ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ወሳኝ የልማት አቅጣጫ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Jun 15, 2026 44
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ የልማት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ ኮፕ-32ን ስታስተናግድ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች ሀገር መሆኗን ለዓለም እናበስራለንም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የዘንድሮው አረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ በቢሾፍቱ ከተማ መካሄዱ ከተማዋ ከራሷ አልፎ ለአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ችግኞችን የምታመርት መሆኗን ዕውቅና የሚሰጥ ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን፣ የሰብልና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ወሳኝ የልማት አቅጣጫ መሆኑን አስረድተዋል። የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት የሚደፈረው በሁለት ጉዳዮች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንዱ ባዕዳን ኃይሎች አልመውና ድንበር ጥሰው ሲገቡ ሲሆን፤ ሌላኛው የእኛ ሃብትና ንብረት በዋዛና ፈዛዛ ሲወጣም የሉዓላዊነት መደፈር ነው ብለዋል። ኢትዮጵያም ባለፉት ዓመታት ያጣችው የአፈር መጠን በገንዘብ ሊተመን የማይችል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል። የእኛ አባቶች ዓድዋ ላይ ወራሪን በማሳፈር ገድል ሠርተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የእኛ ትውልድም በአረንጓዴ ዐሻራ ሌላኛውን ለትውልድ የሚሻገር ታላቅ ገድል እየሰራ ነው ብለዋል። የዘንድሮው "ተስፋን እንትከል" መሪ ሃሳብ የነገን ብሩህ ዛሬ በመፃፍ፣ የተስፋ ስሮች ዘልቀው የብልፅግና ግንድ፣ ቅርንጫፍና ፍሬ ተስፋፍቶ ሃብት እንዲሆኑ የሚያመላክት መሆኑንም ተናግረዋል። የተስፋ ምርጫም የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎችና መላው ኢትዮጵያውያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የትኛውም የአየር ሁኔታ ሳይበግራቸው ተስፋን በመሰነቅ ድምፅ መስጠታቸውን ከመሪ ሃሳቡ ጋር አሰናስለው አስገንዝበዋል። ተስፋ የአረንጓዴ መቀነት ነው፣ ሀገርን ያለብሳል፣ የተራቆተና የገረጣን መሬትም ያለመልማል፣ ተስፋ አረንጓዴ ፀዳልና መንፈስን የሚያድስ አረንጓዴ ወርቅ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የአረንጓዴ ውርስ ትውልድ የሚከበርበት ቀጣዩ ትውልድ ልምድና ባህል የሚያደርገው የብልፅግና መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ በመደመር መርህ የኢትዮጵያን የተረጂነት ታሪክ ወደ ማድረግ ዘመን የሚያሸጋግር መሆኑን አንስተው፤ መርሃ ግብሩ አፈራችንን ከስደት፥ ግድባችንን ከደለል የሚታደግ ስኬታማ የልማት ዓምድ ነው ብለዋል። ከአስር በላይ አዳዲስ የፍራፍሬ ዝርያዎችን በኢትዮጵያ በማላመድ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለዚህ ስኬትም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ በችግኝ ማፍላት፣ በእንክብካቤ፣ በመትከል፣ በችግኝ ሽያጭ፣ በንብ ማነብና በእንስሳት ማድለብ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል። በቀጣይም የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ በሁሉም መስክ የተመዘገበውን ስኬት ማስፋትና ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም አፅንኦት ሰጥተዋል። ከ2011 ዓም ጀምሮ በተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመው፥ ዘንድሮም ከስምንት ቢሊየን በላይ ችግኝ በመትከል በአጠቃላይ 56 ቢሊየን እንደሚደርስ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ-32ን ስታስተናግድ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች ሀገር መሆኗን ለዓለም እናበስራለን ብለዋል። ለዚህም ሁሉም ዜጋ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት በማስቀጠል በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥሉት የክረምት ወራትም "ተስፋን በመትከል" በዓድዋ ድል ቅድመ አያቶች የተቀዳጁትን ድል በአረንጓዴ አሻራ ልማት በመድገም የኩራት ምንጭ የሆነች ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
ረቂቅ አዋጁ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት ለመዘርጋት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል - ቋሚ ኮሚቴው
Jun 15, 2026 46
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት ለመዘርጋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ይፋዊ ውይይት መድረክ አካሂዷል። በገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ተወዳጅ መሀመድ የማሻሻያ አዋጁን መነሻ ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት አዋጁ የታክስ አስተዳደሩን ቀልጣፋ በማድረግ የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ የሚያስችል ነው። የግብር ከፋዮችን መብትና ግዴታ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማስከበር ፍትሐዊነትንና ታክስ የመክፈል ግዴታን በተጠናከረ መልኩ ማስፈፀም እንደሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም ታክስ ከፋዩ በታክስ ሥርዓቱ አመኔታ ኖሮት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ እንደሚረዳ ገልፀዋል። የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ የታክስ አስተዳደር አዋጁ ማሻሻያ የተቀላጠፈ ሥርዓት በመገንባት ከግብር ከፋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን ምላሽ መስጠት የሚያስችል እንደሆነ አስታውቀዋል። ታክስን በአግባቡ በመሰብሰብ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በውስጥ አቅም መሸፈን የሚያስችል ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል። ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነ በዲጂታል የተደገፈ አሠራር በመዘርጋት ተደራሽነትና ቅልጥፍናን በማረጋገጥ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ከብልሹ አሠራር ነፃ እንዲሆን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጆ በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ በታክስ ሥርዓቱ ላይ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን ለማረም መዘጋጀቱን አንስተዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰበሰበው የታክስ ገቢ እያደገ ነው ያሉት ሰብሳቢው ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የፊሲካል ፖሊሲና የታክስ ሥርዓት ማሻሻያዎችን ውጤታማነት የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል። በግብር ከፋዩ ዘንድ እየተሠራ ያለው የግንዛቤ ፈጠራ እና ማበረታቻ የግብር ከፋዮችን ተነሳሽነት በማሳደግ ግዴታቸውን እንዲወጡ እያስቻለ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በደን መሸፈን አስችሏል
Jun 15, 2026 40
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በደን እንዲሸፈን ማስቻሉን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዛሬ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ዓመት 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ በማስቀመጥ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊየን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል። የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መንግሥትና ሕዝብ ተቀናጅተው ያሳኩት ታላቅ ታሪክ ነው። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ሰባት ዓመታት 48 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን አንስተው በየዓመቱ በአማካይ 25 ሚሊየን ዜጎች በመርሃ ግብሩ መሳተፋቸውንም ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ከተተከሉት ችግኞች መካከል 60 በመቶ ያህሉ ለጥምር እርሻ የሚውሉ መሆናቸውን አንስተው 35 በመቶ ያህሉ ደግሞ የደን ዛፎች ናቸው ብለዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ትግበራ 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በደን እንዲሸፈን ማስቻሉንም አስረድተዋል። የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከማሳደጉ ባለፈ የአረንጓዴነት ምጣኔን በመጨመር ወደ ውሃ አካላት የሚወርደውን የደለል መጠን እንዲቀንስ አስችሏል ነው ያሉት። የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ በየዓመቱ ወደ ወንዞች ታጥቦ ይገባ የነበረውን የአፈር ሀብት ከ2 ቢሊየን ቶን ወደ 208 ሚሊየን ቶን ዝቅ እንዲል ማስቻሉን ተናግረዋል። መርሃ ግብሩ የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርታማነትን ማሳደግ ማስቻሉን አንስተው የመድረቅ አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ የውሃ አካላት እንዲያገግሙ አድርጓልም ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባትም ትልቅ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዓለም ዋንጫው አፍሪካዊቷ ኬፕቨርዴ ከስፔን ጋር አቻ ተለያየች
Jun 15, 2026 150
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ስምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ስፔን እና ኬፕቨርዴ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስፔን በኳስ ቁጥጥር እና በግብ ሙከራ ከፍተኛ ብልጫ ብትወስድም ጎል ከመረብ ላይ ማሳረፍ ተስኗታል። በአንጻሩ ኬፕቨርዴ በጨዋታው ላይ የተከተለቸው የመከላከል ስልት አንድ ነጥብ አስገኝቶላታል። የኬፕቨርዴው ግብ ጠባቂ ቮዚኒሃ ያዳናቸው ኳሶች ወሳኝ ነበሩ። 166 ሺህ ህዝብ ያላት የአፍሪካ የደሴት ሀገር ኬፕቨርዴ ከእግር ኳስ ኃያሏ ስፔን ነጥብ በመውሰድ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግባለች። ብሔራዊ ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ እየተሳተፈ ይገኛል። የአንድ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን ጉዞዋን በአቻ ውጤት ጀምራለች። በዚሁ ምድብ ሳዑዲ አረቢያ ከኡሯጓይ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በሚያሚ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ሥራችን ከተፈጥሮ የመታረቅ በልማት የመላቅ አዲስ ጎዳና ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jun 15, 2026 162
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ሥራችን ከተፈጥሮ የመታረቅ በልማት የመላቅ አዲስ ጎዳና ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ለአንዲት ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሕዝብ ተደምረን በሠራነው የአረንጓዴ ዐሻራችን፣ ልምላሜ የተራቡ ተራሮች አረንጓዴ ለብሰዋል ብለዋል። ምንጮች እና ተፋሰሶች ምድሩን አረስርሰዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በረሃማነት ይጸናባቸው የነበሩ ክበበ ምድሮች ነፋሻማ ሆነዋል ሲሉም ገልጸዋል። የተፈጥሮን ጫና ተቋቁመናል! ይህ ደግ የተፈጥሮ ዕርቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል በመልዕክታቸው። የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥን ከተፈጥሮ ጥበቃ ጋር በማስተሣሠር በተሠራው ሥራ የፍራፍሬ ተክሎች በስፋት ለምተዋል፤ ፍሬ መስጠትም ጀምረዋል ብለዋል። ይህም በምግብ ራስን ለመቻል ለጀመርነው ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ ተደማሪ ዐቅም ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል። አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያ ልጆች ከፖለቲካ አሰላለፍ አልፈው፣ ከሐሳብ ተቃርኖ ተሻግረው፣ ገጸ ብዙ ልዩነቶችን አሸንፈው ለሀገርና ለትውልድ አስበው ያሳኩት የመተባበር ድል፣ የተጨበጠ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ልጆች ስንተባበር ትርፋችን እልፍ፣ ዕቅዳችንም የተሳካ የሠመረ ይሆናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ የእስከ ዛሬ ድካማችን መደምደሚያ፣ የድላችን መዳረሻ፣ በድል ላይ ቆመን ለሌላ የላቀ ድል የምንነሣበት ልዩ ዓመት ነው ብለዋል። ሁላችንም በሩጫ ትግል ሊያልቅ ሲል እንደሚበረቱት ሊጠናቀቅ ሲል እንደሚፈጥኑት ጀግኖች አትሌቶቻችን ካለፉት ዓመታት አስበልጠን እንትከል! እንበርታ! እንፍጠን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ፖለቲካ
በባህር ዳር ከተማ የሰላምና ጸጥታ ሥራዎችን በማስቀጠል የህዝብን ኑሮ ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ
Jun 15, 2026 299
ባህር ዳር፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ በማህበረሰቡ ተሳትፎ የሚከናወኑ የሰላምና ጸጥታ ሥራዎችን በማስቀጠል የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። የባህር ዳር ከተማ አመራሮች የተሳተፉበት በልማትና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት ባህርዳርን በመሰረተ ልማት በማዘመን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው። በማህበረሰቡ ተሳትፎ የከተማዋን ሰላምና ልማት በማጠናከር የህዝብን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል። በተለይም የከተማዋን ማህበረሰብ በማሳተፍ የተከናወኑ የሰላምና የህግ ማስከበር ሥራዎች ለሁለንተናዊ የልማት ተግባራት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠሩ ገልጸዋል። የሰላሙ መጠናከር የኮሪደር ልማት፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የስማርት ሲቲ ትግበራ እና ሌሎች ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በፍጥነትና በጥራት ለማከናወን አስችሏል ብለዋል። ይህም ከተማዋን ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝምና ለኑሮ ምቹ በማድረግ የነዋሪውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እንደሚያስችል አስረድተዋል። ማህበረሰቡም በጠቅላላ ምርጫው ድምጹን ከመስጠት ባለፈ ለምርጫው ሰላማዊነትና ስኬት ያደረገው አስተዋጽኦ ለሰላምና ልማት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያሳያል ብለዋል። በቀጣይም ህዝቡ በከተማዋ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎች ላይ የሚያደርገውን ንቁ ተሳትፎ በማሳደግ ለዘላቂ የብልጽግና ጉዞ የሚጠበቅበትን መወጣት አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል። የከተማ አስተዳደሩም በቀጣዮቹ 90 ቀናት የክረምት ሥራዎችን በላቀ ደረጃ በመፈጸምና የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመፍታት በጊዜ የለኝምመንፈስ ሊሰራ እንደሚገባ ምክትል ከንቲባው አሳሰበዋል። በብልጽግና ፓርቲ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ሃላፊ አቶ ጊዜው ታከለ እንዳሉት፣ በየደረጃው ያለው አመራር ዋነኛ ትኩረቱ ህዝብን በሰላምና በልማት ተጠቃሚ ማድረግ ነው። ለዚህም ህዝባዊነትን በመላበስ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ተአማኒነት ያለው አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በመድረኩ ላይ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደርና የክፍለ ከተሞች አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ማረጋገጥ የሚቻለው ችግሮችን በምክክር በመፍታትና መግባባት በመፍጠር ነው - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Jun 15, 2026 328
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ፈተናዎች ለመሻገርና ዘላቂ ጥቅሟን ለማስከበር ዋናው መንገድ ችግሮችን በምክክር መፍታትና ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተው፣ በሰላማዊ መንገድ ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ጋር በአዳማ ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል። ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የቀድሞ ታጣቂዎቹ አጀንዳዎቻቸውን ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡም ይሆናል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በመድረኩ እንደገለጹት፣ ወጣቶች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ያሏቸውን ጥያቄዎች በአጀንዳ መልክ ቀርጸው ወደ ሀገራዊ ምክክሩ ማምጣታቸውን አድንቀዋል። ጥያቄዎችን ይዞ ወደ ምክክር መምጣት፣ ለችግሮች በጋራ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ትልቁን በር እንደሚከፍትም ገልጸዋል። የትኛውም ፍላጎትና ጥያቄ በመሳሪያ ሳይሆን በውይይት፣ በመነጋገርና በመመካከር መግባባት ላይ የሚደረስበት መሆኑን ወጣቶች ሊገነዘቡ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ማረጋገጥ የሚቻለው መሳሪያ ይዞ ጫካ ውስጥ በመግባት የወጣትነት እድሜን መስዋዕት በማድረግ ሳይሆን፣ የሀገሪቱን ችግሮች በፊት ለፊት ውይይትና ምክክር በጋራ በመፍታት መሆኑን አንስተዋል። የኮሚሽኑ ዋና ዓላማም ለማንም ወገን አድሎ ሳይደረግ፣ ሁሉም አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው ሀሳብ ለሀሳብ እንዲመካከሩ በማድረግ ለችግሮች ዘላቂ እልባት መፈለግና በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር መሆኑን አስረድተዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት የሰላም ጉዳዮች አማካሪ ብርጋዴር ጄነራል ኃይሉ ጎንፋ በበኩላቸው፣የትኛውንም አጀንዳ በሰላማዊ መንገድ በመደማመጥ መፍታት መቻል ትልቅ እሴት መሆኑን አብራርተዋል። ማህበረሰቡ በየትኛውም ሁኔታ ሰላም እንዲደፈርስ አይፈልግም ያሉት ብርጋዴር ጄነራሉ፣ ልጆቹ ከነፍጥ ይልቅ የሰለጠነ ፖለቲካን እንዲለማመዱ ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። የሰላም መንገድ ሁሉንም አሸናፊ በማድረግ ወጣቶች የነገዋን ሀገር ለመገንባት አሻራቸውን የሚያሳርፉበት መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህ ዓይነቱ በምክክር ላይ የተመሰረተ አካሄድ ትልቁ የትግል ማዕቀፍ መሆን እንደሚገባ በማንሳት፥ ሀገራዊ ፋይዳውም የላቀ ነው ብለዋል።
በዞኑ ማህበረሰቡን በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥና የልማት ስራዎችን የማስቀጠል ተግባራት ይጠናከራሉ
Jun 15, 2026 275
መተማ፣ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):-በምዕራብ ጎንደር ዞን ማህበረሰቡን በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል ተግባራትን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ የዞኑ አመራሮች ገለጹ። የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ከየወረዳው ከተወጣጡ አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች ጋር በወቅታዊ የፀጥታና የልማት ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደዋል። በወቅቱም የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ እያሱ ይላቅ እንደገለጹት፤ በዞኑ ላለው ለውጥ፣ ዕድገትና አስተማማኝ ሰላም ዋነኛው ባለቤትና አጋዥ ህብረተሰቡ ነው። ዞኑ ሰፊ የኢንቨስትመንት እና የልማት ቀጠና መሆኑን ጠቅሰው የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ለሀገር ኢኮኖሚም ጭምር ወሳኝ ሚና እንዳለው አንስተዋል። "ባለፉት ጊዜያት ከህዝባችን ጋር በመቀናጀት በርካታ ፈተናዎችን ማለፍ ችለናል" ያሉት አስተዳዳሪው፣በቀጣይም ይኸው ህዝባዊ ትስስር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ ሙላው እንዳሉት፤ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን ለማፋጠን ከህዝቡ ጋር መወያየትና አብሮ መስራት ይጠበቃል። አርሶ አደሩ ያለምንም ስጋትና በነፃነት ምርቱን ማምረት እንዲችል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል። ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር ያለውን ሰላማዊ ትስስር ለማጥበቅና የወንጀል ድርጊቶችን በጋራ ለመግታት ከህብረተሰቡ የሚገኘው ጥቆማና ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰራም አንስተዋል። የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ግዛት ሰረፀ በበኩላቸው፣ ወረዳው በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ፣ ሰፊ የእርሻ መሬት ያለበት በመሆኑ ይህን ሀብት ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር ሰላምን ማረጋገጥ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በመሆኑም በየቀበሌው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር የፀጥታ ስጋቶችን በጋራ የመከላከል ስራ በተጠናከረ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰሩም አመራሮቹ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን አርዓያ የሚሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ ሰላማዊና የተሳካ ምርጫ ማካሄዷ የሚደነቅ ነው
Jun 15, 2026 437
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን አርዓያ የሚሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ ሰላማዊና የተሳካ ምርጫ ማካሄዷ የሚደነቅ መሆኑን በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ ያሉ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት የምርጫ ታዛቢዎችን በማሰማራት ገለልተኛና ዲሞክራሲያዊነቱን የመሰከሩለት ጠቅላላ ምርጫ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ በምርጫው የሀገር ውስጥ ታዛቢዎችም የተሳተፉ ሲሆን 55 የሲቪል ማህበራትን ያቀፈው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሳታፊ፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊ መሆኑን መታዘቡን ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የጸጥታ፣ የፍትሕና የዲሞክራሲ ተቋማት ምርጫውን በገለልተኝነትና በተቋማዊ ብቃት እንዲካሄድ ማስቻላቸውን መታዘቡን አረጓግጧል፡፡ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት የተሳካ ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምርጫው በፊት አሳታፊ ምርጫ እንደሚካሄድ በገቡት ቃል መሰረት መንግሥት ለምርጫው ዲሞክራሲያዊነት ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም አድንቀዋል። ምርጫው በርካታ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን የሰጡበት፣ የሴቶችና የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ የታየበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ ያሉ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት የምርጫ ታዛቢዎችን በማሰማራት ምርጫው ሰላማዊና ፍትሐዊ መሆኑን ማረጋገጣቸውም የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት የሚያሳይ መሆኑን በአድናቆት ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ከእጩዎችና መራጮች ምዝገባ ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ለአፍሪካውያን አርዓያ የሚሆን ነፃ፣ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ችላለች ነው ያሉት። የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን መፈታት አለበት ያሉት አምባሳደሩ፤ በኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ታዛቢዎች መሰማራታቸው የዚህ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን የመገንባት ሂደት በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ነው
Jun 15, 2026 381
ባህርዳር፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስፈን የሚያስችል የፀጥታ ኃይል እየተገነባ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገለፁ። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ደህንነት አፈፃፀምን የሚገመግምና በቀጣይ ሁለት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር መድረክ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው። በመድረኩም የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን የመገንባት ሂደት በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል። ባለፋት ጊዜያት የፀጥታ ሃይሉ በተቀናጀ መንገድ በተሰራ ህግ የማስከበር ተግባር በክልሉ ሰላም ማስፈን መቻሉን ገልፀዋል። በዚህም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙና የክልሉን ብሎም የሀገሪቱ ሰላም መሆን የማይዋጥላቸው ፀረ-ሰላም ኃይሎች የክልሉን ብሎም የሀገርን ሰላም አደጋ ላይ ለመጣል የተደረገውን ሙከራ ማክሸፍ እንደተቻለ አንስተዋል። በተለይም እነዚህ የህዝብና የሀገር ጠላት የሆኑ ፅንፈኛ ቡድኖች ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማደናቀፍ በተቀናጀ መንገድ ያደረጉትን ጥረት የፀጥታ ኃይሉ በላቀ ብቃት ማምከን መቻሉን ተናግረዋል። ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አባላት በጥምረት በሰሩት ስራም ምርጫው እንዳይካሄድ የተደረጉ ሙከራዎችን ሙሉ በሙሉ በማክሸፍ ምርጫው በስኬት እንዲከናወን ማድረጋቸውን አብራርተዋል። የፀጥታ ኃይሉ ህዝባዊነትን በተላበሰ መንገድ ባካሄደው ርብርብም ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ሊፈፀም የታሰበን አጥፊ ድርጊት ሊያመክን እንደቻለም አክለዋል። ምርጫው በስኬት እንዲከናወን የፀጥታ ኃይሉ ለተወጣው ኃላፊነት አመስግነው፤ በቀጣይም ሰላምን የማስጠበቁ ተግባር በላቀ ቁርጠኝነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በመድረኩ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የተቋሙ አመራሮች እየተሳተፋ ሲሆን የምርጫ ደህንነት አፈፃፀምና የቀጣይ ሁለት ወራት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
የፌዴራል መንግሥት የትግራይን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማስቀጠል የወሰደውን ቁርጠኝነት የቀድሞ ሕወሓት ቡድን ራሱን ለዕኩይ ዓላማ ለማደራጀት ተጠቅሞበታል
Jun 15, 2026 440
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ክልልን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማስቀጠል የወሰደውን ቁርጠኝነት ህልውናው ያከተመው ህገወጡ የቀድሞ የሕወሓት ቡድን ራሱን ለዕኩይ ዓላማ ለማደራጀት እንደተጠቀመበት አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ገለጹ። የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞው ሕወሓት የቀድሞ ሊቀ መንበር የነበሩት አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የፌዴራል መንግሥት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የትግራይ ክልልን ጊዜያዊ አስተዳደር በማዋቀር ሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ግንባታን ለማፋጠን ከፍተኛ በጀት መድቦ ሲሰራ ቆይቷል። ሆኖም ጦርነት ናፋቂው የቀድሞ ሕወሓት ፅንፈኛ ቡድን የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ቢፈርምም አደገኛና ህገወጥ ወታደራዊ አቅም እየገነባ መቀጠሉን አመልክተዋል። የፌዴራል መንግሥቱ የዘላቂ ሰላምና ልማት ግንባታ ጥረቶች እንዳይሳኩ ጽንፈኛው የቀድሞ ሕወሓት ቡድን ተደጋጋሚ የማደናቀፍ ተግባራትን እየፈጸመ መሆኑን አስረድተዋል። የትግራይ ክልል ወጣቶችን ለአስገዳጅ ወታደራዊ አፈሳና ምልመላ በመዳረግ ስጋት እንዲያንዣብብ ማድረጉን በመጥቀስ፥ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በፅንፈኛ ቡድኑ አማካኝነት የሰላም ስምምነቱ ሲደናቀፍ በዝምታ መመልከቱን አውስተዋል። የቀድሞ ሕወሃት ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ለክልሉ ሕዝብ ዘላቂ ሰላምና ልማት ግንባታ ከመጠቀም ይልቅ ራሱን ለማደራጀትና የጥፋት ዓላማውን ለማሳካት በጊዜ መግዣነት ተጠቅሞበታል ብለዋል። የቡድኑ አመራሮችም ከውጪ ጠላት በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ሕጻናትን ከወላጆቻቸው በመንጠቅ ጭምር አዲስ ኃይል አደራጅተው ወደ ዳግም ግጭት ለመግባት የተሳሳተ አቅጣጫ እየተከተሉ መሆኑን አስረድተዋል። የክልሉ ሕዝብም ልጆቹን ከግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ ለመታደግ ከክልሉ ውጭ ወደሚገኙ አካባቢዎችና በውጭ ሀገራት ጭምር በማሸሽ የቡድኑን ሕገ-ወጥ ድርጊት አጥብቆ እየተቃወመ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ፅንፈኛ ቡድን በመሰላቸት ተስፋ የቆረጡ ነባር ታጣቂዎችም ለቀው በመውጣት ቡድኑን መዋጋት መጀመራቸውን አንስተዋል። የቀድሞ ሕወሓት ፅንፈኛ አካላት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተቋቋመውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በማፍረስ ግጭት የሚያስከትል መዘዝ እየፈጠሩ መሆናቸውን አብራርተዋል። በሀገር ውስጥና በውጭ ዓለማት የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች፣ሌሎች ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የዚህን ፅንፈኛ ቡድን ሕገወጥ እንቅስቃሴ አጥብቀው ሊያወግዙ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የሀሳብ ልዩነቶችንና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ የስልጡንነት መገለጫ ነው
Jun 15, 2026 404
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦የሀሳብ ልዩነቶችንና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ የስልጡንነት መገለጫ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተው በሰላማዊ መንገድ ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ጋር በአዳማ ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የቀድሞ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የወሰኑትን ውሳኔ አድንቀዋል። የሀሳብ ልዩነቶችንና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ የስልጡንነት መገለጫ ነው ያሉ ሲሆን፣ በሀገሪቱ ዘላቂ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሰላም መመካከርና መነጋገር ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሚሽኑ ዋናውን ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚያካሂድ መግለጹ ይታወቃል። ለዚህም በተለያዩ ምዕራፎች ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማካሄድ የሚያስችል አሳታፊና አካታች የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ሥራ ማከናወኑም ይታወቃል። ኮሚሽኑ በክልሎች፣ በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ በወረዳዎች እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ዜጎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ የምክክር መድረክ ማካሄዱም አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ተሳትፎ ጥሪ አቀረበ
Jun 15, 2026 450
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚካሄደው የማጠቃለያ የምክክር ጉባኤ መላው ሕዝብ ከጎኑ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለመግባባት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በሕዝባዊ ውይይት ሰብስቧል፡፡ በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክረ ሀሳብ የሚያሰናዳበትን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤም ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቅቋል። ስለሆነም ኮሚሽኑ መላው ኢትዮጵያውያን ለዚህ ታሪካዊ ሁነት መሳካት ከጎኑ በመሆን የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የባለድርሻ አካላት ወኪሎች ውጤታማ ጉባኤ ማካሄድ የሚያስችላቸውን ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

ማህበራዊ
አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በተሠራው ሥራ የሕክምና ተቋማት አቅምና ዘመናዊነት እያደገ መጥቷል
Jun 15, 2026 198
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤናው ዘርፍ ባከናወናቸው መጠነ-ሰፊ የልማት ሥራዎች የሕክምና ተቋማት አቅምና ዘመናዊነት እያደገ መምጣቱን የከተማዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላፍቶ ሆስፒታልን በቅርቡ በመረቁበት ወቅት፤ የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢትዮጵያን ቀዳሚ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተሰነቀውን ትልቅ ራዕይ ከግብ ለማድረስ እንደ አንድ ትልቅ የአሸጋጋሪ ምዕራፍ ተጠቃሽ መሆኑን መግለጻቸው ይታወቃል። ይህም ዜጎች ለላቀ የህክምና አገልግሎት ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገር በሚጓዙበት ወቅት የሚባክነውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ የሚረዳ ሲሆን፤ የዘርፉን የአገልግሎት ጥራትም ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግረዋል። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን የህክምና ማዕከልነት ሚና ይበልጥ እንደሚያጎላውም መግለጻቸው ይታወሳል። የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ከአዳዲስ ሆስፒታሎች ግንባታ እስከ ዲጂታል የጤና መረጃ ሥርዓት ዝርጋታ የተከናወኑ ተግባራት አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተያዘው ትልቅ ሀገራዊ ራዕይ አካል ናቸው። በከተማዋ የዘመናዊ ሕክምና አቅምን ከሁለት እጥፍ በላይ ያሳደገ ታሪካዊ ተግባር ተከናውኗል ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ዘጠኝ አዳዲስ ዘመናዊ ጤና ጣቢያዎች ወደ አገልግሎት የገቡ ሲሆን፤ በዚህም ከዚህ ቀደም የጤና ተቋም ያልነበራቸውን አምስት ወረዳዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በ40 ነባር የጤና ጣቢያዎች ላይ ሰፊ የማስፋፊያና የማጠናከሪያ ሥራዎች መከናወናቸውንም ነው ያብራሩት። ዘውዲቱ መታሰቢያ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው እና ዳግማዊ ምኒሊክን ጨምሮ ነባር ሆስፒታሎች ታድሰዋል፤ አዳዲስ ማስፋፊያ ሕንጻ ተገንብቶላቸዋል ያሉት ኃላፊው፤ የአገልግሎት አቅማቸውም በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ተደርጓል ብለዋል። በጤና መሠረተ ልማት ረገድ ከተመዘገቡት ስኬቶች መካከል የአበበች ጎበና እናቶችና ሕጻናት ሆስፒታል ግንባታ በግንባር ቀደምትነት እንደሚጠቀስ ተናግረዋል። አዲስ አበባ የእናቶችና ሕጻናት ሞት ምጣኔን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ፣ በዘላቂ ልማት ግቦች ሥር የተቀመጠውን ዓለም አቀፍ መለኪያ ካቀደችው ጊዜ አስቀድማ ማሳካቷንም ነው ያነሱት። በከተማዋ የሕክምና ጥራትንና የቴክኖሎጂ አቅምን ዓለም ከደረሰበት ደረጃ የሚያደርሱና ለውስብስብ የሕክምና ዓይነቶች በራስ አቅም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ልዩ የሕክምና ልህቀት ማዕከላት ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል። ሁሉም ሆስፒታሎች የራሳቸውን ኦክስጅን በማምረት ቀደም ሲል በሲሊንደር አቅርቦት ላይ የነበረባቸውን ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ አስቀርተዋል ብለዋል። የአገልግሎት ፍጥነትን፣ ወጥነትንና የመረጃ አያያዝን ለማዘመን በተከናወነው ሥራ፤ ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ 67 የጤና ተቋማት በዲጂታል የሕክምና መረጃ ሥርዓት ውስጥ መካተታቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በመንግስት ድጋፍና ምቹ ሁኔታዎች በመታገዝ የግል ባለሀብቶችም በጤናው ዘርፍ ዘመናዊ ሆስፒታሎችን በማቋቋም ለአገልግሎት ማብቃት መቻላቸውን ገልጸዋል።
የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ እየተሰጠ ነው-የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
Jun 15, 2026 170
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ በተሳካ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገለፁ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ ባሉ 767 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 85 ሺህ 17 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። የፈተናውን ሂደት የሚከታተሉ 3 ሺህ 400 የፈተና አስፈጻሚዎች በከተማዋ በሚገኙ በ199 የፈተና ጣቢያዎች መመደባቸውንም ገልጸዋል። ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አንስተው በፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ፈተናው መጀመሩን ተናግረዋል። በትምህርት ቤቶች በተደረገው ምልከታ በመፈተኛ ጣቢያዎች ለተማሪዎች በራስ መተማመን የሚፈጥር ዐውድ መኖሩን ተመልክተናል ብለዋል። ተማሪዎች ታዳጊዎች በመሆናቸው በስነልቦና ለማዘጋጀት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። የተማሪዎችን በራስ መተማመን ለማሳደግና ኩረጃን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸውንም አንስተዋል።
ረቂቅ አዋጁ ሀገራዊ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብን ለማሻሻል ወሳኝ መሰረት የሚጥል ነው- ቋሚ ኮሚቴው
Jun 15, 2026 228
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ረቂቅ አዋጁ ሀገራዊ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብን ለማሻሻል ወሳኝ መሰረት የሚጥል መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅ ሰሙ ማሞ ገለጹ፡፡ የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብ ረቂቅ አዋጅ ላይ ይፋዊ የሕዝብ ውይይት መድረክ አካሒዷል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የአዋጁን አስፈላጊነት በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ፤ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብ የምግብን ከእርሻ እስከ ጉርሻ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሰንሰለት የሚያመላክት ነው ብለዋል። ረቂቅ አዋጁ ዜጎች በልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ምግብ እንዲያገኙ በማስቻል ጤናማ እና አምራች ትውልድ ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚያበረክት አመላክተዋል፡፡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እንደ መነሻ በመውሰድ የተዘጋጀው ይህ አዋጅ፥ ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕግ እንዲመራ ከማስቻሉም በላይ የተቋማትን ቅንጅታዊ ሥራ ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ተወካይ ገነት ስዩም፤ የነገ ሀገር ተረካቢ ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ረቂቅ አዋጁ ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ ምግብ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር አሻግረው ዘውዱ(ዶር) በበኩላቸው፤ የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብ በህግ እንዲመራ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አንቀጾች መካተቱን ያደነቁት ደግሞ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበር ፌዴሬሽን የመጡት አዳነች መለስ ናቸው፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅ ሰሙ ማሞ፤ ረቂቅ አዋጁ የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብን በሕግ በመምራት ሀገር እና ትውልድ የሚገነባበት ነው ብለዋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ መዘጋጀት በሀገራችን የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ-ምግብን ለማሻሻል ወሳኝ መሰረት እንደሚጥል ገልጸዋል፡፡
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ለ500 ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሰጠ
Jun 15, 2026 154
አምቦ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ለ500 ያህል ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት መስጠቱን ገለጸ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አበበ መገርሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሆስፒታሉ ባለፉት አራት ቀናት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎትን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን አዘጋጅቷል። በዚህም እንቅስቃሴ ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ህክምናውን ፈልገው የመጡ 500 ሰዎች ህክምናውን በነጻ ማግኘት ችለዋል ብለዋል። በዘመቻው የአምቦ ከተማን ጨምሮ የጀልዱ፣ የድሬ ኢንጪኒ፣ የአደአ በርጋና የቶኬ ኩታዬ ወረዳ በበሽታው ተይዘው የነበሩ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። የተሰጠው የህክምና አገልግሎት በገንዘብ ሲሰላ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑንም አስታውቀዋል። በሆስፒታሉ የዓይን ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ጉዲና ሚሊኬሳ በበኩላቸው፤ በሽታው የሚከሰተው በአብዛኛው ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ገልጸዋል። በህክምና ዘመቻው በተደረገው ርብርብ የብዙዎችን ብርሃን መመለስ ተችሏል ያሉት ኃላፊው፤ ህብረተሰቡ በሽታው እንደተከሰተ ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ በወቅቱ መታከም እንደሚገባው አመልክተዋል። የዓይን ሞራ ግርዶሽ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ካለመጠበቅም ሊከሰት የሚችል በመሆኑ፣ ማህበረሰቡ የራሱንና የአካባቢውን ንጽህና በመጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ ሊከላከለው እንደሚገባም ዶክተር ጉዲና አሳስበዋል። በነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ዘመቻ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ከአደአ በርጋ ወረዳ የመጡት አቶ ዱጉማ ደሜ፤ ለስድስት ዓመታት በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ማየት ተስኗቸው መቆየታቸውን ገልጸው፣ በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ህክምና ማየት እንደቻሉ ተናግረዋል። ከኢንጪኒ ከተማ የመጡት ወይዘሮ ቢሪቱ ኮርሳ በበኩላቸው፤ የህክምና አገልግሎቱን ማግኘት ባለመቻላቸው ለሦስት ዓመታት ማየት ተስኗቸው መቆየታቸውን ተናግረው፣ ከዚህ ችግር ለታደጓቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ለተመሳሳይ ችግር ተዳርገው የነበሩት የኤጄሬ ወረዳ ነዋሪው አቶ ጎዳ ሻንኩራ፤ በተደረገላቸው ህክምና እይታቸው በመመለሱ ራሳቸውን ችለው ለመንቀሳቀስም ሆነ ለመሥራት ዕድል በማግኘታቸው ደስታቸው ድርብ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢኮኖሚ
ረቂቅ አዋጁ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት ለመዘርጋት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል - ቋሚ ኮሚቴው
Jun 15, 2026 46
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት ለመዘርጋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ይፋዊ ውይይት መድረክ አካሂዷል። በገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ተወዳጅ መሀመድ የማሻሻያ አዋጁን መነሻ ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት አዋጁ የታክስ አስተዳደሩን ቀልጣፋ በማድረግ የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ የሚያስችል ነው። የግብር ከፋዮችን መብትና ግዴታ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማስከበር ፍትሐዊነትንና ታክስ የመክፈል ግዴታን በተጠናከረ መልኩ ማስፈፀም እንደሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም ታክስ ከፋዩ በታክስ ሥርዓቱ አመኔታ ኖሮት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ እንደሚረዳ ገልፀዋል። የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ የታክስ አስተዳደር አዋጁ ማሻሻያ የተቀላጠፈ ሥርዓት በመገንባት ከግብር ከፋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን ምላሽ መስጠት የሚያስችል እንደሆነ አስታውቀዋል። ታክስን በአግባቡ በመሰብሰብ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በውስጥ አቅም መሸፈን የሚያስችል ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል። ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነ በዲጂታል የተደገፈ አሠራር በመዘርጋት ተደራሽነትና ቅልጥፍናን በማረጋገጥ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ከብልሹ አሠራር ነፃ እንዲሆን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጆ በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ በታክስ ሥርዓቱ ላይ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን ለማረም መዘጋጀቱን አንስተዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰበሰበው የታክስ ገቢ እያደገ ነው ያሉት ሰብሳቢው ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የፊሲካል ፖሊሲና የታክስ ሥርዓት ማሻሻያዎችን ውጤታማነት የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል። በግብር ከፋዩ ዘንድ እየተሠራ ያለው የግንዛቤ ፈጠራ እና ማበረታቻ የግብር ከፋዮችን ተነሳሽነት በማሳደግ ግዴታቸውን እንዲወጡ እያስቻለ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በደን መሸፈን አስችሏል
Jun 15, 2026 40
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በደን እንዲሸፈን ማስቻሉን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዛሬ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ዓመት 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ በማስቀመጥ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊየን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል። የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መንግሥትና ሕዝብ ተቀናጅተው ያሳኩት ታላቅ ታሪክ ነው። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ሰባት ዓመታት 48 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን አንስተው በየዓመቱ በአማካይ 25 ሚሊየን ዜጎች በመርሃ ግብሩ መሳተፋቸውንም ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ከተተከሉት ችግኞች መካከል 60 በመቶ ያህሉ ለጥምር እርሻ የሚውሉ መሆናቸውን አንስተው 35 በመቶ ያህሉ ደግሞ የደን ዛፎች ናቸው ብለዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ትግበራ 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በደን እንዲሸፈን ማስቻሉንም አስረድተዋል። የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከማሳደጉ ባለፈ የአረንጓዴነት ምጣኔን በመጨመር ወደ ውሃ አካላት የሚወርደውን የደለል መጠን እንዲቀንስ አስችሏል ነው ያሉት። የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ በየዓመቱ ወደ ወንዞች ታጥቦ ይገባ የነበረውን የአፈር ሀብት ከ2 ቢሊየን ቶን ወደ 208 ሚሊየን ቶን ዝቅ እንዲል ማስቻሉን ተናግረዋል። መርሃ ግብሩ የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርታማነትን ማሳደግ ማስቻሉን አንስተው የመድረቅ አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ የውሃ አካላት እንዲያገግሙ አድርጓልም ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባትም ትልቅ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ረቂቅ አዋጁ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ወቅታዊ እና አስተማማኝ የስታቲስቲክስ መረጃዎች እንዲመነጩ ያስችላል
Jun 15, 2026 121
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ወቅታዊ እና አስተማማኝ መረጃዎች እንዲመነጩ፣ እንዲሰራጩና እንዲቀናጁ የሚያደርግ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩ ማር አባተ ገለጹ። ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ 23/2018 ዙሪያ የአስረጂ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩም ቋሚ ኮሚቴው ግልጽነትና ማብራሪያ በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አዋጅ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ወቅታዊ እና አስተማማኝ መረጃዎች እንዲመነጩ፣ እንዲሰራጩና እንዲቀናጁ የሚያደርግ ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ሥርዓት መዘርጋት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በቦርድ እንዲመራ የሚደነግግ ሲሆን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲ አቅጣጫ ቁጥጥር የሚያከናውንበት እንዲሁም ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ አሰራርን በመከተል መረጃ ማመንጨት፣ መተንተንና ጥቅም ላይ እንዲውል ማስቻል ከዓላማዎቹ መካከል ይገኙበታል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ እንዳሉት፤ ረቂቅ አዋጁ በጥናት ላይ ተመስርቶ ተቋማትን ባቀናጀ አግባብ መዘጋጀቱን አብራርተዋል። የብሔራዊ የስታቲስቲክስ ሥርዓትን ለመዘርጋት እንደሚያስችል ጠቅሰው፥ ይህም የተቋማትን ሚናና ኃላፊነት በግልጽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ የሥራ ድግግሞሽና መረጃ መፋለሶችን የሚያስቀር መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ጂኦስፓሻል፣ ዲጂታል፣ በሴንሰር ላይ የተመሰረቱ በመስኩ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል። በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን ለማጎልበት አዋጁ ዓይነተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ(ዶ/ር) እንዳሉት፤ የመረጃ አመንጪዎችን ሚስጥራዊነት መጠበቅ በረቂቅ አዋጁ በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ ነው። ከመረጃ ጥራት ጋር በተያያዘም ተቋማት የሚያመነጩት መረጃ ትክክለኛና መሰረታዊ መርህን ተከትለው መረጃ እንዲያመነጩ የአቅም ግንባታ ተግባራት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ ከዓለም አቀፍና አህጉራዊ የስታቲስቲክስ መርሆና ድንጋጌዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል። ረቂቅ አዋጁ በስታቲስቲክስ መስክ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመጸፈም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ የመረጃ ሰጪዎችን ማንነትና ሚስጥራዊነት መጠበቅ ለዘርፉ ሥራ መቃናት ቁልፍ ሚና አለው ያሉት ሰብሳቢው በአዋጁ የመረጃ አመንጪዎች ግለሰቦችና ተቋማት ሚስጥራዊነት መጠበቅ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የሚደረጉ ማበረታቻዎች አመርቂ ውጤት አምጥተዋል -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Jun 15, 2026 228
አገና፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የሚደረጉ ማበረታቻዎች አመርቂ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የተገነባው ቪታሳሉቲ የላሜራና ቱቦላሬ ብረት ፋብሪካን መርቀዋል። በእዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪው መስክ ባለሀብቶችን በብዛት ለመሳብ በትኩረት እየተሰራ ነው። በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ለማበረታታት በቦታ አቅርቦት፣ በመሰረተ ልማት፣ በገንዘብ ብድር እና ሙያዊ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸው፤ ይህም ለዘርፉ ውጤታማነት የራሱን አስተዋጾ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በሚደረጉ ማበረታቻዎች ምርትን በሚፈለገው ልክ የሚያቀርቡ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎችን ከመገንባት ባለፈ ተኪ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ መጥተዋል ብለዋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካ በዞኑ በተኪ ምርት ላይ የተሰማራ የመጀመሪያ ግዙፍ ፋብሪካ መሆኑን ተናግረዋል። በአካባቢው በተለያዩ የኢንቨስትመት ዘርፍ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች መሰረተ ልማት የተሟላላቸው ቦታዎች መዘጋጀታቸው በባለሃብቱ ተመራጭ አድርጎታል ያሉት ደግሞ የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ናቸው። ፋብሪካው ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ አድርጓል ብለዋል። የቪታሳሉቲ የላሜራና ቱቦላሬ ብረት ፋብሪካን ባለቤት አቶ ሰዒድ ሃጂ ኑሩ፤ ዘርፉን ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት እና የተመቻቸላቸውን ዕድል በመጠቀም ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል። ለፋብሪካው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልጸው፤ በሙሉ አቅሙ ወደስራ ሲገባ ለ123 ቋሚ እንዲሁም ለ273 ሰዎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠር አስታውቀዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የጅማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የስራ ተነሳሽነትን አሳድጓል
Jun 15, 2026 203
ጅማ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ በጅማ ዞን የሚገኙ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት፣ ለማህበረሰቡ እየሰጡት ካለው ቀልጣፋና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በተጨማሪ የአገልጋዮችን የስራ ተነሳሽነት ማሳደጋቸው ተገለጸ። ማዕከላቱ በብቁ ባለሙያዎች መደራጀታቸውና ዘመናዊ አሰራርን መከተላቸው ለአገልጋዩም ሆነ ለተገልጋዩ ትልቅ እረፍት መሆኑ ተመላክቷል። የሊሙ ገነት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለሙያዎች ሪዳ ከማል እና አዳል ኃይለማርያም፤ በማዕከሉ ለህብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት የስራ ተነሳሽነት እንደጨመረላቸው ገልጸዋል። ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የተደራጀ በመሆኑ የአገልግሎት ፍጥነቱን ከመጨመሩ በላይ የሰራተኛውንም ሆነ የህብረተሰቡን ውድ ጊዜ መቆጠብ አስችሏል። በተመሳሳይም የጅማ ማዕከል ባለሙያዎች አብዱልኑራ አባተማም እና ሰሚራ ሐሰን በበኩላቸው፣ ምቹ የስራ ቦታ መፈጠሩ ያለምንም የተገልጋይ ቅሬታ ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። ሌላው በዞኑ በቅርቡ አገልግሎት በጀመረው የኦሞ ናዳ ወረዳ አሰንዳቦ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል በማገልገል ላይ የሚገኙት ማረሜ በቀለ እና አንዋር አባዲጋ፣ ለማህበረሰቡ በንቃትና በትጋት አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። ምቹ የስራ ሁኔታ መኖሩ ሰራተኞች ያለመሰልቸት በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ማድረጉን የጠቀሱት ባለሙያዎቹ፣ በዚህም ለዓመታት የህብረተሰቡ የቆየ ጥያቄ የነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ሙሉ በሙሉ መቀረፉን አስታውቀዋል። በማዕከላቱ አገልግሎት ለማግኘት የመጡት ሙስጠፋ አብዱረህማን በበኩላቸው፣ በአካባቢያቸው እንዲህ ያለ ዘመናዊ ማዕከል መከፈቱ በእጅጉ እንዳስደሰታቸው ገልጸው፤ ገና ወደ ማዕከሉ ስገባ ከመስተንግዶው ጀምሮ የባለሙያዎቹ አቀባበልና ፍጥነት ከፍተኛ እርካታ የሚሰጥ ነው ብለዋል። ለመንጃ ፈቃድ አገልግሎት የመጣው ጀማል አብዱረህማንም ማዕከሉ ከምንም በላይ ወደ ህብረተሰቡ የቀረበና ለዓመታት ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ መሆኑን ተናግሯል። በጅማ ከተማ በሚገኘው ማዕከል የልደት ካርድ ለማውጣት የመጣችው የጅማ ከተማ ነዋሪ ቤተመቅደስ አምሀ፣ ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል ማግኘቷ እንዳስደሰታት ገልጻለች። የጅማ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ጀማል ሳሊ፣ በማዕከሉ የሚሰጠው አገልግሎት ለተገልጋዩ ብቻ ሳይሆን ለአገልጋዮችም ጭምር የእርካታ ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ጊዜና ገንዘቡን ቆጥቦ ፈጣን አገልግሎት አግኝቶ መመለሱና በተሰጠው አገልግሎት ረክቶ የሚሰጠው አዎንታዊ ምላሽ ለሰራተኛው ትልቅ ተነሳሽነት መፍጠሩን አብራርተዋል።
"ቤጉ መሶብ" አዳዲስ አገልግሎቶችን በማካተት ተደራሽነቱን እያሰፋ ነው
Jun 15, 2026 211
አሶሳ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ (ቤጉ) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አዳዲስ አገልግሎቶችን በውስጡ በማካተት ለተገልጋዮች ያለውን ተደራሽነት እያሰፋ መሆኑ ተገለጸ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እያደገ የመጣውን የንግድ፣ የግብርና እና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ለማስተናገድ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ለማዘመን በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በዚህም ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በአምስት የክልል እና ሶስት የፌደራል ተቋማት 33 አገልግሎቶችን አካቶ ስራ የጀመረው "ቤጉ መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአሁኑ ሰዓት አገልግሎቱን በማስፋት ተደራሽነቱን እያሳደገ ይገኛል። የቤጉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ኢንጂነር ሰመረ ጅራታ እንደተናገሩት፤ ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት 33 የነበሩትን አገልግሎቶች ወደ 42 በማሳደግ ዜጎች ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራ ነው። ፍትህ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በማዕከሉ እየሰጧቸው ከሚገኙ አገልግሎቶች በተጨማሪ ውልን መርምሮ ማጽደቅ እና የመድን ፈንድ አገልግሎት መስጠትን የመሳሰሉ አዳዲስ የስራ ዘርፎችን በማካተት የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በቅርቡም የክልሉ ማዕድን ቢሮን ጨምሮ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና ሌሎች ተቋማት ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል። ቤጉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እስካሁን ድረስ ከ28 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት መስጠቱን ጠቁመው፤ የተገልጋዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል። ቤጉ መሶብ በቅርቡ ስራ ለጀመረው አሶሳ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም አስፈላጊውን የሙያ ዕገዛ በማድረግ ማዕከሉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ ማድረጉን አብራርተዋል። በቅርቡም በባምባሲ፣ ግልገል በለስ እና ካማሽ ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
አገልግሎቱ አሰራርን ከማዘመን ባለፈ የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ ነው
Jun 15, 2026 257
ወልቂጤ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰራርን ከማዘመንና ከማቀላጠፍ ባለፈ የአገልጋይነት ባህልን በማዳበር የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በወልቂጤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅቱ እንዳሉት፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት ተቋማትን አሰራር ከማዘመን ባለፈ የአገልጋይነት ባህል በመገንባት የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ ነው። ለዚህም የአገልግሎት አሰጣጡን በየጊዜው በማዘመንና ተግባሩን በማጥናት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል። በክልሉ ሦስት ማዕከላት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸው በክልሉ የመንግስት አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል በተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የሚስተዋለውን እንግልት በመቀነስ እርካታን እንደሚያመጣ ጠቁመዋል። በማዕከሉ ሰባት የፌደራልና የክልል ተቋማት 41 የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶችን እየሰጡ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ናቸው። በቴክኖሎጂ የተደራጀው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዚህ ቀደም ረጀም ቀናትን ይፈጅ የነበረውን ጉዳይ በአጠረ ጊዜ በመጨረስ ፈጣን ምላሽን ይሰጣል ብለዋል። በክልሉ ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የወልቂጤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሆሳዕናና በወራቤ ከተሞች ከተገነቡት ቀጥሎ ሦስተኛው መሆኑ ይታወቃል።
አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማስተዋወቅ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን እየተሰራ ይገኛል
Jun 14, 2026 961
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 7/2018 (ኢዜአ)፦ የምርምር እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማስተዋወቅ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን እየተሰራ እንደሚገኝ የፌደራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ኢንስቲትዩቱ ከሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ እና የቴክኖሎጂ ውድድር የመዝጊያና የአሸናፊዎች ሽልማት መርሀግብር አካሂዷል። በመርሀግብሩ የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ተመራማሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ጉባኤው አዳዲስ አሰራሮችንና ፈጠራዎችን በማስተዋወቅ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለመደገፍ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። በጉባኤው የቀረቡት የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለፖሊሲና ስትራቴጂ ግብዓት የሚሆኑ ሲሆን፣ ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር በማቀላጠፍ በኩል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ10 በላይ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ የምርምርና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በሶስት ቀናት ቆይታ 18 የምርምር ስራዎች፣ 100 የፈጠራ ስራዎችና 34 የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ መቅረባቸው ተናግረዋል። ከቀረቡት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች መካከል 6ቱ የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ከኢትዮጵያ የቀረቡት (IOT SMART IRRIGATION FOR CLIMATE) እና (CEREBRO-LOGIC) አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን፣ ከናይጄሪያ የቀረበው (ECOLYFT) ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ለሽልማት በቅተዋል። አሸናፊ የሆኑት እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተግባር ላይ ውለው ወደ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ተቋማዊ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተገልጿል። የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሃብታሙ ሙለጌታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ባለፉት ሶስት ቀናት በርካታ የምርምር የሳይንስና ቴክኒሎጂ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል። እንደ ሀገር በተለይም ከአምስቱ የልማት ምሰሶዎች ትኩረት ያደረጉ ጥናቶች መቅረባቸው ገልፀጸው፤ ጥናቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ጠቁመዋል። ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘም አሁን ላይ የተጀመረው የልምምድ ስራ ሊያዳብሩ የሚችሉ በርካታ የፈጠራ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን የተኪ ምርት ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው ብለዋል። ከቀረቡት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች መካከል 6ቱ የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ከኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ሲሆን ከናይጄሪያ የመጣችው ተወዳዳሪ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። አንደኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ከዜድ ቴን ቴክኖሎጂ ዘላለም እንዳለው ውድድሩ ጠንካራ እንደነበር ገልጾ፤ አንደኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ ደስታ እንደተሰማው ተናግሯል። የሰራው የፈጠራ ስራ ዘመናዊ የመስኖ መቆጣጠርያና መከታተያ ቴክኖሎጂ ሲሆን 50 በመቶ ውሃን መቆጠብ እንዲሁም 30 በመቶ ምርትን ማሳደግ የሚያስችል እንደሆነ ገልጿል። አንጎል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮች ያለቀዶ ጥገና ህክምና ማወቅ የሚያስችል የፈጠራ ስራ በማቅረብ ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁትን በመወከል የገለጸችው ደግሞ ተማሪ ሩት ተሾመ ናት።
ስፖርት
በዓለም ዋንጫው አፍሪካዊቷ ኬፕቨርዴ ከስፔን ጋር አቻ ተለያየች
Jun 15, 2026 150
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ስምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ስፔን እና ኬፕቨርዴ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስፔን በኳስ ቁጥጥር እና በግብ ሙከራ ከፍተኛ ብልጫ ብትወስድም ጎል ከመረብ ላይ ማሳረፍ ተስኗታል። በአንጻሩ ኬፕቨርዴ በጨዋታው ላይ የተከተለቸው የመከላከል ስልት አንድ ነጥብ አስገኝቶላታል። የኬፕቨርዴው ግብ ጠባቂ ቮዚኒሃ ያዳናቸው ኳሶች ወሳኝ ነበሩ። 166 ሺህ ህዝብ ያላት የአፍሪካ የደሴት ሀገር ኬፕቨርዴ ከእግር ኳስ ኃያሏ ስፔን ነጥብ በመውሰድ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግባለች። ብሔራዊ ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ እየተሳተፈ ይገኛል። የአንድ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን ጉዞዋን በአቻ ውጤት ጀምራለች። በዚሁ ምድብ ሳዑዲ አረቢያ ከኡሯጓይ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በሚያሚ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
Jun 15, 2026 108
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ43ኛው ደቂቃ ግቡን ከመረብ ላይ አገናኝቷል። የፋሲል ከነማው ሀብታሙ ተከስተ በ38ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ፋሲል ከነማ በ49 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 12ኛ ድሉን አግኝቷል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ35ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ነገሌ አርሲ ሃዋሳ ከተማን እና አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል። አርባምንጭ ከተማ ምድረ ገነት ሽሬን 2 ለ 0 ረትቷል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ
Jun 15, 2026 101
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ዛሬ በሊጉ አክሲዮን ማህበር ይፋ ሆኗል። በዚሁ መሰረት መስፍን ታፈሰ (ሲዳማ ቡና)፣ ዳዊት ተፈራ (ነገሌ አርሲ)፣ ያሬድ ባየህ (ሲዳማ ቡና) ፣ ቸርነት ጉግሳ (መቻል) ፣ አብዱልከሪም ወርቁ (መቻል) ፣ ናትናኤል ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ፍፁም ጥላሁን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ፍፁም አለሙ (መቀሌ 70 እንደርታ)፣ ሮሆቦት ሰላሎ (ነገሌ አርሴ) እና አቤል ያለው (ሲዳማ ቡና) በኮከብ ተጫዋች እጩነት ውስጥ ተካተዋል። ሄኖክ ይበልጣል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ሁዘይፋ ሻፊ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ከቤ ብዙነህ (ነገሌ አርሲ)፣ ያሬድ ብሩክ (ሃዋሳ ከተማ)፣ ሀብታሙ ጉልላት (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዳዊት ካሳው (ሸገር ከተማ) እና ዳዊት አውላቸው (ኢትዮጵያ መድን) የኮከብ ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ናቸው። ደጋፊዎች በhttps://t.me/ethiopianlea የቴሌግራም ገጽ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድምጽ መስጠት እንደሚችሉ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል። ከተመልካቾች ድምጽ በተጨማሪ አሰልጣኞች፣ ጋዜጠኞችና የሊጉን ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት መብት የወሰደው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የቴሌቪዥን ጣቢያ በድምጽ አሰጣጡ ድርሻ እንዳላቸው ተመላክቷል። የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋቾች የሽልማት ስነ- ስርዓት የሚካሄድበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ታውቋል።
የመውረድ ስጋት ያለበት አዳማ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል
Jun 15, 2026 124
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ እና አቤነዘር ሲሳይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ናትናኤል ዳንኤል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፍጹም ቅጣት ምት ጎሏን አስቆጥሯል። በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በ42 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 15ኛ ከፍ አድርጓል። ከወራጅ ቀጠና በመጠኑ ፈቀቅ እንዲርቅ ያደረገውን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። በውድድር ዓመቱም ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል። በአንጻሩ በሊጉ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ45 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ናትናኤል ዳንኤል በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 14 ከፍ በማድረግ ተመሳሳይ የግብ ብዛት ካለው የሲዳማ ቡናው አቤል ያለው ጋር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጋራ መምራት ጀምሯል።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ወሳኝ የልማት አቅጣጫ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Jun 15, 2026 44
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ የልማት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ ኮፕ-32ን ስታስተናግድ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች ሀገር መሆኗን ለዓለም እናበስራለንም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የዘንድሮው አረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ በቢሾፍቱ ከተማ መካሄዱ ከተማዋ ከራሷ አልፎ ለአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ችግኞችን የምታመርት መሆኗን ዕውቅና የሚሰጥ ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን፣ የሰብልና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ወሳኝ የልማት አቅጣጫ መሆኑን አስረድተዋል። የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት የሚደፈረው በሁለት ጉዳዮች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንዱ ባዕዳን ኃይሎች አልመውና ድንበር ጥሰው ሲገቡ ሲሆን፤ ሌላኛው የእኛ ሃብትና ንብረት በዋዛና ፈዛዛ ሲወጣም የሉዓላዊነት መደፈር ነው ብለዋል። ኢትዮጵያም ባለፉት ዓመታት ያጣችው የአፈር መጠን በገንዘብ ሊተመን የማይችል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል። የእኛ አባቶች ዓድዋ ላይ ወራሪን በማሳፈር ገድል ሠርተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የእኛ ትውልድም በአረንጓዴ ዐሻራ ሌላኛውን ለትውልድ የሚሻገር ታላቅ ገድል እየሰራ ነው ብለዋል። የዘንድሮው "ተስፋን እንትከል" መሪ ሃሳብ የነገን ብሩህ ዛሬ በመፃፍ፣ የተስፋ ስሮች ዘልቀው የብልፅግና ግንድ፣ ቅርንጫፍና ፍሬ ተስፋፍቶ ሃብት እንዲሆኑ የሚያመላክት መሆኑንም ተናግረዋል። የተስፋ ምርጫም የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎችና መላው ኢትዮጵያውያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የትኛውም የአየር ሁኔታ ሳይበግራቸው ተስፋን በመሰነቅ ድምፅ መስጠታቸውን ከመሪ ሃሳቡ ጋር አሰናስለው አስገንዝበዋል። ተስፋ የአረንጓዴ መቀነት ነው፣ ሀገርን ያለብሳል፣ የተራቆተና የገረጣን መሬትም ያለመልማል፣ ተስፋ አረንጓዴ ፀዳልና መንፈስን የሚያድስ አረንጓዴ ወርቅ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የአረንጓዴ ውርስ ትውልድ የሚከበርበት ቀጣዩ ትውልድ ልምድና ባህል የሚያደርገው የብልፅግና መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ በመደመር መርህ የኢትዮጵያን የተረጂነት ታሪክ ወደ ማድረግ ዘመን የሚያሸጋግር መሆኑን አንስተው፤ መርሃ ግብሩ አፈራችንን ከስደት፥ ግድባችንን ከደለል የሚታደግ ስኬታማ የልማት ዓምድ ነው ብለዋል። ከአስር በላይ አዳዲስ የፍራፍሬ ዝርያዎችን በኢትዮጵያ በማላመድ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለዚህ ስኬትም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ በችግኝ ማፍላት፣ በእንክብካቤ፣ በመትከል፣ በችግኝ ሽያጭ፣ በንብ ማነብና በእንስሳት ማድለብ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል። በቀጣይም የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ በሁሉም መስክ የተመዘገበውን ስኬት ማስፋትና ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም አፅንኦት ሰጥተዋል። ከ2011 ዓም ጀምሮ በተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመው፥ ዘንድሮም ከስምንት ቢሊየን በላይ ችግኝ በመትከል በአጠቃላይ 56 ቢሊየን እንደሚደርስ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ-32ን ስታስተናግድ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች ሀገር መሆኗን ለዓለም እናበስራለን ብለዋል። ለዚህም ሁሉም ዜጋ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት በማስቀጠል በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥሉት የክረምት ወራትም "ተስፋን በመትከል" በዓድዋ ድል ቅድመ አያቶች የተቀዳጁትን ድል በአረንጓዴ አሻራ ልማት በመድገም የኩራት ምንጭ የሆነች ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ሥራችን ከተፈጥሮ የመታረቅ በልማት የመላቅ አዲስ ጎዳና ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jun 15, 2026 162
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ሥራችን ከተፈጥሮ የመታረቅ በልማት የመላቅ አዲስ ጎዳና ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ለአንዲት ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሕዝብ ተደምረን በሠራነው የአረንጓዴ ዐሻራችን፣ ልምላሜ የተራቡ ተራሮች አረንጓዴ ለብሰዋል ብለዋል። ምንጮች እና ተፋሰሶች ምድሩን አረስርሰዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በረሃማነት ይጸናባቸው የነበሩ ክበበ ምድሮች ነፋሻማ ሆነዋል ሲሉም ገልጸዋል። የተፈጥሮን ጫና ተቋቁመናል! ይህ ደግ የተፈጥሮ ዕርቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል በመልዕክታቸው። የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥን ከተፈጥሮ ጥበቃ ጋር በማስተሣሠር በተሠራው ሥራ የፍራፍሬ ተክሎች በስፋት ለምተዋል፤ ፍሬ መስጠትም ጀምረዋል ብለዋል። ይህም በምግብ ራስን ለመቻል ለጀመርነው ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ ተደማሪ ዐቅም ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል። አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያ ልጆች ከፖለቲካ አሰላለፍ አልፈው፣ ከሐሳብ ተቃርኖ ተሻግረው፣ ገጸ ብዙ ልዩነቶችን አሸንፈው ለሀገርና ለትውልድ አስበው ያሳኩት የመተባበር ድል፣ የተጨበጠ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ልጆች ስንተባበር ትርፋችን እልፍ፣ ዕቅዳችንም የተሳካ የሠመረ ይሆናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ የእስከ ዛሬ ድካማችን መደምደሚያ፣ የድላችን መዳረሻ፣ በድል ላይ ቆመን ለሌላ የላቀ ድል የምንነሣበት ልዩ ዓመት ነው ብለዋል። ሁላችንም በሩጫ ትግል ሊያልቅ ሲል እንደሚበረቱት ሊጠናቀቅ ሲል እንደሚፈጥኑት ጀግኖች አትሌቶቻችን ካለፉት ዓመታት አስበልጠን እንትከል! እንበርታ! እንፍጠን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ አስጀመሩ
Jun 15, 2026 187
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠን፣ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል። ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጭው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራዎን ያኑሩ ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ከጤና ጠንቅነት ወደ ንጹህ ውብ መዝናኛ ስፍራነት የተለወጠው የወንዝ ዳርቻ ልማት
Jun 14, 2026 728
ከእንጦጦ እስከ ፒያሳ የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት ቀደም ሲል የቆሻሻ መጣያና ለጤና ጠንቅ የነበሩ አካባቢዎችን ወደ አረንጓዴ፣ የንግድና የመዝናኛ ማዕከልነት በመቀየር የነዋሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ስኬታማ ሥራ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ከእንጦጦ እስከ ፒያሳ (ቀጨኔ መድኃኔዓለም) የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት፣ የአዲስ አበባን ገጽታ ከመቀየርና የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት ከማሻሻል አንጻር እጅግ ሰፊና ዘርፈ-ብዙ ትርጉም ያለው ግዙፍ ስራ ነው። ቀደም ሲል እነዚህ የወንዝ ዳርቻዎች የፍሳሽና የደረቅ ቆሻሻ መጣያ፣ እንዲሁም ለከባድ ጠረንና ለበሽታ መፈልፈያነት የተጋለጡ ነበሩ። ይህ ፕሮጀክት ግን የወንዝ ዳርቻዎቹን በማጽዳትና የተፈጥሮ ፍሰታቸውን ጠብቀው እንዲፈሱ በማድረግ የስነ-ምህዳር መዛባትን ታድጓል። ፕሮጀክቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አረንጓዴ ተክሎች፣ አበቦችና ዛፎች በመተከላቸው አካባቢው ንጹህ አየር እንዲኖረውና የሙቀት መጠንን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። የእግር ጉዞ መስመሮች እና የብስክሌት መንገዶች ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ምቹ ዕድል ፈጥረዋል። ቤተሰቦችና ጓደኛማቾች የሚገናኙባቸው፣ የተለያዩ ማህበራዊና ባህላዊ ሁነቶች የሚስተናገዱባቸው ሰፊና ውብ ስፍራዎች ተፈጥረዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ልማቱ ከመጀመሩ በፊት የነበረውን አስቸጋሪ ሁኔታ በማስታወስ አሁን የመጣውን ለውጥ አስደሳችና የሚስደንቅ መሆኑን ይናገራሉ። ወይዘሮ አስናቀች ካሳ እንደገለጹት ፤ የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ከመሰራቱ በፊት አካባቢው ንጽህናው የተበላሸ፣ የቆሻሻ መከማቻ እና ለጤና የማይበጅ ነበር። አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ እጅግ መልካም ገጽታን መላበሱን ልማቱ የአካባቢውን ንጽህና ከመጠበቅ ባለፈ፣ ለልጆች መጫወቻነት፣ ለአዋቂዎች መዝናኛነት እና ለሥራ ዕድል መፍጠሪያነት እየዋለ ይገኛል ብለዋል፡፡ ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ አቶ ኪዳነቃል እርጌ በበኩላቸው፤ የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ለአካባቢው ሰላምና ጸጥታ መከበር ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በልማቱ አማካኝነት በርካታ መንገዶች በመገንባታቸው ለነዋሪዎች ምቹና አማራጭ የትራንስፖርት ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል። ፕሮጀክቱ የያዛቸው ዘርፈ-ብዙ መሰረተ-ልማቶች ሕፃናትን፣ ወጣቶችንና ወላጆችን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሁም ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎች ያካተቱ ሆነው መገንባታቸው ልዩ ያደርገዋል ስትል የተናገረችው ወጣት አዳነች አይሳ ናት። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ኃይሌ ሰለሞን ከልማቱ በፊት በአካባቢው የወንዝ መሻገሪያ ድልድይ ባለመኖሩ እና በቆሻሻ ሽታ ሳቢያ በእጅጉ ይችገሩ እንደነበር ተናግረው ፤አሁን ግን የአካባቢው ገጽታ ተስተካክሎ ለሌሎች ሰዎች ጭምር ተመራጭ መዝናኛ ሆኖ በመገኘቱ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 8197
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 6730
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 5553
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 5460
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
Jun 15, 2026 252
በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? 👉የተራሮች ስር ፈርጥ - ወልዲያ የዛሬው የወፍ በረር ምልከታችን የሚጀምረው የተራሮች ስር ፈርጥ በሆነችው ወልዲያ ከተማ በመገኘት ነው። ከደሴ በ120 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውና በረጃጅም ተራሮች የተከበበችው ወልዲያ ከተማ ከነበረችበት ጉስቁልና ወጥታ አሁን ላይ በውበት ፈክታ ትገኛለች። በሳምንቱ በዚህች ከተማ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የኮሪደር ልማቷንና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀዋል፤ ተዘዋውረውም ጎብኝተዋል። በተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ትውፊቶች ስሟ ጎልቶ የሚጠራው ወልዲያ እንደ ከዋክብት ፈክታ እንግዶቿን ተቀብላ አስተናግዳለች። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ወደ ገጠር ጭምር እየተስፋፉ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ኢትዮጵያ ዕዳዎቿን እያራገፈች ተስፋዎቿን እየጨበጠች ትገሰግሳለች ብለዋል። 👉የሸደር አዳሪ ትምህርት ቤት የሚቀጥለው መዳረሻችን በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን አውበሬ ወረዳ ሼደር ከተማ አዲስ የተገነባውን አዳሪ ትምህርት ቤት መመረቅ ይሆኗል። የትምህርት ቤቱን ግንባታ መርቀው ስራ ያስጀመሩት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ናቸው። ርዕሰ መስተዳድሩ በመልእክታቸው፤ በክልሉ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማስፋት የተማረ ትውልድ ማፍራት የሚያስችሉ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። በ138 ሚሊየን ብር የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ስራ መጀመሩ ለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል። 👉የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የበረራ ቅኝታችን ቀጥሎ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቂምቢቢት ወረዳ በመስኖ እየለማ ያለ የስንዴ ምርት የመጎብኘት እድል አግኝተናል። በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ቂምቢቢት ወረዳ በ21 ሺህ 463 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የመስኖ ስንዴ ሰብል መሰብሰብ ተጀምሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፤ በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው የበጋ መስኖ ልማት ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የአርሶ አደሩን ገቢ እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ ይገኛል ብለዋል። የግብርና ሜካናይዜሽንን በስፋት በመጠቀም እንዲሁም ፈጠራን በማከል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረቱ በተሳካ መልኩ መቀጠሉን አንስተዋል። 👉ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ዓለም አቀፍ ክስተት ነው። ችግሩ በተለይም በታዳጊ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብአዊ ጉዳቶችን እያስከተለ ይገኛል። ኢትዮጵያም የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንደመሆኗ መጠን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ መፍትሄ ለመስጠት ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች። በዚህ ረገድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርንና ፍልሰትን ለመግታት በሚከናወኑ ሥራዎች በምርምር እያገዙ ናቸው። በሂደቱ ውጤታማነት ላይ የሚመክር መድረክ በሰመራ በተደረገበት ወቅት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲዎች የሕግና ማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኖች ችግሩን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት በምርምርና በማማከር እያገዙ መሆናቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሰዎች ህገወጥ ዝውውርንና ፍልሰትን ለመግታት የነፃ የሕግ ድጋፍና የማማከር አገልግሎትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን ለህብረተሰቡ እየሰጡ ናቸው። 👉የኢትዮጵያ እያመረተች ነው በአማራ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር «ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት» በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል። መርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እና ሌሎችም በተገኙበት ተካሂዷል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የገቢ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ ለውጭ ምንዛሬ አይነተኛ የገቢ ምንጭ መሆን አስችሏል ብለዋል። 👉መሶብ በአርባ ምንጭ፣ ዲላ እና ነቀምቴ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተስፋፋ የመጣው የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት በዚህ ሳምንት አርባ ምንጭ፣ እና ዲላ ከተሞች ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። የመሶብ ማእከላቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀዋል። የዲጅታል አሰራርን በማስፋት ለዜጎች ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት የመስጠት ጥረቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። 👉ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በኢፌዴሪ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሠረት፣ በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች እና የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር በተለያዩ ግንባሮችና ካምፖች የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በመደበኛው የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ለመስጠት የሚቸገሩ ስለመሆኑ ያነሳል። በመሆኑም ይህን መሠረታዊ መብት ለማስከበርና የምርጫውን አካታችነት ለማረጋገጥ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ መመሪያዎችን በማውጣት ልዩ የምርጫ ጣቢያዎችን አደራጅቷል። በመሆኑም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በእለቱ ድምፅ መስጠት ካልቻሉት መካከል የሰሜን ምስራቅ ዕዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከቀናት በፊት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል እና በደብረ ብርሃን ከተማ በጊዜያዊ መጠለያዎች የሚገኙ ዜጎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል። 👉የመኸር እርሻ ንቅናቄ በሲዳማ ክልል የመኸር እርሻን በንቅናቄ በመምራት የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡና ገበያን የሚያረጋጉ የግብርና ልማት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በንቅናቄ መድረኩ ርእሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት መሬት ጦሙን እንዳያድርና ግብአትን በወቅቱ በማቅረብ እንዲሁም ለግብርና ቴክኖሎጂ ትኩረት በመስጠት ምርታማነቱን ማሳካት አስችሏል። ዘንድሮም ተግባሩን በማስቀጠል የበልግ ሰብልን ከመሰብሰብ ጎን ለጎን የመኸር እርሻን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱ በዘገባው ተመላክቷል። ይህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ትርፍ በማምረት ገበያን ለማረጋጋትና ለኢንደስትሪዎች ግብአት ለማቅረብ ያስችላል ነው የተባለው። በምርት ዘመኑ የተያዘውን እቅድ ለማሳካትም አመራሩ ህብረተሰቡን በማስተባበር ለውጤቱ መትጋት እንዳለበትም በውይይቱ ተነስቷል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የምርጥ ዘር ብዜትን በዓይነት፣ በመጠንና በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ማቅረብ ተችሏል። ቢሮው በግብርና ግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዘርፍ እና በክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዘር ብዜት ዕቅድ አፈጻጸምና ዝግጅት ላይ ያተኮረ የባለ ድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የግብርና ግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ እንደገለጹት፤ በክልሉ የምርጥ ዘርን በጥራትና በመጠን ለአርሶ አደሩ በወቅቱ በማድረስ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል። ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ለኢንዱስትሪዎች በቂ ግብዓትን ለማቅረብና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር አግዟል። ተግባሩን በማስቀጠልም በ2017/18 የምርት ዘመን በክልሉ ከ2 ሺህ 200 ሄክታር በላይ መሬት ላይ ከ30 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ማምረት መቻሉንም ገልጸዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ - ለዓየር ንብረት ለውጥ ላለመበገር የሚደረግ ትጋት
Jun 14, 2026 605
በኢዜአ ዐይን …! በሙሴ መለሰ አረንጓዴ ዐሻራ - ለዓየር ንብረት ለውጥ ላለመበገር የሚደረግ ትጋት የዓየር ንብረት ለውጥ የምድራችን ፈተና ነው። ልብ መባል ያለበት ግን አፍሪካ ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዋ አነስተኛ ሆኖ ሳለ ጉዳቷ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ስለዚህ አኅጉሪቱ ዕጇን አጣጥፋ ወቃሽና ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በፈተና ውስጥ ሆናም በዘላቂነት የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ለማምጣት መትጋት አለባት። የሩቅ መፍትሔ አይጨበጥም፤ አይዘልቅምና። ከመፍትሔዎች አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ነው።በዚህ ሂደት ደግሞ የኢትዮጵያ ድንቅ ስራ የሚወደስ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት፤ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ለዓየር ንብረት ለውጥ ከተሰጡ ምላሾች መካከል በፊትአውራሪነት ይጠቀሳል። መርሐ-ግብሩ የጋራ ነው በሚል ዕሳቤ በርካቶችን በንቃት አሳትፎ ለዓለም የሚደርስ የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ማምጣት እንደሚቻል በተግባር ዐሳይቷል። የደን ሽፋን መጠንን አሳድጓል። ይህም በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ የራሱን ሚና እያበረከተ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአረንጓዴ ዐሻራ ሚና ልቆ ይነሳል። ይህም የተራቆተ መሬትን ወደ ነበረበት ከመመለስ፣ የውኃ ሀብት አሥተዳደርን ምቹ ከማድረግ እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩ በዕድሜ፣ በጾታ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በሥራ ዘርፎች፣ በኑሮ ደረጃ፣ በሐይማኖት ሳትለይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲሳተፉበት በማድረጓ በዘርፉ ስኬታማ ጉዞ ላይ ናት። ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀት ከመሆን አልፎ ለጎረቤቶቿ ችግኝ በመለገስ መርሐ-ግብሩ እንዲስፋፋ እየተጋችም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ሲናገሩ፤ አረንጓዴ ዐሻራ ኢትዮጵያ ትላልቅ ነገር አስባ፣ ትላልቅ ነገር ተልማ፣ ትላልቅ ነገር አቅዳ እና ሕዝቦቿን አስተባብራ ማሳካት እንደምትችል ለሌሎቹ ማሳያ ነው ማለታቸውም ከላይ ያነሳነውን ሐሳብ ያዳብረዋል። በተጨማሪም አረንጓዴ ዐሻራ በልዩ ትኩረት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሳይቆራረጥ እየተሠራ መሆኑን፤ በየዓመቱም በሚተከሉ ችግኞች ብዛት፣ በሚተከልበት መሬት ስፋት እና በሚሳተፉ ታታሪዎች ቁጥር እያደገ መሆኑን ያመላክታል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች እየወጡ በችግኝ ተከላ መሳተፋቸው የሀገርን የጋራ ራዕይ ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል። #አረንጓዴ_ዐሻራ #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 4192
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም --
Jun 5, 2026 8632
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
ትንታኔዎች
በኢዜአ ዐይን…!
Jun 15, 2026 119
በዮሐንስ ደርበው ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ • እንደ መነሻ ባሳለፍነው ወርኃ ግንቦት ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አካሂዳለች። ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መታያ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ገቢራዊነት መገለጫ፤ ሕዝባዊ መንግሥትን አንባሪ ብሎም በሕዝባዊ ምርጫ ብቻ ወደሥልጣን የሚመጣበት መንገድ ነው። ለሀገራዊ መግባባትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታም ቁልፍ ነው። ቅድመ ምርጫ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ባለድርሻ አካላት ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነዋል። ለአብነትም፤ የምርጫ ሕጉን ከማሻሻል ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥርዓቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የምርጫ ትምህርትና ግንዛቤን ለማስፋት ለሚሠሩ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። የምርጫ ሂደትን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥም በርካታ ድርጅቶች በታዛቢነት ተመዝግበዋል። የመራጮች ምዝገባም፤ በመደበኛ የመራጮች ምዝገባ (ማኑዋል)፣ ምርጫዬ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና በድረ ገጽ አማራጭ በመቅረቡ በርካታ መራጮችን አሳትፏል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በ24 ሬዲዮ፣ በ20 ቴሌቪዥን እና በ6 ጋዜጦች በሕዝብና በንግድ ሚዲያዎች ነጻ የአየር ሠዓት ተደልድሏል፤ ሐሳባቸውንም ተደራሽ አድርገዋል። • በምርጫ ወቅት በምርጫ ካርድ ሀገር የሚመራን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ ከሥልጣኔ መገለጫዎች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል። የመራጮች ንቁ ተሳትፎም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያጎለብታል። ምርጫ፤ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ፣ ተቋማዊ አሠራሮች እንዲጠናክሩ ቁልፍ በመሆኑ ጠቅላላ ምርጫው ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡበት ነው። የሕዝቡን ትጋት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክትም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተዓምረኛም ሕዝብ ነው፤ ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባሕል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል ብለዋል። ታሪካዊ በሆነው ዕለትም፤ የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣ የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው፣ ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣ ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣ የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣ ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣ ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤ በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል ያሳዩት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ሁሉ የሥልጡን ሕዝብ ትጋት በኋላ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አረጋግጠዋል። ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ከማለዳው 12፡ 00 ሠዓት ጀምሮ ድምፃቸውን መስጠታቸውን አስታውቀዋል። ረጃጅም ሰልፍ የነበረባቸውን የምርጫ ጣቢያዎችም እስከ ሌሊቱ 6 ሠዓት በማራዘም መራጮች ድምፅ እንዲሰጡ መደረጉን አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ የ7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተመለከተ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን በነፃነት እና በሙሉ ፈቃዳቸው እንደተጠቀሙበትም ልዑካቸው ታዝቧል። ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተግባር አሳይተዋል፤ ያለምንም ጫና የሚፈልጉትን ፓርቲ መርጠዋል፤ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ እና በተዓማኒነት የተሞላ ሂደት ነው ብለዋል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያውያን የዜግነት መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን መስጠታቸውን ዐይተናል ብለዋል። የምርጫ ሂደቱ በተቀናጀ መንገድ መካሄዱን፣ በምርጫ ጣቢያዎችም ነፍሰ ጡር እናቶች፣ ልጆቻቸውን የያዙ እናቶች፣ ወጣቶች እና አዛውንቶች ሳይቀሩ ከማለዳው ጀምሮ ድምጽ ሲሰጡ እንደነበር መታዘባቸውን ተናግረዋል። በሁሉም አካባቢ የድምፅ መስጠት ሒደቱ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመጠቆም፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የታየበት መሆኑን አስታውቀዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈፀም ዐቅም እያደገ መምጣቱ የታየበት ስኬታማ ምርጫ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን ናቸው። ምርጫውን መታዘባቸውን በመጥቀስ፤ ምርጫው በርካታ ዜጎች የተሳተፉበት፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምርጫው አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ዜጎች ድምጻቸውን እንደሰጡም ነው የገለጹት፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ይበልጥ አካታች ተሳትፎን እያጎለበተ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል። አክለውም፤ መንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃንና ሌሎችም አጋር አካላት ለምርጫው ስኬታማነት ሚናቸውን መወጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ የዴሞክራሲና የፍትሕ ተቋማት እንዲጠናከሩ በትኩረት መሠራቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ቦርዱ ነፃና ገለልተኛ በመሆን የማስፈጸም ዐቅሙ እያደገ መምጣቱን በማንሳት፤ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በአብነት ጠቅሰዋል፡፡ • ድኅረ ምርጫ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ፤ የ1 ሺህ 8 የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ቦርዱ የማረጋገጫ ማዕከል መግባቱን ተናግረዋል። የምርጫ ጣቢያዎች የውጤት ቆጠራ ተጠናቅቆ በምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል። ከ501ዱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች 446ቱ ወደ ማዕከል መድረሳቸውንና ቀሪዎቹ የክልል ምክር ቤቶች መሆናቸውንም አብራርተዋል። በሌላ በኩል በመጠለያ ጣቢያዎችና በካምፖች የድምፅ አሰጣጥ መከናወኑን ጠቁመው፤ ውጤት የማዳመር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። #ምርጫ #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #በኢዜአ ዐይን
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 4192
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው?
Jun 12, 2026 1232
የጤና ነገር … በዮሐንስ ደርበው የሰው ልጅ ሊሻሻሉ በሚችሉ እና በማይችሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለልብ ህመም ሊጋለጥ እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የአዋቂ የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሃኑ ሞገስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የልብ ህመም ከተወሳሰብ ዘላቂ የጤና እክል እስከ ድንገተኛ ኅልፈት ያደርሳል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ሰዎች ማሻሻል በሚችሏቸው (ሞዲፋይብል) እና ማሻሻል በማይችሏቸው (ነን ሞዲፋይብል ወይም ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች) ለልብ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዶክተር ብርሃኑ ይገልጻሉ። መሻሻል ከሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም (በአግባቡ መድኃኒቱ ካልተወሰደ)፣ተገቢ ያልሆነ የስብ ክምችት፣ ከፍተኛ ውፍረት (ክብደት)፣ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብ አለመኖር እንዲሁም አብዝቶ ስኳር፣ ጣፋጭና አልኮል መጠቀም የሚሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ እንዲሁም ሰዎች ማሻሻል ከማይችሏቸው (ተፈጥሯዊ) አጋላጮች መካከል፤ በቤተሰብ የሚተላለፍ መኖሩን፣ በዕድሜ መጨመር የሚከሰት መሆኑን (ለምሳሌ፡- ወንድ ከ45 ሴት ከ55 ዓመት በላይ ሲሆናቸው ለልብ ህመም ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን) እንዲሁም ወንዶ ከሴቶች በይበልጥ ለልብ ህመም ተጋላጭ የመሆናቸው አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም የልብ ህመም ምልክቶች የደረት ውጋት በግራ በኩል ወይም መሐል ላይ፣ ከወትሮው የተለየ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት መኖር፣ የሰውነት በተለይም እግር አካባቢ እብጠት፣ ራስን መሳት እና ሳል የልብና ተያያዥ ህመም ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ አብራርተዋል። የልብን ጤናን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ጤናማ አመጋገብን መከተል እንደሚገባ የሚመክሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ አትክልት ማዘውተር፣ ምግብ ሲዘጋጅም ፈሳሽ ዘይት መጠቀም፣ ስኳር፣ ጨው እና ጣፋጭ ነገሮችን መገደብ ከተቻለም ማስወገድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህም ብስክሌት መንዳት፣ በእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ዋና መዋኘት፣ እስከሚያልብ እና የልብ ምት እስከሚጨምር ብሎም እስከሚደክሙ የአካል ብቃት መሥራት የልብን ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽዖ አለው ነው ያሉት፡፡ ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ “ቦዲ ማስ ኢንዴክስ (ቢ ኤም አይ)” ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 እንዲሆን ይመከራል ብለዋል፡፡ ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠቀም፣ የስኳር ህመምና ከፍተኛ ደም ግፊት ካለም የመድኃኒት አወሳሰድን አለማስተጓጎል፣ አመጋገብ ላይ ስብ አለማብዛትና አብዝቶ አለመቀመጥ የልብ ህመምን ለመከላከል እንደሚያግዙ ነው ያስረዱት፡፡ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች የሆኑ ጤናማ ሰዎች ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ባሉ ጊዜያት አንድ ጊዜ፣ ዕድሜያቸው ከ45 በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም የልብ ህመም ያለባቸው እንደሁኔታው በየጊዜው ክትትል እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከልብ ህመም እንዲጠብቁ መክረው፤ ከዚህ ያለፈ ችግር ሲኖር ቶሎ የሕክምና ክትትል ማድረግ እና “ዛሬ ነገ” በማለት ጊዜ እያባከኑ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማይገባቸው አሳስበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ጤና #የልብ_ህመም
ባሳለፍነው ሳምንት …
Jun 7, 2026 3205
ባሳለፍነው ሳምንት … ከግንቦት 23 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ባሳለፍነው ሳምንት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለመራጮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምርጫው ወቅት ድምጽ ስለሰጡ መራጮች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል ብለዋል። ማገልገል መታደል መሆኑን ገልጸው፤ ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይህንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ ሲሉም አስገንዝበዋል። ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 22 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን ይሸፍናል። ይህ ፕሮጀክት የማይቆራረጥ የልማት ሥራችን ኅያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሀገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት ከያዘው የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል። ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፤ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን ሲሉም አመላክተዋል። የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳን የያዘ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ እንዲሁም ከእንጦጦ እስከ ቀበና ባለው መስመር የሚከናወነው መጠነ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽንም፤ ከወንዞቹ ባሻገር እስከ 50 ሜትር የሚዘልቅ መሆኑን አስረድተዋል። የአረንጓዴ ኮሪደሮችን፣ የሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን እና የንግድ ቦታዎችን ልማት ማካተቱን ጠቅሰው፤ ከተማዋን በእጅጉ የቀየረ ነው ብለዋል። የወንዝ ዳርቻዎችን ገጽታ እና አገልግሎት ከማሻሻል ባለፈ በኮንስትራክሽን፣ በኢንጂነሪንግ፣ በመልክዓ-ምድር ውበት ግንባታ፣ በሎጂስቲክስ እና በተያያዙ ዘርፎች ለብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም አብራርተዋል። አብዛኛው ሥራ በሀገር ውስጥ መሐንዲሶች መቀረጹና መተግበሩ፤ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በከተማ ልማት እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላቸው ዐቅም እያደገ መምጣቱን ያሳያል ነው ያሉት። ቀደም ሲል መርዛማ ኬሚካሎች እና ቆሻሻዎች የሚጣሉባቸው፣ በወንዝ ዳርቻዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች ላይ የጎርፍ አደጋ ይጋርጡ የነበሩት እነዚህ አካባቢዎች፤ አሁን ላይ ወደ አረንጓዴ፣ ጤናማ እና ለሕይወት ምቹ ወደሆነ የከተማ ቦታነት እየተቀየሩ መሆኑንም ገልጸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታም፤ የንግድ እና የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ተቀናጅተው መገንባታቸው፤ የአካባቢ ጥበቃ እና የኢኮኖሚ ዕድገት ከዚህ ቀደም ከነበረው ያልተናበበ ሥራ ተላቀው በጥናትና በጋራ ግብ ተባብሮ መሥራት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ስለመሆኑ አመላክተዋል። ይህ ፈጣን የልማት ሥራ አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ ይበልጥ የተሳሰረች፣ በኢኮኖሚ ንቁ እና ሰውን ማዕከል ያደረገች ከተማ የማድረግ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ ላይ መሰረት የተጣለበት የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 14832
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 8177
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 13946
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 12401
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም --
Jun 5, 2026 8632
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 7077
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !