ቀጥታ፡

ተመካካሪዎች በተመደቡባቸው አጀንዳዎች ላይ መምከር ጀምረዋል-ኮሚሽነር መሐሙድ ድሪር

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተመካካሪዎች በተመደቡባቸው አጀንዳዎች ላይ ዛሬ መምከር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

የምክክር ጉባኤው ተመካካሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለው በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር መጀመራቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ዛሬ የተጀመረው ሂደት የምክክሩ ቁልፍ አካል መሆኑን ጠቅሰው፥ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ በርካታ ሀሳቦች እንደሚንሸራሸሩበት ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ ልምድ ያላቸው አመካካሪዎችን በመመደብ የምክክሩን ሂደት እየተከታተለ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም