ቀጥታ፡

በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ) ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት 5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ ያዘጋጀው የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ተመራቂ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም በሰጠችው አስተያየት ፕሮግራሚንግን ለማወቅ የግድ የኮምፒውተር ሳይንስ ወይም ልዩ የትምህርት ዘርፍ አያስፈልግም ብላለች።

ሰዎች በእጃቸው ያሉትን የኢንተርኔት እና የቴክኖሎጂ መረጃዎች በመጠቀም እንዲሁም የአካባቢያቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመተንተን ተግባራዊ መፍትሔ ማምጣት እንደሚችሉ አብራርታለች።

በአሁኑ ወቅት ዲጂታል የትምህርት ቁሳቁሶች እና የመማሪያ አማራጮች በቀላሉ በእጃችን እንደሚገኙ ያነሳችው ማኅሌት፤ ወጣቶች ለዲጂታል ክህሎት ተነሳሽነትንና ጥረትን በማድረግ አበይት ችግሮችን መፍታት እንደሚችሉ ጠቁማለች።

ለዚህም ወጣቶች ዘወትር እውቀታቸውን ማደስ፣ አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ እንዲሁም ራሳቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ማብቃት እንደሚኖርባቸው ገልጻለች።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለመመዝገብ፦ ethiocoders.et

#PMOEthiopia #DigitalEthiopia2030 #5MillionEthiopianCoders

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም