ቀጥታ፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን በክረምት ወራት ለተተከሉ ችግኞች የሚደረገው እንክብካቤ ቀጥሏል

ጊምቢ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡-በምዕራብ ወለጋ ዞን በክረምት ወራት ለተተከሉ ችግኞች የሚደረገው እንክብካቤ መቀጠሉን የዞኑ የግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የምዕራብ ወለጋ ዞን የግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፈይሳ ሀምቢሳ እንደገለጹት በዞኑ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል።


 

ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች ውጤታማ እንዲሆኑ በዞኑ ነዋሪዎች የችግኝ እንክብካቤ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ወቅትም በተለይም ባለፈው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ በዞኑ ባለፉት ዓመታት በተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች አካባቢውን አረንጓዴ ከማልበስ ባለፈ ለግብርና ስራም እገዛ እያደረጉ መሆኑ ገልጸዋል።

በችግኝ እንክብካቤው እየተሳተፉ ከሚገኙ መካከል ወይዘሮ ለሊሴ ብርሃኑ፣ በክረምት ወራት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን እየተንከባከቡ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በአካባቢያቸው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን በመገንዘባቸው አሁንም በእንክብካቤው መጠንከራቸውን ጠቅሰዋል።

አቶ ገረመው ነገራ በበኩላቸው የተተከሉ ችግኞች ለውጤት እንዲበቁ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።


 

ሁሉም በየአካባቢው ችግኞችን በመንከባከብ ለውጤት ማብቃት አለበት ያሉት ደግሞ አቶ ነጻነት አበበ ሲሆኑ ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች የተለያየ ጥቅም እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም