ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ከገበታ ወደ ገበያ
Sep 24, 2023 1
(ሰለሞን ተሰራ) ኢትዮጵያ ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ አዝእርትና እንስሳት ሀብት መፍለቂያ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከዚያ ዘመን ጀምሮ የአገራችን ገበሬ በስራ ያካበተውንና በተፈጥሮ የተሰጠውን ችሎታ በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ በወለዳቸው መሳሪያዎች ሳይታገዝ፣ በየጊዜው የአፈሩ ለምነት እየቀነሰ ከሄደው መሬትና ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ጋር እየታገለ ቁጥሩ እየናረ የሚሄደውን ህብረተሰብ ከመመገብ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። ግብርናው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ባገኘበት በዚህ ዘመንም ከተደቀኑበት እጅ ጠምዛዥ ጉዳዮች ጋር ግብግብ ውስጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፣ የፖለቲካና የገበያ አለመረጋጋት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዘርፉ ኢንቨስትመንት አለመዳበር የዘርፉ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በተለይ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽእኖ በሚገባ አመላክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በተለይ በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገራት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲበጅ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ እየተሳተፉበት ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በሰራችው ስራ በአካባቢ ጥበቃና በግብርናው ዘርፍም ውጤት ማግኘቷ እሙን ነው። ነገር ግን ፈተናዎቹን በድል ለመሻገር የሚደረጉ ጥረቶችና በዘርፉ የተገኙ አበረታች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በተደራጀ የግብርና መሳሪያና ማቀነባበሪያ በመደገፍ አገርና ህዝብ ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ መስራት ይጠይቃል። በተለይ የግብርና ሜካናይዜሽንን ከማስፋፋትና ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ አኳያ መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት የበለጠ መጠናከርና ማደግ ይኖርበታል። የግብርናና የገጠር ልማት የፋይናንስና ብድር አቅርቦትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢና ስነ ምህዳር ጥበቃ ስራዎችን በዘላቂነት መተግበር ያሻል። በተለይ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየሰራችበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብርና አሰራር በመቀየርና አማራጮችን በማማተር እውን ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ በዝናብ ወይም በመስኖ መልማት የሚችል ያልተነካ ሰፊ መሬት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ይህን ያልታረሰ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አንዱ አማራጭ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግብርናው ከ34 በመቶ በላይ የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ዘርፉ 79 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ ሲሆን በተመሳሳይ 79 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ንግድ ገቢ በመሸፈንና ለአገር ውስጥ ኢንቨስትመንትና ገበያ የጥሬ እቃ አቅራቢ በመሆንም ይታወቃል። መንግስት በግብርናው ዘርፍ የወሰዳቸው የሪፎርም ስራዎችና ግብርናን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የሰራቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። በተለይ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተሰራው ስራ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ የስንዴ ምርታማነቷን በ27 በመቶ ማሳደግ መቻሏ ስንዴ ከመሸመት ወደ መላክ የመሸጋገሯ ማረጋገጫ ሆኗል። በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በዚህ ረገድ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ አላስገባችም። በዚህም 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በቅርቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ያመረተች ሲሆን በተያዘው ዓመት ደግሞ ምርቱን ወደ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህንኑ ግብ ለማሳካት ደግሞ የስንዴ ማሳዋን በማሳደግ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን እየሰራች ነው። ከዚህ ውስጥ በመስኖ የሚለማ ስንዴን በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት በመስኖ የሚለማውን ስንዴ በ54 በመቶ ለማሳደግ እየሰራች ነው። ይህ ደግሞ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የግብርናው ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል። በዚህም ዘርፉ በ2013 ከነበረበት 5 ነጥብ 1 በመቶ በ2014 ወደ 5 ነጥብ 8 በመቶ ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65 ነጥብ 5 በመቶ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ደን ልማት 8 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የእንሰሳት ሃብት ልማቱ 25 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ 627 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት ታቅዶ ከተቀመጠው ግብ በላቀ ደረጃ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል። ከበጋ ስንዴ ልማት ጎን ለጎን በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ የቡና፣ አቮካዶና አኩሪ አተር የመሳሳሉት ትላልቅ የግብርና ልማት ስራዎች በተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የአዝርት፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የስንዴ ምርት ከውጭ ገበያ ስትገዛ የኖረች ሲሆን በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች አቅርቦቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የስንዴና የገብስ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የቻለች ሲሆን የሩዝ ፍላጎቷን ደግሞ 50 በመቶ መሸፈን ችላለች። በስንዴ ምርታማነት የተገኘውን ተሞክሮ ወደሌሎች ሰብሎች በማስፋት የገቢ ምርቶችን በቀጣይ ለመተካት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን ለማሳካት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ለግብርና ዘርፉ የተሻለ በጀት መመደቡ፣ እስካሁን ለመጣውና ለወደፊትም ይመጣሉ ተብለው ለሚታሰቡ ለውጦች ትልቅ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ከተመደበው 786 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ፣ ለግብርናው ዘርፍ 34 በመቶ የሚሆን በጀት ተመድቧል። ይህ ደግም ከለውጡ በፊት ከአሥር በመቶ ያልበለጠ በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ያደርገዋል። በተጨማሪም መንግሥት ለኩታ ገጠምና ለመስኖ እርሻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ፣ ሙሉ በሙሉ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ስራ በመስኖ የታገዘ እንዲሆንና አርሶ/አርብቶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት ማድረጉ ውጤቱን ጉልህ አድርጎታል። እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ቡና፣ አቦካዶ ሁሉ በግብርና ሚኒስቴር ከተያዙና በልዩ ትኩረት ከሚከናወኑ ዕቅዶች አንዱ የማር ምርትን ማሳደግ ሲሆን፣ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ እንደተመላከተውም የማር ምርትን በማዘመን ምርቱን ለማሳደግ በስፋት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለማር ምርት ተስማሚ የሆነ አግሮ ኢኮሎጂና ብዛት ያላቸው ዕፅዋት መኖራቸው የሚመረተው ማር የተፈጥሮ ጥራት እንዲኖረው ያግዛል። ይህንኑ ዕምቅ ሀብት ትኩረት ሰጥቶ ማልማት ከተቻለ ከ500 ሺሕ ቶን በላይ ማርና ከ50 ሺሕ ቶን በላይ ሰም ማምረት እንደሚቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ በሀገሪቱ አለ ተብሎ ከሚገመተው ሰባት ሚሊዮን የንብ መንጋ ውስጥ 90 በመቶው በባህላዊ ቀፎ ውስጥ የሚገኝ ነው። የንብ መንጋዎቹ በባህላዊ ቀፎ ከመኖራቸው በተጨማሪ በጫካ መገኘታቸው ሃብቱ ለአገር ዕድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይውል አድርጎታል። ያም ቢሆን ባለፈው ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” ለማር ምርት ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተደርጓል። በዚህም የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል። ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የማር ምርት የማምረት አቅም ካላቸው አሥር ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ሃብቱን ለማልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በአጠቃላይ መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት/አሻራ፣ ለአፈርና አካባቢ ጥበቃ የሰጠው ትኩረት ሁሉን አቀፍ የግብርና ዕድገት እንዲመጣ መሠረት ሆኗል። በተጨማሪም መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌማት ትሩፋትና ምግባችን ከደጃችን መርሐ ግብር ኅብረተሰቡ የከተማ ግብርናን እንዲያስፋፉ በገጠርም ሆነ በከተማ ያከናወነው ተግባር ውጤት አስመዝግቧል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ የልማትና የሪፎረም ሥራዎች ግብርናውን ከአዝጋሚ ጉዞ በማውጣት ወደ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞ ማሸጋገር ችለዋል። ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ያልተነኩ ዕምቅ ሀብቶች ያሏት መሆኗን እንደ እድል በመውሰድ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል። ይህን ማድረግ ስትችል የግብርና ሽግግር ይረጋገጣል። ግብርናውን ለማሻገር ደግሞ በፋይናንስ፣ በግብአት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ያሻል። ወጣቱ ግብርናን እንደ ንግድ (Agri-Bussiness) ማየትና በዚያው ልክ መስራት ይጠበቅበታል። በዚህ ልክ በርብርብ ሲሰራ ግብርናን በማሸጋገር ገበታን ከመሙላት ወይም ከፍጆታ አልፎ ገበያን ማማተር ይቻላል።
ለጊፋታ በዓል የምናደርገው ዝግጅት ቁጠባን፣ አብሮነት እና የሥራ ባህልን ለማጠናከር እያገዘን ነው---የወላይታ ዞን ነዋሪዎች
Sep 24, 2023 21
ወላይታ ሶዶ ፤ መስከረም 13/2016(ኢዜአ)፡-ለ"ጊፋታ" በዓል ዓመቱን ሙሉ የሚደረገው ዝግጅት የቁጠባ ባህላችንን ከማሳደግ ባለፈ አብሮነት እና የሥራ ባህልን ለማጠናከር እያገዘን ነው ሲሉ የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። "ጊፋታ" ቂምና ቁርሾን በማስወገድ ተስፋ፣ ልምላሜና የቀጣይ ስኬትን በማለምና በማቀድ የሚቀበሉት የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ ዓመቱን ሙሉ በሚደረግ ዝግጅት የሚከበር ሲሆን "ጊፋታ" በኩር፣ ታላቅ፣ መሻገር የሚል ትርጓሜም አለው። የብሔሩ ተወላጅ የሆኑ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶች፣ ልጆች ባላቸው የሥራ ክፍፍል የእርድ ሰንጋ መግዣ፣ የቅቤና ለሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ዕቁብ በማሰባሰብ ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግና የዘመን መለወጫን በዓሉን ለመቀበል ዓመቱን ሙሉ ይዘጋጃሉ። በበዓሉም በዓመቱ ጠንክሮ በመስራት ከሌሎች ልቆ የታየ ለሌሎች ተሞክሮ እንዲሆን ይሞገሳል፤ በዘፈንም ይወደሳል። በእዚህም ሁሉም በየተሰማራበት ጠንክሮ በመስራት ውጤታማ እንዲሆን ይበረታታል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለ”ጊፋታ” በዓል ዓመቱን ሙሉ የሚደርጉት ዝግጅት የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ነው የገለጹት። ከነዋሪዎቹ መካከል የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ፈለቀ እንዳሉት "ጊፋታ" ለዓመት በተያዘ ዕቅድ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎበት የሚከበር በዓል ነው። በወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሬ ታርዶ ቅርጫ እንደተከፋፈለ ለቀጣዩ ዓመት ቁጠባ እንደሚጀመር ገልጸው፣ ለዓመት በሚቆጠበው ገንዘብ ከበዓሉ ባለፈ ለሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች እንደሚውል ተናግረዋል። ይህም በዓሉ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑንም ገልጸዋል። ሴቶችም ለበዓሉ የሚያስፈልገውን የቂቤ እቁብ በወላይቲኛ "ኦይሳ ሹፋ" በመጣልና እንሰት ፍቆ በማዘጋጀት በዓሉ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳይፈጥር ዝግጅት ያደርጋሉ ያሉት ደግሞ የዞኑ ተወላጅ ወይዘሮ ጸጋ ፈንታ ናቸው። ይህም ወጪን በመቀነስና የቁጠባ ባህላቸውን ከማሳደግ ባለፈ ህብረትን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። የጊፋታ በዓል ከዘመን መለወጫነት ባለፈ የህዝቡን የቁጠባ ባህል ስለሚያሳድግ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ አስደሳች ጆርጌ በበኩላቸው ለጊፋታ ተብሎ የሚጣለው የገንዘብ፣ የቂቤ እና አይብ እቁብ በዓሉን ተረጋግቶ ከማክበር ባለፈ ለልጆቻቸው የትምህርትና ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። በሴቶች በኩል የሚደረገው ዝግጅት ቁጠባን እንዲለማመዱና ሕብረትን እንዲያጠናክሩ በማድረግ በዓሉ ኢኮኖሚያዊ ጫና ሳይፈጥር ለማክበር እንደሚረዳም ገልጸዋል። ይህም ከጥንት ጀምሮ በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የተለመደ የበዓሉ እሴት በመሆኑ ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እየተጠቀሙበት መሆኑንም ገልጸዋል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በበኩላቸው የ”ጊፋታ” በዓል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ፓለቲካዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ለበዓሉ ዓመቱን ሙሉ የሚደረገው ዝግጅትም የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ተሞክሮውን ለማስፋት ይሰራል ብለዋል። በዓሉ ህዝቡ የቀደመ የቁጠባ ባህል እንዳለው ከማሳየት በተጨማሪ ዕዳ ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር የሚያደርግበት እሴት ጭምር ያለበት መሆኑን ተናግረዋል። ሰላም፣ አንድነት፣ ይቅርታና ጠንክሮ መስራትን የሚያበረታታው የ”ጊፋታ” በዓል ዕሴቶቹ በአግባቡ ተይዘው ለትውልድ ከማሸጋጋር ባለፈ ለሀገር ልማትና ብልጽግና ሚናውን ለማላቅ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ሳሙኤል እንዳሉት የቁጠባ ባህሉ አቅም የሌላቸውን ከመደገፍ ጀምሮ በህብረተሰቡ ውስጥ አብሮነትን የሚያጠናክር ነው። የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የ”ጊፋታ” በዓል የፌዴራልና የክልል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የብሔሩ ተወላጆችና ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የመጡ እንግዶች በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ዛሬ በድምድቀት ተከብሯል።
ለችግሮች ሁሉ በምክክር መፍትሄ በመሻት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የጋራ ሃላፊነታችን ነው - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
Sep 24, 2023 83
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ በምክክር መፍትሄ በመሻት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የጋራ ሃላፊነታችን ሊሆን ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ገለጹ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም የሰላምና መረጋጋት ጉዳይ ላይ በማተኮር ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም ለጋራ ሀገራችን የጋራ መፍትሄ የማበጀት ጉዳይ ለማንም የሚተው ሳይሆን የሁላችንንም ጥረትና ትብብር የሚጠይቅ ነው ብለዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ገዥው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከ60 በላይ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ መሆኑን ጠቅሰው ለሀገራዊ አንድነትና ሰላም ከምንም በላይ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የአገር ሉዓላዊነትንና ህልውናን የሚገዳደር ችግር ሲያጋጥም ጉዳቱ የሀገርና አጠቃላይ የህዝብ በመሆኑ ሁላችንም የመፍትሄው አካል ሆነን መገኘት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የሰለጠነ የውይይት ባህልን በማዳበር የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ማጠናከርም ይገባል ነው ያሉት። በመሆኑም የግጭት ምክንያቶችን በመለየትና በንግግር መፍትሄ በመሻት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሁላችንም ዝግጁ መሆን አለብን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በምንም አጋጣሚ የሚፈጠር ችግር መፍትሄ አለው የሚሉት የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ፤ በንግግርና በይቅርታ ቅራኔዎችን በመፍታት ብሄራዊ መግባባት መፍጠር አለብን ብለዋል። በተለያዩ የዓለም አገራት የነበሩ ችግሮች በዘላቂነት የተፈቱት በመነጋገር በመሆኑ በኢትዮጵያም ችግሮች ሁሉ በሃይል ሳይሆን በውይይትና በንግግር ብቻ ሊፈቱ ይገባል ነው ያሉት። በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል።
አገር በቀል ባህሎችና እውቀቶች ለሰላምና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ፋይዳቸው የጎላ በመሆኑ ጠብቆ ማቆየት ይገባል--የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ታዳሚዎች
Sep 24, 2023 59
ቦንጋ፤ መስከረም13/2016(ኢዜአ)-፡ አገር በቀል ባህሎችና እውቀቶች ለሰላምና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ፋይዳቸው የጎላ በመሆኑ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉ በካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ላይ የታደሙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። የካፈቾ ብሔር የ2016 የዘመን መለወጫ (የመኔ ሸድዬ ባሮን) በዓል በቦንጋ ከተማ በፓናል ውይይት እና በባህል ፌስቲቫል ተከብሯል። የዘመን መለወጫ በዓሉ ከጥንት የካፋ ንጉስ ጀምሮ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበርና በካፋ ህዝብም ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው በዓል ነው። የአካባቢው ተወላጆችና ሌሎች እንግዶች በየዓመቱ መስከረም 12 እና 13 በበዓሉ ለመታደም ወደካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ይመጣሉ። በዘንድሮ የብሔሩ የዘመን መለወጫ በዓል ላይ ለመታደም ወደቦንጋ ከተማ ከመጡት መካከል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የመጡት የሺናሻ ብሔረሰብ ተወላጅ ወይዘሮ አስካለ አለቦሮ እንዱ ናቸው። በዓሉ የህዝቦችን አንድነት የሚያጠናክር በመሆኑ ለትውልድ ጠብቆ ለማስተላለፍ ተባብሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። በተለይም ለዘላቂ ሰላም ግንባታና አንድነት መጠናከር ያለውን እሴት አጐልብቶ መጠቀም ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉት ወይዘሮ አስካለ፣ አብሮነትን ለማጠንከር በበዓሉ መታደማቸውን ገልጸዋል። በዓሉ ሰላምና አብሮነትን ከማጠንከር ባለፈ በሥራ እና በምክንያታዊነት የሚያምን ትውልድ ከመፍጠር አንጻር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓሉን ለማክበር ከኦሮሚያ ክልል የመጡትና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ሻምበል ግርማ ማለቶ ናቸው። በየዓመቱ ወደአካባቢው መጥተው በዓሉን እንደሚያከብሩ ገልጸው፣ በዓሉን በአብሮነት ተሰባስቦ ከማክበር ባለፈ ለአካባቢው ልማትና እድገት በአንድነት መረባረብ እንደሚገባም ተናግረዋል። እንዲህ አይነት ባህሎች የህብረተሰቡን የእርስ በእርስ ትስስር ስለሚያጠናክሩ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም አቶ ግርማ ተናግረዋል። የመኔ ሸድዬ ባሮን በዓል ባህላዊ እሴት ሳይጠፋ ለረጅም ዘመናት ከትውልድ ወደትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱን የገለጸው የካባቢው ተወላጅ ወጣት ሙሉቀን መንገሻ በበኩሉ፣ በዓሉን ይበልጥ በማልማት ጠብቆ በማቆየት ለዓለም ማስተዋወቅ ይገባል ብሏል። የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ሰላምና አንድነት ከማጎልበት ባለፈ በውስጡ ያሉት ሰርቶ የመለወጥና ሌሎች እሴቶች ለትውልዱ ጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግሯል። "በመሆኑም በአግባቡ በመጠበቅና በማልማት ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋጋር ሁላችንም ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል" ብሏል። እንደ ወጣት ሙሉቀን ገለጻ ወጣቱ ወደውጭ ከማየት ይልቅ የአባቶቹን ባህልና ታሪክ በአግባቡ አውቆ፣ ከመጠበቅ ባለፈ አልምቶ መጠቀምና በማንነቱ መኩራት አለበት። ሌላኛው የአካባቢው ተወላጅ አቶ አሰፋ ማሙዶ በዓሉ በኃይማኖት፣ በዘር እና በፖለቲካ ልዩነት ሳይኖር በጋራ የሚከበር የአንድነት ተምሳሌት በዓል ነው። የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆና መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲሻገር ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል። በዓሉ የህዝቦች አንድነት እንዲጠነክር እና የሥራ ባህል እንዲጎለበት በማድረግ በኩል ያለውን ፋይዳ ለአካባቢውና ለሀገር ልማት ማዋል ይገባል ብለዋል። ከፓናል ውይይቱ በተጨማሪ በዞኑ ከሚገኙ 12 ወረዳዎችና አምስት ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ባህላዊ ፌስቲቫሎችን አቅርበዋል። ኑሯቸውን በተለያዩ አካባቢዎች ያደረጉ የአካባቢው ተወላጆች፣ ከአጎራባች ዞኖች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች
Sep 24, 2023 53
አዲስ አበባ ፤መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች፡፡ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው 49ኛው የጀርመን በርሊን ማራቶን ዛሬ ሲደረግ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአስደናቂ ብቃት አሸንፋለች። በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል ያሸነፈችው አትሌቷ ባለፈው ዓመትም የበርሊን ማራቶንን ማሸነፏ ይታወሳል ፡፡ በወንዶች ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ርቀቱን በበላይነት አጠናቋል፡፡
ፖለቲካ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናው አገራትን የሚያስተሳስር የልማት ፕሮጀክት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Sep 23, 2023 95
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016 (ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵዊያንና የቀጣናው አገራትን የሚያስተሳስር የልማት ፕሮጀክት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። አቶ ደመቀ ይህንን ያሉት በአሜሪካ ኒው-ዮርክ እየተካሄደ ባለው 78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ነው። በንግግራቸውም የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የአገራትን ትስስርን በማሳለጥም የዜጎችን ህይወት በማሻሻል የማይተካ ሚና እንዳለቸው ተናግረዋል። ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የዜጎችን ሕይወት በማሻሻልና የአገራትን ትስስር የሚያጠናከር ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ጎን ለጎንም በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄድ የሦስትዮሽ ድርድም ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል የሚል ጽኑ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና አለመረጋጋት ችግሮችን ለመፍታት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትብብር ይጠይቃል ብለዋል። ሱዳንም ከገባችበትን ውስጣዊ ችግር በሰላማዊ መንገድ እንደምትፈታ ያላቸውን እምነት ጠቁመው ኢትዮጵያም ለሱዳን ሰላምና ደኅንነት የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል። የሰላም ሂዳትን ለማጠናከር በትብብር መሥራት ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ደመቀ፤ ኢትዮጵያም ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባትን ኃላፊነት እንደምትወጣ አረጋግጠዋል። በዚህ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነትን የማረጋገጥ ገንቢ ሚናዋን በመወጣት በኢኮኖሚያዊ ትብብር ለተመሰረተ የልማት እንቅስቃሴ መሳለጥ በትኩረት እየሰራች እንደምትገኝ አንስተዋል። ከጉረቤት አገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት በማሳደግ በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቀጣናዊ የመሰረተ ልማት ውህደት እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝም አብራርተዋል። የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን ለመቅረፍም በትብብር ላይ የተመሰረተ የመፍትሔ አካሄድን መከተል አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።
መምሪያው ህዝቡን ደጀን አድርጎ ሰላም የማስጠበቁን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል
Sep 23, 2023 81
ድሬዳዋ፤ መስከረም 12 ቀን 2016(ኢዜአ)፡- የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ህዝቡን ደጀን በማድረግ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቁ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቅላይ መምሪያው ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ገለጹ። የተቀየረውን የአስተዳደሩ የመደበኛ ፖሊስ የደንብ ልብስ የማልበስ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል። ኮሚሽነር ዓለሙ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ፤ ፖሊስ ህዝብን ደጀን አድርጎ የድሬዳዋና የአካባቢዋን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ እየጠበቀ ነው። በድሬዳዋ በተከናወኑ የተቀናጁ ስራዎች ከለውጥ በፊት ሲከሰቱ የነበሩት የፀጥታ ችገሮች ተወግደው በአሁኑ ወቅት አስተማማኝ ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነር ዓለሙ ገለጻ ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን መመሪያ ተከትሎ የድሬዳዋ አስተዳደር የመደበኛ ፖሊስ የደንብ ልብስ እንዲለወጥ ተደርጓል። በፌደራል ፖሊስ የወጣውን ወጥ አደረጃጀትና የደንብ ልብስ መመሪያ ተከትሎ የፖሊስ ኃይሉን በተለያዩ ዘርፎች በማጠናከር የተጀመረውን የሰላምና የፀጥታ የማስከበር ስራ ያጠናክራል ብለዋል። የተለወጠው የመደበኛ ፖሊስ የደንብ ልብስ ዛሬ በተካሄደው የማልበስ ሥነ-ሥርዓት ላይ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮችና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የዓለም የጸጥታ ዘርፍ ቅኝት የሀገራትን ሉዓላዊነት ያከበረ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር እና አካታችነትን የተከተለ ሊሆን ይገባል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
Sep 23, 2023 104
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦ የዓለም የጸጥታ ዘርፍ ቅኝት የሀገራትን ሉዓላዊነት ያከበረ፣ የባለብዙ ወገን ትብብር እና አካታችነትን የተከተለ እንዲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ። አቶ ደመቀ ይህን ያሉት "ሰላም፣ ብልፅግና፣ ለውጥና ዘላቂነት" በሚል መሪ ሀሳብ በአሜሪካ ኒዮርክ እየተካሄደ ባለው 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ኢትየጵያ ለመንግስታቱ ድርጅት መመስረት ታሪካዊ ሚና እንደተጫወተች ሀገር የጋርዮሽ ዓለም እንዲኖር ትሻለች ብለዋል። የነበረው አካታች ያለሆነ መዋቅር የጋራ ፍላጎትን ለማስፈጸም የማያስችል በመሆኑ ሁላችንም በተባበረ መንገድ የባለብዙ ወገን ስርዓት ለመዘርጋት አቋም ሊኖረን ይገባል ብለዋል። አለም አቀፋዊ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን ከተፈለገ አዲሱ የዓለም የጸጥታ ስርዓት የአባል ሀገራትን ሉዓላዊነት ያከበረ መሆን እንዳለበት ኢትዮጵያ በጽኑ እንደምታምን ነው አቋሟን የገለጹት። ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት ሰላም ማስከር ተልዕኮ ስር ለዓለም ሰላም ቁልፍ ሚና እንደተጫወተ ሀገር የጸጥታው ምክር ቤት ሪፎርም የምርጫ ሳይሆን ፍጹም አስፈላጊ ጉዳይ እንደሆነ እንደምታምን ተናግረዋል። የጸጥታው ምክር ቤት አሳታፊ አና አካታች ሆኖ መዋቀር ያሻዋል ያሉት ምከት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተለይም በምክር ቤቱ ለአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ የመስጠት ጉዳይ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊና ፍትሃዊ ውሳኔ የመስጠት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ለአፍሪካ የሰላም ተልዕኮ በቂ የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት እና ለሀጋራት የህግ ማስከበር ስራዎች ስኬታማነት አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተጨማሪም የተናጠላዊ ማዕቀብ እና ተገቢ ያልሆኑ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች የመንግስታቱን ድርጅት መርህና አሰራር የሚጣረሱ በመሆኑ ኢትዮጵያ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚጣሉ መሰል እርምጃዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊነሱ ይገባል ብላ እንደምታምን አንስተዋል። በሉዓላዊ ሀገራት መካከል የሚፈጠሩ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በተናጠላዊ ማዕቀብ ሳይሆን በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በውይይት መፍታት አማራጭ መሆን እንደላበትም ነው ያነሱት። ኢትዮጵያና መሰል ታዳጊ ሀገራት የመንግስታቱ ድርጅት አጠቃላይ ቅርጽ መስተካከል እንዳለበት ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። አሁንም ይበልጥ አካታች፣ ውጤታማና ለብዝሀነት የተመቸ እንዲሁም ታዳጊ ሀገራትን ታሳቢ ያደረገ አሰራር መዘርጋት እንዳለበት ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የተቀላቀለችበት 'ብሪክስ' በዚህ ረገድ ትልቅ ምሳሌ መሆኑን አንስተዋል። በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለልማት ግቦች ስኬት የፋይናንስ አቅርቦት ቢኖርም በታዳጊ አገራት ግን ፍትሃዊነት የጎደለው በመሆኑ ይህንን ለማስተካከል አዲስ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እና ዓለም አቀፍ ትብብር ይፈልጋል ብለዋል። ኢትዮጵያ ሰላማዊና የበለጸገ ማህበረሰብ ለመገንባት የልማት ግቦችን ቀርጻ እየሰራች መሆኗን ጠቅሰው፤ ለዚህ ግን አዲስ የሆነ አካታች ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስርዓት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላምና ዴሞክራሲ መስፈን ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ችግር የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ የመፍታት መርህ በፕሪቶሪያ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መፍታት መቻሉን ለአብነት አንስተዋል። ስምምነቱ በመልካም አፈጻጸም ላይ መሆኑን ጠቀስው፣ ከሰላም ስምምነቱ ባሸገርም በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ፣ የሽግግር ፍትህ ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ለኢትዮጵያዊያን የተሻለ እና ብሩህ ነገ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አገራዊ ምክክሩን በስኬት ለማካሄድ ሕዝቡ ተሳትፎውን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ
Sep 23, 2023 68
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦አገራዊ ምክክሩን በስኬት ለማካሄድ ሕዝቡ ተሳትፎውን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ለውይይት የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የሚለዩና በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮችን ምርጫ ከመስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ወረዳዎች እያከናወነ ነው። በዛሬው ዕለትም በጉለሌና ልደታ ክፍለ ከተማ በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮች ምርጫ ተከናውኗል። በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መርኃ-ግብር የተገኙት ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ፤ ሁሉን ያሳተፈ አገራዊ ምክክር ለማካሄድ በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ ተወካዮችን የመምረጥ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ይህም በአገር ደረጃ የማያግባቡ ልዩነቶችን ከመሠረቱ በመለየት በሕዝብና መንግሥት እንዲሁም በሕዝቦች መካከል መተማመን ለመፍጠርና ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። ሕብረተሰቡም ተወካዮችን ለመምረጥ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልና ከመምረጥ ጎን ለጎንም ለሚመርጡ ተወካዮች መነሻ የአጀንዳ ሃሳብ በመስጠት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። በልደታ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ለአጀንዳ ልየታ ተወካዮች ምርጫ የተገኙት ኮሚሽነር ዶክተር ተገኝወርቅ ጌቱ በበኩላቸው፤ ሕብረተሰቡ በአገራዊ ምክክሩ አጠቃላይ ሂደት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። በልደታ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መርኃ-ግብር የተገኙት ወይዘሮ ፋናዬ መንግሥቱ፤ አገሪቱን ከተለያዩ ተግዳሮቶች ለማውጣት ሁሉም ማኅበረሰብ የኮሚሽኑን ጥረት መደገፍ አለበት ብለዋል። የኢትዮጵያ ሠላም የሁሉም ሠላም መሆኑን ገልጸው፤ መድረኩ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ መሆኑን የተገነዘብንበት ነው ብለዋል። በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መርኃ-ግብር የተሳተፉት አቶ ወንድወሰን አጎናፍር በበኩላቸው፤ በሁሉም የምርጫ መዋቅር አካታች ምርጫ መካሄዱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔድ የተናጥል ማዕቀብን አትደግፍም-አቶ ደመቀ መኮንን
Sep 23, 2023 106
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2016 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔዱ የተናጥል ማዕቀቦችን እንደማትደግፍ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የመንግስታቱ ድርጅት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔዱ የተናጥል ማዕቀቦችንና የኢኮኖሚ ተጽእኖዎችን ትቃወማለች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርሆዎችንና ዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጻጸር በመሆኑም ድርጊቶ ሊቆም እንደሚገባ ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አደረጉ
Sep 23, 2023 110
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የመንግስታቱ ድርጅት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ሃገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮችን ዳሰዋል። የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እና የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትን ገቢራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት፣ አለምአቀፍ ሰላም እና ፀጥታ ፣ ዘላቂ ልማት ግቦች ፣ የአለም የአየር ንብረት በንግግራቸው የተዳሰሱ ጭብጦች ነበሩ። ኢትዮጵያ የአስር አመት የልማት እቅዷን ከተባበሩት መንግስታት ዘላቂ የልማት ግቦች ጋር አጣጥማ በመቅረፅ እየተገበረች ትገኛለች ያሉት አቶ ደመቀ፤ የአለም አየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የተቀናጀ ስራ እያከናወነች እንደምትገኝም አንስተዋል። ለአብነትም የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በማንሳት በገጠርና በከተሞች ከአካባቢ ጋር የተቆራኙ የልማት ስራዎችን በማስፋፋት ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። እ.አ.አ. በ2030 ለማሳካት የታቀዱትን ዘላቂ የልማት ግቦች የእስከ አሁን አፈፃፀማቸው አመርቂ አለመሆኑን የጠቀሱ ሲሆን በቀሩት ጊዜያት የተሻለ ስኬት እንዲኖር የፓለቲካ ቁርጠኝነት እና አዲስ አለምአቀፍ ትብብር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አቶ ደመቀ ድህረ ፕሪቶሪያ ያለውን የሰላም ስምምነት አተገባበር ያነሱ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ስኬታማ ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። የሽግግር ፍትህን ለማረጋገጥ ፖሊሲ ተረቆ በሃገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እንደተደረገ የጠቀሱ ሲሆን እርቅ ፣ እውነትን ለማፈላግለግ እና ተጠያቂነትን እውን ለማድረግ መንግስት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ የአለም አየር ንብረት ለውጥ በአዳጊ ሃገራት ላይ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት እስከ 2030 ድረስ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ የተቀመጠው እቅድ እየተሳካ እንዳልሆነ አንስተዋል። በቀጣይ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚካሄደው የአለም አየር ንብረት ጉባኤ ሃገራት ተግባራዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለተልዕኮው ስኬታማነት ተቋማዊ ማሻሻያን ማድረግ አማራጭ ሳይሆን አስፈላጊ ነው ብላ ኢትዮጵያ እንደምታምን አቶ ደመቀ የገለፁ ሲሆን ፤ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀጫ እንዲኖራትም በአህጉር ደረጃ የተያዘው አቋሞ ተገቢነትን አንስተዋል። ኢትዮጵያ በሰላም እና ልማት ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ አጠናክራ የማስቀጠል ፍላጎት እንዳላት ያነሱ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የጋራ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኗንም አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአካባቢው ሃገራት ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል የሚያግዝ ተምሳሌታዊ የልማት ፕሮጀክት እንደሆነም አቶ ደመቀ መኮንን አንስተዋል።
የአገር መከላከያ ሠራዊት በሠላም ማስከበር ተልዕኮ ያተረፈውን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስምና ዝና አስጠብቆ ይቀጥላል - ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ
Sep 23, 2023 102
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ያተረፈውን ውጤታማ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስምና ዝና አስጠብቆ እንደሚቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ ገለጹ። ዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በግጭት አፈታትና ሠላም ማስከበር ሙያ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች አስመርቋል። በዚሁ ወቅት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ የሠላም ማስከበር ግዳጅ ከበሬታ የተጎናጸፈች አገር ናት ብለዋል። በቀጣይም የዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮን በብቃት በመወጣት ሠራዊቱ በሚሰማራበት ቦታ ሁሉ በመስዋዕትነቱ ያተረፈውን የከበረ ስምና ዝና ተጠብቆ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖቹም ቀጣይ የሚሰጣቸውን ወታደራዊ ግዳጅ በብቃት በመወጣት የአገራቸውን ታሪካዊ የሠላም ማስከበር ውጤታማ የግዳጅ አፈጻጸም ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የመከላከያ ሠራዊት የሠላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ፤ መከላከያ ባካሄደው የለውጥ እርምጃ የሠራዊቱን አቅም ማጎልበት የሚያስችል ትምህርትና ሥልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ በግጭት አፈታትና ሠላም ማስከበር ሙያ ብቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን በማሰልጠን ዛሬ ለምርቃት ማብቃታቸውን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ፤ ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር በሁለንተናዊ ዘርፎች የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ዘርፍ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አገር መሆኗን ጠቁመው፤ ኢንስቲትዩቱ የሚያስመርቃቸው ሙያተኞችም በሠላም ማስከበር የአመራር ቦታዋን ለማስጠበቅ ጉልህ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። የዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዛዥ ኮሎኔል ደመቀ መንግሥቱ፤ ተቋሙ በግጭት አፈታትና ሠላም ማስከበር ሙያ ብቃት ያላቸው የጦር መኮንኖችን እያፈራ ነው ብለዋል። ተመራቂዎቹም የሚፈለገውን መስፈርት በማሟላት ሦስት ከጎረቤት አገራት የመጡ መኮንኖችን ጨምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ 20 ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን በሁለተኛ ዲግሪ ማስመረቁን አስታውቀዋል። ተመራቂ ከፍተኛ የጦር መኮንኖቹም ለሁለት ዓመታት ሲከታተሉት የቆዩት ትምህርትና ሥልጠና የቀጣይ ግዳጃቸውን በእውቀትና በብቃት መወጣት የሚያስችል ግንዛቤ መያዛቸውን ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ በግጭት አፈታትና ሠላም ማስከበር በሁለተኛ ዲግሪ ሥልጠናውን የሰጠው ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) ባደረገው የቴክኒክ ድጋፍና የጃፓን መንግሥት ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነ ተገልጿል። በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ተወካዮችና ወታደራዊ አታሼዎች ጨምሮ የተመራቂ ቤተሰቦችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ማህበራዊ
አገር በቀል ባህሎችና እውቀቶች ለሰላምና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ፋይዳቸው የጎላ በመሆኑ ጠብቆ ማቆየት ይገባል--የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ታዳሚዎች
Sep 24, 2023 59
ቦንጋ፤ መስከረም13/2016(ኢዜአ)-፡ አገር በቀል ባህሎችና እውቀቶች ለሰላምና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ፋይዳቸው የጎላ በመሆኑ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉ በካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ላይ የታደሙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። የካፈቾ ብሔር የ2016 የዘመን መለወጫ (የመኔ ሸድዬ ባሮን) በዓል በቦንጋ ከተማ በፓናል ውይይት እና በባህል ፌስቲቫል ተከብሯል። የዘመን መለወጫ በዓሉ ከጥንት የካፋ ንጉስ ጀምሮ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበርና በካፋ ህዝብም ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው በዓል ነው። የአካባቢው ተወላጆችና ሌሎች እንግዶች በየዓመቱ መስከረም 12 እና 13 በበዓሉ ለመታደም ወደካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ይመጣሉ። በዘንድሮ የብሔሩ የዘመን መለወጫ በዓል ላይ ለመታደም ወደቦንጋ ከተማ ከመጡት መካከል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የመጡት የሺናሻ ብሔረሰብ ተወላጅ ወይዘሮ አስካለ አለቦሮ እንዱ ናቸው። በዓሉ የህዝቦችን አንድነት የሚያጠናክር በመሆኑ ለትውልድ ጠብቆ ለማስተላለፍ ተባብሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። በተለይም ለዘላቂ ሰላም ግንባታና አንድነት መጠናከር ያለውን እሴት አጐልብቶ መጠቀም ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉት ወይዘሮ አስካለ፣ አብሮነትን ለማጠንከር በበዓሉ መታደማቸውን ገልጸዋል። በዓሉ ሰላምና አብሮነትን ከማጠንከር ባለፈ በሥራ እና በምክንያታዊነት የሚያምን ትውልድ ከመፍጠር አንጻር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓሉን ለማክበር ከኦሮሚያ ክልል የመጡትና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ሻምበል ግርማ ማለቶ ናቸው። በየዓመቱ ወደአካባቢው መጥተው በዓሉን እንደሚያከብሩ ገልጸው፣ በዓሉን በአብሮነት ተሰባስቦ ከማክበር ባለፈ ለአካባቢው ልማትና እድገት በአንድነት መረባረብ እንደሚገባም ተናግረዋል። እንዲህ አይነት ባህሎች የህብረተሰቡን የእርስ በእርስ ትስስር ስለሚያጠናክሩ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም አቶ ግርማ ተናግረዋል። የመኔ ሸድዬ ባሮን በዓል ባህላዊ እሴት ሳይጠፋ ለረጅም ዘመናት ከትውልድ ወደትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱን የገለጸው የካባቢው ተወላጅ ወጣት ሙሉቀን መንገሻ በበኩሉ፣ በዓሉን ይበልጥ በማልማት ጠብቆ በማቆየት ለዓለም ማስተዋወቅ ይገባል ብሏል። የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ሰላምና አንድነት ከማጎልበት ባለፈ በውስጡ ያሉት ሰርቶ የመለወጥና ሌሎች እሴቶች ለትውልዱ ጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግሯል። "በመሆኑም በአግባቡ በመጠበቅና በማልማት ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋጋር ሁላችንም ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል" ብሏል። እንደ ወጣት ሙሉቀን ገለጻ ወጣቱ ወደውጭ ከማየት ይልቅ የአባቶቹን ባህልና ታሪክ በአግባቡ አውቆ፣ ከመጠበቅ ባለፈ አልምቶ መጠቀምና በማንነቱ መኩራት አለበት። ሌላኛው የአካባቢው ተወላጅ አቶ አሰፋ ማሙዶ በዓሉ በኃይማኖት፣ በዘር እና በፖለቲካ ልዩነት ሳይኖር በጋራ የሚከበር የአንድነት ተምሳሌት በዓል ነው። የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆና መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲሻገር ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል። በዓሉ የህዝቦች አንድነት እንዲጠነክር እና የሥራ ባህል እንዲጎለበት በማድረግ በኩል ያለውን ፋይዳ ለአካባቢውና ለሀገር ልማት ማዋል ይገባል ብለዋል። ከፓናል ውይይቱ በተጨማሪ በዞኑ ከሚገኙ 12 ወረዳዎችና አምስት ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ባህላዊ ፌስቲቫሎችን አቅርበዋል። ኑሯቸውን በተለያዩ አካባቢዎች ያደረጉ የአካባቢው ተወላጆች፣ ከአጎራባች ዞኖች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
የጋሞ፣ የጊድቾ እና የዘይሴ ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው
Sep 24, 2023 37
አርባ ምንጭ መስከረም 13/2016 (ኢዜአ) ፦ የጋሞ፣ የጊድቾና የዘይሴ ብሔረሰቦች "ዮ--ማስቃላ"፣ "ባላ ካዳቤ" እና "ቡዶ ከሶ" የዘመን መለወጫ በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው። የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ለኢዜአ እንደገለጹት በዓሉ "ባህላችን ለዘላቂ ሰላምና ልማት" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ባህላዊ ኩነቶችና አውደ ጥናት እየተከበረ ነው። በዓሉ የዘመን መለወጫ ከመሆኑ በተጨማሪ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ በዓል መሆኑንም ገልጸዋል። በበዓሉ ህዝቡ ዓመቱን ሙሉ ጠብቆ ያቆየውን ፈጣሪውን ከማምስገን ባለፈ የእርቅና የይቅርታ መሆኑንም ገልጸዋል። አቶ ሞናዬ እንዳሉት በበዓሉ የመስቀል ደመራ ባህላዊ እሴቶች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል። በተጨማሪም የባህል ተምሳሌትና የህፃናት አጋዥ ማስተማሪያ መጻህፍት እንደሚመረቁ አመልክተዋል። የባህል ቅርስ እና የግብርና ምርቶችን የሚያስተዋወቅ ኤግዚቢሽን ለበዓሉ ታዳሚዎች ክፍት ሆኗል። በበዓሉ ላይ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የመንግስት ሥራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከአጎራባች ዞኖች እና ወረዳዎች የተጋበዙ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) በቦንጌ ሽምበቶ እየተከበረ ነው
Sep 24, 2023 42
ቦንጋ ፤ መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ የ2016 የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) ቦንጋ ከተማ በቦንጌ ሽምበቶ እየተከበረ ነው። የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) ቦንጋ ከተማ በበዓሉ መከበሪያ ቦታ በቦንጌ ሽምበቶ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በታላቅ ድምቀት መከበር ጀምሯል። የካፈቾ ብሔር ባህላዊ ምክር ቤት አባላት በባህላዊ አልባሳት አጊጠውና ባህላዊ ስርዓታቸውን በጠበቀ መልኩ በወጣቶችና አረጋዊያን ታጅበው በዓሉ በሚከበሩበት ቦታ ተገኝተዋል። በአሉ የይቅርታና የዕርቅ እንዲሁም የአብሮነትና አንድነት ተምሳሌት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የ"ጊፋታ" በዓል እሴቶች እንዲለሙ በትኩረት ይሰራል- አቶ ቀጄላ መርዳሳ
Sep 24, 2023 53
ወላይታ ሶዶ ፤መስከረም 13/2016(ኢዜአ)፡- የጊፋታ ባህላዊ እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች እንዲለሙና እንዲጠበቁ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ። የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የመቻቻል እሴት የሆነውን የ"ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው። በዓሉን ለመታደም ወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም የተገኙት የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ እንዳሉት የወላይታ ብሔር የበርካታ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኑን ተናግረዋል። ወላይታ ቀደምትና አኩሪ ከሆኑ ትውፊቶች የሚጠቀሱ ባህሎች ባለቤት መሆኑን አንስተው፤ የበዓሉ ባህላዊ እሴቶቹ ለምተውና ጎልብተው መውጣት ይገባቸዋል ብለዋል። የ"ጊፋታ" በዓል ባህላዊ ቅርሶችና ሀገር በቀል እውቀቶች እንዲለሙና እንዲጠበቁ በሚሰራው ስራ የሚኒስቴሩ ድጋፍ እንደማይለየው አንስተዋል። የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ የ"ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በታላቅ ድምቀት በመከበር ላይ ነው።
ኢኮኖሚ
ለጊፋታ በዓል የምናደርገው ዝግጅት ቁጠባን፣ አብሮነት እና የሥራ ባህልን ለማጠናከር እያገዘን ነው---የወላይታ ዞን ነዋሪዎች
Sep 24, 2023 21
ወላይታ ሶዶ ፤ መስከረም 13/2016(ኢዜአ)፡-ለ"ጊፋታ" በዓል ዓመቱን ሙሉ የሚደረገው ዝግጅት የቁጠባ ባህላችንን ከማሳደግ ባለፈ አብሮነት እና የሥራ ባህልን ለማጠናከር እያገዘን ነው ሲሉ የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። "ጊፋታ" ቂምና ቁርሾን በማስወገድ ተስፋ፣ ልምላሜና የቀጣይ ስኬትን በማለምና በማቀድ የሚቀበሉት የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ ዓመቱን ሙሉ በሚደረግ ዝግጅት የሚከበር ሲሆን "ጊፋታ" በኩር፣ ታላቅ፣ መሻገር የሚል ትርጓሜም አለው። የብሔሩ ተወላጅ የሆኑ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶች፣ ልጆች ባላቸው የሥራ ክፍፍል የእርድ ሰንጋ መግዣ፣ የቅቤና ለሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ዕቁብ በማሰባሰብ ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግና የዘመን መለወጫን በዓሉን ለመቀበል ዓመቱን ሙሉ ይዘጋጃሉ። በበዓሉም በዓመቱ ጠንክሮ በመስራት ከሌሎች ልቆ የታየ ለሌሎች ተሞክሮ እንዲሆን ይሞገሳል፤ በዘፈንም ይወደሳል። በእዚህም ሁሉም በየተሰማራበት ጠንክሮ በመስራት ውጤታማ እንዲሆን ይበረታታል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለ”ጊፋታ” በዓል ዓመቱን ሙሉ የሚደርጉት ዝግጅት የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ነው የገለጹት። ከነዋሪዎቹ መካከል የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ፈለቀ እንዳሉት "ጊፋታ" ለዓመት በተያዘ ዕቅድ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎበት የሚከበር በዓል ነው። በወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሬ ታርዶ ቅርጫ እንደተከፋፈለ ለቀጣዩ ዓመት ቁጠባ እንደሚጀመር ገልጸው፣ ለዓመት በሚቆጠበው ገንዘብ ከበዓሉ ባለፈ ለሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች እንደሚውል ተናግረዋል። ይህም በዓሉ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑንም ገልጸዋል። ሴቶችም ለበዓሉ የሚያስፈልገውን የቂቤ እቁብ በወላይቲኛ "ኦይሳ ሹፋ" በመጣልና እንሰት ፍቆ በማዘጋጀት በዓሉ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳይፈጥር ዝግጅት ያደርጋሉ ያሉት ደግሞ የዞኑ ተወላጅ ወይዘሮ ጸጋ ፈንታ ናቸው። ይህም ወጪን በመቀነስና የቁጠባ ባህላቸውን ከማሳደግ ባለፈ ህብረትን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። የጊፋታ በዓል ከዘመን መለወጫነት ባለፈ የህዝቡን የቁጠባ ባህል ስለሚያሳድግ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ አስደሳች ጆርጌ በበኩላቸው ለጊፋታ ተብሎ የሚጣለው የገንዘብ፣ የቂቤ እና አይብ እቁብ በዓሉን ተረጋግቶ ከማክበር ባለፈ ለልጆቻቸው የትምህርትና ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። በሴቶች በኩል የሚደረገው ዝግጅት ቁጠባን እንዲለማመዱና ሕብረትን እንዲያጠናክሩ በማድረግ በዓሉ ኢኮኖሚያዊ ጫና ሳይፈጥር ለማክበር እንደሚረዳም ገልጸዋል። ይህም ከጥንት ጀምሮ በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የተለመደ የበዓሉ እሴት በመሆኑ ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እየተጠቀሙበት መሆኑንም ገልጸዋል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በበኩላቸው የ”ጊፋታ” በዓል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ፓለቲካዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ለበዓሉ ዓመቱን ሙሉ የሚደረገው ዝግጅትም የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ተሞክሮውን ለማስፋት ይሰራል ብለዋል። በዓሉ ህዝቡ የቀደመ የቁጠባ ባህል እንዳለው ከማሳየት በተጨማሪ ዕዳ ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር የሚያደርግበት እሴት ጭምር ያለበት መሆኑን ተናግረዋል። ሰላም፣ አንድነት፣ ይቅርታና ጠንክሮ መስራትን የሚያበረታታው የ”ጊፋታ” በዓል ዕሴቶቹ በአግባቡ ተይዘው ለትውልድ ከማሸጋጋር ባለፈ ለሀገር ልማትና ብልጽግና ሚናውን ለማላቅ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ሳሙኤል እንዳሉት የቁጠባ ባህሉ አቅም የሌላቸውን ከመደገፍ ጀምሮ በህብረተሰቡ ውስጥ አብሮነትን የሚያጠናክር ነው። የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የ”ጊፋታ” በዓል የፌዴራልና የክልል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የብሔሩ ተወላጆችና ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የመጡ እንግዶች በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ዛሬ በድምድቀት ተከብሯል።
ኩባንያው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የምታስገባውን የታጠበ የድንጋይ ከሰል በሀገር ውስጥ መተካት የሚያስችል ስራ ጀምሯል- ዮ ሆልዲንግ ንግድ እና ማኑፋክቸሪንግ
Sep 23, 2023 68
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የምታስገባውን የታጠበ የድንጋይ ከሰል በሀገር ውስጥ የሚተካ ፋብሪካ አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ዮ ሆልዲንግ ንግድ እና ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘው ሀገር በቀል ኩባንያ አስታወቀ። 'ዮ ሆልዲንግ ንግድ እና ማኑፋክቸሪንግ' የተሰኘው ሀገር በቀል ኩባንያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የድንጋይ ከሰል እጥበት ፋብሪካ ገንብቶ ወደ ምርት መግባቱን የኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል። ኩባንያው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታወጣበትን የድንጋይ ከሰል ምርት የማቀነባበር ሥራውን ይበልጥ ለማሳደግ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ውል ለማሰር በሂደት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል። የኩባንያው ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አታክልቲ ተስፋዬ እንዳሉት፤ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2019 በግማሽ ቢሊየን ብር ካፒታል ያቋቋመው ዮ ሆልዲንግ ሥራ ጀምሯል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገነባው የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ከውጭ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ሲጠይቅ የኖረውን የታጠበ የድንጋይ ከሰል ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ውስጥ ማቀነባበር ጀምሯል ብለዋል። የድንጋይ ከሰል ማምረትና ማቀነባበር ሂደቱን ለማሳለጥ እና የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ለማምጣት የካበተ ልምድ ካላቸው የውጭ ኩባንያዎች ጋር ለመሥራት የሚያስችል ውል ለማሰር ዝግጅት አጠናቋል ብለዋል። ፋብሪካው አሁን ላይ የሲሚንቶ፣ የብረት፣ የወረቀት፣ የሴራሚክ፣ የጂፕሰም እና ሌሎች ፋብሪካዎች ግብዓትነት የሚውል በዓመት 1 ሚሊየን ቶን የታጠበ የድንጋይ ማቅረብ እንደሚችል ጠቅሰዋል። እስካሁን ለ200 ኢትዮጵያውያን ቀጥተኛ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልፀው፤ ግብዓቱን ለተለያዩ ፋብሪካዎች በቀላሉ ማቅረብ የሚችል ነው ብለዋል። የኩባንያው የግብይትና ቢዝነስ ልማት ኦፊሰር ይታሰብ ደጉ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው ወደ ሙሉ የማምረት አቅም ሲገባ 2 ነጥብ 16 ሚሊየን ቶን በዓመት የታጠበ የድንጋይ ከሰል እንደሚያቀርብም ጠቁመዋል። ፋብሪካው አገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ጫና የማቃለል እና በሂደትም ወደ ውጭ በመላክ ገቢ የማምጣት ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል። የኩባንያው የአቅርቦት ሰንሰለት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ፍቅሬ በበኩላቸው፤ በዮ ሆልዲንግ ብቻ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2020 በተጠቀሰ መረጃ ከውጭ የምታስገባውን የታጠበ የድንጋይ ከሰል 95 በመቶ ለመሸፈን ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል። በዮ ሆልዲንግ ተሳትፎ ብቻ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ እስከ 5ኛ ደረጃ ከሰል አቅራቢ ሀገር እንድትሆን እንደሚያደርግም ነው የሥራ ኃላፊዎቹ የጠቀሱት። የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ኤፍሬም ታደሰ በበኩላችው፤ ፋብሪካው በክልሉ 7ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ድንጋይ ከሰል ለማውጣት ፈቃድ ወስዷል። ድርጅቱ ባደረገው ጥናት በሥፍራው ከ40 እስከ 50 ዓመት የሚያቆይ የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳለው ተናግረዋል። በዮ ሆልዲንግ የማዕድን ዘርፍ አስተባባሪ ኤርሚያስ ወልዴ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው በአካባቢው ብክለት ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንዳያሳድር የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑን ገልፀዋል። የከሰል ማውጫ ሥፍራዎችና አካባቢውን መልሶ በማልማት የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።
በአማራ ክልል 250ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ ነው- የክልሉ ግብርና ቢሮ
Sep 23, 2023 63
ባህርዳር መስከረም 12/2016 (ኢዜአ)... በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወቅት 250ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው የዞን አመራሮችና ባለሙያዎችን ያሳተፈ ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን የገመገመና የቀጣይ አቅጣጫዎች ያስቀመጠ የውይይት መድረክ ዛሬ በባህርዳር አካሂዷል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ በዘንድሮው የበጋ ወቅት 250 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ በማልማት 10 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል። በመስኖ ስንዴ ልማቱ የሚሳተፉ አርሶ አደሮችን በመደገፍና በማበረታት በክልሉ ያለውን የከርሰና የገፀ ምድር የውሃ ሃብትን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ ይደረጋል ብለዋል። በተለይ በዚህ ዓመት አዲስ ወደ ልማት የሚገቡና ቀደም ሲል የገቡ ዘመናዊ የመስኖ ግድቦችንና የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን በመጠቀም ዕቅዱን ለማሳካት በቅንጅት እንደሚሰራ አስረድተዋል። የበጋ ስንዴ መስኖ ልማቱ ውጤታማ እንዲሆን ከግማሽ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያና ከ200 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ እንደሚውልም ተናግረዋል። አርሶ አደሩም የዘር እጥረት እንዳይገጥመው ባለፈው ዓመት ካመረተው ዘር እርስ በርስ በመለዋወጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱን እንዲያከናውን ጥረት ይደረጋል ብለዋል። የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካ በየደረጃው ያለው አመራር፣ የግብርና ባለሙያና አርሶ አደሩ የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርግ አቶ አጀበ አሳስበዋል። የዝናብ ስርጭት መቆራረጥን ጨምሮ በሌሎች ምክንያቶች በመኽር ልማቱ ለያጋጥም የሚችለውን የምርት መቀነስ በመስኖ ልማቱ ለማካካስ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ ቀኝአዝማች መስፍን እንዳሉት በዞኑ በዘንድሮው የበጋ ወቅት 26 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት 1 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ምርት ታቅዷል። አያይዘውም የአፈር ማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትን እንዳያጋጥም ከሚመለከተው አካል ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሰሜን ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ በቀለ ወርቁ በበኩላቸው ዞኑ አዲስ የተቋቋመ ቢሆንም ራሱን በሰው ሃይልና በስራ መሳሪያዎች አደራጅቶ ዕቅዱን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ዞኑ ለመስኖ ልማት አመቺ በመሆኑ አርሶ አደሩ ያለውን የውሃ ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት እንደሚደረግም ተናግረዋል በክልሉ በቀዳሚው ዓመት በበጋ መስኖ ስንዴ ከለማው 213 ሺህ ሄክታር መሬት 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በቡናው ዘርፍ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት የተሻለ ምርት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ርብርብ ይደረጋል- ባለሥልጣኑ
Sep 23, 2023 82
ቦንጋ፤ መስከረም 12/ 2015 (ኢዜአ)..በያዝነው በጀት ዓመት በቡናዉ ዘርፍ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት የተሻለ ምርት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አሳሰበ። "የቡና ምርት ጥራት ለጋራ ብልጽግናችን" በሚል መርህ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሄዷል። በዚህ ወቅት የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር እንዳሉት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ አረዳድ ይዘው ከምርት ጥራትና ሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት ለማቅረብ ሊረባረቡ ይገባል። በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበው የቡና ምርት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው በተያዘው በጀት ዓመት 350 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን አስታውቀዋል። ዓምና ለውጭ ገበያ ከቀረበው የቡና ምርት ውስጥ የኦሮሚያና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመዋል። ከነዚህ ክልሎች በ2016 የምርት ዘመን የተሻለና ጥራቱን የጠበቀ ደረጃ አንድ፣ ደረጃ ሁለትና ደረጃ ሶስት ምርት በብዛት ማቅረብ እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል። ከብድር፣ ከሰርተፊኬሽን ማዕከል ፣ ከኬሻና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸውው አካላት ጋር በመቀናጀት እልባት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ተወካይ አቶ ዮሐንስ መላኩ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ክልሉን በሰፊው እየደገፈ መሆኑን በጠንካራነት አንስተዋል። በቀጣይም ይበልጥ ተቀራርቦ በመስራት በቡናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ቡናን በብዛትና በጥራት ለማቅረብ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በቡና ግብይት ዙሪያ ከዘርፉ ተዋናዮች የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራ ጠቅሰው በክልሉ የሚገኙ አምራቾችን፣ አቅራቢ ባለሀብቶችን እና አርሶ አደሮችን አቅም በመገንባት በጥራት ዙሪያ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ይሰራል ብለዋል። የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ ኩጁአብ በቡና ዘርፍ አርሶ አደሩ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ። በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት 64 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ተቅዶ 42 ሺህ ቶን መቅረቡን ጠቁመው የምርት መጠን መቀነስ፣ የአለም የቡና ዋጋ መውረድ እና ህገወጥ የቡና ዝውውር መበራከትና ሌሎች ጉዳዮችን ለዕቅዱ አለመሳካት በምክንያትነት አንስተዋል። ይህንን ዝቅተኛ አፈጻጸም በያዝነው በጀት ዓመት በማሻሻል 69 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በጥራት ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በሌላ በኩል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህገ ወጥ የቡና ግበይትን ለመከላከል በተደረገ ቁጥጥር 138 ሺህ ቶን ቡና መያዙን ገልጸው 128 ሺህ ቶኑን በህጋዊ መንገድ በመሸጥ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን ተናግረዋል። ከመድርኩ ተሳታፊዎች መካከል የቡና አልሚና ላኪ አቶ ዝናቡ አባመጫ እንዳሉት ለቡና ጥራት መጓደል ሁሉም የዘርፉ ተዋናዮች ድርሻ አላቸው ብለዋል። ቡናን በጥራት እያመረቱ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን ገልፀው በአካባቢያቸው ከሚገኙ 260 አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠር የስልጠና፣ የግብዓት እንዲሁም የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አውደ-ርዕዩ በዘርፉ ያካበተ ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እድል ፈጥሯል - የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Sep 22, 2023 200
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 11/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ለአንድ ወር የተካሄደው የውኃና ኢነርጂ አውደ-ርዕይ በዘርፉ ያካበተ ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እድል መፍጠሩን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር "የውኃ ኃብታችን ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ኃሳብ በሳይንስ ሙዚየም ለአንድ ወር ያካሄደው አውደ ርዕይ ትላንት ተጠናቋል። አውደ ርዕዩ ምን አስገኘ? የሚለውን ለማወቅ ኢዜአ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በአውደ-ርዕዩ አገልግሎታቸውን ያቀረቡ ተቋማትን አነጋግሯል። በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ጌጡ፤ በአውደ-ርዕዩ ዘርፉን ለማዘመን በትግበራ ላይ ያሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል ብለዋል። ለአብነትም ኢትዮጵያ የውኃ መጠኗን በዲጂታል መተግበሪያ በመታገዝ እንዴት እንደምትከታተልና እንደምትቆጣጠር ማሳየት መቻሏን ጠቁመዋል። አውደ-ርዕዩን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጨምሮ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም አምባሳደሮች መጎብኘታቸውን ነው ያረጋገጡት። በመሆኑም አውደ-ርዕዩ አገሪቱ በዘርፉ የምታከናውነውን ሥራ ለማስገንዘብ እድል ሰጥቷል ነው ያሉት። ከዚህ በተጠማሪም አውደ-ርዕዩ በዘርፉ ከተለያዩ ተቋማት ጋር አዳዲስ አጋርነትና ትብብር ለመመሥረት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ገልጸዋል። በመድረኩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ያቀረቡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በበኩላቸው አውደ-ርዕዩ የውኃና ኢነርጂ ዘርፍን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሠሯቸውን ሥራዎች ለሕዝብ ለማቅረብ እድል ሰጥቶናል ብለዋል። በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በመረጃና ክላይማቶሎጂ ክፍል ተመራማሪ የሆኑት ለታ በቀለ ተቋማቸው በአውደ-ርዕዩ በአገሪቱ ያለውን የአየር ፀባይ ሁኔታ ጥናት ለማካሄድ የሚጠቀምባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አውደ-ርዕዩን መጎብኘታቸው ገልጸው ይህም በቀጣይ በሚቲዎሮሎጂ ዘርፍ አብረው መሥራት የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ለመለየት ዕድል መፍጠሩን ነው የገለጹት። የአነጋ ኢነርጃይዝ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሽያጭ ባለሙያ እየሩሳሌም ደጀኔ በበኩሏ በአውደ-ርዕዩ ኅብረተሰቡ የሚጠቀምባቸውን ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎች ማቅረባቸውን ተናግራለች። በዝግጅቱ ላይ መሳተፋቸው ኃይል ቆጣቢ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ለማስተዋወቅ እንደረዳቸው በመግለፅ እንደ አገር መሰል አውደ-ርዕዮች በተለያዩ አካባቢዎች ሊስፋፉ እንደሚገባ ተናግራለች። በሐፍ አስመጪና አቅራቢ ድርጅት የኦፕሬሽን ማናጀር ሃበን ገብሩ በአውደ-ርዕዩ ምንም አይነት ኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ ማጣሪያ ኬሚካል ሳይጠቀም ውኃን ማጣራት የሚችል ቴክኖሎጂ ለኅብረተሰቡ በስፋት አሳይተናል ብለዋል።
የውሃ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ማደራጀት ሥራ እየተከናወነ ነው- ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ
Sep 21, 2023 97
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የውሃ ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ገለጹ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ፤ የውሃ ሃብት አጠቃቀምና በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም የኢትዮጵያን የውሃ ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። የመረጃ ቴክኖሎጂው አጠቃላይ የውሃ ሃብትን ለማስተዳደር፣ የሃብቱን መገኛ አካባቢዎች በመለየት ለማልማትና የአጠቃቀም ስልቶችን የሚያመላክት መሆኑን ጠቁመዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያን የውሃ ሃብት በተደራጀና ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት በመሰነድ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል። የውሃ ሃብት መረጃን በዘመናዊ የመረጃ ቋት በማስቀመጥ ከአካባቢው አገራት ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጠናከርና የውሃ ዲፕሎማሲ (ሃይድሮ ዲፕሎማሲን) ለመገንባት ጠቃሚ መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል። የኢትዮጵያን የውሃ ሃብት በምርምር የተደገፈና በተጨባጭ መረጃ የተደራጀ በማድረግ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። የውሃ ሃብትን በዘለቄታ በመጠቀም ሁለንተናዊ ልማትና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል። የውሃ ሃብትን በእውቀትና ምርምር ታግዞ ጥቅም ላይ ለማዋል የተቀናጀ ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ የሁሉም ጥረት እንዲታከልበት ጠይቀዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከማይክሮሶፍት ኩባንያ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ
Sep 21, 2023 112
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2016 (ኢዜአ)፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር በለጠ ሞላ በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማይክሮሶፍት ኩባንያ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ ማይክሮሶፍትና ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስለሚገኘው የቴክኖሎጂ መስፋፋት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም ወጣቶችን በዲጂታል እውቀት ለማበልጸግ እየተደረገ ስለሚገኘው ጥረት ለሃላፊዎቹ ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለማሳደግ እየሰራች ስለምትገኘው ስራ ያብራሩ ሲሆን ይህም ከኩባንያው ጋር በትብብር የሚሰራበት አንዱ ዘርፍ እንዲሚሆን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የዲጂታል መሰረተ-ልማትን ለማስፋት በተለይ በክላውድ አገልግሎት፣ ዳታ ማእከልና ሌሎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤቶች ከማይክሮሶፍት ጋር መስራት እንደምትፈልግም ገልጸዋል። በቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ላይ ጀማሪዎችን ለማበረታታት ኩባንያው በገንዘብ፣ በስልጠናና አስፈላጊ ግብአቶችን በማቅረብ ኢትዮጵያን ሊያግዝ ስለሚችልባቸው ጉዳዮች ገለጻ አድርገዋል። የማይክሮሶፍት ኩባንያ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለጤና፣ ለግብርና እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል። በተጨማሪም በአፍሪካ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ፕሮግራሙን ለማስፋፋት ኢትዮጵያን እንደ አማራጭ ለመጠቀም ፍላጎት እንዳለውም ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።
ሀገራት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንዲሠሩ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ጥሪ አቀረቡ
Sep 19, 2023 154
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2016 (ኢዜአ)፦ ሀገራት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንዲሠሩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ጥሪ አቀረቡ። አቶ ሰለሞን ሶካ "የመንግስታት፣ የሲቪል ማህበራት እና የንግድ ማህበረሰቦች ትብብር ዓለም አቀፍ የመረጃ ደህንነትን ለማረጋገጥ" በሚል መሪ ሀሳብ ከመስከረም 7-9 /2016 በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ የቪዲዮ መልእክት አስተላልፈዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው በተለይም የሳይበር ቴክኖሎጂው በየጊዜው መራቀቅ የሰውን የአኗኗር ዘይቤ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አስተሳሰቦችን ጭምር እየቀየራቸው እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ የቴክኖሎጂው እያደገ መምጣት ለኢኮኖሚው፣ ለፖለቲካው፣ ለባህሉና ለማህበራዊ መስተጋብሩ አወንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ሁሉ አሉታዊ ጎንም እንደሚኖረው አቶ ሰለሞን መጥቀሳቸውን አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡ አቶ ሰለሞን አያይዘውም አሁን ላይ ሁሉም ሐገራት ተግባራቸውን ለማከናወንና ከሌላው ዓለም ለመገናኘት የዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም ግድ እያላቸው ከመምጣቱም በላይ አንድ ሐገር ደሴት ሆኖ ተገልሎ መኖር እንደማይችል ሁሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂው ያመጣቸውን መልካም አጋጣሚዎች እና የሚያስከትለውን የደህንነት ስጋት በጋራ መምከር አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ ድንበር የለሽ እና ወስብስብ ተፈጥሮ ያለውን የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ሐገራት በተናጠል በሚያደርጉት ጥረት ማረጋገጥ እንደማይችሉና ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ይኸውም ትብብር፤ እውቀታችንን፣ ልምዳችንን እና ሪሶርሳችንን በማስተባበር ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር ዓለምን መፍጠር ያስችላል ሲሉ አቶ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች የምትገኘው ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት አጀንዳን ፈጽሞ ቸል እንደማትል የገለጹት አቶ ሰለሞን፤ ለዚህም በዋናነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ከማቋቋም አንስቶ፣ ፖሊሲዎችን መቅረጽ፣ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ መደንገግን እንዲሁም የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች ብለዋል፡፡ ይሁንና የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች ለመፍታት በተናጠል ከምናደርገው ጥረት ይልቅ ከተለያዩ ሐገራት ጋር በትብብር የምንፈጥረው አቅም የተሻለ በመሆኑ መንግስታት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስፖርት
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች
Sep 24, 2023 53
አዲስ አበባ ፤መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች፡፡ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው 49ኛው የጀርመን በርሊን ማራቶን ዛሬ ሲደረግ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአስደናቂ ብቃት አሸንፋለች። በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል ያሸነፈችው አትሌቷ ባለፈው ዓመትም የበርሊን ማራቶንን ማሸነፏ ይታወሳል ፡፡ በወንዶች ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ርቀቱን በበላይነት አጠናቋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከግብጹ አል አህሊ ጋር ይጫወታል
Sep 24, 2023 40
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2023/24 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ11 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ የግብጹ አል አህሊ ጋር ዛሬ ያከናውናል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ 75 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይከናወናል። አል አህሊ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የዛንዚባሩን ኬኤምኬኤም ክለብን በደርሶ መልስ 5 ለ 2 ውጤት ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ፈረሰኞቹ አል አህሊን በደርሶ መልስ ካሸነፉ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባታቸውን ያረጋግጣሉ።
ሉሲዎቹ ነጥብ ተጋርተዋል
Sep 22, 2023 81
አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2016 (ኢዜአ)፦ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ አንድ አቻ ተለያይቷል። በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ ረድኤት አስረሳኸኝ በ39ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ ቡድኑን መሪ አድርጋለች። ይሁንና ከእረፍት መልስ ካንያሙኔዛ ኤሪካ በ49ኛው ደቂቃ ከመረብ ያሳረፈችው ግብ ብሩንዲን አቻ አድርጓል። የሉሲዎቹ የፊት መስመር ተሳላፊ ሴናፍ ዋቁማ ከእረፍት በፊት በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብታለች። በሁለቱ አገራት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ስምምነት የቡድኖቹ የመልስ ጨዋታ መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ በደርሶ መልስ ጨዋታ ካሸነፈ በቀጣዩ ዙር ከዩጋንዳና አልጄሪያ አሸናፊ ጋር ይጫወታል። በሞሮኮ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 15ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በሕዳር ወር 2024 ይካሄዳል።
የኢትዮጵያን እግር ኳስ ስፖርት ውጤት ማጣትን ለመፍታት ሳይንሳዊ የአሰለጣጠን ዘዴን መተግበር ይገባል- በኃይሉ በቀለ
Sep 22, 2023 77
አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ስፖርት ውጤት ማጣት ችግር ለመፍታት ከታዳጊዎች ጀምሮ ሳይንሳዊ የአሰለጣጠን ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል አማካሪ በኃይሉ በቀለ ገለፁ። እግር ኳስ በኢትዮጵያ እጅግ ተወዳጅ ከሆኑና በበርካቶች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ከሚዘወተሩ ስፖርቶች ቀዳሚው መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራ ተቋም በአህጉሪቱ እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክታለች። እግር ኳስ በኢትዮጵያ አንድ ምዕተ-ዓመት የቆየና ሕዝባዊ መሠረት ያለው ስፖርት ቢሆንም በሚፈለገው መልኩ አላደገም። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል አማካሪ በኃይሉ በቀለ በኢትዮጵያ ያለው የእግር ኳስ አሰለጣጠን ዘይቤ ተመሳሳይ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህም ደግሞ ለታዳጊዎች፣ ለወጣቶችና ለጀማሪዎች በሚል እንደ ሀገር የተቀመጠ የሥልጠና መመሪያ አለመኖሩ ዋንኛ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል። የአሰለጣጠን ሥርዓቱ ዓለም የደረሰበትን ሳይንሳዊ አሠራር የተከተለ ባለመሆኑ ሳቢያም፤ በእግር ኳስ ስፖርት የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አልተቻለም ሲሉ አክለዋል። በፊፋ እንደተቀመጠውና በበርካታ የዓለም አገራት እንደሚሰራው የእግር ኳስ ሥልጠና ከስድስት ዓመት ጀምሮ ለህፃናት የሚሰጥ እንደሆነ አቶ በኃይሉ በቀለ አስረድተዋል። ሆኖም በኢትዮጵያ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ስፖርት ሥልጠና ከ13 እና ከ15 ዓመት የዕድሜ ክልል እንደሚጀምር ገልፀዋል። ይህም ታዳጊዎች በዕድሜያቸው ማግኘት የሚገባቸውን ሥልጠና እንዳያገኙና በአፍሪካ ውድድሮች ላይ ለሚመጡት ውጤቶች ደካማ መሆን መነሻ ምክንያት ናቸው ብለዋል። ይህንንም ለማስተካከል እያንዳንዱ የስፖርት ክለብ የራሱን መመሪያ ማዘጋጀት እንዳለበትና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በየደረጃው የአሰለጣጠን ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት አስረድተዋል። ሌሎች ሀገራትም የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ስፖርት ሥልጠና መተግበሪያ እንዳላቸውና ኢትዮጵያም ሊኖራት እንደሚገባ ገልፀዋል። የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ስፖርት ሥልጠና በኢትዮጵያ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። ትንሹ የሥልጠና ዕድሜ ከ13 ዓመት በታች መሆኑ ግን ከታችኛው የዕድሜ ክልል ጀምሮ እንደማይሰራ ያሳያል። ስለዚህ የሚመለከታቸው የፌደራል ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል ብለዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Sep 23, 2023 74
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። አቶ ደመቀ መኮንን ይህንን ያሉት በአሜሪካ ኒው-ዮርክ እየተካሄደ ባለው በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። በንግግራቸውም የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸው ተጽዕኖው በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ባሉ አገራት ከፍተኛ ነው ብለዋል። ያደጉ አገራት አፍሪካን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ አገራት የአየር ንብረትን ለውጥን እንዲቋቋሙ ለመልቀቅ የወሰኑትን የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አለመለቀቁን አንስተዋል። እንዲያም ሆኖ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲሰጥ እየሰራች መሆኑን ገልጸው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል። መርኃ ግብሩ የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ መርኃ ግብሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ ለማካፈል እየሰራች መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ችግሩን ለማቃለል ተጨባጭ እርምጃ ለመውሰድ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላ በኩል አንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ድኅነት ለመቀነስ እየተሰራ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እነዚህ ችግሮች እየጨመሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል። ጎን ለጎንም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋለው የሸቀጦች የዋጋ ንረት የአብዛኛውን ተጋላጭ ማኅበረሰቦች ፈተና ይበልጥ እያወሳሰበው መሆኑንና ትኩረት እንደሚሻ ጠቁመዋል።
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለመኸር እርሻ ሥራ አመቺ ዝናብ ይኖራል- የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Sep 22, 2023 74
አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2016(ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኞቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አካባቢዎች ለመኸር እርሻ አመቺ ዝናብ እንደሚዘንብ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኞቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የሚኖረው ዝናብ ለመኸር እርሻ ሥራ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጿል። በተለይም ከክረምት አጋማሽ አካባቢ ጀምሮ የዝናብ እጥረት በነበረባቸው የምስራቅ እና የሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች ዝናብ ያገኛሉ። በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኘው ዝናብ በተለያዩ የውሃ ማቆያ ዘዴ ተጠቅሞ ለእርሻ ሥራ ማዋል እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል። በአንፃሩ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ከመጣው የደመና ሽፋን ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል እርጥበት ለአርብቶ አደርና ለከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በጎ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቅሷል። በተጨማሪም በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብና በመካከለኛው ምስራቅ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም ግን በአንዳንድ አካባቢዎች የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ በተዳፋትና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የአፈር መሸርሸር ሊያስከትል ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። ከቀን ወደ ቀን የውሃ መጠናቸው ከፍ እያለ በመጡት እንደ ቆቃ፣ አዋሽ ተፋሰስ፣ ጣና በለሰና ፊንጫ ግድቦች ላይ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ትንበያው አመልክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመከላከል ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Sep 21, 2023 120
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2016 (ኢዜአ)፦ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመከላከል ዓለም አቀፍ ቅንጅታዊ ትብብርን ማጎልበት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ “ሰላም፣ብልጽግና፣ለውጥና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጉባኤው ጎን ለጎን በተካሄደ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል። አቶ ደመቀ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከፍተኛ የሚባል መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። በመርሐ-ግብሩ እስከ አሁን ከ32 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውንና የተለያዩ ውጤቶች እየተገኙበት መሆኑንም አመልክተዋል። የአደጋዎች ስፋት፣ መጠንና የሚከሰቱበት የጊዜ ገደብ ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ ፖሊሲዎቿን በመለወጥ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የማጠናከር ስራ በማከናወን ላይ ነች ብለዋል። በዚህ ረገድም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉትዬሬዝ “ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም” በሚል የጀመሩትን ኢኒሺዬቲቭ አቶ ደመቀ አድንቀዋል። ዓለም አቀፍ ትብብር አስፈላጊውን ቅንጅትና ትስስር በመፍጠር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለውም ነው ያብራሩት። በአገር፣ በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ውጤታማ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ለመገንባት አስፈላጊው የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
ዓለም እያጋጠማት ለሚገኘው አሳሳቢ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ይገባል-የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Sep 19, 2023 181
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2016 (ኢዜአ) ፦ ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እያጋጠማት የሚገኘውን ተጽእኖ ለመዋጋት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ዓለም አቀፍ ተቋማት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችንና ለውጦችን በሚመጥን መልኩ ራሳቸውን በማሻሻል ለሚታዩ ችግሮች የመፍትሄ አካል መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በኒውዮርክ ተጀምሯል። በጉባኤው ከ140 በላይ የሀገራት መሪዎች እየተሳተፉ ሲሆን አሳሳቢ በሆኑና ምላሽ በሚሹ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ይገኛሉ። የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ጉባኤውን ያስጀመሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ዓለም በበርካታ የተፈጥሮ አደጋዎች እየተፈተነች ትገኛለች ያሉት ዋና ጸሐፊው የአየር ንብረት ለውጡ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ የሰው ህይወት እየቀጠፈ እና ሰዎችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ይገኛል ብለዋል። በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ዓለም ለችግር መጋለጧን ጠቅሰው ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎችን ለመዋጋት በትብብር መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። የአየር ንብረት ለውጡ በተለይ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉት ዋና ጸሀፊው ለዚህም ያደጉ ሀገራት የሚለቁትን የካርበን መጠን ለመቀነስ ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ስምምነት ማክበር ይገባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል። ሀገራት የሚለቁትን የካርበን መጠን ለመቀነስ ከነዳጅና የድንጋይ ከሰል ሀይል ፊታቸውን ወደ ታዳሽ ሀይል ማዞር እንዳለባቸው ጠቁመው የታዳሽ ሀይልን ማስፋፋት ዋነኛው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ መቀነሻ መንገድ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ያደጉ ሀገራት የራሳቸውን የካርበን ልቀት ከመቀነስ ባለፈ ለታዳጊ ሀገራት የአረንጓዴ ልማትና የታዳሽ ሀይል መስፋፋት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ገልጸዋል። ዓለም አቀፍ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ በፍጥነት እየተቀየረ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ጸሀፊው የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ ሳያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል። ለዚህም ዓለም አቀፍ ተቋማት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችንና ለውጦችን በሚመጥን መልኩ ራሳቸውን በማሻሻል ለሚታዩ ችግሮች የመፍትሄ አካል መሆን እንዳለባቸውም ነው የገለጹት። በመሆኑም እየተወሳሰበ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰላምና ጸጥታ ችግር ለመፍታት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተቋማዊ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚገባቸውም ዋና ጸሐፊው ያሳሰቡት። በተለይ የጸጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ የሰላምና የጸጥታ የፋይናንስ ስርዓቱን እንደገና መፈተሽ አለበት ሲሉም አሳስበዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓለምን እየቀየራት እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ይህን መቆጣጠር የሚችል ዓለም አቀፍ ተቋም ማቋቋም እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። በዚህ ዙሪያም ለሚደረግ ምክክር የተባበሩት መንግስታት ድረጅተ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም አስታውቀዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአማርኛ ቋንቋ በሞስኮ ከተማ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀመረ
Sep 20, 2023 153
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 09/2016 (ኢዜአ)፦ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል። የሩሲያው ዜና አግልግሎት ስፑቲኒክ እንደዘገበው አማርኛን ጨምሮ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል። የቋንቋዎቹ ትምህርት መጀመር በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ባሕላዊ መስኮች የነበሩ ትስስሮችን ይበለጥ ለማሳድግ ሚናው የጎላ መሆኑን የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተናግረዋል። አማርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ቋንቋነት መማር የጀመሩ ተማሪዎች ለስፑቲኒክ እንደተናገሩት፣ የአማርኛ ቋንቋ ከማወቅ ባሻገር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የህዝቡን ባህልና አኗኗር የማወቅ ጉጉት አሳድሮባቸዋል። ሩሲያ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር እንደምትጀምር ባለፈው ዓመት ማስታወቋ ይታወሳል።
የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል በማድረግ ተጠናቀቀ
Sep 10, 2023 310
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2015(ኢዜአ)፦በሕንድ አስተናጋጅነት ኒውዴልሂ ከተማ ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቡድን 20 አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ ኅብረትን 21ኛ አባል በማድረግ ዛሬ ተጠናቋል። በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ዳ ሲልቫ የቡድን 20 ፕሬዝዳንትነት ቀጣይ መንበር አስረክበዋል። ሉላ ዳ ሲልቫ ማኅበራዊ አካታችነትን፣ ረሃብን መዋጋት፣ የኃይል ሽግግርን እና ዘላቂ ልማትን የቡድን 20 አገራት ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጧቸው እንደሆነም ከወዲሁ ይፋ አድርገዋል። ጉባዔው 55 አባል አገራት ያቀፈውን የአፍሪካ ኅብረትን ታሪካዊ በተባለ ውሳኔ የቡድን 20 አባል አድርጎ ተቀብሏል። የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 ሃያ አንደኛ አባል ሆኖ መቀላቀሉ የቡድኑን አካታችነት መርህ እንደሚያጎላው የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል። ሕንድ ባስተናገደችው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ በተከፋፈሉ የዓለም ኃያላን መንግሥታት መካከል ስምምነትን መፍጠር ችላለች ተብሏል። ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ላቅ ያለ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት እንደሆነም ተገልጿል። ጉባዔው የኒውዴልሂ የጋራ መግለጫ ሰነድ ይፋ በማድረግ ሲጠናቀቅ ሁሉም የቡድን 20 አባላት አገራት በዓለም ዙሪያ ሰላም፣ ደህንነት እና ግጭት በማስወገድ አንድ ሆነው ለመስራት ተስማምተዋል። ሰነዱ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ገቢራዊ ለማድረግ እኤአ እስከ 2030 ድረስ ከ5 ነጥብ 8 እስከ 5 ነጥብ 9 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል። እንዲሁም እስከ 2030 ድረስ ለታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂዎች 4 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋቸውና ይህም እኤአ በ2050 የካርባን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ እንደሚረዳቸው ግልጽ አድርጓል። በተጨማሪም አባል አገራት የኃይል እርምጃን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው።
በቴል አቪቭ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግጭት 160 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ
Sep 2, 2023 461
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2015 (ኢዜአ) ፦ በእስራኤል ቴል አቪቭ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራዊያን ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግጭት ፖሊሶችን ጨምሮ 160 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ። እንደ እየሩሳሌም ፖስት ዘገባ የኤርትራ ኤምባሲ በቴል አቪቭ ያቀረበውን የባህል ዝግጅት ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በመቃወማቸው ምክንያት በተነሳ ብጥብጥ ብዙዎቹ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተቃውሞው ላይ በነበራቸው ተሳትፎ ከቆሰሉት ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራዊያን መካከል ስምንቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። እየሩሳሌም ፖስት የሆስፒታልና የፖሊስ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከቆሰሉት መካከል 13ቱ መጠነኛ እንዲሁም 93 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ናቸው። ዛሬ ከቀትር በኋላ በቴል አቪቭ የኤርትራ ኤምባሲ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ በተነሳው የተቃውሞ ብጥብጥ 50 የሚሆኑ ፖሊሶች መቁሰላቸውን ጨምሮ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል። ኤርትራዊያኑ ስደተኞች የሃገራቸውን መንግስት በመቃወም በተነሳው ብጥብጥ የሱቆችን መስኮቶች፣ የፖሊስ ተሽርካሪዎችን የሰባበሩ ሲሆን ፖሊስም ሁኔታውን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስና ሌሎችንም አማራጮች መጠቀሙ ተዘግቧል።
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የአፍሪካን አጀንዳና ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የሚረዳ ነው- በአልጀዚራ የጥናት ማዕከል የምርምር ግንኙነት ኃላፊ ቴምቢሳ ፋኩዴ
Aug 26, 2023 670
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2015 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድን አባል አገር መሆኗ የአፍሪካን ድምጽ ከማሰማት አልፋ አሕጉራዊ ጥቅሞችን ታስጠብቃለች የሚል እምነት እንዳላቸው በአልጀዚራ የጥናት ማዕከል የምርምር ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ቴምቢሳ ፋኩዴ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በብዙ ዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸው ላቅ ያለ ተቀባይነት የአፍሪካን አጀንዳ ያሳከሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል። በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ከሚዘግበው ኢ-ኒውስ ቻናል አፍሪካ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የአፍሪካን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የሚረዳ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በብሪክስ አባል አገራት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ የአፍሪካ አጀንዳን በማንሳት አሕጉራዊ ጥቅሞች እንዲጠበቁ የማድረግ ብቃት እንዳላት ተናግረዋል። ቴምቤሳ ፋኩዴ አክለውም ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎችን በማቀንቀን አፍሪካዊ አንድነት እንዲጠናከር የምትሰራ አገር መሆኗ ለአባልነት ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል የገነባች አገር መሆኗ ደግሞ በብሪክስ አባል አገራት ተመራጭ እንድትሆን አድርጓታል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ካለፉት ሃያ ዓመታት ወዲህ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ የቻለች ብቻ ሳይሆን በቀጣይም ይህን ዕድገት ማስቀጠል የምትችል አገር መሆኗ ለመመረጧ በዋቢነት አንስተዋል። በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 አገራት በአባልነት መቀበሉ የሚታወቅ ነው።
ሐተታዎች
የአባቱን የጀግንነት ፈለግ የተከተለው ዳግም ኤቢሳ
Sep 19, 2023 155
በኢትዮጵያ የሺህ ዘመናት ታሪክ ለሀገር ክብር፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ጠብቆ ለማቆየት የተዋደቁ፣ ጀግንነትን የተዋረሱ እና መስዋዕትነት የከፈሉ ቤተሰቦች ማግኘት የተለመደ ነው። በየዘመኑ ለአገር ሉዓላዊነት፣ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ዘብ የቆሙ ወታደሮች ጀግንነታችውን ለልጆቻቸው አውርሰዋል፤ ልጆችም የአባትና አያቶቻቸውን ፈለግ በመከተል የራሳቸውን የጀግንነት አሻራ ያሳርፋሉ። ለእናት አገር ዘብ መቆምን በትውልድ ቅብብሎሽ ካስቀጠሉ ቤተሰቦች መካከል የወይዘሮ እሙዬ ፈለቀ ባለቤት ኮሎኔል ኤቢሳ ታይሳ እና ልጃቸው ዳግም ኤቢሳ ይገኙበታል። "እኛ የመከላከያ ሰራዊት ቤተሰብ ነን" የሚሉት ወይዘሮ እሙዬ ፈለቀ፣ ባለቤታቸው ኮሎኔል ኤቢሳ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አገልግሎ ለሀገሩ ክብር በጀግንነት መሰዋቱን ያነሳሉ። የጀግና አባቱን ገድል እየሰማ ያደገውና የሀገር ፍቅርን የወረሰው ልጃቸው ዳግም ኤቢሳ ደግሞ በጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ወታደርነት ተመርቋል። ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ጦላይ በመሄድ በልጃቸው ምርቃት ላይ ያገኘናቸው ወይዘሮ እሙዬ ፈለቀ፣ "ልጄ የአባቱን የኮሎኔል ኤቢሳ ታይሳ ጀግንነትና የሀገር ፍቅር ለመከተል ከፍተኛ ስሜት ነበረው" ይላሉ። "የጀግና ልጅ ጀግና ነውና ልጄም ሰራዊትን በመቀላቀል ጀግንነቱን በተግባር አረጋግጧል" ሲሉም ይናገራሉ። ባለቤታቸው እና ልጃቸው ለሀገር ክብር ዘብ በመሆናቸውም የላቀ ክብርና ኩራት እንደሚሰማቸው የሚያነሱት ወይዘሮ እሙዬ፤ ልጃቸውን "እንደ አባትህ ጀግና ሁን" እያሉ ጀግንነትን እንዲላበስ ማድረጋቸውንም ይገልጻሉ። "ልጄ የአባቱን ወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሶ በማየቴ ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶኛል" ያሉት እናት፣ ሀገርን በቅንነትና ታማኝነት በማገልገል የአባቱን የጀግንነት ታሪክ እንዲያስቀጥል መምከራቸውንም አንስተዋል። ባለቤታቸው ለከፈለው መስዋዕትነትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለቤተሰቡ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። መሰረታዊ ወታደር ዳግም ኤቢሳ በበኩሉ በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና ወስዶ ከጓዶቹ ጋር በመመረቁ ተደስቷል። "የእናት ሀገሬን ሉዓላዊነት አንድነት በመጠበቅ የአባቴን አሻራ ለማስቀጠል ዝግጁ ነኝ" ብሏል። ወታደራዊ ግዳጅን በብቃት መወጣት የሚያስችል ትምህርትና ስልጠና መውሰዱን የሚናገረው ዳግም ኤቢሳ፣ እንደ አባቱ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ከፍሎ ሀገሩን ለማገልገል ያለውን ወኔና ቁርጠኝነትም ገልጿል።
ችግር ፈቺ ፈጠራ
Sep 9, 2023 314
ባስልኤል የእንጨትና ብረታ ብረት ማህበር በጅንካ ከተማ በክላስተር ማዕከል ውስጥ ከተደራጁ 8 ማህበራት አንዱ ነው ። የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ሙሐመድ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ማህበሩ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ባገኘው 450 ሺህ ብር የብድር ድጋፍ በ2007 ዓ.ም ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰዋል። ከብድር አቅርቦቱ በተጨማሪ በመንግስት የማሽነሪ እና የማምረቻ ሼድ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም ተናግረዋል። ማህበሩ ከሚያመርታቸው የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች በተጨማሪ ከውጪ በከፍተኛ የዶላር ምንዛሪ የሚገቡ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ያመርታል። ማህበሩ ካመረታቸው አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች አንዱ የጥልቅ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽን ይጠቀሳል። ቀደም ሲል ማሽኑን ለመግዛት እስከ 2 ሚሊዮን ብር ይፈጅ እንደነበር የገለፁት የማህበሩ ሰብሳቢ ፤ ይህንኑ ማሽን በተሻለ ጥራት ማምረት በመቻላችን ለማሽኑ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ማዳን ችለናል ብለዋል። የጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኑንም በጅንካ ከተማ ለሚገኙ ለተለያዩ ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ የጥልቅ ጉድጓድ በመቆፈር የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግራቸውን መቅረፉንም ነው አቶ ጌታቸው የሚናገሩት። በተጨማሪ ኃይል ቆጣቢ የእህል ወፍጮ፣ ኃይል ቆጣቢ ምድጃ፣ በሰአት እስከ 10 ኪሎ ግራም ቡና የሚቆላ ማሽን፣የገብስ መፈተጊያና የአተር መቁያ ማሽን በአገልግሎት ላይ ከሚገኙ የማህበሩ የፈጠራ ውጤቶች ይጠቀሳሉ። ከተጠቀሱት ምርቶች ባለፈም ማህበሩ በሚሰራቸው የብረት ማቅለጫና ቅርፅ ማውጫ ማሽኖች የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችንም ያመርታል። የማህበሩ የረጅም አመታት ደንበኛ እንደሆኑ የሚገልጹት የጅንካ ከተማ ነዋሪ አቶ አወቀ አይኬ፤ ''ማህበሩ የሚሰራቸው አዳዲስ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች የማህበረሰቡን ችግር በእጅጉ እያቃለሉ ናቸው'' ብለዋል። ከዚህ ቀደም የተሽከርካሪ የመለዋወጫ ዕቃዎችን ለማግኘት 730 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ወደ አዲስ አበባ እንደሚሄዱ አስታውሰው አሁን ማህበሩ የምንፈልገውን ብሎንም ሆነ ሌሎች የመለዋወጫ ዕቃዎችን በፈለግነው ዲዛይን እዚሁ አምርቶ በማቅረቡ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የምናባክነውን ጊዜና ገንዘብ እንድንቆጥብ አስችሎናል ብለዋል። በተለይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ከማቃለል አኳያ ትልቅ ሚና እየተወጣ እንዳለም ተናግረዋል። ወይዘሮ ትዕግስት አባይነህ የተባሉ የጅንካ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው ማህበሩ የፈጠራቸው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በተለይ የሴቶችን ድካም በእጅጉ እንዳቃለለ ተናግረዋል። ቀደም ሲል ገብስ ለመፈተግ፣አተር ለመቁላት እና ሌሎች ቅመማ ቅመሞችን ለማዘጋጀት ብዙ ውጣ ውረዶች እንደነበር ገልፀው ይህም ከቢሮ የስራ ሰአት ውጪ ባለው ትርፍ ጊዜ ለማከናወን አስቸጋሪ እንደነበር ገልጸዋል ። በተለይ በቤት ውስጥ የበአልና ሌሎች ፕሮግራሞች ሲኖሩ እነኚህን ስራዎች መስራት አድካሚ እንደሆነ ገልፀው አሁን ማህበሩ በፈጠራቸው ዘመናዊ ማሽኖች አድካሚ ስራዎችን ግማሽ ሰአት ባልሞላ ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ ተናግረዋል ። ማህበሩ የሰራቸው ወጪ ቆጣቢ ምድጃዎችም በቤት ውስጥ ምግብ ለማዘጋጀት አመቺና ጥራታቸውም ወደር እንደሌለው የገለፁት ወይዘሮ ትዕግስት እነዚህ ምርቶች በእጅጉ የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉና ህይወትን ቀለል የሚያደደርጉ በመሆናቸው እንዲህ ያለ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች ሊበረታቱ እንደሚገባም ተናግረዋል ። የባስልኤል የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ማህበር ከማህበሩ አባላት በተጨማሪ ለ8 ሰራተኞች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሯል፤ ቀደም ሲል በማህበሩ ይሰሩ የነበሩ አባላትም ከማህበሩ በቀሰሙት ዕውቀትና ልምድ የግል ድርጅት በመክፈት የራሳቸውን ገቢ እያመነጩ ለሌሎችም የሥራ ዕድልን ፈጥረዋል። በማህበሩ ተቀጥረው ከሚሰሩ ባለሙያዎች አንዱ አቶ ደረጀ ሙሐመድ ሲሆኑ በማህበሩ ውስጥ በመስራታቸው ተጠቀሚነታቸው የደሞዝ ብቻ እንዳልሆነና የዕውቀት ሽግግር ዕድልን ተጠቃሚ እንደሆኑ ያነሳሉ። ታዲያ የነዚህ የፈጠራ ሀሳቦች ባለቤት የሆነውና የማህበሩ መስራች አቶ ጌታቸው ሙሐመድ ይህን የፈጠራ ሀሳብ በማፍለቅ እውን የሚያደርገው እንደ ሙሉ ጤነኛ ሰው በእግሩ እንደ ልቡ እየተንቀሳቀሰ ሳይሆን በዊልቸር እየተገፋ ነው። አቶ ጌታቸው በ1990 ዓመተ ምህረት በድሬዳዋ ከተማ በስራ ላይ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ አደጋ ከፎቅ ላይ በመውደቁ በእግሮቹ ላይ ጉዳት ሊደርስበት መቻሉን ተናግሯል። አደጋው ካጋጠመው ጊዜ አንስቶ በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፉን አስታውሶ ለፈተናዎች እጅ ባለመስጠቱ ለዚህ ስኬት መብቃቱን ይናገራል። ''ያጋጠመኝን የተሽከርካሪ ችግር ለመቅረፍ የወዳደቁ ሞተር ሳይክሎች በመጠገን ለራሴ እንድትመቸኝ አድርጌ የሰራኋት ተሽከርካሪ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ አድርጋኛለች'' ብለዋል። ማህበሩ አሁን ላይ ከቋሚ ንብረቶች በተጨማሪ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብትእያንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አቶ ጌታቸው ገልጿል። በቀጣይም እንደ አገር በተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በውድ ዋጋ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በተሻለ ዲዛይን በማምረት የውጭ ምንዛሪውን ለማስቀረትና የማህበረሰቡንም ችግር ለማቃለል ማህበሩ በትጋት እንደሚሰራም ተናግረዋል። የአምራችነት ቀን '' ከሸማችነት ወደ አምራችነት'' በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኝበት በዛሬው ዕለት የመሰል ማህበራት ተሞክሮ የሚያስተምረው ነገር ብዙ ነው።
በጎነት ለሌሎች መኖር ነው- ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ
Sep 8, 2023 314
"በጎነት ለሌሎች መኖር ነው" ሲሉ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ተናገሩ። በኢትዮጵያ የጳጉሜን ቀናት የተለያየ ስያሜ በመስጠት በጎነትን ፣አብሮነትን ፣መተሳሰብንና መስዋዕትነትን የሚያንጸባርቁ ሃሳቦችን በመስጠት መከበር ከጀመረ ቆይቷል። በዚህም የዛሬዋ ጳጉሜን 3 ቀን “በጎነት ለሀገር” በሚል ሀሳብ በጎ ተግባራትን በሚያንጸባርቁ የተለያዩ መርሐ-ግብሮች እየተከበረ ነው። ቀኑን ምክንያት በማድረግ ኢዜአ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደርን አነጋግሯል። "የኢትዮጵያውያን እርስ በርስ የመደጋገፍ ባህል እየጎለበተ መምጣቱን" የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል። ከተመሰረተ 29ኛ ዓመቱን የያዘው ድርጅቱ ከ11 ሺህ ያላነሱ ጧሪና ደጋፊ ያጡ አረጋዊያንን በመንከባከብና የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ከ39 ሺህ በላይ ሕፃናትን ደግፎና አስተምሮ ለቁምነገር ማብቃት መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡ በተለይ ላለፉት 17 ዓመታት "ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን" በሚል መርህ በሀገር ልጆች ሀብት ላይ ተመስርቶ በሶስት ክልሎች በ 24 ከተሞችና 112 ወረዳዎች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም በትምህርት፣ጤና፣ የሕጻናት ጥበቃና የኢኮኖሚ አቅምን ማጎልበትና አረጋውያንን የመንከባከብ ስራዎችን በስፋት ሲያከናወን መቆየቱን ይጠቀሳሉ። በጎነት ለሌሎች መኖር ነው የሚሉት ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፤ በጎነት ሕይወትንና ስኬትን ሙሉ የሚያደርግ እሳቤ መሆኑን ገልጸዋል። በጎነት ለግለሰብም ሆነ ለማህበረሰብ ብሎም ለአገር የሚጠቅም በጎ ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል። በጎነት ለሁሉም ሰው የተሰጠ ነው የሚሉት ሲስተር ዘቢደር ልዩነቱ በጎነትን መለማመድ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያውያን በመተባበር ለአገርና ለወገን ትልቅ ስራ ማከናወን ይቻላሉ ብለዋል። በመስጠት ብዙ መቀበል እንደሚቻልና በጎነት የሕይወት አካል ማድረግ እንደሚገባም ነው ሲስተር ዘቢደር የገለጹት። ሜሪጆይ በ1986 ዓ.ም የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በተቀናጀ የልማት መርሐ-ግብሮች ለችግር የተጋለጡና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ዋና ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
ምስጉንና ትጉህ የጤና ባለሙያ አርጃ ቲሎ
Sep 6, 2023 497
የጤና መኮንን ባለሙያው አርጃ ቲሎ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ምስጉን እና ታታሪ ሠራተኛ ናቸው። በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተቀናጀ ድንገተኛ የማህፀን ፅንስና አጠቃላይ ቀዶ ህክምና ባለሙያው ከ35 ዓመታት በላይ በተለያዩ ተቋማትና አካባቢዎች ሀገራቸውን አገልግለዋል። ካገለገሉባቸውም አካባቢዎች በጋሞ፣ወላይታና ደቡብ ኦሞ ዞኖችን ጨምሮ ሀዋሳና ጂንካ ተጠቃሽ ናቸው። የህክምና ትምህርታቸውን በሀገር ውሰጥና በውጭ ሃገር በመከታተል ሙያቸውን አሻሽለዋል። የጤና መኮንን ባለሙያው አርጃ ቲሎ በበዓላትና በእረፍት ቀናት ጭምር ከቤተሰብ ይልቅ ለታካሚዎቻቸው ቅድሚያ በመስጠታቸው ምስጋናን ተችረዋል ። ከሌሎች ሰራተኞች ከመግባታቸው በፊት ቀድመው ቢሮ መግባታቸውና ታታሪነታቸው ለሽልማት አብቅተቸዋል፡፡ ባለሙያው አርጃ ቲሎ ባለፈው አመት ከደቡብ ኦሞ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማትን ተቀብለዋል። በ35 ዓመታት የስራ ቆይታቸው ብዙ ነገሮችን ያሳለፉት ባለሙያው አርጃ ቲሎ ታዲያ አንዴ ያጋጠማቸውን ከባድ ፈተና መቼም እንደማይረሱት ይናገራሉ ። በጂንካ ሆስፒታል በማገልገል ላይ እያሉ አንዲት ነፍሰ ጡር እናት በወሊድ ወቅት ባጋጠማት የተራዘመ ምጥ በሞትና በህይወት መካከል ነበረች ሲሉ ያስታውሳሉ። ይቀጥሉናም በወቅቱ በሆስፒታሉ የደም አቅርቦት እና በዘርፉ የሰለጠኑ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ባለመኖራቸው ለዚህች እናት ህክምና መስጠት አልተቻለም ነበር ። ስፔሻሊስቱ ለተሻለ ህክምና ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ሪፈር መፃፍ ቢጠበቅባቸውም ታካሚዋ እስከ አርባ ምንጭ በህይወት ስለመድረሷ ይጠራጠራሉ ሲሉ ትውስታቸውን ይተርካሉ። ይህን የተገነዘቡት የጤና መኮንኑ ታዲያ አንድ ነገር ለማድረግ ወሰኑ፡፡ ወደ አርባ ምንጭ ልከው ነፍሰ ጡሯ መንገድ ላይ ህይወቷ ከሚያልፍ አቅማቸው የፈቀደውን አድርገው የመጣውን ለመቀበል ወሰኑ። ውሳኔውም ህክምናውን ሳያደርጉ ሞቷን ከመጠባበቅ እንደሚሻል በማመን ከህመምተኛዋ ቤተሰቦች ባገኙት ደም የተሳካ የቀዶ ጥገና በማድረግ ወላዷን እናት ከሞት ሊታደጉ መቻላቸውን በኩራት ይተርካሉ። 'የፈጣሪ እርዳታ ታክሎበት ቀዶ ጥገናውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቄያለሁ' ታካሚዋም በህይወት ቆይታ ጤናማ ህይወት ስትመራ በማየታቸው ቃላት ሊገልፁት የማይችሉት ደስታ ይሰማቸዋል። በመሆኑም ማንኛውም ሀኪም ቁሳቁስ አልተሟላም እጥረት አለ በማለት ከማማረርና ባለው አቅም ተገልጋዩን በማገልገል ኃላፊነቱን ይወጣ ሲሉም ምክራቸውን ይለግሳሉ። የረጅም አመታት የስራ ባልደረባ አቶ ኢያሱ ታንቱ የአርጃን ከሰራተኛው ጋር ተግባቢነት ፣ደከመኝ ሰለቸኝ የማያውቁ፣ለስራቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው ክብር ያላቸው ፣ታካሚውን በርህራሄ የሚያገለግሉ፣ ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆኑ ሲሉም ይገልጿቸዋል። በጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ክፍል የነርሶች አስተባባሪ አቶ አማኑኤል ካሳ የባልደረባቸውነ ምስክርነት ይጋራሉ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አይፎክሩ ግዛቸው በበኩላቸው አቶ አርጄ በሆስፒታሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ከመመደባቸው አስቀድሞ ስፔሻሊስት ሀኪሞች እጥረት በነበረበት ወቅት በአጠቃላይ ቀዶ ህክምናና ነፍሰ ጡር እናቶችን በቀዶ ህክምና በማዋለድ ትልቅ ሙያዊ ኃላፊነት ሲወጡ የነበሩ ትጉህ ሰራተኛና የሀገር ባለውለታ ናቸው ሲሉ ይመሰክራሉ። ወይዘሮ ዘላለም ሰኢድ የጅንካ ከተማ ነዋሪ ናቸው፤ የአርጃ ቲሎ የህክምና ሙያ ከጎበኟቸው ተገልጋዮች አንዷ ሲሆኑ የሀኪሙን መልካምነት ይመሰክራሉ፡፡ እንዲ ሲሉ የህክምና ሙያን ከመልካም ስነምግባር ጋር የያዙ።
ትንታኔዎች
ከገበታ ወደ ገበያ
Sep 24, 2023 1
(ሰለሞን ተሰራ) ኢትዮጵያ ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ አዝእርትና እንስሳት ሀብት መፍለቂያ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከዚያ ዘመን ጀምሮ የአገራችን ገበሬ በስራ ያካበተውንና በተፈጥሮ የተሰጠውን ችሎታ በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ በወለዳቸው መሳሪያዎች ሳይታገዝ፣ በየጊዜው የአፈሩ ለምነት እየቀነሰ ከሄደው መሬትና ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ጋር እየታገለ ቁጥሩ እየናረ የሚሄደውን ህብረተሰብ ከመመገብ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። ግብርናው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ባገኘበት በዚህ ዘመንም ከተደቀኑበት እጅ ጠምዛዥ ጉዳዮች ጋር ግብግብ ውስጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፣ የፖለቲካና የገበያ አለመረጋጋት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዘርፉ ኢንቨስትመንት አለመዳበር የዘርፉ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በተለይ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽእኖ በሚገባ አመላክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በተለይ በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገራት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲበጅ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ እየተሳተፉበት ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በሰራችው ስራ በአካባቢ ጥበቃና በግብርናው ዘርፍም ውጤት ማግኘቷ እሙን ነው። ነገር ግን ፈተናዎቹን በድል ለመሻገር የሚደረጉ ጥረቶችና በዘርፉ የተገኙ አበረታች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በተደራጀ የግብርና መሳሪያና ማቀነባበሪያ በመደገፍ አገርና ህዝብ ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ መስራት ይጠይቃል። በተለይ የግብርና ሜካናይዜሽንን ከማስፋፋትና ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ አኳያ መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት የበለጠ መጠናከርና ማደግ ይኖርበታል። የግብርናና የገጠር ልማት የፋይናንስና ብድር አቅርቦትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢና ስነ ምህዳር ጥበቃ ስራዎችን በዘላቂነት መተግበር ያሻል። በተለይ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየሰራችበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብርና አሰራር በመቀየርና አማራጮችን በማማተር እውን ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ በዝናብ ወይም በመስኖ መልማት የሚችል ያልተነካ ሰፊ መሬት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ይህን ያልታረሰ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አንዱ አማራጭ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግብርናው ከ34 በመቶ በላይ የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ዘርፉ 79 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ ሲሆን በተመሳሳይ 79 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ንግድ ገቢ በመሸፈንና ለአገር ውስጥ ኢንቨስትመንትና ገበያ የጥሬ እቃ አቅራቢ በመሆንም ይታወቃል። መንግስት በግብርናው ዘርፍ የወሰዳቸው የሪፎርም ስራዎችና ግብርናን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የሰራቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። በተለይ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተሰራው ስራ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ የስንዴ ምርታማነቷን በ27 በመቶ ማሳደግ መቻሏ ስንዴ ከመሸመት ወደ መላክ የመሸጋገሯ ማረጋገጫ ሆኗል። በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በዚህ ረገድ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ አላስገባችም። በዚህም 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በቅርቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ያመረተች ሲሆን በተያዘው ዓመት ደግሞ ምርቱን ወደ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህንኑ ግብ ለማሳካት ደግሞ የስንዴ ማሳዋን በማሳደግ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን እየሰራች ነው። ከዚህ ውስጥ በመስኖ የሚለማ ስንዴን በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት በመስኖ የሚለማውን ስንዴ በ54 በመቶ ለማሳደግ እየሰራች ነው። ይህ ደግሞ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የግብርናው ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል። በዚህም ዘርፉ በ2013 ከነበረበት 5 ነጥብ 1 በመቶ በ2014 ወደ 5 ነጥብ 8 በመቶ ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65 ነጥብ 5 በመቶ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ደን ልማት 8 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የእንሰሳት ሃብት ልማቱ 25 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ 627 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት ታቅዶ ከተቀመጠው ግብ በላቀ ደረጃ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል። ከበጋ ስንዴ ልማት ጎን ለጎን በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ የቡና፣ አቮካዶና አኩሪ አተር የመሳሳሉት ትላልቅ የግብርና ልማት ስራዎች በተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የአዝርት፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የስንዴ ምርት ከውጭ ገበያ ስትገዛ የኖረች ሲሆን በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች አቅርቦቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የስንዴና የገብስ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የቻለች ሲሆን የሩዝ ፍላጎቷን ደግሞ 50 በመቶ መሸፈን ችላለች። በስንዴ ምርታማነት የተገኘውን ተሞክሮ ወደሌሎች ሰብሎች በማስፋት የገቢ ምርቶችን በቀጣይ ለመተካት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን ለማሳካት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ለግብርና ዘርፉ የተሻለ በጀት መመደቡ፣ እስካሁን ለመጣውና ለወደፊትም ይመጣሉ ተብለው ለሚታሰቡ ለውጦች ትልቅ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ከተመደበው 786 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ፣ ለግብርናው ዘርፍ 34 በመቶ የሚሆን በጀት ተመድቧል። ይህ ደግም ከለውጡ በፊት ከአሥር በመቶ ያልበለጠ በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ያደርገዋል። በተጨማሪም መንግሥት ለኩታ ገጠምና ለመስኖ እርሻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ፣ ሙሉ በሙሉ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ስራ በመስኖ የታገዘ እንዲሆንና አርሶ/አርብቶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት ማድረጉ ውጤቱን ጉልህ አድርጎታል። እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ቡና፣ አቦካዶ ሁሉ በግብርና ሚኒስቴር ከተያዙና በልዩ ትኩረት ከሚከናወኑ ዕቅዶች አንዱ የማር ምርትን ማሳደግ ሲሆን፣ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ እንደተመላከተውም የማር ምርትን በማዘመን ምርቱን ለማሳደግ በስፋት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለማር ምርት ተስማሚ የሆነ አግሮ ኢኮሎጂና ብዛት ያላቸው ዕፅዋት መኖራቸው የሚመረተው ማር የተፈጥሮ ጥራት እንዲኖረው ያግዛል። ይህንኑ ዕምቅ ሀብት ትኩረት ሰጥቶ ማልማት ከተቻለ ከ500 ሺሕ ቶን በላይ ማርና ከ50 ሺሕ ቶን በላይ ሰም ማምረት እንደሚቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ በሀገሪቱ አለ ተብሎ ከሚገመተው ሰባት ሚሊዮን የንብ መንጋ ውስጥ 90 በመቶው በባህላዊ ቀፎ ውስጥ የሚገኝ ነው። የንብ መንጋዎቹ በባህላዊ ቀፎ ከመኖራቸው በተጨማሪ በጫካ መገኘታቸው ሃብቱ ለአገር ዕድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይውል አድርጎታል። ያም ቢሆን ባለፈው ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” ለማር ምርት ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተደርጓል። በዚህም የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል። ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የማር ምርት የማምረት አቅም ካላቸው አሥር ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ሃብቱን ለማልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በአጠቃላይ መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት/አሻራ፣ ለአፈርና አካባቢ ጥበቃ የሰጠው ትኩረት ሁሉን አቀፍ የግብርና ዕድገት እንዲመጣ መሠረት ሆኗል። በተጨማሪም መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌማት ትሩፋትና ምግባችን ከደጃችን መርሐ ግብር ኅብረተሰቡ የከተማ ግብርናን እንዲያስፋፉ በገጠርም ሆነ በከተማ ያከናወነው ተግባር ውጤት አስመዝግቧል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ የልማትና የሪፎረም ሥራዎች ግብርናውን ከአዝጋሚ ጉዞ በማውጣት ወደ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞ ማሸጋገር ችለዋል። ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ያልተነኩ ዕምቅ ሀብቶች ያሏት መሆኗን እንደ እድል በመውሰድ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል። ይህን ማድረግ ስትችል የግብርና ሽግግር ይረጋገጣል። ግብርናውን ለማሻገር ደግሞ በፋይናንስ፣ በግብአት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ያሻል። ወጣቱ ግብርናን እንደ ንግድ (Agri-Bussiness) ማየትና በዚያው ልክ መስራት ይጠበቅበታል። በዚህ ልክ በርብርብ ሲሰራ ግብርናን በማሸጋገር ገበታን ከመሙላት ወይም ከፍጆታ አልፎ ገበያን ማማተር ይቻላል።
ኢትዮጵያ እና መስከረም
Sep 22, 2023 71
(በአየለ ያረጋል) መቼስ ሀገሬው መስከረምን ሲናፍቅ ‘ለብቻ’ ነው። በባህሉ፣ በትውፊቱ፣ በስለ-ምኑ፣ በኪነ-ቃሉ እና ስነ-ቃሉ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል ለመስከረም። እንደ መስከረም ክብር፣ ሞገስ እና ፀጋ የተቸረው የትኛው ወር ይሆን? ማንም! ሀገሬው ለቆንጆ ልጁ ስም ሲያወጣ ‘መስከረም’ እንጂ በሌላ ወር ሰይሞ ያውቃል? አያውቅም። በኢትዮጵያ ምድር መስከረም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳት እና አዕዋፋት ራሱ ልዩ ጊዜ ነው። ‘ኢትዮጵያ ነይ በመስከረም…’ እንዲሉ መስከረም ለኢትዮጵያ ውበቷ፣ ቀለሟ፣ ትዕምርቷ፣ የባህር ሃሳቧ መባቻ ነው። ተናፋቂው መስከረም ዝም ብሎ ወር ብቻ አይመስልም። እውቁ ሠዓሊ እና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ መስከረምን “… በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፤ ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን…” ሲል የአዲስ ተስፋና መንፈስ መሻቱን አሳይቷል። ተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ደግሞ “… መስከረም ለምለሙ፣ መስከረም ለምለሙ፣ ብሩህ ዕንቁጣጣሽ ደስታ ለዓለሙ…” ትለዋለች መስከረምን ስታዜመው። እንደየ ንፍቀ ክበቡ ዓመታት በወራት ሲመነዘሩ የራሳቸው መልክና መገለጫ አላቸው። ኢትዮጵያም ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር በሰባት ዓመት ከስምንት ወራት ልዩነት ያለው የራሷ የዘመን ቀመር አላት። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 13 ወራት ሀገር ነች። ወራቱም መጸው(መኸር)፣ ሐጋይ(በጋ)፣ ፀደይ(በልግ) እና ክረምት በሚል በአራት ወቅቶች ይከፈላሉ። ወቅቶቹም የራሳቸው ጸባይ፣ ክዋኔ፣ ትውስታና ትዕምርት ይቸራቸዋል። እያንዳንዱ ወርም እንደዚሁ። ከዘመን መባቻው መስከረም እስከ ማዕዶተ-ዘመኗ ጳጉሜን ወራቱ በሰማይና በምድሩ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ውቅራቸው ግላዊ ገጽታ ይነበብባቸዋል። የወራቱ ቅላሜ እና ሕብርነት ልዩ መልክዓ-ኢትዮጵያን ይፈጥራል። ‘የ13 ወር ፀጋ’ የሚለው መጠሪያም በ‘ምድረ ቀድምት’ እስኪተካ ድረስ ለብዙ አሥርት ዓመታት መለያ ሆኖ ዘልቋል። ይህን መለያ ስም ያወጡት እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት የሚሰኙት አቶ ኃብተሥላሴ ታፈሠ “ኢትዮጵያ የ13 ወራት ፀሐይ ባለቤት ናት። ስያሜው ከምንም የፖለቲካና ሃይማኖት ጋር ንክኪ የለውም” ብለው ነበር። የኢትዮጵያ ወራት ስያሜ ከመልክና ግብራቸው ይመነጫል። የወራት መባቻው መስከረም እንደዛው። ሊቃውንት መስከረምን ሲፈትቱት መስ - 'ዐለፈ፤ ከረመ' ይሉትና “ክረምቱን ማስከረሚያ፤ የጥቢ መባቻ" ወርኅ ሲሉ ያመሰጥሩታል። መስከረም ዘመን ያስረጃል፤ አዲስ ሕይወትና ተስፋ ደግሞ ይደግሳል። አንዳንዴም ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎም ይጠራል፡፡ 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ከሚሰባረቅባቸው ወራት አንዱ መስከረም ነው። መስከረም አገርኛ አለባበስ፣ አገርኛ ዝማሬ፣ አገርኛ ጨዋታ፣ አገርኛ ትውፊትና ቀለም በመስከረም በዓላት በተግባር ይታያል። መስከረም ሁለንተናዊ ውበቱ ድንቅ ነው፤ ትዕምርቱም ጉልህ ነው። የመልክዓ-መስከረም ድምቀት ማሳያዎች ዘመን መለወጫ በኢትዮጵያ ዘመን ስሌት ቀለበት መስከረም 1 ቀን ዘመን ይለወጣልና። የዘመን መለወጫ በዓል ‘ርዕሰ ዓውደ- ዓመት’ ይሰኛል። የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም ለምን የዘመን መለወጫ እንደሆነ ሲያትቱ “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው” ይላሉ። በመስከረም ሌሊቱ ከቀኑ እኩል ነው። ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር “ቀዳማይ፣ ርዕሰ ክራሞት፣ መቅድመ አውርኅ፣ ርዕሰ ዐውደ-ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ” ይሉታል ወርኃ መስከረምን። እናም ዘመነ ማዕዶቷን፤ ወርኅ ተውሳኳን ‘ጳጉሜን’ ተሻግሮ መስከረምን መሳም ይጓ'ጓ'ል። የመስከረም ጥባት በአያሌው ይሻታል። 'መስከረም ሲጠባ ወደ አገሬ ልግባ …’ እንዲሉ የተሰደዱት በአዲስ ዓመት መባቻ የአገራቸውን አፈር ለመሳም ያማትራሉ። ’አበባዬ ሆይ፤ አበባዬ ሆይ’ የሚሉ ሕፃናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፤ የ’ዕደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይንቦጫረቃሉ። በዚህ ድባብ ነው እንግዲህ መስከረምን የግዑዛንም የሕይወታውያንም የነፃነት፣ የተስፋና የፍቅር ወርኅ ተደርጎ የሚናፈቀው። የብዙ ሺህ ዘመናት ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ አዱኛ ሳይርቃት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጠላት ፍላፃዎች እና በድንቁርና ብዛት... ሰንኮፎቿ ሳይነቀሉ በመልከ-ብዙ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ዛሬ ደርሳለች። ጊዜው የኢትዮጵያን መስከረም ያስናፍቃል። ዕንቁጣጣሽ መስከረም በአደይ አበባ የሚያሸበርቅ ወር ነው። የነገረ-ዕንቁጣጣሽ የትመጣ መልከ-ብዙ አተያዮች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባ መፈንዳት ለማመላከት እንደሆነ የሚጠቅሱ አሉ። ንግሥት ሳባ /አዜብ/ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የእጅ መንሻ ይዛ ስትሄድ ንጉሡም “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በሚል ቀንና ከሌሊት የሚያበራ ቀለበት ስለሰጣት ነው የሚል አፈታሪክም ይነገራል። የስያሜው መነሻ ያም ሆነ ይህ መስከረም ለመልክዓ-ምድሩ፣ ለሰውና ለእንስሳት ሁሉ ‘ፍስሐ ወተድላ’ የሆነ ወር ነው። በመስከረም ምድር በዕንቁጣጣሽ ትፈካለች፤ በአበቦች ታጌጣለች፤ ውኆች ይጠራሉ። ሰማዩም የክብረ-ሰማይ ብርሃኑን ያጎላል። ጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት እንደፈንዲሻ በዲበ-ሰማይ ይደምቃሉ። ዕጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሳር እየነቸረፉ ይቦርቃሉ። እርሻ የከረሙ በሬዎች፣ ጭነት የከረሙ አህዮች መስከረም አንጻራዊ የእፎይታ ወራቸው ነው። ነጎድጓድ በአዕዋፋት ዝማሬ ይተካል። ንቦች አበባ ይቀስማሉ፤ ቀፏቸውን ያደራሉ። ቢራቢሮ ሳትቀር ‘በመስከረም ብራ ከኔ በላይ ላሳር..’ ብላ ትከንፋለች። በ’ዕንቁጣጣሽ’ ምድር ብቻ አይደለችም የምትዋበው። መስከረም ለሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸት እና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብባል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ ይናፈቃል። የተጠፋፋ ዘመድ አዝማድ ይገናኛል። ‘ሰኔ መጣና ነጣጠለን’ ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና ‘መስከረም ለምለም’ ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፤ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፣ ትኩስ ቡና ይሽታል። ደመራ ወመስቀል ሊቃውንት የደመራን የትመጣን ሲፈትቱ ‘ደመረ፣ ተሰባሰበ’ ይሉታል። ጎረቤት፣ የሩቅ የቅርብ ዘመድ አዝማድ ተደምሮ የሚከውነው ነውና። ነገረ መስቀሉ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱ ብዙ ነው። መስቀል በሃይማኖተ-አበው ሀተታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን፣ ለፍጡር የሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸበት ዓርማ ነው። በዚህም መስቀልን አማኝ ምዕመናን እና ካህናት የደኅንነትና የእምነት ምልክታቸው፤ የርኩስ መንፈስ ማባረሪያ መሳሪያቸው አድርገው ይመለከቱታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ‘ተቀጸል ጽጌ’ በሚል የክርስቶት መስቀል ግማድ (ቀኝ እጁ ያረፈበት ክፋይ) ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ኢትዮጵያ የገባበትን ቀን ታከብረዋለች፤ መስከረም 17 ቀን ደግሞ መስቀሉ የተገኘበትን። መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚከበረው የደመራ መስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ባህላዊ ትውፊትነቱ የጎላ በመሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ይናፈቃል። ደመራና መስቀል የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ… እሴቶች የሚገለጹበት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ነው። ደመራ እና መስቀል በዓላት ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓል ቢሆንም እንደየ አካባቢው ባህል፣ መንፈሳዊነት፣ ትውፊት፣ ዕውቀት አገርኛ ህብር ጥበባት የሚጎሉበት፣ አገር የውበት አክሊል የምትደፋበት ዕለት ነው። መስቀል የዓለማችን የማይዳሰስ የኢትዮጵያ ወካይ ቅርስ መዝገብ ሥር ሰፍሯል። በመስቀል አገርኛ ቀለም ይጎላል። 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ይሰባረቃሉ። የባህር ማዶ ጎብኚዎች በአግራሞትና መደነቅ ሲናገሩ ይደመጣሉ። የዕንቁጣጣሽ ተከታይ የመስከረም መልክ ነው መስቀል። የደመራ አደማመር እና ማብራት ሥነ-ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተመሳሳይ እንዳልሆነ ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ይተርካሉ። በትግራይ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በአዊና በከፊል ጎጃም ደመራ ማታ ላይ ተደምሮ ንጋት ላይ ይለኮሳል። በከፊል ጎጃም፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ በጉራጌ፣ በጋሞ፣ በወላይታና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ እንደየ አካባቢው ተለምዶ መስከረም 16 ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ ደመራው ይለኮሳል። መስቀል በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ርዕሰ ዓውደ-ዓመት ይመስላል። በደቡብ ኢትዮጵያ መስቀል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባህላዊ ጎኑ ይጎላል። ጉራጌዎች፣ ጋሞዎችና ሌሎችም መስቀልን ከሁሉም በዓላት የበለጠ ይናፍቁታል። የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት የፍቅር፣ የደስታና የእርቅ በዓል ነው መስቀል። በጋሞ ብሔረሰብ ባህል በዋዜማው ሰው ቢሞት እንኳን በሌሊት ተወስዶ ይቀበራል እንጂ ለቅሶ እንደማይለቀስ ይነገራል፤ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱም ልዩ መኖ እንደሚቀርብላቸው ይነገራል። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደሚባለው በጋሞዎች ደግሞ ‘ለመስቀል ያልሆነ ዱንጉዛ ይበጣጠስ’ በሚመስል መልኩ የባህል ልብስ አለባበስ እንደሚዘወተር መምህር ካሕሳይ (በሕብረ-ብዕር ድርሰታቸው) ጽፈዋል። መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ እንደ አውራው በዓል ይቆጠራል። ለመስቀል ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት ይደረጋል። አባወራው ሰንጋ ለመግዛት፣ እማወራ ማጣፈጫውን ለማዘጋጀት፣ ወጣቶች ደመራና ደቦት ለማዘጋጀት፣ ልጆች ምርቃት ለመቀበል የየራሳቸውን ይዘጋጃሉ። ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ለትዳር የደረሱ ሚስት የሚያጩበትና የሚመርጡበት ጥላቻና ቂም በፍቅርና በይቅርታ የሚታደስበት ነው። በጉራጌዎች ዘንድ መስቀል ትልቅ ቦታ ይቸረዋል። መስቀል እንደየአካባቢውና ባህሉ የሚናፈቅበት ዕልፍ ገጽታዎች አሉት። ለምሳሌ እኔ በተወለድኩበት ገጠራማ አካባቢ ያለውን በወፍ በረር እንቃኘው! በደመራ ዋዜማ ቀናት ልጆች ተራራ ለተራራ፣ ወንዝ ለወንዝ፣ ቋጥኝ ለቋጥኝ በልጅነት ወኔና ስስት በመዞር ለደመራ የሚሆን እንጨት፣ አደይ አበባ፣ ደቦት(ችቦ) ያጠራቅማሉ። ልክ መስከረም 16 አመሻሽ ከብቶች ወደ ግርግም ከገቡ የመንደሩ ወጣቶች ወደ ‘አፋፍ’ ይወጣሉ። ደመራ ወደሚደመርባት ሥፍራ። ሁሉም የአንድ ዕድር አባላት ቤተሰብ ተወካዮች ባሉበት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የደመራው ሥራ ይጠናቀቃል። ደመራው ሲጠናቀቅ ወደየ ቤታችን እንበታተናለን። (አዲስ አበባን ጨምሮ በከተሞች እንደሚደረገው በመስከረም 16 አመሻሽ ደመራው አይለኮስም። ይልቁኑ መስከረም 16 ለ17 አጥቢያ ጀምሮ ይለኮሳል እንጂ።) ለመስከረም 17 አጥቢያ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ሰው ከየቤቱ ደቦቱ (ችቦውን) እየለኮሰ ‘እዮሃ ደመራ’ እያለ ወደ ደመራው ሥፍራ ይተማል። እንደየ ግለሰቡ ቤት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ሊጠይቅ ይችላል። የመስከረም እኩሌታ አረንጓዴያማ ውብ ማሳ ከየቤቱ ከሚወጡ የችቦ እሳት ነበልባል ብርሃን ይታጀባል። ከሌሎች አጎራባች የመንደር ደመራዎች ቀድሞ ለመለኮስ ጉጉቱ የትየለሌ ነው። ከቤት እስከ ደመራው ሥፍራ እስኪደርሱ ድረስ ሰዎችን፣ በረት ያሉ ከብቶቹንና የጓሮ አዝመራውን ጨምሮ ሕይወታዊያንን በሙሉ “እንጎረጎባህ፤ እንጎረጎባችሁ” ይባላል። የተጠያቂው ሰው ምላሽ ደግሞ “ዓመት ዓመቱን ያድርስህ” የሚል ይሆናል። ከደመራ ግጥም ተዘውታሪ ስንኞች መካከልም፡- “እዮሃ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሃ አረሬ አረሬ፣ መስቀል ጠባ ዛሬ፣ በሸዋ በትግሬ…” የሚለው ይጠቀሳል። ከደመራው ሥፍራ ስንደርስ የ’እንጎረጎባህ!’ ድምፆች ይበረታሉ። የ’ዓመቱን ያድርስህ’ መልስ ካልሆነም እኩይ አፀፋ ይኖራል። ሁሉም ከተሰባሰበ በኋላ ደመራን የሚያሞካሹና የአዲሱን ዓመት መልካምነት የሚመኙ ‘እዮሃ አበባዬ” ግጥሞች እየተደረደሩ ደመራው ሦስት ጊዜ እንቧለሌ ይዞራል። በዕድሜ ታላቅ እና የተከበረ ሰው በቅድሚያ ደመራውን ይለኩሳል። ቀጥሎ ሁሉም ወደ ደቦቱን(ችቦውን) ወደ ደመራው ውስጥ ያስገባል። ደመራውም ይቀጣጠላል። የእሳቱ ነበልባል በመስከረም የንጋት ውርጭና ብርድ ላይ ያይላል። ሁሉም በደመራው ዙሪያ ተኮልኩሎ የክረምት ወራት ትዝታ ይነሳል፤ ሹፈት፣ ቀልድና ቁምነገር በየፈርጁ ይሰለቃል። ሌሊቱ የአህያ ሆድ እስኪመስል ይቀጥላል። የተጣላም ይታረቃል። የደመራው አምድ (ምሰሶ) አወዳደቅ ለማየት ሁሉም በጉጉት ይጠብቃል። ምሰሶው ወደ ምሥራቅ ከወደቀ የጥጋብ ዓመት፤ ወደ ምዕራብ ከሆነ ግን የችጋር ዓመት ተደርጎ ይታመናል። ከደመራው ሁነቶች አንዱ ባህሉ የበቆሎ እሸት ናፍቆት ነው። የደመራው ምሰሶ ከወደቀ በኋላ በአቅራቢያ ካለ የበቆሎ ማሳ በቆሎ እሸት ይመጣል። በመስቀል ደመራ ፍም ተጠብሶ ይበላል። ባለበቆሎው ሰው ዓመታዊ ደንብ ስለሆነ የበቆሎ ማሳዬ ተጎዳብኝ ብሎ አይቆጣም። ከደመራው ዓመድ ግንባራችን ላይ መስቀለኛ ምልክት ማድረግ እና ‘የዛሬ ዓመት አድርሰኝ’ ስለት ይቀጥላል። ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመስል ልጆች በደቦ ወደ መንደር ለመንደር በመዞር ‘እንጎረጎባችሁ’ እንላለን። የቤቱ ባለቤትም በሳህን፣ ጣሳ ወይም ሌላ ዕቃ ጤፍ ዱቄት ይሰጣል። የሰበሰብነውን ዱቄት ይዘን ወደ ደመራው ሥፍራ እንመለሳለን። በደመራው ጉባዔ ተወስኖ ከዕድሩ ለተመረጠች ቀጭን እመቤት (ባለሙያ ሴት) ዱቄት ይሰጣትና በ17 ምሽት ለሚኖረው የእራት ሰዓት ዝግጅት በአነባበሮ መልክ ዱቄት አብኩታና ጋግራ ታቀርባለች። መስቀል የወል ክብረ በዓል ነው። የመስቀል ዕለት (መስከረም 17) በግ ይታረዳል። እህል ውሃ ቀርቦ የመንደሩ ሰው በጋራ ሲጫወት ይውላል፤ በሕብረት ይበላል። ለመስቀል የተጣላ ጎረቤት ይታረቃል። ልጆች በሕብረት ይቦርቃሉ። የመስቀል ትዝታ በእኛ መንደር ይናፈቃል። ሁሉም እንደየ ቀየው ትውፊት እና ልማድ ይህን ሁነት ይናፍቃል….!! ጊፋታ ጊፋታ/ ግፋታ ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን በለኬላ ትርጓሜው መሻገር ማለት ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት አንድ ብሎ የሚጀመርበት የአዲስ ዓመት መግቢያና የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ነው፡፡ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውንም ይገልጻል፡፡ ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ ዘንድ መስከረም ወር በገባ ከቀን 14 እስከ 20 መካከል የሚውለው እሑድ አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበር ዕለት ይሆናል፡፡ በዓሉ የሚውልበት እሑድ ስሙም ‹‹ሹሃ ወጋ›› የእርድ እሑድ ይባላል፡፡ እሑድ የአዲስ ቀን ብሥራትም ነው፡፡ ቀጣዮቹ የሳምንቱ ቀናት የየራሳቸው ስያሜና አከባበር አላቸው። ለአብነት ‹‹ጋዜ ኦሩዋ›› ማንሳት ይቻላል። የአዲስ ዓመት አራተኛ ቀን ነው። የሰፈሩ ወጣቶች በየመንደሩ በታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ደጅ ተሰባስበው የግፋታ በዓል ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ጋዜ በጋራ ሆነው ‹‹ሀያያ ሌኬ›› እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው የሚጫወቱበትና ልጃገረዶችን ሎሚ በመለመን የሚፈልጓትን የሚመርጡበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ልጃገረዶች አንድ ላይ ሆነው በየቡድን ቁጭ ብለው ወንዴና ሴቴን ከበሮ እየመቱ ‹‹ወላወላሎሜ›› እያሉ የሚመርጡትን ወንድ ሎሚ በመስጠት የሚመርጡበት፣ እንዲሁም ሴቶች ለሚዜነትና ለጓደኝነት ከመረጧት ሴት ጋር በጥርስ አንድ ሎሚን ለሁለት የሚከፋፈሉበትና ስማቸው ሲጠራሩ ‹‹ሎሜ ሎሜ›› የሚባባሉበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ዕለት ጋዜ ኦሩዋ ነው፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡ ዮ …ማስቃላ በጋሞዎች ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓል በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ «ዮ ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል። መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞን ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግበት ቀን ነው። ጋሞዎች ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል። ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ለቅመማቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ያጠራቅማሉ። በጋሞ ዞን የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋትም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል። ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው። በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው። የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ሕብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው። የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል ነው፤ ይህ ሥርዓት እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ። ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሰላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል። ያሆዴ መስቀላ የክረምቱ ወራት አልፈው መስኩ በልምላሜና በአደይ አበባ ሲያሸበርቅ በሃድያዎች ዘንድ ትልቅ ዝግጅት አለ - ያሆዴ መስቀላ። “ያሆዴ“ ማለት እንደ ብሔሩ የባህል ሽማግሌዎች ትርጓሜ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የሚል የብስራት ትርጉም ያለው ሲሆን ”መስቀላ” ማለት ደግሞ ብርሃን ፈነጠቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ያሆዴ መስቃላ ብርሃን ፈነጠቀ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል ትርጉም አለው። በዓሉ በወርኃ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን ወሩ ብርሃን፣ ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት፣ በረከት የሚሞላበት ተምሳሌት ወር ተደርጎ ይቆጠራል። የሃድያ አባቶች ”ከባለቤቱ የከረመች ነፍስ በያሆዴ መስቀላ ትነግሳለች“ የሚል ብሂል አላቸው። የሃድያ አባቶች እንደ ዘመን መለወጫ የመጀመሪያ ቀን አድርገው በመውሰድ ማንኛውንም ዓይነት ክስተት ከዚያ ጋር አያይዘው እንደሚቆጥሩ ይነገራል። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። በብሔሩ አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማኅበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ/ሼማታ/ሲሆን ይህ ማለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተደራጀ ቋሚ የሆነ ከአራት እስከ ስምንት አባላትን የያዘና በሥጋ ቅርጫ የተደራጀ ማኅበር ነው። የዚህ ማኅበር አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን በመቀናጀት የበዓሉ እለት ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ፤ በበዓሉ ወቅትም ለእርድ የሚሆን በሬ መግዣ ገንዘብ እንዳይቸገሩና በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሕብረታቸው ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለከብቶች የግጦሽ ሳር የሚሆን ቦታ ከልሎ በማስቀመጥ የበዓሉ ቀን ከብቶች ተለቀውበት እንዲጠግቡ የሚደረግ ሲሆን በአዲስ ዓመት መግቢያ እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም ቢሆኑ መጥገብ እንዳለባቸው እንዲሁም የጥጋብ ዘመን እንዲሆን በብሔሩ በዓሉ ለሰው ብቻ ሳይሆን እንሰሳትም ሆዳቸው ሳይጎድል አዲሱን ዓመት መቀበል እንዳለባቸው በመታመኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል። ኢሬቻ ኢሬቻ ከመስከረም ደማቅ መልኮች አንዱ ነው። ኢሬቻ የዘመነ መፀው መጀመሪያ ሁነት ነው። የኢሬቻ ክብረ በዓል ኢሬቻ ቢራ (መልካ) በሐይቆች ወይም በወንዞች ዳር የሚከበር ነው። ከክረምት ወደ መፀው መሸጋገርን ምክንያት በማድረግ የሚከወን የምስጋና በዓል ነው። በኦሮሞ ዘንድ ለዘመናት የሚከበር እና ከገዳ ሥርዓት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። ኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ ለፈጣሪ (ዋቃ) የክረምት ወቅትን በማሳለፉ፣ ወይንም ወደ አዲስ ዓመት በማሸጋገሩ የሚቀርብ ምስጋና ነው። ‹‹ዋቃ›› ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሒደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ‹‹ኢሬቻ ሰላም ነው፣ ሰላም ጥልቅ ትርጉም አለው፣ ሰው ከሰው ጋር፣ ሰው ከራሱ ጋር፣ ሰው ከተፈጥሮ ጋርና ሰው ከፈጣሪው ጋር ሰላም ሊኖረው ይገባል፤›› የሚለው ጽንሰ ሐሳብ የክብረ በዓሉ ጭብጥ ነው፡፡ ለሕዝቡና ለአገሩ ምርቃትና መልካም ምኞት የሚገለጽበትም ነው-ኢሬቻ። ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ሥፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታልኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ እንደ ዕንቁጣጣሽ በመስከረም ጥባት ውሃ ጎድሎ፣ የተራራቀ ዘመድ አዝማድ የሚገናኝበት ነው። በተለያዩ ጸሐፍት እንደተጠቀሰው፣ ኢሬቻ አንድም ‘ዋቃ’ ከብርድና መብረቅ፣ ከጎርፍ፣ ከአውሎ ነፋስ እና መሰል የክረምት ተፈጥሯዊ ክስተቶች ጠብቆ ወደ ብራ እና ፀሐያማው የመፀው ወቅት በሰላም ስላሸጋገረ፣ አንድም በዋቃ ፈቃድ ዝናብ ዘንቦ፣ መሬቱ ረስርሶ፣ አዝመራው ለምልሞ፣ መልካም ፍሬ በመታየቱ፣ እሸት በመስጠቱ ስለማያልቀው ቸርነቱ ለማመስገን ነው። ከክረምቱ ጨለማ ወደ ብርሃን የማለፍ ብሥራት ነው ኢሬቻ። በሌላ በኩል ደግሞ መጪው አዲሱ ዓመት የተባረከና የተቀደሰ፣ የደስታና የብልፅግና፣ የተድላና ፍስሃ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞትን የመግለጫ በዓልም ነው። በኢሬቻ ክዋኔ አባ ገዳዎችና የሕዝብ መሪዎች ይመርቃሉ። በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ አለባበሱን በማጌጥ ወደ ክብረ-በዓሉ የሚያመሩ ኢሬቻ አክባሪዎች እርጥብ ሳር እና አደይ አበባን ይይዛሉ። ከኢሬቻ ክብረ-በዓል የምርቃት ስንኞች መዘን እንሰናበት። “… ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
ያሆዴ- የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት
Sep 22, 2023 94
(በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና) ያሆዴ የሃድያ ብሔር የአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ በዓል ነው። በዓሉ ሲከበር ቂምና ቁርሾ ተወግዶ ያለፈው ዓመት መልካምና በጎ ያልሆነ ሁኔታ ታይቶ ለቀጣይ ስኬት አዲስ ተስፋና ልምላሜ ሰንቆ የሚሻገሩበት በዓልም እንደሆነ ይነገራል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሃድያ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ እንዳሉት ሃድያ የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ባህል፤ ልማድ፤ ወግና ስርዓት አለው። ለዚህም እንደ ማሳያ በብሔሩ ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረውን የያሆዴ ክብረ በዓል ለአብነት ጠቅሰዋል። በዓሉ የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሚመጣው ዘመን የስኬት እንዲሆን እያንዳንዱ ካለፈው ዓመት ስኬትና ውድቀት ልምድ እየቀመረ ሃገር ሰላም እንዲሆን ተመራርቀው በደስታ እየተበላ፤ እየተጠጣ የሚከበር በዓል መሆኑንም ተናግረዋል። በብሔሩ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የያሆዴ ክብረ በዓል አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበትም ነው። በዓሉ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ክዋኔዎች የሚከበር ሲሆን በዓሉ መቅረቡን ታዳጊ ልጆች በተለያዩ ገላጭ በሆኑ ድርጊቶች እንደሚያበስሩ አቶ ታምሬ ተናግረዋል። በተለይም ታዳጊዎቹ ያሆዴ መድረሱን ለማብሰር ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ድረስ በብሔሩ አጠራር ገምባቡያ ወይም (ዋሽንት) በመጠቀም የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎችን በማሰማት በዓሉ መቅረቡን ያበስራሉ። በሃድያ ብሔር ዘንድ የአዲስ ዘመን ብስራት “ያሆዴ" የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ በዓል መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በመስከረም ሰውና እንስሳ ከዶፍ ዝናብ፣ ከውርጭ፣ ከጤዛና ከጭቃ፣ ከጉም፤ ከጭጋግና ጽልመት ነጻ ይሆናሉ። ምድሩ በሃምራዊ ቀለም ደምቆ ያሸበርቃል። ፀሐይ ሙሉ ገላዋን ገልጣ ጸዳሏን ትሰጣለች። በመሆኑም በስራ የደከመ ሰውነት ዘና፣ የታመመ ቀና ይልበታል፣ ልጅ አዋቂ የደስታ ነጋሪቱን ይጎስማል፣ የፍቅር ጽዋ ይጠጣል፣ የአእምሮ እርካታ ይነግሳል፣ በሁሉም ነገር ደስታ ይሰፍናል ወርሃ መስከረም በጥጋብና ደስታ ይጀመራል ። በዓሉ ከመግባቱ በፊት የራሱ የሆነ የሥራ ክፍፍል ኖሮት ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው የቤተሰብ አባላት ሁሉም በየድርሻቸው ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚጠብቁት ተናግረዋል። ለአብነትም ለበዓሉ መድመቅ በዓሉ ከመድረሱ ሦስትና አራት ወራት በፊት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት የሚወጡት ድርሻ አላቸው። የሃድያ አባቶች የያሆዴን የዘመን መለወጫ በዓል የሚያከብሩት በቅንጅት አማካኝነት ከአራት እስከ ስድስት ሰው በመሆን ተቀናጅተው ሰንጋ በመግዛት ነው። ለበዓሉ ሰንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ማስቀመጥ የሚጀምሩትም ቀደም ብለው ነው ። እናቶች በዓሉ ከመቃረቡ ከሦስትና እና አራት ወራት በፊት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ለማጠራቀም በሚገቡት (ዊጆ) በተሰኘ ዕቁብ ቅቤ ማከማቸት ይጀምራሉ። በተጨማሪም ለስጋ መብያና ለአተካና መስሪያ የሚሆን እንሰት በመለየትና በመፋቅ፣ ቆጮ፣ ሜሬሮና፣ ቡላን ጨምሮ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት የድርሻቸውን ይወጣሉ። የደረሱ ልጃገረዶች የቤቱን ወለል ቆፍረው ይደለድላሉ፣ የተለያዩ ውበት የሚሠጡ ቀለማትንና የተለያዩ ኖራዎችን በመጠቀም የቤቱን የውስጥና የውጭ ግርግዳን በመቀባት ያስውባሉ። ወጣቶች ከነሐሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚመርጡላቸውን ዛፍ፣ ግንድ ቆርጠው ለምግብ ማብሰያና ለደመራ የሚሆን ችቦ የማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይቆያሉ። ከመስከረም መግቢያ ጀምሮ ያሉ የቅዳሜ ገበያዎች ስያሜ (መቻል ሜራ ) የእብድ ገበያ በመባል ይጠራሉ።እነዚህ የግብይት ቀናት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የግብይት ቀናት በተረጋጋ መንገድ የሚተገበሩ ባለመሆኑና በጠዋት ቆሞ በጊዜ የሚበተን ገበያ በመሆኑ (መቻል ሜራ) የእብድ ገቢያ የሚል ስያሜ አሰጥቶታል ነው ያሉት አባቶች ሰንጋ ገዝተው ለመብላት ባደራጁት (ቱታ) ቅንጃ አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ ወደ መቻል ሜራ (እብድ ገበያ) በመሔድ የሚፈልጉትን ሰንጋ ገዝተው ይመለሳሉ። ገንዘብ ያላስቀመጡና በወቅቱ ማግኘት የማይችሉ አባወራዎች በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲያሳልፉ ሌላኛው አማራጭ (ሃባ) በመባል የሚታወቅና ምንም ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ለበዓሉ የሚሆን ሰንጋ በብድር የሚወስዱበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የኖረ የመተጋገዝና የመተሳሰብ እሴት አንዱ ነው። የሚፈልጉትን ሰንጋ ከመረጡ በኋላ እህል በሚደርስበት በታህሳስና በጥር ለመክፈል በዱቤ ይወስዳሉ። የበሬ ነጋዴውም ያለ ማንገራገር ሰንጋውን በመስጠት ወቅቱ ሲደርስ ገንዘቡን ለመውሰድ ተስማምቶ ይሰጥና ወቅቱን ጠብቆ ገንዘቡን ይወስዳል። በትውስት ተወስዶ ገንዘብ ያልከፈለ አባወራ ለቀጣይ የዘመን መለወጫ አይደርስም ተብሎ በብሔሩ ዘንድ ስለሚታመን በተስማሙበት ወቅት ገንዘቡን የመስጠት ግዴታቸው የተጠበቀ ነው። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የመምሪያው ባለሙያ አቶ ይዲድያ ተስፋሁን እንዳሉት በዓሉ ያለው ለሌለው አካፍሎ በጋራ የሚበላበትና ወደ አዲስ ዘመን በጠንካራ አብሮነት የሚሻገሩበት ነው። በመሆኑም የያሆዴ በዓል በዜጎች መካከል ጠንካራ አንድነትና አብሮነትን መሰረት ያደረጉ ዕሴቶች ያሉበት መሆኑን አንስተው ለትውልድ ግንባታ የሚሆኑ ዕሴቶችን አጎልብቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል ። ለበዓሉ ዋዜማ ከሚዘጋጁ ሁነቶች መካከል አተካና ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። አተካና በተለይም ለዚህ በዓል ከዚህ ባሻገር ለትልልቅ እንግዶች ከሚዘጋጁ ምግቦች መካከል አንዱ ነው። አተካና ከወተት፣ ከቅቤ፣ አይብና ቡላ የሚዘጋጅና በበዓሉ የምግብ ፍላጎትን የሚከፍት ተበልቶ የማይጠገብ በእናቶች የሚዘጋጅ ጣፋጭ ምግብ ነው። የበዓሉ ዋዜማ አተካን ሂሞ (የአተካና ምሽት) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በዓሉን ለማክበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበ ቤተሰብና እንግዶች በናፍቆት የሚመገቡት ምግብ ነው። በዚሁ ዕለት በአካባቢው ትልቅ የሚባል አባወራ (አዛውንት) ቤት ችቦ (ሳቴ ) ተዘጋጅቶ ማምሻውን አባቶች ወይም የሃገር ሽማግሌዎች የማቀጣጠያ (ጦምቦራ) ደመራ ማቀጣጠያ ይዘው ይወጣሉ። ከዚያም የአካባቢው ማህበረሰብም የሃገር ባህል ልብስ ለብሰው እንዲሁም ወጣቶች ተሰብስበው ያሆዴ ይጨፍራሉ። የሃገር ሽማግሌዎች ይመርቃሉ፤ ከዚያም የተዘጋጀውን ችቦ በእሳት ለኩሰው ያበራሉ። ይህም አዲስ ዘመን መግባቱን ማብሰርና ዓመቱ የብርሃን ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞት የሚገለፅበት ነው። ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ ወጣቶች ያሆዴ (ኦሌ) ጭፈራ ሲጫወቱ ያነጋሉ። ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ አይጨፈርም። ወጣት ደመቀ አባቴ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪ ሲሆን ስለ በዓሉ አስተያየቱን ሲሰጥ ''በአባቶች ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ እኛ ወጣቶች ያሆዴ ....ያህዴ....ሆያ ሆ... /ኦሌ/ ጭፈራ እየተጫወትን እናነጋለን፤'' ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ ስለማይጨፈር በዓሉን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁት ተናግሯል። ተራርቀው የቆየ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ ያለምንም ልዩነት ችግርም ካለ በዕርቅና ሰላምን በማውረድ የሚመጣው ዘመን የልምላሜና የስኬት እንዲሆን ተመራርቀው የሚለያዩበት በዓል በመሆኑ በተስፋ የሚጠብቁት እንደሆነ ነው ወጣቱ የሚናገረው። የበዓሉ እለት ለዕርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኃላ የባህል ሽማግሌዎች (ጋቢማ ) ሥርዓት ያከናውናሉ። ክዋኔውም የበሬውን ሻኛ በለጋ ቅቤና በሠርዶ ሳር በመቀባትና ወተት በማፍሰስ ይከናወናል። ይህም በሚከናወንበት ወቅትም ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሃገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን በማለት (ፋቴ) ዳግም ምርቃት ፈጽመው በሬው ይጣልና የዕርድ ሥርዓት ይካሔዳል። በዕለቱም ከታረደው ሥጋ ቅምሻ በጋራ ይበሉና ቀሪውን ለማህበሩ (ለቱታ) አባላት ክፍፍል ይፈፀማል። ከእርድ ሥርዓቱ በኃላ በማግስቱ ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ዘራሮ የሚባል አበባ ይዘው እየጨፈሩ ያስማሉ -ይመረቃሉ የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባባላሉ፤ ከስጋውም ፣ከቦርዴውም ፣ ከአተካናውም የሚመገቡበት ክዋኔ (ሚክራ) በመባል ይታወቃል። ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ስጋና (ዘራሮ) አደይ አበባ ጭምር ይዘው የሚሔዱበት እንዲሁም ያላገቡ ወጣቶች ለትዳር የሚሆናቸውን አጋር የሚፈልጉበትና የሚያጩበት ባህልም ያለው ነው ያሆዴ ክብረ በዓል። ከእርድ ስነ ስርዓቱ በኋላ ከሶስት ሳምንታት እስከ ወር ለሚሆን ጊዜ የመጠያየቂያና የመረዳጃ ወቅት ይሆናል። የያሆዴ በዓል ያሉ ዕሴቶች ለህዝብ ትስስር፣ ጠንካራ የስራ ባህልና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማላቅ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደምገባ የሚያነሱት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የአቶ ዳንኤል ገዴ በዚህ ላይ በአከባቢው ያሉ የማህበረሰብ ልምዶችና ወጎች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መስራትና የሃገር በቀል ዕውቀትን ማጠናከር እንደምገበባ ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የዋቸሞ ዩኒቨረሲቲ የሃድያን ብሔር የዘመን አቆጣጠር ታሪክ : ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሌሎች ዕሴቶች ተሰንደው እንዲቀመጡና ለማስተማሪያነት እንዲውሉ ለማስቻል በጥናትና ምርምርና የተደገፈ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም ባህሉ ይበልጥ እንዲታወቅና በዩኔስኮ ተመዝግቦ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚገባውን ጥቅም እንዲያመጣና ከቱሪዝም አንጻር ሚናውን እንዲጫወት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የመኔ ሸድዬ ባሮ - የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት
Sep 20, 2023 594
በሽመልስ ጌታነህ (ኢዜአ) የመኔ ሸድዬ ባሮ የካፈቾ ብሄር ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ የሚሸጋገሩበት፣ የአዲስ ዘመን ብስራትና የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት በዓል እንደሆነ ይነገርለታል። በዚህም የካፋ ብሄር ለዘመናት የገነባውና ጠንካራ የስራ ባህል፤ ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ እንዲሁም ከተለያዩ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የሚኖር ሲሆን ቱባ ዕሴቱ ዛሬም ላለው ትውልድ መሰረት መሆኑን ያምኑበታል። የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ከሆነ የካፋ ህዝብ ጠንካራ ንጉሳዊ ሥርዓት የነበረው፤ የታሪክና የቱባ ባህል ባለቤትም ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ባለሙያና የሀገር ሽማግሌ አቶ አሰፋ ገብረማሪያም የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በሃገሬው አጠራር ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል የካፋ ህዝብ ከሚያከብራቸው በርካታ በዓላት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በዓሉ ያለውን ግዝፈት ሲያመለክቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ፀሐፍት ጭምር “ታላቁ በዓል ወይም (ግሬት ፌስቲቫል)” ተብሎ እንደሚጠራም ተናግረዋል። በዓሉ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዳራ ያለው ሲሆን ከጥንት ካፋ ንጉስ ጀምሮ በየአመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል እንደሆነም ጠቁመዋል። የካፋ ህዝብ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከጎሳ መሪነት አንስቶ ጠንካራ የመንግስት መዋቅር የነበረው ታላቅ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት አቶ አሰፋ፣ በዚህም በዓሉ በዘመኑ የነበሩ መንግስታት በዓል እንደነበረም አብራርተዋል። ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም የሚገመገምበት ጥሩ የሠራና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገበ የሚሸለምበትና ለበለጠ ሥልጣን የሚታጭበት፤ ሰነፉ ደግሞ የሚወቀስበትና ስልጣኑ የሚነጠቅበት ታላቅ በዓልም ነው ብለዋል። ይህም በብሄሩ ዘንድ ለዘመናት የተሻገረ የጠንካራ የሥራ ባህል ግንባታ መሰረት ሆኖ የቆየ መሆኑን አንስተዋል። ይህ ሁሉ ሲከናወን በማህበረሰባዊ የህግ ተገዥነት መሰረት መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸው ከሁሉ በፊት ሰላምን በማስቀደም መንግስትንና ህግን ማክበር እንዲሁም ህግ የሚመራው ህዝብ የበላይ መሆኑን አመላካች ሥርዓት መሆኑን አንስተዋል። በዓሉ ከአዝመራ ጋር የተያያዘ የዘመን አቆጣጠርን ተከትሎ እንደሚከበርም የታሪክ ባለሙያው አቶ አሰፋ ይገልጻሉ። እንደ ታሪክ ተመራማሪው ገለጻ የካፋ ህዝብ አብዛኛው አርሶ አደር አልፎም አርብቶ አደር ሲሆን ለአዝመራ የተለየ ትኩረት ይሰጣል፤ በዓሉ ሊከበር 77 ቀናት ሲቀሩት ህዝቡ የአዲስ ዘመን መለወጫ ብሎ ሃምሌ አንድ አዝመራውን እንደሚጀምርም ጠቁመዋል። የአዝመራ ወቅት ሊገባደድ 25 ቀናት ሲቀሩት (ከሼ ዋጦ) ብሎ አዝመራውን ያጠናቅቃል። ወቅቱም ጨለማው አልፎ በብርሃን የሚተካበት፤ ክረምቱ ለበጋ ቦታውን የሚለቅበት በመሆኑ አዲስ አመት መድረሱን ያሳውቃል። ያን ጊዜ በጥንት የካፋ ምክርቤት ከሚገኙ ሰባት የሚክረቾ አባላት ውስጥ አንዱ የሆነው አዲዬ ራሾ ፤ የንጉሱ መቀመጫ በሆነው ቦንጌ ሸምበቶ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫው ለሚመጣው ህዝብ መንገዶችን በማፅዳት እና ለወንዞች ድልድይ በማበጀት በዓሉ መድረሱን ያበስራል። ያን ጊዜ በዓሉን ለማክበር ህዝብ ከያለበት አቅጣጫ ወደ ቦንጌ ሸምበቶ ይተማል። ህዝቡ በቦንጌ ሸምበቶ ከተሰበሰበ በኋላም ንጉሱ በተገኙበት የእያንዳንዱ ወራፌ ራሾ ሥራ ይገመገማል፤ ጥሩ ሥራ የሠራ ጠንካራ መሪ ይሸለማል፤ ለበለጠ ስልጣንም ይታጫል፤ ሀላፊነቱን በተገቢ ሁኔታ ያልተወጣው ደግሞ ይመከራል፣ ይወቀሳል አልፎም ስልጣኑን ይነጠቃል። ዛሬም ሀገራችን ይህ አይነቱን ጠንካራ የሥራ ባህል አብዝታ ትሻለች፤ እንዲህ አይነት ሀገር በቀል ዕውቀቶች ትውልዱን በጠንካራ ሥነ-ምግባርና የሥራ ባህል ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው። በተጨማሪም በዓሉ ቅሬታዎችን ለመፍታትና ሰላምን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፤ ቂምና ጥላቻን ይዞ ወደ ንጉሱ ፊት መቆምም ይሁን ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር ነውር ተደርጎ የሚወሰድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ በዓሉ ከመምጣቱ አስቀድሞም ይሁን በበዓሉ ወቅት የተጣላ ይታረቃል፤ ጥላቻም በፍቅር ይተካል ብለዋል የታሪክ ተመራማሪው። እንዲህ አይነቱ ሀገር በቀል ዕውቀት ጠንካራ ባህል ለመገንባት፤ ቅራኔዎችን በሰላም ለመፍታትና ማህበራዊ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ስላላቸው በትምህርት ሥርዓት ውስጥ አካቶ ማስተማርና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌና የካፋ፣ጫራ እና ናኦ የባህል ምክርቤት አባል አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም እንደሚሉት የካፋቾ ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል ማህበራዊ ግንኙነትን በማጠናከሩ ረገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው። ምክንያቱ ደግሞ፣ በዓሉን ለማክበር በአካባቢው ያሉ፣ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እንዲሁም ባህር ማዶ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች የሚሰበሰቡበት ታላቅ በዓል ስለሆነ ነው ብለዋል። በዚህም የተራረቀ የሚገናኝበት፤ የተጠፋፋ የሚጠያየቅበት ሲሆን ህዝቡ በአንድ ላይ ተሰብስቦ በንጉሱ ተመርቆ፣ በልቶ ጠጥቶ እንዲሁም ተጫውቶ ወደ ቀጣዩ አመት በደስታና በታላቅ ተስፋ የሚሸጋገርበት እንደሆነም አብራርተዋል። ይህ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ከ120 ዓመታት በላይ ሳይከበር እንደቆየ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም ዳግም መከበር ከጀመረበት ስምንት ዓመታት ወዲህ የነበረውን ታሪክና ባህል በሚያስቀጥል መልኩ በየዓመት በድምቀት እየተከበረ መሆኑንም አንስተዋል። ወጣቱ ትውልድ ባህሉንና ታሪኩን አውቆ እንዲኖርና እንዲያስቀጥል ግንዛቤ የመፍጠርና የማስተማር ሥራ በሰፊው እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል። ከዚህ ባለፈም ባህሉንና ታሪኩን ለማስቀጠል የባህል ምክር ቤቱ የወረዳ የባህል ምክር ቤቶችን የማጠናከር፣ ታሪካዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና የማደራጀት ሥራ እየሠራ ነውም ብለዋል። በዓሉ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ጠንካራ የሥራ ባህልን የሚያበረታታ እና የተፈጥሮ ጥበቃን የሚያጠናክር በመሆኑ ከካፋ ብሔረሰብ በዓልነቱ ባለፈ የሀገርና የአለም ቅርስና ሀብት እንዲሆን ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ፀጋዬ አሳስበዋል። የካፋቾ ዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በዞን ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሾመ አምቦ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ በአደባባይ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በዓሉ በሁሉም የካፋ ህዝብ በጋራ ያለምንም ልዩነት የሚከበር ታሪካዊ በዓል ሲሆን አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከተለያዩ ምሁራንና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶች እየተሠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በበዓሉ ንጉሱ የተራቡትን የሚመግቡበት (ጮንጎ) የተሰኘ ስርዓት የሚፈፀምበትና የተጣሉ የሚታረቁበት ስርዓት እንደሚፈፀም የገለፁት አቶ ተሾመ አሁንም በዓሉ በየዓመቱ ሲከበር ይህ ሥርዓት ይከወናል ብለዋል። ቀጣይ ይህን በዓል በሰፊው አስተዋውቆ ወደ ቱሪዝም በማሳደግ ህዝቡ ከዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተጀመሩም ሃላፊው ገልፀዋል። የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል በቦንጋ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፓናል ውይይትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 4881
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 9876
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 3412
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 4197
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
“ዮ-ማስቃላ''- ሁሉም የሚደሰትበት በዓል
Sep 23, 2023 81
በሳሙኤል አየነው የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የሆነው የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ-ማስቃላ” ከወርሃ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል ። በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ተራርቀው የነበሩ ወገኖች ወደ የአካባቢያቸው በመመለስ ከቤተሰቦቻቸው ብሎም ከቀየው ህብረተሰብ ጋር አብረው የሚያከብሩት የዓመቱ ታላቅ በዓል ነው ። ታዲያ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ወንዶች ሰንጋ በሬ ለመግዛት እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻቸውና ለልጆቻቸው ልብስና ጌጣ ጌጥ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሴቶችም ለባህላዊ ምግቦች፣ ለቅመማ ቅመም፣ ለቅቤና ለባህላዊ መጠጦች እህል ግዥ የሚሆን ገንዘብ ዓመቱን ሙሉ ሲቆጥቡ ይከርማሉ። መስከረም ወር ከገባበት ዕለት አንስተው ወንዶችም ሆኑ ሴቶቹ በቆጠቡት ገንዘብ በየፊናቸው ለበዓሉ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይጀምራሉ። ይህም የዝግጅት ጊዜ “እንግጫ” በመባል ይጥራል። በ”ዮ--ማስቃላ” ጊዜ አብሮነት እንጂ ግለኝነት የሚባል ነገር በጋሞዎች ዘንድ ፈጽሞ አይታሰብም፤ አብሮ እርድ ማካሄድ፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጠጣት፣ አብሮ መጫወት የጋሞዎች መገለጫ ነው። እንደ ሌሎቹ በዓላት ሁሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችም በዓሉን እንዴት እናሳልፍ የሚል ስጋት አያድርባቸውም። ምክንያቱም የሌለውም ካለው ጋር አብሮ የሚቋደስበት፣ የሚደሰትበት፣ የሚተሳሰብበትና የሰብአዊነት ልክ የሚንጸባረቅበት ልዩ ድባብ ያለው በዓል ነውና ዮ-ማስቃላ ። የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ስለ “ዮ--ማስቃላ” በዓል በትንሹ እንዲያወጉን ጠይቀናቸው በዓሉ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትና አዕዋፋት ሁሉ የሚደሰቱበት እንደሆነ ነግረውናል። በአካባቢው ቋንቋ ተፈጥሮ ሁሉ በዓሉን በደስታ እንደሚያሳልፍ ለመግለጽ “ካፎስ ካናስ ማስቃላ” በማለት የሚገለጽ ስሆን “ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም መስቀል ነው” እንደማለት ነው ብለዋል። በዓሉ ከመድረሱ ከሶስት ወራት አስቀድሞ በየአካባቢው ለእንስሳት የግጦሽ ሥፍራ ተከልሎ የሚዘጋጅ ሲሆን ችቦው በሚለኮስበት በደመራው ዕለት የቤት እንስሳት በሙሉ በዚያው የሚሰማሩ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉ ሲያርሱ የነበሩ የእርሻ መሣሪያዎችም በበዓሉ ጊዜ ታጥበውና በቅቤ ታሽተው በክብር ይቀመጣሉ። ክብር ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለእርሻ መሣሪያዎችም ይሰጣል። በባህሉ መሠረት ችቦ በሚወጣበት ሰዓት አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶችን ጋጣና የበር ጉበኖችን ግራና ቀኝ በችቦው ጫፍ በማነካካት ወደ ውጭ ካወጣ በኋላ ወንድ ልጆች የየራሳቸውን ችቦ ተራ በተራ እየለኮሱ አባታቸውን ተከትለው “ዮ---ማስቃላ” እያሉ ወደ ደመራ ቦታ ያመራሉ። ከዚያም አባት በቅድሚያ ችቦውን ከለኮሰ በኋላ ልጆች ደግሞ ተከትለው ደመራውን ይለኩሳሉ። ከዚህ ፕሮግራም መልስ ወደ ቤት ተመልሰው የተዘጋጀውን ገንፎ በአንድ ወጭት ላይ “ዮ--ማስቃላ”እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ተሰባስበው በጋራ ይመገባሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል በዋናነት እርድ የሚከወን ሲሆን ቁርጥ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ክትፎና የወጣ ወጥ ዓይነቶች ተሠርተው ለምግብነት ይቀርባሉ። ከባህላዊ ምግቦች ደግሞ የገብስ ቅንጬ፣ የቆጮና ገብስ ውህድ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ ሀረግ ቦዬ፣ እንዲሁም ከመጠጥ አይነቶች ደግሞ ቦርዴ፣ ጠላ፣ የማርና የቦርዴ ጠላ ውህድና ሌሎች ተወዳጅ ምግቦችና መጠጦች ይዘጋጃሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል ዕለት የሚቀራረቡ ጎረቤታሞች በጋራ ሆነው አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ የእርድ ሥነሥርዓት ያከናውናሉ። የእርድ ሥነ-ሥርአቱም በደመራው ዕለትና ማግስት እንደ ህብረተሰቡ ይሁንታ የሚፈጸም ይሆናል። ከማግስቱ ጀምሮ የተዘጋጀውን ሥጋ በጋራ እየበሉና እየጠጡ የበዓሉን ድባብ የሚያስቀጥሉ ሲሆን “ዱንግዛ” በተሰኘው የጋሞ ባህላዊ ጥበብ ልብስ ደምቀው በጌጣጌጥ አሸብርቀው ሁሉም በየአደባባዩ በባህላዊ ጫዋታዎች እየተደሰተ በዓሉን ያከብራል። ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና አብሮነት ካለ በአዲሱ ዓመት ምድሪቱ ተገቢውን ምርት እንደምትሰጥ ሁሉም ሰው በተሰማራበት መስክ ውጤታማ እንደሚሆን ይታመናል። ከዚም የተነሳ በአሮጌው ዓመት ሃዘን ላይ የነበሩ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ሀዘናቸውን በመተው በአዲስ መንፈስ ወደ መደበኛው ህይወት ይመለሳሉ። የተጣሉ ወገኖች ቂም ይዘው አዲስ ዓመትን መሻገር በጋሞዎች ዘንድ ነውር በመሆኑ በባህላዊ ሸንጎ ሥርአት /ዱቡሻ/ በጋሞ አባቶች አሸማጋይነት እርስ በርስ ተነጋግረው በመታረቅ አዲሱን ዓመት በጋራ ያበስሩታል። በሌላ መንገድ “ዮ..ማስቃላ” በዓል ተጠብቆ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተጫጩት ደግሞ ጋብቻ የሚከውኑበት እንዲሁም ያገቡት በየገበያው ዕለት “ሶፌ” የሚባል ሥነ-ሥርዓት በማከናወን በማህበራዊ ህይወት ማህበረሰቡን በይፋ የሚቀላቀሉበት መሆኑን ጋሽ አመሌ አውግተውናል። ጋሞዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በአብሮነት ለሁለት ሳምንታት በደስታ ካሳለፉ በኋላ ወደ ግብርና ሥራቸው በመመለስ ቀደም ሲል በክብር ያስቀመጧቸውን የእርሻ መሣሪያዎች በማንሳት ወደ እርሻ ሥራ ይገባሉ። እስከ ታህሳስ ወር መውጫ ድረስ የበዓሉ ድባብ ሳይጠፋ ይቆይና በመጨረሻም የመሰናበቻ ድግስ ወይም “ጮዬ ማስቃላ” በማዘጋጀት በህብረት ከተመገቡና ከጠጡ በኋላ የዓመት ሰው ይበለን፣ ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ይሁን በማለት በመመራረቅ “ዮ--ማስቃላ”ን ይሸኛሉ። በዓሉ የህዝቡን ሰላም ፣አንድነትና አብሮነት የሚያንጸባርቅ ልዩ በዓል ነው በማለት የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ የጋሞ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት የአቶ አመሌ አልቶን ሃሳብ ይጋራሉ። ባህላዊ እሴቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጠብቆ እንዲቆይ “ዮ--ማስቃላ” ትልቅ ድርሻ አለው። የባህል እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በጥናትና ምርምር በማስገፍና የቋንቋና ባህል አውደ ጥናት በየዓመቱ እየተደረገ እንደሆነም ነግረውናል። አባቶች በልዩነት ውስጥ ያለንን አንድነት እንዳቆዩልን ሁሉ ወጣቶችም ኢትዮጵያዊ ለዛ ያላቸው የጋራ እሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ጠብቀው ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለባቸው የሚለውን የንግግራቸው ማሳረጊያ አድርገዋል።
የዕልፍ ሕጻናትን ዕጣ ፈንታ ከሞት ወደ ሕይወት የለወጠው ወጣት ላሌ ላቡኮ
Sep 8, 2023 482
በሀገራችን በርካታ አካባቢዎች የታዳጊዎችን ተስፋና ህልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የሚገዳደሩ ከባህላዊ እምነት ጋር የተቆራኙ አይነተ ብዙ ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች እና ክዋኔዎች አሉ። ለአብነትም ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የተለመደው እና ከህጻናት ጥርስ አበቃቅል ጋር የተያያዘው ’ሚንጊ' የሚሰኘው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ይጠቀሳል። በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል። ከዚህ ጋር በማገናኘትም የሚወለዱ ህጻናት የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ከሆነ እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ይህ ልማድ “ሚንጊ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አያሌ ህጻናትን ቀጥፏል። ይህ ብቻም ሳይሆን የማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። ሚንጊ ተብለው የተፈረጁ ህጻናት በማህበረሰቡ ዘንድ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… እንደሚያመጡ ስለሚቆጠር ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል ዕጣ ይገጥማቸዋል። ሚንጊንና መሰል በየማህበረሰቡ ዘንድ ለዘመናት የተለመዱ ጎጂ ድርጊቶችን ለማስቀረት እና ማህበረሰብ አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ግን ውስብስብ እና ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ላሌ ላቡኮና መሰል ብርቱና አርቆ አሳቢ ሰዎች ግን ባደጉበት ብርቱ ጥረት የማህብረሰብን አስተሳስብ በመለወጥ ለዘመናት ለሚከወኑ ውስብስብ ችግሮችን መፍትኤ መስጠት ችለዋል። ላሌ ላቡኮ በተወለደበት ቀዬ እና አባል በሆነበት ደመ ከልብ ሆነው የሚቀሩ ህጻናትን ዕጣ ፈንታ ከወንዝ፣ ከገደልና ከጫካ ከመጣል ተርፈው ለወግና ማዕረግ እንዲበቁ አስችላል። በአጉል ባህል ሕይወታቸውን የሚነጠቁ ዕልፍ አዕላፍ ህጻናት ነፍስ እንዲዘሩ በማድረግ ትውልድ ያሻገረ፣ ማህበረሰብን የለወጠ አርበኛ ነው። ላሌ ላቡኮ ይህን ነባር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለመቃወምና መፍትሄ ለማምጣት ያነሳሳው ሁለት እህቶቹን ጨምሮ ምንም ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት በሚንጊነት ተፈርጀው ሲቀጠፉ በማየቱና በመስማቱ እንደሆነ ይናገራል። ከ17 ዓመታት በፊት ‘ኦሞ ቻይልድ’ በሚል ባቋቋመው ድርጅት 'ሚንጊ' የተባሉ 58 ሕፃናትን ከገዳዮች ፈልቅቆ ከሕልፈት ወደ ሕይወት ለውጧል፣ ለቁም ነገር ለማብቃትም እያስተማራቸው ይገኛል። እህቶቹን ጨምሮ የትውልድ መንደሩ ሕጻናትን ሕይወት ለመቀጠፍ የዳረጋቸው የሚንጊ ድርጊት የሚፈጸመው፣ በማህበረሰቡ ዕውቀት ማነስ ነው ብሎ ያምናል። በዚህም ይህን አስከፊ ድርጊት እና አስተሳሰብ ለመቀየር ቆርጦ በመነሳቱ ቤተሰቡን ጨምሮ ከማህበረሰቡ መገለል እስከ ማስፈራሪያ ጥቃቶች አስተናግዷል። እርሱ ግን ፈተናዎች ሳይበግሩት በዓላማው ጸንቶ፣ ትዕግስትና ብልሃት ተላብሶ ሸውራራ ማህበረሰብ አቀፍ አመለካከቶችን መስበር ችሏል። የሚንጊ ባህል አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀረፈ የሚናገረው ላሌ፣ ስር ነቀል የአስተሳስብ ለውጥ ለማምጣት ለህብረተሰቡ አሁንም ብርቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እንደሚገቡ ገልጿል። ላሌ በመሰረተው ድርጅት ከሚማሩ ሕጻናት ባሻገር ከ300 በላይ ህጻናት ከቤተሰባቸው ዘንድ ሆነው ለመማር እንዲችለኩ ማድረጉንም ይናገራል። ሕፃናቱን ከሞት አፋፍ ታድጎ ከራሳቸው ሕልውና ባለፈ ለቁም ነገር እንዲበቁና ለሀገርና ለወገን የሚበጁ ሰዎች እንዲሆኑ በመስራቱ አዕምራዊ እርካታ እንደሚሰማው ይገልጻል። ላሌ የሚንጊን ጎጂ ድርጊት ከመታደጉ በተጨማሪ በደቡብ ኦሞ ትምህርት ቤት ገንብቶ ከ700 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ናሽናል ጂኦግራፊ፣ ቴድ ቶክ፣ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም እና የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት የላሌን ትውልድ የመታደግ ተግባር ዕውቅና ከሰጡት ወስጥ ይጠቀሳሉ።