ቀጥታ፡

በሃገራዊ ምክክሩ ባለ 500 ተመካካሪ ቡድኖች የቀረቡላቸውን ሃሳቦች እያዳበሩ ይገኛሉ - መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ) ፦  በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ባለ 500 ተመካካሪ ቡድኖች 250 አባላት ባሏቸው ስልታዊ ቡድኖች የቀረቡላቸውን ሃሳቦች እያዳበሩ እንደሚገኙ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን አሁናዊ ሂደት አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከነሃሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከስምንቱም ቡድኖች በተመረጡ 30 አባላት ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን ተቀናጅተው 500 አባላት ላሏቸው 8 የስራ ቡድኖች መቅረብ መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

ይህ የምክክር ደረጃ 500 ተመካካሪዎች በሚወያዩበት አጀንዳ ላይ የመጨረሻ ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ ጥልቅ ውይይት የሚያደርጉበት መሆኑንም ገልጸዋል።

በእነዚህ የተጠናቀሩ የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ የመወያየቱ ሂደት እስከ ዛሬ ድረስ የቀጠለ መሆኑን ገልጸው 500 አባላት ላሏቸው 8 የስራ ቡድኖች የቀረቡ ሃሳቦችን እያደበሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በስልታዊ ቡድኖቹ የቀረቡላቸውን አጀንዳዎች አዳብረው የጨረሱ እንዳሉ ሁሉ ያላጠናቀቁ ቡድኖችም በሚጨርሱበት ጊዜ ቀጣዩ ቡድን እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም