ቀጥታ፡

በድሬዳዋ ከተማ ሊደረጉ የነበሩ የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታዎች ወደ ሃዋሳ ተዘዋውረዋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፦ በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ ሊደረጉ የነበሩ የመክፈቻ ጨዋታዎች ወደ ሃዋሳ መዘዋወራቸውን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

የሊጉ የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ውድድር በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ መገለጹ ይታወቃል። 

ይሁንና በአሁኑ ወቅት ድሬዳዋ ከተማ ውድድሩን ለማስተናገድ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ በመሆኑና ዝግጁ አለመሆኑን በመግለጹ ድሬዳዋ ላይ ሊደረጉ የነበሩ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች ወደ ሃዋሳ ከተማ መዞሩን ማህበሩ ገልጿል።

የተስተካከለውን መርሃ ግብር በቅርቡ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል።

20 ክለቦች በሁለት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም