ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዳሴ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዳሴ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 2 ለ 1 በመርታት ሻምፒዮን ሆኗል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊ ጌታቸው እና አዲሱ አቱላ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ሲያሳርፉ፤ የመቻልን ብቸኛ ግብ ቻርልስ ሙሴጌ አስቆጥሯል።


 

በውድድሩ መቻል የብር እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም