የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም ብሄራዊ የልማት እና የዘርፎች እቅድ ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ማካሄድ ጀመረ 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2017 (ኢዜአ)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም ብሄራዊ የልማት እና የሁሉም ዘርፎች እቅድ ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። 


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2017 የሥራ ዘመን ትርጉም ያለው እና ለመጪው የ2018 የቀጠለ የእድገት ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚሆን እድገት መመዝገቡን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። 

በዚህ መነሻም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመጪው ዓመት ለትግበራ የተዘጋጀውን የ2018 የተሟላ የሁሉም ዘርፎች እቅድ እና ሀገራዊውን የልማት እቅድ ግምገማ ማድረግ መጀመሩን ተናግረዋል። 


 



ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ከግምገማ እና ውይይቱ ጎን ለጎን የአረንጓዴ ዐሻራቸውን እንዳሳረፉም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም