ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በገላን ጉራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው
May 18, 2026 0
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018(ኢዜአ)፦ በገላን ጉራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል ገላን ጉራ የብልጽግና አሻራ! የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ ስፋትና ጥልቀት የሚለካው፣ የከተማዋን እምብርት በማስዋብ ብቻ ሳይሆን፣ ትናንት በአግባቡ ያልተጠቀምንባቸውን ሀብትና አካባቢዎችን ዓይናችንን ገለጥ በማድረግ ተመልክተን የልማትና የዕድገት ማዕከል በማድረግም ጭምር ነው። ከ5 ዓመት በፊት፣ ምንም የሚታይ መሠረተ ልማት ያልነበረው የገላን ጉራ አካባቢ፣ ዛሬ ላይ የታሪክ ምዕራፉ ተቀይሮ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ከፍታና መዋቅራዊ ሽግግር የሚያሳይ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስተጋብር ማዕከል ሆኗል። ዛሬ በዚህ ስፍራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው። ለአብነትም:- 1. በአዲስ አበባ የመጀመሪያው እና ትልቁ ባለ 325 ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር ስፉት ዘመናዊ ድልድይ፣ 2. 21 ነጥብ 73 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው (ቃሊቲ ቀለበት -ቱሉዲምቱ እና ቃሊቲ ቀለበት - ቂሊንጦ አደባባይ) የኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደርን ያሳለጠ እና ቀጥታ ከአየር መንገድ ካርጎ የሚያገናኝ ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት፣ 3. የከተማችንን የመኖርያ ቤት አቅርቦት ችግር ለማቃለል አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል የሆነ 60 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ 4. ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን የገነባነው ምቹና የተቀናጀ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የሚገኝበት፣ 5. የኅብረተሰባችንን ጤና በላቀ ደረጃ ለመጠበቅ በከተማችን በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የገላን ትሯማ ሆስፒታል ግንባታ፣ 6. በአካባቢው ለዚሁ ልማት ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬት ለለቀቁልን አርሶ አደሮች የተቀናጀ ዘመናዊ የግብርና ልቀት ማዕከል ግንባታ፣ 7. መንፈስን የሚያድሱ ሰፋፊ አረንጓዴ ስፍራዎችና ፓርኮች፣ 8. የስፖርት ማዘውተሪያዎችና የልጆች መጫወቻዎች፣ ለእናቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር የእንጀራ ፉብሪካ ግንባታና የመሳሰሉት የብልፅግና አሻራዎች ደምቀው አካባቢውን ከመሐል ከተማ የበለጠ ተመራጭ አድርገውታል።
ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል
May 18, 2026 34
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018(ኢዜአ)፦ ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ምክንያታዊነት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እንዴት እየተቃኘ ነው? ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተቋቋመበት የመመስረቻ አዋጅ ላይ ምክንያታዊነት ከሀገራዊ ምክክሩ መርሆዎች አንዱ ተደርጎ መደንገጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ፅንሰ-ሀሳቡ በምክክር ሂደት ውስጥ በምን መንገድ እየተተገበረ እንዳለ ማወቁ አስፈላጊ ነው፡፡ በሀገራዊ ምክክር ዓውድ ውስጥ ምክንያታዊነት ከስሜታዊነት፣ ከጥላቻ እና ከሃሳብ ግትርነት የፀዳ በአንፃሩ አመክንዮን እና ማስረጃን መሰረት ያደረገ ውይይቶችን ለማድረግ እና ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያግዝ ቁልፍ የሥነ-ምግባር መርህ ነው፡፡ ይህም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የጋራ መፍትሔን ለመፈለግ የሚያደርጉትን በጎ ጥረት ያጠናክራል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ ምክንያታዊነት በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ እንዴት ተፈፃሚ እንደሚሆን የሚከተሉት ሀሳቦች ያብራራሉ፡፡ 1/ አመክንዮን እና ማስረጃን መሰረት በማድረግ በዚህ ሂደት ዜጎች እና ባለድርሻ አካላት ከስሜታዊነት እና ጥላቻ በፀዳ አኳኋን በውይይቶች ላይ ተሳትፎን ያደርጋሉ፡፡ ይህም የምክክሩ ዓውድ ሰላማዊ እንዲሆን የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ 2/ ገለልተኝነትን እና ፍትአዊነትን መሰረት በማድረግ ምክንያታዊ የሆነ የሀገራዊ ምክክር ሂደት ሚዛናዊ የሆኑ ውይይቶች እንዲደረጉ ከማገዙም በላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድምፆቻቸው በእኩልነት እንዲሰሙ በር ከፋች ነው፡፡ 3/ በሰው ልጆች እኩልነት ማመንን በማበረታታት በሀገራችን የሚደረጉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የሰው ልጆች በጋራ ችግሮቻቸው ላይ የሚወያዮባቸው እንደመሆናቸው መጠን የሰው ልጀችን እኩልነት እና ተፈጥሯዊ ማንነት በማክበር እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል ከበርንሌይ ጋር ይጫወታል
May 18, 2026 92
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት አርሰናል ከበርንሌይ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የሁለቱ ክለቦች መርሐ ግብር ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። አርሰናል በ79 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ካሸነፈ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ያደርጋል። ጨዋታው ለመድፈኞቹ ዋንጫውን ለማንሳት እያደረጉት ባለው ጉዞ እጅጉን ወሳኝ የሚባል ነው። የሰሜን ለንደኑ ክለብ የዋንጫውን ዕድል ራሱ የመወሰን ዕድል አለው። ከሊጉ መውረዱ የተረጋገጠው በርንሌይ በ21 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አርሰናል 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። የ45 ዓመቱ ፖል ቲርኒ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 15 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቀቀች
May 18, 2026 78
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በጋና አክራ ከግንቦት 5 አንስቶ ሲካሄድ የቆየው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። ኢትዮጵያ በአምስት ወርቅ፣ አራት የብር እና ስድስት የነሐስ በአጠቃላይ 15 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች። በአህጉራዊው መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የገቡ አትሌቶች ባስመዘገቡት አንጸባራቂ ድል በኩራት የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ማድረግ መቻላቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በውድድሩ ከፍተኛውን ክብር ያገኙትና የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፉት አትሌቶች አትሌት አጃይባ አልዩ ፣ አትሌት ምስጋና ኃይሉ፣ አትሌት ገመቹ ጎዳና ፣አትሌት ምስጋናው ዋቁማ እና አትሌት ውብአለም ሽጉጤ ናቸው። የብር ሜዳሊያ ስኬት ያስመዘገቡት አትሌቶችና ቡድኖች ደግሞ የ4 በ 400 ሜትር የሴቶች ሪሌ ቡድን፣ አትሌት ኦታጌ ኦባንግ፣ አትሌት ሙቢን ሀጂ እና አትሌት ሀጎስ እዮብ መሆናቸው ታውቋል። በውድድሩ የነሐስና የክብር አሻራቸውን ያሳረፉት ቀሪዎቹ ስኬታማ አትሌቶች ደግሞ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ፣ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው፣ አትሌት ዘይን አየልኝ፣ አትሌት በፀሎት አለማየሁ፣ አትሌት አሰፉ አብርሃ እና አትሌት አብዱልሰላም አብዱልዋሂብ ናቸው። ኢትዮጵያ በዚህ በአህጉሪቱ የስፖርት መድረክ ላይ በ32 ሴት እና በ31 ወንድ አትሌቶች፣ በአጠቃላይ 63 አባላትን በመያዝ ጠንካራ ተሳትፎ አድርጋለች። የተመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ የበላይነት በአህጉሪቱ መድረክ ላይ ዳግም ያስመሰከረ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ኬንያ ስድስት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሰባት የነሐስ በድምሩ 17 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች። ደቡብ አፍሪካ በስድስት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ስድስት የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። ናይጄሪያ እና ኮትዲቭዋር አራተኛና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሻምፒዮናው ላይ ከተሳተፉ ሀገራት መካከል 25ቱ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብተዋል። ኢትዮጵያ በካሜሮን ዱዋላ በተደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስት የወርቅ፣ አራት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አራተኛ መውጣቷ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ሻምፒዮና የሜዳሊያ ብዛት እና ደረጃዋን አሻሽላለች።
ቀጣናዊው የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም በአዲስ አበባ
May 18, 2026 78
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፡- 73ኛው የታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም (GHACOF 73) ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀመራል። ፎረሙ የሚካሄደው “የአየር ንብረት አገልግሎቶች፤ ለአይበገሬነት እና ዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና የመተግበሪያ ማዕከል(ICPAC) ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ፎረሙን እንዳዘጋጀው ተገልጿል። ስብሰባው ትንበያ ከመስጠት ባለፈ ትንበያዎቹን ወደ ተግባር መቀየር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ዝግጅት እርምጃዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። የአየር ንብረት መረጃዎች አርሶ አደሮች፣ የጤና ባለሙያዎችንና የአደጋ ስጋት አመራሮችን በቀጥታ እንዲደግፉ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። በብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ሌላኛው የመወያያ አጀንዳ ነው። መድረኩ ለታላቁ የአፍሪካ ቀንድ ግብርና እና የውሃ ሀብት ወሳኝ የሆነውን ከእ.አ.አ ከጁን እስከ ሴፕቴምበር 2026 ያለውን የዝናብ ወቅት ትንበያ ይቀርብበታል። ሚኒስትሮች፣ የምርምር ተቋማት፣ ሰብአዊ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የግል ባለሀብቶች ይሳተፋሉ። ይህ የተሳታፊዎች ስብጥር ሳይንስን ከፖሊሲ ጋር ለማገናኘት የታለመ ነው። የአየር ንብረት መዛባት የሩቅ ስጋት መሆኑ ቀርቶ በደጃፋችን ላይ ያለ ተጨባጭ አደጋ ነው ያለው ኢጋድ ፎረሙ በታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ማህበረሰቦች በቂ መረጃ እንዲኖራቸውና አስቀድመው ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻል ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አመልክቷል። በፎረሙ ማብቂያ የጋራ አቋም መግለጫ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። የጋራ መግለጫው በቀጣይ ለሚከናወኑ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ተግባራትና ለማህበረሰብ ጥንካሬ ግንባታ ስራዎች እንደ ዋና ግብዓት እንደሚያገለግል ተመላክቷል። ከዋናው መድረክ አስቀድሞ ከባለድርሻ አካላት ጋር የበይነ መረብ ውይይት እና የአየር ንብረት ትንበያ ልማት አውደ ጥናት ተደርጓል። ቀጣናዊ ፎረሙ እስከ ነገ ይቆያል። 72ኛው የታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም (GHACOF 72) በጥር ወር 2018 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
ፖለቲካ

የምርጫው ሂደት ፖሊሲና ፕሮግራሞችን በነጻነት ለማስተዋወቅ እድል ፈጥሯል
May 17, 2026 413
ሰቆጣ ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ፓርቲዎች ፖሊሲና ፕሮግራሞቻቸውን በነጻነት ለማስተዋወቅ እድል የፈጠረ መሆኑ ተመለከተ። ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ ለሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ማኑፌስቶውንና እጩዎችን አስተዋውቋል። የጥምረቱ የምርጫና ፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊና የአገው ብሄራዊ ሸንጎ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ አላምረው ይርዳው እንደገለጹት፤ ጥምረቱ የብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ በመሆኑ ለእኩልነት መከበር ይሰራል። ፓርቲው የብሄራዊ ጥቅም መከበርን ዋነኛ አላማው በማድረግ ለሰላምና ብሄራዊ መግባባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ መልኩ በነጻነት በመንቀሳቀስ የፓርቲያቸውን ፖሊሲና ፕሮግራም ለማስተዋወቅ እድል የፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል። በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ የፓርቲው አባላት በበኩላቸው ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻችንን እየተወጣን ነው-ተፎካካሪ ፓርቲዎች
May 17, 2026 346
ጎንደር፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በፉክክርና በትብብር ላይ ተመስርቶ በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን በጎንደር ከተማና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ። ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ተወካይ አቶ የዝናወርቅ ታደለ እንደገለጹት፤ የፖለቲካ ምኅዳሩ እየተሻሻለ መምጣቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዓላማና ፕሮግራሞቻቸውን ወደ ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ እየፈጠረላቸው ነው። ፓርቲያቸው በመጪው ምርጫ በሕዝብ ድምፅ አሸንፎ የፓርላማ ወንበር ለመያዝ የሚያስችለውን የምርጫ ቅስቀሳ በነፃነት እያካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል። የሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ ተወካይ አቶ ደሴ ዓለሙ በበኩላቸው፤ መጪው ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና በሕዝብ ዘንድ ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲያቸው በትብብርና በፉክክር መርህ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የአንድ ሀገር የዴሞክራሲ መገለጫ ሰላማዊ የፓርቲዎች የምርጫ ውድድር በመሆኑ፣ ፓርቲያቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎችን ያለአንዳች ተፅዕኖ እያካሄደ እንደሚገኝም አስረድተዋል። የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ኃላፊና የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ተገኑ ደረጀ በበኩላቸው፤ ዴሞክራሲ በአንድ ጀንበር የሚገነባ ሂደት ባለመሆኑ፣ የሥልጣን ባለቤት የሆነው ሰፊው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በስፋት እንዲጠቀም ስለ ምርጫው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ነፃ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተቀራርበው እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በብልጽግና ፓርቲ የጎንደር ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን በበኩላቸው፤ ለምርጫው ስኬታማነት የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየጊዜው ተቀራርቦ በውይይትና በንግግር በመፍታት፣ ለምርጫው አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር በኩል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። በጋራ ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በምርጫው ለመወዳደር የተመዘገቡ ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የተጀመሩ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት ይጠናከራሉ
May 17, 2026 358
ጭሮ ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በብልፅግና ፓርቲ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የተጀመሩ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት ይጠናከራሉ ሲሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ኢክራም ጠሀ አስታወቁ። የፓርቲው የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐግብር ዛሬ በዞን ደረጃ በጭሮ ከተማ ተካሂዷል። በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና የፓርቲው ምክር ቤት አባል ወይዘሮ ኢክራም ጠሀ እንደገለጹት፤ ፓርቲው ለኢኮኖሚ ዕድገት ጠንካራ መሠረት በመጣል የብልፅግና ብርሃን እንዲፈነጥቅ አድርጓል። ለአብነትም ባለፉት ዓመታት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ብቻ 108 የጤና ተቋማት እና 5 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ማኅበረሰቡን የመሠረተ ልማት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል። ፓርቲው በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ግልጽ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪዋ፤ በገጠርና በከተማ ዜጎችን ከድህነት የሚያወጡ ልዩ ልዩ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ አመርቂ ውጤት መመዝገቡንና በቀጣይም ይህ ስኬት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አሰፋ በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ የገባውን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር ባለፉት ዓመታት ተጨባጭ የሆኑ የልማት ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል። ፓርቲው የልዩነት ምንጭ የነበሩ የተሳሳቱ ትርክቶችን በወል ትርክቶች በመቀየር ለሕዝቦች አንድነት ከፍተኛ ሥራዎችን ሰርቷል ያሉት ወይዘሮ መሰረት፤ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል እኩል የፖለቲካ ተሳትፎን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በዜጎች መካከል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማስፋት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋት እንደሚሰራ አመልክተዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ የፓርቲው አባላትና የከተማው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ ብልፅግና ፓርቲ የጀመራቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ቃሉን በተግባር መተርጎም መቻሉን አንስተዋል። በተለይም በከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የአካባቢን ገጽታ በፍጥነት ከመቀየር ባለፈ፣ ለአዲስ የሥራ ባህል መዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ያከናወናቸው ተግባራት አርሶ አደሩን ቀጥተኛ የልማቱ ተጠቃሚ በማድረግ ሕይወቱን እንዲቀይር ረድቶታል ነው ያሉት። በተለይም በበጋ ስንዴ ልማት እየተሰራ ያለው ታሪካዊ ሥራ ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩም በላይ የአርሶ አደሩን ገቢ በእጅጉ አሳድጓል ብለዋል። በጭሮ ከተማ በተካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐግብር ላይ ከዞኑ ልዩ ልዩ ወረዳዎች የተወጣጡ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎችና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ዘመናት ላስቆጠሩ የልማትና የፖለቲካ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ችሏል - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ
May 17, 2026 393
ሰመራ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብን ድምፅ በትዕግሥት በመስማት ዘመናት ያስቆጠሩ የልማትና የፖለቲካ ጥያቄዎችን በተግባር ምላሽ መስጠት የቻለ መሆኑን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሠመራ ከተማ አባላቱና ደጋፊዎቹ በተገኙበት የምርጡኝ ቅስቃሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በዕለቱ የተገኙት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የፓርቲው ስራ አሰፈፃሚ አባል አወል አርባ እንዳሉት፤ ፓርቲው የአፋርን ህዝብ የመልማት ጥያቄ መመለስ ችሏል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፓርቲው ያስመዘገባቸውን ዘርፈ-ብዙ የልማት ስኬቶች ይበልጥ በማጠናከር፣ የህዝባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነትና በትጋት እንሰራለን ብለዋል። በለውጡ መንግሥት በተፈጠረው ምቹ ሥርዓት ምክንያት በሕዝቦች መካከል ያለው ነፃነት፣ አንድነትና እኩልነት ይበልጥ እየጎለበተ መጥቷል ነው ያሉት። የአፋር ሕዝብ ላለፉት በርካታ ዓመታት ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በጋራ ሲያነሳቸው የነበሩት ጥያቄዎች በለውጡ መንግሥት ምላሽ ማግኘት ችለዋል፤ ይህም የሚያሳየው ፓርቲያችን በህዝብ የተገነባና ለሕዝብ ተጠቃሚነት የቆመ መሆኑን ነው ሲሉም ገልጸዋል። ፓርቲው የአፋር ሕዝብ በሀብቱ ቀዳሚ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሥርዓት ከመዘርጋቱም በላይ፣ እውነተኛ ፌዴራሊዝም በተግባር እንዲረጋገጥ አድርጓል ሲሉም አክለዋል። ብልፅግና ፓርቲ በመደመር ፍልስፍና ላይ በመመስረት የህዝቦችን ዘላቂ አንድነትና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚተጋ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዚህም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል። በቅስቀሳ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ ኑር ሳሊም በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየዘርፉ ማኅበረሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ በቁርጠኝነት እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል። በከተሞች አካባቢ በስፋት እየተተገበሩ ያሉትን የኮሪደር ልማት ስራዎች እንደ ዋነኛ ማሳያ የጠቀሱት ከንቲባው፤ ብልፅግና ፓርቲ ማህበረሰቡን ማዕከል ያደረጉና የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተጨባጭ የልማት ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በወሰድነው ካርድ ሀገርን ለማሳደግ ይሰራል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል
May 17, 2026 312
ጅማ ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በወሰዱት ካርድ ሀገርን ለማሳደግ ይሰራል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ቀን እየጠበቁ መሆኑን የጅማ ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የጅማ ዞን ነዋሪዎችም ይበጀናል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቱን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዞኑ የኦሞ ናዳ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ሳሊያ ዩሱፍ እንደተናገሩት፤ ምርጫ በድምፅ የሀገርን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ለመወሰን የሚያስችል በመሆኑ፣ በዕለቱ ሀገርን ያሳድጋል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። ሁሉም የምርጫ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች በዕለቱ ወጥተው ላመኑበት ፓርቲ ድምፅ እንዲሰጡና እንዲመርጡም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሌላኛው የዚሁ ወረዳ ነዋሪ አቶ መሀመድ ሼኽ ከድር በበኩላቸው፤ በወሰዱት የምርጫ ካርድ ለሀገርና ለሕዝብ ይጠቅማል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ይህም ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው መሆኑን ተገንዝበው ሌሎችንም እያነቁ መሆኑን ጠቅሰዋል። የጅማ ከተማ ነዋሪው ወጣት ወንድወሰን አሰፋ ምርጫ ለዴሞክራሲ መሠረት የሚጥልና የሀገሪቱን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመወሰን የሚረዳ በመሆኑ፣ ዕለቱን በጉጉት እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም ሁሉም ዜጋ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በዕለቱ ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 17, 2026 1251
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 2 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ጋር መምከራቸው ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል። በዚሁ ወቅትም በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሐሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ሥራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ሲሉ ተቀብለዋቸዋል። ከአቀባበሉ በኋላም፤ መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በዚህም መሠረት፤ በታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ብድርን ጨምሮ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈርሟል። · ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፤ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል። በዓለም የፖስታ ኅብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፤ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። በተያያያዘም፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ መሆኑን አስገንዝበው፤ ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው፤ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል ብለዋል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል። ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ሆኗልም ነው ያሉት። ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። · የገላን ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው ብለዋል። ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል ሲሉም ገልፀዋል። ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ይፈጥራል፤ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል። · ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ መጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። · የፖሊሲ ቀን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ ባሳላፍነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የፖሊሲ ቀን ተከብሯል። በዚሁ ወቅትም፤ ውጤታማ ፖሊሲ ለሀገራዊ ዕድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስገንዝበው፤ መንግሥት በግልፅ፣ ተተግባሪና ጥራት ባላቸው ፖሊሲዎቹ ለሕዝብ የገባውን ቃል እየተገበረ ስኬትም እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጂኦ-ፖለቲካዊና በቴክኖሎጂ ለውጦች ላይ ቀድሞ ምላሽ የሚሰጡ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በዕውቀት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ለማስረጃዎች ዋጋ በመስጠት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የፖሊሲ ሥነ-ምኅዳር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለዚህ ስኬት ሁላችንም በጋራ እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ምዕራፍ ያሸጋግራል ብለን ያመንበትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል -የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
May 16, 2026 642
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ምዕራፍ ያሸጋግራል ብለው የሚያምኑበትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የምርጫ ካርድ የወሰዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባም ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን ሁለት የበዓል ቀናትን ሳይጨምር እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በማራዘም ተካሂዶ ተጠናቋል። በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ድምፅ መስጫ ካርድ ላልወሰዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ በዩኒቨርስቲ ለሚገኙ ተማሪዎችና በካምፕ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በልዩ ሁኔታ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በማራዘም አጠናቋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ በማስተዋወቅ ላይ ናቸው። መራጮችም በዲጂታል "ምርጫዬ" መተግበሪያና በየምርጫ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ከ50 ሚሊየን 514 በላይ መራጮች ድምፅ መስጠት የሚያስችለቸውን የምርጫ ካርድ መውሰድ ችለዋል። ኢዜአ በአዲስ አበባ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው መራጮች እንዳሉት፤ ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገለጫና የሕገ-መንግሥታዊ የመምረጥ መመረጥ መብት ማረጋገጫ መሳሪያ ነው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወጣት ፍቃዱ ለታ፤ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚያስችለኝን ካርድ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ምርጫ ጣቢያ ወስጃለው ብሏል። የፓለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና በመገናኛ ብዙኅን የሚያቀርቡት የፖሊሲ አማራጭ አስተምህሮ ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ መምረጥ የሚያስችል ግንዛቤ እየሰጣቸው መሆኑን ገልጿል። በዚህም የፓርቲዎችን የቀጣይ ሀገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂ መረዳት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ምዕራፍ ያሸጋግራል ለሚለው ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት እያዘጋጃቸው መሆኑን ተናግሯል። ዜጎችም በምርጫው የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ የሚያጎለብት ተሳትፎ በማድረግ ላመኑበት ፓርቲ ድምፅ መስጠት እንዳለበት አስገንዝቧል። ሙሉጌታ አለሙ በበኩላቸው፤ በጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚያስችላቸውን ካርድ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ምርጫ ጣቢያ ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። በሚቀጥለው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት ዕለትም ለሀገር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበጃል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ምርጫ ጣቢያ የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የገለጹት ካሚል ሃምዛ፤ በምርጫው ወቅት ለሀገር ዕድገትና አንድነት ለሚሰራ ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ የህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ያሉት ደግሞ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ ሰባት የምርጫ ጣቢያ የመራጭነት ካርድ የወሰዱት ኤልሳቤት ሙሉጌታ ናቸው፡፡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስር የምርጫ ጣቢያ የምርጫ ካርድ የወሰዱት ሽፈራው ሰራልኝ፤ ለሀገር ጥሩ ይሰራል ብለው ያመኑበትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

ማህበራዊ
በክልሉ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል
May 17, 2026 255
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በሀረሪ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸውን የክልሉ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ገለጸ። የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ ባለፉት አምስት ዓመታት በሴቶች፣ሕጻናትና ወጣቶች ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶች በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በክልሉ ባለፉት አመታት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። በእነኚህ አመታትም 26 ሺህ 241 ወጣቶችና ሴቶችን በተለያዩ ተቋማት ብሎም ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል። ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋር ተያይዞ በክረምት በጎ ፈቃድ 46ሺህ 200 ወጣቶችን በማሳተፍ 216ሺህ 156 የህብረተሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል። ከተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ውስጥም የአረጋውያንንና የአቅመ ደካማ ዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱም 402 ሚሊዮን 802 ሺህ 904 ሚሊዮን ብር የሚገመት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል። በዚህም የ398 የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት በመገንባትና በማደስ ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካማ ዜጎች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል። ሴቶች በክልሉ ቁልፍ ተቋማትን በብቃት እየመሩ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊዋ ይህም ሴቶች ለተሳትፎ ብቻ ሳይሆን በተግባር ውጤታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ አስችሏል ነው ያሉት። ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ በተሰሩ ሰፋፊ ስራዎች ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። በቀጣይም በሴቶች ፣ህፃናትና ወጣቶች ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች ለማስቀጠል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
May 17, 2026 2525
በኢዜአ ዐይን …! በዮሐንስ ደርበው እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉን የሚሉ እሮሮዎች በተለያዩ ሕዝባዊ ውይይቶች ሲነሱ ቆይተዋል። በተለይም በአንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት እዚያም እዚህም መንከራተት፤ደግሞም ወረፋ በመጠበቅ መጉላላት ብሎም ለጊዜና ገንዘብ ወጪ መዳረግ ይስተዋላል የሚሉ ሐሳቦች ተስተጋብተዋል። ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ባሳለፍነው ሳምንት … መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል አሠራር በመንደፍ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ አስጀመረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕከሉ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅትም ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለው ነበር። አሁን ላይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።መስፋፋቱም በማዕከላት ብዛት፣በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ቁጥር እና በአገልግሎት ዐይነቶች እየተገለጠ ነው። በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት የተደራጁ ሲሆን ይህ አሃዝም ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና ያለውን ፈጣን እድገት ያመላክታል። ጉዳዩ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ፤ ብልሹ አሠራርንም መቅረፍ ነውና መንግሥት በልዩ ትኩረት ይዞታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ አሥተዳደርና በሐረሪ ክልል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የምልከታቸው አካል ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ከፍያለ ትኩረት ያሳያል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሶብ የሞባይል አገልግሎትን በመረቁበት ወቅት ደግሞ፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል። አክለውም፤በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች ዕርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል፤ ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ መሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ማለቱም ይታወቃል። የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ ያስቻለ ስኬት ተገኝቷል ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶችም ዜጋ ተኮር፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዲጂታል 2030 የአገልግሎት አሰጣጥ አመላካች ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ 50 ሀገራት መካከል አንዷ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዜጎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦንላይን በየትኛውም ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም እንዲሁ። አገልገሎቱን ያገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ እንግልትን ያስቀረ፣ ጊዜና ወጭን የቀነሰ ነውና ይስፋፋ፤ ተጠናክሮም ይቀጥል። #መሶብ_የአንድ_ማዕከል_አገልግሎት #የዜጎችን_እንግልትና_ብልሹአሠራርን_መቅረፍ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #በኢዜአ_ዐይን
ለፍትህ ስርዓት መጠናከር ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉልህ ሚና አላቸው
May 17, 2026 263
አርባምንጭ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ ለሀገሪቱ ፍትህ ስርዓት መጠናከር ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉልህ ሚና እንዳላቸው የፌዴራል የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ገለጸ። አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 10ኛው ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ከግንቦት 7 እስከ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄዶ ተጠናቋል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ፤ መንግስት የፍትህና የዳኝነት ተቋማትን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የፍትህ አገልግሎትን በዲጂታል ስርዓት ለማገዝ፤ ባለጉዳዮች ባሉበት ሆነው ያለ ምንም የአካል ንክኪ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ መሰል የምስለ ችሎት ውድድሮች የሀገሪቱን የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በበኩላቸው፤ ሀገሪቱ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በመቅረጽ እውነትን የመፈለግ እና ተጠያቂነትን የማስፈን ስራዎችን በትኩረት እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል። በተለይም ለፍትህ ስርአት መጠናከር እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ባለሙያዎችን በማፍራቱ ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉልህ ሚና እያበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል። ሀገራዊ የምስለ ችሎት ውድድሩ ተማሪዎች የህግ ዕውቀት፣ የክርክር ብቃትና የሙያ ስነ-ምግባር እንዲያዳብሩ ይረዳል ያሉት ደግሞ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አብደላ ከማል(ዶ/ር) ናቸው። ከተወዳዳሪ ተማሪዎች መካከል የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ አብርሃም ወርቁ ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድሩ በንድፈ ሃሳብ የቀሰምነውን ዕውቀት በተግባር እንድንፈጽም ብሎም የትንተና እና የሙግት ችሎታችንን እንድናዳብር አግዞናል ብሏል። በሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር መርሃ-ግብሩ በ12 ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የህግ ተማሪዎች የተወዳደሩ ሲሆን አርባምንጭ፣ ሰላሌ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ከአንደኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።
የባህል ሳምንቱ የእርስ በእርስ ትስስርን ለማጠናከር ሚናው የጎላ ነው
May 17, 2026 176
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገር አቀፍ የባህል ሳምንቱ ለተለያዩ የባህል ልምድ ልውውጦች ዕድል የሰጠና የእርስ በዕርስ ትስስርን የሚያጠናክር ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የባህል ሳምንት ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ "የባህል ልማት ለኅብረብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ግንቦት 6 ቀን የተጀመረው ሀገር አቀፍ የባህል እና ቋንቋ ሳምንት ነገ ይጠናቀቃል፡፡ ይህም የኢትዮጵያን የባህል ትርኢት ከማሳየት ባለፈ በሕዝቦች መካከል ትስስርን በመገንባት የጋራ እሴቶችን ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ ነው፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የባህል ምግቦችን ይዘው የቀረቡ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፤ ሀገር አቀፍ የባህል ሳምንቱ የተለያዩ የባህል ልምድ ልውውጦች የሚያገኙበት ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ከኦሮሚያ ክልል የባህል ምግቦችን ይዛ የቀረበችው ሀዊ እጅጉ፤ የባህል ሳምንቱ መዘጋጀቱ የተለያዩ አካባቢዎች የባህል ምግቦች እንዲተዋወቁ የሚያስችል መሆኑን ትገልጻለች፡፡ በተለይም እንደዚህ አይነት የባህል ሳምንቶች መኖራቸው የገበያ ትስስርን በመፍጠር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጨምራ ገልጻለች፡፡ ከአማራ ክልል የባህል ምግቦችን ይዛ የቀረበችው ኢሌኒ እንየው፤ የባህል ሳምንቱ ዜጎች ባህሎቻቸውን የሚያውቁበት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ትገልጻለች፡፡ ከሲዳማ ክልል የባህል ምግቦችን ይዞ የቀረበው ይርጋለም መንግስቱ በበኩላቸው፤ ይዘናቸው የቀረብናቸው ባህላዊ ምግቦች ክልሉን ይበልጥ ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡ የባህል ሳምንቱ የተለያዩ የገበያ ትስስርና የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ የሚያደርግ ነው ያለችው ደግሞ ከአዲስ አበባ የባህላዊ የወይባ ጢስ ይዛ የቀረበችው ካሚላት አህመድ ናት፡፡
ኢኮኖሚ
በገላን ጉራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው
May 18, 2026 0
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018(ኢዜአ)፦ በገላን ጉራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል ገላን ጉራ የብልጽግና አሻራ! የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ ስፋትና ጥልቀት የሚለካው፣ የከተማዋን እምብርት በማስዋብ ብቻ ሳይሆን፣ ትናንት በአግባቡ ያልተጠቀምንባቸውን ሀብትና አካባቢዎችን ዓይናችንን ገለጥ በማድረግ ተመልክተን የልማትና የዕድገት ማዕከል በማድረግም ጭምር ነው። ከ5 ዓመት በፊት፣ ምንም የሚታይ መሠረተ ልማት ያልነበረው የገላን ጉራ አካባቢ፣ ዛሬ ላይ የታሪክ ምዕራፉ ተቀይሮ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ከፍታና መዋቅራዊ ሽግግር የሚያሳይ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስተጋብር ማዕከል ሆኗል። ዛሬ በዚህ ስፍራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው። ለአብነትም:- 1. በአዲስ አበባ የመጀመሪያው እና ትልቁ ባለ 325 ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር ስፉት ዘመናዊ ድልድይ፣ 2. 21 ነጥብ 73 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው (ቃሊቲ ቀለበት -ቱሉዲምቱ እና ቃሊቲ ቀለበት - ቂሊንጦ አደባባይ) የኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደርን ያሳለጠ እና ቀጥታ ከአየር መንገድ ካርጎ የሚያገናኝ ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት፣ 3. የከተማችንን የመኖርያ ቤት አቅርቦት ችግር ለማቃለል አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል የሆነ 60 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ 4. ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን የገነባነው ምቹና የተቀናጀ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የሚገኝበት፣ 5. የኅብረተሰባችንን ጤና በላቀ ደረጃ ለመጠበቅ በከተማችን በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የገላን ትሯማ ሆስፒታል ግንባታ፣ 6. በአካባቢው ለዚሁ ልማት ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬት ለለቀቁልን አርሶ አደሮች የተቀናጀ ዘመናዊ የግብርና ልቀት ማዕከል ግንባታ፣ 7. መንፈስን የሚያድሱ ሰፋፊ አረንጓዴ ስፍራዎችና ፓርኮች፣ 8. የስፖርት ማዘውተሪያዎችና የልጆች መጫወቻዎች፣ ለእናቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር የእንጀራ ፉብሪካ ግንባታና የመሳሰሉት የብልፅግና አሻራዎች ደምቀው አካባቢውን ከመሐል ከተማ የበለጠ ተመራጭ አድርገውታል።
ልማት የማያገኙ የነበሩ አካባቢዎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
May 17, 2026 347
ቦንጋ ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ባለፉት አምስት አመታት ልማት የማያገኙ የነበሩ አካባቢዎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕስ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አስታወቁ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ 142 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንጽህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርቀው ስራ አስጀምረዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በክልሉ ባለፉት አምስት አመታት ከልማት የራቁ አካባቢዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። በዚህም የኮንታ ኮይሻ ወረዳ አንዱ መሆኑንና ማህበራዊ ተቋማትን በማዳረስ ህብረተሰቡ አገልግሎቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው በበኩላቸው፤ ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ የውሀ ተቋማት ተገንብተዋል ብለዋል። በዚህም ክልሉ ሲመሰረት የነበረውን ንፁሃ የመጠጥ ውሃ ሽፋን በእጅጉ ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። ዛሬ ለተመረቀው የኮንታ ኮይሻ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ 90 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል። የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ በበኩላቸው፤ በዞኑ ባለፉት አምስት ዓመታት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል። ዛሬ የተመረቁ ፕሮጀክቶችም ለማህበረሰቡ የጎላ ጠቀሜታ የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል ። የኮንታ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማርቆስ ወንድሙ፤ የውሀ ተቋሙ የኮይሻ ከተማ ማህበረሰብ ጥያቄን የመለሰ መሆኑን ተናግረዋል ። በለውጡ መንግስት የኮይሻ ወረዳ የውሃ፣ የመንገድ፣ የመብራት የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች ተጠቃሚ መሆኗን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በወረዳው 52 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የደለባ አልፋ ቶልካ የመንገድ ፕሮጀክትም ተመርቋል። መንገዱ 12 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ከሶስት በላይ ቀበሌዎችን የሚያገናኝ መሆኑ ተመላክቷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በክልሉ ለማህበረሰቡ የልማት ጥያቄ ምላሽ የመስጠት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል
May 17, 2026 263
ቡኢ ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለማህበረሰቡ የልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ የመስጠት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ። ርዕሰ መስተዳድሩ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ከ56 ሺህ 750 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሁለት ጤና ጣቢያና አንድ አጠቃላይ ጤና ኬላን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ባሉ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው። በክልሉ ለማህበረሰቡ የልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። ለዚህም ስኬት ከማህበረሰቡ የሚነሱ የጤና ተቋማት፣ መንገድንና መብራት ጨምሮ ሌሎች የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ የመስጠት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው፤ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ የጤና አገልግሎትን በብቃት ለመስጠት አጋዥ ናቸው ብለዋል። በመንግስትና በማህበረሰብ ተሳትፎ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ የአዴሌና የሱተን ጤና ጣቢያ እንዲሁም የዱግዳ ጤና ኬላ ከ56 ሺህ 750 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል። የእናቶችንና የህፃናት ሞት ለመቀነስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የጤና ተቋማቱ መጠናቀቅ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን እንደገለፁት፤ የጤና ተቋማቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው መንግስት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር የያዘውን አቅጣጫ እውን የሚያደርግ ነው። በዞኑ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደሚያግዝም ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም በአካባቢው የጤና ተቋም ባለመኖሩ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ረጅም ርቀት ለመጓዝ ይገደዱ እንደነበር የገለጹት ደግሞ በሶዶ ወረዳ ሱተን ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ወርቅነሽ አበበ ናቸው። ዛሬ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጤና ጣቢያ ከዚህ ቀደም የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሌላ ስፍራ በመጓዝ ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት እንደሚያስቀር ገልጸዋል። በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሩ በሶዶ ወረዳ ሪፌንሶ ከተማ ለሚካሄደው የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ ስራ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ ያኖሩ ሲሆን በመርሐ ግብሩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጣቸው የላቁ አገልግሎቶች የሚደነቁ ናቸው
May 17, 2026 167
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን አየር መንገዱ ባዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ገለጹ። ተሳታፊዎቹ የዋና ከተማዋ የአዲስ አበባ ዘመናዊና ፈጣን እድገት እጅግ አስደናቂ መሆኑንም አንስተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ አመት ምስርታ በዓልን በማስመልከት ባዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ በርካታ እንግዶች ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹ ለኢዜአ እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ስምንት አስርት ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች አስደናቂ ናቸው። ከአሜሪካ የመጣችውና በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው ካቲ ቴለር በመላው አውሮፓ፣ አሜሪካና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለምታደርጋቸው ጉዞዎች ሁልጊዜ የምትጠቀመው የኢትዮጵያ አየር መንገድን መሆኑን ገልጻለች። አየር መንገዱ በሀገር ውስጥ፣ በአህጉሩና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስም ያለውና እጅግ አስደሳች አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን በመግለጽ አድናቆቷን ችራለች። የሩጫ ውድድሩ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበትና እጅግ ደማቅ ዝግጅት እንደነበር የጠቀሰችው አሜሪካዊቷ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ መሆኑንም ገልጻለች፡፡ ይህ ደግሞ በጣም የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው ብላለች። የአዲስ አበባን ፈጣን ለውጥ በተመለከተም በየጊዜው አዳዲስ ግንባታዎችን፣ ዘመናዊ ሕንፃዎችንና አዳዲስ መሰረተ ልማቶችን መመልከቷን አስታውቃለች፡፡ ከብራዚል የመጣችው ተሳታፊ ሊዲያ ቡርኖ በበኩሏ፤ ይህ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ውድድር እንዳልሆነና ቀደም ሲል በሐዋሳ ግማሽ ማራቶን ላይ መሳተፏን አስታውሳለች። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ውበት የታደለች ሀገር መሆኗን የጠቆመችው ብራዚላዊቷ፣ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባም በፈጣን እድገት ላይ የምትገኝ ሳቢ ከተማ መሆኗን ገልጻለች። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተደጋጋሚ መጓዟን እና የአየር መንገዱ አገልግሎት እጅግ አስደናቂና በጣም የሚያኮራ መሆኑን ጨምራ ተናግራለች። ሁልጊዜ ከጃፓን ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ቀዳሚ ምርጫችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው፤ የበረራ አባላቱን ጨምሮ እያንዳንዱ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ሙያዊ ስነ ምግባሩ የላቀ ነው ሲል የገለጸው ደግሞ ጃፓናዊው ዲያላስ ኒዩሳኮ ነው።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የከተሞችን መሬት በአግባቡ ለማስተዳደርና ዘመናዊ አገልገሎት መስጠት የሚያስችል የመሬት ዲጂታል አድራሻ ተግባራዊ እየተደረገ ነው
May 16, 2026 482
አዳማ፤ ግንቦት 8/2018(ኢዜአ)፦ የከተሞችን የመሬት ሃብት በአግባቡ ለማስተዳደርና ዘመናዊ አገልገሎት መስጠት የሚያስችል የመሬት ዲጂታል አድራሻ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አብዱልአዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) ገለጹ። በአዳማ ከተማ የመሬት ሃብትን በአግባቡ ማስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን የሚያስችል የመሬት ዲጂታል አድራሻ ትግበራ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ተመርቆ በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን የዲጂታል ማፕ ርክክብም ተደርጓል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አብዱልአዚዝ ዳውድ (ዶ/ር)፤ በከተሞች የመሬት ሀብትን በአግባቡ ማስተዳደር የሚያስችል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በከተሞች ዜጎች ለንብረታቸው ዋስትና እንዲያገኙ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመጨመርና ስማርት መሰረተ ልማት ለማስፋፋት የመሬት ትራንስፎርሜሽንና ዲጂታል አድራሻ ትግበራ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም በአዳማ ከተማ የመሬት ሃብትን በአግባቡ ማስተዳደር የሚያስችል የመሬት ዲጂታል አድራሻ ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል። በአዳማ ከተማ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት በመተግበርና የካዳስተር ስርዓት ወደ ስራ በማስገባት ቀዳሚና ብዙ ልምድ የተገኘበት እንደሆነም ገልጸዋል። በቀጣይም በከተሞች ቴክኖሎጂን የማስፋፋትና ወደ ስራ በማስገባት የአገልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ፤ የአዳማ የዲጂታል መሬት ትራንስፎርሜሽን ስርዓት የከተማዋ ለዲጂታል ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበርም የመሬት ካዳስተር ስርዓት እውን እንዲሆን ማገዙን አንስተው በዛሬው እለት ተመርቆ ወደ ተግባር የገባው ፕሮጀክትም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። እንዲህ አይነት ትግበራዎች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እቅድን ለማሳካት መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ (ዶ/ር)፤ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ፕሮግራም በ73 ከተሞች የመሬት ዲጂታል አድራሻ ለመገንባት እየተሰራ ነው ብለዋል። የአዳማን ጨምሮ የዘጠኝ ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ግንባታ መጠናቀቁን ገልጸው የ32 ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ግንባታ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት። የአዳማ ከተማ ዲጂታል አድራሻ የመሬት፣ የትራንስፖርት፣ የገቢ፣ የንግድና ሌሎች አገልግሎቶችን ዜጎች በተንቀሳቃሽ ስልክ ካሉበት ሆነው እንዲገለገሉ ያስችላል ብለዋል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሃይሉ ጀልዴ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት የስማርት አዳማ ፕሮግራም በመቅረጽና በመተግበር ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመንና ዲጂታል በማድረግ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓትን ከማዘመን ባለፈ የሃብት ምዝበራ እንዳይከናወን ማድረግ ተችሏል ብለዋል። በዚህም የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር፣ በመሬት አካባቢ የነበረውን ህገ ወጥ አሰራር የመከላከልና የገቢ አቅምን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።
ከኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የሚገኝ የቴክኖሎጂ እውቀት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ያስችላል
May 16, 2026 305
ደብረ ብርሃን፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የቴክኖሎጂ እውቀትና ክሕሎት እያሳደገ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ገለፀ። በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ደመላሽ በላይ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና የወጣቱን የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እየጨመረ ይገኛል። በዋናነትም የወጣቱን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሰፊ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አመልክተዋል። ሥልጠናው በተለይ ወጣቱን በአንድሮይድ ማበልጸግ፣ በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስና በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ባለቤት እንዲሆን ማድረጉንም አብራርተዋል። በዞኑ በተያዘው በጀት ዓመት 30 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ለመስጠት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ሥልጠናውን መውሰዳቸውን የገለጹት አቶ ደመላሽ፤ ሌሎች 10 ሺህ የሚደርሱት ደግሞ ሥልጠናውን በመከታተል ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሥልጠናውን ካጠናቀቁት መካከል 90 የሚሆኑት በቀሰሙት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀት የራሳቸውን ሥራ መፍጠራቸውንም ተናግረዋል። የደብረ ብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ አየለ ፍሥሐ በበኩላቸው እንዳሉት፤ የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ወጣቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቃት ያለው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖረው እያደረገ ነው። ሥልጠናው በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የኢንዱስትሪ ዘርፍ በብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ከመደገፍ ባሻገር፣ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል። በዘርፉ የበቃ የሰው ኃይል ለማፍራት በሚደረገው ጥረትም በትብብር እየተሠራ መሆኑን አንስተው፣ ይህም የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ሥልጠናውን ከወሰዱት ወጣቶች መካከል የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪው ወጣት ዳዊት ዳምጠው፤ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ሲሆን፣ የኮደርስ ሥልጠና በመውሰድ ተጨማሪ ዕውቀትና ክህሎት ማዳበሩን ይናገራል። በዚህም «አቢሲኒያ ዲጂታል» የተሰኘ ሲስተም በማበልጸግ ተጨማሪ ገቢ እያገኘ መሆኑን ገልጿል። ሥልጠናው ዘመኑ የሚሻውን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ሀገርን፣ አካባቢንና ራስን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፣ ሌሎች ወጣቶችም ዕድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል ሲል መክሯል። ወጣት መክሊት ጌቱ በበኩሏ፤ ሥልጠናው የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎቷን ለማሳደግ እንዳገዛት አንስታ፣ በቀጣይም በዘርፉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ለመሰማራት ማቀዷን ተናግራለች።
የዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳካት እያገዘ ነው
May 16, 2026 284
ዲላ፤ ግንቦት 8/2018(ኢዜአ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳካት እያገዘ መሆኑ ተገልጿል። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ታምራት በየነ (ዶ/ር) እንዳሉት የዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከማቀላጠፍ ባለፈ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት እያገዘ ነው። ዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመተግበር ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ለማሳደግ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል። ይህም የልዩ ፍላጎት ትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ አቅም መፍጠሩን አመልክተዋል። በዩኒቨርሲቲው የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ክፍል ዳይሬክተር መምህርና ተመራማሪ አባቡ ተሾመ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የዲጂታል ኢትዮጵያ ትግበራ ልዩ ፍላጎት ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን የልማት ተሳትፎ እያሳደገ ነው። በተለይም ተማሪዎቹ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚታገዙበትን አካታች ስርአት ለመዘርጋት ማስቻሉን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ ያደረገው ጽሁፍን ወደ ብሬል የሚቀይር ቴክኖሎጂ፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን የዲጂታል አቅም የማሳደግ ተግባር እንዲሁም የዲጂታል ቤተ መጽሐፍት አገልግሎቶችን ተደራሽነት በማሳያነት ጠቅሰዋል። የዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽነት የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርትን ለማቀላጠፍ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን ያነሱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የሥነ ትምህርት መምህርና ተመራማሪ ወንድወሰን ገበያው (ዶ/ር) ናቸው። ለዚህም የተማሪዎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ማሳደግና መሰረተ ልማትን ማሟላት ላይ ወሳኝ ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል። ዩኒቨርሲቲው የዘረጋው የዲጂታል ተክኖሎጂ ትግበራ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ነው ያለው ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል 3ኛ ዓመት ተማሪ ኢስማኤል ሽፍ ነው። ዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ተክኖሎጂ ተደራሽነትን ከማስፋት ባለፈ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች የሚያስተናግድ የመማር ማስተማር ምህዳር መፍጠሩ ለሌሎች አርአያ እንደሚሆንም ገልጿል። ቴክኖሎጂው ትምህርታቸውን በቀላሉ እንዲከታተሉ በማድረግ ውጤታማ እንዳደረጋቸውም ጨምሮ ተናግሯል።
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ የምርምር ስራዎች እያከናወነ ነው
May 15, 2026 421
አዳማ፣ ግንቦት 7/2018(ኢዜአ)፦ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ የምርምር ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። ችግር ፈቺ ምርምሮች የሚቀርቡበት 4ኛው ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ፤ ዩኒቨርሲቲው ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት እያከናወነ ካለው የመማር ማስተማር ስራ በተጓዳኝ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል። በተለይ ከአካባቢና ተፈጥሮ ጋር የሚስማማ የተቀናጀ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማትና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ሀገሪቱ እያደረገች ያለችውን ጥረት በሙያ፣ በዕውቀትና በምርምር እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አሰራርና አገልግሎትን ለማዘመን፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታና በልማት ፕሮጀክቶች ጭምር በማማከር እያገዘ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በአካባቢ ጥበቃና በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፣ በአፈር ለምነት፣ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትና ግንባታ ዙሪያ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን የመፍትሔ ሐሳቦች እየጠቆመ መሆኑንም ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው አዳማ ከተማን ጨምሮ በቢሾፍቱና በሸገር ከተማ እየተገነቡ ያሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂና አገልግሎቶች የማዘመን ስራን በሙያ፣ በዕውቀትና በምርምር እያገዘ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የምርምር ፓርክ በመገንባት፣ በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ የምርምር ቴክኖሎጂ፣ በላቦራቶሪዎችና በመሳሪያዎች እያደራጀ መሆኑንም ጠቁመዋል። በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መስፍን ነገዎ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር መደገፍ አለባቸው። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምር የተደገፉ አመላካች መፍትሄዎችን በማቅረብ ለአሰራር፣ ለስትራቴጂና ለፖሊሲ ግብዓት እንዲሆኑ ማገዝ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል። በተለይ መንግሥት አገልግሎቶችን ለማዘመን የጀመረው የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሳካ ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ጠቅሰዋል። በኢንዱስትሪ ትስስር፣ በኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ልማት፣ በማህበረሰብ አገልግሎቶች እንዲሁም በምርምር ፓርክና በልህቀት ማዕከላት በማደራጀት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለመሻገር እያደረገ ያለው ጉዞ የሚደነቅ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። በተለይ የዲጂታል አገልግሎትን ጨምሮ የስማርት መሰረተ ልማት ዝርጋታን በሳይንሳዊ ምርምር በመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል። በዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ጥበቃና የተፈጥሮ ሀብት መምህር ዶክተር ኬይረዲን ተማም እንደተናገሩት፤ በሀገሪቱ የተጀመሩ የስማርት መሰረተ ልማት ፕሮግራሞችን በምርምር ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። አካታችና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የአየር ንብረት ተፅዕኖን መቋቋም የሚችል ስማርት መሰረተ ልማት ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘመናዊ መሰረተ ልማት መገንባት ለዘላቂ ልማት መረጋገጥ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል። ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኮንፈረንስ ላይ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ ተመራማሪዎችና ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል።
ስፖርት
የሊጉ መሪ አርሰናል ከበርንሌይ ጋር ይጫወታል
May 18, 2026 92
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት አርሰናል ከበርንሌይ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የሁለቱ ክለቦች መርሐ ግብር ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። አርሰናል በ79 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ካሸነፈ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ያደርጋል። ጨዋታው ለመድፈኞቹ ዋንጫውን ለማንሳት እያደረጉት ባለው ጉዞ እጅጉን ወሳኝ የሚባል ነው። የሰሜን ለንደኑ ክለብ የዋንጫውን ዕድል ራሱ የመወሰን ዕድል አለው። ከሊጉ መውረዱ የተረጋገጠው በርንሌይ በ21 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አርሰናል 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። የ45 ዓመቱ ፖል ቲርኒ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 15 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቀቀች
May 18, 2026 78
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በጋና አክራ ከግንቦት 5 አንስቶ ሲካሄድ የቆየው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። ኢትዮጵያ በአምስት ወርቅ፣ አራት የብር እና ስድስት የነሐስ በአጠቃላይ 15 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች። በአህጉራዊው መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የገቡ አትሌቶች ባስመዘገቡት አንጸባራቂ ድል በኩራት የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ማድረግ መቻላቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በውድድሩ ከፍተኛውን ክብር ያገኙትና የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፉት አትሌቶች አትሌት አጃይባ አልዩ ፣ አትሌት ምስጋና ኃይሉ፣ አትሌት ገመቹ ጎዳና ፣አትሌት ምስጋናው ዋቁማ እና አትሌት ውብአለም ሽጉጤ ናቸው። የብር ሜዳሊያ ስኬት ያስመዘገቡት አትሌቶችና ቡድኖች ደግሞ የ4 በ 400 ሜትር የሴቶች ሪሌ ቡድን፣ አትሌት ኦታጌ ኦባንግ፣ አትሌት ሙቢን ሀጂ እና አትሌት ሀጎስ እዮብ መሆናቸው ታውቋል። በውድድሩ የነሐስና የክብር አሻራቸውን ያሳረፉት ቀሪዎቹ ስኬታማ አትሌቶች ደግሞ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ፣ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው፣ አትሌት ዘይን አየልኝ፣ አትሌት በፀሎት አለማየሁ፣ አትሌት አሰፉ አብርሃ እና አትሌት አብዱልሰላም አብዱልዋሂብ ናቸው። ኢትዮጵያ በዚህ በአህጉሪቱ የስፖርት መድረክ ላይ በ32 ሴት እና በ31 ወንድ አትሌቶች፣ በአጠቃላይ 63 አባላትን በመያዝ ጠንካራ ተሳትፎ አድርጋለች። የተመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ የበላይነት በአህጉሪቱ መድረክ ላይ ዳግም ያስመሰከረ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ኬንያ ስድስት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሰባት የነሐስ በድምሩ 17 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች። ደቡብ አፍሪካ በስድስት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ስድስት የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። ናይጄሪያ እና ኮትዲቭዋር አራተኛና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሻምፒዮናው ላይ ከተሳተፉ ሀገራት መካከል 25ቱ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብተዋል። ኢትዮጵያ በካሜሮን ዱዋላ በተደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስት የወርቅ፣ አራት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አራተኛ መውጣቷ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ሻምፒዮና የሜዳሊያ ብዛት እና ደረጃዋን አሻሽላለች።
በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ በኒውካስትል ዩናይትድ ተሸነፈ
May 17, 2026 284
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዊሊያም ኦሱላ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኒክ ዎልትማደ ቀሪዋን ጎል ለኒውካስትል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ቫለንቲን ካስቴላኖስ ለዌስትሃም የማስተዛዘኛውን ጎል አስቆጥሯል። ባለሜዳው ኒውካስትል ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል። በሊጉ 14ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኒውካስትል ዩናይትድ በ49 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 19ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዌስትሃም ዩናይትድ በ36 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። የለንደኑ ክለብ በሊጉ የመቆየት ተስፋው ተመናምኗል። ማክሰኞ ቶተንሃም ቼልሲን ካሸነፈ ዌስትሃም ወደ ሻምፒዮንሺፑ ይወርዳል። ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2 በማሸነፍ በ68 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ መጨረሱን አረጋግጧል። ሰንደርላንድ ኤቨርተንን 3 ለ 1፣ ሊድስ ዩናይትድ ብራይተንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ ሁለት አቻ ሲለያዩ ፉልሃም እና ዎልቭስ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል። የ37ኛ ሳምንት ነገም ቀጥሎ ሲውል የሊጉ መሪ አርሰናል ከበርንሌይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ከነገ በስቲያ ቦርንማውዝ ከማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ
May 17, 2026 178
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መካከል ተከናውኗል። በዚህም መሠረት፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእሙሽ ዳንኤል እና ረድዔት አስረሳኸኝ ግቦች ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 አሸንፏል። ውጤቱን ተከትሎም፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት በአጠቃላይ ለ9ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል። ቀደም ብሎ በተከናወነ የዕለቱ መርሐ-ግብር መቻል እና አዲስ አበባ ከተማ 2 አቻ ተለያይተዋል። ይህን ተከትሎም መቻል በ56 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን ሲያጠናቅቅ፤ በ16 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ወርዷል።
አካባቢ ጥበቃ
ቀጣናዊው የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም በአዲስ አበባ
May 18, 2026 78
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፡- 73ኛው የታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም (GHACOF 73) ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀመራል። ፎረሙ የሚካሄደው “የአየር ንብረት አገልግሎቶች፤ ለአይበገሬነት እና ዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና የመተግበሪያ ማዕከል(ICPAC) ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ፎረሙን እንዳዘጋጀው ተገልጿል። ስብሰባው ትንበያ ከመስጠት ባለፈ ትንበያዎቹን ወደ ተግባር መቀየር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ዝግጅት እርምጃዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። የአየር ንብረት መረጃዎች አርሶ አደሮች፣ የጤና ባለሙያዎችንና የአደጋ ስጋት አመራሮችን በቀጥታ እንዲደግፉ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። በብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ሌላኛው የመወያያ አጀንዳ ነው። መድረኩ ለታላቁ የአፍሪካ ቀንድ ግብርና እና የውሃ ሀብት ወሳኝ የሆነውን ከእ.አ.አ ከጁን እስከ ሴፕቴምበር 2026 ያለውን የዝናብ ወቅት ትንበያ ይቀርብበታል። ሚኒስትሮች፣ የምርምር ተቋማት፣ ሰብአዊ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የግል ባለሀብቶች ይሳተፋሉ። ይህ የተሳታፊዎች ስብጥር ሳይንስን ከፖሊሲ ጋር ለማገናኘት የታለመ ነው። የአየር ንብረት መዛባት የሩቅ ስጋት መሆኑ ቀርቶ በደጃፋችን ላይ ያለ ተጨባጭ አደጋ ነው ያለው ኢጋድ ፎረሙ በታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ማህበረሰቦች በቂ መረጃ እንዲኖራቸውና አስቀድመው ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻል ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አመልክቷል። በፎረሙ ማብቂያ የጋራ አቋም መግለጫ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። የጋራ መግለጫው በቀጣይ ለሚከናወኑ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ተግባራትና ለማህበረሰብ ጥንካሬ ግንባታ ስራዎች እንደ ዋና ግብዓት እንደሚያገለግል ተመላክቷል። ከዋናው መድረክ አስቀድሞ ከባለድርሻ አካላት ጋር የበይነ መረብ ውይይት እና የአየር ንብረት ትንበያ ልማት አውደ ጥናት ተደርጓል። ቀጣናዊ ፎረሙ እስከ ነገ ይቆያል። 72ኛው የታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም (GHACOF 72) በጥር ወር 2018 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
በመዲናዋ ለአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የችግኝ ዝግጅትና አቅርቦት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
May 17, 2026 265
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦በመዲናዋ ዘንድሮ ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የችግኝ ዝግጅትና አቅርቦት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ገለጸ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ተነሳሽነት ሲተገበር ቆይቷል። በመርሀግብሩ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጉልህ ድርሻ እየተጫወተ ይገኛል። ይህ ግዙፍ ብሔራዊ የልማት ፕሮጀክት በኅብረተሰቡ ዘንድ ችግኞችን የመትከልና የመንከባከብ በጎ ባህል እንዲዳብርና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል። በተለይም በችግኝ ማፍላት፣ በተከላና ተያያዥ ሥራዎች ላይ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር በሀገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በችግኝ ዝግጅት ሥራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች እንዳሉት፣ ዘርፉ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ በሀገራዊ የልማት ሥራዎች ላይ የራሳቸውን አዎንታዊ ድርሻ እንዲያበረክቱ አስችሏል። በየካ ክፍለ ከተማ ሱስኒ ችግኝ ጣቢያ በችግኝ ዝግጅት ሥራ ላይ የተሰማሩት ወይዘሮ ሥራ ምናለ፣ ጣቢያው በአካባቢያቸው መኖሩ የሥራ ዕድል እንዳስገኘላቸውና የሥራው ዓላማና ግብም ሂደቱን በደስታ ለማከናወን እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል። በተመሳሳይ ወይዘሮ ፅጌ ነጋአብ በበኩለቸው፣ ያዘጋጇቸው ችግኞች በተለያዩ ቦታዎች ተተክለው ከተማዋን ውብ፣ አረንጓዴና ነፋሻማ ሲያደርጉ መመልከት ደስታን የሚሰጥ ነው ብለዋል። ሥነ-ምህዳሩ የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር በሚደረገው ሀገራዊ ተልዕኮ ውስጥ የራሳቸውን በጎ አሻራ እንዲያኖሩ እያስቻለ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ራሔል ዮሐንስ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የአረንጓዴ ቦታዎች አያያዝ፣ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አጥናፉ፣ የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላኑን ተከትሎ የከተማዋን አረንጓዴ ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ ያለሙ ተግባራትን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። ይህንን ግብ ለማሳካትም በቢሮው ሥር በሚገኙ ዘጠኝ የችግኝ ጣቢያዎች እና በዘርፉ በተሰማሩ 285 ማኅበራት አማካኝነት ከፍተኛ የችግኝ ዝግጅትና አቅርቦት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። በተለይም በከተማዋ ዘንድሮ ለተከላ ከሚዘጋጁት ችግኞች መካከል ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑት የፍራፍሬ ችግኞች ናቸው ብለዋል።
የምስራቅ ሐረርጌ ህዝብ የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃና ተፋሰስ ልማት ስኬት በተሞክሮነት የሚቀመር ተምሳሌታዊ ተግባር ነው
May 16, 2026 349
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018(ኢዜአ)፦ የምስራቅ ሐረርጌ ህዝብ የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃና ተፋሰስ ልማት ስኬት በተሞክሮነት የሚቀመር ተምሳሌታዊ ተግባር መሆኑን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት የሥራ ኃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና የግብርና ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ ተፋሰስ ልማት የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ለግብርና ምርታማነት ትልቅ አቅም እየፈጠረ ነው ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳ የተከናወነው አስደናቂ የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ ተፋሰስ ልማት ስኬትም በምርጥ ተሞክሮነት ሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ መጠነ ሰፊ የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ ተፋሰስ ልማት ሥራም ከ18 ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት መልማቱን ተናግረዋል። በዚህም የአርሶና አርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የልማት ተሳትፎ በማላቅ ከ38 ሚሊዮን በላይ ሔክታር መሬት እንዲያገግም ያስቻለ ውጤት መገኘቱን አንስተዋል። የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በትጋት እየሰሩ ለሚገኙ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። ይህም የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዕውቅና በማጉላት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እንድትገነባ እያስቻላት መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይም የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ ተፋሰስ ልማት ሥራን የበለጠ በማጠናከር ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሻገር በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በኢሉአባቦር ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅተዋል
May 16, 2026 273
መቱ፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቦር ዞን በመጪው የክረምት ወቅት የሚተከሉ የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ። በፍራፍሬ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች በበኩላቸው በዘርፉ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። የኢሉአባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ፤ በዞኑ በልዩ ኢኒሼቲቭ እየተተገበሩ ከሚገኙ ዋና ዋና የግብርና ሥራዎች መካከል የፍራፍሬ ልማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ለዜጎች የምግብ ዋስትና መረጋገጥና ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ትልቅ አቅም እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል። በዞኑ በልዩ ትኩረት እየተዘጋጁ ከሚገኙት የፍራፍሬ ችግኞች መካከል የአቮካዶ፣ የሙዝ እና የፓፓያ ችግኞች ዋናዎቹ መሆናቸውን አስታውሰዋል። ይህንኑ መልካም ጅምር ይበልጥ ለማጠናከርና ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት፣ በመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ45 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል። በችግኝ ዝግጅት ሂደቱም ምርታማነታቸው በተረጋገጠ ምርጥ ዝርያዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሠራቱን ኃላፊው አብራርተዋል። በፍራፍሬ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮችም ዘርፉ ለምግብ ዋስትናና ለገቢ ምንጫቸው ተጨማሪ አቅም እየሆናቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል መዘሚል አደም፣ "የምናመርተውን ፍራፍሬ ለአካባቢው ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ከመሸጥ ባለፈ፣ ለሌሎች አርሶ አደሮችም የፍራፍሬ ችግኞችን እያቀረብን በዓመት ጥሩ ገቢ እያገኘንበት ነው'' ብለዋል። አርሶ አደር ተካ መሐመድ እና ፈቀደ አረጋ፣ በግብርና ሥራቸው ውስጥ ለፍራፍሬ ልማት ትልቅ ትኩረት መስጠታቸውን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሠራር በተሻለ መልኩ የመልማት አቅማቸውን በማስፋት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በመጪው ክረምትም በተለይ የአቮካዶ ችግኞችን በስፋት ለመትከል ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 894
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 618
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 542
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በአዲስ አበባ ይካሄዳል
May 13, 2026 580
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በሕብረቱ ዋና መቀመጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ይደረጋል። በውይይቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደሚገኙ ይጠበቃል። ውይይቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል በአፍሪካ ልማት እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅት፣ የጋራ ተጠያቂነት እና ትብብርን በልማት፣ በአስተዳደር፣ በሰብአዊ ድጋፍ እና በሰላም ግንባታ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ያላቸውን ትስስር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ይካሄዳል። በዚህ የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ላይ በርካታ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ሲሆን፣ በተለይም የአጀንዳ 2063 እና የሁለተኛው የአስር ዓመት ምዕራፍ የትግበራ ዕቅድ አፈፃፀምን ማፋጠን እንዲሁም አፍሪካን በዓለም አቀፍ ፖሊሲ እና አስተዳደር ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና መጠበቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል። በተጨማሪም "ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት" የተሸጋገረ የልማት ፋይናንስ፣ የ2026 የአፍሪካ ሕብረት የዓመቱ መሪ ቃል የሆነው ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና የንጽህና አጠባበቅ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፎርም እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ውክልና የተመለከቱ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል። መድረኩ ለአህጉራዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ማምጣት፣ የአገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብን ማሳደግ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲሁም በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የልማት የቅድሚያ ትኩረቶች መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ አጽንኦት የሚሰጥበት እንደሆነ ተመላክቷል። ከውይይቱ ከሚጠበቁ ውጤቶች መካከል የተሻለ ስትራቴጂካዊ ቅንጅት፣ ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ለውጥ፣ በአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ቃል ዙሪያ ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር እና በተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ውስጥ ፍትሐዊ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር የቀረቡ ጥሪዎችን ማጠናከር እንደሚገኙበት ህብረቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የውይይቱን ውጤቶች አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ይሰጣሉ።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 227
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 10, 2026 1178
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታ- በሱሉልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳምንቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል። መንግሥት በግብርናው ዘርፍ በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተገኙ ያሉ ውጤቶች አመርቂና ለቀጣይ ሥራዎች ስንቅ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል። መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት የተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ስለመሆኑም አንስተዋል። ከልመና ራሳችንን መገላገል አለብን፤ ሊታረስና ሊለማ የሚችል መሬት መታረስ አለበት በሚል ጽኑ እምነት የበጋ ስንዴ ልማት መጀመሩን አስታውሰው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት የወፍ በረር ጉዟችን የቀጠለ ሲሆን ከሱሉልታ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር አምርተናል። የባህር ዳር መዳረሻችን በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይሆናል። የሪዞርቱ ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ባሳምንቱ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት አላማ በማድረግ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መገንባቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸው በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ጣና የሆቴል ፕሮጀክት ግንባታም አስጀምረዋል። በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ዓለም አቀፍ ሆቴልም በ18 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። የመልካ ቁንጡሬ ሁነት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ በሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ተከብሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ፤ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይቀጥላሉ ብለዋል። ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ የተደረገውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው። የልማት ስራዎቹ ከተማዋ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን¸፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችን በማስተናገድ ተመራጭ እየሆነች እንድትመጣ አድርገዋታል ብለዋል። የሀይቅ ዳርቻ ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ብለዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻን በማልማትና ከአካባቢው መስህቦች ጋር በማስተሳሳር ሀይቁን የቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል። ጅማ ዞን ጎማ ሁለት በጅማ አጠር ያለ ቆይታችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ዞን ጎማ ሁለት የምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን በማስተዋወቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ የቅስቀሳ ስነ ስርአት ላይ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ደጋፊዎች በመውጣት የተሳተፉበት መሆኑን ለማየት ችለናል። በመርሃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸው በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ርዕሰ መስተዳድሩ በሚወዳደሩበት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳና እጩ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችንን ሲያከናውን ቆይቷል። በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። የሽንሌ እመርታ በሳምንቱ በሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ የተገነባው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድና በሽንሌ ጠቅላላ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተመርቋል። በሽንሌ ወረዳ የመርማርሳ ከተማን ከድሬዳዋ ጋር የሚያስተሳስር የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታንም አስጀምረዋል። የተገነቡት የልማት ስራዎች በተለይም ለወረዳው እመርታ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት የማልማትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ሳተላይት በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ተከላ ስራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በተገኙበት በዚሁ ሳምንት ተጀምሯል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን የመረጃ ግብዓት ከመሆን አኳያም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል። የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ሌሎችም የተሟላ መረጃ ለመስጠት የሚጠቅም መሆኑ ታውቋል።
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 1003
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 1080
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
ትንታኔዎች
እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
May 17, 2026 2525
በኢዜአ ዐይን …! በዮሐንስ ደርበው እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉን የሚሉ እሮሮዎች በተለያዩ ሕዝባዊ ውይይቶች ሲነሱ ቆይተዋል። በተለይም በአንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት እዚያም እዚህም መንከራተት፤ደግሞም ወረፋ በመጠበቅ መጉላላት ብሎም ለጊዜና ገንዘብ ወጪ መዳረግ ይስተዋላል የሚሉ ሐሳቦች ተስተጋብተዋል። ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ባሳለፍነው ሳምንት … መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል አሠራር በመንደፍ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ አስጀመረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕከሉ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅትም ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለው ነበር። አሁን ላይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።መስፋፋቱም በማዕከላት ብዛት፣በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ቁጥር እና በአገልግሎት ዐይነቶች እየተገለጠ ነው። በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት የተደራጁ ሲሆን ይህ አሃዝም ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና ያለውን ፈጣን እድገት ያመላክታል። ጉዳዩ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ፤ ብልሹ አሠራርንም መቅረፍ ነውና መንግሥት በልዩ ትኩረት ይዞታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ አሥተዳደርና በሐረሪ ክልል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የምልከታቸው አካል ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ከፍያለ ትኩረት ያሳያል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሶብ የሞባይል አገልግሎትን በመረቁበት ወቅት ደግሞ፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል። አክለውም፤በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች ዕርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል፤ ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ መሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ማለቱም ይታወቃል። የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ ያስቻለ ስኬት ተገኝቷል ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶችም ዜጋ ተኮር፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዲጂታል 2030 የአገልግሎት አሰጣጥ አመላካች ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ 50 ሀገራት መካከል አንዷ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዜጎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦንላይን በየትኛውም ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም እንዲሁ። አገልገሎቱን ያገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ እንግልትን ያስቀረ፣ ጊዜና ወጭን የቀነሰ ነውና ይስፋፋ፤ ተጠናክሮም ይቀጥል። #መሶብ_የአንድ_ማዕከል_አገልግሎት #የዜጎችን_እንግልትና_ብልሹአሠራርን_መቅረፍ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #በኢዜአ_ዐይን
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 17, 2026 1251
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 2 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ጋር መምከራቸው ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል። በዚሁ ወቅትም በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሐሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ሥራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ሲሉ ተቀብለዋቸዋል። ከአቀባበሉ በኋላም፤ መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በዚህም መሠረት፤ በታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ብድርን ጨምሮ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈርሟል። · ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፤ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል። በዓለም የፖስታ ኅብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፤ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። በተያያያዘም፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ መሆኑን አስገንዝበው፤ ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው፤ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል ብለዋል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል። ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ሆኗልም ነው ያሉት። ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። · የገላን ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው ብለዋል። ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል ሲሉም ገልፀዋል። ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ይፈጥራል፤ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል። · ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ መጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። · የፖሊሲ ቀን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ ባሳላፍነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የፖሊሲ ቀን ተከብሯል። በዚሁ ወቅትም፤ ውጤታማ ፖሊሲ ለሀገራዊ ዕድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስገንዝበው፤ መንግሥት በግልፅ፣ ተተግባሪና ጥራት ባላቸው ፖሊሲዎቹ ለሕዝብ የገባውን ቃል እየተገበረ ስኬትም እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጂኦ-ፖለቲካዊና በቴክኖሎጂ ለውጦች ላይ ቀድሞ ምላሽ የሚሰጡ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በዕውቀት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ለማስረጃዎች ዋጋ በመስጠት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የፖሊሲ ሥነ-ምኅዳር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለዚህ ስኬት ሁላችንም በጋራ እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የጤና ነገር
May 15, 2026 1110
በዮሐንስ ደርበው ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ሾተላይ የሚከሰተው RH-Negative የሆነች እናት RH-Positive የሆነ ፅንስ በምታረግዝበት ወቅት የእናትየው በሽታ የመከላከል ሥርዓት የፅንሱን ደም እንደ ባዕድ ነገር በመቁጠር በሚያመነጨው ንጥረ-ነገር (Antibodies) አማካኝነት መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የጽንስና ማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር ዳንኤል ኃብተማርያም ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከወሊድ ጋር በተያያዘው አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ወይም ሾተላይ እየተባለ በሚጠራው በጽንስ ላይ የሚያጋጥም ችግር ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሾተላይ ወይም አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ዳንኤል ማብራሪያ፤ ሰዎች ከሚታወቁበት አራቱ የደም ዓይነቶች ምደባ (ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ) በተጨማሪ በቀይ ደም ኅዋስ ሰርፌስ ላይ በፕሮቲን መኖርና አለመኖር ይለያሉ። በዚህም መሠረት አር ኤች ፖዘቲቭ (RH+) እና አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ተብለው እንደሚከፈሉ ያስረዳሉ። በዚህ ምደባ መሠረት ከአጠቃላይ ሕዝቡ 85 በመቶው አር ኤች ፋክተር ፖዘቲቭ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ማለት በቀይ ደም ኅዋሳቸው ሰርፌስ ላይ ፕሮቲን አላቸው ማለት ነው ይላሉ። 15 በመቶው ደግሞ አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም በቀይ የደም ኅዋሳቸው ሰርፌስ ላይ ፕሮቲን የሌላቸው ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። አክለውም አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም ፖዘቲቭ መሆን በሽታ እንዳልሆነ በአጽንኦት ገልጸው፤ ከወላጆች የሚወረስ መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ አንድ ልጅ ሲወለድ እንደ ወላጆቹ አር ኤች ፋክተር መሠረት አር ኤች ፖዘቲቭ ወይም አር ኤች ኔጌቲቭ ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። ይህን በምሳሌ ሲያስረዱም፤ አንዲት ሴት አር ኤች ፋክተሯ ኔጌቲቭ ሆኖ ጽንሷ ደግሞ አር ኤች ፖዘቲቭ ቢሆን ተገቢው የሕክምና ክትትል ካልተደረገ ብሎም የእናትና ልጅ ደም ንክኪ ከተፈጠረ የበሽታ መከላከል ሥርዓቷ የሚያመነጨው አንቲ ቦዲ ጽንሱን እንደ ባዕድ ነገር ስለሚቆጥረው ጉዳት (ሾተላይ) ያስከትላል ይላሉ። የአንቲ ቦዲ ሥራ ሴቷ ለአር ኤች ፖዘቲቭ የምትጋለጥበት ሁኔታ ከተፈጠረ ጽንሱን (አር ኤች ፋክተሩ ከእሷ ተቃራኒ ሲሆን) እንደ ባዕድ ነገር ቆጥሮ ሴትዮዋን ለመከላከል በጽንሱ ላይ ጥቃት ማድረስ መሆኑንም አመላክተዋል። መፍትሔው ምንድን ነው? ለማንኛውም ጤናማ የእርግዝና ሂደት የሕክምና ክትትል ማድረግ ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን መክረዋል። ከሾተላይ ጋር በተያያዘ ደግሞ በእርግዝና ወቅት የሚስትና ባልን አር ኤች ፋክተር መለየት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። ይህን ተከትሎም አር ኤች ፋክተራቸው ተመሳሳይ ከሆነ ጽንሱም ከእነሱ ጋር ስለሚመሳሰል ጤናማ እንደሚሆን ገልጸዋል። በአንጻሩ ግን፤ አር ኤች ፋክተሯ ኔጌቲቭ የሆነች ሴት የባለቤቷ አር ኤች ፋክተር ፖዘቲቭ ከሆነ ወይም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ ሰውነቷ መከላከያ አምርቷል ወይስ አላመረተም የሚለው በሕክምና ምርመራ እንደሚታወቅ አስረድተዋል። ይህ ምርመራ ሲሠራ ውጤቱ ኔጌቲቭ ከሆነ ወይም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ ሰውነቷ መከላከያ አላመረተም የሚል ከሆነ በዚህኛው እርግዝናም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ፣ የእናትና የጽንስ ደም ንክኪ ኖሮ መከላከያ እንዳታመርት የሚሰጥ ሕክምና እንዳለ አረጋግጠዋል። ይህ ሕክምናም 28ኛ ሳምንት ላይ በመርፌ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሰጣል ብለዋል። ከወለደች በኋላ ደግሞ የተወለደው ልጅ አር ኤች ፋክተር ታይቶ እንደእናቱ ከሆነ ተጨማሪ መድኃኒት እንደማያስፈልግና ከአባቱ ጋር ከተመሳሰለ ግን (አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ) በመርፌ ተጨማሪ መድኃኒት በወለደች በ72 ሠዓት ውስጥ በመስጠት ለቀጣይ እርግዝናዎች ሰውነቷ መከላከያ እንዳያመነጭ ማድረግ እንደሚቻል አብራርተዋል። በሌላ በኩል ከሾተላይ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ያልሆኑ ልማዳዊ ድርጊቶችን ኮንነው፤ ትክክለኛው መፍትሔ ያለው የሕክምና ክትትል በማድረግ መሆኑን አስረድተዋል። እንዲሁም፤ በተለይም የጎንዮሽ ህመም ያለባቸው ሴቶች (የኩላሊት፣ የደም ግፊት፣ ስኳር እና ሌሎችም) ቀድመው ሐኪም አማክረው ወደ እርግዝና ቢገቡ እንደሚመከር ገልጸው፤ የቅድመ እርግዝና ክትትል ማድረግ ካልተቻለ እንኳን በእርግዝና ወቅት በአግባቡ ክትትል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ለመከላከያ ትልቅ ትኩረት መስጠት ችግሩ ተፈጥሮ ከመታከም የተሻለና ተመራጭ መፍትሔ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። #የጤና_ነገር #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት
ለተቃና ነገ የኢትዮጵያ ትጋት አንዱ መገለጫ
May 11, 2026 1770
በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያ ከምትከውናቸው ዐበይት ጉዳዮች መካከል ሰው ተኮር ተግባራት ቀዳሚው ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ጥረት ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ብለዋል። መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል አድርጎ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ ስለመሆኑም አስረድተዋል። በዚህም መሠረት፤ የልጆች ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ የምገባ ሥርዓትን ማሳደግ፣ የሕጻናት መጫወቻ ሥፍራዎች ግንባታ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች መምጣታቸውንም ነበር የጠቀሱት። ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማትና ትምህርት ፖሊሲ የዘላቂ ብልጽግና መንገዳችን ከሆነው የመደመር ዕሳቤ ጋር በተናበበ መልኩ እየተተገበረ በስኬት ቀጥሏልም ብለዋል። ኢትዮጵያ ለነገ የተዘጋጀ ትውልድ ለመገንባት በሕግና በፖሊሲ የተደገፉ የቀዳማይ ልጅነት ኢኒሼቲቮችን እየተገበረች እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ለአብነትም፤ በ2015 ተሻሽሎ የፀደቀው ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማት እና ትምህርት የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲሁም በ2017 የፀደቀውን አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ መሠረት በማድረግ ከ35ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላው ሀገሪቱ እየተተገበረ መሆኑን አንስተዋል። በመንግሥት ተቋማት የሕጻናት ማቆያ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በመጠቆምም፤ ኢትዮጵያ የሕጻናትን ደኅንነት ማሻሻል የሚያስችል ጉልኅ ብሔራዊ መርሐ-ግብር መጀመሯን አንስተዋል። በሰቆጣ ቃል ኪዳን አማካኝነት የ15 ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ከሁለት ዓመት በታች በሆኑ ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን መቀንጨር በ2022ዓ.ም ዜሮ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። የሌማት ትሩፋትና የአልሚ ምግቦች ምርታማነት የሕጻናትን ጉዳት ለመቀነስና የልጆችን ጤናማነት መጨመር እያስቻሉ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ ለዘላቂ የልማት ግቦችና ለሕጻናት መብቶች ጥበቃ የገባቻቸውን ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባር እየለወጠች መሆኑን በማንሳት፤ ይህንንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። መንግሥት ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የቀዳማይ ልጅነት ልማትን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አመላክተዋል። በዚህም መሠረት፤ በጀት በመመደብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የተማሪዎችን ምገባ በማስፋፋት ውጤት ማምጣቱን ነው የሚያብራሩት። ልጆች በአካልና በመንፈስ የሚጎለብቱባቸው የስፖርትና የመዝናኛ ቦታዎች በየአካባቢው በመገንባት፣ በኮሪደር ልማት ለልጆች ምቹ ሥፍራ እየተፈጠረ መሆኑንም በመጥቀስ። ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር፣ አኅጉር እና ዓለም ላይ መሥራት በመሆኑ በትጋት ማስቀጠል እንደሚገባም በአጽንኦት ይናገራሉ። አፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታት የራሷን መፍትሔዎች በማፍለቅ፣ በብሔራዊ የልማት አጀንዳዋ እያካተተች መሆኑን የሚገልጹት ደግሞ የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ከበደ ወርቁ ናቸው። በሕጻናት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማንኛውም ሀገር በመጪው ትውልድ ላይ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው እጅግ አስፈላጊ ኢንቨስትመንቶች አንዱ መሆኑንም ያነሳሉ። አፍሪካ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ላይ ያሉባትን ተግዳሮቶች ከመጋፈጥ ባለፈ፤ የራሷን መፍትሔዎች እያመነጨች መሆኑንና ጉዳዩን የብሔራዊ ልማት አጀንዳዋ አካል እያደረገችው እንደምትገኝም ገልጸዋል። አዲስ አበባ ይህን ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ እንድታስተናግድ የተመረጠችበት ዋና ምክንያትም፤ በዘርፉ እያከናወነች ያለው ተግባር አርዓያነት ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል። ከተማዋ የጤና እና የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶችን ያካተተ የተቀናጀ ዘርፈ-ብዙ አሠራር መዘርጋቷን ጠቅሰው፤ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት እና የቀን የሕጻናት እንክብካቤ ማዕከላትን በከተማ አቀፍ ስትራቴጂ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝም ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ መዲናዋ በቀዳማይ ልጅነት ያመጣችው ተጨባጭ ውጤት በአርዓያነት እንድትጠቀስ እንዳደረጋት አንስተዋል። በሕጻናት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች፤ በትምህርት፣ በሰው ሃብት ልማትና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል። በዚህም በአዲስ አበባ ፍትሐዊና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሐ-ግብርን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ የትውልድ ግንባታ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። "ሕጻናት የአዲስ አበባ የነገ ተስፋዎች" የሚል ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ለሚሆኑ ከስድስት ዓመት በታች ሕጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት መረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ-ግብርም ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ ዩኒፎርምና በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ በማቅረብ በሕጻናት ክብካቤ ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል ነው ያሉት። የሕጻናት ማቆያና መጫወቻ የመሠረተ-ልማት ግንባታ፤ ሕጻናት ነፃ የሕክምና፣ የምገባና የሥነ-ልቦና አገልግሎት የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። የቀዳማይ ልጅነት መርሐ-ግብር በ2015 ዓ.ም ሲጀመር በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩ የሕጻናት መጠን ከነበሩበት 13 በመቶ አሁን ላይ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ከንቲባዋ አመላክተዋል። አክለውም፤ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጁነታቸው ከነበረበት 49 በመቶ አሁን ወደ 90 በመቶ ማደጉንም ተናግረዋል። ሀገር በሁሉም ዘርፍ የበቃ መጪ ትውልድ እንዲኖራት መንግስት የያዘው ጥረት በሚፈለገው መጠን ለውጤት እንዲበቃ የሁሉንም ትኩረትና ተሳትፎ ይሻል። ለነገ በሁሉም ዘርፍ የዳበረ ትውልድና የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን መሆን ዛሬ ላይ እየተደረገ ያለው ርብርብ የሀገራችንን መፃኢ ብሩህ ተስፋ ይበልጥ የሚያለመልም ነውና ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 5844
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 3681
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 9474
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7955
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 673
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 1833
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።