ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የሀገርን ብልጽግና የሚያሳልጥ ችግር ፈቺ የፈጠራ አቅም እየጎለበተ ነው
Dec 6, 2025 19
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ የሚያሳልጥ ችግር ፈቺ የፈጠራ አቅም እየጎለበተ መምጣቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩትና በኤስ.ኤን.ቪ ዓለም አቀፍ ድርጅት ትብብር ለ10 ቀናት የተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ''ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር'' ተጠናቋል። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ፤ በውድድሩ ከተሳተፉ 251 የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪዎች ውስጥ አንድ መቶ የሚሆኑት ለሽልማት በቅተዋል ብለዋል። ''ማሰልጠን፣ መሸለምና ማብቃት” የሚል መሪ ሃሳብ በተሰጠው ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር የግብርና፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂና ሌሎች ዘርፎች ምርታማነትን የሚያሻሽሉ የፈጠራ ስራዎች መቅረባቸውን ገልጸዋል። አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችንም በመረጃ ቋት በማደራጀት በኢንተርፕርነርሽፕ ስታርት አፕ ፈጠራ የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያሳልጥ ችግር ፈቺ የፈጠራ አቅም እየጎለበተ ነው ያሉት አቶ ሰለሞን፤ በፈጠራና ፍጥነት በዕውቀትና ክህሎት የበለጸጉ ዜጎችን የማፍራት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን (ዶ/ር)፤ ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር የኢትዮጵያዊንን ዕምቅ የፈጠራ ክህሎት በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያዊያን የፈጠራ ክህሎት ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና አጋዥ የሚሆንበትን የማበረታቻ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የፈጠራ ባለሙያዎችም የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በትጋት በማለፍ ለበለጠ ውጤት እንዲበቁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቦሩ ካና በበኩላቸው፤ ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር ውጤታማ ስታርት አፖችን ማፍራት እያስቻለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በኤስ.ኤን.ቪ ዓለም አቀፍ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጁሊ ግርሃም፤ በውድድሩ የተመረጡ የፈጠራ ስራዎች ወደ ስራ እንዲገቡ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የፈጠራ ስራዎች ለኢትዮጵያ እድገት ማዕከል ሆነው እንዲቀጥሉ በትብብር እንሰራለን ብለዋል። በፈጠራ ውድድሩ በግብርና ፣ በጤና ፣ በቴክኖሎጂና ሌሎች ዘርፎችን የሚደግፉ የፈጠራ ስራዎች ተሸላሚ ሆነዋል። ከእነዚህም መካከል አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራቸው ለተኪ ምርት፣ ለግብርና ምርት ጥራት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ባማከለ መልኩ የሚኖረውን ጠቀሜታ ገልጸዋል። በቀጣይም የፈጠራ ስራቸውን በስፋት ወደ ገበያ ለማስገባትና የስራ ዕድልን ለማስፋፋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በድምቀት ለማክበር የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
Dec 6, 2025 17
ሆሳዕና፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በድምቀት ማክበር የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለፁ፡፡ 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በመጪው ሰኞ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሆሳዕና ከተማ ለሚከበረው በዓል የተደረጉ ዝግጅቶችን አስመልክተው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም በመጪው ሰኞ በክልሉ የሚከበረውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በደመቀ መልኩ ለማክበር የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የክልሉ ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹና ውብ እንዲሆኑ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል። በዓሉን በድምቀት ለማክበር በሁለንትናዊ መልኩ ሲደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በአሁኑ ወቅት በተሟላ መልኩ ተጠናቀው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችን እየተቀበሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በዓሉ ቀደም ሲል በክልሉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ ሲከበር መቆየቱንም አመልክተዋል፡፡ በዚህም በክልሉ ህዝቦች መካከል የጋራ ትርክትን ለመገንባትና የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ከማድረግ ባለፈ የኢትዮጵያዊነት እሴት እንዲጎለብት ተሰርቷል ብለዋል፡፡ የቀኑ መከበር የጋራ ትርክትን ለመገንባት ካለው ፋይዳ በተጨማሪ የክልሉን ሰላምና የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል የጎላ እገዛ እንዳለውም ገልጸዋል። በነገው እለትም በፌዴራሊዝም ዕንሰ ሀሳብ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ገልጸው፣ በመድረኩ የሚነሱ ሀሳቦችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ ሥራ ይከናወናል ነው ያሉት። በበዓሉ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጪ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ርዕሰ መስተዳድሩ አመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለመጉዳት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ከመንግስት ጋር በመሆን እንታገላለን - የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት
Dec 6, 2025 28
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለመጉዳት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ከመንግስት ጋር በመሆን እንደሚታገል የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) ገለጸ። የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) አመራር አባላት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር ባደረጉት ዘላቂ የሰላም ስምምነት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ኢትዮጵያን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ ጠላት ከውጭም ከውስጥም እያካሄደ ያለው ሴራ እንደማይሳካም የአመራር አባላቱ ጠቁመዋል። የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በክልሉ በተከሰተው ግጭት ህዝቡ ያልተገባ መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል። ይህ እንዲያበቃ ድርጅቱ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር ዘላቂ የሰላም ስምምነት ማድረጉን አስታውሰው፤ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንዲሁም ለህዝቡ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን አብራርተዋል። በማረሚያ ቤት ያሉና የገንጣይ አስገንጣይ አጀንዳ የማይከተሉ የፋኖ አባላት ከእስር እንዲፈቱ፣ የአካል ጉዳትና ሌሎች ጉዳቶች የደረሰባቸው መልሰው እንዲቋቋሙ ስምምነት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል። አቅምና ችሎታ ያላቸው የፋኖ አባላት ወደነበሩበት የስራ መዋቅር ተመልሰው እንዲሰሩ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ ጠላት ከውጭም ከውስጥም እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ከመንግስት ጋር በመተባበር ይህ ሴራ እንዳይሳካ እናደርጋለን፤ ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅምም እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የመረጃና ደህንነት ሃላፊ መስፍን አባተ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የፋኖን ትግል ለመቀማት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ። የውጭ ጠላቶችን ሴራ መገንዘብ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ድርጅቱ ወደ ስምምነቱ የመጣው ይህ የውጭ ሃይሎች ሴራ እንዳይሳካ ለማድረግም ጭምር ነው ብለዋል። ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በተደረገው ድርድር የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መደረሱን አብራርተዋል። የፌዴራል መንግሥትና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል። በዚህም ጥረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) መካከል ዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወቃል።
የመደመር መንግስት ለዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል
Dec 6, 2025 40
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት ለዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ሥራዎችን እንደሚገነባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ ማግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን አስደናቂ የልማት ስኬት መምጣቱን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ መድረክ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ''የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና የመድረኩ ተሳታፊዎች ታድመዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያን የዘመናት የብልጽግና መሻት የሚያረጋግጡ ተጨባጭ የልማት ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። ሀገራዊ ለውጥ የወለደው የብልጽግና መንግስትም አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሁሉም ዘርፎች ዕድገትን የሚያስቀጥል ልማት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባቀረቡት መነሻ ጽሁፍ፤ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ለመዲናዋ ነዋሪዎች የልማት ጥያቄ መልስ የሰጡ የልማት ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የመዲናዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተገባው ቃል መሰረትም ከግዙፍ እስከ መካከለኛ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የአዲስ አበባን የመልማት አቅም የገለጡ ስኬቶች መምጣታቸውን ተናግረዋል። የገበያ ማዕከላትን በመገንባት እንዲሁም የእሁድና ቅዳሜ ገበያ ተደራሽነትን በማስፋት የመዲናዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልልና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት ምቹ ምኅዳር መፈጠሩንም አስረድተዋል። በመኖሪያ ቤት፣ በኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ፣ በቱሪዝምና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የአዲስ አበባ ከተማን ውበት በማላበስ መዲናዋን የኢትዮጵያ ብልጽግና ተምሳሌት የሚያደርጉ ለውጦች መምጣታቸውን አንስተዋል። በቀጣይም በመደመር መንግስት የብዝኅ ዘርፍ የልማት እሳቤ የመዲናዋን ነዋሪዎች የከተሜነት አኗኗር የሚያሻሽሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት የተሳተፉ የመዲናዋ ነዋሪዎችም፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ ማግስት በአጭር ጊዜ አዲስ አበባን የሚመጥን አስደናቂ የልማት ስኬት መምጣቱን ገልጸዋል። በቀጣይም የመሠረተ ልማት ግንባታ አቅሞችንና የመልካም አስተዳደር ስኬቶችን በማስፋት የኑሮ ውድነት ጫናን የሚያቃልሉ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት፤ መንግስት ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። ለአብነትም የመንግስትን የሰላም አማራጭ የተቀበሉ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች የኢትዮጵያ የልማት አካል እየሆኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በቀጣይም የሰላም አማራጭ የሚከተሉ አካላትን ለመቀበል በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፤ መንግስት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ መለወጥ የሚያስችል የልማት ስራ እየሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ተረጂነትን ለማስቀረት የ30 ቢሊየን ዶላር የጉባ ብስራት ግዙፍ የልማት ውጥኖች ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም የመደመር መንግሥት ዜጎች የሚያነሷቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ስኬቶችን እንደሚያሰፋ አረጋግጠዋል።
ፖለቲካ

በዓባይ ወንዝ ጉዳይ የግብጽ ጠቅልሎ የመያዝ የቅኝ ግዛት ትርክት በዓለም አቀፍ የውሃ ህግም ሆነ በሌሎች መመዘኛዎች ተቀባይነት የሌለው ነው
Dec 6, 2025 55
አርባ ምንጭ፤ ህዳር 27/2018 (ኢዜአ)፡- በዓባይ ወንዝ ጉዳይ የግብጽ ጠቅልሎ የመያዝ የቅኝ ግዛት ትርክት በዓለም አቀፍ የውሃ ህግም ሆነ በሌሎች መመዘኛዎች ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚሰሩ ምሁራን ገለጹ። የዓለም ታላቁ ወንዝ ለሆነውን ዓባይ ከ86 በመቶ በላይ የውሃ መጠን የምታበረክተው የጥቁር ዓባይ መነሻ ኢትዮጵያ መሆኗ የማይካድ እውነታ ነው። በዚህ ወንዝ ላይ ከእኔ በላይ ሊወስን ብሎም ሊጠቀም የሚችል ሀገር መኖር የለበትም የሚለው የግብጽ የቅኝ ግዛት አቋምና የተሳሳተ ትርክት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። ኢትዮጵያ ዓባይ የተፋሰሱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በፍትሃዊነት የመጠቀም አቋም በመያዝ እየሰራች መሆኑን ዓለም የሚገነዘበው ሀቅ ነው። የግብጽን የተሳሳተ አቋምና የኢትዮጵያን በፍትሃዊነት የመጠቀም ጥረት በተመለከተ ኢዜአ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምሁራንን አነጋግሯል። በዩኒቨርሲቲው የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምሩ ተሰማ(ዶ/ር) ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ለዘመናት የያዘችው የተሳሳተ ትርክት ለዚህ ዘመን የማይመጥንና ሊነሳ የማይገባው አጀንዳ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የተፋሰሱን ሀገራት በማይጎዳ መልኩ ወንዙን የማልማትና የመጠቀም መብቷን የሚከለክላት እንደሌለ እየታወቀ የበይ ተመልካች ሆና እንድትኖር የግብጽ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንዳይሳካ ከዓለም አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ህግ በተቃርኖ በመቆም ብዙ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን ስታደርግ ብትቆይም በኢትዮጵያውያን ብርቱ ጥረት ግድቡ ለስኬት መብቃቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላም ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን ማድረጓን እንደቀጠለች ያነሱት ኢንጂነር ታምሩ(ዶ/ር)፣ ድርጊቷ የሚወገዝና በፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ውሃ አጠቃቀም ህግ መሰረት ምክንያታዊ፣ ፍትሃዊና የታችኞቹን የተፋሰሱን ሀገራት በጉልህ በማይጎዳ መልኩ የመጠቀም መብት መኖሩን አንስተው የግብጽ ዓላማ ግን ከእኔ ውጭ ሌላው አይጠቀም የሚል ፍፁም ግለኝነት የሚታይበት መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም በዓባይ ጉዳይ የግብጽ ጠቅልሎ የመያዝ የቅኝ ግዛት ትርክት በዓለም አቀፍ የውሃ ህግም ሆነ በሌሎች መመዘኛዎች ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል። የግብፅ ግትር አቋም ኢትዮጵያ አንጡራ ሀብቷን አልምታ የመጠቀም መብቷን የሚጋፋ ቢሆንም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ህግ መርህ ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ አካሄድ እየተከተለች መሆኑን አስረድተዋል። በዩኒቨርሲቲው የውሃ ሀብት ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ኤልያስ ገበየሁ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ግብፅ ከዓባይ ወንዝና ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የምታራምደው ግትር አቋም እና የቅኝ ግዛት እሳቤ በዚህ ዘመን ሊነሳ የማይገባውና ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ተናግረዋል። በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን በመግፋት የቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብን ለማራመድ በግብጽ መንግስት ባለስልጣናት የሚደረገው ተደጋጋሚ እንቅስቃሴ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን እውነታ ጋር የማይሄድ መሆኑን የኢፌደሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹ የሚታወስ ነው።
መንግሥታችን ሕዝብን ያዳምጣል፣ ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ይሰጣል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Dec 6, 2025 88
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ መንግሥታችን ሕዝብን ያዳምጣል፣ ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ይሰጣል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ ዛሬ ከማለዳ አንስቶ ከነዋሪዎቻችን ጋር ሰፊ ውይይቶችን አካሂደናል ብለዋል። ውይይቶቹ በመዲናችን አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ክፍለ-ከተሞች በስፋት ተካሂደዋል ነው ያሉት። የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ባለሀብቶችና ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል ብለዋል። የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋት በሚል ርዕስ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሕዝብ መድረኮች ላይ ከነዋሪዎቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች በተግባር የተሰጡ ምላሾች፣ እንዲሁም ቀሪ ሥራዎችን አስመልክቶ በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደራችን ከፍተኛ አመራሮችና ሚኒስትሮች መድረኮቹን በመምራት ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፤ የቤት ስራም ወስደዋል ነው ያሉት። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማችን በተለያዩ የልማት ሥራዎች አስደናቂ ስኬቶች የተመዘገቡት መንግሥትና ሕዝብ አንድ ሆነው በመቀናጀትና በመናበብ መፈጸም በመቻላቸው ነው ብለዋል። ዛሬም በመንግሥትና በሕዝብ ትብብር የተሰሩ በርካታ ሥራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ እንዲሁም የሕዝብን ተሳትፎ ይበልጥ በሚያረጋግጡ ቀጣይ የጋራ ዕቅዶች ላይ እንደ ወትሮው ከነዋሪዎቻችን ጠቃሚ ግብዓት ያገኘንበት ፍሬያማ የውይይት መድረክ ነበር ሲሉም ገልጸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ለሰጣችሁን ገንቢ አስተያየት፣ ለነበራችሁ ከፍተኛ ተሳትፎ፣ ለሰጣችሁን ውድ ጊዜ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል። በቀጣይም ይበልጥ ተቀራርበን መሥራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም አስታውቀዋል።
አመራሩ በትጋትና በቁርጠኝነት በመስራት ተቋማት ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ሊያደርግ ይገባል
Dec 6, 2025 63
አሶሳ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በየደረጃው ያለው አመራር በትጋትና በቁርጠኝነት በመስራት ተቋማት ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባው በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር አስገነዘቡ። በክልሉ 2ኛ ዙር "በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እምርታ" ሰልጣኝ አመራሮች በአሶሳ ከተማ የተለያዩ ተቋማትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። አመራሮቹ የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የክልሉን ገጠር ቴክኖሎጂ ብዜትና ግብርና መካናይዜሽን ማስፋፊያ ኤጀንሲ የጎበኙ ሲሆን ተቋማቱ በአጭር ጊዜ በሚያመርቷቸው የእንጨት እና ብረታብረት ውጤቶችና ማሽነሪዎች የራሳቸውን የውስጥ ገቢ ማሳደግ ችለዋል። በተጨማሪም በግብርና ውጤቶች፣ አረንጓዴ ልማት እና በሰው ሀይል ስልጠና ውጤታማ የሥራ እንቅስቃሴ እያከናወኑ እንደሚገኙ የየተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች አብራርተዋል። ጉብኝቱን አስመልከቶ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በብልጽግና ፓርቲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር፤ ተቋማቱ በአካባቢያቸው የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በመጠቀም የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ቁሳቁሶችን እያመረቱ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይህም ክልሉን ከወጪ የሚታደግና በራስ አቅም መስራት እንደሚቻል ያመላከተ ነው ብለዋል። የአመራሩ ትጋትና ቁርጠኝነት ለተያዘው ሀገራዊ ተልዕኮ ስኬታማነት ወሳኝ በመሆኑ በትጋትና በቁርጠኝነት በመስራት ተቋማት ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። አመራሮች ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ በሰለጠኑት ልክ የመፈጸም አቅማቸውን ማሳደግና ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ለሁለንተናዊ ብልጽግና መትጋት አለባቸው ብለዋል። ከጉብኝቱ ተሳታፊ አመራሮች መካከል ጫልቱ ነመራ እና አቶ አጠይብ ማህሙድ፤ በተቋማቱ የተመለከቱት የፈጠራ ስራ በአርአያነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በስልጠናውም ያሉን ፀጋዎች ፍጥነትና ፈጠራ በታከለበት መንገድ በመጠቀም ውጤታማ የልማት ስራዎችን ማከናወን እንደሚቻል ያየንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል። አመራሮቹ በጉብኝታቸው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ አሶሳ ህዳሴ ሙዚየም እና ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ እርሻ ልማት ድርጅትን እንዲሁም ሌሎችን ተመልክተዋል።
የመደመር መንግስት እይታ ሀገርን በመለወጥ ህዝብን ተጠቃሚ ስለሚያደርግ ለተግባራዊነቱ እንተጋለን
Dec 6, 2025 89
ሮቤ፤ ህዳር 27/2018 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት እይታ ሀገርን በመለወጥ ህዝብን በቀጥታ ተጠቃሚ ስለሚያደርግ ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት እንተጋለን ሲሉ የባሌ ዞን አመራሮች ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ!” በሚል መሪ ሃሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሰፊ እና ጥልቅ የሆነ ስልጠና መስጠታቸው ይታወቃል። በስልጠናው በተለይም በመንግስት አስፈፃሚ አካላት የሚተኮርባቸውን ግቦች በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን በመፍጠርና በመፍጠን የሚተገበር ቁርጠኛ አመራር መኖር እንዳለበትም አጽዕኖት ሰጥተዋል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የባሌ ዞን አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ አቅጣጫዎች ከአመራሩ ባሻገር ሀገርን መለወጥ የሚችሉና ህዝብን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው አንስተዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የባሌ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልይ መሐመድ እንዳሉት የተሰጠው ሥልጠና በአካባቢያችን የሚገኙ እምቅ ሃብቶችን በመፈተሽ ለህዝብ ጥቅም ለማዋል የሚያግዝ ነው። በተለይ በዞኑ አርሶ አደሩ ከዘልማዳዊ አሰራር ተላቆ ወደ ሜካናይዜሽን እንዲሸጋገር በኩታ ገጠም እርሻና በሌሎችም ኢንሼቲቮች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ለማስቀጠል ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል። በዞኑ በአሁኑ ወቅት በመኸሩ የምርት ወቅት የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ እየለማ የሚገኘው ከ528 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይህንኑ የሚያሳይ ነው ብለዋል። በዘርፎች እመርታ ዙሪያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የስራ አቅጣጫ ለለውጥና ማንሰራራት ወሳኝ መሆኑን የተረዳንበት ነው ያሉት ደግሞ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ኃይሌ ናቸው። በተለይ በዞኑ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና ሰፊ የሰው ኃይል በማስተባበር የታለሙትን የልማት ግቦች ለማሳካት የተሰጣቸው ሥልጠና ትልቅ ስንቅ እንደሚሆናቸውም አመልክተዋል። በባሌ ዞን የመስክ ምልከታ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ኦቱካና ኦዳ (ዶ/ር) ይህንኑ ሀሳብ ያጠናክራሉ። በዞኑ ባደረጉት የመስክ ምልከታ መንግሥት የአርሶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ ተግባራዊ እያደረጋቸው የሚገኙ የግብርና ኢኒሼቲቮች የሚታይ ለውጥ ማስመዝገብ መጀመራቸውን መመልከታቸውን አስታውሰዋል። እንዲሁም በተግባር እያታዩ የሚገኙ ስኬቶች የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያ ብልጽግና ማረጋገጫ መንገድ መሆኑን የሚያሳዩ እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይ የአካባቢው አመራሮች ከግብርና ምርምር ማዕከላት እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የአርሶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ እያደረጉት የሚገኙት ጥረት በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን አውስተዋል።
የዘላቂ ሰላም ስምምነቱ ሁሉንም ወገን አሸናፊ ያደረገና ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሰጠ ነው
Dec 5, 2025 196
አዲስ አበባ፤ህዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ የዘላቂ ሰላም ስምምነቱ ሁሉንም ወገን አሸናፊ ያደረገና ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሰጠ መሆኑን የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራር አባለት ገለጹ። በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) መካከል በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነትና አስተባባሪነት የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል። የዘላቂ ሰላም ስምምነቱን አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የምትገልጸውን የአፍሪካን ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የመስጠት መርህ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል። በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው የዘላቂ ሰላም ስምምነትም አለመግባባቶችን ሁሉንም ወገን አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ በድርድርና መነጋገር ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፤ አለመግባባቶችን በውይይትና ድርድር መፍትሔ መስጠት የሰለጠነ ፖለቲካ ሥርዓት መገለጫ ነው ብለዋል። በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) መካከል የተደረሰው የዘላቂ ስምምነትም ሰላምን የሚያጸና ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል። የዘላቂ ሰላም ስምምነቱም የውጭ ሃይሎችን ሴራን በማክሸፍ ህዝብ የልማት ሥራውን የሚያፋጥንበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል መርህ የአፍሪካ ሕብረትና ኢጋድ ለዘላቂ ሰላም ስምምነቱ መፈረም ያደረጉትን አስተዋጽኦም አድንቀዋል። በቀጣይም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አፍሪካ እንደ አህጉር ሁለንተናዊ ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የዕድገት ጉዞን ለማደናቀፍ የማይሸረብ ሴራ እንደሌለ ሁሉም መገንዘብ እንደሚገባው ተናግረው፤ ሁላችንም ለሰላም መትጋት አለብን ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በበኩላቸው፥በአማራ ክልል መንግስት እና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) የተደረሰው ዘላቂ ስምምነት ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ጥሪ መልስ የሰጠ አስደሳች ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። የአፋህድ የሰላም አማራጭ ቁርጠኝነት ለአማራ ህዝብ እፎይታን የሰጠና በትጥቅ ትግል ለሚገኙ ኃይሎችም ትምህርት የሚሰጥ በአርዓያነት የሚወሰድ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በሰላም ስምምነት ሂደቱ የተደረገው ውይይትና ድርድርም ሁሉንም ወገን በእኩልነት አሸናፊ ያደረገ፤ ለዜጎች የሰላም ፍላጎት ምላሽ የሰጠ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ሌሎችም የሰላማዊ ፖለቲካ ትግልን ተቀዳሚ አማራጫቸው ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የፌዴራል መንግሥትና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።
የአካባቢውን ፀጋ በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንተጋለን- አመራሮች
Dec 5, 2025 134
ገንዳውኃ፤ ሕዳር 26/2018 (ኢዜአ):- ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ አጠናክረው የአካባቢውን ፀጋ በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰሩ የምዕራብ ጎንደር ዞን አመራሮች ገለጹ። በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የተሳተፉበት ሥልጠና "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በገንዳውኃ ከተማ እየተሰጠ ነው። ከሥልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በብልፅግና ፓርቲ የምዕራብ ጎንደር ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ እንዳለው ማሩ እንደተናገሩት፤ ሥልጠናው በየደረጃው ያለውን አመራር ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጎልበት ያግዛል። አመራሩ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለማቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመገንዘብ ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት የድርሻውን እንዲወጣ የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። በመሆኑም እንደ አመራር አንድ ሆነን የዞኑን ሀብት በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን ብለዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ በበኩላቸው፤ ሥልጠናው የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎት እና አቅም የሚገነባ መሆኑን ገልጸዋል። የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነትን በመላበስና በሁሉም መስክ በቂ እውቀት በመያዝ ሰላምን አፅንተው የዞኑን ሕዝብ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ አመራር ዘማች ንጉሴ ፤ ሥልጠናውን በትኩረት ተከታተለው ተግባር ላይ በማዋል የወረዳውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የመጡት አመራር ስጦታው አዱኛ በበኩላቸው፤ ሥልጠናው የአመራርነት ሚናን የሚያጎለብት፤ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት የሚያዳብር ከመሆኑ ባሻገር አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን አንስተዋል። በየደረጃው የሚገኙት አመራሮቹ ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ አጠናክረው የየአካባቢውን ፀጋ በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል የሰላም ስምምነቱ ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ትልቅ ማሳያ ነው
Dec 5, 2025 124
ወልዲያ/ደብረ ብርሃን፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፡ - በአማራ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ትልቅ ማሳያ መሆኑን በአማራ ክልል ኢዜአ ያነጋገራቸው የወልዲያ እና የደብረ ብርሃን ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ። የወልዲያ ከተማ ነዋሪው አያሌው ከበደ እንዳሉት፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተደረሰው ስምምነት የሚበረታታና የሚደነቅ ነው። በስምምነቱ መደሰታቸውን ጠቅሰው፤ ሕብረተሰቡ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትና መኖር እንዲችል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። መንግስት በሆደ ሰፊነት ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል። የሰላም ስምምነቱ በተለይ እንደ ወልዲያ ከተማ ሕዝብ ትልቅ እፎይታን የሰጠ፤ የሰላም አየር የምንተነፍስበትና ስንናፍቀው የነበረ ትልቅ እርምጃ ነው ያሉት ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ የሃገር ሽማግሌ ሲሳይ ጸጋዬ ናቸው። ስምምነቱ የእናቶችንና የህጻናትን እንግልት ከማስቀረት ባለፈ ለሀገር ግንባታ ድርሻው ከፍ ያለ ነው ያሉት ነዋሪው፤ ይህንን መልካም ተሞክሮ በመውሰድም የቀሩትም ወደ ሰላም አማራጭ ሊመጡ እንደሚገባ አንስተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች መካከል ዋለልኝ አምባው እንዳመለከቱት፤ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ስምምነቱ የሚበረታታ ነው። ስምምነቱ በክልሉ ሰላምን በዘላቂነት በማፅናት የሕዝብን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ማጎልበት እንደሚያስችል ተናግረዋል። በተጨማሪም ክልሉ ያሉትን የተፈጥሮ ፀጋዎች አልምቶ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ተግባራትን ለማፋጠን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የተናገሩት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ማቲያስ ክፍሌ ናቸው። አቶ አማን መሐመድ በበኩላቸው፤ በክልሉ የነበረው ችግር ሕዝቡን የጎዳ መሆኑን አብስተው፤ ትናንት የተደረሰው ስምምነት ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት መደላድል የፈጠረ ታሪካዊና የሚደነቅ ነው ብለዋል። የሰላም ስምምነቱ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የተናገሩት። በአማራ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት በትናንትናው ዕለት መፈረሙ የሚታወስ ነው።

ማህበራዊ
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በድምቀት ለማክበር የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
Dec 6, 2025 17
ሆሳዕና፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በድምቀት ማክበር የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለፁ፡፡ 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በመጪው ሰኞ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሆሳዕና ከተማ ለሚከበረው በዓል የተደረጉ ዝግጅቶችን አስመልክተው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም በመጪው ሰኞ በክልሉ የሚከበረውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በደመቀ መልኩ ለማክበር የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የክልሉ ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹና ውብ እንዲሆኑ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል። በዓሉን በድምቀት ለማክበር በሁለንትናዊ መልኩ ሲደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በአሁኑ ወቅት በተሟላ መልኩ ተጠናቀው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችን እየተቀበሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በዓሉ ቀደም ሲል በክልሉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ ሲከበር መቆየቱንም አመልክተዋል፡፡ በዚህም በክልሉ ህዝቦች መካከል የጋራ ትርክትን ለመገንባትና የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ከማድረግ ባለፈ የኢትዮጵያዊነት እሴት እንዲጎለብት ተሰርቷል ብለዋል፡፡ የቀኑ መከበር የጋራ ትርክትን ለመገንባት ካለው ፋይዳ በተጨማሪ የክልሉን ሰላምና የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል የጎላ እገዛ እንዳለውም ገልጸዋል። በነገው እለትም በፌዴራሊዝም ዕንሰ ሀሳብ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ገልጸው፣ በመድረኩ የሚነሱ ሀሳቦችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ ሥራ ይከናወናል ነው ያሉት። በበዓሉ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጪ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ርዕሰ መስተዳድሩ አመልክተዋል፡፡
በከተማው የትምህርት መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተደረገ ጥረት ውጤት ተገኝቷል
Dec 6, 2025 34
ዲላ ፤ህዳር 27/2018 (ኢዜአ)፡- በዲላ ከተማ የትምህርት መሰረተ ልማትን በማስፋት የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል በተደረገ ጥረት ውጤት መገኝቱን የከተማው አስተዳደር ገለጸ። በዲላ ከተማ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነቡ መማሪያ ክፍሎች ተመርቀው ለአገልግሎት በቁ። የዲላ ከተማ አስተደደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በከተማው የትምህርት መሰረተ ልማትን በማስፋት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተደረገ ጥረት ውጤት ተገኝቷል። በተለይ ህብረተሰቡን፣ የግል ባለሃብቱንና ባለድርሸ አካላትን በማስተባበር ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገ ጥረት የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት ተችሏል ብለዋል፡፡ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ ለአገልግሎት የበቃው የመማሪያ ክፍል ምቹ የትምህርት ከባቢን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑንም አስረድተዋል። በከተማው በህብረተሰብና በመንግስት ትብብር ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ 56 የመማሪያ ክፍሎች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ያነሱት ደግሞ የከተማው ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ሆርዶፋ ናቸው። በዚህም በክልላዊና ሀገራዊ ፈተናዎች የማለፍ ምጣኔ መሻሻል መቻሉን ጠቅሰው ተግባሩን በማጠናከር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል። የሀላል ወጣቶች በጎ አድራጎት ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቶፊቅ ተማም በበኩሉ ማህበሩ ከ1 ሺህ 200 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በቋሚነት የመማሪያ ግብዓቶች ሲደግፍ መቆየቱን ገልጿል። በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ግለሰቦችን በማስተባበር በዲላ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስገነባቸውን አራት የመማሪያ ክፍሎች ዛሬ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉንም ተናግሯል። ይህም በእውቀትና ስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመገንባት ወሳኝ በመሆኑ በትምህርት ዘርፍ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩም ገልጿል። የዲላ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ አማኑኤል ኤፍሬም በበኩሉ ከዚህ ቀደም የነበረው የመማሪያ ክፍል ከእንጨትና ጭቃ የተሰራና የቆየ በመሆኑ ለመማር ይቸገሩ እንደነበር ገልጿል። አዲሱ መማሪያ ክፍል ምቹ የትምህርት ሁኔታ እንዲኖር የሚያስችል በመሆኑ ጠንክሮ ለመማር የሚያስችል ነው ብሏል።
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል አብሮነትን በማላቅ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ያጠናክራል
Dec 6, 2025 93
ሰመራ፣ህዳር 27/2018(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል አብሮነትን በማላቅ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ። 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ''ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሀሳብ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተከብሯል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንደገለፁት፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል አብሮነትን በማላቅ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ያጠናክራል። ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡና በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙት ተማሪዎች አብሮነታቸውን በማጠናከር በዓሉን በጋራ ለማክበር መቻላቸውን ተናግረዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመጣችው ተማሪ አበባ ኦላኔ በዓሉን በጋራ ማክበራችን አብሮነታችንንና ትስስራችንን አጠናክሮልናል ብላለች። ልዩነታችን ውበታችንና መገለጫችን በመሆኑ አንድነታችንን ከማጠናከር አላገደንም፤ ሊያግደንም አይችልም ስትልም አክላለች። ከአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን የመጣው ተማሪ ቢኒአሚን ሁሴን በበኩሉ በዓሉን ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚን በመፍጠሩ በደስታ እናከብረዋለን ብሏል። በዓሉ አንድነታችንን አጠንክረን አንድ ላይ በማክበራችን አብሮነታችን እንዲልቅ ከማድረጉም ባለፈ መተሳሰባችን እንዲጨምር አድርጓል ያለው ደግሞ ከደሴ ከተማ የመጣው ተማሪ መሐመድ የሱፍ ነው። ከኦሮሚያ ክልል ነጆ ከተማ የመጣው ተማሪ ዋቅቶላ ታሲሳ በበኩሉ በዓሉ ባህልና ወጋችንን ጠብቀን በድምቀት የምናከብረው ብቻም ሳይሆን አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ብሏል።
በክልሉ ለቱሪዝም ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት የቱሪስት ፍሰትን በመጨመር ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እያደረገ ነው
Dec 6, 2025 51
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ለቱሪዝም ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት የቱሪስት ፍሰትን በመጨመር ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው አመራርና ሠራተኞች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት የዓለም ቱሪዝም ቀን አስመልክቶ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክንና በፓርኩ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን ጉብኝተዋል። የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሰለሞን ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት የተለያዩ መዳረሻ ስፍራዎች በመገንባትና ነባሮችን በማስተዋወቅ ለኢኮኖሚ ምጭነት እንዲውሉ በትኩረት እየተሰራ ነው። ዘርፉ ከገቢ ምንጭነት ባሻገር የክልሉንና የሀገርን በጎ ገጽታ ከመገንባት አኳያ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ያመላከቱት። እየተሰሩ ያሉት ሥራዎች በክልሉ የሚገኙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን አሟጦ መጠቀም የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል። የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ምትኬ ቢተውልኝ(ዶ/ር) በበኩላቸው በክልሉ ወደ ቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች የተሰሩ መንገዶች፣ ሎጆችና ሌሎች አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ፍሰቱ እንዲጨምር አስችለዋል ነው ያሉት። ኮሚሽኑ በተለያዩ ቋንቋዎችና የማስታወቂያ ዘዴዎች በመጠቀም የክልሉን የቱሪስት መዳረሻዎች በስፋት እያስተዋወቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ ገረመው መብራቱ እንደተናገሩት፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት ፓርኩ በመሠረተ ልማት ችግር ምክንያት በቂ የቱሪስት ፍሰት እንዳልነበረው አስታውሰዋል። በመንግሥት በተሰጠው ትኩረት እየተገነቡ ያሉት መሠረተ ልማቶች ችግሩን በመፍታት ላይ መሆናቸውን ጠቁመው ይህም የፓርኩን የጎብኚዎች ቁጥር በማሳደግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ኢኮኖሚ
የመደመር መንግስት ለዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል
Dec 6, 2025 40
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት ለዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ሥራዎችን እንደሚገነባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ ማግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን አስደናቂ የልማት ስኬት መምጣቱን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ መድረክ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ''የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና የመድረኩ ተሳታፊዎች ታድመዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያን የዘመናት የብልጽግና መሻት የሚያረጋግጡ ተጨባጭ የልማት ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። ሀገራዊ ለውጥ የወለደው የብልጽግና መንግስትም አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሁሉም ዘርፎች ዕድገትን የሚያስቀጥል ልማት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባቀረቡት መነሻ ጽሁፍ፤ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ለመዲናዋ ነዋሪዎች የልማት ጥያቄ መልስ የሰጡ የልማት ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የመዲናዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተገባው ቃል መሰረትም ከግዙፍ እስከ መካከለኛ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የአዲስ አበባን የመልማት አቅም የገለጡ ስኬቶች መምጣታቸውን ተናግረዋል። የገበያ ማዕከላትን በመገንባት እንዲሁም የእሁድና ቅዳሜ ገበያ ተደራሽነትን በማስፋት የመዲናዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልልና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት ምቹ ምኅዳር መፈጠሩንም አስረድተዋል። በመኖሪያ ቤት፣ በኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ፣ በቱሪዝምና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የአዲስ አበባ ከተማን ውበት በማላበስ መዲናዋን የኢትዮጵያ ብልጽግና ተምሳሌት የሚያደርጉ ለውጦች መምጣታቸውን አንስተዋል። በቀጣይም በመደመር መንግስት የብዝኅ ዘርፍ የልማት እሳቤ የመዲናዋን ነዋሪዎች የከተሜነት አኗኗር የሚያሻሽሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት የተሳተፉ የመዲናዋ ነዋሪዎችም፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ ማግስት በአጭር ጊዜ አዲስ አበባን የሚመጥን አስደናቂ የልማት ስኬት መምጣቱን ገልጸዋል። በቀጣይም የመሠረተ ልማት ግንባታ አቅሞችንና የመልካም አስተዳደር ስኬቶችን በማስፋት የኑሮ ውድነት ጫናን የሚያቃልሉ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት፤ መንግስት ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። ለአብነትም የመንግስትን የሰላም አማራጭ የተቀበሉ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች የኢትዮጵያ የልማት አካል እየሆኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በቀጣይም የሰላም አማራጭ የሚከተሉ አካላትን ለመቀበል በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፤ መንግስት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ መለወጥ የሚያስችል የልማት ስራ እየሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ተረጂነትን ለማስቀረት የ30 ቢሊየን ዶላር የጉባ ብስራት ግዙፍ የልማት ውጥኖች ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም የመደመር መንግሥት ዜጎች የሚያነሷቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ስኬቶችን እንደሚያሰፋ አረጋግጠዋል።
መንግስት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው
Dec 6, 2025 44
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በማዳመጥ ምላሽ እየሰጠና ሀሳቦቹን በእቅድ በማካተት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በህዝባዊ ውይይት መድረክ ላይ ገለጹ። የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ መንግስት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀዋል። በአዲስ አበባ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች "የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄዷል። በኮልፌ ቀራንዮ በተካሄደው የውይይት መድረክ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ኃላፊ ሊድያ ግርማ እንዲሁም ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ሀላፊ ሊድያ ግርማ ከዚህ ቀደም ከህብረተሰቡ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ የተሰጡ ምላሾችን እና ቀጣይ የልማት ስራዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል። በገለጻቸውም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት መንግስት የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻሉን፣ የተቋማት ሪፎርም እና ዲጂታል አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረጉን ጠቁመው፤ በዚህም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሲስተዋሉ የቆዩ ብልሹ አሰራሮችን እየቀረፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኑሮ ውድነትን ለመፍታትም የምርት አቅርቦት እንዲሻሻል መደረጉን እና በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቁመው፤ መንግስት እያከናወናቸው የሚገኙ የልማት ስራዎች በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም በርካታ የልማት ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው፤ ከነዚህም መካከል ብሔራዊ ፕሮጀክቶች የሆኑት የጉባ ብስራቶችን ጠቅሰዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን አድንቀው፤ ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ሀገራዊ ትልልቅ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። በተማሪዎች ምገባ ላይ የተጀመረው ስራ እንዲጠናከርና የጤና ተቋማት ግንባታ እንዲስፋፋ ጠይቀው፤ በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን ለመፍታት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል። ከመሰረተ ልማት እንዲሁም ከውሃ እና ከኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ ጋር ያሉ ተግዳሮቶች እንዲፈቱላቸውም ጠይቀዋል። በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ፤ መድረኩ ለበለጠ መግባባት እና ስራ ይጠቅማል ብለዋል። አሁንም የላቀ ስኬት ለማሳካት በጋራ በህብረት መቆም እንደሚገባ አስገንዝበው፤ የመንግስት ትልቁ እይታው ህብረተሰቡን አዳምጦና የፍላጎቶቹን ጥያቄዎች በእቅድ አካቶ ምላሽ እየሰጠ ወደፊት እንደሚሄድ ተናግረዋል። መንግስት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በቱሪዝም እንዲሁም በዲጂታላይዜሽን ላይ በርካታ ኢኒሼቲቮች ቀርጾ ተግባራዊ ማድረጉን ገልጸው፤ ይህም በርካታ ውጤቶች እንደተመዘገበበት ገልጸዋል። ከፊት ለፊታችን ለሚጠብቁን ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው፤ በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ተይዘው በየደረጃው እንደሚፈቱም አረጋግጠዋል። የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በበኩላቸው፤ ህዝብን በማሳተፍ እንዲሁም ልማትን ብሔራዊ አጀንዳ በማድረግ በርካታ ድሎች መገኘታቸውን ጠቁመው፤ ለልማት ስራዎች የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በየደረጃው ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዓይናለም፤ የህዝብን አንድነት እና አብሮነት ሊሸረሽሩ የሚሰሩ አካላትን መታገል እንደሚገባ ነው አጽንኦት የሰጡት። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ሀላፊ ሊድያ ግርማ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፤ የውሀ ተደራሽነትን ለማሳደግ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን እና የስራ እድል ፈጠራ የርብርብ ማዕከል ሆኖ መቀጠሉን አስታውቀዋል። በቀጣይም የዜጎችን ጥያቄ በትብብር የመፍታት ስራዎች እንደሚከናወኑ አመልክተዋል።
ማዕከሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ምርጥ ዘርን በጥራትና በፍጥነት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ ነው
Dec 6, 2025 39
አሰላ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ምርጥ ዘርን በጥራትና በፍጥነት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገለጸ። የምርምር ማዕከሉ ከጂአይዜድ ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የዘር ማበጠሪያ ማሽን ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል። የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ አለማየሁ እንዳሉት ማበጠሪያ ማሽኑ ማዕከሉ የሚያባዛውን መስራች ዘር በጥራትና በፍጥነት አርሶ አደር ዘንድ ለማድረስ ቁልፍ ሚና ያለው ነው ብለዋል። ዘመናዊ የምርጥ ዘር ማበጠሪያ ማሽኑ ምርትና ምርታማነት ለመጨመር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካትም ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። ማበጠሪያ ማሽኑ በቀን እስከ 2 ሺህ ኩንታል ዘር የማበጠር አቅም ያለው ሲሆን ማሽኑ ከማዕከሉ ባለፈ በምርጥ ዘር ብዜት ለተሰማሩ የአካባቢው አርሶ አደሮች፣ ማህበራትና ባለሃብቶች ጭምር በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል። ማሽኑ ዘር ከማበጠር እስከ ማሸግ ድረስ ያለውን ሂደት በማከናወን የምርጥ ዘርን ጥራት በከፍተኛ ደረጃ የሚያስጠብቅ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ተወካይና የምርምር ጥራት ማረጋገጫና ግምገማ ዳይሬክተር በድሩ በሽር (ዶ/ር) እንደገለፁት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዛሬ ወደ ስራ ያስገባው ማሽን አገሪቷ የያዘችውን ምርታማነት የማሳደግ እቅድ ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ነው። በተለይ የስንዴና ሌሎች ሰብሎች ምርጥ ዘር በወቅቱ ለአርሶ አደሮች ለማድረስ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በየማዕከላቱ በምርምር የሚወጣውን ምርጥ ዘር በጥራትና በፍጥነት አርሶ አደሩ ዘንድ ለማድረስ ያለውን የማበጠሪያ ማሽን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ። በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በበኩላቸው የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግም ሆነ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ጥራት ያለው ምርጥ ዘር አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ማሽኑ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በክልሉ የነበረውን የምርጥ ዘር ጥራት ችግር የሚቀንስ መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ በምርጥ ዘር ብዜት ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ትልቅ እድል ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘነበ ወልደስላሴ እንደገለፁት ማሽኑ መነሻ ዘሮችን በወቅቱ አበጥሮ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ጠቀሜታው የላቀ ነው። ''ከዚህ በፊት የዘር ማበጠሪያ ማሽን እጥረትና ችግር ነበረብን'' ያሉት አቶ ዘነበ ማዕከሉ ለአገልግሎት ያበቃው ለኮርፖሬሽኑ ስራ መሳካትም ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በጉራጌ ዞን የደረሱ ሰብሎችን በኮምባይነር በመታገዝ በፍጥነት የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ ነው
Dec 6, 2025 41
ወልቂጤ፤ ህዳር 26/2018(ኢዜአ):- በጉራጌ ዞን የደረሱ ሰብሎች ምርት ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይባክን በኮምባይነርና በደቦ እየሰበሰቡ መሆኑን አርሶ አደሮች ተናገሩ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ በቸሃ ወረዳ የሸሬና ቆንደሬቼ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ኑርሀሰን ለጋሽ በሶስት ሄክታር መሬት ላይ ያለሙትን ስንዴና ጤፍ በደቦ እየሰበሰቡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አሁን ላይ እየታየ ያለው እርጥበት የምርት መበላሸት እንዳያስከትል ሁሉም የአካባቢው ነዋሪ በመተጋገዝና በመቀናጀት ምርት ሳይባክን የመሰበሰቡን ስራ እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በወረዳው የቦራና ቱባ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ዚድኒ አህመዲን በ3 ነጥብ ሦስት ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጤፍ በደቦ እየሰበሰቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያለሙትን ጤፍና ስንዴ ምርት በኮምባይነር በመታገዝ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ በዞኑ በአበሽጌ ወረዳ የማመዴ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዳዊት አሰፋ ናቸው። የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፤ በዞኑ በመኸር እርሻ በተለያዩ ሰብሎች ከለማው ከ150 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ከ5 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ። በመኸር እርሻ ወቅት ከዚህ በፊት ያልተለመዱ ሩዝን ጨምሮ በቆሎ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ጤፍና ስንዴ በኩታ ገጠም የእርሻ ስነ-ዘዴ መልማቱን ተናግረዋል። በዞኑ በእርሻው ረገድ ያለውን አቅም በመጠቀምና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ሰብል ራስን የመቻልና ገቢ የማመንጨት ጥረት ውጤት እየታየበት እንደሆነ አስረድተዋል። የደረሱ ሰብሎችን በህዝብ አደረጃጀት እንዲሁም በኮምባይነር በመታገዝ ያለብክነት የመሰብሰብ ስራ በተቀናጀ መንገድ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የሀገርን ብልጽግና የሚያሳልጥ ችግር ፈቺ የፈጠራ አቅም እየጎለበተ ነው
Dec 6, 2025 19
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ የሚያሳልጥ ችግር ፈቺ የፈጠራ አቅም እየጎለበተ መምጣቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩትና በኤስ.ኤን.ቪ ዓለም አቀፍ ድርጅት ትብብር ለ10 ቀናት የተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ''ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር'' ተጠናቋል። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ፤ በውድድሩ ከተሳተፉ 251 የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪዎች ውስጥ አንድ መቶ የሚሆኑት ለሽልማት በቅተዋል ብለዋል። ''ማሰልጠን፣ መሸለምና ማብቃት” የሚል መሪ ሃሳብ በተሰጠው ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር የግብርና፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂና ሌሎች ዘርፎች ምርታማነትን የሚያሻሽሉ የፈጠራ ስራዎች መቅረባቸውን ገልጸዋል። አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችንም በመረጃ ቋት በማደራጀት በኢንተርፕርነርሽፕ ስታርት አፕ ፈጠራ የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያሳልጥ ችግር ፈቺ የፈጠራ አቅም እየጎለበተ ነው ያሉት አቶ ሰለሞን፤ በፈጠራና ፍጥነት በዕውቀትና ክህሎት የበለጸጉ ዜጎችን የማፍራት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን (ዶ/ር)፤ ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር የኢትዮጵያዊንን ዕምቅ የፈጠራ ክህሎት በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያዊያን የፈጠራ ክህሎት ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና አጋዥ የሚሆንበትን የማበረታቻ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የፈጠራ ባለሙያዎችም የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በትጋት በማለፍ ለበለጠ ውጤት እንዲበቁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቦሩ ካና በበኩላቸው፤ ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር ውጤታማ ስታርት አፖችን ማፍራት እያስቻለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በኤስ.ኤን.ቪ ዓለም አቀፍ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጁሊ ግርሃም፤ በውድድሩ የተመረጡ የፈጠራ ስራዎች ወደ ስራ እንዲገቡ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የፈጠራ ስራዎች ለኢትዮጵያ እድገት ማዕከል ሆነው እንዲቀጥሉ በትብብር እንሰራለን ብለዋል። በፈጠራ ውድድሩ በግብርና ፣ በጤና ፣ በቴክኖሎጂና ሌሎች ዘርፎችን የሚደግፉ የፈጠራ ስራዎች ተሸላሚ ሆነዋል። ከእነዚህም መካከል አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራቸው ለተኪ ምርት፣ ለግብርና ምርት ጥራት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ባማከለ መልኩ የሚኖረውን ጠቀሜታ ገልጸዋል። በቀጣይም የፈጠራ ስራቸውን በስፋት ወደ ገበያ ለማስገባትና የስራ ዕድልን ለማስፋፋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ካሜሩን ለካምቴል እና ኢትዮ ቴሌኮም ስትራቴጂካዊ ስምምነት ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር)
Dec 6, 2025 47
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ ካሜሩን በካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (CAMTEL) እና ኢትዮ ቴሌኮም የፈጠሩት ስትራቴጂካዊ ጥምረት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) ገለጹ። የካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (CAMTEL) እና ኢትዮ ቴሌኮም በካሜሩን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማፋጠን የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን በካሜሩን ያውንዴ በመገኘት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የካምቴል ዋና ስራ አስኪያጅ ጁዲት ያህ ሰንዴይ ፈርመዋል። የሁለቱ ተቋማት ስምምነት(Master Service Agreement) የካምቴል ኩባንያ የስራ ኃላፊዎች እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2025 በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተጀመረውና ዕውን የሆነው የትብብር ግንኙነት አካል መሆኑም ተገልጿል። የካሜሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) ኢትዮ ቴሌኮም እና ካምቴል የፈጠሩት ስትራቴጂካዊ አጋርነት አድንቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታላይዜሽን የዘላቂ ልማት ምሰሶ መሆኑን ገልጸው ይህም እውን ሊሆን የሚችለው በአፍሪካ የቴሌኮም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር ሲኖር ነው ብለዋል። በዚህ ረገድም ሁለቱ ተቋማት የወሰዱትን እርምጃ አድንቀዋል። የካሜሮን መንግስት ለተቋማቱ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ጥምረቱ በኢትዮጵያ ያለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በካሜሮንም እንዲደገም ያደርጋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ዲጂታላይዜሽን በማፋጠን አካታች ኢኮኖሚ የመገንባት አቅሙን ሲያጎለብት ኢትዮ ቴሌኮም ‘ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ’ መሰረት ከአፍሪካዊ ኦፕሬተሮች ጋር በአጋርነት የዲጂታል አፍሪካን ጉዞ ለማፋጠንና ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሚከፍት ኢትዮ ቴሌኮም ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ማዕከሉ ድርቅንና በሽታን በመቋቋም በእጥፍ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ የማሽላ ዝርያዎችን እያላመደ ነው
Dec 6, 2025 54
ጂንካ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል ድርቅንና በሽታን በመቋቋም በእጥፍ ምርት መስጠት የሚችሉ ከ374 በላይ የተሻሻሉ የማሽላ ዝርያዎችን እያላመደ መሆኑን ገለጸ። የምርምር ማዕከሉ በተሻሻሉ የማሽላ ዝርያዎች ላይ እያከናወነ ያለው የጥናትና ምርምር ስራ ዛሬ ምልከታ ተካሂዷል። የማዕከሉ ዳይሬክተር እና የሰብል ተመራማሪ ተክሌ ዮሴፍ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ማዕከሉ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማላመድ የአካባቢውን አርሶ እና አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡ በተለይም እየተላመደ ያለው ማሽላ ድርቅን የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተመራጭ የሰብል አይነት መሆኑን ጠቁመዋል። የማሽላ ዝርያው ከምግብ ፍጆታነት ባለፈ ተረፈ ምርቱ ለከብቶች መኖነትና ለቤት መስሪያነት የሚያገለግል በመሆኑ ዝናብ አጠር በሆኑ ቆላማ አካባቢዎች ተመራጭ ነው ብለዋል፡፡ የሰብል ተመራማሪው አወቀ ታደሰ በበኩላቸው የምርምር ማዕከሉ ከ374 በላይ የማሽላ ዘረመሎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት በማስመጣት ላለፉት ሶስት ወራት ምርምር ሲያካሄድ መቆየቱን ተናግረዋል። በምርምር ማዕከሉ ውጤታማነታቸው ከተረጋገጡ የማሽላ ዝርያዎች ''መልካም'' የተሰኘው የማሽላ ዝርያ ተጠቃሽ ሲሆን በሄክታር እስከ 55 ኩንታል ምርት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ የማሽላ ዝርያዎቹ ከአካባቢው የማሽላ ዝርያዎች ጋር ሲነፃፀሩ ድርቅንና በሽታን በመቋቋም በእጥፍ ምርት መስጠት የሚችሉና በአጭር ጊዜ የሚደርሱ መሆናቸው ተመራጭ አድርጓቸዋል ብለዋል። በምስክ ምልከታው የተገኙት የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብረሃም አታ በበኩላቸው የምርምር ማዕከሉ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን የአካባቢውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምርምር ማዕከሉ የተመለከቷቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች መንግስት ግብርናውን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያደረገ ላለው ጥረት አጋዥ ናቸው ብለዋል፡፡ የምርምር ማዕከሉ በዞኑ ለሚከናወኑ የግብርና ልማት ስራዎች የምርምር ውጤቶችን በማበርከት ትልቅ እገዛ እያደረገ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የአሪ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ጉራልቅ ይዥማልቅ ናቸው። አካባቢው ለማሽላ ምርት ተስማሚ ስነ-ምህዳር ያለው በመሆኑ በምርምር ማዕከሉ ውጤታማነታቸው የተረጋገጡ የማሽላ ዝርያዎችን ወደ አርሶ አደሩ የማስፋት ስራ እንደሚከናወንም ገልጸዋል፡፡ በመስክ ምልከታው ላይም የዞኑ ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር በአርዓያነት የሚወሰድ አስደናቂ ሥራ እየተሰራ ነው
Dec 6, 2025 96
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር በአርዓያነት የሚወሰድ አስደናቂ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ለፓን አፍሪካ ንቅናቄና ለአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ጉልህ አበርክቶ የነበራቸው የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ልጆችና የልጅ ልጆች ገለጹ። ለፓን አፍሪካ ንቅናቄና ለአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ጉልህ አበርክቶ የነበራቸው የአፍሪካ መሪዎች ልጆችና የልጅ ልጆች የሳይንስ ሙዝየም ቋሚ ኤግዚቢሽንን ትላንት ማምሻውን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ የመጀመሪያው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የፓትሪስ ሉሙምባ ልጅ፣ የመጀመሪያው የጋና ፕሬዝዳንት ኩዋሜ ኑኩሩሃማ ልጅ፣ የኩዋሜ ኑኩሩማ የልጅ ልጅ፣ የመጀመሪያው የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳ ልጅ፣ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ እና የታንዛኒያ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ ልጅ ተሳትፈዋል። በተጨማሪም ታዋቂው ደቡብ አፍሪካዊ ፀረ አፓርታይድ ታጋይ ስቲቭ ቢኮ ልጅ፣ የፀረ አፓርታይድ ታጋይና ሚኒስትር የነበሩት ደቡብ አፍሪካዊ ዋልተር ሲሱሉ ሴት ልጅ፣ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፕሬዝዳንት፣ የፀረ አፓርታይድ ፖለቲከኛና አክቲቪስት ኦሊቨር ታምቦ ሴት ልጅና ሌሎችም ተገኝተዋል። የቀድሞው የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማ የልጅ ልጅ ክዋሜ ቶማስ፤ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታት የቴክኖሎጂ ለአህጉሪቷ ዜጎች ቅንጦት ሳይሆን ወሳኝነቱን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት ይኖርባቸዋል ብሏል። ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ግብርና፣ ታዳሽ ኃይል አስደናቂ ስራ እየሰራች መሆኗን በሳይንስ ሙዝየም ቋሚ ኤግዚቢሽን መመልከቱንም ገልጿል። የቀድሞው የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማ ልጅ ሳሚያ ያባ ክርስቲና፤ በአፍሪካ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማትን የሚያሳልጡ በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል ማፍራት እንደሚያስፈልግ ገልጻለች። በኢትዮጵያም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት እየተከናወነ የሚገኘው አስደናቂ ስራ የአህጉራዊ የቴክኖሎጂ መሪ ተዋናይነቷን እንደሚያሳድግ ተናግራለች። የጸረ-አፓርታይድ ፖለቲከኛ፣ አክቲቪስትና የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኦሊቨር ታምቦ ልጅ ኖማቴምባ ታምቦ፤ በፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ የአህጉሪቷ ወጣቶች የሚማማሩበትን መድረክ መፍጠር ያስፈልጋል ብላለች። አፍሪካዊያንም የአኗኗር ባህል የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ በማድረግ አሰባሳቢ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልጻለች። የፓን አፍሪካ ንቅናቄና አፍሪካ ሕብረት መስራች ተዋንያን የአፍሪካ መሪዎች ልጆችና የልጅ ልጆች የሳይንስ ሙዝየም ቋሚ ኤግዚቢሽን የቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን የልማት ስራዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ስፖርት
አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
Dec 6, 2025 26
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሙጂብ ቃሲም በአምስተኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በ16 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ15 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ዝቅ ብሏል።
አስቶንቪላ የሊጉ መሪ አርሰናልን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
Dec 6, 2025 24
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር አስቶንቪላ አርሰናልን 2 ለ 1 አሸንፏል። በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማቲ ካሽ በ36ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ አስቶንቪላን መሪ አድርጓል። ሊያንድሮ ትሮሳርድ በ52ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ግብ አርሰናል አቻ ሆኗል። 95ኛው ደቂቃ ላይ ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ያስቆጠራት ጎል አስቶንቪላን አሸናፊ አድርጓል። ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል። በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ አርሰናል 33 ነጥብ ላይ ረግቷል። በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በ30 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ
Dec 6, 2025 52
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዲስ ግደይ በአራተኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ግብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪ መሆን ችሏል። ጌትነት ተስፋይ በ65ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና ስምኦን ማሩ በ96ኛው ደቂቃም በጨዋታ ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ግቦች ወልዋሎን አሸናፊ አድርጓል። ጋናዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋች ካሌብ አማንክዋ በመጀመሪያ አጋማሽ ማብቂያ በሁለት ቢጫ ካርዶች በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ20ኛ ወደ 18ኛ ከፍ ቢያደርግም አሁን ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስምንት ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።
አካባቢ ጥበቃ
ረቂቅ አዋጁ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስራዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ጉልህ ጠቀሜታ ይኖረዋል
Dec 5, 2025 96
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ አዋጅ የሀገሪቱን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ ገለጹ። በሕዝበ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት እና የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይፋዊ ውይይት መድረክ አካሂደዋል። በምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ በዚሁ ወቅት፤ የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ በተለያዩ አሰራሮች ላይ መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡ አንድ ወጥ በሆነ አሰራር፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችና ሀገሪቱ ከደረሰችበት ደረጃ ጋር በተጣጣመ መልኩ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የሀገሪቱን የበለጸገ የስነ ምህዳር ሀብት ዘላቂ በሆነ ወጥ አሰራር ለማጠናከር የአገልግሎት ክፍያ ስርዓቱ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የደን ልማቶች የግብርና ምርታማነትን በማጎልበት አረንጓዴ ልማቶችን የበለጠ ውጤታማ ያደርጋል ብለዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ የተፈጥሮ ሀብቶችን ጥበቃና እንክብካቤን በማጠናከር አካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና የህብረተሰቡን ተጋላጭነት መቀነስ አስፈላጊ ነው። ረቂቅ አዋጁ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች አካባቢያቸውን በመጠበቃቸው ለአገልግሎታቸው ክፍያ እንዲያገኙ የሚያደርግ የማበረታቻ ስርዓት የሚዘረጋ ነው ብለዋል። ስነ ምህዳር ላይ ጉዳት የሚያደርሱ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የአካባቢን ጥበቃ በዘላቂነት የሚያበረታታ ሂደትን የሚፈጥር አዋጅ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙ ባለ ድርሻ አካላት የስነ ምህዳር አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ረቂቅ አዋጁ ላይ መካተት የሚገባቸውን ጉዳዮች፣ ግልጽነትን የሚጠይቁና ከትርጉም ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤በረቂቅ አዋጁ የስነ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ላይ የማህበረሰቡና የባለ ድርሻ አካላት ተጠቃሚነት፣ ተሳታፊነትና ፍትሃዊነት በግልጽ መቀመጡን ተናግረዋል። አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ የመንግስት ተቋማትና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት አገልግሎት አቅራቢዎች ይሆናሉ ብለዋል። ከግብርናና ከደን ልማት ጋር ተያይዞ የስነ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ አስገዳጅ የሆነባቸው አዋጆች መኖራቸውን ጠቅሰው ረቂቅ አዋጁ የክፍያ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። የፌደራልና የክልል ባለ ድርሻ አካላትን ሚና እና ሀላፊነትም በግልጽ አስቀምጧል ብለዋል። በምክር ቤቱ የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)፤ በረቂቅ አዋጁ ላይ አሻሚ ትርጉም የሚሰጡ፣ ግልጽነት የጎደላቸው ጉዳዮች ተሻሽለው ጠንካራ አዋጅ እንዲወጣ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
በኢሉባቦር ዞን በክረምቱ ወቅት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ እየተከናወነ ነው
Dec 2, 2025 246
መቱ ፤ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፡-በኢሉባቦር ዞን በክረምቱ አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በዘመቻ መልክ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የዞኑ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች የተሳተፉበት በክረምቱ ወቅት የተተከሉ ችግኞችን በጋራ እየተንከባከቡ ናቸው። የኢሉባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አወል መሐመድ በዞኑ በክረምቱ ወራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰዋል። የችግኞቹን የጽድቀት መጠን ለማሳደግም ህብረተሰቡ እንክብካቤ እንዲያደርግ ግንዛቤ በመፈጠሩ የዞኑ የመንግስት ሰራኞችን ጨምሮ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎች ባሳተፈ መልኩ እንክብካቤው በዘመቻ መልክ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም የጽድቀት መጠናቸው በአሁኑ ወቅት ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን ተናግረዋል። ለችግኞቹ የሚደረገው እንክብካቤ ጽድቀታቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ በአጭር ግዜ ደርሰው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው እንዲጎላ እንደሚያግዝም አመልክተዋል። በችግኝ እንክብካቤው ከተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች መካከል የዞኑ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ባለሞያ አቶ መላኩ ከበደ በበኩላቸው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድነት የተከልናቸውን ችግኞች በአንድነት የመንከባከብ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል። በመንግስት አገልግሎት ለህዝብ ከሚሰጧቸው አገልግሎት ባለፈ በክረምቱ ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከብ እንዲጸድቁ ለማድረግ በስፍራው መገኘታቸውን ገልጸዋል። በአረንጓዴ አሻራ የተከልሏቸው ችግኞች የሚጠበቀውን ውጤት ለማግኘት መትከል ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የእንክብካቤ ስራውን ማጠናከር በማስፈለጉ ለዚሁ ተግባር መጥቻለሁ ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ፋጡማ የሱፍ ናቸው። አቶ እንዳሻው ጆቴ በበኩላቸው የተተከሉ ችግኞችን በጋራ በመንከባከብ ለውጤት ለማብቃት ያልተቋረጠ ክትትል በማስፈለጉ በተከላ ወቅቱ የገቡትን ቃል በተግባር ለማዋል ስራው ላይ መገኘታቸውን ጠቁመዋል። በክረምቱ የተተከሉት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተገቢው እንክብካቤ ካልተደረገላቸው በመጥፋት የወጣባቸው ከፍተኛ ገንዘብ ለብክነት እንደሚዳረግም አክለዋል።
ኢትዮጵያውያን የደመቁበት የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ
Dec 1, 2025 254
ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ ተከናውኗል። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ የሽልማት መርሃ ግብሩ የሚዲያ አጋር ሲሆን የሁለት ቀኑን የሽልማት መርሃ ግብር የቀጥታ ስርጭት ሽፋን በመስጠት ለመላው አፍሪካውያን ተደራሽ አድርጓል። የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ(አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ አድርጓል። የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ ተሳታፊ የሚዲያ ባለሙያዎች ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያን ጎብኝተዋል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች ተከናውኗል። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት የሚዲያ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያስገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የሚዲያ ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ከ94ቱ ኢትዮጵያውያን የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል ሶስቱ በተለያዩ ዘርፎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የ2025 የሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ አሸናፊ በመሆን ሽልማቱን ተቀብሏል። ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ ሽልማቱን የተጎናጸፈው “Climate Intelligence for Survival: IGAD’s Push for Accurate, Actionable Data” በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሁፍ ነው። የጋዜጠኛ ጌትነት ጽሁፍ በኢጋድ ቀጣና ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ፈተና የሚዳስስ ነው። በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰት ድርቅ፣ የጎርፍ አደጋዎችና ኢ-ተገማች የአየር ጸባይ ለውጦች ዜጎችን በማፈናቀል እና በቁም እንስሳት ላይ ያደረሱትን ጉዳት ይቃኛል። ትክክለኛ፣ ጊዜውን የጠበቀና ለተግባር ምላሽ የሚያገለግሉ የአየር ንብረት መረጃዎች የማይበገር አቅም ለመገንባትና አደጋዎችን ለመከላከል ያላቸውን ሚናም ተዳሷል። በጽሁፉ ላይ የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያና ትግበራ ማዕከል(ICPAC) የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር፣ የትንበያ አቅም ማሳደግና የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት የመቋቋም አቅም ላይ እያከናወነ ያለው ስራ ተቀምጧል። የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎች፣ የአንበጣ መንጋ፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብና ሌሎች ፈተናዎችን ለመከላከል ተአማኒነት ያለው የአየር ንብረት መረጃ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል። በተለይም ኑሯቸው በተለያዩ ወቅቶች ላይ ለተመረኮዙ አርሶ እና አርብቶ አደሮች መረጃው ወሳኝ መሆኑን ያስቀምጣል። ሌላኛው ተሸላሚ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤ) ጋዜጠኛ ሽመክት ጉግሳ ነው። የተሸለመበት ዘርፍ በኦሮምኛ ቋንቋ በሰራው ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ ዛፎች ከሰው ህይወት ጋር ያላቸውን ቁርኝት በዋናነት ይቃኛል። መንደርደሪያውን ከዓለም የዛፍ ጠቀሜታና ጥበቃ በማድረግ በኦሮሚያ ክልል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ይዳስሳል። ዛፍ መትከል ተፈጥሮና የሰው ልጅን እንዴት እንደሚጠብቅ በተቃራኒው መቁረጥ የሚያደርሰውን ጉዳትም ያስቃኛል። የ21 ደቂቃ ፕሮግራሙ የኦሮሞ ህዝብ በዘመናት መካከል ዛፎችና የደን ሀብቶች እንዲጠበቁ ያደረገው አስተዋጽኦ ተወስቶበታል። በተለይም በገዳ ስርዓት ውስጥ ዛፍን መጠበቅ ያለው ሚና በስፋት ተነስቷል። አንድ ዛፍ ለአራት ሰዎች መኖር መሠረት ይሆናል፤ ዛፍ መቁረጥ አራት ሰዎችን እንዲሞቱ ያደርጋል የሚል የአባገዳ አስተያየትም ተጠቃሽ ነው። አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እናቶችና የአካባቢ ማህበረሰቦች ተፈጥሮን ጠብቆ በማቆየት ያላቸው ሚና ቁልፍ እንደሆነ ተመላክቷል። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መስራችና ስራ አስኪያጅ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የህይወት ዘመን ጋዜጠኝነት ሽልማት ተበርክቶላታል። ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ በሬዲዮ ጋዜጠኝነት ግንባር ቀደምና በዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቷንም ኢጋድ ገልጿል። በብሮድካስት ሚዲያው ከ40 ዓመት በላይ የቆየችው ጋዜጠኛ መዓዛ ሸገር ኤፍኤም 102.1ን ከ18 ዓመታት በፊት በማቋቋም በኢትዮጵያ ቀዳሚ የመረጃ እና የመዝናኛ ጣቢያ እንዲሆን ማድረጓ አመልክቷል። ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ አበይት ፕሮግራሞች መካከል “ማንን ምን እንጠይቅልዎ?” እና “ሸገር ካፌ” ተጠቃሽ ናቸው። ጋዜጠኛዋ በፕሮግራሞቹ ህዝብን ከመንግስት አገልግሎቶች ጋር በማገናኘትና በማህበራዊ፣ የህግ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ላይ የተመረኮዙ ውይይቶች እንዲካሄዱ መድረክ መፍጠር መቻሏንም ነው የገለጸው። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መሪ ሀሳብ በሆነው የእናንተ ሬዲዮ መዓዛ በጋዜጠኝነት ሙያ ህዝብን ለማገልገልና የኢትዮጵያውያንን ድምጽ ለማጉላት ያላትን ቁርጠኝነት ኢጋድ አድንቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ኢጋድ አመልክቷል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ወደ ሀገሪቱ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ ይቀጥላል
Dec 1, 2025 240
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገሪቱ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንደገለፀው በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል። ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጥቂት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናቶች ላይ በተዳከመ ሁኔታ ቀጣይነት ይኖራቸዋል። በዚህም የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ገልጿል። በሌላ በኩል ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት በጥቂት የሰሜን፣ መካከለኛውና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ አዊ ፣ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ትንበያው አብራርቷል። የምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ እና የማኦኮሞ ልዩ ዞን፤ የጋምቤላ ክልል ዞኖች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖችም አልፎ አልፎ ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። ስለሆነም በሚኖሩት ደረቅ ቀናቶች የደረሱ ሰብሎች መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገሪቱ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩም በመግለጫው ተብራርቷል። በዚህም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በተለይም በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መካከለኛውና ደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የለሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን ትንበያው ያሳያል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል
Dec 4, 2025 188
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተከናውኗል። በዕውቅና መርሃ ገብሩ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ ሚኒስትሮችና ተወካዮች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሽልማቱ ለአፍሪካ ጋዜጠኝነት፣ ብሮድካስት ሚዲያ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ዘገባዎች እውቅና የሰጠ ነው። በአፍሪካ ሚዲያ ምህዳርን በመቅረጽ ሚናቸውን የተወጡ ጋዜጠኞች ተሸልመዋል። ምርጥ የዜና ዘገባ፣ ምርጥ ቃለ መጠይቅ፣ ምርጥ ዶክመንተሪ፣ ምርጥ ወቅታዊ ፕሮግራም፣ ምርጥ አፍሪካ ተኮር የመዝናኛ ፕሮግራምና ምርጥ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እና ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው። አፍሪካ ተኮር ምርጥ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ምርጥ የወቅታዊ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ እና ምርጥ አጭር የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል የማህበራዊ ሚዲያ ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው። ሁሉም እጩዎች 2000 ዶላር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በእያንዳንዱ ዘርፍ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች የስድስት ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝተዋል። የምርጦች ምርጥ የይዘት ፈጣሪዎች አሸናፊም "The Golden Alkebulan" የተሰኘ ልዩ በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። በሽልማቱ ላይ ከ40 ሀገራት በላይ የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ከ800 በላይ ስራዎችን ማቅረባቸውን ተገልጿል። የአፍሪካ ሕብረት ብሮድካስቲንግ፣ የፓትሪስ ሉሙምባ ፋውንዴሽን፣ የክዋሜ ንክሩማህ ፋውንዴሽን፣ የምዋሊሙ ኒዬሬሬ ፋውንዴሽን፣ የኬኔት ካውንዳ ሌጋሲ ፋውንዴሽን፣ የሲሱሉ ፋውንዴሽን ለማኅበራዊ ፍትህ፣ የፒኤልኦ ሉሙምባ ፋውንዴሽንና የሩስያው አር ቲ ሚዲያ የሽልማቱ አጋር ናቸው።
ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው - የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች
Dec 1, 2025 272
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ሲሉየምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ገለጹ። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን ትርክት በመቀየር ትልቅ ሚና የሚወጣ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ይታወቃል። የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በሴት ጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ ከሆኑት መካከል ዩጋንዳዊቷ ጋዜጠኛ አይባሬ ሲንደሬላ ኢትዮጵያ በዜጎቿ አስተዋጽኦ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቃለች። በበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሚከፍሉት ታክስ ተጨባጭ ውጤቶችን እምብዛም ሲያዩ አይስተዋልም ያለችው ጋዜጠኛዋ ኢትዮጵያ በግልጽነትና በጠንካራ ራዕይ የህዝብን ሀብቶች አሻጋሪ ብሄራዊ ፕሮጀክት መቀየሯን ተናግራለች። የአፍሪካ መሪዎች ከሕዳሴ ግድብ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ሊወስዱ ይገባል ብላለች። የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አዘጋጅ አሻ ሃሚሲ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው ገልጻለች። ሕዳሴ ግድብ ዜጎች ለሀገራቸው መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው ያለችው አሻ ይህም በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ መተማመንና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ላይ መስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላከት ነው ብላለች። ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ እንደሆነም ተናግራለች። በኢጋድ ሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ካሸነፉት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ሱዳናዊው የፊልም ባለሙያ እና ተራኪ ጋብርኤል ጋትሉዋክ ዋል ኬት በበኩሉ ህዳሴ ግድብ አፍሪካ ያላትን አቅም በተግባር ያሳየ ነው ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ካሳካች ሌሎች ሀገራትም ይህን ፈለግ ተከትለው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይችላሉ ብሏል። አፍሪካውያን ሀገራቸውን በራሳቸው መገንባት እንደሚችሉ ማመን አለባቸው ያለው ኬት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ሌሎች እንዲወስኑላቸው መፍቀድ የለባቸውም ሲልም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን እና በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት አንስተዋል። ሕዳሴ ግድ የአፍሪካ የስኬት ተምሳሌት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው ከግድቡ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ይህም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ራዕይ የሆነውን የበለጸገች እና የተሳሰረች አፍሪካን የመፍጠር ራዕይን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። ግድቡ የአፍሪካን ትርክት የመቀየር ትልቅ ኃይል ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል
Nov 21, 2025 630
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ገለጸ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችና የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች ላይ የዌብናር ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ወሳኔ ሰጪዎች፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ ክፍል ኃላፊ ኦዬባንኬ አበጂሪን፤ የምንፈልጋትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት የ2030 ዘላቂ የልማት አጀንዳና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አፈፃጸም ሂደትን የሚከታተል የሪፖርት ሥርዓት መኖሩንም ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት ክትትል ሥርዓትም የአህጉሪቷን ዘላቂና ቁልፍ የልማት ማዕቀፎች አፈፃጸም የሚገመገምበትን መድረክ በማመቻቸት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። እ.ኤ.አ የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት መድረክም የአህጉሪቷ ልማት በሳይንስና ማስረጃ የተመሰረቱ የመፍትሔ አፈፃጸሞችን ያመላከተ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሪፖርቱም የአፍሪካ ዕድገት በጤና፣ በሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በውቅያኖስ ጥበቃና ዓለም አቀፍ ሽርክና ጋር በአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ የ2030 ዘላቂ የልማት ግብና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ወሳኝ አካል መሆኑን አስረድተዋል። የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የትብብር ሥርዓትን በማጠናከር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርትም ወሳኝ የአፈፃጸም ግኝቶችን በማረም የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን በሚገባ ለመተግበር አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። በመድረኩም የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦችና አጀንዳዎች የአፈፃጸም ስኬት ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ የሚችል ተግባቦት መፈጠሩን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካትም አዲስ ዓለም የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። መድረኩም ብሔራዊና ቀጣናዊ የልማት ስኬት አፈፃጸም የአሰራር ስርዓቶችን በመፈተሽ ዕድሎችን በማስፋት የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት አጀንዳዎ ማሳካት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነት አድማሳቸውን ለማስፋት እንደሚሰሩ ገለጹ
Nov 20, 2025 523
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ በትምህርት እና ዲጂታል ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በአፍሪካ ህብረት ዋና ኮሚሽን ዛሬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህብረቱን የጎበኙ የመጀመሪያ ማሌዥያ መሪ ሆነዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። ሊቀመንበሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የአፍሪካ እና ማሌዥያ ትብበር ውስጥ ታሪካዊና የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ ትብብር እንደሚያጠናክር አመልክተዋል። እ.አ.አ በ2024 የአፍሪካ እና ማሌዥያ የንግድ ልውወጥ መጠን 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱን ጠቅሰው፤ ይህም በዘርፉ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ትምህርት የሁለቱ ወገኖች አጋርነት ዋነኛ ምሰሶ መሆኑንና ከእ.አ.አ 2012 አንስቶ ከ40 ሺህ በላይ አፍሪካውያን በማሌዥያ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን ገልጸዋል። ማሌዥያ ቀጣይ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ሊቀ መንበር መሆኗ እና ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት ኢንቨስትመንትን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ነው ያሉት። ሁለቱ ወገኖች በዲጂታል ኢኖቬሽን፣ በግብርና ማቀነባበሪያ ልማት፣ በደቡብ ደቡብ ንግድ እና ትምህርት ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ገልጸዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ ዓመታዊ ምክክር እ.አ.አ በ2026 እንዲካሄድ ሀሳብ አቅርበዋል። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በበኩላቸው፤ ማሌዥያ እና አፍሪካ ንግድ፣ ግብርና እና ትምህርትን ጨምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ትብብር እያደገ መምጣታቸውን አመልክተዋል። ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ በማስፋት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በውይይቱ ላይ የማሌዥያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነታቸውን አድማስ ለማስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል::
ሐተታዎች
ለቀጣናዊ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ልህቀት እውቅና የሚሰጠው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት
Nov 28, 2025 421
የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተጀመረው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አማካኝነት ነው። ሽልማቱ የኢጋድ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና ተቋማዊ አቅምን የማጠናከር ጥረቶች አካል ነው። በኢጋድ ቀጣና በጋዜጠኝነት የላቀ ስራ ላከናወኑ የሚዲያ ባለሙያዎች በሽልማቱ እውቅና ይሳጣቸዋል። ሽልማቱ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ሌሎችም ተጓዳኝ መድረኮችን የሚሸፍን ነው። የሚዲያ ስራው በቀጣናው በተለይም የድርቅ አይበገሬነት፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ያሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል። ዓመታዊው የኢጋድ ሽልማት የቀጣናዊ ተቋሙ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ በግላቸው የሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና የፎቶ ጋዜጠኞች ጨምሮ አጠቃላይ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው። በተጨማሪም የቀጣናውን ጉዳይ የሚሸፍኑ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችም ይሳተፉበታል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ስራቸውን በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ እና በኢጋድ አባል ሀገራት በሚገኙ ቋንቋዎች ያቀርባሉ። ከተለያዩ ሙያዎች የተወጣጡ የውሳኔ ሰጪ ወይም ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሙ ስራዎቹን በመመዘን አሸናፊዎችን ይለያል። የመጀመሪያው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2023 በጅቡቲ ነበር። “የድርቅ ተጽእኖዎችን መቋቋም የሚያስችል ትብብር መፍጠር” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። መሪ ሀሳቡ በድርቅ፣ አይበገሬ አቅም መገንባት፣ የውሃ አስተዳደር እና ቀጣናዊ ትብብር ያተኮረ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመንት፣ ጦማር (ብሎግ) እና የፎቶ ጋዜጠኝነት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። በመጀመሪያው ሽልማት ላይ ከቀጣናው 105 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን 14 ባለሙያዎች በዘርፎቹ ተመርጠው ተሸልመዋል። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ተቋሙ ሚዲያን ለግንዛቤ መፍጠር እና ቀጣናዊ ትብብር እንደ መሳሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ በወቅቱ ገልጾ ነበር። በድርቅ እና በምግብ ዋስትና ላይ ያሉ የጋራ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚዲያ ሚና ወሳኝ እንደሆነም አመልክቷል። ሁለተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2024 በኬንያ ናይሮቢ ነው። “የተስፋ ትርክቶች፤ የቀጣናውን መጻኢ ጊዜ ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ሁሉን አቃፊ ማድረግ” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሽልማቱ በሰላም፣ ደህንነት፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ መጻኢ ጊዜን መፍጠር፣ ቀጣናዊ ትብብር እና መረጋጋት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የእድሜ ዘመን ተሻላሚ ከሽልማት ዘርፎቹ ውስጥ ናቸው። ለ2024ቱ ሽልማት 318 የሚዲያ ባለሙያዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን 18 የሚዲያ ባለሙያዎች በዘርፎቹ ሽልማት አግኝተዋል። ሁለተኛው ሽልማት ከመጀመሪያው በዘርፎች እና በተሳታፊዎች ብዛት መሻሻል የታየበት ነበር። ይህም ሚዲያ በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት እና ቀጣናዊ ትስስር ላይ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ ነው። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መጥቷል። ሽልማቱ ነገ ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን ነው። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያና የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቋል። የዚህ ዓመት ሽልማት በአፍሪካ ቀንድ ውጤታማ የአየር ንብረት ትርክትን ለቀረጹ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። የሁለት ቀን ሁነቱ የአየር ንብረት ጠንካራ ዘገባዎች እና ሀሳቦች የሚቀርቡበት እንዲሁም ቀጣናዊ ትብብር ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች የሚከናወን ነው። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶች ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚዲያ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ሙያተኞች እንደሚሳተፉም ገልጿል። የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቁ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዘገባዎች እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ብዝሃ ድምጾች እንዲሰሙ በማድረግ፣ ለዴሞክራሲ እሴቶች መጎልበት እና ዘላቂ ልማት የበኩሉን ሚና ይወጣል።
የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አዘጋጅነት
Nov 14, 2025 685
ለረጅም አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ምሰሶ ሆና ቆማለች። በሀገራት መካከል የግንኙነት ድልድል እና የአንድነት መልዕክተኛ መሆን ችለላች። ከምስረታው አንስቶ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት። የአፍሪካ መዲና በመባል የምትጠራው አዲስ አበባ በርካታ ድርድሮች፣ የሰላም ውይይቶች እና አህጉራዊ ውሳኔዎች የተላለፈባቸው ሁነቶች ተስተናግደውባታል። ውሳኔዎቹ የአፍሪካ ቀጣና ፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ናቸው። የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና ከዲፕሎማሲውም የተሻገረ ነው። ሀገሪቷ የገባችውን ቃል ከተግባር ጋር በማጣጣም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚለኩ ውጤቶችን እያስመዘገብች ትገኛለች። የተራቆቱ መሬቶች ወደ ነባር ይዞታቸው እንዲመለሱ በማድረግ እና የታዳሽ ኃይል አማራጮቿን በማስፋት ለአረንጓዴ ልማት እና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ ሚሊዮኖችን ከዳር እስከ ዳር በማነቃነቅ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ከችግር ተናገሪነት ወደ ተጨባጭ መፍትሄ አመንጪነት ሽግግር በማድረግ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ምሳሌ የሚሆን ተግባር አከናውናለች። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም ደረጃ ያላትን ተአማኒነት እና ተቀባይነት እንዲያድግ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በከባቢ አየር ጥበቃ ቁርጠኝነት እና አቅምን በማጣመር ለውጥ አምጥታለች። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያገኘችው እምነት እና የመሪነት ሚና ውጤት የሚያሳይ ተጨማሪ ሃላፊነት ከሰሞኑ ከብራዚል የደን ከተማ ቤለም ተሰምቷል። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) በቤለም እየተካሄደ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በአንገብጋቢ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ ይገኛል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የገቡትን ቃል በተግባር ለመቀየር ቁርጠኝነት ባነሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መፈጸሟን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላት ገልጸው የዳበረ የትራንስፖርት አገልግሎት ከብዙ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫነት ጋር ሲደመር የዝግጁነት አቅሟን በላቀ ሁኔታ እንደሚያሳድገው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ልምዱም አቅሙም እንዳላት ገልጸው፣ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ናይጄሪያም ጉባኤውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባ ነበር። የኢትዮጵያ የኮፕ 32 የማስተናገድ ፍላጎት ከአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል። የወቅቱ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን ሊቀመንበር የሆነችው ታንዛንያ የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጻለች። የአፍሪካውያን ውሳኔ ከቃል ባሻገር ኢትዮጵያ የአህጉሪቷን የአየር ንብረት የቅድሚያ ትኩረቶች የማራመድ እና የመወከል አቅም አላት ብለው ይሁንታ የሰጡበት ነው። ይህ ጠንካራ እምነት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሁሉን አፍሪካውያን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ እና አህጉሪቷን ያማከለ ውሳኔዎች በዓለም መድረክ እንዲተላለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግም ነው። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስናግድ ድጋፍ በመስጠታቸው አመስግነው፤ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ አበክራ እንደምትሰራ ተናግረዋል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ መሰል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት ማስተናገድ እንደምትችል የሚያመላክት ነው ብለዋል። አዲስ አበባ እንግዶቿን በሚመጥን ደረጃ ጉባዔውን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደሩ፥ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ሌሎች ሀገራትም ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የኮፕ 32ን ለማስተናገድ መመረጧ በድንገት የመጣ ጉዳይ አይደለም። በተግባር የተረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የመሪነት ሚና፣ አረንጓዴ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያከናወነች ያለቻቸው ስራዎች እና የፖለቲካ ቁርጠኝነቷ፣ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ድምጽ እና ምልክት መሆኗ ከቃል ባለፈ በተጨበጠ ስራ መታየቱ፣ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ ውጤታማነቷ እና የዲፕሎማሲ ተሰሚነቷ ድምር ውጤቶች እንጂ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስተናግድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠን ክብር ይሰማናል ብለዋል። አፍሪካ በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በብራዚል በአንድ ድምጽ ተናግራለች፤ ዓለምም አዳምጧል ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2027 በአዲስ አበባ COP 32ን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለደገፉ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ምሥጋና አቅርበዋል። በሰው ልጆች ኑሮ በጣም አንገብጋቢ ከሆኑት ተግዳሮቶች መካከል አንዱን ለመቅረፍ እንዲቻል የጋራ ጥረቶችን ለመምራት ዕድሉን ስላገኘንም አመሥጋኞች ነን ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ይህ ዕውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ላይ ያላትን ቁርጠኛ ርምጃ፣ አመራር ብሎም ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ የዳበረ ዐቅም ያሳያል ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 መድረክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ ርምጃን የሚያበረታታ ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማዘጋጀቷ በዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ መድረኮች ኢትዮጵያ ያላትን የአየር ንብረት የመሪነት ሚና የበለጠ ያሳድጋል። የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ የሚያስፈልጋትን ፋይናንስ ለማግኘት እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚን ይፈጥርላታል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የጉባኤው ተሳታፊዎች የቱሪዝም መስህቧቿንና መዳረሻዎቿን ሲጎበኙ ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢ ያድጋል ይህም ኢኮኖሚውን በመደገፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ተጽእኖ ፈጣሪን ጉባኤው በማስተናገድ በኩል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው ሲሆን ዘላቂ የሆነ የከባቢ አየር ትብብርን ለመፍጠር ያስችላል። ለኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማስተናገድ ከክብር ባሻገር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሰው ለሚኖርባት ምድር ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የምታሳይበት ይሆናል። ኢትዮጵያ ጠንካራ የከባቢ አየር ጥበቃ ኢኒሼቲቮች፣ የማይበገር ዲፕሎማሲ እና የነገ አረንጓዴ እድገት ህልሟ ከጉባኤው ጋር ተዳምረው የተፈጥሮ ጠበቃነቷን እና የዓለም ትብብር ተምሳሌትና መሪነቷን የበለጠ ያሳድጉታል። ኢትዮጵያ እና ህዝቧቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአየር ንብረት የረጅም ጊዜ ፈተናዎች እንዲፈቱ ከአፍሪካ ብሎም ከመላው ዓለም ጋር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እና ቁርጠኛ ናት።
" መሬት እና ፍትህ" - የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የእድገት ጉዞ
Nov 11, 2025 716
መሬት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። መሬት ከአፍሪካውያን የአኗኗር ዘይቤ፣ ማንነት፣ ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብር ጋር የተቆራኘ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከቅኝ ግዛት ዘመን በፊት የአፍሪካ በርካታ ማህበረሰቦች መሬት በልማዳዊ እና ባህላዊ ስርዓት ያስተዳድሩ ነበር። የቤተሰብ ጎሳዎች ወይም ማህበረሰቦች መሬት የመጠቀም፣ የማስተዳደር እና ባህላዊ መንገዶች በሰጣቸው መብት ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። በእንደዚህ አይነት ስርዓት ውስጥ መሬት ከሀብት ባለፈ ከማህበራዊ ግንኙነቶች፣ መንፈሳዊ መስተጋብሮች እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት ጋር ትስስር አለው። በቅኝ ግዛት ዘመን የአውሮፓ ኃይሎች በስምምነቶች፣ በአዋጆች እና ኃይል በመጠቀም መሬት የቁጥጥር፣ የብዝበዛ እና ሀብትን የመንጠቂያ መሳሪያ አድርገውታል። መሬት ፖሊሲ ኃይልን ማጠናከሪያ እና የኢኮኖሚ ብዝበዛ መንገድ ሆኗል። አፍሪካውያን በልማዳዊ እና ባህላዊ መንገዶች የነበራቸውን የመሬት መብቶች በመንጠቅ ከአፍሪካ ውጪ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የሰፈራ ፕሮግራም ማካሄጃ እንዲሆኑ በር ከፍቷል። በዚህም ከፍተኛ የሆነ የአፍሪካ ሀብት ሲበዘበዝ ቆይቷል። ሀገር በቀል ማህበረሰቦች ከመሬታቸው የመፈናቀል እና የመገለል ሰለባ ሆነዋል። በቅኝ ገዢዎች የወጡ የመሬት ፖሊሲዎች፣ የመሬት ምዝገባ እና የመሬት አስተዳደር ስርዓት የአፍሪካ መሬት ተጠቃሚዎችን መብት የነፈገ ነበር። የቅኝ ግዛት የቀረጸው የመሬት አስተዳደር ስርዓት አፍሪካውያንን ህጋዊ የመሬት ባለቤትነትን ያሳጣ ነው። የአፍሪካ ሀገራት ከነጻነታቸው በኋላ እኩልነት ያልተረጋገጠባቸውን የመሬት መብቶች እና ስርዓቶች ወርሰዋል። ሀገራት የመሬት ፖሊሲዎቹን አሁን ያሉ የልማት ግቦችን፣ የፍትህ ፍላጎቶች እና ወቅታዊ የአስተዳደር ማዕቀፎች ባማከለ ሁኔታ የመቀየር ስራ በማከናወን ላይ ናቸው። በቅኝ ግዛት ዘመን የመሬት መብታቸውን ላጡ ዜጎች በተለይም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመለሰላቸው ይገኛል። ይሁንና የቅኝ ግዛት የመሬት ቅድሚያ መጥፎ፣ በሀገራት ብሄራዊ ህግ ውስጥ ያሉ የተደባለቁ የህግ ማዕቀፎች (ለምሳሌ ልማዳዊ ህጎች ከመደበኛ ህጎች ጋር መደባለቅ) እና የተቋማት የአስተዳደር ስርዓት አለመናከር በአፍሪካ ፍትሃዊ እና እኩልነት የመሬት ስርዓት የማስፈን ጉዞ ላይ ጋሬጣ ሆኗል። ዛሬ ላይ አፍሪካ አጀንዳ 2063 እና ዘላቂ ልማት ግቦች እየተገበረች ትገኛለች። የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች አንኳር ምሰሶ ተደርገው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሬት ነው። እኩል የመሬት መብት የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ለከባቢ አየር ጥበቃ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ የአጀንዳ 2063 ሰነድ ያስረዳል። የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በመተባበር በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ላይ ማዕቀፎች እና የህግ አሰራሮችን በመቅረጽ እያስተዋወቁ ይገኛሉ። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የመሬት ህጎችን የተሰናነሰኑ እንዲሆኑና የተቋማት አቅምን እንዲያጠናክሩ ጥሪ በማቅረብ ላይ ነው። “የመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ለዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ ከህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኮንፍረንሱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በጋራ በመተባበር ነው። ከአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ እና የአካባቢ ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ እና ለነባራዊ እውነታዎች ምላሽ የሚሰጡ የመሬት ፖሊሲ ምርጥ ተሞክሮዎች በኮንፍረንሱ ላይ እየቀረቡ ይገኛል። ህዳር 1 በነበረው የጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸኃፊ ክላቨር ጋቴቴ በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ስብሰባ በወሳኝ ወቅት የተዘጋጀ ነው ብለዋል። አፍሪካውያን ያላቸውን ሰፊ የመሬት ሀብት በቅኝ ግዛት አሰራሮች ሳቢያ በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው በአፍሪካ መሬት ዛሬም የግጭትና የኢ-ፍትሐዊነት መገለጫ ሆኗል ብለዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር በሴቶች፣ በወጣቶችና በዝቅተኛ አርሶ አደሮች ዘንድ ኢ-ፍትሐዊነትን በማንገስ ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት መፍጠሩን ገልጸዋል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ስብሰባ ከአፍሪካ ሕብረት 2025 "የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን" መሪ ሀሳብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አንስተው፤ ዓላማው አፍሪካውያን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል። የአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የካሳ ጥያቄ ያለፈውን ማስመለስ ሳይሆን አሁን ባለው የዓለም የፋይናንስ ስርዓት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪካ 65 በመቶ ያልታረሰ መሬት፣ ከዓለም ኢንዱስትሪ ሁለት በመቶ ብቻ ድርሻ ያላት፣ ለአየር ንብረት ለውጭ ተፅዕኖ ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች የሆነ አህጉር መሆኗን አንስተዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን በማዘመን ፍትሐዊነትን ማስፈን ጊዜው አሁን ነው ያሉት ዋና ጸኃፊው፣ ሴቶችን ወጣቶችና ዝቅተኛ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዜጎችና ዳያስፖራ ዳይሬክተር አምር አልጆዋሊ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ የአህጉሪቱን መፃኢ ጊዜ ለመቀየር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካና ዘርዓ አፍሪካውያን ላይ የደረሰው በደል ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት ገልጸው፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ለሕብረቱ መሪ ሀሳብ ትግበራ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የመሬት አስተዳደር የፍትሐዊነት ምልክት መሆኑን በማንሳት፤ የመሬት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መስፈን አለበት ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 በማሳካት አካታች ብልፅግናና ሰላምን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል። ሕብረቱ በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ግልፅ አሰራር እንዲሰፍን ለአባል ሀገራት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል። ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ውጤታማ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መገንባት፣ ተቋማዊ አቅምን መፍጠር እና የቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የቅኝ ግዛት አሻራዎች እና ወቅታዊ የኢ-ፍትሃዊነት ጉዳዮች በመሬት ባለቤትነት እና አስተዳደር ያሳደሯቸውን ተጽእኖዎች ለመፍታት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ይገልጻሉ። በመሬት ፖሊሲ ቀረጻ፣ ትግበራ እና ቁጥጥር አቅምን መገንባት፣ የእውቀት ሽግግርን ማሳደግ እና የፖሊሲ ቁርጠኝነትን ወደ ሚጨበጥ የተግባር ምላሽ የመቀየር ጉዳይም አጽንዖት የሚሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ህብረቱ ገልጿል። በአህጉራዊ ኮንፍረንሱ ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ የህብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ትውልደ አፍሪካውያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሁነት ነው። የመሬት ፖሊሲ ጉባኤው አፍሪካውያን ፍትሃዊ እና ዘላቂ የመሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩበት የሚገኝ መድረክ ነው። ጉባኤው አፍሪካውያን ከባለፈው ታሪክ በመማር ፖሊሲ፣ ጥናት እና የማህበረሰብ ድምጾችን በማቀናጀት ረገድ ያለው ፋይዳ ወሳኝ ነው። ጉባኤው የመሬት ፍትህን የማስፈን፣ አይበገሬነትን የመገንባት እና ለሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ብልጽግና የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ በመደገፍ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
Nov 7, 2025 762
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንገት በላይ ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ኦሊያድ ታረቀኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ስለ ጆሮ ህመም መንስዔ እና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል። የጆሮ ህመም ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ኦሊያድ ገለጻ፤ በጆሮ አካባቢ ያሉ የአካል ክፍሎችን የሚያጠቁ ህመሞች የጆሮ ህመም ሊባሉ ይችላሉ። በሳይንሱ የውጨኛው፣ የመካከለኛው እና የውስጠኛው የጆሮ ክፍል ህመም ተብለው እንደሚለዩ ጠቅሰው፤ እነዚህን ክፍሎች የሚያጠቁ የተለያዩ የህመም ዓይነቶች እንዳሉም አመላክተዋል። የጆሮ ህመም ዓይነቶች በተለያዩ መንስዔዎች የተለያዩ ህመሞች እንደሚከሰቱ ጠቁመው፤ ከእነዚህ መካከል በስፋት የሚከሰተው በኤንፌክሽን የሚከሰት የጆሮ ህመም መሆኑን ተናግረዋል። ከአደጋዎች፣ ህመሞችና ጉዳቶች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጆሮ ክፍሎች ህመሞች እንዳሉም በመጠቆም። እንዲሁም ከዕባጮች (ዕጢዎች) ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጆሮ ህመሞች እንዳሉ አመላክተዋል። በውጨኛው የጆሮ ክፍል የሚከሰቱ ከአጥንትና ከቆዳ የሚነሱ ዕባጭና ዕጢዎች፣ ከመካከለኛው የጆሮ ክፍል የሚነሱ በአብዛኛው ከደም ሥር ጋር የተያያዙ ዕጢዎች እንዲሁም ከውስጠኛው የጆሮ ክፍል ከነርቭ የሚነሱ የተለያዩ ዓይነት ዕጢዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም አብራርተዋል። ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች የጆሮ ህመም በሁሉም ጾታና የዕድሜ ክልል ሊከሰት እንደሚችል ገልጸው፤ በአብዛኛው አጋላጭ ምክንያቶች ተብለው ከሚነሱት መንስዔዎች መካከል ከታች የተጠቀሱት ዋነኞቹ መሆናቸውን ያብራራሉ። o ባብዛኛው ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች (ልጆች ባላቸው ያልዳበረ በሽታዎችን የመከላከል ዐቅም እንዲሁም አንዳንድ የሰውነት ክፍሎቻቸው በደንብ ባለመዳበራቸው ሊከሰት የሚችል ነው።) o ዕድሜ ሲጨምር የጆሮ መዳከም ችግር ሊኖር ስለሚችል የመስማት ዐቅም እየቀነሰ ሊሄድ ይችላል። o ለተለያየ ከባድ ድምጽ መጋለጥ ለጆሮ ህመም ወይም የተለያየ ደረጃ ላላቸው የመስማት ችግሮች ሊዳርግ ይችላል። o ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት ጭሶች መጋለጥ ለጆሮ ህመም ሊያጋልጥ ይችላል ተብሎ እንደሚታሰብ አስረድተዋል። የጆሮ ህመም ምልክቶች ምልክቶቹ እንደ ህመሙና ህመሙ እንደተከሰተበት ቦታ የተለያዩ መሆናቸውን ዶክተር ኦሊያድ ይገልጻሉ። ለምሳሌ በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት የጆሮ ህመም ከሆነ እንደተከሰተበት የጆሮ ክፍል ምልክቱ ይለያያል ይላሉ። ለአብነትም የውጨኛው የጆሮ ክፍል ላይ የሚከሰት የጆሮ ኢንፌክሽን ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል መጠዝጠዝ፣ ውጋትና ማሳከክ ዋናኞቹ ናቸው ብለዋል። ራሱ ይህ ህመም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ላይ ሲከሰት ደግሞ የመስማት ደረጃ መቀነስ፣ ትኩሳት፣ አልፎ አልፎ ከባድ የጆሮ ውጋት መኖር፣ የህመሙ ደረጃ እየጨመረ ሲሄድም የተለያዩ ፈሳሾችን ሊያሳይ ይችላል (ለምሳሌ እንደ ውኃ የቀጠነ ፈሳሽ፣ ወፍራም መግል የመሰለ ፈሳሽ፣ አንዳንድ ጊዜ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ሊሆን ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።) በተለያዩ ዕባጮችና ዕጢዎች የሚከሰት የጆሮ ህመም ሲሆን ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል፤ የጆሮ መደፈን ስሜት (ጆሮ ድፍን ብሎ ለመስማት መቸገር)፣ የተለያየ ዓይነት የጆሮ ውስጥ ድምጽና ጩኸቶች መኖር (አንዳንድ ጊዜ ከልብ ምት ጋር አብሮ ሊሰማ የሚችል የጆሮ ውስጥ ጩኸት ሊሆን ይችላል) ብለዋል። በውስጠኛው የጆሮ ክፍል ላይ የሚከሰት የዕጢ ዓይነት ደግሞ የመስማት ደረጃ መቀነስ፣ ማዞር እና ቫላንስ እስከ ማጣት (ሚዛንን ጠብቆ ለመንቀሳቀስ እስከመቸገር) የሚያደርሱ ምልክቶችን ሊያሳይ እንደሚችል ጠቁመዋል። ሰዎች ለጆሮ ህመም እንዳይጋለጡ ምን ያድርጉ? ሰዎች የተለያዩ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መክረው፤ ከእነዚህ ጥንቃቄዎች መካከልም፡- o በልማድ የሚደረጉ ጭራሽ ለጉዳት አጋላጭ የሆኑ ጆሮን የማጽዳት ተግባራት (‘የጆሮን ንጽህና እየጠበቅሁ ነው’ ብሎ በማሰብ ጆሮን ለማጽዳት የሚደረጉ ልማዶችን) ማስወገድ፤ o ጆሮ ለከባድ ድምጽ እንዳይጋለጥ ማድረግ። ለምሳሌ ለረጅም ሠዓት ‘ኤርፎን’ መጠቀም ለጆሮ ህመም እንደሚያጋልጥ በመገንዘብ የሠዓቱን እና የድምጹን መጠን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። ‘ኤርፎን’ በአንድ ጊዜ ለ60 ደቂቃ የድምጽ መጠኑ ከ60 በመቶ ባልበለጠ ጊዜ መጠቀም ይመከራል ያሉት ዶክተር ኦሊያድ፤ ከዚህ ደቂቃ በላይ በአንድ ጊዜ መጠቀም ሲያስፈልግ በየመሀሉ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ጆሮን ማሳረፍ እንደሚገባ ይመክራሉ። በሌላ በኩል ማሳከክን ጨምሮ የጆሮ ህመም ስሜት ሲኖር በወቅቱ ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ በማድረግ ህመሙ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ መታከም የጥንቃቄው አካል መሆኑን አስረድተዋል። የጆሮ ህመም ሕክምና ሕክምናው እንደ ህመሙ ዓይነት እንደሚለያይ አስገንዝበው፤ በአጠቃላይ በሚዋጡ፣ በመርፌ በሚሰጡ፣ በጆሮ ውስጥ በሚጨመሩ እንዲሁም በሚቀቡ አማራጮች ሕክምናው እንደሚሰጥ አብራርተዋል። ከላይ ከተጠቀሱት የሕክምና አማራጮች አልፎ የመስማት ደረጃ መቀነስና መቸገር ከተስተዋለ የቀዶ ሕክምና ማድረግ ብሎም የማዳመጫ ማገዣ መሣሪያ መጠቀም የሕክምናው አካል መሆናቸውን አስረድተዋል። የጆሮ ህመም በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ከ5 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ልጆች ላይ 8 በመቶ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ60 በላይ በሆኑ ሰዎች ደግሞ እስከ 73 በመቶ ድረስ የመስማት ችግር እንደሚያጋጥም ጥናት ማመላከቱን ጠቅሰዋል። ጆሮ ላይ የሚከሰቱ ህመሞች የመስማት ችግርን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረዋል።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 2731
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2710
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3606
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 3690
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 1978
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1297
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7116
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5603
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ
Dec 3, 2025 388
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ (በቀደሰ ተክሌ) -ከሚዛን ቅርንጫፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የቤንች ምድር የሰጡትን የሚያበቅል ክረምት ከበጋ የማይጠወልግ ልምላሜን የታደለ ክልል ነው። በቤንች ሸኮ ዞን ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ደን የሚመስልና በመኖሪያ መንደሮች የሚታየው አብዛኛው አረንጓዴ ስፍራ ለምግብነት የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎች፣ ቅጠሎችና ስሮችን የያዘ ነው። የቤንቾች ቤት ዙሪያው በአረንጓዴ ተፈጥሮ ያጌጠ ነው። የቤታቸው ሞገስ፤ የምግብ ዋስትናቸውም ጭምር ነው። ከዚህ ከፍ ሲል ደግሞ ቤንቾች ነፋሻማ አየር እየማጉ የመኖር ልምድን ያጎናጸፋቸው ይኸው አፈር ቆፍረው ዘር ተክለው ያበቀሉትና የተንከባከቡት አረንጓዴ ሀብት ነው። ከአንድ አርሶ አደር ማሳ እንሰት፣ ሙዝ፣ ጎደሬ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ማየት የተለመደ ነው። እግር ጥሎት ወደ ቀዬያቸው ያመራ እንግዳ ከፍራፍሬዎቹ የደረሰ ካለ ተቆርጦ ይሰጠዋል። በተጨማሪም ከብቶች፣ በጎችና ዶሮዎች የገቢ ምንጮቻቸው ናቸው። ወደ ቤታቸው ዘልቆ የገባ ሰው "ኪዥ" የተሰኘና የቤንች እናቶች ከወተት የሚያዘጋጁትን ''ጎደሬ'' ተብሎ ከሚጠራ የስራ ስር ምግብ ጋር ያጣጥማል። ቤንቾች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን ያለማሉ። ማር፣ ቡና፣ ኮረሪማ እና ሌሎች የተፈጥሮ ቅመማ ቅመሞችም ቤንቾች ከገበያ ገዝተው የሚያመጡት ሳይሆን ከማሳቸው የሚያፈሩት ነው። የተቀናጀ እርሻን ባህል ያደረጉት ብርቱ የቤንች አርሶ አደሮች ወደ ገበያ አውጥተው የሚሸጡት እንጂ የሚገዙት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የፋብሪካ ውጤቶችን ለመግዛትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግም ከጓዳቸው ሞልቶ የተረፈውን ወደ ገበያ አውጥተው በመሸጥ ገበያን ያረጋጋሉ። በጠንካራ የእርሻ ባህላቸውም ምክንያት ልጆቻቸው የበሰለ ምግብን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎችንም ከጓሮና ከጫካ ቆርጠው ስለሚመገቡ ረሀብን አያውቁም። የቤንቾች ቤት ዙሪያ ውብና ጽዱ ነው። ለዚህ ደግሞ ሴቶቹ የቤታቸውን ግድግዳ በተፈጥሮ ቀለም ከማስዋብ ጀምሮ ይጠበቡበታል። በቤንቾች ዘንድ የአንድ አርሶ አደር ጉብዝና የሚለካው በቤቱ ነው። ይህም የቤቱ ዙሪያ ያለው ውበትና የቤቱ ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን ገላጣ መሆን አለመሆኑም ጭምር ከግምት ውስጥ ይገባል። አባዎራው በማሳው ላይ የሰብል ስራውን ያከናውናል። ልጆችና እማውራዋ ደግሞ ይኮተኩታሉ ያርማሉ። ከዚህም በተጨማሪ የቤንች እናት ጎደሬና ሌሎች የጓሮ አትክልቶችን የማልማት ኃላፊነት አለባት። የቤታቸው ዙሪያና ቀዬው በሙሉ በአረንጓዴ ልምላሜ አጊጦ የሚታይበት ምስጢሩ ይሄው ነው። ከርቀት ደን መስሎ የሚታየው አረንጓዴው ቀዬአቸው የገቢ ምንጭም በመሆኑ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ነውም ማለት ይቻላል። የሌማት ትሩፋት እሳቤ ቀድሞ የገባቸው ቤንቾች ማር አይገዙም፤ ለእንቁላል ሸመታም ገበያ አይወጡም። ወተት ቢያምራቸው በትኩሱ፤ ከዛም አለፍ ሲል በባህላዊ መንገድ እርሾ ጨምረው የሚያዘጋጁት "ኪዥ" የተሰኘ የወተት ውጤትን እንደ አይብም እንደ እርጎም አደርገው ይጠቀሙታል። የትኛውንም መልክዓ ምድር በሚስማማው የሰብል ዓይነት መሸፈን ያውቁበታል። መሬቱ ረግረጋማ ከሆነ ለጎደሬ፤ ዳገታማ ሆኖ ለማረስ የሚያስቸግር ከሆነ ደግሞ ለሙዝ ልማት ያውሉታል። የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ሥራ የሚሠራው በጓሮ ነው። ይህም ሁሉን ከአንድ ጓሮ ለማግኘት በመጣር የሚመጣ ነው። ይህም ካልሆነ ደግሞ አስተማማኝና ቋሚ ምርት ማሳ ላይ አልያም ጎተራው ላይ ማኖር ያስፈልጋል። እንደ ቤንቾች በቤተሰብ ደረጃ ምግብን በራስ አቅም ለመቻል የሚደረገው ጥረት እንደሀገር ሲጠናከር ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይፋጠናን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥር አብዛኛው አርሶ አደር ነው። ይሁን እንጂ ጾሙን የሚያድር ሰፊ መሬት እንዳለ መረጃዎች ያመለከታሉ። አንድም መሬት ጾም እንዳያድር በየአካባቢው ስራዎች ቢጀመረም ውጤቱ ቀሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው። ዛሬም በምርት እጥረት የኑሮ ውድነትና መሰል ችግሮች ይስተዋላሉ። በእነዚህ መሬቶች ላይ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ ከተማ ቁጭ ማለትን የሚሻ ትውልድ ማየት የተለመደ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች እጃቸው ብርቱ በመሆኑ እነዚህ ችግሮች በስራ አሽንፈዋል። ይህም በምግብ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ በኢኮኖሚም እንዲረጋጉ አድርጓቸዋል። ለሀብት ምንጭ የሆነን ማሳ ለቆ ከተማ በመዋል የሚገኝ ነገር አይኖርም። በከተማም ሆነ በገጠር ለመለወጥ እንደ ቤንቾች ብርቱ እጆች ያስፈልጋሉ። ካልተሰራ ገቢ ሳይሆን ወጪ እያደገ ወዳልተገባ መንገድ ለመሄድ ምክንያት ይሆናል። ለችግርም ሆነ ሰርቶ የመለወጥ ዕድሉ የሚወሰነው በምርጫችንና ለሥራችን በምንሰጠው ትኩረት ነው። እንደ ቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች ሰርቶ ለመለወጥና ራስን ለመቻል በየአካባቢው ያለን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየር ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ። ሰላም!
ብልህ ከችግር ይማራል!!
Dec 2, 2025 267
ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል!! በማሙሽ ጋረደው ገራድ ተስፋዬ ተፈራ ትውልድና እድገታቸው በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ቃልሻ ቀበሌ ሲሆን በ1999 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው እንደነበር ያስታውሳሉ። ገንዘብ ለማግኘትና የመለውጥ ህልማቸውን ለማሳካት በሚል ሩቅ አስበው የጀመሩት ህገ ወጥ ጉዞ መዳረሻውን እስር ቤት አደረገው። ይህም ሁኔታ ''ሩቅ አሳቢ-ቅርብ አዳሪ'' አደረጋቸው። በባዕድ አገር በነበራቸው የ2 ዓመት የእስር ቤት ቆይታም የምግብ እጦትን ጨምሮ አካላዊ ጥቃትና ጉልበት ብዝበዛ እንዲሁም የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶችን እንዳስተናገዱ ይናገራሉ። ይህም አልበቃ ብሎ ከአካባቢው በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ወጣቶችን ጉልበት በመጠቀም ሰፋፊ እርሻዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ የጉልበት ብዝበዛ ይፈፀምባቸው እንደነበርም ያስታውሳሉ። ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል! የሚሉት ገራድ ተስፋዬ ሩቅ ሳይጓዙ፣ ገንዘብ ሳያወጡ ሰርተው መለወጥ የሚችሉበትን አካባቢያቸውን ፀጋ ሳያማትሩ ስደት መሄዳቸው ቁጭት ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ይህም በሀገራቸው እንኳንስ የለማን መሬት ይቅርና የተቦረቦረ መሬትን አልምቶ ጉልበትንና ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ለስኬት መብቃት እንደሚቻል ከእስር ቤት ቆይታቸው ተምረው ከእስር እንደተፈቱም ወዲያውኑ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረዋል። በ2001 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱም በማህበር ተደራጅተው ከመንግሥት ባገኙት 70 ሺህ ብር ብድር በእንስሳት እርባታ ላይ ለመሰማራት 4 የወተት ከብቶችን ገዝተው የእርባታ ስራ መጀመራቸውን ይገልጻሉ፡፡ በዚህም የዞኑ አስተዳደር የሰጣቸውን መሬት አልምተው የእንስሳት እርባታውን አስፋፍተው መስራት ጀመሩ፡፡ አሁን ላይ የወተት ላሞቹን ቁጥር 37 በማድረስ የወተት ምርታማነታቸው አድጎ ከቤት ፍጆታ አልፎ ለሆሳዕና ከተማና አካባቢው በቀን ከ670 ሊትር በላይ ወተት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ለ40 ወጣቶችም ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ከመፍጠራቸውም ባሻገር የተለያዩ የጭነትና የስራ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራት መቻላቸውን ይናገራሉ። የጀመሩትን ስራ በጥምር ግብርና የማስፋትና የሚያገኙትን ወተት በማቀነባበር ምርቱን በተለያየ መልኩ ለገበያ የማቅረብ ራዕይን ሰንቀው በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በህገወጥ ስደት ካጋጠማቸው ችግር ተነስተው በተግባር ያዩትን ለሌሎች በማስተማር የስደትን አስከፊነት ለአካባቢያቸው ወጣቶች እያስገነዘቡ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶች የስደትን አማራጭ ከመመልከታቸው በፊት የአካባቢያቸውን ፀጋ እንዲቃኙና ራዕይ ሰንቀው ራሳቸውን ለማሻሻል እንዲሰሩም መክረዋል። መለወጥ በውጪ ሀገር ብቻ ያለ የሚመስላቸው የቤተሰብ ኃላፊዎችም ልጆቻቸው በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ በማመን ሊያግዟቸው እንደሚገባም አቶ ገራድ አስገንዝበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ፤ በክልሉ በርካታ ወጣቶች ያልተጨበጠ ተስፋ ሰንቀው ለህገወጥ ስደትና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ የሚያስችል አቅም በግብርናው ዘርፍ መኖሩን ጠቅሰው በዘርፉ የተሰማሩ ከስደት ተመላሾች በአካባቢያቸው ሰርተው ለስኬት እየበቁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከራሳቸው አልፈው ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ላይ የሚገኙና የእነዚህን አካላት ተሞክሮ በመውሰድ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡