ቀጥታ፡

የአፋር ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ

ሰመራ፣ነሀሴ 4/2018(ኢዜአ)፦የአፋር ክልል ምክር ቤት ሲያካሒድ የቆየው 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

ምክር ቤቱ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሒድ የቆየው ጉባኤን የስድስት ዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቋል።

የተሾሙት ዳኞች በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሙሳ አብዶ አቅራቢነት ሲሆን ከተሾሙት ውስጥ አምስቱ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት፣አንዱ ደግሞ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጡ እንደሚሆን ገልፀዋል።

የተሾሙት ዳኞች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ከህዝብና ከመንግሰት የተሰጣቸውን ኀላፊነትና አደራና ለመወጣት ቃለ መሐላቸውን ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም