ቀጥታ፡

የስፔኑ ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተጠናቋል።

በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የኮከብ ተጫዋቾች ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዚሁ መሰረት የስፔኑ አምበል ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች በመባል ተመርጧል።

የስፔኑ ተከላካይ ፓዎ ኩባርሲ የወጣት ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አግኝቷል።

ኡናይ ሲሞን (ስፔን ) የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኗል።

ፈረንሳዊው ኪሊያን እምባፔ 10 ግቦች በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሽልማት ወስዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም