ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጊኒ ቢሳውን አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጊኒ ቢሳው ጋር ባደረገችው ጨዋታ 1 ለ 0 አሸንፋለች።

በሩዋንዳ አማሆሮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራምኬል ጀምስ በ27ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል።

በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ በማጣሪያው ሁለተኛ ድሏን አስመዝግባለች። በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች።

ሽንፈት ያስተናገደችው ጊኒ ቢሳው በ10 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም