የአፋር ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአፋር ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ
ሰመራ፤ ነሀሴ 4/2018(ኢዜአ) ፦የአፋር ክልል ምከር ቤት ሲያካሒድ የቆየው 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቋል።
የተሾሙት ዶኞች በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሙሳ አብዶ አቅራቢነት ሲሆን ከተሾሙት ውስጥ አምስቱ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት፣አንዱ ደግሞ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጡ እንደሚሆኑም ገልፀዋል።
ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ከህዝብና ከመንግሰት የተሰጣቸውን ኃላፊነትና አደራና ለመወጣት ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።
ምክር ቤቱ በዚሁ ቀን ውሎው ከዳኞች ሹመት በተጨማሪ ለምክር ቤቱ አባላት የዕውቅና የምሰክር ወረቀት መስጠቱም ተጠቅሷል።