ቀጥታ፡

ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታዳጊ ስፖርት አካዳሚ አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአሸናፊ ግርማ ስፖርት አካዳሚ አባላት፣ ወላጆች እና አስተባባሪዎች በአዲስ አበባ የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞው ተጫዋች በሆነው አሸናፊ ግርማ የሚመራው ይህ የልዑካን ቡድን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክና የተፈጥሮ ጸጋ በቅርበት እንዲያውቁ የሚያግዝና የሀገርን በጎ ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የስፖርት ቱሪዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።


 

የልዑካን ቡድኑ አባላት እና አስተባባሪዎች እንዲሁም የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በተፈጠረላቸው የትውልድ ሀገራቸውን የመጎብኘት እድል መደሰታቸውን ገልጸዋል።


 

በተለይ በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ እና ፈጣን እድገት መደመማቸውን መናገራቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም