸው ያለው ኬት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ሌሎች እንዲወስኑላቸው መፍቀድ የለባቸውም ሲልም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን እና በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት አንስተዋል። ሕዳሴ ግድ የአፍሪካ የስኬት ተምሳሌት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው ከግድቡ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ይህም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ራዕይ የሆነውን የበለጸገች እና የተሳሰረች አፍሪካን የመፍጠር ራዕይን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። ግድቡ የአፍሪካን ትርክት የመቀየር ትልቅ ኃይል ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል
Nov 21, 2025 780
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ገለጸ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችና የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች ላይ የዌብናር ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ወሳኔ ሰጪዎች፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ ክፍል ኃላፊ ኦዬባንኬ አበጂሪን፤ የምንፈልጋትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት የ2030 ዘላቂ የልማት አጀንዳና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አፈፃጸም ሂደትን የሚከታተል የሪፖርት ሥርዓት መኖሩንም ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት ክትትል ሥርዓትም የአህጉሪቷን ዘላቂና ቁልፍ የልማት ማዕቀፎች አፈፃጸም የሚገመገምበትን መድረክ በማመቻቸት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። እ.ኤ.አ የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት መድረክም የአህጉሪቷ ልማት በሳይንስና ማስረጃ የተመሰረቱ የመፍትሔ አፈፃጸሞችን ያመላከተ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሪፖርቱም የአፍሪካ ዕድገት በጤና፣ በሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በውቅያኖስ ጥበቃና ዓለም አቀፍ ሽርክና ጋር በአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ የ2030 ዘላቂ የልማት ግብና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ወሳኝ አካል መሆኑን አስረድተዋል። የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የትብብር ሥርዓትን በማጠናከር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርትም ወሳኝ የአፈፃጸም ግኝቶችን በማረም የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን በሚገባ ለመተግበር አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። በመድረኩም የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦችና አጀንዳዎች የአፈፃጸም ስኬት ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ የሚችል ተግባቦት መፈጠሩን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካትም አዲስ ዓለም የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። መድረኩም ብሔራዊና ቀጣናዊ የልማት ስኬት አፈፃጸም የአሰራር ስርዓቶችን በመፈተሽ ዕድሎችን በማስፋት የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት አጀንዳዎ ማሳካት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነት አድማሳቸውን ለማስፋት እንደሚሰሩ ገለጹ
Nov 20, 2025 670
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ በትምህርት እና ዲጂታል ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በአፍሪካ ህብረት ዋና ኮሚሽን ዛሬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህብረቱን የጎበኙ የመጀመሪያ ማሌዥያ መሪ ሆነዋል።   የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። ሊቀመንበሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የአፍሪካ እና ማሌዥያ ትብበር ውስጥ ታሪካዊና የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ ትብብር እንደሚያጠናክር አመልክተዋል። እ.አ.አ በ2024 የአፍሪካ እና ማሌዥያ የንግድ ልውወጥ መጠን 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱን ጠቅሰው፤ ይህም በዘርፉ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ትምህርት የሁለቱ ወገኖች አጋርነት ዋነኛ ምሰሶ መሆኑንና ከእ.አ.አ 2012 አንስቶ ከ40 ሺህ በላይ አፍሪካውያን በማሌዥያ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን ገልጸዋል።   ማሌዥያ ቀጣይ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ሊቀ መንበር መሆኗ እና ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት ኢንቨስትመንትን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ነው ያሉት። ሁለቱ ወገኖች በዲጂታል ኢኖቬሽን፣ በግብርና ማቀነባበሪያ ልማት፣ በደቡብ ደቡብ ንግድ እና ትምህርት ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ገልጸዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ ዓመታዊ ምክክር እ.አ.አ በ2026 እንዲካሄድ ሀሳብ አቅርበዋል። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በበኩላቸው፤ ማሌዥያ እና አፍሪካ ንግድ፣ ግብርና እና ትምህርትን ጨምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ትብብር እያደገ መምጣታቸውን አመልክተዋል።   ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ በማስፋት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በውይይቱ ላይ የማሌዥያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነታቸውን አድማስ ለማስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል::
ሐተታዎች
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 123
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል።   ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ።   ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡   የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።  
ለቀጣናዊ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ልህቀት እውቅና የሚሰጠው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት
Nov 28, 2025 631
የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተጀመረው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አማካኝነት ነው። ሽልማቱ የኢጋድ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና ተቋማዊ አቅምን የማጠናከር ጥረቶች አካል ነው። በኢጋድ ቀጣና በጋዜጠኝነት የላቀ ስራ ላከናወኑ የሚዲያ ባለሙያዎች በሽልማቱ እውቅና ይሳጣቸዋል። ሽልማቱ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ሌሎችም ተጓዳኝ መድረኮችን የሚሸፍን ነው። የሚዲያ ስራው በቀጣናው በተለይም የድርቅ አይበገሬነት፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ያሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል። ዓመታዊው የኢጋድ ሽልማት የቀጣናዊ ተቋሙ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ በግላቸው የሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና የፎቶ ጋዜጠኞች ጨምሮ አጠቃላይ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው። በተጨማሪም የቀጣናውን ጉዳይ የሚሸፍኑ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችም ይሳተፉበታል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ስራቸውን በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ እና በኢጋድ አባል ሀገራት በሚገኙ ቋንቋዎች ያቀርባሉ። ከተለያዩ ሙያዎች የተወጣጡ የውሳኔ ሰጪ ወይም ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሙ ስራዎቹን በመመዘን አሸናፊዎችን ይለያል።   የመጀመሪያው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2023 በጅቡቲ ነበር። “የድርቅ ተጽእኖዎችን መቋቋም የሚያስችል ትብብር መፍጠር” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። መሪ ሀሳቡ በድርቅ፣ አይበገሬ አቅም መገንባት፣ የውሃ አስተዳደር እና ቀጣናዊ ትብብር ያተኮረ ነው።   ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመንት፣ ጦማር (ብሎግ) እና የፎቶ ጋዜጠኝነት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። በመጀመሪያው ሽልማት ላይ ከቀጣናው 105 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን 14 ባለሙያዎች በዘርፎቹ ተመርጠው ተሸልመዋል። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ተቋሙ ሚዲያን ለግንዛቤ መፍጠር እና ቀጣናዊ ትብብር እንደ መሳሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ በወቅቱ ገልጾ ነበር። በድርቅ እና በምግብ ዋስትና ላይ ያሉ የጋራ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚዲያ ሚና ወሳኝ እንደሆነም አመልክቷል። ሁለተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2024 በኬንያ ናይሮቢ ነው። “የተስፋ ትርክቶች፤ የቀጣናውን መጻኢ ጊዜ ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ሁሉን አቃፊ ማድረግ” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሽልማቱ በሰላም፣ ደህንነት፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ መጻኢ ጊዜን መፍጠር፣ ቀጣናዊ ትብብር እና መረጋጋት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የእድሜ ዘመን ተሻላሚ ከሽልማት ዘርፎቹ ውስጥ ናቸው። ለ2024ቱ ሽልማት 318 የሚዲያ ባለሙያዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን 18 የሚዲያ ባለሙያዎች በዘርፎቹ ሽልማት አግኝተዋል። ሁለተኛው ሽልማት ከመጀመሪያው በዘርፎች እና በተሳታፊዎች ብዛት መሻሻል የታየበት ነበር። ይህም ሚዲያ በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት እና ቀጣናዊ ትስስር ላይ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ ነው። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መጥቷል። ሽልማቱ ነገ ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን ነው። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያና የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቋል። የዚህ ዓመት ሽልማት በአፍሪካ ቀንድ ውጤታማ የአየር ንብረት ትርክትን ለቀረጹ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። የሁለት ቀን ሁነቱ የአየር ንብረት ጠንካራ ዘገባዎች እና ሀሳቦች የሚቀርቡበት እንዲሁም ቀጣናዊ ትብብር ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች የሚከናወን ነው። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶች ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚዲያ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ሙያተኞች እንደሚሳተፉም ገልጿል። የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቁ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዘገባዎች እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ብዝሃ ድምጾች እንዲሰሙ በማድረግ፣ ለዴሞክራሲ እሴቶች መጎልበት እና ዘላቂ ልማት የበኩሉን ሚና ይወጣል።  
 የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አዘጋጅነት
Nov 14, 2025 820
ለረጅም አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ምሰሶ ሆና ቆማለች። በሀገራት መካከል የግንኙነት ድልድል እና የአንድነት መልዕክተኛ መሆን ችለላች። ከምስረታው አንስቶ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት። የአፍሪካ መዲና በመባል የምትጠራው አዲስ አበባ በርካታ ድርድሮች፣ የሰላም ውይይቶች እና አህጉራዊ ውሳኔዎች የተላለፈባቸው ሁነቶች ተስተናግደውባታል። ውሳኔዎቹ የአፍሪካ ቀጣና ፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ናቸው። የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና ከዲፕሎማሲውም የተሻገረ ነው። ሀገሪቷ የገባችውን ቃል ከተግባር ጋር በማጣጣም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚለኩ ውጤቶችን እያስመዘገብች ትገኛለች። የተራቆቱ መሬቶች ወደ ነባር ይዞታቸው እንዲመለሱ በማድረግ እና የታዳሽ ኃይል አማራጮቿን በማስፋት ለአረንጓዴ ልማት እና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ ሚሊዮኖችን ከዳር እስከ ዳር በማነቃነቅ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ከችግር ተናገሪነት ወደ ተጨባጭ መፍትሄ አመንጪነት ሽግግር በማድረግ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ምሳሌ የሚሆን ተግባር አከናውናለች። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም ደረጃ ያላትን ተአማኒነት እና ተቀባይነት እንዲያድግ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በከባቢ አየር ጥበቃ ቁርጠኝነት እና አቅምን በማጣመር ለውጥ አምጥታለች። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያገኘችው እምነት እና የመሪነት ሚና ውጤት የሚያሳይ ተጨማሪ ሃላፊነት ከሰሞኑ ከብራዚል የደን ከተማ ቤለም ተሰምቷል። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) በቤለም እየተካሄደ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በአንገብጋቢ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ ይገኛል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የገቡትን ቃል በተግባር ለመቀየር ቁርጠኝነት ባነሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መፈጸሟን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላት ገልጸው የዳበረ የትራንስፖርት አገልግሎት ከብዙ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫነት ጋር ሲደመር የዝግጁነት አቅሟን በላቀ ሁኔታ እንደሚያሳድገው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ልምዱም አቅሙም እንዳላት ገልጸው፣ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ናይጄሪያም ጉባኤውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባ ነበር። የኢትዮጵያ የኮፕ 32 የማስተናገድ ፍላጎት ከአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል። የወቅቱ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን ሊቀመንበር የሆነችው ታንዛንያ የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጻለች። የአፍሪካውያን ውሳኔ ከቃል ባሻገር ኢትዮጵያ የአህጉሪቷን የአየር ንብረት የቅድሚያ ትኩረቶች የማራመድ እና የመወከል አቅም አላት ብለው ይሁንታ የሰጡበት ነው። ይህ ጠንካራ እምነት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሁሉን አፍሪካውያን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ እና አህጉሪቷን ያማከለ ውሳኔዎች በዓለም መድረክ እንዲተላለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግም ነው። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስናግድ ድጋፍ በመስጠታቸው አመስግነው፤ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ አበክራ እንደምትሰራ ተናግረዋል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ መሰል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት ማስተናገድ እንደምትችል የሚያመላክት ነው ብለዋል። አዲስ አበባ እንግዶቿን በሚመጥን ደረጃ ጉባዔውን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደሩ፥ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ሌሎች ሀገራትም ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የኮፕ 32ን ለማስተናገድ መመረጧ በድንገት የመጣ ጉዳይ አይደለም። በተግባር የተረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የመሪነት ሚና፣ አረንጓዴ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያከናወነች ያለቻቸው ስራዎች እና የፖለቲካ ቁርጠኝነቷ፣ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ድምጽ እና ምልክት መሆኗ ከቃል ባለፈ በተጨበጠ ስራ መታየቱ፣ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ ውጤታማነቷ እና የዲፕሎማሲ ተሰሚነቷ ድምር ውጤቶች እንጂ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስተናግድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠን ክብር ይሰማናል ብለዋል። አፍሪካ በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በብራዚል በአንድ ድምጽ ተናግራለች፤ ዓለምም አዳምጧል ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2027 በአዲስ አበባ COP 32ን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለደገፉ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ምሥጋና አቅርበዋል። በሰው ልጆች ኑሮ በጣም አንገብጋቢ ከሆኑት ተግዳሮቶች መካከል አንዱን ለመቅረፍ እንዲቻል የጋራ ጥረቶችን ለመምራት ዕድሉን ስላገኘንም አመሥጋኞች ነን ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ይህ ዕውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ላይ ያላትን ቁርጠኛ ርምጃ፣ አመራር ብሎም ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ የዳበረ ዐቅም ያሳያል ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 መድረክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ ርምጃን የሚያበረታታ ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማዘጋጀቷ በዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ መድረኮች ኢትዮጵያ ያላትን የአየር ንብረት የመሪነት ሚና የበለጠ ያሳድጋል። የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ የሚያስፈልጋትን ፋይናንስ ለማግኘት እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚን ይፈጥርላታል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የጉባኤው ተሳታፊዎች የቱሪዝም መስህቧቿንና መዳረሻዎቿን ሲጎበኙ ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢ ያድጋል ይህም ኢኮኖሚውን በመደገፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ተጽእኖ ፈጣሪን ጉባኤው በማስተናገድ በኩል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው ሲሆን ዘላቂ የሆነ የከባቢ አየር ትብብርን ለመፍጠር ያስችላል። ለኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማስተናገድ ከክብር ባሻገር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሰው ለሚኖርባት ምድር ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የምታሳይበት ይሆናል። ኢትዮጵያ ጠንካራ የከባቢ አየር ጥበቃ ኢኒሼቲቮች፣ የማይበገር ዲፕሎማሲ እና የነገ አረንጓዴ እድገት ህልሟ ከጉባኤው ጋር ተዳምረው የተፈጥሮ ጠበቃነቷን እና የዓለም ትብብር ተምሳሌትና መሪነቷን የበለጠ ያሳድጉታል። ኢትዮጵያ እና ህዝቧቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአየር ንብረት የረጅም ጊዜ ፈተናዎች እንዲፈቱ ከአፍሪካ ብሎም ከመላው ዓለም ጋር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እና ቁርጠኛ ናት።
" መሬት እና ፍትህ" - የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የእድገት ጉዞ
Nov 11, 2025 849
መሬት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። መሬት ከአፍሪካውያን የአኗኗር ዘይቤ፣ ማንነት፣ ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብር ጋር የተቆራኘ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከቅኝ ግዛት ዘመን በፊት የአፍሪካ በርካታ ማህበረሰቦች መሬት በልማዳዊ እና ባህላዊ ስርዓት ያስተዳድሩ ነበር። የቤተሰብ ጎሳዎች ወይም ማህበረሰቦች መሬት የመጠቀም፣ የማስተዳደር እና ባህላዊ መንገዶች በሰጣቸው መብት ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። በእንደዚህ አይነት ስርዓት ውስጥ መሬት ከሀብት ባለፈ ከማህበራዊ ግንኙነቶች፣ መንፈሳዊ መስተጋብሮች እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት ጋር ትስስር አለው።   በቅኝ ግዛት ዘመን የአውሮፓ ኃይሎች በስምምነቶች፣ በአዋጆች እና ኃይል በመጠቀም መሬት የቁጥጥር፣ የብዝበዛ እና ሀብትን የመንጠቂያ መሳሪያ አድርገውታል። መሬት ፖሊሲ ኃይልን ማጠናከሪያ እና የኢኮኖሚ ብዝበዛ መንገድ ሆኗል። አፍሪካውያን በልማዳዊ እና ባህላዊ መንገዶች የነበራቸውን የመሬት መብቶች በመንጠቅ ከአፍሪካ ውጪ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የሰፈራ ፕሮግራም ማካሄጃ እንዲሆኑ በር ከፍቷል። በዚህም ከፍተኛ የሆነ የአፍሪካ ሀብት ሲበዘበዝ ቆይቷል። ሀገር በቀል ማህበረሰቦች ከመሬታቸው የመፈናቀል እና የመገለል ሰለባ ሆነዋል። በቅኝ ገዢዎች የወጡ የመሬት ፖሊሲዎች፣ የመሬት ምዝገባ እና የመሬት አስተዳደር ስርዓት የአፍሪካ መሬት ተጠቃሚዎችን መብት የነፈገ ነበር። የቅኝ ግዛት የቀረጸው የመሬት አስተዳደር ስርዓት አፍሪካውያንን ህጋዊ የመሬት ባለቤትነትን ያሳጣ ነው።   የአፍሪካ ሀገራት ከነጻነታቸው በኋላ እኩልነት ያልተረጋገጠባቸውን የመሬት መብቶች እና ስርዓቶች ወርሰዋል። ሀገራት የመሬት ፖሊሲዎቹን አሁን ያሉ የልማት ግቦችን፣ የፍትህ ፍላጎቶች እና ወቅታዊ የአስተዳደር ማዕቀፎች ባማከለ ሁኔታ የመቀየር ስራ በማከናወን ላይ ናቸው። በቅኝ ግዛት ዘመን የመሬት መብታቸውን ላጡ ዜጎች በተለይም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመለሰላቸው ይገኛል። ይሁንና የቅኝ ግዛት የመሬት ቅድሚያ መጥፎ፣ በሀገራት ብሄራዊ ህግ ውስጥ ያሉ የተደባለቁ የህግ ማዕቀፎች (ለምሳሌ ልማዳዊ ህጎች ከመደበኛ ህጎች ጋር መደባለቅ) እና የተቋማት የአስተዳደር ስርዓት አለመናከር በአፍሪካ ፍትሃዊ እና እኩልነት የመሬት ስርዓት የማስፈን ጉዞ ላይ ጋሬጣ ሆኗል። ዛሬ ላይ አፍሪካ አጀንዳ 2063 እና ዘላቂ ልማት ግቦች እየተገበረች ትገኛለች። የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች አንኳር ምሰሶ ተደርገው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሬት ነው። እኩል የመሬት መብት የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ለከባቢ አየር ጥበቃ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ የአጀንዳ 2063 ሰነድ ያስረዳል። የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በመተባበር በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ላይ ማዕቀፎች እና የህግ አሰራሮችን በመቅረጽ እያስተዋወቁ ይገኛሉ። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የመሬት ህጎችን የተሰናነሰኑ እንዲሆኑና የተቋማት አቅምን እንዲያጠናክሩ ጥሪ በማቅረብ ላይ ነው።   “የመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ለዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ ከህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኮንፍረንሱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በጋራ በመተባበር ነው። ከአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ እና የአካባቢ ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ እና ለነባራዊ እውነታዎች ምላሽ የሚሰጡ የመሬት ፖሊሲ ምርጥ ተሞክሮዎች በኮንፍረንሱ ላይ እየቀረቡ ይገኛል። ህዳር 1 በነበረው የጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸኃፊ ክላቨር ጋቴቴ በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ስብሰባ በወሳኝ ወቅት የተዘጋጀ ነው ብለዋል።   አፍሪካውያን ያላቸውን ሰፊ የመሬት ሀብት በቅኝ ግዛት አሰራሮች ሳቢያ በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው በአፍሪካ መሬት ዛሬም የግጭትና የኢ-ፍትሐዊነት መገለጫ ሆኗል ብለዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር በሴቶች፣ በወጣቶችና በዝቅተኛ አርሶ አደሮች ዘንድ ኢ-ፍትሐዊነትን በማንገስ ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት መፍጠሩን ገልጸዋል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ስብሰባ ከአፍሪካ ሕብረት 2025 "የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን" መሪ ሀሳብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አንስተው፤ ዓላማው አፍሪካውያን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል። የአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የካሳ ጥያቄ ያለፈውን ማስመለስ ሳይሆን አሁን ባለው የዓለም የፋይናንስ ስርዓት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪካ 65 በመቶ ያልታረሰ መሬት፣ ከዓለም ኢንዱስትሪ ሁለት በመቶ ብቻ ድርሻ ያላት፣ ለአየር ንብረት ለውጭ ተፅዕኖ ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች የሆነ አህጉር መሆኗን አንስተዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን በማዘመን ፍትሐዊነትን ማስፈን ጊዜው አሁን ነው ያሉት ዋና ጸኃፊው፣ ሴቶችን ወጣቶችና ዝቅተኛ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዜጎችና ዳያስፖራ ዳይሬክተር አምር አልጆዋሊ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ የአህጉሪቱን መፃኢ ጊዜ ለመቀየር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።   በአፍሪካና ዘርዓ አፍሪካውያን ላይ የደረሰው በደል ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት ገልጸው፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ለሕብረቱ መሪ ሀሳብ ትግበራ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የመሬት አስተዳደር የፍትሐዊነት ምልክት መሆኑን በማንሳት፤ የመሬት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መስፈን አለበት ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 በማሳካት አካታች ብልፅግናና ሰላምን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል። ሕብረቱ በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ግልፅ አሰራር እንዲሰፍን ለአባል ሀገራት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል። ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ውጤታማ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መገንባት፣ ተቋማዊ አቅምን መፍጠር እና የቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የቅኝ ግዛት አሻራዎች እና ወቅታዊ የኢ-ፍትሃዊነት ጉዳዮች በመሬት ባለቤትነት እና አስተዳደር ያሳደሯቸውን ተጽእኖዎች ለመፍታት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ይገልጻሉ። በመሬት ፖሊሲ ቀረጻ፣ ትግበራ እና ቁጥጥር አቅምን መገንባት፣ የእውቀት ሽግግርን ማሳደግ እና የፖሊሲ ቁርጠኝነትን ወደ ሚጨበጥ የተግባር ምላሽ የመቀየር ጉዳይም አጽንዖት የሚሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ህብረቱ ገልጿል።   በአህጉራዊ ኮንፍረንሱ ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ የህብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ትውልደ አፍሪካውያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሁነት ነው። የመሬት ፖሊሲ ጉባኤው አፍሪካውያን ፍትሃዊ እና ዘላቂ የመሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩበት የሚገኝ መድረክ ነው። ጉባኤው አፍሪካውያን ከባለፈው ታሪክ በመማር ፖሊሲ፣ ጥናት እና የማህበረሰብ ድምጾችን በማቀናጀት ረገድ ያለው ፋይዳ ወሳኝ ነው። ጉባኤው የመሬት ፍትህን የማስፈን፣ አይበገሬነትን የመገንባት እና ለሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ብልጽግና የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ በመደገፍ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
ትንታኔዎች
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ 
Dec 8, 2025 302
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።  
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 2896
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ  7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2835
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር  በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3734
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 2197
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1422
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7236
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5726
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 58080
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 52768
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 33443
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 30971
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 26784
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 25539
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 25109
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 25081
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 58080
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 52768
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 33443
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 30971
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ
Dec 3, 2025 638
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ (በቀደሰ ተክሌ) -ከሚዛን ቅርንጫፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የቤንች ምድር የሰጡትን የሚያበቅል ክረምት ከበጋ የማይጠወልግ ልምላሜን የታደለ ክልል ነው። በቤንች ሸኮ ዞን ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ደን የሚመስልና በመኖሪያ መንደሮች የሚታየው አብዛኛው አረንጓዴ ስፍራ ለምግብነት የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎች፣ ቅጠሎችና ስሮችን የያዘ ነው። የቤንቾች ቤት ዙሪያው በአረንጓዴ ተፈጥሮ ያጌጠ ነው። የቤታቸው ሞገስ፤ የምግብ ዋስትናቸውም ጭምር ነው። ከዚህ ከፍ ሲል ደግሞ ቤንቾች ነፋሻማ አየር እየማጉ የመኖር ልምድን ያጎናጸፋቸው ይኸው አፈር ቆፍረው ዘር ተክለው ያበቀሉትና የተንከባከቡት አረንጓዴ ሀብት ነው። ከአንድ አርሶ አደር ማሳ እንሰት፣ ሙዝ፣ ጎደሬ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ማየት የተለመደ ነው።   እግር ጥሎት ወደ ቀዬያቸው ያመራ እንግዳ ከፍራፍሬዎቹ የደረሰ ካለ ተቆርጦ ይሰጠዋል። በተጨማሪም ከብቶች፣ በጎችና ዶሮዎች የገቢ ምንጮቻቸው ናቸው። ወደ ቤታቸው ዘልቆ የገባ ሰው "ኪዥ" የተሰኘና የቤንች እናቶች ከወተት የሚያዘጋጁትን ''ጎደሬ'' ተብሎ ከሚጠራ የስራ ስር ምግብ ጋር ያጣጥማል። ቤንቾች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን ያለማሉ። ማር፣ ቡና፣ ኮረሪማ እና ሌሎች የተፈጥሮ ቅመማ ቅመሞችም ቤንቾች ከገበያ ገዝተው የሚያመጡት ሳይሆን ከማሳቸው የሚያፈሩት ነው። የተቀናጀ እርሻን ባህል ያደረጉት ብርቱ የቤንች አርሶ አደሮች ወደ ገበያ አውጥተው የሚሸጡት እንጂ የሚገዙት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የፋብሪካ ውጤቶችን ለመግዛትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግም ከጓዳቸው ሞልቶ የተረፈውን ወደ ገበያ አውጥተው በመሸጥ ገበያን ያረጋጋሉ። በጠንካራ የእርሻ ባህላቸውም ምክንያት ልጆቻቸው የበሰለ ምግብን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎችንም ከጓሮና ከጫካ ቆርጠው ስለሚመገቡ ረሀብን አያውቁም።   የቤንቾች ቤት ዙሪያ ውብና ጽዱ ነው። ለዚህ ደግሞ ሴቶቹ የቤታቸውን ግድግዳ በተፈጥሮ ቀለም ከማስዋብ ጀምሮ ይጠበቡበታል። በቤንቾች ዘንድ የአንድ አርሶ አደር ጉብዝና የሚለካው በቤቱ ነው። ይህም የቤቱ ዙሪያ ያለው ውበትና የቤቱ ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን ገላጣ መሆን አለመሆኑም ጭምር ከግምት ውስጥ ይገባል። አባዎራው በማሳው ላይ የሰብል ስራውን ያከናውናል። ልጆችና እማውራዋ ደግሞ ይኮተኩታሉ ያርማሉ። ከዚህም በተጨማሪ የቤንች እናት ጎደሬና ሌሎች የጓሮ አትክልቶችን የማልማት ኃላፊነት አለባት። የቤታቸው ዙሪያና ቀዬው በሙሉ በአረንጓዴ ልምላሜ አጊጦ የሚታይበት ምስጢሩ ይሄው ነው። ከርቀት ደን መስሎ የሚታየው አረንጓዴው ቀዬአቸው የገቢ ምንጭም በመሆኑ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ነውም ማለት ይቻላል። የሌማት ትሩፋት እሳቤ ቀድሞ የገባቸው ቤንቾች ማር አይገዙም፤ ለእንቁላል ሸመታም ገበያ አይወጡም። ወተት ቢያምራቸው በትኩሱ፤ ከዛም አለፍ ሲል በባህላዊ መንገድ እርሾ ጨምረው የሚያዘጋጁት "ኪዥ" የተሰኘ የወተት ውጤትን እንደ አይብም እንደ እርጎም አደርገው ይጠቀሙታል። የትኛውንም መልክዓ ምድር በሚስማማው የሰብል ዓይነት መሸፈን ያውቁበታል። መሬቱ ረግረጋማ ከሆነ ለጎደሬ፤ ዳገታማ ሆኖ ለማረስ የሚያስቸግር ከሆነ ደግሞ ለሙዝ ልማት ያውሉታል።   የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ሥራ የሚሠራው በጓሮ ነው። ይህም ሁሉን ከአንድ ጓሮ ለማግኘት በመጣር የሚመጣ ነው። ይህም ካልሆነ ደግሞ አስተማማኝና ቋሚ ምርት ማሳ ላይ አልያም ጎተራው ላይ ማኖር ያስፈልጋል። እንደ ቤንቾች በቤተሰብ ደረጃ ምግብን በራስ አቅም ለመቻል የሚደረገው ጥረት እንደሀገር ሲጠናከር ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይፋጠናን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥር አብዛኛው አርሶ አደር ነው። ይሁን እንጂ ጾሙን የሚያድር ሰፊ መሬት እንዳለ መረጃዎች ያመለከታሉ። አንድም መሬት ጾም እንዳያድር በየአካባቢው ስራዎች ቢጀመረም ውጤቱ ቀሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው። ዛሬም በምርት እጥረት የኑሮ ውድነትና መሰል ችግሮች ይስተዋላሉ። በእነዚህ መሬቶች ላይ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ ከተማ ቁጭ ማለትን የሚሻ ትውልድ ማየት የተለመደ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች እጃቸው ብርቱ በመሆኑ እነዚህ ችግሮች በስራ አሽንፈዋል። ይህም በምግብ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ በኢኮኖሚም እንዲረጋጉ አድርጓቸዋል።   ለሀብት ምንጭ የሆነን ማሳ ለቆ ከተማ በመዋል የሚገኝ ነገር አይኖርም። በከተማም ሆነ በገጠር ለመለወጥ እንደ ቤንቾች ብርቱ እጆች ያስፈልጋሉ። ካልተሰራ ገቢ ሳይሆን ወጪ እያደገ ወዳልተገባ መንገድ ለመሄድ ምክንያት ይሆናል። ለችግርም ሆነ ሰርቶ የመለወጥ ዕድሉ የሚወሰነው በምርጫችንና ለሥራችን በምንሰጠው ትኩረት ነው። እንደ ቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች ሰርቶ ለመለወጥና ራስን ለመቻል በየአካባቢው ያለን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየር ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ። ሰላም!
ብልህ ከችግር ይማራል!!
Dec 2, 2025 420
ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል!! በማሙሽ ጋረደው ገራድ ተስፋዬ ተፈራ ትውልድና እድገታቸው በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ቃልሻ ቀበሌ ሲሆን በ1999 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው እንደነበር ያስታውሳሉ። ገንዘብ ለማግኘትና የመለውጥ ህልማቸውን ለማሳካት በሚል ሩቅ አስበው የጀመሩት ህገ ወጥ ጉዞ መዳረሻውን እስር ቤት አደረገው። ይህም ሁኔታ ''ሩቅ አሳቢ-ቅርብ አዳሪ'' አደረጋቸው። በባዕድ አገር በነበራቸው የ2 ዓመት የእስር ቤት ቆይታም የምግብ እጦትን ጨምሮ አካላዊ ጥቃትና ጉልበት ብዝበዛ እንዲሁም የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶችን እንዳስተናገዱ ይናገራሉ።   ይህም አልበቃ ብሎ ከአካባቢው በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ወጣቶችን ጉልበት በመጠቀም ሰፋፊ እርሻዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ የጉልበት ብዝበዛ ይፈፀምባቸው እንደነበርም ያስታውሳሉ። ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል! የሚሉት ገራድ ተስፋዬ ሩቅ ሳይጓዙ፣ ገንዘብ ሳያወጡ ሰርተው መለወጥ የሚችሉበትን አካባቢያቸውን ፀጋ ሳያማትሩ ስደት መሄዳቸው ቁጭት ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ይህም በሀገራቸው እንኳንስ የለማን መሬት ይቅርና የተቦረቦረ መሬትን አልምቶ ጉልበትንና ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ለስኬት መብቃት እንደሚቻል ከእስር ቤት ቆይታቸው ተምረው ከእስር እንደተፈቱም ወዲያውኑ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረዋል። በ2001 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱም በማህበር ተደራጅተው ከመንግሥት ባገኙት 70 ሺህ ብር ብድር በእንስሳት እርባታ ላይ ለመሰማራት 4 የወተት ከብቶችን ገዝተው የእርባታ ስራ መጀመራቸውን ይገልጻሉ፡፡   በዚህም የዞኑ አስተዳደር የሰጣቸውን መሬት አልምተው የእንስሳት እርባታውን አስፋፍተው መስራት ጀመሩ፡፡ አሁን ላይ የወተት ላሞቹን ቁጥር 37 በማድረስ የወተት ምርታማነታቸው አድጎ ከቤት ፍጆታ አልፎ ለሆሳዕና ከተማና አካባቢው በቀን ከ670 ሊትር በላይ ወተት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ለ40 ወጣቶችም ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ከመፍጠራቸውም ባሻገር የተለያዩ የጭነትና የስራ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራት መቻላቸውን ይናገራሉ። የጀመሩትን ስራ በጥምር ግብርና የማስፋትና የሚያገኙትን ወተት በማቀነባበር ምርቱን በተለያየ መልኩ ለገበያ የማቅረብ ራዕይን ሰንቀው በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በህገወጥ ስደት ካጋጠማቸው ችግር ተነስተው በተግባር ያዩትን ለሌሎች በማስተማር የስደትን አስከፊነት ለአካባቢያቸው ወጣቶች እያስገነዘቡ መሆኑን ገልጸዋል።   ወጣቶች የስደትን አማራጭ ከመመልከታቸው በፊት የአካባቢያቸውን ፀጋ እንዲቃኙና ራዕይ ሰንቀው ራሳቸውን ለማሻሻል እንዲሰሩም መክረዋል። መለወጥ በውጪ ሀገር ብቻ ያለ የሚመስላቸው የቤተሰብ ኃላፊዎችም ልጆቻቸው በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ በማመን ሊያግዟቸው እንደሚገባም አቶ ገራድ አስገንዝበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ፤ በክልሉ በርካታ ወጣቶች ያልተጨበጠ ተስፋ ሰንቀው ለህገወጥ ስደትና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡   በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ የሚያስችል አቅም በግብርናው ዘርፍ መኖሩን ጠቅሰው በዘርፉ የተሰማሩ ከስደት ተመላሾች በአካባቢያቸው ሰርተው ለስኬት እየበቁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከራሳቸው አልፈው ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ላይ የሚገኙና የእነዚህን አካላት ተሞክሮ በመውሰድ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም