ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና 6 ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 4 /2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው የአለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና 6 ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቀቃላች።

ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በተደረጉ የመጨረሻው ዕለት መርሃግብር በሁለቱም ፆታ በ1500 ሜትር ርቀት የተሳተፈችው ኢትዮጵያ ሜዳልያ ውስጥ መግባት አልቻለችም።

በሴቶች ኤልሳቤት አማረ 4ኛ ፣ ሀረገወይን ካላዩ 9ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።በወንዶች ደስታው ታዴ 12ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 2 ወርቅ ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ አሳክታለች። ከሁለት ዓመት በፊት በፔሩ ሊማ በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ኢትዮጵያ 6 የወርቅ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ሜዳልያ በማግኘት ማጠናቀቋ ይታወሳል።

የዘንድሮውን ውድድር አዘጋጇ አሜሪካ 24 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ በበላይነት አጠናቃለች።

ኬንያ በ11 ሜዳልያ 2ኛ ሆናለች ፤ ኢትዮጵያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም