አልጄሪያ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጨረሻ መርሃ ዛሬ ማምሻውን ተደርጓል።

በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናይጄሪያ እና አልጄሪያ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍጻሜ ገብታለች።

አስቀድማ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለችው የዘጠኝ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ናይጄሪያ በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ ሆና አጠናቃለች።

በዚሁ ምድብ በፔሬ ጄጎ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቦትስዋና ቱኒዚያን 2  ለ 1 አሸንፋለች።

ሌሴጎ ራዲያካንዮ እና ጋኦንያዲዌ ኦንትላሜትሴ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የስሚን ካንቹች ለቱኒዚያ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥራለች።

ውጤቱን ተከትሎ ቦትስዋና በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ምርጥ ሶስተኛ ሆና ለማለፍ የነገ የምድብ ሶስት ጨዋታዎች ውጤት ትጠብቃለች።

ቱኒዚያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃን ይዛ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም