ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
መንግስት ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብና ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት እንዲሆኑ አድርጓል
Oct 12, 2025 48
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡-መንግስት ተደብቀው የቆዩ ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብና ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት እንዲሆኑ ማድረጉን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ ገለጹ። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአዳብና ፌስቲቫል መዝጊያ መርሃግብር ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣የአካባቢው ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤ኢትዮጵያ አኩሪ የሆነ ብዝሃ ባህል ያላት አገር ናት። ከለውጡ በኃላ አቧራ ለብሰው ተሸፍነው የቆዩ ባህሎች እያደጉ የቱሪስት መስህብ እየሆኑ በመምጣት የአገሪቱ ምድረ ቀደምትነት እየተገለፀ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ባህላዊ እሴቶች ለሁለንተናዊ ብልፅግና አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻሉን ገልጸዋል። አዳብና ከጊዜ ወደጊዜ እየተረሳ መምጣቱን ጠቁመው፥ መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሳይበረዝ ወደቀድሞ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ የተከበረው የአዳብና በዓል ማህበራዊ መስተጋብርንና በህዝቦች መካከል ያለ ትስስርን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። በበዓሉ ለሰላም እሴት ግንባታና በሁሉም ዘርፍ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲቆይ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ በበኩላቸው፥ አዳብና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ማህበረሰብ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። ሚኒስቴሩ ባህላዊ ስርዓቶች በሚገባ ተጠንተውና ለምተው የአገር ብልፅግና ለማረጋገጥ እንዲውሉ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዳልካቸው ጌታቸው፥ አዳብና የሶዶ ክስታኔ ዋነኛ መገለጫ ከሆኑት ባህልና እሴቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል። አዳብና ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በገበያና ሃይማኖት ቦታዎች የሚካሄድ ነው ያሉት ደግሞ በዞኑ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ብሩክታዊት ፀጋዬ ናቸው። የአክራሜ በጎ አድራጎት ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ሳራ ስዩም በበኩላቸው፥ የአዳብና በዓል የወጣቶች የነፃነትና የመተጫጨት በዓል መሆኑን ተናግረዋል። በዓሉን በሀገርና በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ ብሎም በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ለማሳደግ እየተሰራ ነው-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር)
Oct 12, 2025 45
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 አፈጻጸም እና የ2018 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች ንቅናቄ መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር) በንቅናቄ መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት፤ በክልሉ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ለማሳደግ እየተሰራ ነው። የክልሉ መንግስት የግብርናና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማሳፋትም ለስራ እድል ፈጠራ ለማዋል ትኩረት መስጠቱን አስረድተዋል። ለተግባራዊነቱም ጥራት ያለው እቅድ ማዘጋጀትና በቅንጅት መተግበር ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የግብርናውን ኢኮኖሚ አቅም እውን ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም ግብዓቶችን ተደራሽ ማድረግ፣የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምና የጥናትና ምርምር ስራዎችን ወደ ተግባር መቀየር ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። አርሶ አደሩን በቅርበት የሚደግፉ ባለሙያዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው እንዲሰሩ ማድረግ ላይ ማተኮር ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል። በክልሉ የኤክስፖርት ምርት ማሳደግና፣ተኪ ምርቶችን በማምረት በገጠር እና በከተማ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ላይ ማተኮር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር ) በበኩላቸው፤ የሀገርን ሀብት ታሳቢ ያደረገ የግብርና የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል። በግብርናው ዘርፍ በሀገር እና በቤተሰብ የምግብ እና የስርዓተ ምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥም የፖሊሲው ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል። የኤክስፖርት ምርትን በአይነት፣ በመጠንና በጥራት በማምረት ላይ እንዲሁም ተኪምርቶችን ማስፋትም የትኩረቱ አካል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል። የግብርናውን ዘርፍ ለስራ እድል ፈጠራና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች ማሳካት እንደሚገባም ጠቁመዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና ክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት ለግብርናው ዘርፍ መዘመን በዋነኛነት የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ ነው። ተቋማቱ የምርምር ስራዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ድህነትን ለማሸነፍ በሚደረገው ጥረት ድርሻቸውን እንዲያጠናክሩም አሳስበዋል። በመድረኩ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው
Oct 12, 2025 62
ወልቂጤ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ) ፡-ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የሰፈነባት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና እንዳለው የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ። የሰላም ሚኒስቴር ለ14ኛ ዙር ያዘጋጀው ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስልጠና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀምሯል። "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በተጀመረውና ለአንድ ወር በሚቆየው ስልጠና ከአንድ ሺህ በላይ ወጣቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው። በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ፍሬሰንበት ወልደተንሳይ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የወጣቶችን የሀገርና የሕዝብ ፍቅር ለማሳደግ አስተዋጾ እያደረገ ነው። አገልግሎቱ በተለይ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የሰፈነባት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ዛሬ ለወጣቶች መሰጠት የተጀመረው ስልጠናም ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና መርሆችን ለወጣቱ ትውልድ ለማስረጽ ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል። ወጣቶቹ በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የሥራ ባህልን በማጎልበት፣ በህይወት ክህሎት፣ መልካም ስነምግባርን በማስረጽና እና በሀገራዊ አንድነት ላይ እንደሚሰሩም አመልክተዋል። በዚህም በህብረተሰቡ ውስጥ አስተሳሳሪ ገዥ ትርክትን በማስረፅ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን መጠናከር፣ ለዘላቂ ሠላም ግንባታና ልማት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል። እንደእሳቸው ገለጻ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወንድማማችነትና እህታማማችነትን ለማጎልበት፣ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማወቅና ከአካባቢ ባሻገር ሀገራዊ አስተሳሰብን ለማዳበር ይረዳል፡፡ "ሁሉም ዜጋ ለሰላምና ልማት መረጋገጥ አምባሳደር መሆን አለበት" ያሉት ደግሞ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት የሺሀረግ አፈራ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ በስልጠናው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ወጣቶች እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ወጣቶቹ ባህልና እሴቶቻቸውን ለሌሎች በማስተዋወቅ አብሮነትን ለማጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በሀገሪቱ ያሉና ለህዝቦች ትስስር ምሶሶ የሆኑ ዕሴቶች እንዲጎለብቱ በመሰነድና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ በማድረግ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑንም ተናግረዋል። ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ላእመቾ ፍቅሬ እና ህይወት ኤልያስ ስልጠናው በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ እሴቶችን የበለጠ ለመረዳት ከሚሰጠው እድል ባለፈ በህይወት ክህሎት ላይ የተሻለ ዕውቀት የሚያስጨብጥ ነው ብለዋል፡፡ እንደሀገር የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር በሰላም፣ በብሔራዊ መግባባትና በአብሮነት ላይ ለመስራት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡
በሶማሌ ክልል የሚከናወኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ህዝቡ በጉልበቱና በገንዘቡ ለመደገፍ ዝግጁ ነው
Oct 12, 2025 65
ጅግጅጋ፣ ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡-በሶማሌ ክልል የሚገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ህዝቡ በጉልበቱና በገንዘቡ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የተመረቁ ፕሮጀክቶችና የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠላቸው ፕሮጀክቶችን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ የክልሉ ከተሞች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ተካሂደዋል። የድጋፍ ሰልፉ ደገሀቡር፣ ቀብሪደሀርና ጎዴ ከተሞችን ጨምሮ በሁሉም የዞንና የወረዳ መዋቅሮች ተካሂዷል። የሰልፉን ዓላማ በማስመልከት ለኢዜአ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ መንግስት ኮሙንኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ አዳን፣ ከለውጡ በኋላ በክልሉ እየተካሄዱ ባሉ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። በዚህም የክልሉ ህዝብና መንግስት ተጠቃሚና ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ ህዝቡ ለተከናወኑ የልማት ሥራዎችና በቀጣይ ለሚከናወኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ያለውን ድጋፍና ምስጋና ለመግለጽ በተለያዩ ከተሞችና መዋቅሮች ሰልፍ ማካሄዱን ተናግረዋል። በድጋፍ ሰልፎቹ ህዝቡ ደስታውንና ድጋፉን ከመግለጽ ባለፈ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በክልሉ በቅርቡ ላስጀመሯቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የተፈጥሮ ጋዝ ሥራ ምስጋና ለማቅረብ ያለሙ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በተለይ በክልሉ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ስራ መግባት የሀገርንም ሆነ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እድገት የማፋጠን ሚናው የጎላ መሆኑን የገለጹት አቶ መሀመድ፣ ህዝቡ የልማት ፕሮጀክቶቹ ፈጥነው እንዲጠናቀቁ የበኩሉን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጧል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የክልሉ ህዝብ ከልማት ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰጡት ላለው የላቀ አመራርም ህዝቡ በሰልፉ ማመስገኑን ጠቅሰው፣ ፕሮጀክቶቹን በጉልበትና በገንዘብ በመደገፍ የራሱን ሃላፊነት ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየቱንም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ለተጀመሩ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ህዝቡ የሚያደርገውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጡበት ሰልፍ መሆኑንም አንስተዋል። እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች እየመለሱ በመሆናቸው ህዝቡ ተጠቃሚ እየሆነ መጥቷል።
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
Oct 12, 2025 81
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያይተናል ብለዋል። በውይይታቸውም፤ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው ያስታወቁት።
ሠንደቅ ዓላማ የማንነታችን መለያ የእኛነታችን ጌጥ ነው - የመከላከያ ሰራዊት አባላት
Oct 12, 2025 105
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦ሠንደቅ ዓላማ ከአባቶቻችን የወረስነው የማንነታችን መለያ የእኛነታችን ጌጥ ነው ሲሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ገለጹ። 18 ኛው የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን ነገ ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል። ሠንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ አገር ዜጎች አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀባረቁበት የአገራዊ አንድነትና ህብረት አርማ ነው። በመሆኑም ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በህግ ተደንግጓል። በዓሉ በፌዴራል፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች እና በሌሎች ዓለማት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ሠንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በዓሉን አስመልክተው ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ሚኒሊክ ዋለ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የምትታወቀው የምትወከለው በሠንደቅ ዓላማዋ ነው። ሠንደቅ ዓላማ ይበልጥ የሚገለጸውም በመከላከያ ሰራዊቱ መሆኑን ገልጸው፤ በተልእኮዎቹ ሁሉ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ጠቁመዋል። በዚህም የበዓሉ መከበር ለሰራዊቱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጭ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን ኮሎኔል መሰረት ሞላ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ረጅም ታሪክ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ሠንደቅ ዓላማ አርማ ብቻ ሳይሆን ከአባቶቻችን የወረስነው የማንነታችን መገለጫ ነው ብለዋል። ኮሎኔል ሚኒሊክ ዋለ (ዶ/ር) ሠንደቅ ዓላማ አባቶቻችን እና እናቶቻችን መስዋእትነት ከፍለው ከዘመን ዘመን አሻግረው የሰጡን የማንነት መለያ መሆኑን ጠቁመዋል። ሰራዊቱ ለሠንደቅ ዓላማ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸው፤ በዓሉ በየቀኑ መከበር ያለበት መሆኑን አመላክተዋል። ኮሎኔል መሰረት ሞላ (ዶ/ር) ሠንደቅ ዓላማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን አንስተዋል። ሀገርን የመጠበቅ ሀላፊነት ለተጣለበት የመከላከያ ሰራዊት የበዓሉ መከበር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አመላክተዋል።
የጀግንነት ምልክትና የህብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ክብር ጠብቆ መዝለቅ የትውልዱ አደራ ሊሆን ይገባል-የቀድሞ ሠራዊት አባላት
Oct 12, 2025 83
ወላይታ ሶዶ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፦የጀግንነት ምልክትና የህብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ክብር ጠብቆ መዝለቅ የትውልዱ አደራ ሊሆን ይገባል ሲሉ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ተናገሩ። የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባል ሻምበል አንጁሎ ኦልባሞ እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷ ከነሙሉ ክብሯ ተጠብቆ ታፍራና ተከብራ የቆየውችው በየዘመናቱ ልጆቿ በከፈሉት መስዋዕትነት ነው። የአሁኑ ትልድ በጀግኖች ልጆቿ የአጥንትና ደም መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል ጸንታ ለቆየችው ኢትዮጵያና ለሰንደቅ ዓላማ ተገቢውን ክብር እንዲሰጥ የባንድራን ምንነት ማስረጽ ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ክብሩ ከሀገርም የተሻገረ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነፃነት ምልክት መሆኑን ገልጸው፣ በዚሁ ልክ ሁሉም ክብር መስጠት እንዳለበት አመልክተዋል። ሌላው የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩትና በክብር የተሰናበቱት ሻለቃ ጳውሎስ ገብረስላሴ በበኩላቸው፥ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ክብር ሲሉ በየዘመናቱ በርካታ ጀግኖች ዋጋ እየከፈሉ ሀገርን እስከዛሬ አስቀጥለዋል። የሰንደቁ ክብርና የሀገር ሉአላዊነት አሁንም በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መጠበቁ ሁሉንም የሚያስደስት ተግባር ነው ሲሉም ተናግረዋል። በመሆኑም የጀግንነት ምልክትና የህብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ክብር ጠብቆ መዝለቅ የትውልዱ አደራ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው እለት በብሔራዊ ደረጃ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።
የአፍሪካን የትርክት ሉዓላዊነት እና የሚዲያ ነጻነት የማረጋገጥ ጅማሮ
Oct 11, 2025 271
ለዘመናት የአፍሪካ ታሪክ ሲነገር የቆየው በሌሎች ነው። አህጉሪቱን አስመልክቶ የሚሰሩ ዘገባዎች አፍሪካውያንን በተሳተተ መነጽር የሚመለከቱና ማንነታቸውን የማይወክሉ፣ ትርክቱ አፍሪካን በቀውስ መነጽር ብቻ እንድትሳል የሚያደርጉ ናቸው። ከቅኝ ግዛት ፕሮፓጋንዳ እስከ ዘመናዊ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ የአፍሪካ አብዛኞቹ ትርክቶች የተቀረጹት በውጭ ኃይሎች ነው። ውጪዎቹ የአፍሪካን እሳቤ እና አጀንዳ የማህበረሰቦችን እሴት፣ ባህል፣ ታሪክ እና የአንድነት መንፈስ በውል ያልተረዱ ናቸው። ዓለም ስለአፍሪካ ሁሌም የሚያዳምጠው ስለጦርነት፣ ስለድህንት እና ስለአህጉሪቱ ፈተናዎች ነው። ምልከታዎቹ የአፍሪካ ፈጣሪዎችን፣ ልሂቃንን ህልመኞችን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎችንና ስኬታማ ሰዎችን ያገለሉ መሆናቸው በግልጽ ይታያል። አፍሪካ ሁሌም የምትበየነው ለመልማት እና ለመበልጸግ ባላት መሻትና አቅም ወየም ለተቀረው ዓለም በምታቀርባቸው መልካም እድሎች ሳይሆን ባጣቻቸው ነገሮች ነው። የዓለም መገናኛ ብዙሃን የአፍሪካ ዘገባዎች ፈተናዎችን ብቻ የሚያጎሉ ናቸው። የዓለም አርዕስተ ዜናዎች የአፍሪካን የመፍጠር አቅም፣ አይበገሬነት እና ለውጥ የሚያንጸባርቁ አይደሉም። በአህጉሪቱ ያለው ሚዛናዊነት የጎደለው እይታ ከዓለም እይታ ብቻ የሚመነጭ አይደለም። አፍሪካውያን ራሳቸውን የሚመለከቱበትና የሚለኩበት መንገድም የተዛባ በመሆኑም ጭምር ነው። መረጃ ኃይል በሆነበት በዚህ ዘመን የአፍሪካን እውነተኛ ድምጽ የሚያሰማ ሚዲያ አለመኖር አሉታዊ ተጽእኖዎች ያሉት ነው። የሚዲያ ትርክቶች ፖሊሲ፣ ኢንቨስትመንትና ዲፕሎማሲ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ከመሆናቸው ባሻገር በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ሀገር ተረካቢ ወጣትን በእሳቤ የሚቀርጹ ናቸው። የአፍሪካ ገጽታ ስቃይ እና ሁሌም ችግር የዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ላይ በገነነበት ወቅት ዓለም አፍሪካን እንደ አጋር ሳይሆን እንደ ርዳታ ጠባቂ አህጉር አድርጎ እንዲመለከታትም ምክንያት ሆኗል። የዓለም መገናኛ ብዙሃን የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት፣ የቴክኖሎጂ እምርታ፣ ታሪክ እና ባህል ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ችግርን አብዝተው ማቀንቀናቸው አህጉሪቱ በሚዲያው ዘርፍ ፍትሃዊ ውክልና ሊኖራት ይገባል የሚሉ ድምጾች ጎልተው እንዲሰሙ አድርጓል። የሚዲያ ውክልናው ጋዜጠኝነት ተኮር ሳይሆን አፍሪካ የማንነቷ ባለቤት እንድትሆን እና የራሷን መጻኢ ዕድል የመወሰን መብቷን እንድታረጋግጥ ያለመ ጥሪ ነው። እ.አ.አ 2022 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተካሄደበት ወቅት ነው። የአፍሪካ መሪዎች በአህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ ለመምከር በአዲስ አበባ ተገኝተዋል። በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ያደረጉት ንግግር በርካታ የአፍሪካ አጀንዳዎችን ቃኝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በወቅቱ አፍሪካ የትርክት ነጻነትቷን ማግኘት አለባት በሚል ያነሱት ሀሳብ የጉባኤውን ተሳታፊዎች ቀልብ የሳበ ጉዳይ ነበር። ለዘመናት የአፍሪካ ምስል የተቀረጸው በውጭ ኃይሎች እንደሆነ አንስተው የትርክት ቅኝቱ አህጉሪቱ የድህነት፣ የግጭት እና የተረጂነት ምሳሌ አድርጎ የሚያቀርብ መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ አፍሪካውያን የአህጉሪቱን ብዝሃነት፣ አይበገሬነት እና የኢኖቬሽን አቅም የሚያሳዩ ሀገር በቀል የኮሙኒኬሽን አማራጮች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ማቅረባቸውም ይታወሳል። አፍሪካ የራሷን ጉዳይ በራሷ አፍ የምትናገርበት አህጉራዊ የፖን አፍሪካ ሚዲያ እንዲቋቋም ሀሳብ አቅርበው እንደነበርም እንዲሁ። ይህ ሀሳብ በጉባኤው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ድጋፍ አገኝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) Pulse of Africa የተሰኘ የፓን አፍሪካ ሚዲያ በያዝነው ሳምንት በይፋ አስጀምረዋል። ሚዲያው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እ.ኤአ በ2022 በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካን እይታ እና ትርክት የሚያንፀባርቅ የአኅጉራዊ ሚዲያን አስፈላጊነት አስመልክተው ያቀረቡትን ጥሪ በመመርኮዝ የተመሠረተ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። Pulse of Africa የአፍሪካን ድምፆች የሚያጎላ፣ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር እና አኅጉራዊ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ሕልሞችን በአፍሪካዊ እይታ የሚገልጥ ሚዲያ የመሆን አላማ አለው። በዚህም Pulse of Africa ሚዲያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ እና ህልም ቀጥተኛ ምላሽ የሰጠ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፓን አፍሪካ ሚዲያው ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ ትልቅ ሳለች ትንሽ መስላ እንድትታይ ያደረጋት ዋነኛ ምክንያት የአፍሪካ ሀገራት በትርክት ጭንቅላትን የመመገብ ዝግጁነት ውስን በመሆኑ ነው ብለዋል። የPulse of Africa ሚዲያ በጥቂት ዓመታት በአፍሪካ ቀደምት እና ታዋቂ ከሆኑ ሚዲያዎች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉም ነው የተናገሩት። የአንድ ሀገር ሚዲያ እድገት ከሀገራት ኢኮኖሚ እና እድገት ጋር የተሳሰረ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ አመልክተዋል። የዛሬ 10 ዓመት የምትኖረው ኢትዮጵያ በአፍሪካ በብዙ ነገር ግንባር ቀደም ትሆናለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያኔ ትርክት መገንባት የመሻት ጉዳይ ሳይሆን የኃላፊነት ጉዳይ መሆኑንም ነው ያነሱት። ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዋ እያደገ ሲሄድ በአፍሪካ ትርክት ውስጥ ጉልህ ስፍራ መጫወት ኃላፊነቷ እንደሚሆንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከራሷ በመሻገር የአፍሪካን ትልቅነት፣ ሀብታምነት፣ የማድረግ አቅም እንዲሁም አፍሪካውያን ሲደመሩ የተሻለ ነገር ማምጣት እንደሚችሉ የPulse of Africa ሚዲያ በብዙ ነገር እንደሚያስተምርም ተናግረዋል። Pulse of Africa የአፍሪካ ድምጽ ነው፤ የአፍሪካ ምስል፣ ባህል እና ሀብት መገለጫ መሆኑንና ከአፍሪካ ወንድሞቻችን ጋር በሁሉም ነገር በትብብርና በመደመር በጋራ መቆም ይገባናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ረገድም Pulse of Africa የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማሳሰባቸው ይታወሳል። Pulse of Africa ሚዲያ ጋዜጠኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ታሪክ ነጋሪዎችን ጨምሮ አፍሪካውያን ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማገናኘት የአፍሪካን እውነተኛ መልክ ለማሳየት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣና የአፍሪካን ትርክት መገንባት፣ ብዝሃነት በማንጸባረቅ እና የአፍሪካን እውነተኛ ታሪክ በአህጉራዊ መነጽር ለመቃኘት የሚያስችል ነው። Pulse of Africa ከሚዲያ ኢኒሼቲቭ ባለፈ አፍሪካ ራሷን በራሷ መበየን የምትችልበት አዲስ ምዕራፍ እንደሆነ ብሎ መውሰድ እንደሚቻልና አህጉሪቱ እውነቷን እንድትናገርና በዓለም መድረክ ተገቢውን ክብር እንድታገኝ የማድረግ ጉዞ አካል ነው። ሚዲያው ዜናን ከመዘገብ ባለፈ አፍሪካ የራሷን ታሪክ በራሷ ቃና እና ድምጽ እንድትናገር ትልቅ ዕድል ይዞ መምጣቱም ተመላክቷል።
በሀዋሳ ከተማ የህብረተሰቡን ህይወት የሚያሻሽሉ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላሉ-ከንቲባ ተክሌ ጆንባ
Oct 11, 2025 164
ሀዋሳ ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፦ በሀዋሳ ከተማ የህብረተሰቡን ህይወት የሚያሻሽሉ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ከንቲባ ተክሌ ጆንባ ተናገሩ። የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን በጉባኤውም የከንቲባ ተክሌ ጆንባን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ ከሹመቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ተክሌ በሥራ ዘመናቸው የከተማዋን ነዋሪ ህይወት የሚያሻሽሉ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላሉ ብለዋል። በተለይ የድህነት ቅነሳና ሰው ተኮር ልማት ሥራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚከናወኑ ገልጸው የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የማህበራዊ ልማት ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከዚህም ባለፈ የከተማዋ ወጣቶች ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ሙያዊ ክህሎት እንዲጨብጡና የሥራ ዕድል እንዲመቻችላቸው ይሰራል ብለዋል፡፡ የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ጠብቆ ማስቀጠል እንዲሁም ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የከተማዋን የቱሪስት መዳረሻዎች ማዘመንና መንከባከብ ብሎም ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ማድረግም ቀጣዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ምክር ቤቱ በጉባኤው በከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ የቀረቡለትን ሹመቶችም ያጸደቀ ሲሆን ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ገዛኸኝ አርሲቻ የመሬት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ስጦታው ከንባታ የግብርና መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ገነነ ገላሳ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡
የጀግንነትና አሸናፊነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብሩን አስጠብቆ ማቆየት የሁሉም ኃላፊነት ነው
Oct 11, 2025 147
ቦንጋ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡- የጀግንነትና አሸናፊነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብሩን አስጠብቆ መዝለቅ የሁሉም ሃላፊነትና አደራ መሆኑ ተገለጸ። የፊታችን ሰኞ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በመዘዋወር የፖሊስ አባላትንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋግሯል። የክልሉ ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች መካከል ዋና ኢንስፔክተር ብርሃኑ አበራ እና ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከጥንት እስካሁንም የዘለቀ የጀግንነት፣ የአይበገሬነትና የአሸናፊነት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የሰንደቁን ክብር በመጠበቅ ጸንታ የምትቀጥል ጠንካራ ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሁሌም ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል። በቦንጋ ከተማ የሚኖሩት አቶ መንገሻ ወልደማሪያም፤ በበኩላቸው የህብረ ብሄራዊ አንድነትና የጀግንነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ለቀጣዩ ትውልድ ከነክብሩ ማስረከብ ይገባል ብለዋል። የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ መምህር ተስፋዬ ወንድማገኝ፣ሰንደቅ ዓላማ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ልዩ ቦታና ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸው በተለይም ትውልድ የመቅረጽ ሃላፊነት ያለብን መምህራን ልዩ የቤት ስራ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብሄራዊ ደረጃ የፊታችን ሰኞ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበር ይሆናል።
ሰንደቅ ዓላማችን የክብራችንና የማንነታችን ማህተም በመሆኑ ልዩ ክብር ልንሰጠው ይገባል - አፈ-ጉባኤ መሠረት ማቲዎስ
Oct 11, 2025 156
ጋምቤላ ፤ ጥቅምት 1/ 2018(ኢዜአ) ሰንደቅ ዓላማችን የትናንት የጋራ ታሪካችን፣ የዛሬ የጋራ ጥረታችንና የነገ ተስፋችንን አጣምሮ የያዘ የክብራችንና የማንነታችን ማህተም ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሠረት ማቲዎስ ገለጹ። 18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አካባበርን አስመልክቶ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ዛሬ በጋምቤላ ተካሄዷል። የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሠረት ማቲዎስ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ የትናንት የጋራ ታሪካችን፣ የዛሬ የጋራ ጥረታችንና የነገ ተስፋችንን አጣምሮ የያዘ የክብራችንና የማንነታችን ማህተም በመሆኑ ልዩ ክብር ልንሰጠው ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ህብረ ብሔራዊ አንድነትንና ዘላቂ መግባባትን የሚያጠናክር የጋራ ዓርማችን ነውም ብለዋል። ዕለቱ ቀደምት አባቶች ለሰንደቅ ዓላማው ክብርና ለሀገራቸው ሉዓላዊነት ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት የምንዘክርበት ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። በዓሉን በየዓመቱ መከበሩ ዜጎች ስለ ሰንደቅ ዓላማው ክብርና ትርጓሜ በተገቢው መንገድ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ቀደምት አባት አያቶቻችን ሉዓላዊነቷንና ክብሯን ጠብቀው ያስረከቡንን አንድነቷ የተጠበቀና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ቃላችንን የምናድስበት ዕለት ነው ብለዋል። ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ቾል ኮር በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ የሁላችንም የማንነት መገለጫ በመሆኑ ልዩ ክብር እንሰጠዋለን ብለዋል። ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባትና የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት ለማጠናከር የሚያስችል ነው ያሉት ደግሞ ፓስተር ማን ሙን ናቸው ። ቄስ ልብሰ ወርቅ በበኩላቸው ሰንደቅ ዓላማው ኢትዮጵያዊ አንድነታችን የሚጠናከርበትና ማንነታችን በዓለም መድረክ ጎልቶ እንዲተዋወቅ የሚያደርግ ዓርማ ነው ብለዋል። በፓናሉ ላይም ስለ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ የሚዳስስ ጽሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል። የሰንደቅ አላማ ቀን ''ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፤ ለብሔራዊ አንድነታችን ፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ'' በሚል መሪ ሀሳብ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ቀን በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ይታወቃል።
የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የአሁኑ ትውልድ ኃላፊነት ነው
Oct 11, 2025 185
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፦ ትውልዱ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ፣ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀኑን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ሥልጣን፣ ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያ መሣሪያ መሆኑን ገልጿል። ሠንደቅ ዓላማ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ የታተመ የሀገራዊ አንድነትና ነፃነት መገለጫ ታላቅ የብሔራዊ ኩራት አርማ እንደሆነ አመልክቷል። የአንድነታችንና የሕብረታችን ማሳያ፣ ጀግኖች አያቶቻችን ወራሪዎችን በማሸነፍ ለመላው የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት የሆነውን ሠንደቅ ዓላማ የሕይወት መስዋዕትን ከፍለው ለአዲሱ ትውልድ ማስረከባቸው በመግለጫው ተወስቷል። ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሠንደቅ ዓላማ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት የሚከበር ታላቅ ሀገራዊ በዓል መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል። በመሆኑም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሀገራዊ ሉዓላዊነትንና የግዛት አንድነትን ማስቀጠል፤ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት በማጽናት የሀገሪቷን የዕድገት ከፍታ ማረጋገጥ ከአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝቧል። የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (በተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል። በዚሁም መሰረት የሠንደቅ ዓላማ ቀን የዘንድሮው በፌዴራል፣ በክልሎችና በሁለቱም የከተማ አስተዳደር ከተሞች ከሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች ጋር ተገናዝቦና የኢትዮጵያን ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራትና ማንሰራራት በሚያረጋግጡ ውይይቶች ታጅቦ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነት በመላው ሀገሪቱ ይከበራል፡፡ የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበሩ ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን በማስጠበቅ የኢትዮጵያን የከፍታ ብሥራትና ሕዳሴ ለማረጋገጥ ለሀገር ክብርና ጥቅም ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በሠንደቅ ዓላማ ፊት ዳግም ቃሉን የሚያድስበት ዕለት መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል። በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ30 ላይ ሠንደቅ ዓላማ በመስቀልና በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ የመፈፀም ሥነ-ስርዓት እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ጠቁሟል።

ማህበራዊ
መንግስት ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብና ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት እንዲሆኑ አድርጓል
Oct 12, 2025 48
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡-መንግስት ተደብቀው የቆዩ ባህላዊ እሴቶች ለምተው ለቱሪስት መስህብና ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት እንዲሆኑ ማድረጉን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ ገለጹ። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአዳብና ፌስቲቫል መዝጊያ መርሃግብር ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣የአካባቢው ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤ኢትዮጵያ አኩሪ የሆነ ብዝሃ ባህል ያላት አገር ናት። ከለውጡ በኃላ አቧራ ለብሰው ተሸፍነው የቆዩ ባህሎች እያደጉ የቱሪስት መስህብ እየሆኑ በመምጣት የአገሪቱ ምድረ ቀደምትነት እየተገለፀ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ባህላዊ እሴቶች ለሁለንተናዊ ብልፅግና አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻሉን ገልጸዋል። አዳብና ከጊዜ ወደጊዜ እየተረሳ መምጣቱን ጠቁመው፥ መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሳይበረዝ ወደቀድሞ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ የተከበረው የአዳብና በዓል ማህበራዊ መስተጋብርንና በህዝቦች መካከል ያለ ትስስርን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። በበዓሉ ለሰላም እሴት ግንባታና በሁሉም ዘርፍ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲቆይ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ በበኩላቸው፥ አዳብና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ማህበረሰብ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። ሚኒስቴሩ ባህላዊ ስርዓቶች በሚገባ ተጠንተውና ለምተው የአገር ብልፅግና ለማረጋገጥ እንዲውሉ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዳልካቸው ጌታቸው፥ አዳብና የሶዶ ክስታኔ ዋነኛ መገለጫ ከሆኑት ባህልና እሴቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል። አዳብና ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በገበያና ሃይማኖት ቦታዎች የሚካሄድ ነው ያሉት ደግሞ በዞኑ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ብሩክታዊት ፀጋዬ ናቸው። የአክራሜ በጎ አድራጎት ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ሳራ ስዩም በበኩላቸው፥ የአዳብና በዓል የወጣቶች የነፃነትና የመተጫጨት በዓል መሆኑን ተናግረዋል። በዓሉን በሀገርና በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ ብሎም በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው
Oct 12, 2025 62
ወልቂጤ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ) ፡-ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የሰፈነባት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና እንዳለው የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ። የሰላም ሚኒስቴር ለ14ኛ ዙር ያዘጋጀው ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስልጠና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀምሯል። "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በተጀመረውና ለአንድ ወር በሚቆየው ስልጠና ከአንድ ሺህ በላይ ወጣቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው። በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ፍሬሰንበት ወልደተንሳይ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የወጣቶችን የሀገርና የሕዝብ ፍቅር ለማሳደግ አስተዋጾ እያደረገ ነው። አገልግሎቱ በተለይ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የሰፈነባት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ዛሬ ለወጣቶች መሰጠት የተጀመረው ስልጠናም ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና መርሆችን ለወጣቱ ትውልድ ለማስረጽ ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል። ወጣቶቹ በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የሥራ ባህልን በማጎልበት፣ በህይወት ክህሎት፣ መልካም ስነምግባርን በማስረጽና እና በሀገራዊ አንድነት ላይ እንደሚሰሩም አመልክተዋል። በዚህም በህብረተሰቡ ውስጥ አስተሳሳሪ ገዥ ትርክትን በማስረፅ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን መጠናከር፣ ለዘላቂ ሠላም ግንባታና ልማት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል። እንደእሳቸው ገለጻ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወንድማማችነትና እህታማማችነትን ለማጎልበት፣ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማወቅና ከአካባቢ ባሻገር ሀገራዊ አስተሳሰብን ለማዳበር ይረዳል፡፡ "ሁሉም ዜጋ ለሰላምና ልማት መረጋገጥ አምባሳደር መሆን አለበት" ያሉት ደግሞ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት የሺሀረግ አፈራ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ በስልጠናው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ወጣቶች እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ወጣቶቹ ባህልና እሴቶቻቸውን ለሌሎች በማስተዋወቅ አብሮነትን ለማጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በሀገሪቱ ያሉና ለህዝቦች ትስስር ምሶሶ የሆኑ ዕሴቶች እንዲጎለብቱ በመሰነድና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ በማድረግ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑንም ተናግረዋል። ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ላእመቾ ፍቅሬ እና ህይወት ኤልያስ ስልጠናው በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ እሴቶችን የበለጠ ለመረዳት ከሚሰጠው እድል ባለፈ በህይወት ክህሎት ላይ የተሻለ ዕውቀት የሚያስጨብጥ ነው ብለዋል፡፡ እንደሀገር የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር በሰላም፣ በብሔራዊ መግባባትና በአብሮነት ላይ ለመስራት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ- የጤና ሚኒስቴር
Oct 12, 2025 62
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦መንግሥት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የዓለም የልብ ቀን "አንድም የልብ ምት አታምልጠን" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። በእለቱም የኢትዮጵያ የልብ ማህበር አባላት፣ የህክምና ባለሙያዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ቀኑን ምክንያት በማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ አካሒደዋል። ጤና ሚኒስቴርን በመወከል የተገኙት አቶ ሌሊሳ አማኑኤል፤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በማሕበረሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ካሉ ችግሮች ዋነኛው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ናቸው። በዚሁ ሳቢያም መንግስት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል የሚያስችል የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ የተጠናከሩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ከዚህ ውስጥም የባለሙያዎች አቅም በማጠናከር፣ መድሃኒቶች ከውጭ በማስገባት እና የልብ ቀዶ ጥገናዎች በዘመቻ እንዲካሔዱ የማድረግ ተጠቃሽ ስራዎች ናቸው ብለዋል። መንግስት በሽታውን ለመከላከል ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ዜጎች አመጋገባቸውን በማስተካከል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ራሳቸውን የመጠበቅ ባሕል ሊያጎለብቱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ የልብ ማኅበር ፕሬዝደንት እንዳለ ገብሬ በበኩላቸው፤ ማህበሩ የዓለም አቀፉ የልብ ቀን ምክንያት በማድረግ የልብ ህክምናዎችን ከመስጠት ባሻገር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ከልብ ህመም ጋር ተያይዞ ሕክምና ለማግኝት በርካታ ዜጎች ተራቸውን በመጠባበቅ ላይ በመሆናቸው ይህንኑ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በአሁኑ ወቅትም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በተለይ በትምህርት ቤቶች የልብ ህመም ጋር ተያይዞ ህክምና የሚፈልጉ ዜጎችን መረጃ የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ማሕበሩ የሕዝብ መድሃኒት ቤቶችን በመክፈት ለረዥም ጊዜ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት መድሃኒት ለሚወስዱ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል። የልብ ህመም በሕብረተሰቡ ላይ አያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቀነስም በየወቅቱ ምርመራ የማድረግ ባሕልን ማጎልበት እንደሚገባም ነው የጠቀሱት። በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙ ከልብ ህመም ጋር ተያይዞ ህክምና የወሰዱ ታካሚዎች በበኩላቸው፤ማሕበረሰቡ የልብ ህመም የሚያመጡ በሽታዎች ምልክቶችን ሲያይ ፈጥኖ ወደ ሕክምና በመሄድ ህክምና ማድረግ እንደሚገባ ይመክራሉ። አስተያየት ሰጪዎቹ ወይዘሮ እመቤት አሰሙ እና ወይዘሮ ሚዛን ሀጎስ፤ ልብ ህክምና ከባድና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ በቅንጅት ቢሰራ አቅም የሌላቸው ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ነው የሚሉት።
ኪነ-ጥበብን ለልማትና ለሀገራዊ ትርክት ግንባታ ማዋል ይገባል
Oct 12, 2025 85
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፦ኪነ-ጥበብን ለሀገራዊ ልማትና ትርክት ግንባታ ይበልጥ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየወሩ የሚያዘጋጀው የስነ-ጽሁፍ ምሽት "ድህረ ህዳሴ" በሚል መሪ ሀሳብ ተዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ስራ አስፈጻሚ ነጋሲ አምባዬ በወቅቱ፥ ኢትዮጵያ የቁጭት ዘመን አብቅቶ የማንሰራራት ዘመን ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል። ይህንን አዲስ ምዕራፍ በሚገባ ለመግለጽና ለማሳየት የኪነጥበብ ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትም ይህንኑ ለማሳደግ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ኪነ-ጥበብ የሀገርን ልማት በማፋጠን ሂደት ውስጥ ትልቅና አዎንታዊ ሚና ለማሳደግም ሚዲያ ያለውን አበርክቶ እውን በማድረግ ልማትንና ገጽታ ግንባታን ለማፋጠን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን የተዘጋጀው የኪነ-ጥበብ ምሽትም የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ ያለመና የጋራ ትርክትን የሚፈጥሩ አጀንዳዎችን ለማንሸራሸር ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል። በኪነ-ጥበብ ምሽቱ ላይ የተገኙት የዓባይ ንጉሶች ሚዲያ መስራች ኡስታዝ ጀማል በሽር በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያውያን በትብብር ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በማጠናቀቅ ታሪክ መሥራታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ ኪነ-ጥበቡ ከፍተኛ ሚናውን እንደተጫወተ አንስተዋል። የኪነ-ጥበብ አቅምን በማጎልበት በሕዳሴው ግድብ ያሳየነውን ህብረት በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይም መድገም እንደሚገባ ጠቁመዋል። የስነ-ጥበብ ኮሌጅ ዲን አገኘሁ አዳነ፥ ኪነ-ጥበብ በሀገር ግንባታ ያለውን ትልቅ አበርክቶ በመጠቀም ህብረተሰብን ለልማት ማነሳሳት እንደሚገባ ተናግረዋል። የለውጡ መንግሥት የኪነ-ጥበብ ዘርፍን ለማሳደግ በሰጠው ትኩረት ክዋኔ ጥበባት መድረኮች እንዲስፋፉ ማድረጉን አንስተዋል። ይህም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ለሰብዓዊና ለሀገር ልማት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ እድል መፍጠሩን ጠቅሰዋል። በኪነጥበብ ምሽቱ መርሃ ግብር ላይ፣ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ጋር ተያይዘው የተዘጋጁ ግጥሞች፣ መጣጥፎች እና ሌሎች የስነ-ጽሁፍ ስራዎች ቀርበዋል፡፡
ኢኮኖሚ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ለማሳደግ እየተሰራ ነው-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር)
Oct 12, 2025 45
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 አፈጻጸም እና የ2018 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች ንቅናቄ መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር) በንቅናቄ መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት፤ በክልሉ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ለማሳደግ እየተሰራ ነው። የክልሉ መንግስት የግብርናና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማሳፋትም ለስራ እድል ፈጠራ ለማዋል ትኩረት መስጠቱን አስረድተዋል። ለተግባራዊነቱም ጥራት ያለው እቅድ ማዘጋጀትና በቅንጅት መተግበር ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የግብርናውን ኢኮኖሚ አቅም እውን ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም ግብዓቶችን ተደራሽ ማድረግ፣የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምና የጥናትና ምርምር ስራዎችን ወደ ተግባር መቀየር ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። አርሶ አደሩን በቅርበት የሚደግፉ ባለሙያዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው እንዲሰሩ ማድረግ ላይ ማተኮር ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል። በክልሉ የኤክስፖርት ምርት ማሳደግና፣ተኪ ምርቶችን በማምረት በገጠር እና በከተማ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ላይ ማተኮር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር ) በበኩላቸው፤ የሀገርን ሀብት ታሳቢ ያደረገ የግብርና የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል። በግብርናው ዘርፍ በሀገር እና በቤተሰብ የምግብ እና የስርዓተ ምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥም የፖሊሲው ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል። የኤክስፖርት ምርትን በአይነት፣ በመጠንና በጥራት በማምረት ላይ እንዲሁም ተኪምርቶችን ማስፋትም የትኩረቱ አካል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል። የግብርናውን ዘርፍ ለስራ እድል ፈጠራና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች ማሳካት እንደሚገባም ጠቁመዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና ክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት ለግብርናው ዘርፍ መዘመን በዋነኛነት የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ ነው። ተቋማቱ የምርምር ስራዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ድህነትን ለማሸነፍ በሚደረገው ጥረት ድርሻቸውን እንዲያጠናክሩም አሳስበዋል። በመድረኩ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በሶማሌ ክልል የሚከናወኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ህዝቡ በጉልበቱና በገንዘቡ ለመደገፍ ዝግጁ ነው
Oct 12, 2025 65
ጅግጅጋ፣ ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡-በሶማሌ ክልል የሚገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ህዝቡ በጉልበቱና በገንዘቡ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የተመረቁ ፕሮጀክቶችና የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠላቸው ፕሮጀክቶችን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ የክልሉ ከተሞች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ተካሂደዋል። የድጋፍ ሰልፉ ደገሀቡር፣ ቀብሪደሀርና ጎዴ ከተሞችን ጨምሮ በሁሉም የዞንና የወረዳ መዋቅሮች ተካሂዷል። የሰልፉን ዓላማ በማስመልከት ለኢዜአ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ መንግስት ኮሙንኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ አዳን፣ ከለውጡ በኋላ በክልሉ እየተካሄዱ ባሉ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። በዚህም የክልሉ ህዝብና መንግስት ተጠቃሚና ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ ህዝቡ ለተከናወኑ የልማት ሥራዎችና በቀጣይ ለሚከናወኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ያለውን ድጋፍና ምስጋና ለመግለጽ በተለያዩ ከተሞችና መዋቅሮች ሰልፍ ማካሄዱን ተናግረዋል። በድጋፍ ሰልፎቹ ህዝቡ ደስታውንና ድጋፉን ከመግለጽ ባለፈ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በክልሉ በቅርቡ ላስጀመሯቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የተፈጥሮ ጋዝ ሥራ ምስጋና ለማቅረብ ያለሙ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በተለይ በክልሉ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ስራ መግባት የሀገርንም ሆነ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እድገት የማፋጠን ሚናው የጎላ መሆኑን የገለጹት አቶ መሀመድ፣ ህዝቡ የልማት ፕሮጀክቶቹ ፈጥነው እንዲጠናቀቁ የበኩሉን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጧል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የክልሉ ህዝብ ከልማት ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰጡት ላለው የላቀ አመራርም ህዝቡ በሰልፉ ማመስገኑን ጠቅሰው፣ ፕሮጀክቶቹን በጉልበትና በገንዘብ በመደገፍ የራሱን ሃላፊነት ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየቱንም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ለተጀመሩ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ህዝቡ የሚያደርገውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጡበት ሰልፍ መሆኑንም አንስተዋል። እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች እየመለሱ በመሆናቸው ህዝቡ ተጠቃሚ እየሆነ መጥቷል።
የምርት ብክነትን ለመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ሜካናይዜሽን በስፋት ጥቅም ላይ የማዋሉ ተግባር ይጠናከራል
Oct 12, 2025 74
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡-የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሩ የግብርና ሜካናይዜሽንን በስፋት ጥቅም ላይ እንዲያውል የሚደረጉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የምርት ብክነትን በመቀነስ የዜጎችን የምግብ ዋስትና እና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው። ከዚህ ውስጥም አርሶ አደሩ ሜካናይዜሽን የሆኑ የመውቂያ፣ የማጨጃና የምርት መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን እንዲጠቀም በማድረግ የምርት ብክነትን ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል። በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢሳያስ ለማ ለኢዜአ እንዳሉት ግብርናውን በማዘመን የምርት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው። በተለይም ሰብል በሚዘራበት፣ በሚወቃበትና በሚሰበሰብበት ወቅት ሜካናይዜሽን የእርሻ መሳሪያዎችን በማሰራጨትና አርሶ አደሩ ጥቅም ላይ እንዲያውላቸው እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቀት በተለይም የበልግ ምርት የሚሰበሰብበት ወቅት በመሆኑ ብክነትን ለመቀነስ የተጠናከሩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። በዋናነትም ስንዴ በሚያመርቱ አካባቢዎች የመውቂያ ኮምባይነር በስፋት እየተሰራጨ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ምርታና ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀም እየተደረገ ነው። በተለይም በኩታ ገጠም የሚያርሱ አርሶ አደሮችን በማደራጀት በጋራ እንዲሰሩና የምርት ብክነትን እንዲከላከሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። የምርት ብክነት ከዘር ወቅት አንስቶ ምርቱ ወደ ጎተራ እስኪገባ የሚከሰት በመሆኑ አርሶ አደሩ ዘመናዊ እርሻ መሳሪያዎችን እንዲጠቀም እየተደረገ ነው ብለዋል። በተለይ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ብክነት የሚደርሰው በሚጓጓዝበት ወቅት በመሆኑ በዋናነት ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች የተሻሉ ማጓጓዛዎች እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው ብለዋል። ብክነትን መቀነስ ምርትና ምርታማነትን መጨመር ነው የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ብክነትን ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ በአገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት።
ፋብሪካው በሀገር ውስጥ መገንባቱ በሚፈለገው ጊዜ፣መጠን እና ዓይነት ማዳበሪያ ለማግኘት ያስችላል
Oct 12, 2025 84
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡-ፋብሪካው በሀገር ውስጥ መገንባቱ በሚፈለገው ጊዜ፣መጠን እና ዓይነት ማዳበሪያ ለማግኘት እንደሚያስችል ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት እና ፍላጎትን በራስ ዐቅም ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ያጋጥሙ የነበሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እንደሚቀርፍም አመልክቷል። የማዳበሪያ ፋብሪካው በሀገር ውስጥ መገንባቱ ያለውን ፋይዳ በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ጠቅልሎ መግለጽ እንደሚቻል በሚኒስቴሩ የግብዓት አቅርቦት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ተስፋ ለኢዜአ ገልጸዋል። በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ጥቅሙ ማዳበሪያ በምንፈልግበት ጊዜ፣ መጠን እና ዓይነት እንድናገኝ የሚያስችል መሆኑ ነው ብለዋል። የአቅርቦት ሰንሰለትን እና ጊዜን የሚያሳጥር መሆኑ ደግሞ ሁለተኛው የፋብሪካው በሀገር ውስጥ መገንባት ፋይዳ መሆኑን አንስተዋል። ከውጭ ሀገር ማዳበሪያ ሲገዛ ከጨረታ እስከ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ድረስ ባለው ሂደት የተንዛዛ ሰንሰለትን ማለፍ እና ረዥም ጊዜ መፍጀት አስገዳጅ መሆኑን አስረድተዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የአፈር ማዳበሪ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ እየናረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሦስተኛው የፋብሪካው ጥቅም ወጪ መቀነስ መሆኑን አስገንዝበዋል። መንግሥት በከፍተኛ ድጎማ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚያስገባ ጠቅሰው፤ በ2017 ዓ.ም ብቻ 84 ቢሊየን ብር ድጎማ ማድረጉን አረጋግጠዋል። በሀገር ውስጥ ማምረት ሲጀመር ለመርከብ ማጓጓዣና ለወደብ ኪራይ ይወጣ የነበረን ወጪ ያስቀራል ብለዋል። አስተማማኝ አቅርቦትና ሀገራዊ የማድረግ ዐቅምን የሚያሳድግ መሆኑን ያስረዱት አቶ መንግሥቱ፤ ለአርሶ አደሩም ማዳበሪያውን በወቅቱ ለማቅረብ እንደሚያስችል ነው ያስገነዘቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባውን የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሀገርን የሚያሻግሩ ትልልቅ የዲጂታል ኢኒሼቲቮችን የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ ዋነኛ ትኩረት መሆን አለበት
Oct 11, 2025 136
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡-ሀገርን የሚያሻግሩ ዲጂታል የልማትና የአገልግሎት ኢኒሼቲቮችን ለማሳካት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል መሆን እንዳለበት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ገለፁ። ከዛሬ ጥቅምት 1 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆየው ስድስተኛው አገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የማስጀመሪያ መረሃ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሒዷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ ማሳያ የሆኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተመረቁና የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መንግስት ለዘላቂ ልማትና እድገት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩ ናቸው ብለዋል። የዜጎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና የመንግሥትን አገልግሎት የሚያሳልጡ የዲጂታል አሠራሮችን በመተግበር ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከ900 በላይ የሚሆኑና በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ አማካይነት ለተገልጋዮች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል። ቴክኖሎጂና ልማት ተሰናስለው የሚሔዱ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ፤ የልማት ስራዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የሚተሳሰር በመሆኑ በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ለዚህም በተለያዩ አማራጮች ተደራሽ የሚደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ነው የጠቆሙት። የሳይበር ደህንነት ወር እንደ ሀገር በሳይበር ደህንነት ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን በስፋት ለማስገንዘብ እድል የሚፈጥርና የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል። ስለሆነም በመላ ሀገሪቱ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የተከናወኑ የልማት ስራዎች፣ ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችና የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሀገሪቷን ኢኮኖሚያዊና ሁሉን አቀፍ እድገት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። እነዚህና ሌሎች የልማት ስራዎች ለዘላቂ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት ያላቸውን ፋይዳ ለማጉላት ደህንነታቸውን በአግባቡ ጠብቆ ማቆየት የግድ ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የሳይበር ደህንነት ጉዳይን ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል። ለአብነትም በየዓመቱ የሚከበረው የሳይበር ደህንነት ወር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር አንዱና ዋነኛው መሆኑን አስረድተዋል። በእነዚህና ሌሎች የቅድመ መከላከል ስራዎች በተከናወኑ ተግባራት የሳይበር ጥቃት ምጣኔን መቀነስ ተችሏል ነው ያሉት። የዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር "የሳይበር ደህንነት የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሔድ ይሆናል፡፡
የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ይገባል
Oct 11, 2025 138
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፦ የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የሚተሳሰር መሆኑን በመገንዘብ በዘርፉ የሚከናወኑ ቅንጅታዊ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ገለፁ። 6ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ማስጀመሪያ ስነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ ማሳያ የሆኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተመረቁና የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መንግስት ለዘላቂ ልማትና እድገት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩ ናቸው ብለዋል። የዜጎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና የመንግሥትን አገልግሎት የሚያሳልጡ የዲጂታል አሠራሮችን በመተግበር ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከ900 በላይ የሚሆኑና በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ አማካይነት ለተገልጋዮች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል። ቴክኖሎጂና ልማት ተሰናስለው የሚሔዱ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ፥ የልማት ስራዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ከሀገር ሉአላዊነት ጋር የሚተሳሰር በመሆኑ በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ለዚህም በተለያዩ አማራጮች ተደራሽ የሚደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ነው የጠቆሙት። የሳይበር ደህንነት ወር እንደ ሀገር በሳይበር ደህንነት ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን በስፋት ለማስገንዘብ እድል የሚፈጥርና የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል። በመሆኑም በመላ ሀገሪቱ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንሚገባ አስገንዝበዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጽናት እየሠራ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Oct 10, 2025 192
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2018(ኢዜአ)፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጽናት እየሠራ ይገኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ቴክኖሎጂ መር አዘማኝነት ላይ የሚያተኩረው የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በስኬት መጠናቀቅን ተከትሎ አሁን በበለጠ የማሽን ግብዓት(አቶሜሽን) በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያጠናክረውን ዲጂታል 2030ን አስጀምረናል ብለዋል። የፍትኅ ተደራሽነት ለዜጎች እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን እውቅና በመሥጠትም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጽናት እየሠራ ይገኛል ነው ያሉት። ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቶች በአግባቡ መቀዳታቸውን ለማረጋገጥ ድምጽን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር ብሎም በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠብቀው የሚቆዩበትን ስማርት የፍርድ ሥርዓት አልምቶ በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል በመልዕክታቸው። ሥርዓቱ ፍትኅ ፈላጊዎች ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በአካል በችሎት መገኘት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ጉዳያቸውን መከታተል እንደሚያስችላቸውም ነው ያስታወቁት። በተጨማሪም የለሙት የNetwork Operation Center እና Integrated Case Management System የፍርድ ሂደት ባለጉዳዮች በዲጂታል አውታሮች ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ያስችላሉ ብለዋል። በአሁኑ ወቅት 24 የፌደራል ቅርንጫፎች በሥርዓቱ የተሸፈኑ መሆኑ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ ወደ ክልሎችም እንደሚስፋፋ ተስፋ አለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በኮሜሳ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ጉዳይ አድርጋ እየሰራች መሆኑን ማስገንዘብ ተችሏል
Oct 10, 2025 165
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2018(ኢዜአ)፦ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ጉዳይ አድርጋ እየሰራች መሆኑን ማስገንዘብ እንደቻለች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ። 24ኛው የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ ትናንት በኬንያ ናይሮቢ ተካሂዷል። በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ከኮሜሳ አባል ሀገራት የተውጣጡ የሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባኤው ባደረጉት ንግግር ዲጂታላይዜሽን የኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ወሳኝ ምሰሶ መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ የኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ ባሉ ጠንካራ የዲጂታል መሠረተ ልማት በመገንባትና ሰፊ ክህሎት ከማፍራት አኳያ ኢትዮጵያ አመርቂ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ እንደምትገኝ መጥቅሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች የኢትዮጵያን ዕድገትና ለውጥ ለመምራት ብሎም ጠንካራ ዲጂታል መሠረተ ልማት ለመፍጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓትና የመንግሥት አገልግሎቶችን አውቶሜት የማድረግ ተግባራት ለዲጂታል ዘርፉ እድገት እንደ ቁልፍ ምሳሌዎች የሚወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እንደ ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ ያሉ መርሐ ግብሮች ወጣቶች የዲጂታል ክህሎትን በመታጠቅ እና በዘርፉ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጡ የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የሀገር ውስጥ የዲጂታላይዜሽን ጥረቶች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስገኙ ከቀጣናዊ ግቦች ጋር መጣጣም እንደሚገባም መናገራቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም አክለውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ወጣቶች ለአህጉሪቱ ልማትና ዕድገት ወሳኝ ሃብት መሆናቸውን ማንሳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ሀገራት የአህጉሪቱን የጎለበተ የወጣቶች ተሰጥኦ እና አቅም መጠቀም እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
ስፖርት
ኢትዮጵያ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከቡርኪናፋሶ ጋር ዛሬ ታደርጋለች
Oct 12, 2025 76
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ከቡርኪናፋሶ ጋር ትጫወታለች። የሀገራቱ ጨዋታ በኦገስት 4 ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ይደረጋል። በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በፊት ከጊኒ ቢሳው ጋር ባደረገው የማጣሪያ መርሃ ግብር 1 ለ 0 በማሸነፍ በምድቡ ሁለተኛ ድሉን ማስመዝገቡ ይታወቃል። በብራማ ትራኦሬ የሚሰለጥነው የቡርኪናፋሶ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በፊት ከሴራሊዮን ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 0 አሸንፏል። ቡድኑ ነጥቡን ወደ 18 ከፍ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ሀገራት በዚሁ ምድብ ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ቡርኪናፋሶ 3 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። ሀገራቱ ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው አምስት የእርስ በእርስ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ ስታሸንፍ ቡርኪናፋሶ ሶስት ጊዜ ድል ቀንቷታል። አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታዎቹ ቡርኪናፋሶ 12 ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ ኢትዮጵያ ሶስት ግቦችን አስቆጥራለች። ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ለሆነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የዛሬው ጨዋታ የማጣሪያ ጉዞውን በድል ለመደምደም ያስችለዋል። ቡርኪናፋሶ ማሸነፍ ከቻለች ለዓለም ዋንጫው ለማለፍ በሚደረገው የጥሎ ማለፍ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችላትን እድል ታሰፋለች። በዚሁ ምድብ የምትገኘው ግብጽ በ23 ነጥብ ለዓለም ዋንጫ በቀጥታ ማለፏ የሚታወስ ነው። በምድብ አንድ ግብጽ ከጊኒ ቢሳው፣ ጅቡቲ ከሴራሊዮን ዛሬ በተመሳሳይ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በድሬዳዋ ከተማ ሊደረጉ የነበሩ የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታዎች ወደ ሃዋሳ ተዘዋውረዋል
Oct 11, 2025 129
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፦ በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ ሊደረጉ የነበሩ የመክፈቻ ጨዋታዎች ወደ ሃዋሳ መዘዋወራቸውን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ። የሊጉ የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ውድድር በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ መገለጹ ይታወቃል። ይሁንና በአሁኑ ወቅት ድሬዳዋ ከተማ ውድድሩን ለማስተናገድ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ በመሆኑና ዝግጁ አለመሆኑን በመግለጹ ድሬዳዋ ላይ ሊደረጉ የነበሩ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች ወደ ሃዋሳ ከተማ መዞሩን ማህበሩ ገልጿል። የተስተካከለውን መርሃ ግብር በቅርቡ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። 20 ክለቦች በሁለት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጊኒ ቢሳውን አሸነፈች
Oct 8, 2025 298
አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጊኒ ቢሳው ጋር ባደረገችው ጨዋታ 1 ለ 0 አሸንፋለች። በሩዋንዳ አማሆሮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራምኬል ጀምስ በ27ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል። በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ በማጣሪያው ሁለተኛ ድሏን አስመዝግባለች። በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች። ሽንፈት ያስተናገደችው ጊኒ ቢሳው በ10 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አካባቢ ጥበቃ
በምዕራብ ወለጋ ዞን በክረምት ወራት ለተተከሉ ችግኞች የሚደረገው እንክብካቤ ቀጥሏል
Oct 11, 2025 127
ጊምቢ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡-በምዕራብ ወለጋ ዞን በክረምት ወራት ለተተከሉ ችግኞች የሚደረገው እንክብካቤ መቀጠሉን የዞኑ የግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። የምዕራብ ወለጋ ዞን የግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፈይሳ ሀምቢሳ እንደገለጹት በዞኑ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል። ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች ውጤታማ እንዲሆኑ በዞኑ ነዋሪዎች የችግኝ እንክብካቤ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ወቅትም በተለይም ባለፈው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ ነው ብለዋል። በአጠቃላይ በዞኑ ባለፉት ዓመታት በተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች አካባቢውን አረንጓዴ ከማልበስ ባለፈ ለግብርና ስራም እገዛ እያደረጉ መሆኑ ገልጸዋል። በችግኝ እንክብካቤው እየተሳተፉ ከሚገኙ መካከል ወይዘሮ ለሊሴ ብርሃኑ፣ በክረምት ወራት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን እየተንከባከቡ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በአካባቢያቸው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን በመገንዘባቸው አሁንም በእንክብካቤው መጠንከራቸውን ጠቅሰዋል። አቶ ገረመው ነገራ በበኩላቸው የተተከሉ ችግኞች ለውጤት እንዲበቁ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል። ሁሉም በየአካባቢው ችግኞችን በመንከባከብ ለውጤት ማብቃት አለበት ያሉት ደግሞ አቶ ነጻነት አበበ ሲሆኑ ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች የተለያየ ጥቅም እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ትራንስፖርት ያሏትን ተሞክሮዎች የምታቀርብበት አህጉራዊ ሁነት
Oct 10, 2025 224
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፦ “ አፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ዊክ 2025” የተሰኘ የአፍሪካ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሳምንት ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይደረጋል። ሳምንቱ “ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የትራንስፖርት ስርዓትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ይካሄዳል። ተቀማጭነቱን ኬንያ ናይሮቢ ያደረገው ”አፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ አሊያንስ” የተሰኘ ድርጅት፣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም እና ሌሎች አጋሮች ሁነቱን በጋራ አዘጋጅተዋል። በሁነቱ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ኢኖቬተሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ ተዋናያን ይሳተፋበታል። ሳምንቱ አፍሪካ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽርካሪዎች የምታደርገውን ሽግግር ማፋጠን ዋንኛ ትኩረቱ አድርጓል። የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን በአረንጓዴ ትራንስፖርት ሳምንቱ ላይ ከ500 በላይ ሰዎች በአካል እና ከ2000 በላይ ሰዎች በበይነ መረብ አማራጭ እንደሚሳተፉ ለኢዜአ ገልጸዋል። በሳምንቱ ላይ ከ30 በላይ የውይይት መድረኮች እና አውደ ርዕዮች እንደሚካሄዱ ጠቅሰው ከነዚህም አንዱ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚገኙበት መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል። አረንጓዴ ትራንስፖርትን የተመለከቱ የጥናት ውጤቶች እና ግኝቶች ይፋ እንደሚደረጉም ነው የገለጹት። ከሁነቶቹ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪ ጉብኝት መርሃ ግብር እንደሚኖር ጠቅሰው ከ200 በላይ ተሳታፊዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገጣጣሚዎችን፣ የኤሌክትሪክ ባሶች እንቅስቃሴ፣ የተሰሩ የኃይል መሙያ ማዕከላት፣ ዴፖዎች እንዲሁም በሽያጭ፣ አቅርቦት እና ጥገና የተሰማሩ አካላትን እንቅስቃሴ እንደሚጎበኙ አመልክተዋል። በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተካሄደው “ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024” ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ላይ የተነሱ አጀንዳዎች አፈጻጸም እንደሚገመገምም እንዲሁ። የትራንስፖርት ሳምንቱ አካል የሆነ የ1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መኪና ጉዞ በመካሄድ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ተጓዦቹ ዛሬ ሶስተኛ ቀናቸውን እንደያዙና የፊታችን እሁድ አዳማ እንደሚደርሱ ጠቁመዋል። ጉዞው በኤሌክትሪክ መኪናዎች አማካኝነት ቀጣናዊ የትራንስፖርት ስርዓትን መፍጠርን ያለመ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በማድረግ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የማስፋት ስራ እያከናወነች እንደምትገኝም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት። በኢትዮጵያ መንገዶች ላይ ካሉ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎች መካከል ከ115 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች እንደሚገኙበት ጠቁመው ይህም ከአጠቃላይ ተሽከርካሪዎች የሰባት መቶ ድርሻ እንደያዙ ጠቁመዋል። የግሉን ዘርፍ እና የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ጣቢያዎች መገንባታቸውን ነው ያብራሩት። በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት 16 ተቋማት የኤሌክትሪክ መኪናዎችን እየገጣጠሙ መሆናቸውን ጠቅሰው የአረንጓዴ ትራንስፖርት በህዝብ ትራንስፖርት ላይ እየሰፋ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኤሌክትሪክ አውቶቢሶች የማስፋት ስራ ውጤት እያስገኘ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት በኤሌክትሪክ መኪና ለተሰማሩ አካላት የታክስ ማበረታቻ ማድረጉንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ትራንስፖርት በፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመደገፍ ውጤታማ ስራን እያከናወነች እንደምትገኝና ይህንንም መልካም ተሞክሮዋን በአህጉራዊው ሁነት ላይ እንደምታቀርብ አመልክተዋል። የትራንስፖርት ሳምንቱ አካል የሆነ የወጣቶች ጉባኤ በበይነ መረብ መካሄዱንና በዚህም መደረክ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ ለአፍሪካ ሀገራት ማቅረቧን ገልጸዋል። የአፍሪካ አረንጓዴ ትራንስፖርት ሳምንት አህጉሪቷ ከብክለት የጸዳ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ስርዓት ለመፍጠር ለምታደርገው ጥረት አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተመላክቷል።
ከተሽከርካሪ የሚወጣውን የበካይ ጋዝ ልቀት ለመከላከል የሚረዱ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Oct 9, 2025 191
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2018(ኢዜአ)፦ከተሽከርካሪ በሚለቀቅ ጭስ የሚከሰተውን የበካይ ጋዝ ልቀት ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የተሽከርካሪ በካይ ጋዝ ልቀት መጠን ደረጃ እና የአፈጻጸም መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዘውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዛሬ ሰጥቷል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ያብባል አዲስ በመርሃ ግብሩ ላይ የተሽከርካሪዎች ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት፣ በቴክኖሎጂ አለመዘመን እና ከነዳጅ አይነቶች ጋር ያሉ ማነቆዎች ለችግሩ ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል። መንግስት ችግሮቹን ለመፍታት በአገር አቀፍ ደረጃ በተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ ልቀት ላይ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን አስታውቀዋል። ቢሮው መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ማካሄዱን ጠቅሰው ለተፈጻሚነቱ የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል የተጀመሩ ተግባራት ከበካይ ጋዝ ልቀት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያግዙ ሃላፊው ተናግረዋል። 'የፓርትነርሺፕ ፎር ሄልዝ ሲቲ ፕሮጀክት' ከፍተኛ አማካሪ ተፈሪ አበጋዝ በበኩላቸው፤ ከተሽከርካሪዎች የሚወጣው በካይ ጋዝ ጤናማ አካባቢ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ፈተና መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ከተሽከርካሪዎች የሚወጣውን የበካይ ጋዝ ልቀት ለመቆጣጠር መመሪያውን በፍጥነት መተግበር አስፈላጊ ነው ብለዋል። የተሽከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ ማህበር ምክትል ሰብሳቢ በሀይሉ ገረሱ ከበካይ ጋዝ ልቀት ጋር በተያያዘ የወጣው መመሪያ ውጤታማ እንዲሆን ማህበሩ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት አስታውቀዋል። የጎህ ታክሲ ባለንብረቶች ሰብሳቢ ሰላማዊት ጌታቸው በበኩላቸው ተሽከርካሪዎች ከበካይ ጋዝ ልቀት ነፃ እንዲሆኑ የሚከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለአብነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲገቡ መደረጉ እና የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቆጣጠር መመሪያ መውጣቱ የሚደገፍ ተግባር መሆኑን አንስተዋል። መንግሥትም ተሽከርካሪዎች ከበካይ ጋዝ ልቀት ነፃ እንዲሆኑ ለዘርፉ ተዋናዮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በአሪ ዞን በክረምት ወራት የተተከሉ ችግኞችን ለውጤት ለማብቃት እንክብካቤ እየተደረገ ነው
Oct 8, 2025 208
ጂንካ፤መስከረም 28/2018(ኢዜአ) :-በአሪ ዞን በክረምት ወራት የተተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ሀገር በቀል ችግኞችን ለውጤት ለማብቃት ሕብረተሰቡን ያሳተፈ እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። በጽሕፈት ቤቱ የደን ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ክንዴ ፍስሃ፤ በዞኑ የተራቆቱ አካባቢዎችን በማልማት የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ስራውን ለማጠናከር ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በክረምቱ ወቅት አርሶ አደሮችና ወጣቶችን ጨምሮ ከ174 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መካሄዱን አስታውሰዋል። በመርሃ ግብሩ የአንድ ጀምበርን ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው በርካታ ሀገር በቀል ችግኞች መተከላቸውን አንስተው፤ አሁን ላይ የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ የእንክብካቤ ስራ በየደረጃው እየተሰራ ነው ብለዋል። ችግኞቹ በወቅቱ የተተከሉት በተራሮች አካባቢዎች መሆኑን ጠቅሰው፤ 1 ሺህ 421 ሄክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ልማትና ሌሎች የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። በዞኑ ደቡብ አሪ ወረዳ የሸጲ ቀበሌ አርሶ አደር ማርቆስ ደጉ፥ በአካባቢው ቀደም ሲል የእርሻ ማሳ ለማስፋፋት ደኖች ያለ አግባብ ሲጨፈጨፉ እንደነበር አስታውሰዋል። በአካባቢው የደኖች ያለ አግባብ መጨፍጨፍ የጎርፍና የአፈር መንሸራተት አደጋዎች እንዲከሰቱ ማድረጉን ጠቅሰው፥ይህም በግንዛቤ እጥረት እንደሆነ መረዳታቸውን ተናግረዋል። አሁን ላይ ከግብርና ባለሙያዎች ባገኙት ግንዛቤ የተራቆቱ አካባቢዎችን እያለሙ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው ክረምትም በህዝብ ተሳትፎ የተተከሉ ችግኞችን እየተንከባከብን ነው ያሉት አርሶ አደር ማርቆስ፤ ይህም ለአካባቢ ልማት እያስገኘ ያለውን ውጤት እየተመለከትን ስለሆነ የበለጠ ለማስፋት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በዞኑ ባካ ዳውላ አሪ ወረዳ የሴኔጋል ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አለሙ ፈለቀ በበኩላቸው፤ በአካባቢው የአረንጓዴ ልማት ስራን ማከናወን ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በጎርፍ የሚታጠበውን ለም መሬት መጠበቅ መቻላቸውን ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን በሙሉ አቅም መተግበር ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው - መሐመድ አሊ ዩሱፍ
Oct 10, 2025 199
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ሙሉ ለሙሉ ገቢራዊ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 24ኛው የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ አገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሁነቶች በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት እና ተወዳዳሪነት ተጽእኖ እያሳደሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህም ከመቼው ጊዜ በላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሙሉ ለሙሉ በአፋጣኝ መተግበር እንደሚገባው የሚያመላክት ነው ብለዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ከቀረጥ ጋር ያልተያያዙ የንግድ ገደቦችን በማንሳት እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የተሳለጠ የንግድ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችሉ ማዕቀፎችን በመተግበር ለአጀንዳ 2063 መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የኮሜሳ፣ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ (ሳዴቅ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) የሶስትዮሽ ትብብር ማዕቀፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ማዕቀፉ የትስስር አጀንዳ ተምሳሌት እና አንድ የሆነች፣ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች አህጉር ለመፍጠር የተጀመረውን ጉዞ የተስፋ ብርሃን ፈንጣቂ መሆኑን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ቀጣናዊና አህጉራዊ የትስስር አጀንዳዎችን ትግበራ ለማፋጠን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መግለጻቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢጋድ እና ጀርመን በፍልሰት አስተዳደር እና አየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
Oct 10, 2025 214
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና ጀርመን በፍልሰት አስተዳደር እና አየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያላቸውን የቆየ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። ጀርመን ለኢጋድ ቀጣና የተለያዩ የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጋለች። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና ጀርመን በልማት ትብብራቸው ዙሪያ በጅቡቲ ስትራቴጂካዊ ምክክር አድርገዋል። በምክክሩ ላይ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ዘርፍ ኃላፊ ሃኒንግ እና በጅቡቲ የጀርመን አምባሳደር ሄይከ ፉለር (ዶ/ር) ተገኝተዋል። ስትራቴጂካዊ ምክክሩ ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር የገመገሙ ሲሆን በቀጣይ የግንኙነት ማዕቀፎች ላይም መክረዋል። ፍልሰት እና አየር ንብረት ለውጥ የውይይቱ አበይት ማጠንጠኛዎች ናቸው። ሁለቱ ወገኖች የጀርመን ቀጣናዊ የፍልሰት ፈንድ ዳግም ማዋቀር ሂደት መልካም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በማንሳት የኢጋድ የቀጣናዊ የፍልሰት ፖሊሲ ማዕቀፍ ፣ የነጻ እንቅስቃሴ የህግ ማዕቀፎች እና የዜጎችን የአኗኗር ሁኔታ የማጠናከር ስራ ለመደገፍ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ጀርመን ለኢጋድ የፍልሰት ፖሊሲ ትግበራ ፕሮጀክት ቀጣይ ምዕራፍ ትግበራ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ለመደገፍ ቃል መግባቷን ኢዜአ ከቀጣናዊ ተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም ጀርመን በኢጋድ አባል ሀገራት ለሚከናወኑ የማይበገር የአየር ንብረት ለውጥ አቅም ግንባታ ስራዎች በቀጣናዊ የአደጋ ፋይናንስ ፕሮግራም አማካኝነት 22 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ለመደገፍ መዘጋጀቷ ተመላክቷል። የፋይናንስ ማዕቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ድንገተኛ አደጋዎችን የመከላከል ስራዎች የሚደገፍ እና የኢጋድ የድርቅ አደጋን የመቋቋም እና ዘላቂነት ኢኒሼቲቭ ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን የሚደግፍ ነው። በስትራቴጂካዊ ምክክሩ ሁለቱ ወገኖች ውጤት ተኮር፣ አሳታፊ እና ተጠያቂነትን መሰረት ያደረገ አጋርነትን መፍጠር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢጋድ እና ጀርመን ትብብራቸውን ለማጠናከር፣ የጋራ ስራዎቻቸው የአባል ሀገራት የቅድሚያ ትኩረቶች ያማከሉ እንዲሆኑና የፖሊሲ ምክክራቸውን በመደበኛነት ለማከናወን ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ኢጋድ እና ጀርመን 37 ዓመታትን ያስቆጠረ አጋርነት እንዳላቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።
የአፍሪካ ህብረት የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል
Oct 7, 2025 281
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷ ወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራውን ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ከፓን አፍሪካ የወጣቶች ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት ዲያላ ሞሙኒ እና አህመድ ቤኒንግ ጋር በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። የአፍሪካ ህብረት የወጣቶች ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ኡቺዚ ምካንዳዋየር በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። የአፍሪካ ህብረት ስምምነቱ የአህጉሪቷ ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ወጣቶችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልጿል። በስምምነቱ አማካኝነት የፓን አፍሪካ የወጣቶች ህብረት በሀገራት ደረጃ ያሉ የወጣት ምክር ቤቶች የሚያቀናጅ አህጉራዊ ማዕቀፍ እና ለአፍሪካ ወጣቶች እንደ ጋራ ድምጽ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የፓን አፍሪካ የወጣቶች ህብረት የፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት ንቅናቄ የወለደው አህጉራዊ አደረጃጀት ሲሆን እ.አ.አ በ1962 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጊኒ ኮናክሪ ባደረጉት ስብስባ ህብረቱን አቋቁመዋል። ህብረቱ የተመሰረተው በወቅቱ ወጣቶች አፍሪካ ከቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ ለነበረው ትግል አቅም እንዲሆኑ ከማሰብ የመነጨ ነው። የወጣቶች ህብረቱ እንቅስቃሴ የፖለቲካ ድጋፍን በማሰባሰብ እና የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ስትራጂካዊ ሚናውን ተጫውቷል። የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት እ.አ.አ በ2006 ባደረገው ስብስባ የፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት በድጋሚ የማደራጀት የውሳኔ ሀሳብ በማፅደቅ ህብረቱ የአህጉሪቷ የወጣት መዋቅር እንዲሆን በይኗል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካ በዓለም መድረክ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት ድጋፉን ሊሰጥ ይገባል- አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ
Sep 24, 2025 861
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2018(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካ በዓለም መድረክ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት እያደረገችው ላለው ጥረት ድጋፍ እንዲሰጥ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ ጥሪ አቀረቡ። 80ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ በድርጅቱ ዋና መቀመጫ ኒውዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። የጠቅላላ ጉባኤው አካል የሆነ ከፍተኛ የምክክር እና ክርክር መድረክ ዛሬ በኒው ዮርክ ተጀምሯል። “'ደህናነት በአብሮነት፤ 80 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሰላም፣ ለልማት እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ጉባኤው የሚካሄደው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ “እየተለወጠ ባለው የዓለም የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ የአፍሪካ ምልከታዎች” በሚል መሪ ሀሳብ ለጉባኤው ተሳታፊዎች የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። አምባሳደር ሳልማ በመልዕክታቸው አፍሪካ በተለያዩ መስኮች ራሷን ለመቻል እያከናወነቻቸው ያሉ ስራዎች ፍሬ እያፈሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች በራሷ ፋይናንስ በማድረግ ረገድ ለውጥ ማምጣቷን በማሳያነት ጠቅሰው የአፍሪካ የሰላም እና ደህንነት ማዕቀፍ በአፍሪካውያን ገንዘብ እና ባለቤትነት እየተመራ እንደሚገኝም አመልክተዋል። የአፍሪካ ህብረት የሰላም ፈንድ በአፍሪካውያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በትግበራ ላይ መሆኑን አንስተዋል። አምባሳደሯ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ላይ ያላቸውን ሀሳብ ያጋሩ ሲሆን የንግድ ቀጣናው ዜጎች እና ገበያን ከማስተሳሰር ባለፈ ሰው ሰራሽ ድንበሮች በእኛ ላይ ከመጫናቸው በፊት የነበረውን የንግድ ትስስር እና ትብብር እንደሚመለስ ተናግረዋል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ ያላት ድርሻ እያደገ መምጣቱን ገልጸው አህጉሪቷ በቡድን 20 ቋሚ መቀመጫ ማግኘቷ አበይት ማሳያ ነው ብለዋል። አፍሪካ በቡድን 20 ውስጥ ያገኘችው ቋሚ መቀመጫ ለዓለም ችግሮች መፍትሄ ያላትን አይተኬ ሚና በግልጽ የሚያመላክት እንደሆነም ተናግረዋል። እየተለወጠ ያለው የዓለም ስርዓት ለአፍሪካ በርካታ እድሎችን ይዞ መጥቷል ያሉት ምክትል ሊቀመንበሯ ይህን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አምባሳደር ማሊካ ዓለም አቀፍ አጋሮች አፍሪካ የዓለም የፋይናንስ ስርዓት እኩልነት የሰፈነበት እንዲሆን እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ውክልና እንድታገኝ እያነሳች ያለው ፍትሃዊ ጥያቄ እና እውነተኛ መሻት እንዲደግፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አፍሪካ ከዓለም ጋር ያላት ትብብር በጋራ መከባበር እና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸው አፍሪካ ስታድግ የዓለም ብልጽግና እና መረጋጋት ይረጋገጣል ሲሉም ተናግረዋል።
ሐተታዎች
ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ በሀገሩ ህልሙን እውን ያደረገው ወጣት...
Oct 9, 2025 221
ሐረር ፤መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦በሐረር ከተማ ተወልዶ ያደገው ነስረዲን አህመድ፤ በውጭ ሀገር ሰርቶ መለወጥን በማሰብ ከአመታት በፊት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ እንቅስቃሴ ጀመረ። የመጓዝ እቅዱም ተሳካለትና በዱባይ ለስምንት ዓመታት በስራ ላይ ማሳለፉን ያስታውሳል፤ በበረሃው ምድር ሌት ተቀን በስራ እየደከመ ህይወቱን ሊለውጥለት የሚችል ገንዘብ ለመያዝ ቢጥርም ባሰበው ልክ ሊሳካለት አልቻለም። በመሆኑም ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ በመመለስ ሰርቶ የመለወጥ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይውል ሳያድር ወደ ስራ ገባ። ከበረሃው ንዳድ ወጥቶ በሀገሩ ሰርቶና አልምቶ መለወጥን የሰነቀው ነስረዲን በሀረር የንብ ማነብ ስራን ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንደሆነው ያስታውሳል። በምንሰራበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት ሌት ከቀን መስራት ከቻልን የማናሳካው ነገር አይኖርም የሚለው ወጣቱ አሁን በሀገሩና በወንዙ በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን ይናገራል። የነስረዲን የንብ ማነብ ስራ የተጀመረው በጥቂት ቀፎዎች የነበረ ቢሆንም በስድስት ወራት ውስጥ ግን 50 ቀፎዎች ማድረስ መቻሉን ያስታውሳል። በሀገሬ ህልሜ እውን እየሆነ ነው የሚለው ወጣቱ የንብ ማነብ ስራውን አጠናክሮ በመቀጠል አሁን ላይ የንብ ቀፎዎቹን 300 ሲያደርስ ለ30 የአካባቢው ወጣቶችም የስራ እድል ፈጥሯል። በአረብ ሀገር የቆየባቸውን ዓመታት በቁጭት የሚያስታውሰው ነስረዲን መልፋትና መድከም ከተቻለ በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል እኔ ጥሩ ማሳያ ነኝ ይላል። ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ ወደ ሀገሬ ተመልሼ የስኬት መንገድን ጀምሬያለሁ በቀጣይም ጠንክሬ እሰራለሁ ብሏል። በቀጣይ ከንብ ማነብም ባለፈ የማር ማቀነባበርያ አነስተኛ ኢንዱስትሪ የማቋቋም ትልም እንዳለው ተናግሮ ለዚህም እንደሚተጋ አረጋግጧል። በዚሁ የልማት ፕሮጀክት ላይ የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ሸዊብ መሀመድ፤ ከዚህ ቀደም ያለምንም ስራ ተቀምጦ መሽቶ ይነጋ እንደነበር አስታውሶ አሁን እያገኘ ባለው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብ እየረዳ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት በድሪ ሙሳም፤ በነስረዲን ጥረት እርሱን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ስራ የተፈጠረላቸው በመሆኑ ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን አንስቶ በቀጣይ እርሱም የራሱን ተመሳሳይ ስራ ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል። በሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የንብ እርባታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኢብሳ ዩስፍ፤ የነስረዲን ጥረትና የአጭር ጊዜ ስኬት ለሌሎች ወጣቶችም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። በመሆኑም በክልሉ የማር ምርታማነትን ለማጎልበት በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ የንብ መንደር በመመስረት ዘርፉን የማጎልበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአፍሪካ መምህራን፤ የአህጉሪቷ መጻኢ ጊዜ ቀራጺዎች
Oct 3, 2025 462
አፍሪካ በወጣቶች የታደለች ሀገር ናት። ከአህጉሪቷ ህዝብ መካከል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው እድሜው ከ25 ዓመት በታች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ መጻኢ ጊዜን የሚወስነውን ወጣት ማን ያስተምረዋል? የሚለው ጥያቄ ቁልፍ ነው። ይህ ጥያቄ ከመማሪያ ክፍሎች እና መጻሕፍት ባለፈ የአፍሪካ ልማት አበይት አጀንዳ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። በዓለም ደረጃ ትልቅ የእድገት እና የልማት ሞተር የሆነውን ወጣት በብዛት የያዘችው አፍሪካ ትውልዱን የሚቀርጽ መምህራን ውጪ ህልሟን ማሳካት የሚታሰብ አይሆንም። የአፍሪካ ህብረት በአህጉር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እ.አ.አ በ2030 በትንሹ 15 ሚሊዮን አዲስ መምህራን እንደሚያስፈልጉ አስታውቋል። ይህን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እና ጠንካራ ሪፎርሞችን ማድረግ ይጠይቃል። አፍሪካ የትምህርት መሰረተ ልማትን ለማሻሻል፣ የመምህራንን ቁጥር ለመጨመር እና በትምህርት ዘርፍ የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት 90 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ሲል ህብረቱ ገልጿል። ጉዳዩ ከትምህርት ባለፈ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ያለው ነው። መምህራን የእያንዳንዱ ክህሎት፣ ስራ እና ኢኖቬሽን የሀሳብ መሐንዲስ ናቸው። የአፍሪካ መጻኢ ጊዜ የመወሰን አቅም አላቸው። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የመምህራን ትምህርት ስርዓታቸው ላይ ማሻሻያ እያደረጉ ይገኛል። የአፍሪካ መዲና የሆነችው ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ በርካታ ሪፎርሞችን እያደረገች ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ የመምህራንን አቅም መገንባት እና የብቃት ደረጃን ማሳደግ ይገኝበታል። የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ የመምህራን ልማት ንቅናቄ በማድረግ መምህራን በተለያዩ የትምህርት እርከኖች አቅማቸውን እንዲጎለብት ተከታታይ ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ነው። በአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም አማካኝነንት ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ መምህራን የዲጂታል ክህሎታቸው በማዳበር እና ተከታታይ የብቃት ምዘና በማድረግ አቅማቸውን እየተገነባ ይገኛል። በነዚህ ስራዎች የትምህርት ውጤት ላይ አበረታች መሻሻሎች ታይተዋል። መንግስት የሰለጠነ መምህራንን ቁጥር ማሳደግን የሪፎርሙ አካል አድርጎ እየሰራ ነው። ጋና የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችን ወደ ዩኒቨርስቲ በማሳደግ ሙያዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ እየሰራች ትገኛለች። ኬንያ ብቃት ላይ የተመሰረተ የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ የመምህራን መማር ማስተማር የበለጠ ተግባር ተኮር እና ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን የጀመረችው ተግባር ተጠቃሽ ነው። ሩዋንዳ የስርዓተ ትምህርት አሰራሮቿን ከመምህራን ስልጠና ጋር በማጎዳኘት የመምህራን እጥረትን ለመቀነስ እና ክህሎታቸውን ለማሳደግ እየሰራች ነው። ለትምህርት ዘርፍ የሚመደበው በጀት በቂ አለመሆን፣ የተማሪ እና ክፍል ጥምርታ አለመመጣጠን፣ የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር በሚፈለገው ደረጃ አለማደግ፣ የዲጂታል ክህሎት ማነስ እና ከፍላጎት አንጻር በቂ የሰለጠነ መምህራን አለመኖር የአህጉሪቷ የትምህርት ዘርፍ ፈተናዎች ናቸው። የፓን አፍሪካ የመምህራን ትምህርት ኮንፍረንስ በያዝነው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሄዷል። "በአፍሪካ የመምህራን ትምህርት ስርዓትን መቀየር” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ኮንፍረንስ የትምህርት ሚኒስትሮች፣ የመምህራን ማህበራት ተወካዮች፣ ምሁራን፣ የግሉ ዘርፍና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና የልማት አጋሮች ተወካዮች ተሳትፈዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በኮንፍረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር ትምህርት ለሰው ሃብት ልማትና ለምጣኔ ሀብት ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል። በአፍሪካ የሚፈለገውን ልማትና ዕድገት ለማምጣት የትምህርት ተደራሽነት ላይ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሪፎርሞችን ተግባራዊ ማድረጓንና በዚህም ውጤት መገኘቱን አንስተዋል። የመምህራንን አቅም ለመገንባት የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት በኩልም የተሻለ ስራ መሰራቱን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የጠቀሱት። የትምህርት ጥራትና የመምህራን እጥረት ላይ እንደ አህጉር አሁንም ያልተፈታ ችግር መኖሩን ጠቁመው፤ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አባል ሀገራቱ ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የትምህርት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ጋስፓርድ ባንያንኪምቦና በበኩላቸው በአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ሳይንስና ፈጠራን የበለጠ ለማዳበር የመምህራንን አቅም ማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል። ለዚህም ለመምህራን አቅም ግንባታ የተለያዩ ኤኒሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ የአፍሪካ የ2063 የልማት ዕቅዶች ዕውቀት መር በሆነ መንገድ ቢተገበሩ ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል። የአፍሪካ መምህራንን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከፈጣንና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ ጋር መላመድ እንደሚገባም ነው ያነሱት። በአፍሪካ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን የበለጠ ለማሳደግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከወቅቱ ጋር ማዛመድ ይገባል ብለዋል። በኮንፍረንሱ ላይ መምህራንንና ትምህርትን የተመለከቱ የተለያዩ አህጉራዊ ስትራቴጂዎች ይፋ ተደርገዋል። የአፍሪካ የትምህርት ስትራቴጂ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035 የሚተገበር) የአፍሪካ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ፣ የአፍሪካ ሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ እንዲሁም የአፍሪካ የትምህርት የክህሎት ልማት የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ሆነዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ መምህራትን ማህበረሰብ የአሰራር ማዕቀፍ ወደ ትግበራ ገብቷል። ይፋ የሆኑት ስትራቴጂዎች እና የአሰራር ማዕቀፎች የመምህራን ትምህርት፣ ሙያዊ ልህቀት፣ መሰረተ ትምህርት፣ ዲጂታል ክህሎቶች እና ኢኖቬሽን ተኮር የማስተማር ዘዴ ላይ መዋቅራዊ ለውጦችን የማምጣት ግብ እንዳላቸው የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል። በኮንፍረንሱ ላይ የ2025 የአፍሪካ መምህራን ሽልማት የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮው የዓለም የመምህራን ቀን በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተከብሯል። አህጉራዊው ሁነት በአፍሪካ የመምህራን ድምጽ የበለጠ ጎልቶ እንዲሰማ የማድረግ ፣ የትምህርት ኢንቨስትመንት መጠን እንዲያድግ እና የባለድርሻ አካላት ትብብርን የማጠናከር አላማ እንዳለው ተገልጿል። የመምህራንን አቅም ማሳደግ የአፍሪካ የትምህርት ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ አበይት ትኩረቶች መካከል አንደኛው መሆኑን ህብረቱ በመረጃው አመልክቷል። ህብረቱ እ.አ.አ 2024 የትምህርት ዓመት ብሎ በመሰየም የሰጠው ስትራቴጂካዊ ትኩረት የዚሁ ማሳያ ነው። የፓን አፍሪካ ኮንፍረንሱ የመምህራን ትምህርት የአፍሪካ የልማት አጀንዳ አበይት ትኩረት መሆኑ በግልጽ ታይቶበታል። የመምህራንን እጥረትን መቀነስ ብዙ መምህራንን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን ስልጠና ጥራት ያለው፣ ነባራዊ እውነታን ያገነዘበ እና መጻኢውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል። የአፍሪካ መንግስታት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች የመምህራን ትምህርት ስርዓትን መቀየር ትኩረታቸውን ባደረጉበት በአሁኑ ወቅት የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ የቀና የሚያደርገውን አፍሪካዊ ማን ያስተምራል? የሚለው ጥያቄ ተስፋ የሚሰጥ ምላሽ ያገኛል። የሰለጠነ፣ በክህሎት የዳበረ እና የኢኖሼሽን እውቀቱ ያደገ መምህር ለአፍሪካ ቀጣይ ጉዞ መቀናት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።
"ያሆዴ"- ከተናጠል ይልቅ በትብብር የመድመቅ ተምሳሌት
Sep 28, 2025 555
(በማሙሽ ጋረደው - ከኢዜአ ሆሳዕና ቅርንጫፍ) የሀዲያ የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓል የሆነው "ያሆዴ" የማህበራዊ መስተጋብር መሰረት ነው። ለማህበራዊ የህይወት አመራር ጉልህ አስተዋጾም ስላለውም በሀዲያዎች ዘንድ በየዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል፡፡ "ያሆዴ" ያለፈውን አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲስ ዘመን የሚቀበሉበት፤ የመጻኢ ተስፋ ብስራትና የልምላሜ ምልክትም ጭምር ተደርጎም ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በዓሉ ሲቀርብ የሀዲያ ተወላጆችና የበዓሉ ተሳታፊዎች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ከያሉበት ወደአካባቢው በመምጣት ይሰባሰባሉ፡፡ በዘንድሮ የያሆዴ በዓልም የሀድያ ተወላጆች የተለያዩ ማህራዊና ባህላዊ ክዋኔዎችን ለመከወን እንዲመች ታስቦ በተዘጋጀ ስፍራ (ነፈራ) ተሰባስበው በዓሉን በድምቀት አክብረውታል፡፡ በበዓሉ አከባበር ያለፈው ዓመት ስኬትም ይገመገማል፤ በአዲሱ ዓመትም የተሻለ ተሰርቶ ስኬት እንዲመዘገብ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ይካሄዳል። ሊተገበር የሚችል ዕቅድም ይታቀዳል፡፡ በግልና በቤተሰብ የመጡ ስኬቶች በጋራ በመሆን ይገመገማሉ። የበረቱና ውጤት ያስመዘገቡም እንዲበረታቱ ይደረጋል። ለዚህም ነው "ያሆዴ" የማህበራዊ መስተጋብር መሰረት ነው የሚባለው። ሰዎች እንዲሰሩና ስኬት እንዲያስመዘግቡ የሚያበረታታ እሴት አለው። የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፋን ቦጋለ እንደሚሉት የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል "ያሆዴ" ከተናጠል ይልቅ በትብብር የመድመቅ ተምሳሌት ነው፡፡ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ የበዓሉ መቃረብን የሚያበስሩት ታዳጊ ልጆች ናቸው። ልጆቹ የዋሽንት (ገምባቡያ) ድምጽ ማሰማት ከጀመሩ በጉጉት የሚጠበቀውን የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል መድረሱ ምልክት ነው። በዓሉ ሀድያዎች አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበት ወቅት ነው። በዓሉ የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት በመሆኑም የተለየ ትርጉምና ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ በዓሉ ሲከበር በተለያዩ ምክንያቶች ተራርቀው የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት ከያሉበት ይሰባሰባሉ። በዓሉ በአማረ መልኩ እንዲከበርም ሁሉም የቤተሰብ አባላት የየራሳቸው የሥራ ድርሻቸውን ያከናውናሉ። አባውራዎች ለበዓሉ ሠንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ በቱታ ወይም በቅርጫ ቡድናቸው አማካኝነት እየቆጠቡ ይቆያሉ። እንዲሁም ለእንስሳት የሚሆን የግጦሽ ሳር የሚያበቅል ቦታ ከልለው ያዘጋጃሉ፡፡ ይህ የሚሆነበት ምክንያት ደግሞ በዓሉ በሚከበርበት ሰሞን የሰው ልጅ ይቅርና እንስሳትም መጥገብ አለባቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ እማውራዎች ከበዓሉ ሦስትና አራት ወራት አስቀድመው እንሰት በመፋቅ ቆጮና ቡላ ያዘጋጃሉ። በተጨማሪም ከአካባቢው እናቶች በጋራ በመሆን (ዊጆ) የተሰኘ የቅቤ እቁብ በመግባት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ማጠራቀም ይጀምራሉ፡፡ ከእዚህ በተጨማሪ ለአተካናና ለሥጋ መብያ ናቀሮ ወይም ዳጣን እንዲሁም የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት ድርሻ የእናቶች ነው፡፡ ለበዓሉ የቤት ውስጥና የውጭ ግርግዳን በቀለምና በተለያዩ ጌጣጌጦች የማስዋብ ሃላፊነት ደግሞ የልጃገረዶች ነው። ወጣት ወንዶች ከነሀሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚያሳዩዋቸውን ግንድ በመቁረጥ ለምግብ ማብስያ እንዲውል ፈልጠው ያዘጋጃሉ። በሀዲያዎች አጠራር ለችቦ የሚሆን እንጨት ወይም ጦምቦራ ከጫካ ለቅመው አስረው እንዲደርቅም ያስቀምጣሉ፡፡ ለበዓሉ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት በዓሉ በስኬትና በድምቀት እንዲከበር ጠቀሜታው የጎላ ነው። በዚህም ያሆዴ ከተናጠል ይልቅ ትብብርን የሚያጠናክር ነው ማለት ይቻላል። እሴቱ በትብብር መድመቅ እንደሚቻልም የሚያሳይ ነው። ይህን ሀሳብ የሚጋሩት አቶ መስፍን የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል በምንም ሁኔታ መነጣጠል የማይቻል ትስስርን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ይገልጻሉ። ሀገራዊ አንድነትና አብሮነትን የሚያጠናክር ዘመናትን የተሻገረና ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ባህላዊ እሴት ያለው መሆኑንም ይናገራሉ። በዓሉ ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀረው አባውራዎች በቅርጫ ማህበራቸው አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ የእርድ በሬ ይገዛሉ። በዚህ ወቅት ገንዘብ ማዋጣት ያልቻሉ የቅርጫ አባላት እህል በሚደርስበት ወቅት ለመክፈል ተስማምተው በሬውን በዱቤ እንዲገዙ ይደረጋል፡፡ ይሄም የሚሆነው በያሆዴ በዓል አንዱ ሲበላ ሌላው ተመልካች መሆን ስለሌለበት ነው። እርስ በርስ መጨካከን እንዳይኖርና በዓሉን በአብሮነት ሁሉም ተደስቶ ማክበር እንዲችል ለማድረግ ነው። ከበዓሉ ዕለት በፊት ያለው የመጨረሻ ገበያም የእብድ ገበያ (መቻዕል ሜራ) የሚል ስያሜ አለው። ይሄ ሥያሜ ያገኘው በዓሉ ሲቃረብ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚፈጠረውን ውጥረት ታሳቢ በማድርግ ነው፡፡ በዚህ የእብድ ገበያ ህብረተሰቡ መገበያየት የሚጀምረው ጠዋት ማለዳ ጀምር ሲሆን የግብይት ሂደቱ የሚጠናቀቀው ደግሞ እኩለ ቀን ላይ ነው፡፡ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለመግዛትና የያሆዴ በዓል ከተከበረ በኋላ ለአንድ ወር ገበያ ስለማይቆም ይህን ታሳቢ ያደረገ ግብይት ለመፈጸም የግብይት ሂደቱ ጥድፊያ የበዛበት ሆኖ ይታያል። ያሆዴ በዓል መከበር የሚጀምረው በአተካን ሂሞ ወይም በአተካና ምሽት ሲሆን ይህም ከበዓሉ አንድ ቀን በፊት ያለው ምሽት ነው። ስያሜውን ያገኘው "አተካና" ከተሰኘና በያሆዴዎች ዘንድ ለክብር እንግዳ እና በዘመን መለወጫ ከሚዘጋጅ ምግብ ነው። አተካና ከወተት፣ ከአይብ፣ ከቡላ፣ ከቅቤና ከሌሎች የቅመማ ቅመም ውጤቶች የሚዘጋጅ ምግብ ሲሆን በጣም ጣፋጭና የምግበ ፍላጎትን የሚጨምር ምግብ ነው፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ይሄንን የተለየ ምግብ ተሰባስቦ በአብሮነት በመመገብ በደመቀ መልኩ በዓሉን ማክበር ይጀምራል፡፡ የአካባቢው አባቶች በወጣቶች የተዘጋጀ የማቀጣጠያ እንጨት (ሳቴ) ይዘው ትልቅ በሚባሉ አባውራ ቤት ደጃፍ ወደ ተዘጋጀው የችቦ ደመራ (ጦምቦራ) ቦታ ይመጣሉ:: የሀገር ሽማግሌች አዲሱ ዓመት የብርሃን ዓመት እንዲሆን፤ ለሀገርና ለህዝቦቿ ሰላም እንዲጸና፤ አብሮነት እንዲጠናከር፣ ሰላምና ፍቅር እንዲነግስ ፈጣሪያቸውን ከተማጸኑ በኋላ ችቦውን በእሳት ይለኩሳሉ፡፡ ችቦው ከተለኮሰ በኋላ የአካባቢው ወጣቶች ተሰባስበው ያሆዴ …ያሆዴ! …ያሆዴ! በማለት እየጨፈሩ ያነጋሉ ይጨፍራሉ:: በሀድያዎች ዘንድ "ያሆ" ማለት የአዲስ ዓመት መግባትን ተከትሎ ማብሰሪያ ጭፈራ ሲሆን "ኤዴ" ማለት ደግሞ አገናኝ ማለት ነው፡፡ በያሆዴ በዓል የእርድ ሥነ ስርዓት ለማከናወን ነዋሪዎች የሚሰበሰቡበት ስፍራ "ነፈራ" የሚል ስያሜ አለው። የተለያዩ ማህራዊና ባህላዊ ክዋኔዎችን ለመከወን እንዲመች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ሰፋ ያለ ቦታ ሰሆን በተለያዩ የጥላ ዛፎች የተዋበና ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀም ነው። በእለቱ ለእርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኋላ የባህል ሽማግሌዎች የበሬውን ሻኛ በሰርዶ ሳር ለጋ ቅቤ ይቀባሉ፤ ወተትም ያፋሱበታል፡፡ ይህ ባህላዊ ሥነ ስርዓት ጋቢማ የሚባል ሲሆን (የመልካም ምኞት) መግለጫ ስነ ስርዓትም ነው፡፡ ይህም ሥነስርአት በሚከናወንበት ወቅትም "ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሀገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን " እያሉ በአባቶች ምርቃት ከተካሄደ በኋላ የእርድ ስነ ስርዓት ይከናወናል፡፡ የእርድ ሥነ ስርዓቱ የተከናወነበት ቤት እማወራ አስቀድመው ባደረጉት ዝግጅት መሰረት ቅቤ፤ (ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ) እንዲሁም ከታረደው የበሬ ሥጋ አርዚ ማራ (ቅምሻ) ይወሰድና ክትፎ ከተዘጋጀ በኋላ በጋራ እየበሉ እየተጫወቱ ይውላሉ፡፡ በዚህም በቅርጫ ሥጋው ላይ ከሚሳተፉት የቤተሰብ አባላት ውጪ በአካባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞችም ጭምር አብረው በመብላት በመጠጣት በዓሉን በአንድነት ያሳልፋሉ፡፡ ቀሪውን የቅርጫ ሥጋም አባላቱ ተከፋፍለው ወደ እየቤታቸው ይወስዱታል፡፡ በዓሉ አብሮ የመብላት፣ የመጠጣት፣ የመጠያየቅ፣ ችግርንና ግጭትን በጋራ ተወያይቶ የመፍታት፣ መፈቃቀርና መተሳሰብን የሚፈጥር፣ አቅመ ደካሞችና የተቸገሩ የሚረዱበት የአብሮነት መገለጫ በመሆኑ በተለየ መልኩ ይከበራል፡ ከእርድ ሥርዓቱ በኋላ በማግስቱ ልጆች አደይ አበባ (ዘራሮ) ይዘው ወደ ወላጆቻቸው እየጨፈሩ ይመጣሉ። የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባላሉ። ከስጋውም፣ ከቦርዴውም፣ ከአተካናውም እንዲመገቡ ያደረጋል። ይህ ስነ ስርዓትም ሚክራ ይባላል። በያሆዴ የዘመን መለወጫ በዓል ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ሥጋና አደይ አበባ ጭምር ይዘው ይሄዳሉ። በዓሉ ያላገቡ ወጣቶች የሚተጫጩበትና ለአዲስ ህይወት ጅማሬ የሚያበስሩበት በመሆኑን የተለየ ድባብ አለው፡፡ የያሆዴ በዓል ካሉት እሴቶች አንዱ የህብረተሰቡን የአካባቢ ልማት ተሳትፎ ማበረታታት ተጠቃሽ መሆኑን የገለጹት አቶ መስፍን ዕሴቱ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው ለማህበረሰብ ጥቅም እንዲውሉ ጭምር አቅም እየሆነ መምጣቱን ነው የሚናገሩት።ይህ የአብሮነት ማስተሳሰሪያና የማህበራዊ መስተጋብር መጋመጃ የሆነው በዓል እሴቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል መስራት ይገባል። እሳቸው እንዳሉት በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ወካይ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማስቻል እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም መምሪያው ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ዕሴቱን የመሰነድና ምርምሮች ማካሄድን ጨምሮ እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።
80ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ተሳትፎ
Sep 27, 2025 674
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ግዙፉና ጉምቱው የዓለም የብዝሃወገን ዲፕሎማሲ መድረክ ነው። 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ከጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ “ደህናነት በአብሮነት፤ 80 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሰላም፣ ለልማት እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። የጠቅላላ ጉባኤው አካል የሆነ ከፍተኛ የምክክር እና ክርክር መድረክ ከመስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተደረገ ነው። ከሰላም እስከ አየር ንብረት ለውጥ፣ ከዘላቂ ልማት እስከ ዲጂታል አካታችነት፣ ከሰብዓዊነት እስከ የዓለም የኢኮኖሚ አወቃቀር፣ በዓለም መድረክ ፍትሐዊ ውክልናን ከማግኘት እስከ ዓለም በቀጣይ ምን ትሆን? ድረስ በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ውይይቶችና ክርክሮች በማድረግ ለወደፊቱ ይበጃሉ የተባሉ ሀሳቦች በመነሳት ላይ ይገኛሉ። በጉባኤው ይፋዊ መክፈቻ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባደረጉት ንግግር ዓለም በተለያዩ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች፣ ድህነት፣ ረሃብ፣ ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣የኢኮኖሚ ቀውስ እየተፈተነች ባለበት ወቅት የሚከበረው የተመድ 80ኛ ዓመት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የተመድ ሥርዓትንና መዋቅር 21ኛው ክፍለ ዘመን በሚመጥን ልክ መለወጥ እንደሚገባ አመልክተዋል። ዋና ፀሐፊው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምርጫውን ሰላም፣ ፍትህ ዘላቂ ልማት እና ሰብአዊ ክብር ሊያደርግ እንደሚገባና ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነት እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል። በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ተሳትፎ እያደረገ ነው። ልዑካን ቡድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትን አካቷል። ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ የራሷን ብሔራዊ ጥቅሞች እና የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ እንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ከዋናው ጉባዔ ተሳትፎ በተጨማሪ በርካታ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን የጎንዮሽ የውይይት መድረኮች ላይም ኢትዮጵያ የራሷን ብሄራዊ ጥቅሞች ቅድሚያ እየሰጠች እንደምትሳተፍም አመልክዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል። ዋና ፀሐፊው ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠናቃ በመመረቋ ፣ የአየር ንብረት ጉባዔ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በማስተናገድ ላስመዘገበችው ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው እና በሌሎች ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዝዳንት አናሌና ባርቦክ ጋር ተወያይተዋል። ሁለቱ መሪዎች በወቅታዊ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች እና በባለብዙ ወገን ግንኙነት ላይ እያሳደረ ስለሚገኘው ተጽዕኖ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ የባለብዙ ወገን ግንኙነት እና የጋራ ደኀንነት መርሆዎችን ለማስጠበቅ የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በቅርቡ የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተመድ ዘላቂ ልማት ግቦችን ከማሳካት ረገድ በተለይም ግብ ሰባትን ለማሳካት ግድቡ ንጹሃ የኃይል አቅርቦት ከማሳደግ አኳያ ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት አናሌና ባርቦክ በበኩላቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መርሆዎችን ማክበር እና መጠበቅ ለዓለም ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ ልማት፣ ቀጣናዊ ሰላም እና ደኀንነትን ጨምሮ በተለያዩ ቀጣናዊ የትኩረት መስኮች ላይም መክረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ ይገኛል። አምባሳደር ሃደራ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መንደይ ሲማያ ኩምባ የኢትዮጵያ እና ሱዳን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ግፍንኙነት ማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የትብብር መድረኮች የተባበረ አቋም እንዲኖራቸው ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። ከሞዛምቢክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማኑኤላ ዶስ ሳንቶስ ሉቃስ ጋርም ተወያይተዋል። ሽብርተኝነትን መከላለከል፣ አቪዬሽን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል። አምባሳደሩ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሥልጣን አምባሳደር ጆናታን ፕራት ጋር በሀገራቱ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ተስማምተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ከአውሮፓ ከአውሮፓ ሕብረት የውስጥ ጉዳይ እና የፍልሰት ኮሚሽነር ማግነስ ብሩነር ጋርም የተወያዩ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች ዓለም አቀፍ ፈተና በሆኑ ከፍልሰት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። አምባሳደሩ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቦት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ በሚያጠናክሩ ዕድሎች እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። አምባሳደር ሃደራ አበራ ከኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር በሁለትዮሽ ትብብር ዙሪያ መክረዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ከአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄሁን ቤራሞቭ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ኢትዮጵያና አዘርባጃን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን በመጥቀስ ሁለቱ አገራት በተለይ በኢኮኖሚ ዘርፎች ይበልጥ ተቀናጅተው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልፀዋል። ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ሀገራቱ በንግድ፣ በኢንቬስትመንት፣ በቱሪዝም በግብርናና በትምህርት ዘርፎች እንዲሁም በባለብዙ ወገን መድረክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል። ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ባሉ የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ እየሳተፈች ይገኛል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያ የአፍሪካን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ማስፋት አላማ ያደረገው “Mission 300” ኢኒሼቲቭ ተቀላቅላለች። በዓለም ባንክ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚመራው ኢኒሼቲቭ እ.አ.አ በ2030 በአፍሪካ የሚገኙ 300 ሚሊዮን ዜጎችን በኤሌክትሪክ ኃይል የማስተሳሰር ውጥን ያለው ነው። ፕሮጀክቱ የአፍሪካ መንግስታት፣ የግሉ ዘርፍ እና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ ሲሆን በአፍሪካ አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ፣ አካታች እና ተመጣጣኝ የኢነርጂ አቅርቦትን ተደራሽ በማድረግ የኢኮኖሚ እድገት እና ቀጣናዊ ትስስርን የማጠናከር አላማንም አንግቧል። ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም እና ቀጣናዊ የኃይል ትስስሯን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንጹህ ኢነርጂ ሽግግር ውስጥ ያላትን የመሪነት ሚና እንደሚያሳድግና አፍሪካ ከኢነርጂ ድህነት የማላቀቅ እና ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ ትልም ለማሳካት እንደሚያግዝም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ በአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ አፍሪካ) ኮሚቴ አባል የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ የጤናን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥ የሀብት ማሰባሰብ እና ፈጠራ የተሞላበት የፋይናንስ ግኝት እንደምትከተል አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጠቅላላ ጉባኤው ብሔራዊ ጥቅሞች እና የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ ማድረጓን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገልጸዋል። በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያን ልዑክ የመሩት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የጉባኤው አካል በሆነው ከፍተኛ የምክክር እና ክርክር መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በመልክዓ ምድራዊ ሁኔታዎች ምክንያት የትኛውም ሀገር የእድገት፣ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ዕድሎች ዝግ መሆን የለበትም ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር በመሆን በቀይ ባሕር እና በሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ሀገሮች እኩል ልማት እና ደኀንነትን ማረጋገጥ ወደሚያስችል ሁለንተናዊ አሠራር እንዲዘረጋ ትሠራለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ይህንን ሕጋዊ ፖሊሲዋን ለማሳካትም የዲፕሎማሲያዊ እና ሰላማዊ አማራጮችን እንደምትከተል አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንቱ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትን ለማሻሻል አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። በማሻሻያውም ለአፍሪካ ውክልና በምክር ቤቱ በሁለቱም በኩል ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበው፤ ለአፍሪካ የረጅም ጊዜ የፍትሕ መሻት ጥያቄ አቋራጭ ወይም ግማሽ መፍትሔ እንደሌለ አስገንዝበዋል። ከታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘም፤ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ በፈረንጆቹ ጥቅምት 2024 ወደ ተግባር መግባቱን እና የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ወደ መቋቋም ደረጃ መቃረቡን አስረድተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ መመረቁ፤ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ንጹህ የኃይል ምንጭ እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል። ግድቡ በከባድ የውኃ እጥረት ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖቻችን ንጹህ ውኃ ለማቅረብ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና አጠቃላይ ልማትን እውን ለማድረግ አቅማችንን ያሳድጋል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ግድቡ ለሰፋፊ ክልላዊ ትስስር ተስፋን የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ 1945 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሲመሰረት መስራች አባል ከነበሩት ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ይህም ኢትዮጵያ የባለብዝሃ ወገን እና ዓለም አቀፍ ትብብር ያላትን የማይናወጥ አቋም እና የጸና ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ጉባኤ ሰላም፣ ደህንነት፣ ዘላቂ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በዓለም አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ያራሷ እና የአፍሪካን ድምጽ በማሰማት የነቃ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 746
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 1587
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 2370
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 2545
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 152
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 6032
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 4510
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 6020
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል። በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል። የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
መጣጥፍ
ኢሬቻ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ማንሰራራት!
Oct 3, 2025 537
ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ሰዎች በክረምት ወቅት ከሚከሰት መለያየትና መራራቅ በኋላ ዳግም የሚገናኙበት፣ በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት ዕለት ነው። ስለ ሰላምና አንድነት የሚዘመርበት፣ ስለመጪው ጊዜ መልካም ምኞት የሚገለጥበት፣ ሁሉን ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት የአብሮነት በዓል ነው። ኢሬቻ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለው ጥብቅ ቁርኝት የሚገለጽበት የገዳ ስርዓት አንዱ አካል ነው፡፡ የኢሬቻ እሴቶች ጠንካራ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ያላት ሀገር ለመገንባት የሚያግዙ ናቸው። አንድነት፣ ወንድማማችነት፣ አብሮነት፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ዕርቅ እና ሌሎችም ተጠቃሽ የመልካም እሴቶች መገለጫ ነው። በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የገዳ ስርዓት አንዱ እሴት ኢሬቻ ሲሆን፤ ለሀገር ማንሠራራትና ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ መሠረት ይሆናል፡፡ ኢሬቻ አብሮነት የሚጸናበት፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት ይበልጥ የሚጎላበት፣ አሰባሳቢ ትርክት የሚጎለብትበት፣ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት ማሰሪያ ከፍ ያለ በዓል ነው፡፡ ኢሬቻ በጋራ የሚያከብሩትና የዓለም ቱሪስቶች የሚታደሙበት ሲሆን፤ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትና የኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ጎልቶ የሚታይበት ነው፡፡ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል አከባበር ሀገራዊ ማንሰራራት በተግባር የተረጋገጠበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተመርቆ ዓለም የኢትዮጵያን መቻል በተግባር ባየበትና ሌሎች ለሀገር ማንሰራራት ዕውን መሆን መሠረት የሚጥሉ ትላልቅ ሀገራዊ ኘሮጀክቶች ይፋ በተደረጉበት ማግስት መሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡ በዓሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመላው ኢትዮጵያዊያንን ሕብረት የሚንጸባረቅበት ሆኖ በተለያዩ አከባቢዎች በድምቀት እየተከበረም ይገኛል፡፡ በልመናው፣ በምርቃቱ፣ በምስጋናው ሁሉ ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!) የሚሉ ድምፆች ይስተጋባሉ። Hayyee! Hayyee! Hayyee! Hayyee! Hayyee! Hayyee! Waaqa Uumaa, Waaqa Uumamaa ፍጥረትን የፈጠርክ ፈጣሪ Gurraacha garaa garbaa የእውነትና የሰላም አምላክ! Dogoggora nu oolchi ከስህተትና ከክፉ ነገሮች ሁሉ ጠብቀን! Dacheef nagaa kenni ለምድራችን ሰላም ስጥ! Laggeenif nagaa kenni ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! Olota keenyaaf nagaa kenni ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! . . . Loowan keenyaaf nagaa kenni " ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ!" በማለት ይመረቃል። ሕዝቡም ይሁንልን ይደረግልን ሲል "አሜን! አሜን! አሜን!” ይላል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ እሑድ መስከረም 25 ቀን በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ " ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት " በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል። የክራምት ወራት እንዳበቃ የሚከበረው "ኢሬቻ መልካ" Irreecha Birraa (በውኃ ዳርቻ የሚከበር) ሲሆን፤ በዓመቱ አጋማሽ ላይ "ኢሬቻ ቱሉ" Irreecha Arfaasaa ደግሞ በተራራማ ቦታ ይከበራል። ኢሬቻ መልካ የሚከበረው በመስከረም ወር ከመስቀል በዓል በኋላ ነው። የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመምጣቱ ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ይህ ከማህበራዊ መስተጋብር አኳያም ሰዎች የሚሰባሰቡበትና የሚገናኙበት ነው። ከባዱ የክረምት ወቅት አልፎ ብርሃን (ብራ) ስለደረሰ ለዚያ ምልክት ይሆን ዘንድ የለመለመ እርጥብ ሣር ይዘው ወደ ወንዝ በመውረድ ንጹህ ውሃ ውስጥ እየነከሩና እየረጩ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት ነው፡፡ ኢሬቻ ቱሉ የሚከበረው የበጋው ወራት አልፎ የበልግ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ነው። በዚህም ፈጣሪ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፤ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ለፈጣሪ ተማጽኖ የሚቀርብበት ነው። "ይህን ተራራ የፈጠርክ ፈጣሪ ወቅቱን የሰላም አድርግልን፣ የሰላም ዝናብ አዝንብልን፣ ጎርፍን ያዝልን፣ የተዘራው ፍሬ እንዲያፈራ እንለምንሃለን" እያለ በኢሬቻ ቱሉ ላይ ፈጣሪውን ይለምናል፡፡ በኢሬቻ በዓል የፈጣሪ ምህረት፣ ዕርቅ፣ አብሮነት እና በዓሉ የሰላም በዓል እንዲሆን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ኦሮሞ ፈጣሪውን ይጠይቃል፤ ይማፀናል፤ ለተደረገለትም ነገር ሁሉ ያመሰግናል። ኢሬቻ ምድርን እና ሰማይን ለፈጠረው "ዋቃ" "Waaqa" ምስጋናውን ለማድረስ የሚከበር ሲሆን፤ በዕድሜ ልዩነት ሳይገደብ ለዘመናት በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር ሲከበር ቆይቷል። በዝናባማው የክረምት ወቅት በጅረቶችና ወንዞች መሙላት ምክንያት ተራርቆ የቆየው ዘመድ አዝማድ በኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ሥፍራ ይገናኛል፤ ይጠያየቃል፤ ናፍቆቱንም ይወጣል። አባቶች ክረምት በለሊት ይመሰላል ይላሉ። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ደግሞ ውበት ነው፤ መታያና መድመቂያም ነው። ለዚህ ነው በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ሁሉም ውብ የባህል ልብሱን በመልበስ በደስታ በዓሉን ለማክበር የሚመጣው። ሕዝቡ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ሥፍራ የሚሄደው በተናጠል ሳይሆን በሕብረትና በአንድነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢሬቻ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው የሚባለው። ኢሬቻ የወንድማማችነትና የአንድነት አርማ ሲሆን፤ የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ፣ የህብረ ብሔራዊ አብሮነት ማስተሳሰሪያም ጭምር ነው፡፡ በኢሬቻ ልዩነት የለም፤ ፀብ የለም፤ ክፋት የለም፤ ይልቁንም ምስጋና ይበዛል፤ ፍቅር ይሰፍናል፤ አብሮነት ያብባል፣ አንድነት ይጸናል። ኢሬቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሰላምና የአብሮነት ምልክት ነው። የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚወጣው ታዳሚም እንደ እርጥብ ሣር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ የበዓሉን ስነ-ስርዓት ያከናውናል። ይህን የሚያደርገውም "ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያፀደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመሰግንሃለን" በማለት የፈጣሪን መልካምነት ለማሳየት ነው። በሌላ በኩል እርጥብ ሣር የልምላሜ ምልክት በመሆኑ የመልካም ምኞት መግለጫም ስለሆነም ነው በኢሬቻ በዓል እርጥብ ሣር የሚያዘው። የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከሚከወኑ ሥርዓቶች መካከል ሴቶች ሲቄ፣ እርጥብ ሣር እንዲሁም ጮጮ ይዘው ከፊት ሲመሩ አባ ገዳዎች ደግሞ ቦኩ፣ አለንጌ እና ሌሎችንም በበዓሉ ሥርዓት የሚፈቀዱትን ሁሉ በመያዝ ወደ ሥርዓቱ አከባበር እንዲህ እያሉ ያመራሉ። ኦ ያ መሬሆ…………………መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ኡማ ሁንዳ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ለፋ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ መልካ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ እያሉ ያመራሉ። የሁሉ ፈጣሪ፣ ምድርን የፈጠርክ፣ ወንዙን የፈጠርክ . . . ምስጋና ለአንተ ይሁን በማለት ያመሰግናሉ፤ ይዘምራሉ። የኢሬቻ በዓል ሥነ-ሥርዓት በአባመልካ ተከፍቶ በአባ ገዳዎች ተመርቆ ከተጀመረ በኋላ መላው ሕዝብ በአንድነት ሥርዓቱን ያከናውናል። ኢሬቻ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው፣ የሁሉም ማጌጫ፣ መድመቂያ እና የአብሮነት መገለጫ ነው። የበዓሉ ታዳሚዎች ከዋዜማው ጀምሮ በሆረ ፊንፊኔና በሆረ ሀርሰዲ በመሰባሰብ፤ የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችን በማዜምና ምስጋና በማቅረብ አድረው በነጋታው ዋናውን የምስጋና በዓልም ያከናውናሉ፡፡ የበዓሉ ታዳሚዎች የደስታና የምስጋና ምልክት የሆነውን ባህላዊ ነጫጭ ልብስ ለብሰው፣ ባህልን የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ሁነቶችን በመከወን ልዩ ልዩ ዜማዎችን በማዜም፣ ግጥሞችን በማቅረብ፣ ወደ ፈጣሪ በመጸለይ እና ምስጋና በማቅረብ ሥርዓቱን ያከናውናሉ፡፡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች የሚታወቁበትን ባህላዊ ልብስ በመልበስ በቋንቋቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን በአንድነት ያከብራሉ። ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በርካታ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ከማቀራረብና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ከመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጾኦ ያለው ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዲ በዓላት ላይ ለመታደም ወደ አገር ቤት ይመጣሉ። የውጭ አገራት ጎብኚዎችና እንግዶችም በትዕይንቱ ይታደማሉ። ለአብነትም ባሳለፍነው ዓመት ከኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ አገር የመጡ ልዑካን በበዓሉ ላይ በመታደም የበዓሉን ትልቅነት እና የኢትዮጵያውያን የአብሮነት መገለጫ መሆኑን መመስከራቸው ይታወሳል። አያሌ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ያሉት ይህ የምስጋና በዓል እውነተኛ ወንድማማችነት የሚታይበት፣ አንድነት የሚጎላበት፣ አብሮነት የሚጠናከርበት፣ ሰላምና ተስፋ የሚታወጅበት አገራዊ እሴት ነው። በባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች፣ ባህላዊ ምግቦችና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት ኢሬቻና መሰል የአደባባይ በዓላትን እንደመልካም የገበያ አማራጭ ይጠቀሙባቸዋል። የኢሬቻ በዓል ለቱሪዝም ፍሰት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው፤ በርካታ የባህር ማዶ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የሚታደሙበት በዓል ነው፡፡ በዓሉ ትልቅ የቱሪዝም መስህብ ሲሆን፤ ዘርፉን በማጠናከር እና ብሔራዊ ልማትን በማሳደግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከፍ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚናንም የሚጫወት ነው፡፡ ኢሬቻ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች በስፋት የሚተዋወቁበት ታላቅ መድረክ ነው። በእርግጥም ይህንን ውብ የጋራ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል። ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነውና በምስጋና እንደጀመርን በምስጋናና ምርቃት እንሰነባበት። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ከመጥፎ ነገር ጠብቀን! ንጹህ ዝናብ አዝንብልን! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ!
በትግራይ ክልል የመስቀል በዓል አከባበር
Sep 27, 2025 650
የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በልዩ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓሉ እንደየአካባቢው ባህላዊና ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። በትግራይ ክልልም የመስቀል በዓል እንደሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሁሉ በናፍቆት ከሚጠበቁና በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት ተርታ ይመደባል። ለዚህም ሲባል የተለያዩ ዝግጅቶች ከበዓሉ ዋዜማ በፊት እንዲጠናቀቁ የሚደረግ ሲሆን፥ በተለይ በየዓመቱ መስከረም 16 እና 17 ዘመድ አዝማድ ተጠራርተው የሚገናኙበት የፍቅርና የአብሮነት በዓል ሆኖ ይከበራል። የክርስቶስ ግማደ መስቀል በንግስት ኢሌኒ አማካኝነት መገኘቱን በማሰብ በየዓመቱ መስከረም አጋማሽ ላይ የሚከበረው የመስቀል በዓል የመስቀል ኃያልነት፣ እውነት በተደበቀበት ለዘላለም እንደማይቀርና ፍቅርን አብዝቶ የሚሰበክበት ከዚህ ባለፈም እርቅ የሚወርድበትና ደስታ የሚገለጽበት አጋጣሚ መሆኑም ይገለጻል። በትግራይ የበዓሉን ታላቅነትና ክብር ለማድመቅ ምእመናን ጽዱ ልብስ ለብሰውና የተለያዩ ዝማሬዎችን በማሰማት ደመራ ወደሚደመርበት ሥፍራ ችቦ ይዘው በመሄድ ደምራውን በማቀጣጠል የሚያከበሩት ሲሆን፣ በእለቱ የቤት እንስሳት ጭምር ቀንዳቸውና ጀርባቸው ላይ ቅቤ ተቀብተው እንዲያርፉ ይደረጋል። ዘመድ አዝማድ፣ ጎረቤታሞች፣ አብሮ አደጎችና የበዓሉ ታዳሚ እንግዶችም ተሰባስበው ማለዳ ላይ ገንፎ በማዘጋጀት ይመገባሉ። የእንስሳት እርድ በማከናወን ባህላዊ መጠጦችን በማዘጋጀት በዓሉን የፍቅር፣ የመሰባሰብ፣ የአንድነትና ተካፍሎ የመብላት በዓል መሆኑን በተግባር የሚያሳይበት ክስተት ሆኖ ያልፋል። "ዓኾይ ዓኾኾይ" የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ በማለትም ችቦ ተሎኮሶ በየቤቱ በመዞር የምረቃ እና ለሚቀጥለው ዓመትም በሰላምና ደስታ እንዲሁም እድሜና ጤናን በመመኘት ይከወናል። የአደባባይ በዓል የሆነው የመስቀል በዓል በዝማሬ፣ በሆታና እልልታ የሚገለጽ ሲሆን፤ ወርሃ መስከረም እሸት አሽቶ አበቦች አብበውና ምድር ልዩ ልምላሜን ተላብሶ የሚታይ በመሆኑ ልክ በታሪኩ እንደሰፈረው የሰላም፣ የእውነትና የአንድነት በዓል መሆኑን በተግባር የሚታይበት ነው።