ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
Sep 18, 2026 123
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የክልሉን የቱሪዝም መስህቦች በጋራ ለማስተዋወቅ የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢዜአ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም እሸት ሽመልስ እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ ተፈራርመውታል። የኢዜአ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም እሸት ሽመልስ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፤ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጀምሮ ለዘርፉ የተሰጠውን ልዩ ትኩረትና ቦታ በመረዳት ወደ ሥራ የገባ ተቋም ነው። ኢትዮጵያ ያላትን በርካታ የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ለአፍሪካና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በርካታ የዴሞክራሲና የአስተዳደር ትምህርቶችን ሊሰጥ የሚችለውን የገዳ ስርዓት ለአብነት መጥቀስ እንደሚቻል አብራርተዋል። የኢዜአ ዋና ተልዕኮዎች ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እና የሀገርን በጎ ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህንም በ"ፐልስ ኦፍ አፍሪካ" (Pulse of Africa) ሚዲያ ለአፍሪካውያንና ለዓለም ማህበረሰብ እንደሚያስተዋውቁ ተናግረዋል። ይህ ስምምነትም እነዚህን ተልዕኮዎች በተግባር ለመወጣት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የሚያከናውናቸውን ሀገር ተሻጋሪ ሥራዎች በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ በበኩላቸው፤ አንጋፋውና ሰፊ ተደራሽነት ያለው ኢዜአ ከኮሚሽኑ ጋር መስራቱ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል። የቱሪዝም ዘርፉ ያለ ፕሮሞሽን እና የመረጃ ተደራሽነት ሊያድግ እንደማይችል ገልጸው፣ ከኢዜአ እና ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር የተደረገው አጋርነት የስራውን ውጤታማነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተናግረዋል። ሁለቱ ተቋማት የቱሪዝም አጀንዳዎችን በጋራ እንደሚያስፈጽሙና ቱሪዝምን የአፍሪካ ህዝቦችን ማስተሳሰሪያ መንገድ አድርገው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ራሱን የቻለ የኤግዚቢሽን ቦታ እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ከሚመጡ ጎብኚዎች ጋር ትስስር እንዲፈጠር ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ይጠናከራሉ
Sep 18, 2026 199
ሆሳዕና ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ያለፈውን በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሄዷል።   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ንጉሤ አስረስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት በመቀየር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ተግባራት ይጠናከራሉ። በተለይም በዘርፉ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአሠራር እና የድጋፍ ማዕቀፎች መዘርጋታቸውን ጠቁመዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራውን ለማበረታታትም ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ የተግባር ሥልጠና እንዲሰጡ መደረጉን ጠቅሰዋል። በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።   የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በበኩላቸው፤ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። በዚህም በግብርና፣ በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከ450 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ከ5 ሺህ 900 ሄክታር በላይ መሬት እና 600 የሚጠጉ ሼዶች ለኢንተርፕራይዞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል። ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት መዘጋጀቱን እና ቀደም ባሉት ዓመታት ሼዶች ወስደው ሀብት ያፈሩ አንቀሳቃሾችን ለማሸጋገር ግብ ተይዞ ወደ ትግበራ ምዕራፍ መገባቱንም ኃላፊው ገልጸዋል። የስልጤ ዞን የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ወርቅቾ፣ ዞኑ በሥራ ዕድል ፈጠራ ያሉ ጸጋዎችን ለይቶ በመጠቀም ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም ወጣቶችን በሥራ ዕድል ፈጠራው ተጠቃሚ ለማድረግ ከ1 ሺህ 350 ሄክታር በላይ መሬት እና ከ150 በላይ አዳዲስ ሼዶችን ገንብቶ ለማስረከብ ታቅዷል ብለዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።      
ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ በሚኖራት ሚና ላይ ያለው ዓለም አቀፍ መግባባት እያደገ መጥቷል
Sep 18, 2026 270
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ባላት ሚና ዓለም አቀፋዊ መግባባት እየተፈጠረበትና አጀንዳው ተቀባይነቱ እያደገ መምጣቱን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተመራማሪ ግዛቸው አስራት (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ፍላጎት ለቀይ ባህር ቀጣና ትልቅ እድል መሆኑንም ከፍተኛ ተመራማሪው ለኢዜአ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ፍትሃዊ እና ተቀባይነት ያለው ስትራቴጂካዊ መብት መሆኑንም ገልጸዋል ። የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ማደግ፣ የኢኮኖሚው እየሰፋ መሄድ፣ የንግድ ልውውጥ ማደግ እንዲሁም ሀገራዊ እና ቀጣናዊ የጸጥታ ዋስትናን በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆን ለዚህ ጥያቄ ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ ነው ያብራሩት። ሀገሪቱ ከቀይ ባህር ጋር ያላት ጂኦግራፊያዊ ቅርበት እና ከቀጣናው ወደቦች ጋር የነበራት ታሪካዊ ትስስር ዘላቂ የባህር መውጫ ለማግኘት ለምታነሳቸው ጥያቄዎች ጠንካራ መሰረት እንደሆነም አንስተዋል። የኢትዮጵያ በባህሩ አቅራቢያ መገኘት እና በኢኮኖሚውም ሆነ በጸጥታው መስክ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለባት የጋራ ግንዛቤ እንዳለም ነው የገለጹት ከፍተኛ ተመራማሪው። ለዚህ ስኬትም ጎረቤት ሀገራት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በጋራ መተማመንና በትብብር መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እውነተኛ ዓላማ በግልጽ መረዳት እንደሚገባ ተመራማሪው አንስተዋል። የጂኦ-ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ከየብስ እስከ ባህር የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቀጣናዊ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም የየብስና የባህር ደህንነትን ነጣጥሎ ከማየት ይልቅ፣ በጋራ ስጋቶችና ጥቅሞች ላይ ያተኮረ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ አመልክተዋል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ወደ ባህር በር መመለስ ለቀጣናው ሰላም፣ ለቀጣናዊ ትስስር እና ለምስራቅ አፍሪካ የጋራ ደህንነት ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያን በቀይ ባህር መድረክ ላይ መሳተፍ ለቀጣናው ትልቅ እድል ነው ሲሉም አክለዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና የፀጥታ ስርዓት ጋር ያላት ቁርኝት ጥልቅ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር እና የባህር መስመሮችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በባለቤትነት መሳተፍ እንዳለባት አሳስበዋል። ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያላት፣ በማደግ ላይ ያለ ኢኮኖሚ እና ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ በምስራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባህር የባህር ፀጥታን ለማስጠበቅ የግድ ሊሟላ የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ከፍተኛ ተመራማሪው አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪነት አስቀድሞ የተረዳው - ብሪክስ
Sep 18, 2026 145
በመቅደስ ወልዴ ብሪክስ እ.ኤ.አ በ2009 ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው በፍጥነት እያደጉ ባሉት በቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ብራዚል የተመሰረተ የደቡብ ደቡብ ትብብር ነው። ብሪክ /BRIC/ በሚል መጠሪያ የመጀመሪየውን ስብሰባውን ያደረገውም በወርሃ ሰኔ እ.ኤ.አ በ2009 በሩሲያዋ የካተሪንበርግ ከተማ ነበር። ጥምረቱ እ.ኤ.አ 2011 ደቡብ አፍሪካን በማካተት ስያሜውን ወደ ብሪክስ /BRICS/ ቀይሯል። የማህበራዊና የባህል መስተጋብር፣ የጂኦ ፖለቲካና የባለብዙ ወገን ትስስር፣ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ትብብር በመፍጠር የጸጥታ፣ የህዝብ ለህዝብና ማህበራዊ ጉዳዮችን ዕድገት ማሳለጥ ያለመ ነው። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ኢራን እ.ኤ.አ በ2024 ቀጥሎም ኢንዶኔዥያ እ.ኤ.አ በ2025 ጥምረቱን መቀላቀላቸውን ከብሪክስ ድረገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። እንደ መረጃው ከሆነ ጥምረቱ የዓለምን 49 ነጥብ 5 በመቶ የህዝብ ብዛት የሚሸፍኑ 11 ሀገራትን በአባልነት የያዘ እንዲሁም የዓለማችንን 40 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚሸፍን ስብስብ ነው። ብሪክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪነትን ማሳደግ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ እንዲሁም እንደ መንግስታቱ ድርጅትና መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት የዘረጉት ኢ-ፍትሐዊ ተቋማዊ አሰራር እንዲሻሻል ተፅዕኖ በመፍጠር ተጨባጭ ለውጥ የማየት ግብ ይዟል። ኢትዮጵያ እንዴት የብሪክስ አባል ሆነች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠንካራ እና በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተሰሚነት አቅምና ተፅዕኖ ፈጣሪነት እያደገ መጥቷል። በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ መግቢያ በር፣ የአፍሪካ ህብረት መስራችና መቀመጫ፣ የተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ፤ የዲፕሎማቶች መናኸሪያ፣ ሰፊ ህዝብና በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ያላት የአፍሪካውያን የአይን ማረፊያ ሆናለች። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቀነስና መቋቋም በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳርቻዎች እንዲሁም በገጠርና በከተሞች ያስመዘገበቻቸው የልማት ውጤቶች የዓለም ቀልብ ስቧል። በአህጉርና በዓለም አቀፍ መድረኮች የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ባለፈ አፍሪካውያንን በመወከል ድምጽ በማስማት ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን አሳይታለች። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላት ተጽዕኖ ፈጣሪነት፣ ለጋራ ልማት ለትብብርና ለፍትሐዊ ተጠቃሚነት የምታደርገው ጥረትና ባላት የጠራ የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የብሪክስ ጥምረትን እንድትቀላቀል በር ከፍቶላታል። በዚህም የኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረት አባልነት ተቀባይነት አግኝቶ እ.ኤ.አ በወርሃ ጥር 2024 በይፋ ተቀላቅላለች። ኢትዮጵያ ጥምረቱን እንድትቀላቀል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች ብስለት የተሞላበት የዲፕሎማሲ ጥረት ስለማድረጋቸው በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል መሆን የሚያስችሏትን አሳማኝ ምክንያቶች ሲያስረዱም ኢትዮጵያ ነጻነቷን ያስጠበቀች፣ ለተገፉ ሀገራት ድምፅ የሆነች፣ ለአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መመስረት ሰፊ ሚና የተጫወተች ሀገር መሆኗን እና ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ላይ የምትገኝ ሀገር መሆኗን በማንሳት የደቡብ - ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር ይህችን ታላቅ ሀገር ማካተት ተገቢ ነው ሲሉ በአፅንኦት ማስረዳታቸውና ማሳመናቸው ጥያቄው ተቀባይነት እንዲያገኝ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲፕሎማሲ አሰራር ብስለትን ካረጋገጡ ሂደቶች መካከል ኢትዮጵያን የብሪክስ ጥምረት አባል ለማድረግ የተጠቀሙት የዲፕሎማሲ ስልት ተጠቃሽ ነው። ይህውም ኢትዮጵያን የጥምረቱ አባል ማድረግ ለጥምረቱ አባል ሀገራት እና በጥቅሉ ለጥምረቱ የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ ለአባል ሀገራት መሪዎች በተናጥልና በጋራ መድረኮች ተገቢውን ግንዛቤ ማስጨበጣቸው ዋነኛው ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል እንድትሆን ያቀረቧቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ስትራቴጂካዊ አመክንዮዎች የጥምረቱን አባል ሀገራት ልብ መግዛቱ ጥያቄው አወንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ አስችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በባለ ብዙ ወገን ዲፕለማሲ መስክ ያላትን ተደማጭነት የሚያሳይ መሆኑንና በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በግብርና እንዲሁም በሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት እድገት እያስመዘገበችው ያለው ስኬት የአባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍተኛ ሚና ማበርከታቸውን ማብራራታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ብሪክስ ለኢትዮጵያ ምኗ ነው የኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል መሆን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን ታሳቢ ያደረገ ነው። ብሪክስ በጠንካራና የተቀናጀ ዲፕሎማሲ የጋራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አቅም በመፍጠር አብሮ ማደግን መዳረሻው አድርጓል። የኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረት አባልነትም የዚህ ጥቅም ተጋሪነትን መርህ ታሳቢ ያደረገ ነው። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል በመሆኗ በፋይናንስና የኢንቨስትመንት የትብብር መስኮች ሰፊ ዕድል እንዲኖራት የሚያስችል መሆኑንና ለጀመረቻቸው የልማት ስራዎች ስኬትም ተጨማሪ የፋይናንስ አቅም እንድታገኝ እንዲሁም ወደ ውጭ ለምትልካቸው ምርቶች ሰፊ የገበያ አማራጭ የሚፈጥር መሆኑን በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) መግለጻቸው ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። ኢትዮጵያ በቱሪዝም፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በኢንዱስትሪ፣ ማዕድንና ግብርና ዘርፎች የጀመረችውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማቀላጠፍ ከብሪክስ ተጨማሪ ልምድና ተሞክሮ ታገኝበታለች፤ ልምዷን ለሌሎች ለማካፈልም ምቹ ዕድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብሎም በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት። ይህ ደግሞ የብሪክስ አባል ሀገራትን ሰፊ የገበያና የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ዕውን ለማድረግ ተጨማሪ አቅም ይፈጥርላታል። ከዚህም ባለፈ ብሔራዊ ጥቅሟና የሌሎችን የጋራ ተጠቃሚነት መሳ ለመሳ የምታካሂድ ለመሆኗ ትልቅ ማሳያ ነው። ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 18ኛው የጥምረቱ ጉባኤ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችንን ያረጋገጥንበትና የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ የተሰማበት ታሪካዊ ስኬት ነው ማለታቸው። ጥምረቱ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማሳካት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፣ የአረንጓዴ ኢነርጂ ልማት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ማረጋገጥ በትብብሩ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል። ኢትዮጵይ በቀጣናው፣ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሃላፊነት ለመወጣት የብሪክስ ማዕቀፍ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ መድረኮች ወሳኝ አጀንዳዎችን ለማራመድ የጎላ ሚና ይኖራቸዋል። ከብሪክስ ጥምረት በኋላ የተገኙ የዲፕሎማሲና ኢኮኖሚ ስኬቶች 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ እ.አ.አ በ2025 በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ በተካሄደበት ወቅት በዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት፣ ባለብዙ ወገን ተቋማት ማሻሻያ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አጀንዳዎች ላይ መምከሩ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን መሸጋገሩን፤ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት በሚያስችል ሁኔታ አፋጣኝ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚገባቸው፤ በብሪክስ አዳዲስ አባላት መጨመራቸው የጋራ ድምፃችን የበለጠ እንዲጠናከር ያስችላል የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል። አቅማችንም ይሰፋል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። በተጨማሪም እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በአለምአቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ እንደምታደርግ ማንሳታቸው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ለአፍሪካ ጥቅም መከበር ሚናዋን መቼም የማትዘነጋ መሆኑን አመላካች ነው። ስለ ዓለም ሰላም፣ የተቀላጠፈ የኢኮኖሚ ሽግግርን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂና ፈጠራ እንዲሁም ለቀጣናዊ ውህደት ያላትን ፍላጎትና ቁርጠኝነት በጉልህ ማሳየታቸው፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ልማት፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብሎም መሰረተ ልማት ዝርጋታና መስፋፋት ያላትን ርዕይ በግልጽ ማንጸባረቃቸው ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላም፣ ልማትና ብልፅዕና ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ነው። የብሪክስ ጥምረት የዓለም የዲፕሎማሲና የጂኦፖለቲካ ተፅዕኖን ለማሳደግ ካለው ሰፊ ዕድል አንጻር ሲታይም በዓለም አቀፍ መድረኮችና ውሳኔዎች ላይ የሀገሪቱንና የአህጉሪቱን ድምፅ ለማጠናከር ከምዕራባውያን ተፅዕኖ የተላቀቀ ሁለገብ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን በጽኑ መሰረት ለመገንባት ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በጥምረቱ የምታደርገው ተሳትፎ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካና የሌሎች አህጉራት ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፍ ባለብዙ ወገን ተቋማት ፍትሃዊ ውክልና ማግኘት እንዳለባቸው በተገኙባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ሁሉ ሲሞግቱ የሚደመጡትም ይህንኑ የሚያመላክት ነው። ዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪና የባለብዘዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትንና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው አጽንኦት መስጠታቸውም እንዲሁ። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ጥቅሞች መከበር ያለባትን ሀላፊነት በውል እንደምትገነዘብ እና ድምጿን ማስተጋባቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ያረጋገጠችበት መድረክ ነው። የብሪክስ ጥምረት ሀገራትን በአባልነት ለማቀፍ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች የሀገራቱን ዓለም አቀፍ ተፈላጊነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ደግሞ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተደማጭነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በግልጽ አሳይቷል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነትን በተቀላቀለችበት ወቅት ከ40 በላይ ሀገራት ጥምረቱን ለመቀላቀል ፍላጎት አሳይተው ነበር። የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ብቻ መመረጣቸው ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላትን ግዙፍ የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ማሳያ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳልና አሳታፊ የዲፕሎማሲ ጥረት የተገኘው የብሪክስ ጥምረት አባልነት ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ከተመዘገቡ የዲፕሎማሲ ስኬቶች አንፃር ትልቁና አንጸባራቂ ድል ተብሎ ይወሰዳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥምረቱ የኢትዮጵያን የአባልነት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ባጸደቀበት ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ጥምረቱን መቀላቀል የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ ልዕልና ማሳያ ነው ሲሉ መግለጻቸውም ይህንኑ ያጠይቃል። የብሪክስ ጥምረት ኢፍትሃዊውን ዓለም አቀፍ መዋቅርና ሥርዓት ወደ ሚዛናዊ መንገድ በማምጣት በዓለም የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሁሉም ሀገራት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራቸው ያስችላል። ብሪክስ ይህ ስርዓት መሬት እንዲረግጥ የራሱ አስተዋጽኦ አለው። ለኢትዮጵያም እነዚህ የተዛነፉ ዓለም አቀፍ ባለብዙ ወገን ተቋማት አሰራር ፈር እንዲይዝ የራሷን ሚና ለመወጣትና ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዋን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የብሪክስ ጥምረት ውጤት የሆነው የአዲሱ የልማት ባንክ ያለምንም ፖለቲካዊ ቅድመ ሁኔታ ሀገራት መሰረተ ልማት ማስፋፋት የሚችሉበትን ብድር ያቀርባል። ኢትዮጵያም ከሀገር ውስጥ ባለፈ ቀጣናውንና አህጉሪቱን በኤሌክትሪክ ሀይል እና በሌሎች መሰረተ ልማቶች የማስተሳሰር ውጥኗን ዕውን እንድታደርግ ያስችላታል። ኢትዮጵያ ለጀመረችው መጠነ ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ይሆናል። እንደ ቻይና፣ ሕንድ እና ሩሲያ ካሉ የዓለምን ኢኮኖሚ ከሚያንቀሳቅሱ ሀገራት ጋር ያላትን የወጭ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቷንና የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን ማሳደግ፣ የወጪ ንግዷን በራሷ የመገበያያ ገንዘብ ለማከናወን ምቹ ዕድል ይፈጥርላታል። የጥምረቱ አባል ሀገራት በቴክኖሎጂ ውጤቶች ፈጠራ እና የማምረት ብቃትና የተወዳዳሪነት አቅም መጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ለመፍጠርም በር ከፍቶላታል። ኢትዮጵያ በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ17ኛ የብሪክስ መሪዎች ጉባዔ የአፍሪካን ድምጽ ለዓለም ማሰማታቸው በ18ኛ የብሪክስ ጉባዔ አመርቂ የዲፕሎማሲ ስኬት እንዲመዘገብ አስችሏል። የአፍሪካን ጥቅም ማስጠበቅ፣ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ሥራዎች የጎላ ድጋፍ እንዲገኙ፣ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥረት ለውጤት እንዲበቃ የብሪክስ ሀገራት መሪዎች በኒው ዴልሂ ቃላቸውን ሰጥተዋል። የብሪክስ ሀገራት በአዲሱ የልማት ባንክ የአባልነት ጥያቄያቸው በፍጥነት እንዲታይ፣ በታዳጊ ሀገራት መካከለ ዘላቂ የዕዳ አስተዳደር ስምምነቶች እንዲኖሩ በማድረግ ኢትዮጵያ ገንቢ ሚና ተጫውታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የኢትዮጵያን ውጤታማ ስኬቶች በጉልህ አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን፣ በቅድመ መከላከል የጤና ፖሊሲ ውጤት ማስመዝገቧን፣ የህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ በማምረት አክሞ የማዳን አቅሟን ማሳደጓን፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ደህንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀምና ሽግግር መፍጠሯን፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም አዳጊ ፍላጎቶችን ሊያሳካ የሚችለውን የመደመር ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታን በማንሳት ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ትብብርና ልማት ያላትን ቀናኢነት አንስተዋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ አስተወሎት ያመጣቸው ዕድሎችን መጠቀምና ስጋቶችን ለመፍታት ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውም ይታወሳል። አፍሪካ ጠንካራ ውክልና እንዲኖራት፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ፤ ንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ትስስርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ያቀረቡበት መድረክ ነበር። አዲሱ የልማት ባንክ በመላው አፍሪካ አድማሱን በማስፋት በአዲስ አበባ ቢሮውን እንዲከፍት የጠየቁበት፤ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጣቸው፣ በአጠቃላይ 18ኛ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ጥቅሞች መከበር ፊት አውራሪነቷን በድጋሚ ያረጋገጠችበት ሆኖ ተጠናቋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የመልማት አቅም ያላት ሀገር ናት። ለያዘቻቸው የልማት ርዕዮች መሳካት አማራጭ የፋይናንስ ምንጮች ያስፈልጓታል። ለዚህ ደግሞ ብሄራዊ ጥቅሟን ያስከበረና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ የዲፕሎማሲ ስኬት እያስመዘገበች በልዩ ጥንካሬ ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች። በታሪካዊው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ የተገኘውን ወርቃማ የዲፕሎማሲ ድል ወደ ዘላቂ ልማት ለመቀየር የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የመንግሥት ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ወጣቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች የጋራ ሀገራዊ ራዕይ በመሰነቅ፣ ብሄራዊ አንድነትንና ጥንካሬን በማንገብ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና በቁርጠኝነት መሰለፍ ይገባቸዋል።  
የሚታይ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ9ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ተሸለመ
Sep 18, 2026 178
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመት በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ሽልማትን አግኝቷል። አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ እና በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት ሽልማቶችንም ተቀብሏል። የአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የSKYTRAX የዓለም አየር መንገድ ሽልማቶች ላይ ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመት በመመረጥ የአህጉሪቱ ቁጥር አንድ አየር መንገድነቱን አረጋግጧል። ከዚህ ታላቅ እውቅና በተጨማሪ አየር መንገዱ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎችም ሽልማቶችን አግኝቷል። ሽልማቶቹም በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ አየር መንገድ፣ በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት አሰጣጥ እና በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ የሚሉት ናቸው፡፡ ሽልማቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጥራት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያላቸውን እምነትና ታማኝነት ያንፀባርቃሉ። ዕውቅናው አየር መንገዱ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት፣ ልዩ የደንበኞችን እርካታ ለመጠበቅ እና በዓለም አቀፍ አውታረ መረቡ ውስጥ እንከን የለሽ የጉዞ ልምድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው። በተጨማሪም የአየር መንገዱን ሰራተኞች ያላሰለሰ ጥረት የሚያጎላ ሲሆን፣ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የአቪዬሽን ቡድን መሆኑን ያረጋግጣል። ሽልማቶቹ አየር መንገዱ የአገልግሎቶች እና የአሠራሮች ደረጃ በመጠበቅ ረገድ ያለውን ቁርጠኛነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
የሕወሃት ቡድን ለትግራይ ህዝብ ከጥፋት ውጪ ሊሰጠው የሚችለው አንዳች ነገር የለውም -አቶ ጌታቸው ረዳ
Sep 18, 2026 218
አዲስ አበባ ፤መስከረም 8/2019 (ኢዜአ)፦የህወሃት ቡድን ከጥፋትና ከመከራ ውጪ ለትግራይ ሕዝብ ሊሰጠው የሚችለው አንዳችም አዲስ ነገር እንደሌለው የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ገለጹ። የትግራይ ሕዝብና ወጣቶች የሕወሃትን አጥፊ ቡድን በመታገል ክልሉን ወደ ሰላምና ልማት መመለስ እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል። የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ህወሃት ባለፉት ዓመታት የትግራይን ህዝብ ማለቂያ የሌለው መከራ እና የጥፋት አዙሪት ውስጥ ከመክተት ውጪ የፈየደለት ነገር እንደሌለ ነው የተናገሩት። የቡድኑ አጥፊ አካሄድ የትግራይ ሕዝብ ከልቡ ከሚሻው እውነተኛ የሰላም እና የመረጋጋት ፍላጎት ጋር ፍጹም የተቃረነ መሆኑን አመልክተዋል። የሀገርና የዓለም ሁኔታ በተለወጠበት በአሁኑ ወቅት የህዋሃት መሪዎች በአሮጌ እና በጠባብ የፖለቲካ አስተሳሰብ ተዘፍቀው እንደሚገኙ አመልክተዋል። ባለፉት ዓመታት በክልሉ የደረሰው ጥፋት ከህወሃት ቡድን የተሳሳተ ውሳኔ የሚመነጭ መሆኑን ገልጸዋል። አመራሮቹ ሁልጊዜ ራሳቸውን ትክክለኛ አድርጎ የማሰብ አባዜ፣ የህዝቡን እውነተኛ ስቃይ እንዳይረዱት አድርጓቸዋል ነው ያሉት። በአሮጌ የትጥቅ ትግል ስልት የታወሩ እና ዕድሜያቸው የገፋ ጥቂት የቡድኑ አመራሮች የትግራይን ህዝብ ዕጣ ፈንታ በብቸኝነት ለመቆጣጠር መነሳታቸው ፍጹም ስህተት ነው ብለዋል። ዛሬ ላይ ያለው ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ እና እውነተኛ የሰላም ፍላጎት እንዳለው ገልጸው ይሁንና የቡድኑ አመራሮች ጊዜው ባለፈበት እሳቤ ህዝቡን ወደ ሌላ የትርምስ አዙሪት ውስጥ ለመክተት እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተፈረመው ጦርነትን ለማስቆም እና ሕዝቡን ወደ መደበኛ ሕይወት ለመመለስ እንደነበር አስታውሰው፤ ይሁን እንጂ የህወሓት አመራሮች ስምምነቱን የራሳቸውን ስልጣን ለማስቀጠል ሲሉ ሂደቱን ሆን ብለው ማደናቀፋቸውን ተናግረዋል። ከቀያቸው ተፈናቅለው በችግር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ጭምር ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ በመከልከል ለፖለቲካ ንግድ መጠቀሚያ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ሰላም የማይፈልጉት የህወሃት ቡድን አመራሮች ሕዝቡን በችግር ላይ ጥለው፣ ከቀውሱ ትርፍ ለማግኘት በሕገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድና የወርቅ ዝውውር ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ ገልጸዋል። የትግራይ ወጣቶች በቡድኑ በሚደርስባቸው ግፍና ጭቆና ተማረው ክልሉን ጥለው እየተሰደዱ ስለመሆኑም ነው የገለጹት። አሁን ላይ ደግሞ የቡድኑ አመራሮች የትግራይን ህዝብ ደህንነትና ጥቅም ወደ ጎን በመተው ከትግራይ ህዝብ ጠላቶች ጋር አዲስ የፖለቲካ ጥምረት መፍጠራቸው እጅግ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። የሕወሃት አመራሮች ውድቀትን እንደ ብቃትና ድል አድርገው የማየት አባዜ የተጠናወታቸው ጸረ ህዝብ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ጌታቸው፤ ቡድኑ አጥፊ ስህተቶቹን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ራሱን ትክክለኛ በማስመሰል ህዝቡን በማሳሳት ዘመቻ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል። የህወሓት ቡድን ለትግራይ ሕዝብ ከጥፋት፣ከስደት፣ ከስቃይ እና ከመከራ ውጪ ሊሰጠው የሚችለው አንዳችም አዲስ ነገር የለም ብለዋል። እውነተኛ ሰላም ሊመጣ የሚችለው ይህንን አጥፊ ቡድን በቁርጠኝነት በመታገል ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ የትግራይ ሕዝብና ወጣቶች የጥቂቶች መጠቀሚያ የሆነውን ይህንን አጥፊ ቡድን በመታገል ክልሉን ወደ ሰላምና ልማት መመለስ እንዳለባቸውም ነው ጥሪ ያቀረቡት።
የዘንድሮው የኢሬቻ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መስከረም 21 ቀን በቢሾፍቱ ይካሄዳል
Sep 18, 2026 197
ቢሾፍቱ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፡-የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ መስከረም 21 ቀን በቢሾፍቱ ከተማ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ። የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2019 ዓ.ም የ2ኛውን የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዴ አዳራሽ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።   በመግለጫው ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባ ገዳዎችና ታዋቂ አትሌቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በዓሉ የባህል እሴትን ከስፖርት ጋር በማጣመር በደመቀና በተዋበ ሁኔታ እንዲከበር የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተገልጿል። የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ እንደገለጹት፤ የኢሬቻ በዓል እና የስፖርት እንቅስቃሴዎች የባህል ዕሴቶችን ለማበልጸግ፣ ፍቅርና ወንድማማችነትን ለማጠናከር እንዲሁም አገራዊ ኢኮኖሚን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው። አክለውም፣ ኢሬቻ የህዝቦችን አንድነት እና ፍቅር በማጽናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሀገራዊ መግባባትን ለመገንባት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አብራርተዋል።   በዘንድሮው የ2ኛው የኢሬቻ ሩጫ ውድድር እስከ 6ኛ ደረጃ ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች ልዩ ልዩ ሽልማት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ በተጨማሪም የዲባባ ቤተሰቦች የኢሬቻ ሩጫ አምባሳደር መሆናቸውን ገልጸዋል። ቢሮውም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2019 የኢሬቻ በዓልን በታላቅ ቅንጅት ለማክበር ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ 2ኛው የኢሬቻ ታላቅ ሩጫ መሆኑንም አብራርተዋል። የጎዳና ላይ ሩጫው ዋና ዓላማ የኢሬቻ በዓል ባህላዊና ሥነ-ምግባራዊ እሴቱን ጠብቆ ከማከበር ጎን ለጎን ከስፖርት ጋር በማያያዝ ለተከታዩ ትውልድ ለማስተላለፍና የህዝቡን ባህል ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል። የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ በበኩላቸው፤ ኢሬቻ ፍቅርና አንድነት በመሆኑ፣ በበዓሉ ምክንያት የተዘጋጀው ሩጫም ፍቅርን፣ አንድነትንና የብሔር ብሔረሰቦችን ቁርኝት ስለሚያጠናክር ህዝቡ እንዲሳተፍ ጥሪ አድርገዋል። ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ድርሻቸውን እንዲወጡና ህዝቡ በሰላም መጥቶ በሰላም እንዲመለስ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑም አመልክተዋል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስማቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠሩት የዲባባ ቤተሰቦች የኢሬቻ ሩጫ አምባሳደር ሆነው ተመርጠዋል።   አትሌቶች በአምባሳደርነታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ውድድሩን በስፋት ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል። ውድድሩ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የህዝብ ሩጫ ሲሆን የኬንያ እና የታንዛኒያ አትሌቶችን ጨምሮ በሁለቱም ጾታ አትሌቶችም ይሳተፉበታል ተብሏል።    
የሶማሌ ክልልን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች በብቃትና በጥራት እየተፈጸሙ ነው
Sep 18, 2026 196
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- የሶማሌ ክልልን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች በብቃትና በጥራት እየተፈጸሙ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በፌዴሬሽን ምክር ቤትና ተጠሪ ተቋማት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል። አፈ ጉባዔው በዚሁ ወቅት፤ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ዜጎች የነበረባቸውን የቤት ችግር በመቅረፍ አስተማማኝ መጠለያ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ብለዋል። ፌዴሬሽን ምክር ቤትም በክልሉ ከአቅመ ደካማ ወገኖች የቤቶች ግንባታ በተጨማሪ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። እንዲሁም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካባቢን በመጠበቅ ለቀጣይ ትውልድ የሚጠቅም መሠረት በመጣል የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። የሶማሌ ክልል በመደመር መንግሥት የአስተዳደር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች እውን የሚሆኑበት ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። በዚህም የክልሉን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ተገንብተው የሕዝብን የልማት ጥያቄ በመመለስ ለአገልግሎት መብቃታቸውን አስረድተዋል። ለአብነትም በማኅበራዊ ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የጤና ተቋማት ግንባታን በማስፋፋት ሕብረተሰቡ በአቅራቢያው የሕክምና አገልግሎት የሚያገኝበት ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በመንገድ፣ በአየር ማረፊያ መሠረተ ልማቶችና በኢንቨስትመንት ፍሰት የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎች መመዝገባቸውን አብራርተዋል። የመደመር መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ጀምሮ ማጠናቀቅ ዋነኛ መለያው መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህም የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት እያሻሻለ መሆኑን አብራርተዋል። የሶማሌ ክልል ሕዝብ ለዘላቂ ልማትና ሰላም ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት አፈ ጉባዔ አገኘሁ፤ በቀጣይም ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማት የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሕብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር በልማት ሥራዎች ያለውን ተሳትፎ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደባባይ በዓላትን ያለምንም ችግር ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል-ፖሊስ
Sep 18, 2026 193
ወላይታ ሶዶ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደባባይ በዓላትን ያለምንም ችግር ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ደግፌ ደበላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ያለምንም ችግር እንዲከበሩ የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በክልሉ በቀጣይ ቀናት በወላይታ ጊፋታ፣ በጋሞ ዮ ማስቃላ፣ በጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና በሌሎችም አካባቢዎች የአደባባይ በዓላት እንደሚከበሩም ገልጸዋል። በክልሉ በአደባባይ ለሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ ክንውን ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የተሟላ እና የተቀናጀ ስምሪት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። የትራፊክ እንቅስቃሴን ከማሳለጥ ጀምሮ በዓላቱ በሚከበሩባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ቁጥጥርና ጥበቃ ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ ማከናወን በሚያስችል መልኩ ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል። በግብይት ወቅት ሕብረተሰቡ ከሐሰተኛ ገንዘብ ስርጭት እና ባዕድ ነገሮችን ቀላቅለው ከሚሸጡ ህገወጦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም ጠቁመዋል። አሽከርካሪዎችም የትራፊክ አደጋን በመከላከል የሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው በአፅንኦት ተናግረዋል። ሕብረተሰቡ ከመደበኛ እንቅስቃሴ የተለየ ነገር ሲመለከት እና የወንጀል ሥጋቶች ሲኖሩ በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር እንደሚገባም አመልክተዋል።  
ወደ 300 የሚጠጉ የህገወጡ ህወሃት ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ
Sep 18, 2026 304
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፦ የህገ ወጡን ህወሃት የጦርነት ዝግጅት በመቃወም ወደ 300 የሚጠጉ ታጣቂዎቹ በተከዜ በኩል ለሚገኘው ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጥተዋል። በምዕራብ ግንባር ተከዜ አቅጣጫ ልዩ ቦታው በተከዜ ድልድይ ግራና ቀኝ አቅጣጫ ለዕዙ ሠራዊት እጅ የሠጡ የህወሃት ታጣቂዎች የኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ የትግራይን ህዝብ ሲጨፈጭፍ ከነበረው ሻዕቢያ ጋር ፅምዶ በሚል የፈጠሩት ጥምረት ለትግራይ ህዝብ የማይጠቅም መሆኑን ታጣቂዎቹ ገልጸዋል። ይሄንን በመገንዘብም በቀጣናው ከሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ጋር ቀደም ብለው በመሠረቱት ግንኙነት በመነጋገር እና መንገድ በማመቻቸት እጅ መሥጠት እንደቻሉ ተናግረዋል።   የትግራይ ህዝብ ጥያቄ የሚፈታው በጠብመንጃ እንዳልሆነ በመረዳት እጃቸውን የሰጡት ታጣቂዎቹ ከ280 በላይ የነፍሰ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ በርካታ የተለያዩ ዓይነት ተተኳሾች፣ የጦር ሜዳ መነፅርና ልዩ ልዩ ዶክመንቶች ይዘው ገብተዋል። ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን ሠላማዊውን የትግራይ ህዝብ ወጣት በማፈስ ወደ ጦርነት ለመማገድ የሚሠሩ ዘራፊ እና ወርቅ አውጪ የህገወጡ ህወሃት አመራሮችን ፍላጎት እንደሚቃወሙም ገልጸዋል። እጅ ከሰጡ ታጣቂዎች መካከል ከክፍለጦር አዛዥ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሻለቃና የሻምበል አመራሮች ይገኙበታል ያለው ዕዙ ይህ የሚያመላክተው ታጣቂው ሃይል ሳይፈልግ በህወሃት ሥርዓት አገዛዝ አስገዳጅነት የሚዋጋ ስለመሆኑም ገልጿል።   ህወሃት ከጦርነት አዙሪት የመውጣት ፍላጎት የሌለው ፅምዶ በሚል አካሔድ ህዝቡን አሁንም ወደ ከፋ ችግር ውስጥ ለመክተት የሚጥር፤ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለሠላም የማይመች፤ የቀረበለትን የሠላም አማራጭ የማይቀበል በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ስለመሆኑም እጅ የሠጡ ታጣቂዎች ተናግረዋል። አሁን ላይ የህወሃትን የአገዛዝ ሥርዓት በመጥላትና ሠላምን በመምረጥ እጅ ለመስጠት የሚጠባበቁ በርካታ የትግራይ ወጣቶች አሉ ያሉት ታጣቂዎቹ የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠልና ሠላም ለማሳጣት ህወሃት ወጣቱን እያስገደደ ሳይፈልግ ለጦርነት እያዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል። ተገዶ የገባው የትግራይ ወጣትም ይህን አውቆ እና ተረድቶ ጊዜና ሁኔታው ሲመቻችለት እጅ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ከመከላከያ ሚዲያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ማንሠራራት እና የመግባባት ዴሞክራሲ ልዕልና
Sep 17, 2026 389
ኢትዮጵያ ከተለመደው የፖለቲካ የመገፋፋት አካሄድ ወጥታ፣ ሁሉንም ዜጎች የሚያካትትና በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉዞ ሀገሪቱን በፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም እና ብሔራዊ መግባባትን በዘላቂነት ለማምጣት የሚያስችል ስኬታማ ተግባር ነው። የምክክሩ ሂደት በሃሳብ መግባባትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ፣ የፖለቲካ ስጋቶችን እና አለመተማመኖችን በእጅጉ ይቀንሳል። የመግባባት ዴሞክራሲ ዋነኛ መርህ ውሳኔዎች በአብላጫ ድምፅ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ወገኖች ስምምነት ላይ እንዲመሰረቱ ማድረግ ነው። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደትም መግባባት ላይ የተደረሰባቸው አጀንዳዎች ከጥቂቶች ፍላጎት የፀዳ፣ የብዙሃኑ ድምጽና ሀሳብ ጎልቶ የወጣበት ነው። ምክክሩ ከተለመደው የፖለቲካ አካሄድ ተላቆ በምክንያት ላይ የተመሰረተ የውይይትና የመደማመጥ ባህል የዳበረበት ሲሆን ይህ መንገድ ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶችን በሰከነ መንፈስ ለማስተናገድ አስችሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ከአስፈጻሚው አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ በመሆን በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ እንዲሆን መደረጉ፣ ተቀባይነትና ተአማኒነት እንዲያገኝ አስችሏል። በተለመደው የፖለቲካ ሥርዓት አጀንዳዎች የሚቀረጹት በጥቂት ልሂቃን ቢሆንም፣ በዚህ ምክክር ግን አጀንዳዎች ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል (ከወረዳ ደረጃ) በተሰበሰቡ ግብዓቶች ላይ ተመስርተው እንዲዘጋጁ መደረጉ ህዝቡ የሂደቱ ባለቤት እንዲሆን አድርጓል። የተለያዩ ማህበረሰቦች ድምፃቸው እኩል ክብደት ኖሮት ውሳኔዎች ላይ እንዲሳተፉ መደረጉ የምክክሩ አንዱ ስኬት እና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ማሳያ ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ በፊት የነበረው የአሸናፊና ተሸናፊ ፖለቲካ አካሄድን ያስቀረው ሀገራዊ ምክክሩ በጠረጴዛ ዙሪያ በመቀመጥ ሁሉንም አካላት አሸናፊ የሚያደርግና የጋራ መፍትሔ ማፈላለጊያ መድረክ ሆኗል። የምክክር ጉባኤው መጠናቀቅ የሂደቱ ማብቂያ ሳይሆን ወደ ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ነው። ኮሚሽኑ ያሰባሰባቸውን ከ400 በላይ ምክረ-ሀሳቦች ለተቋማት በማቅረብ እና የተገኙት ስምምነቶች መሬት ላይ መውረዳቸውን የሚከታተል የቁጥጥር ሥርዓት እያዘጋጀ ይገኛል። በምክክሩ ላይ የታየው ሰፊና ሁለንተናዊ የህዝብ ተሳትፎ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ በመገንባት፣ ብሔራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ እና የጋራ መጻኢ ዕድልን ለመቅረጽ የሚያስችል የዚህ ዘመን የመግባባት ዴሞክራሲ ተጨባጭ ማሳያ ነው።
ግብፅ የዓባይን ጉዳይ ለውስጥ ፖለቲካ ችግሮቿ መሸፈኛ ለማድረግ እየሞከረች ነው
Sep 17, 2026 499
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታደርገው የፖለቲካ ዘመቻ የራሷን ውስጣዊ ችግሮች ለመሸፈን የምትጠቀምበት ስልት መሆኑን የስትራቴጂክ ጥናትና የትስስር ኢኒሸቲቭ ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ አብዱሻኩር አብዱሰመድ ገለጹ። የግብፅ መንግስት አባይን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉ እና የተፋሰሱን ሀገራት በጠላትነት ፈርጆ ማሳየቱ በግብጻውያን ዘንድ ኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተ ጥላቻ እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ከፍተኛ ተመራማሪው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። የሚዲያ ዘመቻ እና የተሳሳተ ትርክት ከውጤታማነቱ ይልቅ የግብፅን ህዝብ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አመልክተዋል። የግብፅ መንግስት ዓባይ ብቸኛው የውሃ ምንጭ እንደሆነ በማስመሰል ለማሳመን ረዥም ረቀት መጓዟን ጠቅሰዋል። ይህ የተሳሳተ አመለካከት አንዳንድ ግብፃዊያን በሌሎች ሀገራት የሚደረጉ የልማት ስራዎች የግብፅን የውሃ ድርሻ የሚነጥቁ አድርጎ እንዲመለከቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። የዚህ ሁሉ ዘመቻ ዋና ዓላማ በግብፅ ውስጥ የሚስተዋሉ ፖለቲካዊ እና ማሕበራዊ ቀውሶች ትኩረት እንዳያገኙ መሸፈኛ ማድረግ መሆኑን ነው ተመራማሪው ያስረዱት። አክለውም፣ ትውልዱ ይህንን የተሳሳተ ትርክት እንደ ፍጹም እውነት እንዲቀበለው ግብፅ የምትሰራው ስራ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል። ግብፅ ሜዲትራኒያን እና ቀይ ባህርን ጨምሮ በርካታ የባህር ዳርቻዎች እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብቶች እንዳሏት ተመራማሪው ጠቁመዋል። ሆኖም በዓባይ ላይ ብቻዋን የመወሰን መብት እንዲኖራት ትፈልጋለች፣ ይህ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል። የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) ሁሉም ሀገራት ፍትሃዊ የመጠቀም መብት እንዳላቸው በግልጽ እንደሚያስቀምጥም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ለመጠቀም የማንንም ፈቃድ እንደማትጠይቅ እና ይህ ተፈጥሯዊ መብቷ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ሀገሪቱ ንጹህ፣ ታዳሽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ሚናዋን በሚገባ እየተወጣች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከጅማሮው አንስቶ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ተደጋጋሚ ጊዜ ጥሪ አድርጋለች። ይሁን እንጂ ግብፅ የመረጠችው አካሄድ ለጋራ ዕድገት እና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከሚያስፈልገው የትብብር አማራጭ ጋር ፍጹም የተቃረነ መሆኑን ከፍተኛ ተመራማሪው አንስተዋል። ጊዜያዊ የፖለቲካ ቅስቀሳዎች ዕድሜያቸው አጭር ነው ያሉት ተመራማሪው በህዝቦች ውስጥ የሚፈጥረው የተሳሳተ ግንዛቤ በጊዜ ሂደት እንደሚቀረፍም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት የዚህ ትውልድ አደራ ነው
Sep 17, 2026 539
ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ የውሃ አካሏና በሯ ብቻ አልነበረም፤ የሺህ ዘመናት የንግድ፣ የሥልጣኔ፣ የሃይማኖትና የባህል መገለጫ፤ ከዓለም ጋር ያላትን መስተጋብር ማሳለጫ መስመር ጭምር እንጂ። የአክሱም ሥልጣኔ በቀይ ባሕር የጠረፍ ከተማዋ በኩል የከተመው የአዱሊስ ወደብ ላይ መልህቁን በመጣል ከዓረብ ልሳነ ምድር እስከ ሜዲትራኒያን፣ ከሕንድ ውቅያኖስ እስከ የአፍሪካ የባሕር ጠረፎች ድረስ የነበረው ሁለንተናዊ ትስስር የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነትና የንግድ ማዕከልነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ገናና የታሪክ አስረጂ ነው። ኢትዮጵያ ምፅዋና አሰብ ወደቦቿን በግፍ ተነጥቃ ከቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካ ከተገለለች የጉልማሳ ዕድሜ አስቆጠረች፤ የቀጣናው የሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ፣ የንግድ መስመር፣ የዲፕሎማሲ ማዕከል የነበረች ሀገር አምጣ በወለደቻቸው ልጆቿ ጭምር ደባ ተሰራባት ። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር የነበራት ጥብቅ ቁርኝት የዘመኑ የፖለቲካ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ከጥንታዊ የንግድና የሥልጣኔ ታሪኳ ጋር የተሳሰረ የትውልድ የህልውና ጉዳይ የሚሆነው። ግብጽ እና ሌሎች ታሪካዊ ጠላቶች የሀገር ውስጥ ባንዳዎችን በማስተባበር በፈጸሙት ደባ ኤርትራን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የሺህ ዘመናት ገናና የሥልጣኔ ልዕልናዋን የሚያሳጣ ክህደት ፈጽመዋል። ይኸውም ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብና ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ያለችውን የቀጣናው ሀያል ሀገር የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በማስተጓጎል በገቢና ወጪ ንግድ እና በኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ዕንቅፋት ደቅኗል። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ - ጅቡቲ ኮሪደር ብቻ የተወሰነ ነው፤ ከዚህም ባሻገር ቀይ ባህር የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሰላምና የሕልውና ጉዳይ እየሆነ መጥቷል። ከቀይ ባሕር በቅርብ ርቀት የምትገኘው ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሰፊ የሕዝብ ቁጥርን፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን፣ የሰላምና የደኅንነት ስጋት እንዲሁም የሕልውና ጉዳይን ሁሉ ታሳቢ ያደረገ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ፍትሐዊና ምክንያታዊ ነው። ህልውናን ማረጋገጥ፣ ከሌሎች ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅምን በማስጠበቅ የኢኮኖሚ፣ የሰላምና ደኅንነት ትብብርን ማጠናከርና የጋራ ብልጽግናን የማረጋገጥ ግብም አንግቧል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎረቤት ሀገራትን በሀይልና በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በጋራ ለመልማትና ለማደግ ያላትን ፅኑ ፍላጎት ያሳያል። ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካ እስረኛ ሆና ያሳለፈቻቸው ዓመታት በዓባይ ዘመን ትውልድ ሊያከትም ይገባል፤ ጥያቄዋም በዓለም አቀፍ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ቅቡልነት እያገኘ እንዴት ይፈጸም ወደሚል ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ ይሄን እውነት ያንጸባርቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያን የባሕር በር አይገባትም የሚል ሰው የተፈጥሮን ህግ የሳተ መሆኑን አስረድተዋል። ቀይ ባሕርና ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተነጣጥለው መኖር እንደማይችሉ፤ ይሄንንም አምኖ መቀበል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጽናትን፣ ፈጠራ፣ ትብብርና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ሃሳብ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤም የኢትዮጵያን የዕድገትና ብልፅግና ተስፋና መፃኢ ዕድል አብራርተዋል። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚውና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብሔራዊ ጥቅሟንና የአፍሪካን ድምፅ ለማስተጋባት የጉዳዩን ወሳኝነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በግልጽ ተናግረዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) ቀደም ሲል ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያውያን በተፈጸመ የታሪክ ስህተት የትውልድን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈን የምንሰጥ ሕዝቦች አይደለንም ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በይፋ በቀረበ ማግስትም በሕዝብ ልብ ውስጥ ለጥቂት ዓመታት ተዳፍኖ የቆየው ቁጭት በአጭር ጊዜ ውስጥ ቅቡልነት ማግኘቱን ገልጸዋል። በቀጣይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ ልዩነት ሊኖረን አይገባም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ትብብርና አንድነት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ቀጣናዊ ትብብርና የጋራ ብልጽግናን ማዕከል ያደረገ ነው ብለዋል። ጥያቄው ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ሕጋዊ መሰረት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ንግድና ኢንቨስትመንትን የማሳለጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ስምምነትና ሕግጋትም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባሕር የመድረስና የመጠቀም መብታቸውን የሚደግፍ ድንጋጌና ማዕቀፍ እንዳለው አስረድተዋል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ቀንድና የውሃ ጂኦፖለቲካ ከፍተኛ ተመራማሪ ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የታሪክ ስብራትን በማረም ኢትዮጵያን ከገናና ታሪክና ሥልጣኔዋ የማስታረቅ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በማጠናከር የአፍሪካን ኢኮኖሚ ውህደት ለማሳለጥ በምታደርገው ጥረት የባሕር በር ባለቤትነት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄው ዓለም አቀፍ ቅቡልነት እያገኘ መሆኑን በማንሳት፤ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙኅን የጉዳዩን አስፈላጊነት በቅጡ መገንዘባቸውን አብራርተዋል።
ምክክሩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል እሳቤና ዝግጁነት የተሰነቀበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው- ምሁራን
Sep 17, 2026 514
ቦንጋ፣ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ እሳቤ የተሰነቀበትና ለሀገር ግንባታ የዜጎች ሁሉ ዝግጁነት የታየበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን የታሪክና የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን ገለጹ። በአዲስ አበባ የተካሄደውና ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ጉባኤተኞች የተሳተፉበት የምክክር ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። የዘንድሮውን አዲስ ዓመት የተቀበልነው ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የጋራ ቃል ኪዳን የተሰነቀበት ታሪካዊ ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። በአዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ በመሰነቅ፤ በህብረ ብሄራዊ አብሮነት በመድመቅ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በመቀበል ሌላ የህይወት ምእራፍ የተጀመረበትም ነው ማለት ይቻላል። የዘንድሮው አዲስ ዓመት ኢትዮጵያዊያን በችግሮቻቸው ላይ መክረው ለመፍትሄው የጋራ አቋም የያዙበት፤ አዲስ መንግስት የሚመሰረትበትና ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባት ሂደት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ነው። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን፤ አዲሱ ዓመት በምክክር የተሸጋገርንበትና እንደ ዜጋም ለሀገራዊ ልማት ትልቅ ተስፋ የተሰነቀበት ነው ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካና አለም አቀፍ ግንኙነት የትምህርት ክፍል መምህር ዘሪሁን ያሬድ፤ ለሀገራዊ ችግሮች እልባት ለማበጀት ምክክርን ሁነኛ መፍትሄ ለማድረግ ወደ ምክክር መገባቱ በራሱ ዘመናዊ እሳቤ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ስኬታማ መሆን የተቻለበት ታሪካዊ አጋጣሚ መፈጠሩን አንስተው በችግሮች ላይ መክረንና ለእልባቱ ተዘጋጅተን ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገራቸው ለሁላችንም ትልቅ ተስፋ ነው ብለዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ እሳቤ የተሰነቀበትና ለሀገር ግንባታ የዜጎች ሁሉ ዝግጁነት የታየበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑንም ገልጸዋል። የምክክሩ ዓላማ ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታት ጥረት መሆኑን አንስተው ከሃይል አማራጭ ይልቅ በውይይት የሚያምን ትውልድ በመፍጠርና ሀገር በመገንባት ሂደትም ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል።   በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር ሰለሞን ማሞ፤ ሀገራዊ ምክክሩ የግጭትና የጦርነት አዙሪት የሚያበቃበትን እድል የፈጠረና ምክክር የችግሮች ሁሉ አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን ሁሉም የተረዳበት መሆኑን ገልጸዋል። በምክክሩ የታየውና ሁላችንም የተገነዘብነው የዜጎች እሳቤ ከምንም በላይ ሀገርን ያስቀደመና ለችግሮች ሁሉ ዘላቂ መፍትሄን መሻት መሆኑን ነው ብለዋል። በመሆኑም በአዲስ ዓመት፤ አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ለተመከረባቸው አጀንዳዎች በሂደት ተፈፃሚነት በጋራ መትጋት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።    

ማህበራዊ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
Sep 18, 2026 123
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የክልሉን የቱሪዝም መስህቦች በጋራ ለማስተዋወቅ የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢዜአ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም እሸት ሽመልስ እና የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ ተፈራርመውታል። የኢዜአ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም እሸት ሽመልስ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፤ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጀምሮ ለዘርፉ የተሰጠውን ልዩ ትኩረትና ቦታ በመረዳት ወደ ሥራ የገባ ተቋም ነው። ኢትዮጵያ ያላትን በርካታ የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ለአፍሪካና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በርካታ የዴሞክራሲና የአስተዳደር ትምህርቶችን ሊሰጥ የሚችለውን የገዳ ስርዓት ለአብነት መጥቀስ እንደሚቻል አብራርተዋል። የኢዜአ ዋና ተልዕኮዎች ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እና የሀገርን በጎ ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህንም በ"ፐልስ ኦፍ አፍሪካ" (Pulse of Africa) ሚዲያ ለአፍሪካውያንና ለዓለም ማህበረሰብ እንደሚያስተዋውቁ ተናግረዋል። ይህ ስምምነትም እነዚህን ተልዕኮዎች በተግባር ለመወጣት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የሚያከናውናቸውን ሀገር ተሻጋሪ ሥራዎች በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ በበኩላቸው፤ አንጋፋውና ሰፊ ተደራሽነት ያለው ኢዜአ ከኮሚሽኑ ጋር መስራቱ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል። የቱሪዝም ዘርፉ ያለ ፕሮሞሽን እና የመረጃ ተደራሽነት ሊያድግ እንደማይችል ገልጸው፣ ከኢዜአ እና ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር የተደረገው አጋርነት የስራውን ውጤታማነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተናግረዋል። ሁለቱ ተቋማት የቱሪዝም አጀንዳዎችን በጋራ እንደሚያስፈጽሙና ቱሪዝምን የአፍሪካ ህዝቦችን ማስተሳሰሪያ መንገድ አድርገው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ራሱን የቻለ የኤግዚቢሽን ቦታ እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ከሚመጡ ጎብኚዎች ጋር ትስስር እንዲፈጠር ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል።
ሀገር የሚገነባው እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ድርሻ ሲወጣ ነው
Sep 18, 2026 99
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2019(ኢዜአ) :- ዛሬ ላይ የምንሰራው የበጎ ፈቃድ ተግባር የዜጎችን ችግር ከመፍታት ባሻገር ለነገው ትውልድ የመተባበርና የመረዳዳት ባህልን ይተክላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ። ጽሕፈት ቤቱ በክልሉ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በገመገመበት ወቅት ኃላፊው እንደተናገሩት 209 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸውና የዜጎችን ችግር ያቃለሉ የበጎ ፈቃድ ተግባራት በክልሉ ተከናውነዋል።   ሀገር የሚገነባው እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ድርሻ ሲወጣ ነው ያሉት አቶ ጌቱ አንድ ወጣት ጊዜውን ሲሰጥ፣ አንድ ባለሙያ እውቀቱን ሲያካፍል፣ አንድ ዜጋ የተቸገረን ወገን ሲደግፍ፣ አንድ ሰው አካባቢውን ሲያፀዳ ወይም ችግኝ ሲተክል በተደመረ ውጤት የሀገር ግንባታ እንደሚሆን አስረድተዋል። በዚህ መርህ የምንከውነው የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር የአንድ ወቅት ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፣ በመረዳዳትና በመተባበር የሀገር ፍቅርን በተግባር የምናሳይበት መድረክ ነው ብለዋል።   ወጣቶች፣ ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች፣ የሀገር አገልጋዮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ለማህበረሰብ እያበረከቱ መሆኑንም ገልጸዋል። የምንሰራው በጎ ተግባር ዛሬ ላይ የዜጎችን ችግር ከመፍታት ባሻገር ለነገ ትውልድ የመተባበርና የመረዳዳት ባህልን የሚተክል በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። በአንድነት የጀመርነውን የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር በክረምት ሳንገድበው በየቀኑ በየቦታው የምንኖረውን የመረዳዳት ባህል እንገንባ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአካል ጉዳተኞችን የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚደረጉ እገዛዎች ተጠቃሚነትን እያሳደጉ ነው
Sep 18, 2026 216
ሰመራ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- የአካል ጉዳተኞችን የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚደረጉ እገዛዎች ተጠቃሚነትን እያሳደጉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ገለፀ። ኢትዮ ቴሌኮም በአፋር ክልል በሠመራ ከተማ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። በርክክብ ስነ ሰርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ ብርሃኑ ንጉሴ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሁሉንም አካላት የነቃ ተሳትፎን ይጠይቃል።   በዚህ ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም ያደረገው ድጋፍ የተማሪዎቹን ውጤታማነት ከማሳደግ ባለፈ ማህበራዊ ኀላፊነትን መወጣት ያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል ። የአካል ጉዳተኞችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚደረጉ እገዛዎች አብሮነትን የሚያጠናክሩ ተደማሪ አቅም መሆናቸውን ጠቁመዋል። ፌዴሬሽኑ በትምህርት ዘመኑ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ለማሳደግ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ስር ለሚገኙ 10 ሺህ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የግብአት ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል።   የአፋር ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ነስሮ ኡዳ እንዳሉት፤ በክልሉ ልዩ ትኩረት የሚያሻቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ ነው። ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ማህበራዊ ጫና ለማቃለል ለ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ መሰራቱን አንስተዋል። ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማህበራዊ ሀላፊነትን በመወጣት ብቁ ዜጋን ለማፍራት ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል።   በኢትዮ ቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ተወካይና የገመድ አልባና መሰረተ ልማት አገልግሎት ዘርፍ ኀላፊ አቶ ሱራፌል አረፈ ሸዋ፤ በበኩላቸው ኢትዮ ቴሌኮም ከመደበኛ ስራው በተጓዳኝ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት አጋርነቱን እያሳየ ነው ብለዋል። የተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያግዛቸው የተናገሩት ደግሞ ተማሪ ኡስማን ሁሴንና ዓሊ መሐመድ ናቸው።
በምስራቅ ቦረና ዞን ከ57 ሺህ በላይ ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋል
Sep 18, 2026 133
ነገሌ ቦረና ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):-በምስራቅ ቦረና ዞን ከ57 ሺህ በላይ ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በህመም ጊዜ ለከፍተኛ የህክምና ወጪ እንዳይጋለጡና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በቅናሽ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘረጋ ስርዓት ነው። በተለይም በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍልና መደበኛ ባልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ለተሰማሩ ዜጎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማረጋገጥ በኩል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በምስራቅ ቦረና ዞንም የህብረተሰቡን የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግና የአባልነት ክፍያን በማቀላጠፍ የመድህን ሽፋኑን ወደ ሁሉም ወረዳዎችና ገጠር ቀበሌዎች ለማስፋፋት ሲሰራ ቆይቷል። በዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት የሀብት ማመንጨትና የህብረተሰብ ተሳትፎ አስተባባሪ አቶ ነጋሽ ቀነኒ፤ ዘንድሮ ወደ 102 ሺህ ለሚጠጋ አባወራ የጤና መድህን ሽፋን ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡   እስካሁን በተደረጉት እንቅስቃሴዎች ነገሌ ቦረና ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች 57 ሺህ 453 ዜጎች የጤና መድህን ሽፋኑ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ከ7 ሺህ 450 በላይ የሚሆኑት የጤና መድህን አገልግሎት ሽፋን ያገኙ አዳዲስ አባላት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም 50 ሺህ 100 አባወራዎች የጤና መድህን ሽፋኑ ተጠቃሚ የነበሩና የአገልግሎቱን መታወቂያ ያደሱ ነባር አባላት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚተዳደሩ ለ12 ሺህ 54 አባወራዎች የጤና መድህን ሽፋን ቅድመ ክፍያ በወረዳና በከተማ አስተዳደር መሸፈኑን ጠቁመዋል፡፡ በዞኑ በሚገኙ 3 ሆስፒታሎችና በ28 ጤና ጣቢያዎች አመቱን ሙሉ ነጻ የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ ተደራሽ እንደሆነም አስተባባሪው አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሀዋሳ፣ ሜጋ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ደሎ መና፣ ጎባ ስፔሻልይዝድ እና ከጎባ ሪፈራል ሆስፒታሎች ጋር ስምምነት ተፈራርመው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ነገሌ ቦረና ከተማን ጨምሮ ሁሉም ወረዳዎች 13 አዳዲስ የማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤቶች መክፈታቸውንም ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ባለፈው አመት የጤና መድህን ሽፋን ያገኙ 370 ሺህ 273 ዜጎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውንም አስታውሰዋል፡፡   ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አበበች ወርቁ፤ አመታዊ ቅድመ ክፍያ በመፈጸም ሙሉውን ዓመት ከሶስት ቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር የጤና መድህን ሽፋን ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ የዚሁ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ታሪኳ ደምሴ የጤና መድህን አባል በመሆናቸው ሳይቸገሩ ነጻ የህክምና ክትትል ለማድረግ እንደቻሉ ተናግረዋል። የጤና መድህን ሽፋን ሳይታሰብ ድንገኛ ህመም ሲያጋጥም ታክሞ ለመዳን እለታዊ ወጪን የማይጠይቅ በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የጤና መድህን አገልግሎት የምርመራ፣ የመድሃኒትና ሌሎች የህክምና ወጪ ስለሚሸፈን ኢኮኖሚያዊ ችግርን የማቃለያ መሳሪያ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ኢኮኖሚ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ይጠናከራሉ
Sep 18, 2026 199
ሆሳዕና ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ያለፈውን በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሄዷል።   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ንጉሤ አስረስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት በመቀየር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ተግባራት ይጠናከራሉ። በተለይም በዘርፉ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአሠራር እና የድጋፍ ማዕቀፎች መዘርጋታቸውን ጠቁመዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራውን ለማበረታታትም ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ የተግባር ሥልጠና እንዲሰጡ መደረጉን ጠቅሰዋል። በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።   የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በበኩላቸው፤ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። በዚህም በግብርና፣ በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከ450 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ከ5 ሺህ 900 ሄክታር በላይ መሬት እና 600 የሚጠጉ ሼዶች ለኢንተርፕራይዞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል። ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት መዘጋጀቱን እና ቀደም ባሉት ዓመታት ሼዶች ወስደው ሀብት ያፈሩ አንቀሳቃሾችን ለማሸጋገር ግብ ተይዞ ወደ ትግበራ ምዕራፍ መገባቱንም ኃላፊው ገልጸዋል። የስልጤ ዞን የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ወርቅቾ፣ ዞኑ በሥራ ዕድል ፈጠራ ያሉ ጸጋዎችን ለይቶ በመጠቀም ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም ወጣቶችን በሥራ ዕድል ፈጠራው ተጠቃሚ ለማድረግ ከ1 ሺህ 350 ሄክታር በላይ መሬት እና ከ150 በላይ አዳዲስ ሼዶችን ገንብቶ ለማስረከብ ታቅዷል ብለዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።      
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ9ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ተሸለመ
Sep 18, 2026 178
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመት በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ሽልማትን አግኝቷል። አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ እና በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት ሽልማቶችንም ተቀብሏል። የአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የSKYTRAX የዓለም አየር መንገድ ሽልማቶች ላይ ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመት በመመረጥ የአህጉሪቱ ቁጥር አንድ አየር መንገድነቱን አረጋግጧል። ከዚህ ታላቅ እውቅና በተጨማሪ አየር መንገዱ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎችም ሽልማቶችን አግኝቷል። ሽልማቶቹም በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ አየር መንገድ፣ በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት አሰጣጥ እና በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ የሚሉት ናቸው፡፡ ሽልማቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጥራት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያላቸውን እምነትና ታማኝነት ያንፀባርቃሉ። ዕውቅናው አየር መንገዱ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት፣ ልዩ የደንበኞችን እርካታ ለመጠበቅ እና በዓለም አቀፍ አውታረ መረቡ ውስጥ እንከን የለሽ የጉዞ ልምድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው። በተጨማሪም የአየር መንገዱን ሰራተኞች ያላሰለሰ ጥረት የሚያጎላ ሲሆን፣ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የአቪዬሽን ቡድን መሆኑን ያረጋግጣል። ሽልማቶቹ አየር መንገዱ የአገልግሎቶች እና የአሠራሮች ደረጃ በመጠበቅ ረገድ ያለውን ቁርጠኛነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
በቡና የወጭ ንግድ የተመዘገበውን አበረታች ስኬት በቅመማ ቅመም መድገም የሚያስችል የምርታማነት አቅም እየተፈጠረ ነው
Sep 18, 2026 98
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):-በቡና የወጭ ንግድ የተመዘገበውን አበረታች ስኬት በቅመማ ቅመም ዘርፍም መድገም የሚያስችል የምርታማነት አቅም እየተፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የቅመማ ቅመም ዘርፉን ስልታዊ በሆነ መንገድ ለማዘመን አጠቃላይ ጥረቶች መጀመራቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ሮዝመሪ፣ ኮረሪማ፣ ጥቁር አዝሙድ እና ዝንጅብልን ጨምሮ 16 የተለያዩ የቅመማ ቅመም ዓይነቶች ለውጭ ገበያ እየቀረቡ ይገኛሉ። ባለፈው የበጀት ዓመት ብቻ ከዚህ ዘርፍ 17 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ አሁን ላይ ይህንን አፈጻጸም ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ለማሳደግ ታቅዶ እየተሠራ ነው። ለእነዚህ 16 የቅመማ ቅመም ዓይነቶች የሚሆን ዘመናዊ የአመራረት፣ የጥራት አጠባበቅ እና የገበያ ሥርዓት ፓኬጆች ተዘጋጅተዋልም ብለዋል። እነዚህን አዳዲስ ፓኬጆች ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችሉ ዝርዝር መመሪያዎችም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ተግባራዊነቱን ውጤታማ ለማድረግም በአርሶ አደሮች እና በግብርና ባለሙያዎች ላይ ያተኮረ ሥልጠና መሰጠቱን ጠቅሰዋል። በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል የምርት ጥራት ወሳኝ በመሆኑ ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓቶች እየተዘረጋ ይገኛል ብለዋል። በዚህ ረገድም ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በምርት ጥራት ቁጥጥር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት መፈረሙን አስታውቀዋል። አሁን ላይ በዓመት የሚመረተው የቅመማ ቅመም መጠን 10 ሺህ ቶን የደረሰ ሲሆን፣ ይህንን ወደ 13 ሺህ ቶን ከፍ ለማድረግና መዳረሻ ገበያዎችን ለማስፋት ግብ ተይዞ እየተሠራ ነው ብለዋል። በድህረ ምርት ዙሪያ ለአርሶ አደሮች በፓኬጅ የተደገፉ ሥልጠናዎች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች የኢትዮጵያን የቅመማ ቅመም ምርቶች ተወዳዳሪነት በማሳደግ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ከፍ እንደሚያደርጉት ይጠበቃልም ነው ያሉት።      
የሶማሌ ክልልን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች በብቃትና በጥራት እየተፈጸሙ ነው
Sep 18, 2026 196
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- የሶማሌ ክልልን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች በብቃትና በጥራት እየተፈጸሙ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በፌዴሬሽን ምክር ቤትና ተጠሪ ተቋማት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል። አፈ ጉባዔው በዚሁ ወቅት፤ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ዜጎች የነበረባቸውን የቤት ችግር በመቅረፍ አስተማማኝ መጠለያ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ብለዋል። ፌዴሬሽን ምክር ቤትም በክልሉ ከአቅመ ደካማ ወገኖች የቤቶች ግንባታ በተጨማሪ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። እንዲሁም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካባቢን በመጠበቅ ለቀጣይ ትውልድ የሚጠቅም መሠረት በመጣል የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። የሶማሌ ክልል በመደመር መንግሥት የአስተዳደር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች እውን የሚሆኑበት ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። በዚህም የክልሉን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ተገንብተው የሕዝብን የልማት ጥያቄ በመመለስ ለአገልግሎት መብቃታቸውን አስረድተዋል። ለአብነትም በማኅበራዊ ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የጤና ተቋማት ግንባታን በማስፋፋት ሕብረተሰቡ በአቅራቢያው የሕክምና አገልግሎት የሚያገኝበት ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በመንገድ፣ በአየር ማረፊያ መሠረተ ልማቶችና በኢንቨስትመንት ፍሰት የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎች መመዝገባቸውን አብራርተዋል። የመደመር መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ጀምሮ ማጠናቀቅ ዋነኛ መለያው መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህም የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት እያሻሻለ መሆኑን አብራርተዋል። የሶማሌ ክልል ሕዝብ ለዘላቂ ልማትና ሰላም ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት አፈ ጉባዔ አገኘሁ፤ በቀጣይም ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማት የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሕብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር በልማት ሥራዎች ያለውን ተሳትፎ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መንግስት ለህዝብ የሰጠው ፈጣንና ቁርጠኛ ምላሽ
Sep 18, 2026 198
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መንግስት ለህዝብ የሰጠውን ፈጣን እና ቁርጠኛ ምላሽ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ተገልጋዮች ገለጹ። መንግስት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ባደረገው ጥረት ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ተቋማትን በመገንባት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ለዚህም ማሳያ የሆነው የመሶብ አገልግሎት እጅግ ፈጣን እና ቀልጣፋ በመሆኑ በዜጎች ዘንድ ትልቅ እርካታን ፈጥሯል። በተለይም የተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት ነዋሪዎች ወደ መንግስት ተቋማት መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ሆነው ጉዳያቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈጽሙ ምቹ ሁኔታን መፍጠር የቻለ ነው። የተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት በአካባቢያቸው ሲያገኙ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎችም መንግስት ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በፍጥነት መቅረፉ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል አቶ ታምሩ አሰፋ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ይሰጥ የነበረው የመንግሥት አገልግሎት ረጅም ጊዜ የሚወስድና ለእንግልት የሚዳርግ እንደነበር አስታውሰዋል።   አሁን ላይ አሠራሩ እጅግ ዘመናዊ በመሆኑ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል። በተለይ የተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት በመኖሪያ አካባቢዎቻቸው የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት መቻሉ የበለጠ እርካታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።   ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ታምራት ከበደ በበኩላቸው፤ የተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት አሰጣጡ ከአቀባበል ጀምሮ ያለው መስተንግዶ ቀደም ሲል ከነበረው አሠራር ፈጣን እና ቀልጣፋ መሆኑን ጠቁመው፣ በተሰጣቸው አገልግሎት እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል። በተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ መገልገላቸውን የተናገሩት አቶ ዋበላ ሐጂከድር፤ አገልግሎቱን ባጠረ ጊዜ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።   መንግሥት ለህዝብ ፈጣን አገልግሎት በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ካውንተር ባለሙያ ደርቤ ፋንታሁን፤ ቀደም ሲል ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋሙ በአካል ለመሄድ ይገደዱ እንደነበር ያስታውሳሉ።   አሁን በተዘረጋው ተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመታገዝ በርካታ ተቋማትን ባቀናጀ መልኩ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።   በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የሁሉ አገልግሎት ባለሙያ ሃና ተፈራ፤ እስካሁን ድረስ ወደ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በመንቀሳቀስ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ እያረጋገጥን እንገኛለን ብለዋል። የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ዓለማየሁ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ተበታትነው የነበሩ የመንግሥት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ በአንድ ማዕከል ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረው የመሶብ አገልግሎት ከፍተኛ ሀገራዊ ውጤት እያስመዘገበ ነው።   ይህም በመሶብ ማዕከላት በአካል በመሄድ መገልገል ለማይችሉ ዜጎች መኖሪያ አካባቢያቸው ድረስ ሄዶ ማገልገል የሚቻልበት ሥርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል። ይህ አሠራር በአካል መገኘት ለማይችሉ ዜጎች ትልቅ ዕድል የፈጠረ በመሆኑ በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ አቶ ዮናስ ዓለማየሁ አረጋግጠዋል።      
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ተማሪዎች በፈጠራ ስራዎች ላይ በስፋት እንዲሳተፉ እያገዘ ነው
Sep 18, 2026 251
ጅማ ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):-የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ተማሪዎች በዘርፉ ያላቸውን እውቀትና ግንዛቤ በማሳደግ በምርምርና በፈጠራ ስራዎች ላይ በስፋት እንዲሳተፉ እያገዘ መሆኑን ገለጸ። በአሁኑ ወቅት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚ፣ በጤና፣ በእርሻ እና በትምህርት ዘርፎች ፈጣን ለውጥ እያመጣ የሚገኝ ቁልፍ የፈጠራ መሳሪያ ነው። በኢትዮጵያም ሀገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት እና የኢንዱስትሪ አብዮት ተሳትፎን ለማሳደግ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አቅም ያላቸውን ወጣቶች ማፍራት ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል። የጅማ ዩኒቨርሲቲም ይህንን ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ሀገራዊ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የተማሪዎችን የፈጠራና የምርምር አቅም ለማጎልበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል አቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።   ማዕከሉ ተማሪዎች የንድፈ ሐሳብ እውቀትን ከተግባራዊ ልምድ ጋር እንዲያናብቡ፣ በችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ እንዲሰማሩ እና በዲጂታል ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው። በዩኒቨርሲቲው የማዕከሉ ዳይሬክተር ኢንጂነር ጃርሚያ ባይሳ እንዳሉት፤ የዩኒቨርሲቲው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ተማሪዎች በዘርፉ የሚያሳዩትን እውቀትና ግንዛቤ ለማጎልበት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።   ማዕከሉ ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ የፈጠራ ስራዎችንና ሶፍትዌሮችን እንዲያበለጽጉ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል ። እንዲሁም ልዩ ልዩ እውቀትና ግንዛቤ ያላቸው ተማሪዎች በአንድ የስራ ቦታ በመሰባሰብ ልምድ የሚለዋወጡበት እድል ማመቻቸቱን ጠቁመዋል። በተጨማሪም ተማሪዎች በማዕከሉ የስራ ላይ ልምምድ የሚያደርጉበትን እድል በመፍጠር፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመስራት ተግባራዊ ልምድና እውቀት እንዲገበዩ እያደረገ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። በዓመት ሁለት ጊዜ ደግሞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ የሃካቶን ውድድር በማዘጋጀት፣ ተማሪዎች በፈጠራ እንዲወዳደሩና የልዩ ልዩ ሽልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል እያመቻቸ እንደሚገኝም ገልጸዋል። የማዕከሉ እንቅስቃሴዎችም በዩኒቨርሲቲው ጊቢ ብቻ የተገደቡ አለመሆናቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፣ ተማሪዎችና መምህራን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ተጨባጭ የማህበረሰብ ችግሮችን የሚፈቱ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች ላይ በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   ከተከናወኑ የፈጠራ ስራዎች መካከል በቡና ላይ የሚከሰቱ በሽታዎችን ቀድሞ ለመለየት፣ መፍትሄ ለመስጠት እና የቡና ደረጃን ለመወሰን የሚያገለግለው "ደቦ ቡና አፕ" ፈጠራን ለአብነት አንስተዋል። እንዲሁም ባህላዊ ጨዋታዎችን በሮቦቲክስ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት በማቀናጀት የሚያቀርብ ፕሮጀክት፣ የአፈርን ይዘት በመለየት ተስማሚ የምርት አይነት የሚያመላክተው "ኦሚሽቱ ጆይ አፕ" እና የእንስሳትን ጤና እና በሽታ ለመከታተል የተሰሩ ፈጠራዎች እንደሚገኙበትም አመልክተዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ እነዚህና ሌሎች ፕሮጀክቶች በተማሪዎችና መምህራን ንቁ ተሳትፎ የሚከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ስራዎቹ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሽልማቶችና እውቅናዎችን ማጎናጸፋቸውን ጠቁመዋል። ማዕከሉ በቀጣይም ተማሪዎች፣ መምህራንና ተመራማሪዎች በዘርፉ የታገዙ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን እንዲያከናውኑና በርካታ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ ጀማሪ ድርጅቶች (ስታርት አፕስ) እንዲቋቋሙ በትኩረት እንደሚሰራ ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።   ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ የተመረቀችውና በተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ላይ ስትሳተፍ የቆየችው ወጣት ኢክራም አልቃድር፣ በማዕከሉ የነበራት ቆይታ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ እንድታካብት እንደረዳት ገልጻለች። በአሁኑ ወቅትም በግል ተቋም ውስጥ በዘርፉ ተሰማርታ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ላይ ትገኛለች። ሌላኛው ወጣት አደም ሰይድ በማዕከሉ ያገኘውን እውቀትና ልምድ በመጠቀም 'ክሬቲቭ ሀብ' በተሰኘ ተቋም ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በሶፍትዌር ማበልፀግ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለጸው ወጣቱ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ለስኬቱ ትልቅ መሰረታዊ እውቀት እንዳበረከተለት ጠቅሷል።
 የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው
Sep 17, 2026 353
ድሬደዋ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አስታወቁ። በድሬደዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ከወረቀት ንክኪ የፀዳ የዲጂታላይዜሽን አገልግሎት ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።   አገልግሎቱ በተጀመረበት ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል መስሪያ ቤት አመራሮች ተገኝተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ትግበራው የፍትህ ስርዓቱን ተደራሽ፣ ግልፅና ውጤታማ በማድረግ የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ እያስቻለ ይገኛል። የፍርድ ቤቶች አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው ጉዳያቸውን የሚከታተሉበትን ስርዓት ለመዘርጋት እንዳስቻለም ነው የጠቀሱት። በተለይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውስጥ የተጀመረውን የስማርት ኮርት ስርዓት በመላው አገሪቱ በማስፋት ፈጣንና ግልፅ የፍትህ አገልግሎት በማስፈን የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ማስቻሉን ገልጸዋል።   የፍርድ ቤቶችን መረጃ አያያዝ ለማዘመን ተግባራዊ የተደረጉ የዲጂታል አገልግሎቶችም ፈጣንና ተደራሽ ፍትህን ለማስፋት እንዳስቻሉም ነው የገለጹት። ዛሬ በድሬደዋ ተመርቆ ወደ አገልግሎት የገባው የዲጂታል አገልግሎት አሰራር በክልሎች የተጀመሩትን አበረታች ውጤቶች በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ለተከናወኑት ተግባራት ማሳያ እንደሚሆንም አንስተዋል። የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎቶች የፍትህ ስርዓቱን ግልፅነትና ተጠያቂነት ከማስፈን ባሻገር፣ ተገልጋዮች ካሉበት ስፍራ ሆነው መረጃዎችን ለማግኘት እያስቻሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።   የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፤ የፍርድ ቤቶችን አሰራር ዲጂታላይዝ ማድረግ ፍትህን በእኩልነት፣ በግልፅነት እና በቅልጥፍና ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም ፍርድ ቤቶች ከወረቀት ንክኪ የፀዳ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። በድሬዳዋ በተካሔደው የፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ይፋዊ ጅማሮ እና ጉብኝት ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሙክታር እና ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች፣ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል ዘመናዊ አሠራር የተገልጋዮችን እንግልትና የጊዜ ብክነት አስቀርቷል
Sep 17, 2026 143
ጅማ ፤መሰከረም 7/2019 (ኢዜአ)፡- የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል አሠራሩን የዘመነ በማድረጉ ተገልጋዮች እንግልትና የጊዜ ብክነት ሳይገጥማቸው ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ገለፁ። የከተማዋ ተገልጋዮች እንደገለጹት፣ በመሶብ የአንድ ማዕከል የሚሰጡ የህዝብ አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከሩ፣ እየዘመኑ እና ቀልጣፋ እየሆኑ መጥተዋል። ማዕከሉ በርካታ መሥሪያ ቤቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር በማስተሳሰሩ፣ ተገልጋዮች ከቢሮ ቢሮ ያጋጥማቸው የነበረውን እንግልት፣ አላስፈላጊ ወጪና የጊዜ ብክነት ማስቀረት ችሏል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ተስፋዬ በቀለ እንደገለጹት፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት የነበረው ቢሮክራሲያዊ አሰራር ለአላስፈላጊ እንግልትና የጊዜ ብክነት ይዳርግ ነበር።   በአንድ ዓመት ውስጥ አንድን ጉዳይ ለማስፈጸም ከስድስት ወር በላይ ይመላለሱበት የነበረበት ወቅት እንደነበር በማስታወስ፣ የማዕከሉ መቋቋም ያንን ውጣ ውረድ በመቅረፍ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ቀደም ሲል ወደ ማዕከሉ ያልገቡ ተጨማሪ የመንግሥት ሴክተሮች አሁን ላይ ተካተው አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው፣ የማዕከሉ የአሰራር አቅምና የተቀላጠፈ አገልግሎት የመስጠት አቅም ይበልጥ መጠናከሩን ጠቁመዋል። ወይዘሮ መሬማ መሀመድ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ እጅግ ያስጨንቀን ነበር ብለዋል።   በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚታየው ያልተገባ አሰራር ለእንግልትና ንብረት ብክነት ሲዳርገን ቆይቷል ያሉት ወይዘሮ መሬማ፤ ዛሬ ግን ወደ መሶብ አንድ ማዕከል ስንሄድ በፍፁም መተማመንና በደስታ ነው ብለዋል። የማዕከሉ ሠራተኞች ለባለጉዳይ ትልቅ ትኩረት መስጠታቸው እንዲሁም አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የታገዘና ፈጣን መሆኑ ከምንም በላይ አስደሳች ነው ብለዋል። አገልግሎቱ በየጊዜው እየዘመነ መጥቷል ያሉት ደግሞ የጅማ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ አለምነሽ ዲኮ ናቸው።   ለሦስት የተለያዩ ጉዳዮች ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውንና ሦስቱንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ አጠናቀው መመለሳቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። ወጣት ሚፍታ አብዱልቃድር በበኩሉ መሶብ የአንድ ማዕከል ለአቅመ ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹና አግባብነት ያለው አሠራር መዘርጋቱን ጠቁሞ፣ ያለምንም መጉላላት ገብቶ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት መቻሉን ተናግሯል።   የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሰራተኞች ሊና አብዱለዚዝ እና ሀናን አሙቲ፤ ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ ሲመጡ አገልግሎቱን አጠናቀው ለመውጣት ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ብቻ እንደሚወስድባቸው ገልጸዋል።   አሠራሩ ዲጂታላይዝ የሆነና ፈጣን በመሆኑ ተገልጋዮች ለእንግልትና ለጊዜ ብክነት እንደማይዳረጉ የጠቀሱት ሠራተኞቹ፤ እያንዳንዱ ሠራተኛ አገልግሎት የሰጠበት ደቂቃ እየተለካ የሚገመገም በመሆኑ ምንም ዓይነት የአገልግሎት ክፍተት አይፈጠርም ብለዋል። የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አብዲ ሰለሞን፤ ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ከ135 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ማስተናገዱን ገልጸዋል። እንዲሁም በማዕከሉ ይሰጡ የነበሩት አገልግሎቶች ከ135 ወደ 139 የደረሱ ሲሆን፤ ወደ ማዕከሉ የገቡት ሴክተሮች ደግሞ ከ25 ወደ 29 ማደጋቸውን አስረድተዋል።
ስፖርት
የዘንድሮው የኢሬቻ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መስከረም 21 ቀን በቢሾፍቱ ይካሄዳል
Sep 18, 2026 197
ቢሾፍቱ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፡-የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ መስከረም 21 ቀን በቢሾፍቱ ከተማ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ። የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2019 ዓ.ም የ2ኛውን የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዴ አዳራሽ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።   በመግለጫው ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባ ገዳዎችና ታዋቂ አትሌቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በዓሉ የባህል እሴትን ከስፖርት ጋር በማጣመር በደመቀና በተዋበ ሁኔታ እንዲከበር የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተገልጿል። የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ እንደገለጹት፤ የኢሬቻ በዓል እና የስፖርት እንቅስቃሴዎች የባህል ዕሴቶችን ለማበልጸግ፣ ፍቅርና ወንድማማችነትን ለማጠናከር እንዲሁም አገራዊ ኢኮኖሚን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው። አክለውም፣ ኢሬቻ የህዝቦችን አንድነት እና ፍቅር በማጽናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሀገራዊ መግባባትን ለመገንባት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አብራርተዋል።   በዘንድሮው የ2ኛው የኢሬቻ ሩጫ ውድድር እስከ 6ኛ ደረጃ ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች ልዩ ልዩ ሽልማት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ በተጨማሪም የዲባባ ቤተሰቦች የኢሬቻ ሩጫ አምባሳደር መሆናቸውን ገልጸዋል። ቢሮውም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2019 የኢሬቻ በዓልን በታላቅ ቅንጅት ለማክበር ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ 2ኛው የኢሬቻ ታላቅ ሩጫ መሆኑንም አብራርተዋል። የጎዳና ላይ ሩጫው ዋና ዓላማ የኢሬቻ በዓል ባህላዊና ሥነ-ምግባራዊ እሴቱን ጠብቆ ከማከበር ጎን ለጎን ከስፖርት ጋር በማያያዝ ለተከታዩ ትውልድ ለማስተላለፍና የህዝቡን ባህል ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል። የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ በበኩላቸው፤ ኢሬቻ ፍቅርና አንድነት በመሆኑ፣ በበዓሉ ምክንያት የተዘጋጀው ሩጫም ፍቅርን፣ አንድነትንና የብሔር ብሔረሰቦችን ቁርኝት ስለሚያጠናክር ህዝቡ እንዲሳተፍ ጥሪ አድርገዋል። ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ድርሻቸውን እንዲወጡና ህዝቡ በሰላም መጥቶ በሰላም እንዲመለስ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑም አመልክተዋል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስማቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠሩት የዲባባ ቤተሰቦች የኢሬቻ ሩጫ አምባሳደር ሆነው ተመርጠዋል።   አትሌቶች በአምባሳደርነታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ውድድሩን በስፋት ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል። ውድድሩ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የህዝብ ሩጫ ሲሆን የኬንያ እና የታንዛኒያ አትሌቶችን ጨምሮ በሁለቱም ጾታ አትሌቶችም ይሳተፉበታል ተብሏል።    
የ"ጊፋታ" በዓል የአብሮነት እሴቶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ይጠናከራሉ
Sep 18, 2026 155
ወላይታ ሶዶ ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):-የ"ጊፋታ" በዓል የአብሮነት እሴቶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የወላይታ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡ "የትውልድን ቅርስ እንጠብቅ፤ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል" በሚል መሪ ሐሳብ የሩጫ ውድድር በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄዷል።   በወቅቱም የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የጊፋታ በዓል የአብሮነትና የአንድነት እሴቶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ጊፋታ የኅብረ-ብሔራዊነትና የሰላም መገለጫ በመሆኑ በዓሉ አብሮነትን በማጠናከር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።   በየዓመቱ የሚካሄዱ የጊፋታ ጨዋታዎች፣ የጊፋታ ጉዞና እና የጊፋታ ሩጫን በማጠናከር በዓሉ የፍቅርና የሰላም መሆኑን የማስተዋወቅ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማርያም በበኩላቸው፤ ጊፋታ በቂ ዝግጅት በማድረግ በጉጉት ጠብቀን የምናከብረው የሕዝብ በዓል ሆኗል ብለዋል።   በመሆኑም በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸው በመሰል ሩጫ ላይ መሳተፍ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በጋራ አቅም ለማስቀጠል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። የሩጫ ውድድሩ በዜጎች መካከል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለአካባቢው ልማትና እድገት በጋራ ለመንቀሳቀስ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምኦን ስላሎ ናቸው፡፡   በዕለቱ በተካሄደ ውድድር በወንዶች ምድብ እስራኤል አባተ፣ በሴቶች ምድብ ደግሞ ምንትዋብ ወልዴ አንደኛ በመሆን አጠናቅቀዋል።   በወንዶች ምድብ ውድድር አንደኛ የወጣው እስራኤል አባተ በጊፋታ ሩጫ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፉ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል። አሸናፊዎቹ በሰጡት አስተያየት መሰል ውድድሮች በሕዝቦች መካከል ያለው ትስስር እንዲጠናከር ያደርጋሉ ብለዋል።   ጊፋታ የሕዝብ ሀብት በመሆኑ አቅማቸውን በማሳደግ የተሻለ በመሥራት ሀገርን ወክለው የኢትዮጵያን ባንዲራ በዓለም አደባባይ ለማውለብለብ በርትተው እንደሚሠሩም ተናግረዋል። በውድድሩ በሁለቱም ምድቦች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለወጡ አትሌቶች የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ብሬንትፎርድ ከቼልሲ፤የሊጉ የአምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ
Sep 18, 2026 130
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል። ምሽት አራት ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከቼልሲ በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ባለሜዳው ብሬንትፎርድ በስድስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ቼልሲ በሰባት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ የለንደን ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ11ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ቼልሲ በአራቱ ድል ሲቀናው ብሬንትፎርድ ሶስት ጊዜ አሸንፏል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ቼልሲ በ10ሩ ጨዋታዎች ላይ 15 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ብሬንትፎርድ 12 ጎሎችን አስቆጥሯል። ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ ጃንዋሪ 2026 ሲሆን በወቅቱ ቼልሲ በኮል ፓልመር እና ጆአኦ ፔድሮ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል። ብሬንትፎርድ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች፣ ቼልሲ ደግሞ ባለፉት ሁለት የሊግ መርሐ ግብሮች ማሸነፍ አልቻሉም። የለንደኖቹ ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።
አካባቢ ጥበቃ
በጋምቤላ ክልል በሚቀጥሉት ወራት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ይጠበቃል
Sep 18, 2026 172
ጋምቤላ ፤መስከረም 8/ 2018 (ኢዜአ) ፡-በጋምቤላ ክልል በሚቀጥሉት ወራት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ሊኖር እንደሚችል በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት የጋምቤላ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አስታወቀ። በክልሉ የሚኖረው የዝናብ ስርጭት ለእርሻ ስራ አወንታዊ ሚና እንዳለው ሁሉ ቅጽበታዊ ጎርፍ በመፍጠርም አሉታዊ ተጽኖ ሊኖረው እንደሚችል ማዕከሉ ገልጿል። የማዕከሉ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋሁን ዓለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት ከተያዘው መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በቀጣዮቹ ወራት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ሊኖር እንደሚችል የአየር ትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በክልሉ በተለይም በጥቅምትና ህዳር 2019 ዓም መደበኛና ከመደበኛ በላይ ጠንከር ያለ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ገልጸዋል። በክልሉ ሊኖር የሚችልው የዝናብ ስርጭት ዘግይተው ለሚዘሩና ለረጅም ጊዜ ሰብሎች አመች ሁኔታ እንደሚኖረው ተናግረዋል። እንዲሁም ለበጋ የግብርና ልማት ስራዎች እርጥበታማ አፈርን በመፍጠርና የውሃ አቅሞችን በማሳደግ ረገድ አዎንታዊ አስተዋፆ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በአንፃሩ የክልሉ መልከአ ምድራዊ አቀመማጥ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአጎራባችና በአካባቢው የሚጥለው ጠንክር ያለ ዝናብ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችለል ብለዋል። በተለይም ባሮን ጨምሮ ክልሉን አቋርጠው የሚያልፉ አራት ታላላቅ ወንዞች ሞልተው በመፍሰስ ለጎርፍ ሊያጋልጡ ስለሚችሉ በወንዞች አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል። በተጨማሪም የዝናቡ ስርጭት ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥርና የወባ በሽታ ሊጨምር ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዘርፉ ልማት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው- የውጭ ሀገራት ተመራማሪዎች
Sep 18, 2026 137
ሀዋሳ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስደናቂና በዘርፉ ልማት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን የተለያዩ ሀገራት የደን ዘርፍ ተመራማሪዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት በድምሩ 56 ነጥብ 2 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል በዘርፉ ልማት የመሪነት ሚናዋን አጠናክራ ቀጥላለች። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ለምግብ ዋስትናም መሰረት እያኖረ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀገራት የዘርፉ ባለሙያዎች፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ትልቅ ስኬት የተመዘገበበት አስደናቂ የልማት ስራ መሆኑን ገልጸዋል። ኒዘርላንዳዊው የዘርፉ ተመራማሪ አልበርት ስቼንክ፤ ኢትዮጵያ የዓለም ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ በመካላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን በተግባር እያሳየች መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስደናቂና በዘርፉ ልማት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድና ሁሉም ሊደግፈው የሚገባ መልካም ተግባር መሆኑን አንስተዋል። የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል ጉዳይ የሁሉም ሀገራት የጋራ ሃላፊነት መሆኑን የተናገሩት ተመራማሪው ሀገራት የኢትዮጵያን ፈለግ መከተል ይገባቸዋል ብለዋል። የተፈጥሮ ሀብትና ደንን ለመንከባከብ የሚደረግ ጥረት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው በአረንጓዴ ልማት ላይ የሚውል ጉልበትና ገንዘብ መልሶ የሚከፍል ሀብት በመሆኑ ሊተኮርበት እንደሚገባ አሳስበዋል። ሌላኛው ኡጋንዳዊው የደን ሃብት ልማት ተመራማሪ ሮበርት አቱጎንዛ፤ በደን ልማትና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ኢትዮጵያ ትልቅ እቅድ ሰንቃ እየሰራችና በተግባርም እያሳየች ትገኛለች ብለዋል።   የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት የዓለም ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ የመከላከል ጥረት፣ የተፈጥሮ ሃብትን የመጠበቅና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ መሰረት ሆኖ መቀጠሉ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የአፍሪካ ሀገራት በተለይም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ ልምድ በመቀመር በተባበረ አቅም የልማት ስራውን ማስቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል። በታንዛኒያ የደን ጥበቃ ፕሮግራም አስተባባሪና የደንና የተፈጥሮ ሀብት ተመራማሪ አልማስ ካሽንዲዬ፤ በኢትዮጵያ የችግኝ ተከላ እና እንክብካቤ ስራ የህዝብ አጀንዳ ሆኖ የቀጠለ አስደናቂ መርሃ ግብር ነው ሲሉ ተናግረዋል።   የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅና መንከባከብ የብዝሃ ህይወትንና የውሃ አካላትን መጠበቅ፤ የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከልና የምግብ ዋስትና መሰረት በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ሲሉ አስረድተዋል። የዘርፉ ምሁር የሆኑት ቦሊቪያዊው ሁምቤርቶ ጎሜዝ፤ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከሏቸው ችግኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ላለው የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ትልቅ ትርጉም ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።   በመሆኑም ኢትዮጵያና ዜጎቿ በአረንጓዴ አሻራ ልማት እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን አለበት 
Sep 17, 2026 458
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን እንዳለበት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢጋድ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 ለ10 ዓመታት የሚተገብረውን የቀጣናው የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት ዕቅድ እና የኢጋድ ቀጣና የግብርና ዘር ፖሊሲ የባለሙያዎች ግምገማ በማድረግ በሚኒስትሮች አጸድቋል። የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቋቋም በትብብር የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው ያለነው ብለዋል ። ኢጋድ በቀጣናው ሀገራት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ቀዳሚ መርሁ መሆኑን ገልጸዋል።   የኢጋድ የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት የ10 ዓመት ዕቅድ በቀጣናው ቀጣይነት ያለውና አይበገሬ የምግብ ሥርዓት መገንባት ያስችላል ብለዋል። የኢጋድ ቀጣናዊ የግብርና ዘር ፖሊሲም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም ዘላቂ ኢኮኖሚ ማንበር እንደሚያስችል ገልጸዋል። በአፍሪካ አህጉራዊ ሽግግር ለመፍጠር የኢጋድ ኢኒሼቲቮች ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸው ጠቁመው፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የኢጋድ ቀጣና ሀገራት ሕዝባቸውን፣ ሀብታቸውንና እውቀትን በማስተባበር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከርና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባቸው ገልጸዋል።   የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ጌታቸው ድሪባ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢጋድ ቀጣና ሀገራት በባህል፣ በታሪክና በኢኮኖሚ የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ መዋቅር ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰው፤ ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብና የግብርና ዘር ፖሊሲ ዋና አጀንዳዋ ነው ያሉት ከፍተኛ አማካሪው፤ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ገልጸዋል።  
የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ መረጃዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የተሻለ ዝግጁነት እንዲኖር በቅንጅት እየተሰራ ነው
Sep 17, 2026 227
አዳማ፤ መስከረም 7/2019(ኢዜአ )፡-የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ መረጃዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የተሻለ ዝግጁነትና ቅድመ ጥንቃቄ እንዲኖር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ የባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማና የመጪው በጋ ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ መድረክ በአዳማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።   የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት፤ ኢንስቲትዩቱ ለሀገሪቷ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጠቀሜታ ያላቸውን የአጭርና የረዥም ጊዜ የአየር ፀባይ ትንበያዎችን በወቅቱ በማቅረብ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። መረጃዎቹ በተለይም ለግብርና፣ ለውሃ ሀብት አስተዳደር፣ ለአደጋ ስጋት ቅነሳ፣ ለአቪየሽንና ትራንስፖርት፣ ለመስኖ ልማት እንዲሁም ለትምህርትና ጤና ዘርፎች እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ቁልፍ አጋዥ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም ወቅታዊና አስተማማኝ የአየር ፀባይ መረጃዎችን ለተጠቃሚው ህብረተሰብና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል። ወቅቱን የጠበቀና ትክክለኛ የአየር ፀባይ መረጃ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ወሳኝ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ባለድርሻ አካላትም በየወቅቱ ተደራሽ የሚደረጉ የአየር ፀባይ ሁኔታዎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማድረግ ሀገራችን የጀመረችው ልማትና ዕደገት እንዲፋጠን እያደረግን ያለነውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። መድረኩ የክረምት የአየር ፀባይ ሁኔታን ከመገምገም ባለፈ በመጪው የበጋ ወቅት ሊኖር የሚችለውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃን ለተጠቃሚዎች በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ ቀድመን ለማዘጋጀትና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል መሆኑንም ገልጿል። የአየር ፀባይ ሁኔታ ትንበያን መሰረት በማድረግ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎችን መውሰድ ከባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ያሉት ፈጠነ(ዶ/ር)፤ የአየር ፀባይ ተፅዕኖን ለመቋቋምና ቅድመ እርምጃ ለመውሰድ መድረኩ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።   የመጪውን የበጋ ወቅት የአየር ፀባይ ሁኔታ ትንበያ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በመጪው የበጋ ወቅት በአርብቶ አደር አካባቢዎች ለግብርና ልማት ምቹ የሆነ የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራል ብለዋል። በተለይም ምስራቅ ሐረርጌን ጨምሮ የቦረናና ጉጂ ዞኖች፣ ሲዳማና ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች በበጋ ወቅት የተሻለ የዝናብ ስርጭት ያገኛሉ ብለዋል። አብዛኞቹ የበጋ ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ዓመታዊ የዝናብ ስርጭታቸውን ከ75 በመቶ በላይ የሚያገኙት በዚህ ወቅት መሆኑን ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ይህም የአየር ፀባይ ተፅዕኖ ለመቋቋምና የውሃ ሀብትን አቅቦ ለመጠቀም ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። በዘንድሮው የበጋ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና ጉጂ ዞኖች፣ በሶማሌ ክልል ዞኖች፣ እንዲሁም በሲዳማና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች አከባቢዎች ከ75 በመቶ በላይ መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። የበጋ ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ አከባቢዎች ከመጪው ጥቅምት ወር ጀምሮ የዝናብ ስርጭቱን የሚያገኙ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 569
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።   በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 528
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 719
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 2020
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ሐተታዎች
"ጊፋታ"- ከጅምሩ እስከ ጋዜ ኦሩዋ
Sep 18, 2026 96
(በማስረሻ ሀብታሙ ከኢዜአ ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" ሕዝቡ ለዘመናት ሲያከብረው የኖረ ደማቅ ባህላዊ እሴት ነው፡፡ ጊፋታ የተጣሉና የተኮራረፉ የሚታረቁበት እንዲሁም የሕዝቦች አንድነትና አብሮነት ይበልጥ የሚጠናከርበት የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡ ጊፋታ አዲስ ተስፋና ብርሃን ጭምር ነው፡፡ አሮጌው አልፎ አዲሱን ዘመን በአዲስ መንፈስና መነሳሳት የሚቀበሉበት በጉጉት የሚጠበቅ በዓል ነው፡፡ ጊፋታ ለአብሮነትና ለሰላም እንዲሁም ለልማትና ብልጽግና በመዘጋጀት የሚቀበሉት ልዩ በዓልም ነው፡፡ በዓሉ ማኅበረሰቡ ሁለንተናዊ የሕይወት ዑደትን የሚማርበት፣ ከትናንት በመማር ለነገ የሚዘጋጅበት፣ የአብሮነትና የትስስር እሴት ነው፡፡   ያነጋገርናቸው የወላይታ ባህል፣ ታሪክና ቅርስ ባለሙያ አቶ አዳነ አይዛ እንደሚሉት፤ ጊፋታ ታላቅ፣ በኩር፣ የመጀመሪያ፣ መሻገር የሚል ትርጓሜ አለው፤ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገርን የሚያሳይ ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ይህ በዓል በወላይታ ባህላዊ የጊዜ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር መሆኑን ያብራራሉ። ዕለቱም የጨረቃንና የፀሐይን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገውን የወላይታዎች ባህላዊ የጊዜ አቆጣጠርን በመከተል የሚከበር መሆኑን ነው የሚናገሩት፡፡ ረጅም የመዘጋጃ ጊዜን የሚወስደው የጊፋታ በዓል ከአባቶች እስከ ሕፃናት በበዓሉ ዝግጅት ላይ የየራሳቸው የሥራ ድርሻ ያላቸው ሲሆን፤ የቅድመ ዝግጅት ሥራው በአብዛኛው በደቦ ይከወናል። በዓሉ በሚቃረብበት ወቅት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል እርቅ ዋናው መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያው፤ በዚህ ወቅት የተጣሉ ሰዎች እርስ በርሳቸው ታርቀው እና ጥላቻን ረስተው የጊፋታን በዓል እንደሚያከብሩ አውስተዋል፡፡ የተበደሩትን ዕዳ መክፈል ሌላኛው የጊፋታ በዓል ቅድመ ዝግጅት እንደሆነ እና ዕዳን ሳይከፍሉ ጊፋታን ማለፍ የተወገዘ ተግባር እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ ጊፋታ ከመድረሱ ሦስት ወር ቀደም ብሎ ከአሮጌው ዓመት ጉሌ ወር ላይ ወጣቶች ተሰባስበው በአካባቢው የወደቁና ከጥቅም ውጭ የሆኑ እንጨቶችን በመልቀም በአንድ ቦታ ላይ በማከማቸት በዓሉን በእሳት ብርሃን እንደ ወደፊት ተስፋ በመውሰድ ያከብራሉ፡፡ እንዲሁም በዓሉ ሲቃረብ የመታደስ ምልክት የሆነውን አካባቢያቸውን የማጽዳት ሥራ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ መኖሪያ ቤታቸውን የማሳደስና የተለያዩ ያረጁ ቁሶችን በአዲስ የመተካት ተግባር ያከናውናሉ፡፡   በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አበሻ ሺርኮ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዓሉ የሁለት ወር ጊዜ ሲቀረው አባወራዎች የእርድ በሬ በመግዛት ለተመረጠ ቤተሰብ በማስረከብ ከብቱ እንዲደልብና በደረቅ የኮባ ቅጠል በተሸፈነ ልዩ በረት በልዩ እንክብካቤ እንዲቀለብ ያደርጋሉ። በጊፋታ በዓል ዝግጅት አባቶችና ታላላቅ ወንድ ልጆች የጉሊያ እንጨት በማሰባሰብ፣ ማቆምና የማገዶ እንጨት መፍለጥ፣ ቆጮ መቁረጥ እና ሌሎችንም ሥራዎች ይሠራሉ። እናቶች እና ሴት ልጆቻቸው ደግሞ ለተለያዩ ባህላዊ ምግቦች እንሰትን መፋቅ፣ የማሽላና የበቆሎ ዱቄት፣ ዳጣ በርበሬ የማዘጋጀት፣ የተለያዩ ባህላዊ መጠጦችን እንደ ቦርዴና ጠላ ያሉትን በትላልቅ እንስራ ያዘጋጃሉ። የጊፋታ በዓል የሚከበርበት የአዲሱ ዘመን የመጀመሪያ ቀን ከሆነው እና እርድ ከሚከናወንበት የእሑድ ቀን በፊት ቅዳሜ (በወላይታ አቆጣጠር የአሮጌው ዓመት መጨረሻ ቀን) ላይ ሁሉም ሰው ንጽሕናውን የመጠበቅ ሥራ ያከናውናል፡፡ ይህ የሚደረገውም ከአሮጌው ዓመት እድፍና ቆሻሻ ጋር ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር አያስፈልግም በሚል ነው፡፡ የእርድ ዕለት እሑድ (የወላይታ ዘመን መለወጫ) ጠዋት ወፎች ዜማቸውን እንዳሰሙ የእርድ ተግባሩ መከናወን ይጀምራል፤ በዚሁ ወቅትም እናቶች ያዘጋጁት መጠጥ እና ምግብ በእርዱ ለሚሳተፉት ሰዎች ይቀርባል። አባወራዎች ሥጋውን ተከፋፍለው ወደ ቤታቸው ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም በአንድ ላይ ይበላሉ፤ ይጠጣሉ። ይህም ፍቅራቸውን ከአንድ ማዕድ በመቁረስ የሚያድሱበትና አዲሱን ዓመት የሚያበስሩበት እንደሆነ አበሻ (ዶ/ር) ይገልጻሉ። በቀጣይም ዕጣ በመጣጣል ሥጋውን ተከፋፍለው ለጊፋታ ተብሎ በሚገዛ አዲስ ቅርጫ ሥጋውን ይዘው ወደ ቤታቸው እንደሚወስዱ እና እናቶች በቤት ውስጥ የመጣውን ሥጋ ባልተበሳሳ ኮባ ቅጠል ላይ ዙሪያውን በማስቀመጥ በቆጮ፣ በቂጣ፣ በዳጣ በርበሬ አድርገው ሲያቀርቡ፤ አባት ደግሞ እማወራዋን በማጉረስ እንደሚጀምሩ ያስረዳሉ።   በጉሊያ ወር በወጣቶች የተሰበሰበው እንጨት (ጉሊያ) ለጊፋታ በዓል ሁለት ሳምንት ሲቀረው እንዲቆም የሚደረግ ሲሆን፤ በዕለቱ አመሻሽ ላይ ሁሉም በተሰበሰቡበት አባወራው ጉሊያውን በእሳት ይለኮሳሉ፡፡ ወጣቶችም ዙሪያውን በመክበብ ባህላዊ ጭፈራ ይጨፍራሉ። በቀጣዩ ቀንም በቤት ውስጥ የተረፈው ሥጋ ተዘልዝሎ ይጠበስና ማባያ ተዘጋጅቶ ሁሉም ተሰብስበው በመመገብና በመዝናናት በአንድነት ያሳልፋሉ። ከጊፋታ ቀጥሎ የሚመጣው ሦስተኛው ቀን ወይም ጪሻ ጋላሳ ደግሞ በጊፋታ ወቅት ብቻ የሚፈካ፣ በወላይታዎች አባባል ኮርማ-ጪሻ የሚባለውን ነጭ አበባ ወይም የጊፋታ አበባ ይዞ በመሄድ ዘመድ የሚጠያየቅበት ዕለት ይሆናል። ከጊፋታ ሦስተኛው ቀን ጀምሮ ደግሞ በተከታታይ ለሁለት ሳምንታት ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች በአካባቢው ታዋቂ ሽማግሌ ደጃፍ ተሰብስበው በጋዚያ ጨዋታ ያሳልፋሉ፡፡ ይህም ጋዜ ኦሩዋ በመባል ይታወቃል። ለረጅም ጊዜ የቆየው የበዓል ዝግጅትና አጠቃላይ የጊፋታ በዓል ሥነ ሥርዓት የጋዜ ኦሩዋ ጨዋታ ሲጠናቀቅ ጉሊያ በማቀጣጠል ለሚመጣው ዓመት በዓል በሰላም እንዲያደርሳቸው በመመኘት ይሸኛሉ።   ታዲያ ይህ የወላይታ ብሔር አዲስ ዓመት በዓል የሆነው "ጊፋታ" በ2018 ዓ.ም ታኅሣሥ ወር ላይ በሕንድ ሀገር ኒው ዴልሂ ከተማ በተካሄደው በ20ኛው የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ጥበቃ የመንግሥታት ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት በተባበሩት መንግሥታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተመዝግቧል። በዓሉ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖትና ማኅበራዊ ደረጃን ሳይለይ የሚያሳትፍ መሆኑ፣ ቅርሱ ተላልፎ ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ እንዲሁም በትምህርት ቤቶችና በሚዲያዎች ለትውልድ በመሸጋገር ላይ የሚገኝ መሆኑ እና ሌሎች መመዘኛዎችን በማሟላቱ ነው በዩኔስኮ መመዝገብ የቻለው። "ጊፋታ" የዓለም ሕዝብ ሀብት ሆኖ በዩኔስኮ ከተመዘገበ በኋላ የሚከበረው የዘንድሮ መርሃ ግብር በወላይታ ዘመን አቆጣጠር መሰረት የወላይታ ዘመን መለወጫ ወይም "ጊፋታ 1" ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል።    
በአትሌቲክሱ ዘርፍ ታሪክ ለመጻፍ ተስፋን የሰነቁ ታዳጊ ስፖርተኞች
Sep 17, 2026 153
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በየዓመቱ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ታዳጊዎችን በማሰልጠን ተተኪ ስፖርተኞችን እያፈራ ይገኛል። በ2019 በጀት ዓመትም በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በቦክስ፣ በፓራሊምፒክ እና በሌሎች የስፖርት ዓይነቶች ታዳጊዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ነሐሴ 2018 ዓ.ም. በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የመጀመሪያ ዙር የእጩ ታዳጊ ሰልጣኞች ምልመላ አካሂዷል። በመጀመሪያው ዙር ከተመለመሉ እጩ ሰልጣኝ ታዳጊዎች መካከል በዘንድሮ ዓመት አካዳሚውን የሚቀላቀሉ ሰልጣኞችን ለመለየት ደግሞ ከመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የመጨረሻ የምልመላ እያካሄደ ነው። የአካዳሚው አሰልጣኞችና ታዳጊ ሰልጣኞች ለኢዜአ እንዳሉት፤ አካዳሚው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ታዳጊዎች ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበት ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው።   ከአርሲ በቆጂ የመጣውና የአካዳሚውን የመጨረሻ ዙር ሥልጠና እየተወዳደረ የሚገኘው የ17 ዓመቱ ታዳጊ ዳግም ደጀኔ፤ ለአትሌቲክስ ባለኝ ልዩ ፍቅር ሀገሬን በዓለም አደባባይ ለማስጠራት ሕልም አለኝ ብሏል። የሥልጠና ምልመላ ሂደቱንም በስኬት ለማለፍ የቴክኒክ፣ የሥነ-ልቦናና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ መወዳደሩን አስታውቋል። ሌላኛዋ የ17 ዓመት ታዳጊዋ ሰሚራ ሸምሱ በበኩሏ፤ በአካዳሚው ምቹ የስፖርት መሠረተ ልማት በመሰልጠን የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን በመቻሏ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።   አትሌቲክስ የሀገር ፍቅርን የምናሳይበት መድረክ በመሆኑ ይህን የስፖርት ዓይነት ልመርጥ ችያለሁ ያለው ደግሞ ከጉራጌ ዞን የመጣው የ17 ዓመቱ ታዳጊ ሰለሞን ግርማ ነው።   በአትሌቲክስ መስክ የተሻለ ሳይንሳዊ ሥልጠና ወስዶ ስመጥር አትሌት ለመሆን ወደ አካዳሚው መግባት የሚያስችለውን ውድድር በማድረግ የተተኪ ስፖርተኞች አካል ለመሆን መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የ16 ዓመቷ ታዳጊ ሕንደኬ በሬ በበኩሏ በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድር መድረኮች የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ያደረጉ አትሌቶችን እያየች ማደጓ ለአትሌቲክስ ፍቅር እንዲኖራት እንዳስቻላት ገልጻለች። የወደፊት ሕልሟ የመሰናክል ሯጭ መሆን እንደሆነ በመግለጽ፣ ለዚህ የስፖርት ዓይነት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ አካዳሚውን ለመቀላቀል ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ጠቁማለች።   በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የምርምር ቤተ-ሙከራ ወርክሾፕ ኃላፊ በእምነት ተለሞስ እንዳሉት፣ አካዳሚው ታዳጊዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን የሰልጣኞች መመልመያ መስፈርቶችን አዘጋጅቶ እየተጠቀመ ነው። ከመስፈርቶቹ መካከልም ታዳጊዎቹ ለእያንዳንዱ የስፖርት ዓይነት የሚገኙበትን የቴክኒክና የአካል ብቃት፣ የታዳጊዎች የጤና ሁኔታና የሥነ-ልቦና ደረጃ ጉዳዮችን መካተታቸውን አብራርተዋል።   በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌቶች ትምህርትና ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ ኢንስትራክተር ፍቃዱ ከበደ በበኩላቸው፣ በ2019 በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች ከ16 እስከ 17 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ 358 ታዳጊዎችን ለማሰልጠን መታቀዱን አስታውቀዋል። የሥልጠና ዓይነቶችም አትሌቲክስ፣ እግር ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቦክስ፣ ፓራሊምፒክ፣ ቮሊቦል፣ ብስክሌት፣ ወርልድ ቴኳንዶ እና ጠረጴዛ ቴኒስ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዚህም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመጨረሻ ዙር 638 እጩ ሰልጣኞችን በመመልመል አካዳሚውን የሚቀላቀሉ 358 ታዳጊ ስፖርተኞችን ለመምረጥ የመጨረሻ ዙር ምልመላ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻ ዙር ምልመላ የሚያልፉ ታዳጊዎችም በተመለመሉበት የስፖርት ዓይነት ለአራት ዓመታት በአካዳሚውና በአሰላ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሳይንሳዊ ሥልጠና እንደሚከታተሉ ተናግረዋል።  
ጤናማ ዜጋ አምራች ሀገር፤ የመደመር መንግሥት የጤና ፖሊሲ ትሩፋት
Sep 15, 2026 353
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተገበረችው አዲስ የጤና ፖሊሲ የመደመር መንግስት ቃልን በተግባር የመተርጎም ብቃትን ከሚያመላክቱ ትሩፋቶች መካከል ተጠቃሽ ነው። የመደመር መንግስት ባለፉት ስምንት ዓመታት ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች መካከል ማህበራዊ ልማት ዘርፉ ተጠቃሽ ነው። በዚሀ ዘርፍ ከሚመደቡት መካከል ደግሞ የጤና ዘርፉ ተጠቃሽ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትን ዕድል ለመፍጠር የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግን ጨምሮ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታ እና የሰለጠነ የጤና ባለሙያ አቅም ግንባታ ላይ ውጤታማ ተግባራት አከናውኗል። ቅድሚያ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ በመከለስ ለአክሞ ማዳንም ትኩረት እንዲሰጥ መደረጉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግስት ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በርካታ ሆስፒታሎች ተገንብተው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉንና በዚህም በዘርፉ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።   የመደመር መንግስት የህብረተሰቡ ጤና በተሟላ መልኩ ሲጠበቅ ምርታማነት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ሚና በሚገባ በመረዳት ከጤና መሰረተ ልማት ባሻገር ህብረተሰቡ አስቀድሞ ጤናውን ለሚጠብቅባቸው መሰረተ ልማቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ለዚህ ነው በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ የሚገኘው ይህ የመንግስት ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የግል ዘርፉም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ እና ለፖሊሲው ውጤታማነት በኩሉን ድርሻ መወጣት የሚችልበት ዕድል ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የተገበረችው አዲስ የጤና ፖሊሲ እና በዘርፉ የወሰደቻቸው ውጤታማ እርምጃዎች አይበገሬ የጤና ስርዓት መዘርጋት አስችሏታል። መንግስት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለሀገር እድገትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ባለፉት ዓመታት ውጤታማ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች በመውሰዱ የጤና ቱሪዝም ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከለውጡ በፊት ኢትዮጵያ ስትከተል የቆየችው በሽታ መከላከል ላይ ብቻ ያተኮረው የጤና ፖሊሲ፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥና የተቋማት ግንባታ እንዲሁም በዘርፉ ቴክኖሎጂ ከመጠቀም አንጻር ክፍተት ይታይበት ስለነበር ውጤታማነቱ ላይ የራሱን ተግዳሮት ደቅኖ ቆይቷል። የመደመር መንግስት የጤናው ዘርፍ ፖሊሲ ምሉዕ የሚሆነው በሽታ መከላከል ላይ ብቻ በማተኮር ሳይሆን አክሞ ማዳንንም የፖሊሲው የትኩረት ማዕከል ማድረግ ሲቻል መሆኑን በማመነ ፖሊሲው ይህንን ባካተተ መልኩ እንዲሻሻል አድርጓል። በተጨማሪም አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ለጤና መሰረተ ልማት ግንባታ ለአካታች የጤና አገልግሎት ለጤና ፋይናንስ እና ለቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውጤታማነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ በመንግስትም ሆነ በግል ዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ በርካታ የጤና መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል።   ለዚህም ይመስላል በአዲስ አበባ ከተማ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማዘመን፣ በማስፋፋትና ጥራቱን በማሳደግ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሳሪያዎችን በማስገባት የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መናገራቸው። በጤው ዘርፍ የአገልግሎትን ጥራት፣ ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ ቁለፍ ጉዳይ ነው። የመደመር መንግስት እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ለአዳዲስ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ግንባታ እንዲሁም ለነባሮቹ የጤና ተቋማት የማሻሻያ እና የማዘመን ተግባራት በመከናወናቸው በአገልግሎት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አንጻር ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህክምና ተቋማትን በዘመናዊ የህክምና ግብዓት ማደራጀትና አቅማቸውን ማሳደግ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የሆነ እንዲሁም አስተማማኝ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ርዕይ ለማሳካት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል። ባለፉት ስምንት ዓመታት በጤና ዘርፍ የነበሩ ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን የሚገልጹት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚህም የመንግስት የጤና ተቋማት ቁጥርና የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ማደጉን በመጥቀስ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ሽፋን እና የዜጎች ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ለዘርፉ ዕድገት ጥሩ ማሳያ ነው።   ባለፉት ስምንት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት እምርታ መመዝገቡን የመድሃኒት፣ የክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር መጨመሩን እንዲሁም በጤና ፋይናንስ ስርዓት ላይ የተመዘገበውን ለውጥ በማሳያነት ይጠቅሳሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተለይ በጤናው ዘርፍ የተከሰቱ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞችንና በዘርፉ የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። በዚህም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፣ የዲጂታል ጤና እና በዘርፉ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት በጤና ዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን ሚኒስትሯ መጥቀሳቸው ለተፈጠረው አቅም ጥሩ ምሳሌ ነው። የመደመር መንግስት ለማህበራዊ ልማት በተለይም ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ምክንያት በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። እነዚህ በዘርፉ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ለጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ እመርታ አበርክቷቸው ከፍተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያ የተለያዩ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን እንድታስተናግድ ተመራጭ እንዳደረጋት እና ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ዓለም አቀፍ የጤና ድርድሮችንና ንግግሮችን እንድትመራ እንዳስቻላትም እንዲሁ።
የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እመርታ፤ የአረጋውያን በረከት፣ የታዳጊዎች የተስፋ ማዕድ
Sep 14, 2026 453
ሀገር በታሪክ ሰሪዎችና ባለውለታዎች ጀግኖች አባቶች ገድል፣ በነገ ተስፋዎች ጽናት ትገነባለች፤ በጠንካራ ተቋማትና ተስፋን በሰነቁ ፕሮጀክቶች ትጸናለች። የመደመር መንግሥት የዜጎችን ማኅበራዊና ምጣኔ-ሀብታዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከነደፋቸው ውጥኖች መካከል ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ። ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በተማሪዎች ምገባ እና በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ብቻ የተመረኮዙ አይደሉም፤ ይልቁንስ የሀገር ባለውለታዎች ካስማ፣ የነገ ተስፋዎች ማገር ናቸው። የመደመር መንግሥት ማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈን ቀዳሚ አጀንዳው ሲያደርግ፣ የትናንት የሀገር ጀግኖች ውለታ በመመለስ እና ለነገ ታዳጊዎች ብርሃን በመፈንጠቅ ነው። በኢትዮጵያ በከተማና ገጠር፣ በአዛውንቶችና ወጣቶች መካከል አንዳችም ልዩነት ሳይፈጠር የአካባቢያቸውን የመልማት ጸጋ አውጥቶ መጠቀም የሚያስችሉ የዜጎች ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተደራሽ ሆነዋል። በትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸረው ውጤት አስመዝግባለች፤ ሌሎች ክልሎችም ብዙ ተምረውበታል።   መንግሥት በመዲናዋ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር 976 ሺህ 702 ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ቁርስና ምሳ መመገብ የሚያስችል ሥርዓት በማንበር ህዝባዊነቱን በተግባር ገልጧል። ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ኢኒሼቲቩን እንደ ትምህርት በመውሰድ የትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመጀመር የተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ የማቋረጥ ምጣኔ ቀንሰዋል፤ የተማሪዎችን ትኩረት በመሰብሰብ ለውጤታማ መማር ማስተማር ሂደት መሰረት ጥለዋል። የደጃዝማች ወንድይራድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናታኒም በላይ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመጀመሩ ትምህርቱን በሙሉ ትኩረት ሳያቋርጥ የሚማርበት ዕድል ማግኘቱን ገልጿል። በትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር መጀመሩ ለእናቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ገቢ ማግኘትና የአዕምሮ እርካታ እያገኙ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች መጋቢ ወይዘሮ መሰረት እንዳለ ናቸው።   በአዲስ አበባ 30 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትን በማቋቋም ራሳቸውን መመገብ ለማይችሉ አቅመ ደካማ ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ የሚያገኙበት ምቹ ምኅዳር ተፈጥሯል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 30ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ ሲያስጀምሩ፣ የነዋሪዎችን ሕይወት ለመለወጥና ለኑሮ ምቹ አካባቢን መፍጠር ዋና አጀንዳቸው መሆኑን ተናግረዋል። የምገባ ማዕከላትን ማስፋፋት አቅመ ደካማ ወገኖችን ከመመገብ ባለፈ ለነዋሪዎቻችን ያለንን ክብር የምናሳይበትና ለዜጎች የሥራ ዕድል የምንፈጥርበት ነው ብለዋል። ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በመዲናዋ ማኅበራዊ ፍትሕን በማንገስ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚያስችሉ ተናግረዋል። ሀገር ላጸኑ የሃገር ባለ ውለታዎች አባቶችና እናቶች በንጹህ፣ ጽዱና ምቹ ቤት የተደላደለ ሕይወት እንዲመሩ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታኅሣሥ 2016 የአዋሬ መንደር የጋራ መኖሪያ ህንፃ አሰርተው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ለውጥ የሚያመጡ፣ የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያሻሽሉ እና ሀገር የሚያሻግሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አዋሬን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ፤ ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ተሰናስለው ለሀገርና ሕዝብ ካስማና ማገር የሚሆኑ ተጨባጭ ውጤቶች ማምጣት እንደሚቻል አስረድተዋል። "እንሠራለን፣ ኢትዮጵያን እንቀይራለን፣ ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ውብ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ዕድሉ በኢትዮጵያውያን እጅ ላይ እንዳለ አረጋግጠዋል። የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን፣ አለፍ ሲልም አዳዲስ ምቹና ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮችን ከተሟላ የመንገድ፣ የውሃ፣ መብራትና መሰል መሠረተ ልማት ጋር ሰርቶ ማስረከብ የመደመር መንግሥት መገለጫ ሆኗል። በመዲናዋ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ተሰርተው የተላለፉ ቤቶች ተጠቃሚ የሆነው ወጣት ታምራት ተመስገን የአካል ጉዳተኛ በመሆኑ በርካታ ፈተናዎችን ማስተናገዱን ገልጿል።   ይሁን እንጂ አዲስ በተረከበው ቤት እንደ ልብ መንቀሳቀስና ሕይወቱን ማሻሻል የቻለበት ዕድል እንደተፈጠረለት ገልጿል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው የታደሰላቸው እናት ወይዘሮ ታየሁ መኮንን "ቤት ነው ለማለት እንኳን በማያስደፍር" ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር አስታውሰዋል።   በሸራና በላስቲክ ከተጠጋገነ፣ የግድግዳው አፈር ከሚናድ ቤት ውስጥ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ "ቤቴ በመታደሱ 'ቤቱ እላዬ ላይ ይደረመሳል' ከሚል ሰቀቀን ተላቅቄ፣ ያለ ሀሳብ ጎኔን ማሳረፍ ችያለሁ" ብለዋል። በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ከጎዳና ሕይወት ወደ ለውጥ አብነት የተሸጋገሩ ወጣት ልጃገረዶች እልፍ ናቸው። ማዕከሉ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ ሴቶች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሕክምና በማድረግ፣ ዘላቂ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና በመስጠት ሕይወታቸውን የሚያሻሽሉበት ተቋም ነው። ማዕከሉ በ2016 ዓ.ም ሥራ ከጀመረ በኋላ በአምስት ዙሮች ሦስት ሺህ 259 ሴቶችን በማሰልጠን ወጣቶች ተስፋ እንዳላቸውና ለለውጥ ቅርብ እንደሆኑ በተግባር አሳይቷል። በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2018 ዓ.ም በአምስተኛ ዙር በዶሮ እርባታ ሥልጠና ወስዳ የተመረቀችው ትዕግስት ፀጋዬ፣ ማዕከሉ ከጎዳና ሕይወት ወጥታ ጠንካራ ስብዕና መገንባት የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላት ተናግራለች።   በማዕከሉ የቤት አያያዝ ሥልጠና የወሰደችው መሰረት አበራ በበኩሏ፣ ከጎዳና ላይ ከነበረችበት አሰልቺ ሕይወት ተላቃ ጠንካራ የራስ መተማመን በመገንባት ነገን የምታልም ሴት እንዳደረጋት ገልጻለች።        
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪነት አስቀድሞ የተረዳው - ብሪክስ
Sep 18, 2026 145
በመቅደስ ወልዴ ብሪክስ እ.ኤ.አ በ2009 ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው በፍጥነት እያደጉ ባሉት በቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ብራዚል የተመሰረተ የደቡብ ደቡብ ትብብር ነው። ብሪክ /BRIC/ በሚል መጠሪያ የመጀመሪየውን ስብሰባውን ያደረገውም በወርሃ ሰኔ እ.ኤ.አ በ2009 በሩሲያዋ የካተሪንበርግ ከተማ ነበር። ጥምረቱ እ.ኤ.አ 2011 ደቡብ አፍሪካን በማካተት ስያሜውን ወደ ብሪክስ /BRICS/ ቀይሯል። የማህበራዊና የባህል መስተጋብር፣ የጂኦ ፖለቲካና የባለብዙ ወገን ትስስር፣ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ትብብር በመፍጠር የጸጥታ፣ የህዝብ ለህዝብና ማህበራዊ ጉዳዮችን ዕድገት ማሳለጥ ያለመ ነው። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ኢራን እ.ኤ.አ በ2024 ቀጥሎም ኢንዶኔዥያ እ.ኤ.አ በ2025 ጥምረቱን መቀላቀላቸውን ከብሪክስ ድረገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። እንደ መረጃው ከሆነ ጥምረቱ የዓለምን 49 ነጥብ 5 በመቶ የህዝብ ብዛት የሚሸፍኑ 11 ሀገራትን በአባልነት የያዘ እንዲሁም የዓለማችንን 40 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚሸፍን ስብስብ ነው። ብሪክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪነትን ማሳደግ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ እንዲሁም እንደ መንግስታቱ ድርጅትና መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት የዘረጉት ኢ-ፍትሐዊ ተቋማዊ አሰራር እንዲሻሻል ተፅዕኖ በመፍጠር ተጨባጭ ለውጥ የማየት ግብ ይዟል። ኢትዮጵያ እንዴት የብሪክስ አባል ሆነች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠንካራ እና በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተሰሚነት አቅምና ተፅዕኖ ፈጣሪነት እያደገ መጥቷል። በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ መግቢያ በር፣ የአፍሪካ ህብረት መስራችና መቀመጫ፣ የተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ፤ የዲፕሎማቶች መናኸሪያ፣ ሰፊ ህዝብና በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ያላት የአፍሪካውያን የአይን ማረፊያ ሆናለች። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቀነስና መቋቋም በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳርቻዎች እንዲሁም በገጠርና በከተሞች ያስመዘገበቻቸው የልማት ውጤቶች የዓለም ቀልብ ስቧል። በአህጉርና በዓለም አቀፍ መድረኮች የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ባለፈ አፍሪካውያንን በመወከል ድምጽ በማስማት ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን አሳይታለች። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላት ተጽዕኖ ፈጣሪነት፣ ለጋራ ልማት ለትብብርና ለፍትሐዊ ተጠቃሚነት የምታደርገው ጥረትና ባላት የጠራ የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የብሪክስ ጥምረትን እንድትቀላቀል በር ከፍቶላታል። በዚህም የኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረት አባልነት ተቀባይነት አግኝቶ እ.ኤ.አ በወርሃ ጥር 2024 በይፋ ተቀላቅላለች። ኢትዮጵያ ጥምረቱን እንድትቀላቀል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች ብስለት የተሞላበት የዲፕሎማሲ ጥረት ስለማድረጋቸው በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል መሆን የሚያስችሏትን አሳማኝ ምክንያቶች ሲያስረዱም ኢትዮጵያ ነጻነቷን ያስጠበቀች፣ ለተገፉ ሀገራት ድምፅ የሆነች፣ ለአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መመስረት ሰፊ ሚና የተጫወተች ሀገር መሆኗን እና ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ላይ የምትገኝ ሀገር መሆኗን በማንሳት የደቡብ - ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር ይህችን ታላቅ ሀገር ማካተት ተገቢ ነው ሲሉ በአፅንኦት ማስረዳታቸውና ማሳመናቸው ጥያቄው ተቀባይነት እንዲያገኝ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲፕሎማሲ አሰራር ብስለትን ካረጋገጡ ሂደቶች መካከል ኢትዮጵያን የብሪክስ ጥምረት አባል ለማድረግ የተጠቀሙት የዲፕሎማሲ ስልት ተጠቃሽ ነው። ይህውም ኢትዮጵያን የጥምረቱ አባል ማድረግ ለጥምረቱ አባል ሀገራት እና በጥቅሉ ለጥምረቱ የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ ለአባል ሀገራት መሪዎች በተናጥልና በጋራ መድረኮች ተገቢውን ግንዛቤ ማስጨበጣቸው ዋነኛው ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል እንድትሆን ያቀረቧቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ስትራቴጂካዊ አመክንዮዎች የጥምረቱን አባል ሀገራት ልብ መግዛቱ ጥያቄው አወንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ አስችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በባለ ብዙ ወገን ዲፕለማሲ መስክ ያላትን ተደማጭነት የሚያሳይ መሆኑንና በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በግብርና እንዲሁም በሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት እድገት እያስመዘገበችው ያለው ስኬት የአባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍተኛ ሚና ማበርከታቸውን ማብራራታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ብሪክስ ለኢትዮጵያ ምኗ ነው የኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል መሆን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን ታሳቢ ያደረገ ነው። ብሪክስ በጠንካራና የተቀናጀ ዲፕሎማሲ የጋራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አቅም በመፍጠር አብሮ ማደግን መዳረሻው አድርጓል። የኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረት አባልነትም የዚህ ጥቅም ተጋሪነትን መርህ ታሳቢ ያደረገ ነው። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል በመሆኗ በፋይናንስና የኢንቨስትመንት የትብብር መስኮች ሰፊ ዕድል እንዲኖራት የሚያስችል መሆኑንና ለጀመረቻቸው የልማት ስራዎች ስኬትም ተጨማሪ የፋይናንስ አቅም እንድታገኝ እንዲሁም ወደ ውጭ ለምትልካቸው ምርቶች ሰፊ የገበያ አማራጭ የሚፈጥር መሆኑን በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) መግለጻቸው ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። ኢትዮጵያ በቱሪዝም፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በኢንዱስትሪ፣ ማዕድንና ግብርና ዘርፎች የጀመረችውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማቀላጠፍ ከብሪክስ ተጨማሪ ልምድና ተሞክሮ ታገኝበታለች፤ ልምዷን ለሌሎች ለማካፈልም ምቹ ዕድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብሎም በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት። ይህ ደግሞ የብሪክስ አባል ሀገራትን ሰፊ የገበያና የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ዕውን ለማድረግ ተጨማሪ አቅም ይፈጥርላታል። ከዚህም ባለፈ ብሔራዊ ጥቅሟና የሌሎችን የጋራ ተጠቃሚነት መሳ ለመሳ የምታካሂድ ለመሆኗ ትልቅ ማሳያ ነው። ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 18ኛው የጥምረቱ ጉባኤ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችንን ያረጋገጥንበትና የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ የተሰማበት ታሪካዊ ስኬት ነው ማለታቸው። ጥምረቱ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማሳካት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፣ የአረንጓዴ ኢነርጂ ልማት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ማረጋገጥ በትብብሩ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል። ኢትዮጵይ በቀጣናው፣ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሃላፊነት ለመወጣት የብሪክስ ማዕቀፍ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ መድረኮች ወሳኝ አጀንዳዎችን ለማራመድ የጎላ ሚና ይኖራቸዋል። ከብሪክስ ጥምረት በኋላ የተገኙ የዲፕሎማሲና ኢኮኖሚ ስኬቶች 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ እ.አ.አ በ2025 በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ በተካሄደበት ወቅት በዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት፣ ባለብዙ ወገን ተቋማት ማሻሻያ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አጀንዳዎች ላይ መምከሩ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን መሸጋገሩን፤ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት በሚያስችል ሁኔታ አፋጣኝ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚገባቸው፤ በብሪክስ አዳዲስ አባላት መጨመራቸው የጋራ ድምፃችን የበለጠ እንዲጠናከር ያስችላል የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል። አቅማችንም ይሰፋል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። በተጨማሪም እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በአለምአቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ እንደምታደርግ ማንሳታቸው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ለአፍሪካ ጥቅም መከበር ሚናዋን መቼም የማትዘነጋ መሆኑን አመላካች ነው። ስለ ዓለም ሰላም፣ የተቀላጠፈ የኢኮኖሚ ሽግግርን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂና ፈጠራ እንዲሁም ለቀጣናዊ ውህደት ያላትን ፍላጎትና ቁርጠኝነት በጉልህ ማሳየታቸው፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ልማት፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብሎም መሰረተ ልማት ዝርጋታና መስፋፋት ያላትን ርዕይ በግልጽ ማንጸባረቃቸው ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላም፣ ልማትና ብልፅዕና ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ነው። የብሪክስ ጥምረት የዓለም የዲፕሎማሲና የጂኦፖለቲካ ተፅዕኖን ለማሳደግ ካለው ሰፊ ዕድል አንጻር ሲታይም በዓለም አቀፍ መድረኮችና ውሳኔዎች ላይ የሀገሪቱንና የአህጉሪቱን ድምፅ ለማጠናከር ከምዕራባውያን ተፅዕኖ የተላቀቀ ሁለገብ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን በጽኑ መሰረት ለመገንባት ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በጥምረቱ የምታደርገው ተሳትፎ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካና የሌሎች አህጉራት ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፍ ባለብዙ ወገን ተቋማት ፍትሃዊ ውክልና ማግኘት እንዳለባቸው በተገኙባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ሁሉ ሲሞግቱ የሚደመጡትም ይህንኑ የሚያመላክት ነው። ዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪና የባለብዘዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትንና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው አጽንኦት መስጠታቸውም እንዲሁ። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ጥቅሞች መከበር ያለባትን ሀላፊነት በውል እንደምትገነዘብ እና ድምጿን ማስተጋባቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ያረጋገጠችበት መድረክ ነው። የብሪክስ ጥምረት ሀገራትን በአባልነት ለማቀፍ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች የሀገራቱን ዓለም አቀፍ ተፈላጊነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ደግሞ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተደማጭነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በግልጽ አሳይቷል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነትን በተቀላቀለችበት ወቅት ከ40 በላይ ሀገራት ጥምረቱን ለመቀላቀል ፍላጎት አሳይተው ነበር። የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ብቻ መመረጣቸው ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላትን ግዙፍ የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ማሳያ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳልና አሳታፊ የዲፕሎማሲ ጥረት የተገኘው የብሪክስ ጥምረት አባልነት ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ከተመዘገቡ የዲፕሎማሲ ስኬቶች አንፃር ትልቁና አንጸባራቂ ድል ተብሎ ይወሰዳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥምረቱ የኢትዮጵያን የአባልነት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ባጸደቀበት ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ጥምረቱን መቀላቀል የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ ልዕልና ማሳያ ነው ሲሉ መግለጻቸውም ይህንኑ ያጠይቃል። የብሪክስ ጥምረት ኢፍትሃዊውን ዓለም አቀፍ መዋቅርና ሥርዓት ወደ ሚዛናዊ መንገድ በማምጣት በዓለም የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሁሉም ሀገራት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራቸው ያስችላል። ብሪክስ ይህ ስርዓት መሬት እንዲረግጥ የራሱ አስተዋጽኦ አለው። ለኢትዮጵያም እነዚህ የተዛነፉ ዓለም አቀፍ ባለብዙ ወገን ተቋማት አሰራር ፈር እንዲይዝ የራሷን ሚና ለመወጣትና ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዋን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የብሪክስ ጥምረት ውጤት የሆነው የአዲሱ የልማት ባንክ ያለምንም ፖለቲካዊ ቅድመ ሁኔታ ሀገራት መሰረተ ልማት ማስፋፋት የሚችሉበትን ብድር ያቀርባል። ኢትዮጵያም ከሀገር ውስጥ ባለፈ ቀጣናውንና አህጉሪቱን በኤሌክትሪክ ሀይል እና በሌሎች መሰረተ ልማቶች የማስተሳሰር ውጥኗን ዕውን እንድታደርግ ያስችላታል። ኢትዮጵያ ለጀመረችው መጠነ ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ይሆናል። እንደ ቻይና፣ ሕንድ እና ሩሲያ ካሉ የዓለምን ኢኮኖሚ ከሚያንቀሳቅሱ ሀገራት ጋር ያላትን የወጭ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቷንና የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን ማሳደግ፣ የወጪ ንግዷን በራሷ የመገበያያ ገንዘብ ለማከናወን ምቹ ዕድል ይፈጥርላታል። የጥምረቱ አባል ሀገራት በቴክኖሎጂ ውጤቶች ፈጠራ እና የማምረት ብቃትና የተወዳዳሪነት አቅም መጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ለመፍጠርም በር ከፍቶላታል። ኢትዮጵያ በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ17ኛ የብሪክስ መሪዎች ጉባዔ የአፍሪካን ድምጽ ለዓለም ማሰማታቸው በ18ኛ የብሪክስ ጉባዔ አመርቂ የዲፕሎማሲ ስኬት እንዲመዘገብ አስችሏል። የአፍሪካን ጥቅም ማስጠበቅ፣ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ሥራዎች የጎላ ድጋፍ እንዲገኙ፣ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥረት ለውጤት እንዲበቃ የብሪክስ ሀገራት መሪዎች በኒው ዴልሂ ቃላቸውን ሰጥተዋል። የብሪክስ ሀገራት በአዲሱ የልማት ባንክ የአባልነት ጥያቄያቸው በፍጥነት እንዲታይ፣ በታዳጊ ሀገራት መካከለ ዘላቂ የዕዳ አስተዳደር ስምምነቶች እንዲኖሩ በማድረግ ኢትዮጵያ ገንቢ ሚና ተጫውታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የኢትዮጵያን ውጤታማ ስኬቶች በጉልህ አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን፣ በቅድመ መከላከል የጤና ፖሊሲ ውጤት ማስመዝገቧን፣ የህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ በማምረት አክሞ የማዳን አቅሟን ማሳደጓን፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ደህንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀምና ሽግግር መፍጠሯን፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም አዳጊ ፍላጎቶችን ሊያሳካ የሚችለውን የመደመር ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታን በማንሳት ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ትብብርና ልማት ያላትን ቀናኢነት አንስተዋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ አስተወሎት ያመጣቸው ዕድሎችን መጠቀምና ስጋቶችን ለመፍታት ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውም ይታወሳል። አፍሪካ ጠንካራ ውክልና እንዲኖራት፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ፤ ንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ትስስርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ያቀረቡበት መድረክ ነበር። አዲሱ የልማት ባንክ በመላው አፍሪካ አድማሱን በማስፋት በአዲስ አበባ ቢሮውን እንዲከፍት የጠየቁበት፤ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጣቸው፣ በአጠቃላይ 18ኛ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ጥቅሞች መከበር ፊት አውራሪነቷን በድጋሚ ያረጋገጠችበት ሆኖ ተጠናቋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የመልማት አቅም ያላት ሀገር ናት። ለያዘቻቸው የልማት ርዕዮች መሳካት አማራጭ የፋይናንስ ምንጮች ያስፈልጓታል። ለዚህ ደግሞ ብሄራዊ ጥቅሟን ያስከበረና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ የዲፕሎማሲ ስኬት እያስመዘገበች በልዩ ጥንካሬ ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች። በታሪካዊው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ የተገኘውን ወርቃማ የዲፕሎማሲ ድል ወደ ዘላቂ ልማት ለመቀየር የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የመንግሥት ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ወጣቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች የጋራ ሀገራዊ ራዕይ በመሰነቅ፣ ብሄራዊ አንድነትንና ጥንካሬን በማንገብ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና በቁርጠኝነት መሰለፍ ይገባቸዋል።  
የተማሪዎች ምገባ አያሌ ትሩፋቶች
Sep 17, 2026 212
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ466 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህጻናት በትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች የምግብ አማራጭ ብቻ ሳይሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ላይ ያላቸው አዎንታዊ ተጽእኖ እጅግ የገዘፈ ነው። መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የመማር ምጣኔ በመጨመር በተቃራኒው መጠነ ማቋረጥን በእጅጉ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው። ፕሮግራም በተለይም በአደጋ ተጋላጭና ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ወደ ትምህርት ገበታ የሚመጡ ልጆችን ቁጥር እንዲጨምር ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ተማሪዎች በቀን ውስጥ የሚያገኙት የተመጣጠነ ምግብ በክፍል ውስጥ ያላቸውን የንቃት፣ የማስታወስ እና የትምህርት መቀበል አቅም በማሳደግ የትምህርት ውጤታቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል። የኢትዮጵያ የህብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና የዓለም የምግብ ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ምገባው ህጻናት ከስድስቱ የምግብ ምድቦች የተውጣጡ አልሚ ምግቦችን እንዲያገኙ በማድረግ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትንና የጤና አደጋን ይቀንሳል። የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦቱ የህጻናትን አጠቃላይ አካላዊ እድገት፣ የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) እና የአዕምሮ ጤና በመጠበቅ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያስችል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እ.አ.አ በ2030 ሁሉም ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ አቅዶ እየሰራ ይገኛል።   በአፍሪካ ደረጃ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህጻናት የተለያዩ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በኢትዮጵያም የትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናትን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑን ገልጸው፤ ሀገሪቱ የምትመግበው ህጻናት ቁጥር ከአንዳንድ ሀገራት የህዝብ ቁጥር ጋር የሚስተካከል መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዳጊ ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት እንዳይስተጓጎሉ ማድረግ ሊተኮርበት የሚገባ ዋነኛ የሀገር ግንባታ ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።   በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ የምገባ ኤጀንሲ በማቋቋም ተማሪዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የማድረግ ዘላቂ ተግባር በስኬት በመከናወን ላይ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በመዲናዋ በሚገኙ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ-አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ለሚማሩ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ (ቁርስ እና ምሳ) በነፃ ይመገባሉ። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሞክሮ በመነሳት ይህ ስራ በፈረንሳይ ፓሪስ እና በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተከናወኑ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳድረው አሸናፊ በመሆን የሜላን ፓክት ሽልማት (Milan Pact Award) ተቀዳጅቷል። እ.አ.አ በ2022 በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው 8ኛው የዓለም አቀፍ የከተሞች የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ጉባኤ ላይ የተበረከተው ይህ ታሪካዊ የሜላን ፓክት ሽልማት፣ አዲስ አበባ መርሃ ግብሩን በዘላቂነትና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ዘርፍ እጅግ ውጤታማ በሆነ መንገድ በመምራቷ የተሰጠ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ2021 በጣሊያን ሮም በተካሄደው የዓለም ሥነ ምግብ ኮንፈረንስ እና በሚላን የምገባ ፎረም ላይ መዲናዋ የምገባ ፎርም ምርጥ ተሞክሮ በሚል እውቅና አግኝታለች። እነዚህ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች የተሰጡት መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የምገባ ችግር ከመቅረፍ ባለፈ፣ ከተማዋ የምግብ ስርዓትን በዘላቂነት በመምራትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት በማደራጀት ማህበራዊ ፍትህና የኢኮኖሚ ነፃነት እውን እንዲሆን በማድረጓ ነው። የአዲስ አበባ አርአያነት ያለው ተግባር አሁን ላይ ወደ ክልሎች እና ከተሞች በስፋት እየተዳረሰ ይገኛል፤ እንደ ኬንያ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችም መዲናዋን በመጎብኘት ልምድ እየቀሰሙ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን የተመለከተ አዲስ የስነ ምግብ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ አድርጓል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርሃ ግብሩ ተማሪዎች በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት ይሰማቸው የነበረውን የስነ-ልቦና ጫናና የድፍረት ማጣት ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ማህበራዊ ፍትህ ማረጋገጡን በአንድ ወቅት ገልጸዋል። ምግብ በማብሰልና በማቅረብ ሂደት ላይ ከ25 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ በማድረግ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ገንብቷል። የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በሀገር አቀፍ የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብሩ አብዛኛው በጀት በሀገር ውስጥ አቅም እና በመንግስት የሚሸፈን ነው። መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ወዲህ በተለይም ድርቅና የአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ በ10 በመቶ እንዲጨምር እና የትምህርት ማቋረጥ ምጣኔ በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። ትምህርት ቤቶች የወጪ ጫናቸውን እንዲቀንሱ በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ የጓሮ አትክልት ልማት፣ የዶሮ እና የወተት ከብቶች እርባታ እንዲጀመር ተደርጓል። ኢትዮጵያ ይሄን መርሃ ግብር የምግብ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሀገርን የረጅም ጊዜ የሰው ሀብት (Human Capital) መገንቢያ ስትራቴጂ አድርጋ እየሰራች ይገኛል። የምገባ ፕሮግራሙ ከትምህርት ተደራሽነትና ውጤታማነት ባሻገር ህጻናት በጤናማ አካልና አእምሮ እንዲያድጉ በማድረግ ለሀገር አቀፍ የጤና ጥበቃ ስራዎች ትልቅ አበርክቶ እያበረከተ ይገኛል። በምገባ ማዕከላት ዙሪያ የሚደረጉ የንፅህና አጠባበቅና የደህንነት ትምህርቶች ተማሪዎች በለጋ እድሜያቸው ጤናማ የኑሮ ዘይቤዎችን እንዲላመዱና የግል ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ አቅም እየፈጠረ ይገኛል። በአጠቃላይ የምገባ ፕሮግራም በትምህርት ላይ እያሳረፈ ካለው በጎ አሻራ ባለፈ ምርታማ ትውልድ ለመፍጠር እና ለአንድ ሀገር እድገት እና ልማት ያለው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው። በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ በስኬት ጎዳና እና ለሌሎች አርአያ በሚሆን ተምሳሌታዊ ተግባር በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሀገር ናት።
የቱሪዝም ትንሳኤን ያበሰረው የመደመር እሳቤ
Sep 16, 2026 466
ኢትዮጵያ አስደማሚ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቱሪዝም ሀብቶች ባለቤት ናት ። የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ደጋግመው ቢያዩዋቸው ፣ ቢታደሙባቸው የማይሰለቹ ተጠንተውም የማያልቁ ፀጋዎች ቢኖሯትም ለዘመናት በወጉ ሳትገልጣቸው የሚጠበቀውን ያክልም ሳይጎበኙ ሳይተዋወቁም ቆይተዋል። ይህን ባለማድረጓ ደግሞ ከዕልፍ የቱሪዝም ጸዋጋዎቿ ሳትቋደስ ዘመናትን ተሻግራለች። “በታሪክም ሆነ በተፈጥሮ ጸጋዎች ከኛ ጋር ሊወዳደሩ የማይችሉ ብዙ ሀገራት ከኢንዱስትሪው ብዙ አትርፈዋል። እኛ ግን እንቁዎቻችንን ደብቀን ታሪካችንን አቧራ አልብሰን ለዘመናት ቆይተናል።” የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 259 ዛሬ ግን ይህ ታሪክ እየተቀየረ ነው። ከመደመር መንግሥት አምስት ወሳኝ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው ቱሪዝም ቅርሶችንና ወሳኝ ፀጋዎችን ከቁስ ወደ ቁርስ እየለወጠ፣ ኢትዮጵያን እየገለጠ እንዲመጣ እየተደረገ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአራት ኪሎ ቤተመንግስት “ሀ” ተብሎ የተጀመረው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ልማት በገበታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ወደ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ተዳርሷል። በኢትዮጵያ ትኩረት ተነፍጓቸው የነበሩት የሀገራችን የቱሪዝም ሀብቶች በመደመር መንግሥት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ትንሳኤያቸው ተበስሯል። ለዘመናት አቧራ ለብሰው የኖሩ ዕንቁ የቱሪዝም ሀብቶች አቧሯቸው እየተራገፈ ነው። ከዳሎል እስከ ስሜን ተራሮች ማራኪ ተፈጥሯዊ መስህቦች ይበልጥ ለዓለም እየተዋወቁ ነው። አዳዲስ ተፈጥሯዊ ፀጋዎችም በቱሪዝም ልማት ኢኒሼቲቮች የመገለጥና የመታወቅ ዕድል አግኝተዋል። የመደመር እሳቤ የምናብ ከፍታና የመፈጸም ልክ አንዱ ጉልህ ማሳያ የቱሪዝሙ ዘርፍ ፕሮጀክቶች ናቸው። ከነዚህ ኢኒሼቲቮችም መካከል አንዱ ከቤተ መንግስት እደሳት ጀምሮ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ያደረጋት የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት ነው። የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት የቱሪዝም አብዮትን በመቀስቀስ የአንድነት ፓርክን፣ እንጦጦና ወዳጅነት ፓርክና ሌሎች ተያያዥ ፕሮጀክቶችን ዕውን አድርጓል። ዛሬ ላይ አዲስ አበባን አዲስ መልክ አጎናጽፎ፤ የነተቡ ሰፈሮች ወደ ውብ መልኮች ተቀይረው የሚሊዮኖች ጎብኚዎች መዳረሻ ሆነዋል። ከገበታ ለሸገር በመቀጠል የኢትዮጵያን አዳዲስ መልኮች የገለጠው ኢኒሸቲቭ ደግሞ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወንጪን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮና ኮንታን የሸፈነው ኮይሻን፣ከአማራ ክልል የጣናን ምዕራባዊ ዳርቻ የተንተራሰችውን ጎርጎራን ውብ አድርጓል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን አይነተ ብዙ ታሪክ፣ ተፈጥሮንና ባህል በመግለጥ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሞገስና ድምቀት ሆነዋል። ከገበታ ለሀገር ቀጥሎ ገቢራዊ የተደረገው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አድማሱ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ሪዞርትን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደንቢ ኢኮ ሎጅን፣ በአማራ ክልል የሐይቅ ሎጎ ሪዞርትን፣ በአፋር ክልል የኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ እንዲሁም የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን እውን አድርጓል። ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ባሻገር የመደመር መንግስት ታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ፣ እሴት ጨምሮ የመግለጥ አኩሪ ስራዎችንም አከናውኗል። ለዚህ ደግሞ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ጀምሮ ጥንታዊ አብያተ መንግስታት፣ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ተጠግነዋል። የባለፉት ጥቂት ዓመታት የቱሪዝም ዘርፍ ለውጦች የኢትዮጵያን ገጽታ ያስተዋወቁ፤ በየአካባቢው ተስፋና ልማትን የፈነጠቁ፣ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ናቸው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ የዕድገትና የብልጽግና ታሪክ ውስጥ በደማቁ የሚጻፉ አንቀጾች ሆነው ለትውልድ የተኖሩ ዓሻራዎች ናቸው።
የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የከፍታ ጉዞ ማሳያ - ብሪክስ
Sep 13, 2026 915
''የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው" በማለት ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የጥምረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርንና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በህንድ ኒውዴልሂ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑክ ቡድናቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ በሚፈጥረው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። ብሪክስ ለአፍሪካ ቀጣና እና በተለይም ለኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ አዲስ የዓለም ስርዓት እየተፈጠረበት የሚገኝ ጥምረት ነው። የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በዚህም እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያ ካሉ ታላላቅ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በኢነርጂ ዘርፍ በማሳደግ በኩል አይነተኛ አማራጭ የኢንቨስትመንት መንገድ ነው። ጥምረቱ ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ትሩፋት አንጻር ሲታይ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ፤ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘብን የመጠቀም ዕድልን ስለሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እጥረትን ከመቀነስ አኳያም እንዲሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅዷ ኢኮኖሚዋን በመሠረታዊነት ለሚያሳድጉ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ትገኛለች። ከዚህ አኳያ ብሪክስ የመንገድ፣ የባቡር፣ የኃይል ማመንጫዎችና ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና መሰል የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ በማመቻቸት በኩል ኢትዮጵያ ለያዘችው ግብ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ጥምረት ነው። ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ላሳካቻቸው ውጤቶች የዓለም አቀፍ ግንኙነቷን የቃኘችበት አዲስ አካሄድ ተጠቃሽ ነው። ከእነዚህ ስኬቶች መካከል ደግሞ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ አባል የሆነችበት መንገድ አንዱ ሲሆን፤ ይህ የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የራሱን ሚና በመጫወት ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአህጉሪቷ ያላትን መሪነትና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ድምፅ እንድታጎላ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ እንዲያድግ እያስቻለ መሆኑም በተጨባጭ ታይቷል። የብሪክስ ጥምረት በአፍሪካ አለፍ ሲልም በጥምረቱ አባል ሀገራት መካከል ተመጣጣኝ ልማት እንዲኖር እና ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ አስቻይ ምህዳር እየፈጠረም ይገኛል። በተለይ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገቷን እንድታፋጥን አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ መሆን የሚያስችለውን አደረጃጀት እና አሰራር እየዘረጋም ይገኛል። ይህ የጥምረቱ አዳዲስ አደረጃጀት እና አሰራር አዲሱ የልማት ባንክ እንዲወለድ አስችሏል። በዚህ ባንክ አማካኝነት የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጥብቅ መስፈርቶች ነፃ በሆነ መንገድ ለተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ወይም ብድር እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በጥምረቱ አማካኝነት የተፈጠረው አዲሱ የልማት ባንክ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘብ እና ከአሜሪካ ዶላር ተጽእኖ ውጪ ከታላላቅ የብሪክስ ሀገራት ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲያከናውኑ በር እየከፈተ ይገኛል። በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የውሳኔ መድረኮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ፣ ፍትሐዊ የሆነ የዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል። ይህ የብሪክስ ጥምረት መመስረት፣ መስፋፋትና መጠናከር በዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ በርካታ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጦችንና አንድምታዎችን እያስከተለ ይገኛል። የብሪክስ ጥምረት ተመስርቶ እየፈጠረ ያለው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተጽዕኖ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የምዕራባውያን ሀገራት በዓለም ፖለቲካ ላይ የነበራቸውን የበላይነት በመገዳደር፣ ሥልጣንና ውሳኔ ሰጪነት ለተለያዩ የአህጉራት ኃይሎች እንዲከፋፈል፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥያቄዎች ጎልተው እንዲሰሙ የማድረግ አቅም እየፈጠረ ነው። በተጨማሪም የብሪክስ ጥምረት አባል ሀገራት በንግድ ልውውጣቸው ወቅት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘቦች የመጠቀም ዝንባሌያቸው በመጨመሩ፣ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ንግድና መጠባበቂያ ክምችት ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት በማዳከም፤ አዲሱ ልማት ባንክ የብሪክስ የድንገተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ የምዕራባውያኑን ጥብቅ የፖለቲካ መስፈርቶች ሳይከተሉ ለታዳጊ ሀገራት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያቀርቡ ብሎም የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ከፍተኛ የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የብረታ ብረት እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች እና የዋጋ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን እያሳደገ መጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ያላቸውን የመልማት አቅም ለመጠቀም አማራጭ የልማት ፋይናንስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህ ደግሞ የብሪክስ ጥምረት ይዞት የመጣውን ዕድል በውል አንስተዋል። ለዚህም ነው በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው ሲሉ ያመላከቱት። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ከጥምረቱ የሚጠበቅ መሆኑንም ነው ያነሱት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው። የጥምረቱ አቅም ከተናጠል አካሄድ ይልቅ ትብብርና ለጋራ እሴት መጎልበት ያለውን ዕድል ያመላክታል። ኢትዮጵያ ለኮቪድ እና ኤልኒኖን ጨምሮ ለዓለም የኢኮኖሚ እና የንግድ ስርዓት መመሰቃቀል እጅ ሳትሰጥ፤ ይልቁንም መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ ለችግሮች የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ባከናወነቻቸው ተግባራት ጽናትን ገንዘቧ እያደረገች ትገኛለች። ለዚህም ነው "አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል አጀንዳ ላይ ትኩረት ባደረገው የጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ጽናትን ማጠናከር እና የአስተዳደር ስርዓት አካል የማድረግን መሠረታዊ ጠቀሜታ የገለጹት። ይህ ጽኑ ስርዓት ግንባታ ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንድትበረታ ማስቻሉን ለማሳያነት አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን አንስተዋል። በጤና ቅድመ መከላከል ፖሊሲ አካል ሆኖ የሕክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ማምረትን፣ የዲጂታል ስርዓት ሽግግርንና ደኅንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀም የማስፈን አበይት ተግባራት መከናወናቸውን ነው አጽንኦት የሰጡት። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የጀመረችው የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን የገለጹት። በእነዚህና መሰል የልማት ትብብሮች ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ነው ያረጋገጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ጥምረቱ የተቋቋመበትን ዓላማ እና መርህ በተጨባጭ እውን እያደረገች እንደምትገኝ በመጠቆም፤ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ስርዓት ማሻሻያ ባከናወነቻቸው አመርቂ ትግበራዎች፣ በታዳሽ ኃይል መስፋፋት እና የኢንዱስትሪ መሠረት ልማቶቿ፣ በግብርና ስርዓት ማሻሻያ እየተመዘገቡ ያሉ የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ትሥሥርን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት በጥምረቱ ለሚነሱ ተያያዥ የውይይት አጀንዳዎች መሪ ተዋናይ መሆን እንደሚያስችላትም አንስተዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ እሙን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው እያደረጉት ካለው ተሳትፎ ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ከተለያዩ የብሪክስ ስብስብ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። በዚህም ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግ፣ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያ፣ ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያ እንዲሁም ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን አካሂደዋል። የውይይቶቹ ማጠንጠኛም የጥምረቱን አባል ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያበረታቱ እንደ ኢንቨስትመንት፣ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ክህሎት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ ተመላክቷል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 13427
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 22539
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15559
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21308
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 107213
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80917
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59237
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56844
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40444
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40359
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39805
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38290
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 107213
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80917
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59237
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56844
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ጊፋታ እና ኮርማ ጪሻ
Sep 17, 2026 254
"ጊፋታና ኮርማ ጪሻ" (በማስረሻ ሐብታሙ ከኢዜአ ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል ሲደርስ ሜዳና ጋራው በአበቦች ይደምቃል። የአበቦቹ መዓዛ አካባቢውን ያውዳል። ሕዝቡም የወደፊቱን ብሩህ ተስፋ በዐይነ-ሕሊናው እያሰበ ዕለቱን በናፍቆት ይጠብቃል። ከአበቦች መካከልም ከሁሉ ቀድሞ የሚፈካው "ኮርማ ጪሻ" ወይም "የጊፋታ አበባ" በሰፊው መስክ ላይ ሌላ ውበትና ድምቀት ይፈጥራል። ''ኮርማ ጪሻ'' በወላይታዎች ዘንድ የጊፋታ በዓል ዋዜማና የመምጫ ወቅት መጠቆሚያ ከሆኑት የተፈጥሮ ምልክቶች አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ''ኮርማ ጪሻ'' ከአደይ አበባ የሚለይ ሲሆን፤ ነጭ ቀለም እና ትናንሽ ቅጠሎች ያሉት የአበባ ዓይነት ነው።   በወላይታ ዘመን አቆጣጠር መሠረት "ኩሻ አጊና" ወይም ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በጊፋታ ወር መባቻ ላይ በአካባቢው በስፋት በማበብ ለእይታ ድምቀት የሚሰጥና የወላይታ አዲስ ዓመት መቃረቡን የሚያበስር ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው "ኮርማ ጪሻ" ወይም "የጊፋታ አበባ"። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የወላይታ ታሪክ ተመራማሪ አቶ አዳነ አይዛ እንደሚያስረዱት፤ ቀደምት የወላይታ ሥነ-ፈለግ አዋቂዎች ዘመንን ለመቁጠር ከፀሐይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ የተፈጥሮ ለውጦችን ከመልክዓ-ምድሩ ውበትና ከተፈጥሯዊ ምልክቶች ጋር አጣምረው ይጠቀሙ እንደነበር አውስተው፤ ይህ ''ኮርማ ጪሻ'' ትልቁ ማረጋገጫ ስለመሆኑም ይገልጻሉ።   "ጊፋታ" ሲቃረብ የወላይታ ሕዝብ ለበዓሉ ሙሉ ዝግጅት የሚያደርግበት አያሌ የተፈጥሮ ምልክቶች እንዳሉት ተመራማሪው ይናገራሉ። ወላይታዎች የዝናብና የአየር ንብረት ለውጥን መሠረት በማድረግ ጊዜን የሚቆጥሩ ሲሆን፤ የክረምቱ ከባድ ዝናብና ጨለማ ወቅት አልፎ ሙሉ የፀሐይ ብርሃን መተካት ''ቦቃልሳ'' ማለትም ''ኦፊንታ'' (የፀደይ ወቅት) ሊጀምር ሲል ለጊፋታ በዓል ጥቂት ቀናት ብቻ መቅረቱን በማጥናት አንዱ ከአንዱ መረጃ መለዋወጥ ይጀምራሉ ብለዋል። የወንዞች ሙላትና መጉደልም እንደ አንድ ምልክት የሚወሰድ ሲሆን፤ ለሦስት ወራት ምድርን አጨልሞ የነበረው ጭጋግና የጉም ወቅት አልፎ በክረምቱ ጎርፍ ሞልተው የነበሩ ወንዞች ጊፋታ ሲቃረብ እየጎደሉ ይመጣሉ። ጨረቃም በአዲስ መልክ ለመውጣት በአሮጌው ዓመት በጨለማ ውስጥ ለቀናት ቆይታ ''ጤሩዋ'' ወይም መውጫ ጊዜዋ ሲደርስ በ''ግሩዋ'' (በሥነ-ፈለግ አዋቂዎች) ዓይን ከታየች፤ አዲስ ዓመት መቃረቡን በአዋጅ ሳይነገራቸው እንዲሁ በተፈጥሮ ምልክት ብቻ ዝግጅት ማድረግ ይጀምራሉ። ይህ ብቻ አይደለም፤ የጊፋታ መምጣትን ጠቋሚ የሆነው የነጭ ቢራቢሮ መንጋ የወላይታን ምድር በመውረር ከአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላኛው አቅጣጫ መብረር ሲጀምርም ጊፋታ መቃረቡን አመልካች መሆኑን አቶ አዳነ ይገልጻሉ። በዚህ ወቅት ልጆች የቢራቢሮ መንጋ ለማደን ወደ መስክ ወጥተው የሚያደርጉት ጨዋታ የጊፋታ መምጫን ልዩ ያደርገዋል፤ የበዓሉ መቃረብ ደወል ተደርጎም ይወሰዳል። በዚህ ትይዩ ወቅት የሚያብበው ''ኮርማ ጪሻ'' የክረምቱ ጨለማና ያ ከባዱ ዝናብና ጉም አልፎ ወደ ፀደይ ብርሃን በሚሸጋገርበት ወቅት የፀሐይን መውጣት ተከትሎ የሚመጣ ጊዜ ወይም ''ቦቃልሳ'' የሚባለው ወቅት ሊገባ ሲል መሆኑንም የዘርፉ ሊቃውንት ይናገራሉ። በወላይታ ባህል "ኮርማ ጪሻ" ሲያብብ ኅብረተሰቡ የጊፋታ በዓል ዝግጅቱን በይፋ የሚያጧጧፍበት ልዩ የተፈጥሮ ጥሪ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረው፤ ሳይሸራረፍ ዘመናትን እየተሻገረ ይኸው ለዛሬው ትውልድ መድረሱን የገለጹት ደግሞ በወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል፣ የታሪክና ቅርስ ተመራማሪ አቶ ግርማ ገነነ ናቸው።   "ኮርማ ጪሻ" በወላይታዎች ዘንድ ለጊፋታ በዓል "እንኳን አደረሰህ / አደረሳችሁ!" ተብሎ የሚበረከት የመልካም ምኞት መግለጫ የአበባ ስጦታ መሆኑንም አመልክተዋል። ''ኮርማ ጪሻ'' በወላይታ የዘመን አቆጣጠር እና ተፈጥሯዊ ቀመር ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ምስጢራዊ አበባ መሆኑን የገለጹት አቶ ግርማ፤ ወደ አዲስ ዘመን መሻገሪያ ምልክት፣ የተስፋ እንዲሁም ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያበስርና ለመንፈስ እርካታን የሚሰጥ ነው ብለዋል። የወላይታ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት በጨረቃ እና በፀሐይ ዑደት ላይ የተመሠረተ ሆኖ በዓሉ የሚከበርበትን ትክክለኛ ቀን፤ "አዋቂዎች" ከሚያደርጉት ስሌት ጎን ለጎን፣ የተፈጥሮ ጸጋ የሆነው ኮርማ ጪሻ ወይም የጊፋታ አበባ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። አበባው የወቅቱን መለወጥና የአዲሱን ዓመት መባቻ በተፈጥሯዊ ቋንቋ የሚነግር ነው። የዚህን አበባ ምስጢር ታላቅነት የሚያብራሩት ከሀገር ሽማግሌዎች አንዱ የሆኑት አቶ ኢያሱ ጋጃቦ በበኩላቸው፤ ይህ አበባ ለ"ጊፋታ" ወይም ለአዲስ ዘመን በዓል መግቢያ አንድ ወር ጊዜ ብቻ ሲቀረው የሚበቅልና ቀናት ሲቀሩት የሚያብብ ድንቅ የተፈጥሮ ፀጋ መሆኑን ይናገራሉ። ኮርማ ጪሻን ከጊፋታ በዓል መምጫ ወቅት ውጭ በዓመት ውስጥ ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻል ገልጸው፤ ይህንን ተፈጥሮ በመተርጎም ረገድ የቀደምት አባቶች አእምሯዊ ጥበብ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል። ''ኮርማ ጪሻ'' ወይም የጊፋታ አበባ ከጊፋታ በዓል ማግስት ባለው ማክሰኞ ዕለት ወደ አማች ቤት ወይም ወደ አበልጅ ቤት "ዮዮ ጊፋታ" በማለት ይዞ በመሄድ ለአባዎራው ይሰጣል። በዚህ ጊዜ አባወራው "ዮዮ ዮዮ" በማለት ተቀብሎ ከምሰሶ ጋር አስሮ ያስቀምጣል። ይህም የቤቱ መሶብ፣ በረከትና አዲሱ ዘመን እንደ ምሰሶው ጸንቶ እንዲኖር የሚደረግበት የአዲሱ ዓመት መቀበያ ምልክትና ምርቃት ነው፡፡ በዚህም ወቅት አባዎራው ''ጊፋታይ እንተና ቆዶፖ፤ እንቴ ጊፋታ ቆዲቴ'' ወይም "ዘመን እናንተን አይቁጠራችሁ፤ እናንተ ዘመናትን እየቆጠራችሁ ኑሩ" በማለት ይመርቃል። "ኮርማ ጪሻ" የወላይታ ነባር የሥነ-ፈለግ እውቀት የሚገለጥበት ተፈጥሯዊ እውቀት መሆኑንም ተናግረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" ዘንድሮ በ"ጊፋታ አጊና" ወይም መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ተወላጆችና የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
የአፍሪካ የልማት መሰረትና የሰላም ማስከበር አውራ - ኢትዮጵያ
Sep 16, 2026 225
ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር፣ ለአህጉሩ ሀገራት የነፃነት፣ የልማትና የሰላም ማስከበር ጥረቶች ታሪካዊና መዋቅራዊ መሰረት በመጣል ግንባር ቀደም ሚና ስትጫወት ቆይታለች። ሀገሪቱ ለአፍሪካ አንድነት፣ ለቀጣናዊ ትስስርና ለሰላም ማስከበር ያበረከተችው አስተዋጽኦም የላቀ ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ገቢር ነበብ ሆኖ፣ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጋራ ልማትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የሚመራ ነው። አገሪቱ በአፍሪካ አህጉር በሚከናወኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የመሠረተ ልማት ትስስር፣ የሰላም ማስከበርና ተዛማጅ ሁለንተናዊ መስኮች የምትጫወተው የፊት አውራነትና የመሪነት ሚና በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል። የኢነርጂ እጥረት የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛ ማነቆ መሆኑን የተረዳችው ኢትዮጵያ፣ ግዙፍ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመገንባትና ጥቅም ላይ በማዋል አህጉራዊ አርአያነቷን እያስመሰከረች ትገኛለች። በዚህ ረገድ የላቀ ምሳሌ የሚሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ ለጎረቤት አገራትም አስተማማኝ የኃይል ምንጭ በመሆን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በጥብቅ መሠረት ላይ ጥሏል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የቀጣናውን የኢነርጂ ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ፣ ዘላቂ የኃይል ልማት ትስስርን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። በተጨማሪም ከታንዛኒያ፣ ከሩዋንዳ፣ እንዲሁም ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር የኃይል መስመሮችን ለመዘርጋትና ትስስሩን የበለጠ ለማስፋፋት በትጋት እየሰራች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የኃይል ልማት ፖሊሲ ያጋራ ተጠቃሚነትንና አብሮ ማደግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ጎረቤት አገራት የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የድርሻዋን ማበርከቷን ቀጥላለች። ኢትዮጵያ የቀጣናው የሎጅስቲክስና የትራንስፖርት ዋና ማዕከል በመሆንም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን እያጠናከረች ትገኛለች። የሀገሪቱ ተቋማዊ አምባሳደር የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አፍሪካን ከእስያ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ጋር በማያያዝ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወት ወሳኝ የትራንስፖርት አውታር ሆኗል። በተጨማሪም ከጂቡቲ፣ ኬንያ እና ሱዳን ጋር የተዘረጉት የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ መሰረተ ልማቶች፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿና ከቀጣናው አገራት ጋር ያላትን የንግድና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በጥራትና በፍጥነት ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማትም ከሀገራዊና ቀጣናዊ ወሰኖች የተሻገረ ግብ በመሰነቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እና የተፈጥሮ ሀብትን ለመታደግ ያለመ ግዙፍ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ታላቅ የልማት ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነትንና የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ከማሳካት አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅናና አድናቆት ተችሮታል። የአባይ ወንዝ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሯ አማካኝነት የታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት በጎርፍና በደለል እንዳይጠቁ ከመጠበቋም በላይ፣ የጋራ የውሃ ሀብትን በዘላቂነት ለመንከባከብና ለመጠበቅ በትጋት እየሠራች ትገኛለች። ይህ ጥረት የወንዙን ዓመታዊ የውሃ ፍሰት በመጠበቅና የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ለቀጣናው አገራት ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናዊና አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ስራዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ አሁንም በግንባር ቀደምትነት እየሠራች ትገኛለች። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር በሶማሊያ (AMISOM/ATMIS)፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኮንጎና በሌሎችም የአህጉሪቱ የግጭት ቀጣናዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን በማሰማራት ረገድ የኢትዮጵያን ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለና አስተዋጽኦ ያደረገ አገር የለም ለማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ በተለይም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አል-ሸባብን የመሳሰሉ ሽብርተኛ ቡድኖች ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ሽብርተኝነትን በግንባር ቀደምትነት እየታገለች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሶማሊያ መንግሥት ተቋማት እንዲጠናከሩና ቀጣናው ሙሉ በሙሉ ከሽብር ስጋት ነፃ እንዲሆን በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በላቀ ቁርጠኝነት የተጣለባቸውን አገራዊና አህጉራዊ ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ። የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ስምምነት በማጽደቅና በተግባር ላይ በማዋል ረገድም ኢትዮጵያ የጎላ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። አህጉራዊ የንግድ ውሎችና ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የጉምሩክ አሠራሮች የተቀላጠፉና ዘመናዊ እንዲሆኑ በትጋት እየሠራች ነው። ለፓን-አፍሪካኒዝም እሴቶች መጠናከር፣ ለአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ነፃነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ የኢትዮጵያ የታሪክና የፖሊሲ ካፒታል ጠንካራ መሠረት ሆኗል። በአጠቃላይ፣ አገሪቱ የአፍሪካ የልማት ምሰሶና የሰላም ማስከበር ግንባር ቀደም መሪ በመሆን ታሪካዊና አህጉራዊ ኃላፊነቷን በተጠናከረ ሁኔታ እየተወጣች ትገኛለች። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቱን እውነተኛ ትረካዎችና የመረጃ ልውውጥ በግንባር ቀደምትነት የምታስተጋባ "የአፍሪካ ድምፅ" ስትሆን፣ እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባሉ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶቿና ለጎረቤት ሀገራት በምታቀርበው ንጹህ ኤሌክትሪክ የቀጣናውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ትደግፋለች። በተጨማሪም በባቡር፣ በአውራ ጎዳናዎች፣ በቴሌኮም፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢጋድ (IGAD) በኩል አህጉራዊ የመሰረተ ልማትና የንግድ ትስስርን በማጠናከር፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን ከመደገፍ ባሻገር በሰላም ማስከበርና በቀጣናዊ ድርድሮች ረገድ የምትጫወተው ሚና ለዘላቂ ልማትና ሰላም ትልቅ ዋስትና ሆኗል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም