ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሕልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፤ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ስም ለሙሃማዱ ቡሃሪ ቤተሰብ፣ ለናይጄሪያ ሕዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።

በዚህ የሀዘን ጊዜ ሀሳባችን ከእናንተ ጋር ነው ሲሉም ገልጸዋል ።

ሙሃማዱ ቡሃሪ ዛሬ እሁድ ከሰአት በኋላ በለንደን በሚገኝ ክሊኒክ ውስጥ በህክምና ላይ እያሉ በ82 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ሲጂቲኤን ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሶ ቀደም ሲል ዘግቧል።

#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም