ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ወጣቶች የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ ውጤታማ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል
Nov 10, 2025 16
አዲስ አበባ፤ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፦ወጣቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ ውጤታማ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለፁ። ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚካሔደው 10ኛው አገር አቀፍ የወጣቶች የፈጠራ ስራ ውድድር የማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሒዷል። የውድድር መረሃ ግብሩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ እንደገለጹት፤ መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያ በሚል መርህ ለሳይንስ፣ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። በተለይም የቴክኖሎጂ ዘርፉ በአገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጉላት በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማሻሻል የሚያስችሉ የፖሊሲና የሪፎርም ስራዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአጋር አካላት ጋር በትብብር የሚዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር አንዱ ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ አብራርተዋል። በዚህ ውድድር የሚወጡ የፈጠራ ስራዎች ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸው እውቀትና አቅም ከፍ እያለ መምጣቱን በተግባር የሚያሳይ ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው ገልፀዋል። ወጣቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልሉ የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ የሚኖረውን ተወዳዳሪነት ከፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት አራት ዓመታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Nov 10, 2025 32
አዲስ አበባ፤ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፦ባለፉት አራት ዓመታት በውጭ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ዜጎች ከህገ ወጥ ጉዞ ራሳቸውን እንዲጠብቁም አሳስቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በተለያዩ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክቷል። ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፥ በፖሊሲው አማካኝነት በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎቻችን መብት የማስከበር፣ ለዜጎች ተገቢ የቆንስላ አገልግሎት የመስጠት፣በሄዱበት ሀገር ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውና የሀገሩ መንግሥት ዜጎቻችን ሀገራቸውን እንዲለቁ ሲወስን መብታቸው፣ ክብራቸውና ደህንታቸው ተጠብቆ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በዚህም መሠረት ባለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ የመካከለኛ ምስራቅ፣የአፍሪካ እና እንደ ማይናማር ያሉ የእስያ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ጠቁሟል። ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺህ በላይ ዜጎቻችን መመለስ መቻሉንና በአሁኑ ወቅትም በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የመመለሱ ሥራ መቀጠሉን በመግለጫቸው ላይ ተመላክቷል። በተመሳሳይ በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 36 ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን ሌሎችንም አስፈላጊውን የሰነድ ማጣራት በማድረግ የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከዓለም ዓቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በማይናማር፣ላኦስ እና ካምቦዲያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችን የመመለስ ጥረት መቀጠሉንም እንዲሁ። ሆኖም ግን አሁንም ድረስ ዜጎች በተሳሳተ መረጃ በሕገ-ወጥ ደላሎች ተታለው ወደ ተለያዩ ሀገራት በመጓዝ ለእስራት እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑንና መንግሥት ዜጎች ከህገወጥ ጉዞ ራሳቸውን እንዲከላከሉ እና እንዲጠነቀቁ ነው ሚኒስቴሩ ያሳሰበው። ወደ ውጭ ሃገራት የሚደረጉ ጉዞዎችና የስራ ቅጥሮች በህጋዊና መንግስት ባስቀመጠው አሰራር ብቻ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝቧል።
በሐረሪ ክልል የህዝቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይከናወናሉ-ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
Nov 10, 2025 37
ሐረር፤ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በተከናወኑ የልማት፣የሰላም ግንባታና ሌሎች ስራዎችና በቀጣይ ወራት የተያዙትን እቅዶች የገመገመ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩም በክልሉ ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ የልማት፣የሰላም ግንባታ፣ህግ የማስከበር፣ የኮሪደር ልማት፣የመንገድ ግንባታና ሌሎች የህዝቡን ተጠቃሚነትና የክልሉን የብልጽግና ጉዞ የሚያጎለብቱ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት፥ በክልሉ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። በተለይም በክልሉ ባለፉት ጊዜያት ለማከናወን የታቀዱ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም ቢያሳዩም በአንዳንድ ስራዎች ላይ ግን ክፍተት መታየቱን አንስተዋል። ለዚህም የአመራሩ ቁርጠኝነት ማነስና ቅንጅታዊ አሰራርን አለማዳበር መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመው፥ ይህንንም በቀጣይ በመፈጸም የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግና የብልጽግናን ጎዞ ማሳለጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም በቀጣይ አመራሩ የኑሮ ውድነትን የመቀነስ፤ ሌብነት፣ መንደርተኝነት፣ ጽንፈኝነትንና ጠባቂነትን የመታገልና የመቀነስ እንዲሁም ተረጂነትን፣ ኮንትሮባንድና የጸረ ሰላም ሃይሎችን እኩይ ተግባራትን ዜሮ ማድረስ ይገባል ብለዋል። የበጋ ወራት የልማት ስራዎችና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ደግሞ ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አንስተው፤ የኮደርስ ስልጠናና የፋይዳ መታወቂያን ለዜጎች የማዳረስ ስራዎችንም በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። የምርት ማከማቻ፣ የቱሪስት መዳረሻ፣ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ እና የሽያጭ ማዕከላት ግንባታም ጊዜ ሳይሰጣቸው መከናወን የሚገባቸው መሆኑን አንስተዋል። እንዲሁም አዳዲስ የሚከናወኑ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስፋት፣ በከተማና በገጠር የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ማጠናቀቅ እና አዳዲስ የሚገነቡትንም በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት ሌላው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አንስተዋል። አመራሩ የተቀመጡትን የልማት አቅጣጫዎች ፍጥነት በማስቀጠልና ፈጠራን በማከል በተገቢው ጊዜና በጥራት ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ እንዲሁም የወረዳ አመራር አካላት ተገኝተዋል።
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ከባህል ማስተዋወቅ ባሻገር ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ያጠናክራል
Nov 10, 2025 40
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሀገሪቱ የሚገኙ የብዝኃ ባህልና ቋንቋን ከማስተዋወቅ ባለፈ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት መድረክ መሆኑን የኢፌዴሪ የህገ-መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ገለጸ፡፡ የዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት በሆሳዕና ከተማ ይከበራል ፡፡ ኢትዮጵያ የብዝኃ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክና እምነቶች መገኛ ሀገር ናት። ብዝኃ ማንነት፣ ባህል፣ ታሪክና እምነት ያላቸው ብሔረሰቦች ተዋድደውና ተቻችለው በፍቅር የሚኖሩባት የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌትም ናት። የኢፌዴሪ የህገ-መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኃይለየሱስ ታዬ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በየዓመቱ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሀገሪቱ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የአንድነታቸው የቃል ኪዳን ሰነድ ህገ-መንግስት የፀደቀበት ቀን መሆኑን ተናግረዋል። ዕለቱም በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያቀርቡበት፣ የሚተዋወቁበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ምቹ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡ ይህም እንደ ሀገር ያለው ብዝኃ ባህልና ቋንቋ ሀብት ከማስተዋወቅም ባለፈ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት መድረክ ነው ብለዋል። በህገ-መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና አሰልጣኝ አቶ ተስፋዬ መገርሳ በበኩላቸው፣ ህዳር 29 በሀገሪቱ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ያላቸውን አብሮነትና አንድነት እያፀኑና እያጠናከሩ የሚሄዱበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል። ይህም ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን የጠበቀች በቀጠናውም ሆነ በዓለም ደረጃ ጠንካራና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው ብለዋል። ከለውጡ ወዲህ የበዓሉ አከባበር ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አብሮነት፣ አንድነትና ህብረ-ብሔራዊነትን የሚያጠናክሩ የጋራ ትርክቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቅሰዋል። በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታና በሌሎችም ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ያለው የሕዝብ ትብብርና ቅንጅት ኢትዮጵያዊያን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ አንድ የመሆናቸው ማሳያና መገለጫ ነው ብለዋል። ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው በዓል፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ በተመረቀበት ማግስት መሆኑ ልዩና ታሪካዊ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
በሰው ተመርተን መጥተን በራሳችን ተመልሰናል-ታካሚዎች
Nov 10, 2025 53
ደሴ ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ በደሴ ከተማ ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በተደረገላቸው ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በሰው ተመርተው መጥተው የዓይን ብርሃናቸው ተመልሶ በራሳቸው መመለስ በመቻላቸው መደሰታቸውን ታካሚዎች ገለጹ። ሆስፒታሉ ለአንድ ሳምንት በዘመቻ በሰጠው ነጻ የዓይን ቀዶ ሕክምና አንድ ሺህ 730 ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል። ታካሚዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ፤ በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በሰው ተመርተው መጥተው የዓይን ብርሃናቸው ተመልሶ በራሳቸው መመለስ በመቻላቸው ተደስተዋል። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዝቋላ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ዘነቡ ፈንታዬ፤ ሁለቱም ዓይናቸው ማየት ካቆሙ ሦስት ዓመታት እንዳለፉ አስታውሰዋል። በዚህም ማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ሲቸገሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ አሁን ባገኙት ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና የሁለቱም ዓይኖቻቸው ሙሉ ብርሃን መመለሱን አረጋግጠዋል። ከሁለት ዓመታት በላይ የዓይን ብርሃናቸውን በማጣታቸው በጨለማ ውስጥ ለመኖር ተገደው መቆየታቸውን የገለፁት ደግሞ የሰሜን ሽዋ ዞን ደብረ ሲና ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ፈንታዬ ጌታሁን ናቸው። በሆስፒታሉ በተደረገልኝ ነጻ ሕክምና የሁለቱም ዓይኖቼ ብርሃን መመለሱ በልጆቼ እየተመራሁ መጥቼ በራሴ እያየሁ እንድመለስ ማስቻሉ ደስታን ፈጥሮብኛል ብለዋል። ለተደረገላቸው ህክምና አመስግነው አገልግሎቱ በቀጣይም ሌሎች የችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች በማድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተናግረዋል። ከደቡብ ወሎ ዞን ወግዴ ወረዳ ለህክምናው የመጡት አቶ ሀብታሙ ሽፈራው በበኩላቸው በሰው እየተመራሁ መጥቼ ባገኘሁት ሕክምና የዓይን ብርሃኔ ተመልሶ ዳግም ማየት መጀመሬ የመኖር ተስፋዬን አለምልሞልኛል ብለዋል። በዚህም ዳግም የተወለዱ ያህል ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው ወደ ሆስፒታሉ ሲመጡ ሕክምናውን ለመሞከር እንጂ ብርሃናቸው ይመለሳል የሚል እምነት እንዳልነበራቸው አስረድተዋል። በሆስፒታሉ የዓይን ሕክምና ክፍል ኃላፊና የዘመቻው አስተባባሪ እንዳልክ ያረጋል በበኩላቸው ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በተሰጠው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ነጻ ሕክምና አንድ ሺህ 730 ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። የዓይን ሞራ ግርዶሽ በይበልጥ ከዕድሜ ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት ጠቁመው፤ በወቅቱ ካልታከመ ለዓይነ ስውርነት እንደሚዳርግ ገልጸዋል። ችግሩን ለማቃለል ሆስፒታሉ "ኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት" ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ሕክምናውን በዘመቻ በመስጠቱ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ያልታከሙ ወገኖችን ለማገዝ አስችሏል ብለዋል። በደሴ ከተማ የሚገኘው የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ባለፉት ዓመታት በዘመቻ ብቻ 20 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ፖለቲካ

የተሰጠንን ተልዕኮና ግዳጅ በላቀ ብቃት ለመፈፀም ተዘጋጅተናል- የምስራቅ ዕዝ ተመራቂ ወታደሮች
Nov 10, 2025 138
ጅግጅጋ፤ ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፡- የተሰጣቸውን ተልዕኮ እና ግዳጅ በላቀ ብቃት በመፈፀም የሀገር ሉዓላዊነትና የሕዝብን ደህንነት ለማስከበር ዝግጁ መሆናቸውን በመከላከያ የምሥራቅ ዕዝ ተመራቂ ወታደሮች ተናገሩ። የምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ከዕዙ የተለያዩ ኮሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የሰጣቸውን ወታደሮች ማስመረቁ ይታወሳል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት ተመራቂ ወታደሮች፤ ተልዕኳቸውንና ግዳጃቸውን በላቀ ቁርጠኝነት ለመፈፀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ከተመራቂዎቹ መካከል ወታደር ተመስገን በቀለ ለሀገሬና ለሕዝቤ ልዩ ፍቅር አለኝ፤ በዚህም በታማኝነትና በቁርጠኝነት በማገልገል የበኩሌን እወጣለሁ ሲል ገልጿል። በስልጠናው ጠንካራ አቅም ፈጥረናል ያለው ወታደር ተመስገን፤ በማንኛውም መልኩ የሚሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ስልጠናው የአካል ብቃትና የውጊያ ስልቶችን ጨምሮ የተለያዩ የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት አቅሙን ይበልጥ ያጠናከረና ግዳጆችን በብቃት መወጣት የሚያስችል መሆኑን የተናገረው ደግሞ ወታደር ካሳዬ ትዕግስቱ ነው። በተለይም የሀገሪቱንና የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚነሱ ባንዳንዎች፣ ጽንፈኞችንና ተላላኪዎችን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። ስልጠናው በአቅምና በስነ ልቦና እንዲሁም ዘመናዊ የውጊያ ስልትን በአግባቡ የቀሰምንበት ነው ያለው ደግሞ ወታደር ኦልያድ በቀለ ነው። ከአያቶቻችን የወረስነውን ጀግንነት በመላበስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ደህንነት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል የማስከበር ግዳጅና ተልዕኮን ለመወጣት ተዘጋጅቻለው ሲል ገልጿል። በማዕከሉ አሰልጣኝ ከሆኑት መካከል ምክትል መቶ አለቃ ጅሬኛ ጌታሁን በበኩላቸው፤ ወታደሮቹ በኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ማንኛውንም ትንኮሳ መመከት የሚያስችል አቅም እንደገነቡ ተናግረዋል። በማንኛውም ጊዜ እና ሁኔታ የሚሰጣቸውን ሀገራዊ ግዳጅ በላቀ ጀግንነት እና የዓላማ ፅናት ለመፈፀም ቁርጠኛ መሆናቸውንም ነው ምክትል መቶ አለቃ ጅሬኛ ያረጋገጡት። የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ ፤ ሰልጣኝ የሰራዊቱ አባላት በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለሚሰጣቸው ግዳጅ ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ የዝግጁነት ቁመና የገነቡ መሆናቸውን በምረቃው ወቅት አረጋግጠዋል። የሰራዊቱ አባላትም በማዕከሉ ያገኙትን ክህሎት በመጠቀም ሕገ መንግስታዊና ተቋማዊ ተልዕኮን በጀግንነት ታጥቀውና ሕዝባዊ ባሕሪ ተላብሰው መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዘበዋል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የፖሊስ አባላት እውቅናና የማእረግ እድገት ተሰጠ
Nov 9, 2025 183
ደብረ ማርቆስ ፤ጥቅምት 30/2018 (ኢዜአ) ፡-የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ተግባር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አባላቱ እውቅናና የማእረግ እድገት ሰጠ ። የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ተግባር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አባላቱ ዛሬ እውቅናና የማእረግ እድገት ሰጥቷል ። የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ በስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ የህዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ የላቀ አፈጻጸም ላበረከቱ የመደበኛና አድማ መከላከል ፖሊስ አባላት እውቅናና የማእረግ እድገት ተሰጥቷል ። የፖሊስ አባላቱ በተለይም ባለፉት አመታት በተከናወነ የተቀናጀ የሰላምና የጸጥታ እንዲሁም የህግ ማስከበር ተግባር የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተወካይ አቶ መኮንን ሙሉአዳም በበኩላቸው ፖሊስ በህዝብና በመንግስት የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት ባደረገው ጥረት አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል ። የከተማው ፖሊስ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ባከናወነው የጸጥታና የህግ ማከበር ተግባር በከተማውና አካባቢው አሁን ለሰፈነው ሰላም ከፍተኛ አስተዋጾ ማበርከቱን ጠቁመዋል። የተገኘው ሰላም በዘላቂነት እንዲቀጥል የትብብር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ። በከተማው ዛሬ እውቅናና የማእረግ እድገት ከተሰጣቸው የፖሊስ አባላት መካከል የከተማ አስተዳደሩ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ብሩክ ሁነኛው በበኩላቸው የተጣለባቸውን ተልእኮ ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል። የተሰጣቸው እውቅናና የማእረግ እድገት ለቀጣይ ተልእኮ የበለጠ እንደሚያነሳሳቸው አመላክተዋል ። በሀገር መከላከያ ሰራዊት የ602ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴል ጀኔራል ሶፍያ መሀመድ በስነ ስርአቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በአካባቢው የሚከናወነው የህግ ማስከበር ስራ የሀገርንና የህዝብን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ያለመ ነው። ከፖሊስና ሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም አጠናክሮ የማስቀጠል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ።
የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ በፍጥነትና በጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ አስፈላጊ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Nov 9, 2025 243
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፦ የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ በፍጥነትና በጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ አስፈላጊ ነው ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ። "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ከፌደራል፣ ከክልል፣ ከዞን እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ 11 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ላይ የማጠቃለያ ስልጠና ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማጠቃለያ ስልጠና ላይ እንደገለፁት የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ በፍጥነትና በጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። በስልጠናው የመደመር መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ፣ መንገድና መዳረሻ ግቦቹ የተዳሰሱ ሲሆን በዚህም በመደመር መንግሥት መርህ የሚመራው ፓርቲው አመራሮች በፈጠራ፣ በፍጥነትና በብዛት ስራዎችን በማከናወን የህዝባችን ሁለንተናዊ ጥያቄ ከመመለስ በላይ የሀገራችን ራዕይ ለማሳካትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚረዳ መንገድ መምራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትኩረት የሚሹ ግቦችን በየፈርጁ በመለየት አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን ፋይዳ፣ 5 ሚሊዮን ኮደሮች፣ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፣ የምርጫ ምቹነትና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አጀንዳዎች በ100 ፐርሰንት ለማሳካት መትጋት የሚገባን ግቦች ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማጠቃለያ ገለጻ እንዳብራሩት መደመር ትውልድን ወደ ብልፅግና የሚያደርስ መንገድ ነው። የመደመር መንግሥት ለሀገር ብልፅግና ባለአደራ መሆኑን ተናግረው በፈጠራና በፍጥነት ጥራትና ብዛትን እውን ማድረግ ይገባል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው እንዳብራሩት በብዝሀ ዘርፍ ትስስር ወደ ስልጣኔ ሽግግር ማምጣት ይገባል። የሀሳብ ሉዐላዊነት የብልፅግና መሰረት እንደሆነ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሁሉም የፓርቲው አመራር በዚህ አግባብ በመትጋት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለበት ብለዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ባለፉት 11 ቀናት በስልጠና በውይይትና በመስክ ጉብኝትና በማጠቃለያው ገለጻ ያገኟቸውን እውቀትና ልምዶች በዕቅድ በማካተትና ወደ ስራ በመቀየር የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ በሚደረግ ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ለብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የፓርቲው ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሰጡት የስራ መመሪያ ተጠናቀቀ
Nov 9, 2025 238
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፦ ለብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የፓርቲው ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሰጡት የስራ መመሪያ ተጠናቋል። የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ እንዳስታወቁት "በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከጥቅምት 19 እስከ 30 በአዳማ ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሰጡት የስራ መመሪያ ዛሬ በስኬት ፍፃሜውን አግኝቷል ብለዋል። ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወደ 2000 የሚጠጉ የፓርቲያችን አመራሮች የተሳተፉበትና የአስተሳሰብ አንድነት ከመፍጠርና የተግባር አፈፃፀምን ከማላቅ አኳያ እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ በተገኘበት በዚህ ስልጠና ፓርቲያችን እውነተኛ የህብረ ብሔራዊነት ተምሳሌት መሆኑም በተጨባጭ የተንፀባረቀበት ነበር ሲሉም ገልጸዋል። ይህ የስልጠና መርሀ ግብር ከዝግጅት እስከ ገለፃ፣ የቡድን ውይይት፣ ተሞክሮ ልውውጥ፣ የልማት ሥራዎች የመስክ ጉብኝት እና ማጠቃለያ ድረስ ዓላማውን በሚገባ አሳክቶ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታችሁን ለተወጣችሁ አስተባባሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ አወያዮች፣ የፀጥታ ተቋማት፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ልዩ ልዩ ተቋማቱ፣ የአዳማ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮች በሙሉ ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋፅዖ በብልፅግና ፓርቲ ስም ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል አቶ አደም ፋራህ በመልዕክታቸው።
በመደመር መንግሥት ዕይታ በዘርፎች ላይ የመጣውን እመርታዊ ለውጥ በተጨባጭ ማየት ችለናል - የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች
Nov 8, 2025 230
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፦በመደመር መንግሥት ዕይታ በዘርፎች ላይ የመጣውን እመርታዊ ለውጥ በተጨባጭ ማየት መቻላቸውን የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና የአባላቱን አቅም በሚገነቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ መሰጠቱ ይታወቃል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በሀገሪቷ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ዘርፎች በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ላይ ያጠነጠኑ ስልጠናዎችን ወስደዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ትናንት በአዳማ ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት በግብርና እና ከተማ ልማት የተከናወኑ ስራዎችን ተመልክተዋል። የሶማሌ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ፤ የብልጽግና ፓርቲ ብዝሃ ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ በርካታ ድሎችን ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል። በግብርና ኢንዱስትሪ፣ በከተሞች ልማትና በቱሪዝም ዘርፎች የተደረጉ ሪፎርሞችና የተገኙ ውጤቶች የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር መሰረት መጣላቸውንም አንስተዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ኢትዮጵያ ያላት ጸጋዎች ከራሷ አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ መሆኑን ያየንበት ነው ብለዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በነበራቸው ቆይታ በተለያዩ ዘርፎች ላይ እየተከናወኑ ስላሉ ስራዎችና ስለተገኙ ውጤቶች የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸውንም ነው የተናገሩት። የሶማሌ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር ሙስጠፌ እንዳሉት፤ በመደመር እይታ በፈጠራና በፍጥነት ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ከቀጣናው አልፋ ከዓለም አገራት ጋር ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንዳላትና ለዚህ ደግሞ አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰራ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር ጥላሁን እንደተናገሩት፤ በመደመር መንግሥት ዕይታ በዘርፎች ላይ የመጣውን እመርታዊ ለውጥ በተጨባጭ ማየት ተችሏል።
ምሩቃን የፖሊስ አባላትና መኮንኖች ለህገ መንግሥቱ ታማኝ በመሆን ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Nov 8, 2025 244
ቡልቡላ ፤ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ):- ምሩቃን የፖሊስ አባላትና መኮንኖች ለህገ መንግሥቱ ታማኝ በመሆን ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ መሰረታዊ ወታደራዊ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችንና 2ኛ ዙር እጩ መኮንኖችን ዛሬ አስመርቋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የልማት እቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡ በተለይም የፖሊስ አባላት በታማኝነትና በቅንነት ህዝባቸውን በማገልገል ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ የፖሊስ አባላት ማህበረሰቡን በስነ ምግባር በማገልገል የክልሉን ሰላምና ልማት ማጠናከር ላይ ያላቸውን ድርሻ እንዲያጠናክሩም አሳስበዋል፡፡ የዛሬ ምሩቃን የፖሊስ አባላትና መኮንኖችም ለሰንደቅ ዓላማና ለህገ መንግሥት ታማኝ በመሆን ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ በበኩላቸው ኮሚሽኑ የክልሉን ፖሊስ በሰው ኃይል በማደራጀት ለክልሉ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ምሩቃንም የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል የፖሊስ አገልግሎትን በመተግበር ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡ በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ለተልዕኮ ዝግጁ የሚያደርጉ ክህሎት በመጠቀም በታማኝነት ማህበረሰቡን ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ድሪባ መኮንን እንደገለፁት የተጀመሩ የልማት እቅዶችን እውን ለማድረግ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ለዚህም የሁለቱን አጎራባች ክልሎችን ዘላቂ ሰላም በማስጠበቅ የማህበረሰቡን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ጉዞን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። "ኮሌጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ጎሳዬ ከበደ ናቸው፡፡ ኮሌጁ ክልላዊ ትስስርን በማጠናከር ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመተባበር የፖሊስ አካላትን ሲያሰለጥን መቆየቱን አስታውሰው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያግዙ ስልጠናዎች በብቃት እንደተሰጠም ተናግረዋል፡፡

ማህበራዊ
ባለፉት አራት ዓመታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Nov 10, 2025 32
አዲስ አበባ፤ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፦ባለፉት አራት ዓመታት በውጭ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ዜጎች ከህገ ወጥ ጉዞ ራሳቸውን እንዲጠብቁም አሳስቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በተለያዩ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክቷል። ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፥ በፖሊሲው አማካኝነት በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎቻችን መብት የማስከበር፣ ለዜጎች ተገቢ የቆንስላ አገልግሎት የመስጠት፣በሄዱበት ሀገር ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውና የሀገሩ መንግሥት ዜጎቻችን ሀገራቸውን እንዲለቁ ሲወስን መብታቸው፣ ክብራቸውና ደህንታቸው ተጠብቆ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በዚህም መሠረት ባለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ የመካከለኛ ምስራቅ፣የአፍሪካ እና እንደ ማይናማር ያሉ የእስያ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ጠቁሟል። ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺህ በላይ ዜጎቻችን መመለስ መቻሉንና በአሁኑ ወቅትም በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የመመለሱ ሥራ መቀጠሉን በመግለጫቸው ላይ ተመላክቷል። በተመሳሳይ በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 36 ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን ሌሎችንም አስፈላጊውን የሰነድ ማጣራት በማድረግ የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከዓለም ዓቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በማይናማር፣ላኦስ እና ካምቦዲያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችን የመመለስ ጥረት መቀጠሉንም እንዲሁ። ሆኖም ግን አሁንም ድረስ ዜጎች በተሳሳተ መረጃ በሕገ-ወጥ ደላሎች ተታለው ወደ ተለያዩ ሀገራት በመጓዝ ለእስራት እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑንና መንግሥት ዜጎች ከህገወጥ ጉዞ ራሳቸውን እንዲከላከሉ እና እንዲጠነቀቁ ነው ሚኒስቴሩ ያሳሰበው። ወደ ውጭ ሃገራት የሚደረጉ ጉዞዎችና የስራ ቅጥሮች በህጋዊና መንግስት ባስቀመጠው አሰራር ብቻ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝቧል።
በሰው ተመርተን መጥተን በራሳችን ተመልሰናል-ታካሚዎች
Nov 10, 2025 53
ደሴ ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ በደሴ ከተማ ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በተደረገላቸው ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በሰው ተመርተው መጥተው የዓይን ብርሃናቸው ተመልሶ በራሳቸው መመለስ በመቻላቸው መደሰታቸውን ታካሚዎች ገለጹ። ሆስፒታሉ ለአንድ ሳምንት በዘመቻ በሰጠው ነጻ የዓይን ቀዶ ሕክምና አንድ ሺህ 730 ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል። ታካሚዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ፤ በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በሰው ተመርተው መጥተው የዓይን ብርሃናቸው ተመልሶ በራሳቸው መመለስ በመቻላቸው ተደስተዋል። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዝቋላ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ዘነቡ ፈንታዬ፤ ሁለቱም ዓይናቸው ማየት ካቆሙ ሦስት ዓመታት እንዳለፉ አስታውሰዋል። በዚህም ማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ሲቸገሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ አሁን ባገኙት ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና የሁለቱም ዓይኖቻቸው ሙሉ ብርሃን መመለሱን አረጋግጠዋል። ከሁለት ዓመታት በላይ የዓይን ብርሃናቸውን በማጣታቸው በጨለማ ውስጥ ለመኖር ተገደው መቆየታቸውን የገለፁት ደግሞ የሰሜን ሽዋ ዞን ደብረ ሲና ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ፈንታዬ ጌታሁን ናቸው። በሆስፒታሉ በተደረገልኝ ነጻ ሕክምና የሁለቱም ዓይኖቼ ብርሃን መመለሱ በልጆቼ እየተመራሁ መጥቼ በራሴ እያየሁ እንድመለስ ማስቻሉ ደስታን ፈጥሮብኛል ብለዋል። ለተደረገላቸው ህክምና አመስግነው አገልግሎቱ በቀጣይም ሌሎች የችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች በማድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተናግረዋል። ከደቡብ ወሎ ዞን ወግዴ ወረዳ ለህክምናው የመጡት አቶ ሀብታሙ ሽፈራው በበኩላቸው በሰው እየተመራሁ መጥቼ ባገኘሁት ሕክምና የዓይን ብርሃኔ ተመልሶ ዳግም ማየት መጀመሬ የመኖር ተስፋዬን አለምልሞልኛል ብለዋል። በዚህም ዳግም የተወለዱ ያህል ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው ወደ ሆስፒታሉ ሲመጡ ሕክምናውን ለመሞከር እንጂ ብርሃናቸው ይመለሳል የሚል እምነት እንዳልነበራቸው አስረድተዋል። በሆስፒታሉ የዓይን ሕክምና ክፍል ኃላፊና የዘመቻው አስተባባሪ እንዳልክ ያረጋል በበኩላቸው ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በተሰጠው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ነጻ ሕክምና አንድ ሺህ 730 ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። የዓይን ሞራ ግርዶሽ በይበልጥ ከዕድሜ ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት ጠቁመው፤ በወቅቱ ካልታከመ ለዓይነ ስውርነት እንደሚዳርግ ገልጸዋል። ችግሩን ለማቃለል ሆስፒታሉ "ኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት" ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ሕክምናውን በዘመቻ በመስጠቱ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ያልታከሙ ወገኖችን ለማገዝ አስችሏል ብለዋል። በደሴ ከተማ የሚገኘው የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ባለፉት ዓመታት በዘመቻ ብቻ 20 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የጤና አገልግሎትን ለማዘመን የተከናወኑ ስራዎች ውጤት እየተመዘገበባቸው ነው - ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ
Nov 10, 2025 112
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ የዜጎችን ጤና አገልግሎት ለማዘመን የተከናወኑ ስራዎች ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑን የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ። የጤና ሚኒስቴር የመድሀኒት አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳለጥ "ጤንነቴ" የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ አስመርቋል። በተጨማሪም "ለበጎ" የተሰኘ የአምቡላንስ ስምሪት ስርዓትና 952 የጤና መረጃ እና ምክር አገልግሎት ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከልን ስራ አስጀምሯል። ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ በዚሁ ወቅት፤ በሽታን ከመከላከል ባለፈ አክሞ ማዳን ላይ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል። የዜጎችን የጤና አገልግሎት ለማዘመን የተከናወኑ ስራዎች ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑን ጠቁመው፤ በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረጉት መተግበሪያዎችም ዜጎች ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በራስ አቅም የበለጸጉት እነዚህ መተግበሪያዎች የጤና ስርዓቱን በጉልህ የሚያግዙ መሆናቸውን አንስተው፤ በጤና ስርዓቱ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፤ የጤናውን ዘርፍ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስቴሩ የዜጎችን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ እየሰራ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ዕለት ወደ ስራ የገቡት መተግበሪያዎች የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል። "ጤንነቴ" የተሰኘው መተግበሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ህብረተሰቡ መድሀኒቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የለማ መሆኑን ተናግረዋል። "ለበጎ" የተሰኘው የአምቡላንስ ስምሪት ስርዓት እና 952 ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል ለድንገተኛ የጤና አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም አንስተዋል። በዛሬው እለት የተመረቁት መተግበሪያዎች በአጠቃላይ የጤናውን ስርዓት የሚያሻግሩ መሆናቸውን በመጠቆም። በመርሀ ግብሩ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴን ጨምሮ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ ቢልለኔ ስዩም እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ቀኑ ወንድማማችነትንና ብዝኀነትን በሚያጠናክር መልክ ይከበራል
Nov 10, 2025 103
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 1/2018(ኢዜአ)፡- የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ወንድማማችነትና ብዝኀነትን በይበልጥ በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ምክር ቤቱ አስታወቀ። 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት ይከበራል። የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተሾመ ለምጃቦ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ቀኑ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንደሚከበርና በክልል ደረጃ በሳጃ ከተማ ሕዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ይኖራል ብለዋል። በዚህም መሠረት ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በሕገ-መንግሥትና የፌደራሊዝም አስተምኅሮ ሥርፀት ላይ በየደረጃው ሥልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። በተጨማሪም የደም ልገሳ፣ ዐቅመ ደካሞችን ማገዝና ለዐቅመ ደካማ ወላጆች ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብን ጨምሮ ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችም እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ በወልቂጤ ከተማ ባዛርና ሲምፖዚየም እንደሚካሄድ ጠቁመው፤ ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሆሳዕና ከተማ እንደሚከበር ገልጸዋል። በዓሉን ለሚታደሙ እንግዶች ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑንም አስታውቀዋል። ቀኑ ወንድማማችነትን እና ብዝኀነትን በይበልጥ የምናጎለብትበት ነው ብለዋል። የቀኑ መከበር የአካባቢውን ቱሪዝም፣ ባህል እንዲሁም ልማት ለማስተዋወቅና የልማት ሥራዎችን በይበልጥ ለማከናወን ከፍተኛ መነሳሳት መፍጠሩንም አንስተዋል።
ኢኮኖሚ
በጉጂ ዞን 520 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል የመስኖ ግድቦች ግንባታ እየተካሄደ ነው
Nov 10, 2025 59
አዶላ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን 520 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል የመስኖ ግድቦች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ መስኖና አርብቶ አደር ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ በኦሮሚያ ክልል በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች በድርቅ እና ተያያዥ ምክንያቶች የሚጋጥሙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቋቋም አነስተኛ እና መለስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው። ግንባታ ከሚከናወንባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የጎጂ ዞን ሲሆን በዞኑ ባለፉት ዓመታት የተለያየ ጥቅም የሚሰጡ የመስኖ ግድቦች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ወቅት 520 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ መስኖ ግድቦች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ መስኖና አርብቶ አደር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ ገዳ ሸንዶ (ዶ/ር)፤ የግድቦቹ ግንባታ በዞኑ ቆላማ ወረዳዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከጉጂ ዞን 13 ወረዳዎች አምስቱ ቆላማ እና በተደጋጋሚ ጊዜ በድርቅ የሚጠቁ ዝናብ አጠርና በብዛት የእንስሳት እርባታ የሚካሄድባቸው ናቸው ብለዋል። የመስኖ ግድቦቹ ግንባታ እየተከናወነ የሚገኘው ቦሬ፣ ዋደራ፣ ሰባቦሩና ግርጃ ዝናብ አጠር ወረዳዎች መሆኑን አንስተዋል። የመስኖ ግድቦቹ ሲጠናቀቁ ከ520 ሄክታር በላይ መሬት በዘመናዊ መስኖ የማልማት አቅም ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ግንባታቸውም በአማካይ ከ50 እስከ 92 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። ግድቦቹ ከመስኖ ልማት ባሻገር የቤት እንስሳትንም የመጠጥ ውሀ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። የክልሉ መንግስት ለመስኖ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከ457 ሚሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ በጀት መመደቡን አስታውቀው የመስኖ ፕሮጀክቶቹን የግንባታ ስራ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጀት አመቱ ጥራቱን የጠበቀ 80 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማእከላዊ ገበያ ይቀርባል
Nov 10, 2025 62
ጊምቢ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጀት አመቱ ጥራቱን የጠበቀ 80 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማእከላዊ ገበያ እንደሚቀርብ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በምእራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ቡናና ሻይ ልማት ቡድን መሪ አቶ ኤፍሬም መስፍን ለኢዜአ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ የቡና ምርት ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው። የቡና ምርቱ ከህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ እንደሚሰበሰብ ጠቅሰው አርሶ አደሩ የደረሰ ቀይ የቡና ፍሬ ብቻ በመልቀም ጥራቱን ለመጠበቅ እንዲቻል ለአምራቾቹ የባለሙያ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም በተያዘው በጀት አመት በዞኑ በቡና ተክል ከተሸፈነው 600 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተሻለ የቡና ምርት ይሰበሰባል ብለዋል። ከሚሰበሰበው የቡና ምርትም ከ80 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማእከላዊ ገበያ የሚቀርብ መሆኑን ገልጸዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን በላሎ አሳቢ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ጌታሁን ከበደ፣ በወረዳው ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለመሰብሰብ ለአርሶ አደሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የወረዳው ቡና አምራች አርሶ አደሮች በምርት ዘመኑ ከህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ቀይ ቡና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለመሰብሰብ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዘግጅት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከወረዳው ቡና አምራች አርሶ አደሮች መካከል ጌታሁን ጉታታ፣ በየዓመቱ ከ15 እስከ 25 ኩንታል የቡና ምርት እንደሚያገኙ ጠቅሰው ዘንድሮም የነበረው የአየር ሁኔታ ለቡና ምርት አመቺ በመሆኑ ከ20 ኩንታል በላይ የቡና ምርት እንደሚጠብቁ አመልክተዋል። አርሶ አደር ገመቹ መላኩ በበኩላቸው ዘንድሮ የደረሰ የቡና ምርት ጥራቱን ለመጠበቅ ከግብርና ባለሙያዎች ስልጠና ማገኘታቸውን አንስተዋል። ከ15 ኩንታል በላይ የቡና ምርት እንደሚያገኙ ጠቅሰው ዘንድሮም የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ከማዕከሉ የምናገኛቸው የሰብል ዝርያዎች ድርቅና ተባይን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጡ ናቸው-የባምባሲ ወረዳ አርሶ አደሮች
Nov 10, 2025 120
አሶሳ፤፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ከአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የሚያገኟቸው የሰብል ዝርያዎች ድርቅና ተባይን በመቋቋም የተሻለ ምርት እንደሚሰጡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባምባሲ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ። ማዕከሉ በምርምር አውጥቶ በአርሶ አደሮች ማሳ ለማስተዋወቅ ያለማው "BH-520" (ናዳ) የተሰኘ የበቆሎ ዝርያ በአርሶ አደሮችና በግብርና ባለሙያዎች ተጎብኝቷል። በመስክ ምልከታው ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት፤ የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በየጊዜው የሚያመጣቸው የሰብል ዝርያዎች ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል በባምባሲ ወረዳ መንደር 47 ቀበሌ ነዋሪ አርሶአደር ሀይሉ በየነ እና የሺብር ዘገዬ በቀበሌያቸው እየለማ የሚገኘው አዲስ የበቆሎ ዝርያ ዝናብ እና ተባይን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። ማዕከሉ አርሶ አደሩ ምርታማ እንዲሆን በየጊዜው ከሚያፈልቃቸው ምርጥ ዘሮች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን አስታውሰዋል። የአሁኑ የመስክ ጉብኝትም ማዕከሉ ምርታማነታቸውን በመጨመር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰራ ላለው ስራ ልምድ ለመቅሰም እንደሚያግዝ ተናግረዋል። በመስክ ምልከታቸው ያዩት የበቆሎ ዝርያ በጥሩ ቁመና ላይ መገኘቱ የተሻለ ዝርያ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑንም ተናግረዋል። አርሶ አደር መሳይ አበባው በበኩላቸው፤ የምርምር ማዕከሉ በትንሽ ማሳ ላይ ብዙ ምርት መስጠት የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችን በማፍለቅ ማስተዋወቁን ጠቁመዋል። ከዚህ በፊትም ማዕከሉ ያወጣቸውን አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በመጠቀም በግብርና ሥራቸው ላይ ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን አክለዋል። በአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የግብርና ኤክስቴንሽን ተመራማሪና የዘርፉ አስተባባሪ ፍቃዱ ቤኛ ማዕከሉ ለአካባቢው ስነምህዳር ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ የምርምር ስራዎችን በማፍለቅ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። ከበቆሎ በተጨማሪ በሰሊጥ፣ ቦለቄ እና ማሽላ ላይ በስፋት የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ የምርምር ውጤቱን በማስፋት አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ ነው ብለዋል። በወረዳው መንደር 48 ቀበሌ በምርምር ያወጣውና በሄክታር 95 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችል "BH-520" (ናዳ) ዝርያም የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል። የምርምር ማዕከሉ የሚያወጣቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የዘር ብዜት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ፍቅሩ አቡን ናቸው። አርሶ አደሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ተጠቅሞ በኩታ ገጠም እርሻ ልማት ውጤታማ የግብርና ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ለበጋ መስኖ ስንዴ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት በስፋት እየተከናወነ ነው-ግብርና ሚኒስቴር
Nov 10, 2025 102
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 1/2018(ኢዜአ)፡- ለ2018 በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የአርሶ አደሩን የስራ ባህል በመቀየር በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ እየተመረተ ይገኛል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለስንዴ ምርት ልዩ ትኩረት በመስጠት የበጋ መስኖን ጨምሮ የስንዴ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በዚህም የስንዴ ልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተሳካ ውጤት እየተገኘበት ነው። በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ኢሳያስ ለማ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በ2018 የበጋ መስኖ ስንዴ 4 ነጥብ 29 ሚሊየን ሄክታር መሬት በማረስ 175 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው። በዚህ ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ ባለፈው ዓመት ከነበረው የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር ብልጫ እንዳለውም ገልጸዋል። በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ እስከ አሁን ከ767 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ከ359 ሺህ ሄከታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ጠቁመዋል። በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ በበጋ መስኖ ስንዴ የተገኘውን ልምድ የበለጠ በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም የአፈር ማዳበሪያ፣የምርጥ ዘርና እና የውሃ ፓምፕ አቅርቦት ተደራሽ መደረጉን ገልጸዋል። ከመኸር ምርት የተረፈ እና ለመስኖ የተዘጋጀ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች መከፋፈሉንም ተናግረዋል። የስንዴ ምርጥ ዘርም በበቂ ሁኔታ ለበጋ መስኖ ስንዴ ተደራሽ መደረጉን ገልጸዋል። የበጋ መስኖ ስንዴ ከዓመት ወደ ዓመት ትልቅ እመርታ እያስመዘገበ መምጣቱንም ተናግረዋል። የስንዴ ምርት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ መላክ መጀመሩን አስታውሰው፤ ስንዴ በምግብ ራስን ከመቻል ጋር እንደ ሀገር የተጀመረው ስኬት ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ የተያዘው ግብ እንዲሳካ የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትላቸውን እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ወጣቶች የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ ውጤታማ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል
Nov 10, 2025 16
አዲስ አበባ፤ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፦ወጣቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ ውጤታማ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለፁ። ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚካሔደው 10ኛው አገር አቀፍ የወጣቶች የፈጠራ ስራ ውድድር የማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሒዷል። የውድድር መረሃ ግብሩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ እንደገለጹት፤ መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያ በሚል መርህ ለሳይንስ፣ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። በተለይም የቴክኖሎጂ ዘርፉ በአገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጉላት በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማሻሻል የሚያስችሉ የፖሊሲና የሪፎርም ስራዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአጋር አካላት ጋር በትብብር የሚዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር አንዱ ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ አብራርተዋል። በዚህ ውድድር የሚወጡ የፈጠራ ስራዎች ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸው እውቀትና አቅም ከፍ እያለ መምጣቱን በተግባር የሚያሳይ ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው ገልፀዋል። ወጣቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልሉ የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ የሚኖረውን ተወዳዳሪነት ከፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ማዕከሉ ለአርሶ አደሩ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ ነው
Nov 9, 2025 241
አሶሳ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፦ የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ለአርሶ አደሩ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የምርምር ማዕከሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ በምርምር ያወጣውን "BH520"(ናዳ) የተሰኘ የበቆሎ ዝርያ የመስክ ምልከታ አካሂዷል። የምርምር ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ደስታ በቀለ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ማዕከሉ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ ውጤታማ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በማሽላ፣ በቆሎ፣ አኩሪ አተር እና ሌሎች ሰብሎች ያወጣቸው አዳዲስ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም ገልጸዋል። በባምባሲ ወረዳ አራት ሄክታር ማሳ ላይ እየለማ የሚገኘው "BH520"(ናዳ) የበቆሎ ዝርያ በሄክታር እስከ 95 ኩንታል ምርት የሚሰጥና አረምና ተባይን የመቋቋም አቅም ያለው ነው ብለዋል። በተጨማሪም አዲስ የተለቀቀው የበቆሎ ዝርያ ድርቅን መቋቋም የሚችል፣ በአጭር ጊዜ የሚደርስና ምርታማነቱ የተረጋገጠ የምርምር ውጤት እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። የባምባሲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አብዱልዋሂድ አዙቤር በበኩላቸው፤ የምርምር ማዕከሉ በየጊዜው የሚያወጣቸው አዳዲስ ዝርያዎች አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ከማድረግ በተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕገዛ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። አርሶ አደሩ ማዕከሉ የሚያወጣቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመተግበር ውጤታማ የግብርና ስራ ማከናወን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። በወረዳው መንደር 48 ቀበሌ እየለማ የሚገኘው አዲሱ የበቆሎ ዝርያ የሁሉንም አርሶ አደሮች ትኩረት የሳበ እና በግብርና ስራ ላይ የአርሶ አደሩን ተነሳሽነት የጨመረ ነው ያሉት ደግሞ የባምባሲ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጃፈር አኑር ናቸው። በመስክ ምልክታው የክልል፣ የዞና እና የወረዳ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የአካባቢው አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከል በመሆን የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ተግባራትን እያከናወነ ነው
Nov 8, 2025 161
ጅግጅጋ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፡-ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ የምርምር ማዕከል በመሆን የትውልድና ሀገር ግንባታን የሚደግፉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዲ አህመድ ሀሰን (ዶ/ር)፤ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእውቀት እና የምርምር ማዕከል በመሆን ለትውልድና ሀገር ግንባታ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋሙ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ የክልሉን ብሎም የሀገርን እድገት መደገፍ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም በግብርና፣ ስነ- ህይወት፣ ምህንድስና፣ ፊዚክስ እና ሌሎችም ላይ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማሳተም የእውቀትና የምርምር ማዕከል የመሆን ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል። በማሕበረሰብ አገልግሎቱ በተለይም የትምህርት፣የጤና እና የሕግ አገልግሎቶች እንዲሁም የአቅም ግንባታ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አንስተው፤ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አሁን ላይ በጅግጅጋ እና በሼኽ ሀሰን የበሬ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ካምፓሶቹ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኘ ያነሱት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ ሶስተኛውን ካምፓሱን በጎዴ ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት በቴክኖሎጂ ተደግፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ኤጀንሲው
Nov 8, 2025 143
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018(ኢዜአ)፡- ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት በአዳዲስ ቴክኖሎጂ ተደግፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ። በኤጀንሲው የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አስናቀች ሙህዬ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ተቋሙ የተሟላ ሪፎርም ካደረገባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ የቴክኖሎጂ አሠራርን ማስፋት ነው። በዚህም መሠረት አገልግሎት የሚሰጠው በሲስተም መሆኑን ጠቅሰው ይህም ከማዕከል ሆኖ ወረዳ ላይ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ማየት የሚያስችል ነው ብለዋል። አሁን አገልግሎት እየሠጡ ካሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የተሻለ እየበለፀገ መሆኑን ጠቁመው፤ በቅርቡ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሠራሮች ውጤት እያስገኙ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፤ በቀጣይም እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች በአዳዲስ ቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ከብልሹ አሠራር ጋር በተያያዘ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በ17 ባለሙያ እና አንድ ባለጉዳይ ላይ የተለያየ ርምጃ መወሰዱንና በሕግ ሂደት ላይ የሚገኝ እንዳለም ጠቅሰዋል። ከ2015 እስከ 2017 በጀት ዓመት በሐሰተኛ መረጃ ለመገልገል በሞከሩ 188 ተገልጋዮችና በአሠራር ጥሰት ደግሞ 589 ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። ብልሹ አሠራርን በመከላከልና መቆጣጠር ሂደት የቴክኖሎጂ ሚና የጎላ መሆኑን ጠቁመው፤ ለአብነትም ድርጊቱ በየዓመቱ እየቀነሰ እንዲሄድ ማስቻሉን ተናግረዋል። ተገልጋዮች ትክክለኛ መረጃና ማስረጃ አቅርበው አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስገንዝበው፤ ሕገ ወጥ አሠራር ሲያጋጥማቸው በ7533 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።
ስፖርት
በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
Nov 10, 2025 78
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ፣ ዠርሚ ዶኩ እና ኒኮ ጎንዛሌዝ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። አርሊግ ሃላንድ በጨዋታው ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት አምክኗል። ሲቲ በጨዋታው ከተጋጣሚው በተሻለ ለግብ የቀረቡ እድሎችን ፈጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በሊጉ ሰባተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ22 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ ብሏል። በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ወርዷል። አርሊንግ ሃላንድ በሊጉ ያስቆጠረችውን ጎሎች ብዛት ወደ 12 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን አጠናክሯል። በተያያዘም ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች አስቶንቪላ ቦርንማውዝን 4 ለ 0 ሲረታ ብሬንትፎርድ ኒውካስትል ዩናይትድን ኖቲንግሃም ፎረስት ሊድስ ዩናይትድን በተመሳሳይ 3 ለ 1 አሸንፈዋል። ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዓለም አቀፍ የብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ መልስ ከሁለት ሳምንት በኋላ በ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይመለሳል።
መቻል እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርተዋል
Nov 9, 2025 98
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል እና ፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተደርጓል። ሁለቱ ቡድኖች በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና የመረከብ እድላቸውን ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። በሌላ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ያሬድ ብሩክ ለሃዋሳ ከተማ፣ አዲስ ግደይ ለንግድ ባንክ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና እና ሸገር ከተማ በተመሳሳይ አንድ አቻ ወጥተዋል። ብሩክ በየነ ለሀዲያ ሆሳዕና፣ ሄኖክ አዱኛ በፍጹም ቅጣት ምት ለሸገር ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ቀን ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ አዳማ ከተማ በነቢል ኑሪ ጎል ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል። የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር በኋላ ከህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተደርገዋል። ይርጋጨፌ ቡና እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። መንደሪን ክንድሁን ለይርጋጨፌ፣ አህላም ሲራጅ ለአዳማ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ቁጥር እንዲጨምር አግዟል
Nov 9, 2025 172
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎችን ቁጥር በመጨመር በደመቀና በምቹ ሁኔታ እንዲካሄድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ገለጸ። በዓለም የአትሌቲክስ ውድድር የገዘፈ ስም ባለው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በ1994 ዓ.ም የተመሰረተው ታላቁ ሩጫ፤ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ በድምሩ ወደ 700 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን ማስተናገዱን መረጃዎች ያሳያሉ። የመጀመሪያው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ያነሱ ተሳታፊዎች የነበሩት ሲሆን፤ ባለፉት ዓመታት ውድድሩ 50 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን አስተናግዷል። በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሆነ የሚነገርለት ውድድር፤ ከኢትዮጵያውን ባሻገር ከተለያዩ ዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎችም የሚሳተፉበት ሆኗል። በተለያያ ወቅት የዓለም ታላላቅ አትሌቶች ውድድሩን በክብር እንግድነት በማስጀመር የተሳተፉ ሲሆን፤ ለአብነትም ፖል ቴርጋት፣ ገብርኤል ዛቦ፣ ካሮሊና ክሉፍት ፣ ዴቭ ሞርክሩፍት እና ፓውላ ራድክሊፍ ይጠቀሳሉ፡፡ በውድድሩ ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ስለሺ ስህን፣ ጸጋዬ ከበደ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔና ጥሩነሽ ዲባባ ማሸናፋቸው ይታወሳል፡፡ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ እንደገለጸው፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ ኢትዮጵያ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ እንደምትችል እያሳየ ይገኛል። በየዓመቱ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ውድድር የኢትዮጵያን ገጽታ በማስተዋወቅ የቱሪዝም ፍሰት እንዲጨምር የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የውድድሩ ተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያነሳው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ፤ በተለይ የኮሪደር ልማቱ ውድድሩ ያማረና የደመቀ እንዲሆን ማድረጉን ተናግሯል። የታላቁ ሩጫ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ በበኩሉ፤ የኮሪደር ልማቱ የውድድሩ ተሳታፊዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ተናግሯል። አብዛኛዎቹ የከተማዋ መንገዶች ከኮሪደር ልማቱ በፊት ለእግረኞች የተለየ መሄጃ የሌላቸውና ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ እንዳልነበሩ አስታውሷል፤ በዚህም ለተወዳዳሪዎች ደህንነት ሲባል በየዓመቱ የተሳታፊዎችን ቁጥር በአንድ ሺህ ወይም በሁለት ሺህ ብቻ ለመጨመር ተገደው መቆየታቸውን አስታውቋል። የኮሪደር ልማቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በተለይም የመሮጥ ባህልን ለማስፋፋት እና ሰፊ ህዝብ የሚሳተፍባቸውን ውድድሮች ለማዘጋጀት ከፍተኛ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ገልጿል። የኮሪደር ልማቱ ለስፖርቱ የሚያገለግሉ መንገዶችን በመያዙ የታላቁ ሩጫ ውድድር ተሳታፊዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ እንዳስቻለ ተናግሯል። ይህን ተከትሎ በዘንድሮው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መርኃ ግብር 55 ሺህ ተሳታፊዎች እንደሚወዳደሩ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
አዳማ ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
Nov 9, 2025 82
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ነቢል ኑሪ በ58ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ ቡናው በፍቃዱ አለማየሁ በ73ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። አዳማ ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አካባቢ ጥበቃ
በአዋሽ ወንዝ ከልማት ውጪ የነበረን ከ70 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ ልማት ማስገባት ተችሏል
Nov 10, 2025 128
አዳማ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ በአዋሽ ወንዝ ከልማት ውጪ የነበረን ከ70ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ ልማት ማስገባት መቻሉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ገለፁ። በአዋሽ ተፋሰስ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በዘላቂነት ለማስቀረት የተከናወኑ ተግባራት የአዋጭነት ጥናት ግኝት ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ተፋሰሶች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትና የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በስምጥ ሸለቆና ኦሞ ተፋሰሶች የጎርፍ አደጋ ስጋት ተጋላጭነትን ለመቀነስ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል። በተለይም ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በመካከለኛውና ታችኛው አዋሽ ተፋሰስ ላይ ከ250 ኪሎ ሜትር በላይ በወንዝ ግራና ቀኝ የውሃ መገደቢያ በመስራት የጎርፍ አደጋን የመከላከል ሥራ መከናወኑን አንስተዋል። በዚህም ወንዙ ሲሞላ መገደቢያውን አልፎ በመውጣት አደጋ ሲያደርስ የነበረውን ጎርፍ በመከላከል 70ሺህ 140 ሄክታር መሬት ወደ ልማት እንዲገባ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም ከ129 ሺህ በላይ የሚሆን የህብረተሰብ ክፍልን ከመፈናቀል አደጋ መታደግ ተችሏል ብለዋል። የአዋጭነት ጥናቱ ዓላማ የአዋሽ ወንዝን በዘላቂነት ከስጋት ነፃ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ለማስገባትና ወንዙን በሚፈለገው መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲቻል ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል። በወንዙ ግራና ቀኝ በተሰራው የጎርፍ መከላከል ሥራ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከማረጋገጥ ባለፈ የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነትን መቀነስ መቻሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሚካሄደው አህጉራዊ የመሬት ፖሊሲ ጉባኤ
Nov 10, 2025 64
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ):- ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። “የመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ለአፍሪካውያንና ለዘርዓ አፍሪካውያን” በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሚካሄደው ኮንፍረንስ መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ኮንፍረንሱን በጋራ አዘጋጅተውታል። ከአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ እና የአካባቢ ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙና ለነባራዊ እውነታዎች ምላሽ የሚሰጡ የመሬት ፖሊሲ ምርጥ ተሞክሮዎች በኮንፍረንሱ ይቀርባሉ። ውጤታማ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መገንባት፣ ተቋማዊ አቅምን መፍጠርና ቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ባርነት፣ የቅኝ ግዛት ዘመን መሬት የመንጠቅ ተግባርና በዘር ምክንያት መሬት ከማግኘት መገለል በአፍሪካውያንና ትውልደ አፍሪካውያን የመሬት መብቶች፣ ሀብት አጠቃቀምና እኩልነት ላይ ያሳደራቸውን አሉታዊ ተጽእኖዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ችግሩን በዘላቂነት መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይቶች ይካሄዳሉ። በመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ያሉ ውይይቶች ማጠናከር እና ፖሊሲ ተኮር ምላሾችን መስጠት ሌላኛው የኮንፍረንሱ አላማ ነው። የስርዓተ ጾታ እኩልነት፣ የአየር ንብረት ለውጥና ቴክኖሎጂዎችን ከመሬት ፖሊሲ እና አስተዳደር ጋር ማስተሳሰር ትኩረት ተሰጥቶታል። በኮንፍረንሱ የመሬት ፖሊሲ፣ የመሬት ፍትህ፣ የማካካሻ ፍትህ እና የመሬት ባለቤትነትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ ምክረ ሀሳቦች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአህጉራዊ ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ የህብረቱ ተቋማትና አደረጃጀቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ትውልደ አፍሪካውያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። ኮንፍረንሱ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሁነት ነው።
የኮፕ 30 አጀንዳዎች እና የኢትዮጵያ ተሳትፎ
Nov 10, 2025 152
30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ 30) ዛሬ ይጀምሯል። “የአየር ንብረት እርምጃ እና ትግበራ” የጉባኤው ዋና መሪ ሀሳብ ነው። ከኮፕ 30 ቁልፍ ግቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- የኢነርጂ፣ ኢንዱስትሪ እና ትራንስፖርት ስርዓቶችን ሽግግር ማፋጠን። በዚህም የታዳሽ ኃይልን በሶስት እጥፍ መጨመር፣ የኢነርጂ ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ማረጋገጥና የበካይ ጋዞችን በጊዜ ሂደት መጠቀም ማቆም መቀነስ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ይካሄዳሉ። ተፈጥሮን፣ ደኖችን፣ ውቅያኖሶችን የብዝሃ ህይወት ሀብቶችን መጠበቅና ወደ ቀደመ ይዞታቸው መመለስ፣ የደን ጭፍጨፋን ማስቆም እና የተጎዱ ስነ ምህዳሮች ዳግም እንዲያገግሙ ማድረግ። ግብርና እና ስርዓተ ምግብን መቀየር፤ ዘላቂ የመሬት አጠቃቀም፣ የማይበገር ስርዓተ ምግብ መገንባትና የምግብና የስነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ። ለከተሞች፣ ለመሰረተ ልማቶችና ለውሃ ስርዓቶች የማይበገር አቅም መገንባት፣ የሰው ኃይልና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን ጨምሮ ሌሎች አቅሞችን መጠቀም። የንግድ ማህበረሰቦች፣ ከተሞች፣ ባለሀብቶችና የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማትን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በኮፕ 30 የተግባር አጀንዳ አማካኝነት በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ ይገኙበታል። ከተጠቀሱት ግቦች የተለያዩ ውጤቶችም ይጠበቃሉ። የኮፕ 30 የተግባር አጀንዳ የሚያስፈጽም የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት፣ ቃል የተገቡ ጉዳዮች ወደ ተግባር መለወጥና ተግበራዊነቱን የሚቆጣጠሩ ቡድኖች ከጉባኤው በኋላ እንደሚቋቋሙ ይጠበቃል። ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት የፋይናንስ ግብን ማጠናከር ሌላኛው አጀንዳ ሲሆን የበለጸጉ ሀገራት በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ቃል የገቧቸውን የገንዘብ ድጋፎች እንዲሰጡ ጠንካራ ጥሪ ይቀርባል። የአየር ንብረት ለውጥ ፍትህ፣ ፍትሃዊ የኢነርጂ ሽግግር፣ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት፣ አቅም ግንባታና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያማከለ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ የሚጨበጥ ለውጥ ማምጣት የሚጠበቅ ውጤት ነው። መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በአየር ንብረት ለውጥ ስራዎች ላይ ያላቸውን ሚና ማሳደግና የባለድርሻ አካላትን ትብብር ማጠናከር ትኩረት የተሰጠሰው ጉዳይ መሆኑም ተመላክቷል። ለአፍሪካ ኮፕ 30 ለአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዋ መፍትሄ የሚያመጡ ውሳኔዎችን የምትጠብቅበት መድረክም ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ተደራሽነት ማሳደግና ፍትሃዊነትን ማስፈን፣ ፍትሃዊ የኢነርጂና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማረጋገጥ፣ ተፈጥሯዊ መፍትሄዎች፣ የብዝሃ ህይወት ጥበቃ፣ ኢኖቬሽን፣ የማይበገር አቅምን መገንባትና የዜጎች መብት ጥበቃ ከአፍሪካ አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ዝቅተኛ ድርሻ ቢኖራትም ዋነኛ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ናት። ተከታታይ ድርቆች፣ ጎርፎችና በረሃማነት አበይት ፈተናዎቿ ናቸው። በዚህ ረገድ ኮፕ 30 ለአፍሪካ በማይበገር አቅም ግንባታ፣ መሰረተ ልማት አቅርቦትና የኢነርጂ ተደራሽነት ላይ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ይጠበቃሉ። የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ጉዳይ በኮፕ 30 ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አፍሪካውያን ይሻሉ። ኮፕ 30 ለአፍሪካ የትርክት ሽግግር የምታደርግበት ነው ማለት ይቻላል። አፍሪካ የችግሩ ተጎጂ ነኝ ከማለት ባለፈ ታዳሽ ኢነርጂ፣ የካርቦን ገበያና አረንጓዴ ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ መፍትሄዎችን አፍላቂ አህጉር መሆኗን በግልጽ የምታሳይበትና ለዓለም ድምጿን የምታሰማበትም ነው። 13ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ ’’በሳይንስ፣ በገንዘብና በፍትሐዊ ሽግግር የአፍሪካን የአየር ንብረት እርምጃ ማንቃት” በሚል መሪ ሃሳብ በነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ የሚታወስ ነው። በጉባኤው ላይ የተሳተፈው የአፍሪካ የአየር ንብረት ድርድር ቡድን በብራዚል በሚካሄደው ኮፕ-30 የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ የአፍሪካን ቀዳሚ የልማት አጀንዳዎች የሚያንጸባርቁ የድርድር ሃሳቦችን ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉን ገልጿል። በጉባኤው የአፍሪካን የልማት መሻት ያነገቡ የተቀናጁ፣ ወጥነትና ጥራት ያላቸው የድርድር ሀሳቦች ለማቅረብ ዝግጅት እንደተደረገ አመልክቷል። የአፍሪካን የልማት ጸጋዎች የዓለም አቀፍ የመፍትሔ ለማድረግ በአዲስ አስተሳሰብ በመተባበር ላይ የተመሰረተ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ቡድኑ ገልጿል። አፍሪካ በ2030 የአየር ንብረት ግቦቿን ለማሳካት ከሚያስፈልጋትና ቃል ከተገባው ውስጥ ከ3 እስከ 4 በመቶ የማይበልጥ የፋይናንስ ድጋፍ እየተደረገላት መሆኑን መረጃዎች ያመክታሉ። ተደራዳሪ ቡድኑ በብራዚል ቤሌም ከተማ በሚካሄደው ኮፕ-30 ጉባኤ ላይ የአፍሪካን የፋይናንስ ፍትሐዊ አጀንዳ በአንድ አህጉራዊ ድምጽ ማሰማት እንደሚያስፈልግና ለዚህም ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል። ኢትዮጵያ በኮፕ 30 በአፍሪካ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ውስጥ የመሪነት ሚናዋን ለመወጣት ተዘጋጅታለች። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ(ኮፕ 30) የተገቡ ቃሎች ወደ ተግባር የሚቀየሩበት ወሳኝ ምዕራፍ ሊሆን እንደሚገባም ደጋግማ ገልጻለች። በአረንጓዴ ዐሻራ አማካኝነት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ኢትዮጵያ ማንንም ሳትጠብቅ ተጨባጭ እርምጃ ወስዳለች። አረንጓዴ ዐሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥና ለሀገር እድገት የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል። ኢትዮጵያ ግብርናውን ጨምሮ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የታገዙ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እርምጃዎች እየሰወደች ነው። ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማፋጠን፥ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ" በሚል መሪ ሀሳብ ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የአፍሪካን የጋራ ድምጽ የያዘውን የአዲስ አበባ ድንጋጌ በማጽደቅ መጠናቀቁ ይታወሳል። የአየር ንብረት ጉባኤውን በጋራ ያዘጋጁት ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ህብረት የጣምራ መግለጫ ማውጣታቸውም አይዘነጋም። በጉባኤው በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች ቃል መገባታቸውንና ታሪካዊው የአዲስ አበባ ድንጋጌ መጽደቁን ገልጾ፥ ይህም የአፍሪካ መሪዎች በዓለም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ውስጥ ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልጿል። በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት በ“Africa Climate Innovation Compact” እና “African Climate Facility” የተሰኙ ኢኒሼቲቮችን ይፋ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ለሀገር በቀል የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎች 50 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በየዓመቱ የማሰባሰብ ስራ እንደሚከናወን ተመላክቷል። መሪዎቹ በጉባኤው ላይ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውን የገለጸው የጋራ መግለጫው፥ ፈንዱ እዳን ከሚያሸክሙ ብድሮች ይልቅ የፋይናንስ ድጋፍ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ጠቁሟል። በጉባኤው ዓለም አቀፍ አጋሮች የፋይናንስ ድጋፎችን ለማድረግ ቃል ገብተዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ(አፍሪኤግዚም ባንክ)፣ አፍሪካ 50 የተሰኘ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ማዕቀፍን ጨምሮ ሌሎች ግዙፍ የፋይናንስ ተቋማት ለአፍሪካ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ ኢኒሼቲቭ 100 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ሌሎች ሀገር በቀል የአየር ንብረት ፕሮጀክቶችን የሚደግፉ አዳዲስ ፕሮጀክቶችም ይፋ ሆነዋል። መሪዎች በጉባኤው አፍሪካ እ.አ.አ በ2030 በዓለም የታዳሽ ኢነርጂ ኢንቨስትመንት ያላትን ድርሻ ከ2 በመቶ ወደ 20 በመቶ ከፍ ለማድረግም ቃል ገብተዋል። የአረንጓዴ ማዕድናት እና ንጹህ የኢነርጂ ተደራሽነት የሚያሰፉ ስትራቴጂዎችን ማጠናከር ሌላኛው ጉባኤው ከስምመነት ላይ የደረሰበት አጀንዳ ነው። አፍሪካ በብራዚል ቤለም የሚካሄደውን (ኮፕ 30) የፀደቀውን የአዲስ አበባ ድንጋጌ አፍሪካ በዓለም የአየር ንብረት ያላትን የመሪነት ሚና የሚያጸና መሆኑን መግለጫው አመልክቷል። ኮፕ 30 ከዓለም የአየር ንብረት አስተዳደር አንጻር ትልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን ቃል ኪዳኖቹ ወደ ተጨበጡ ውጤቶችና የተግባር እርምጃዎች የሚቀየሩበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በጉባኤው የተገቡ ቃሎችና ትግበራን የሚያስታርቅ ነው ያሉትም አልጠፉም። በአጠቃላይ ጉባኤው ሁሉን አካታችና ተግባር ተኮር የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የሚስተጋባበትና አስቸኳይ ጥሪ የሚቀርበበት ነው። አፍሪካም በጋራ ድምጿን ከማሰማት ባለፈ ፍትህና የተግባር ምላሽን የምትጠብቅበት ነው። ቃልን ወደ ተግባር መለወጥ የሚጨበጥ ለውጥ በማምጣት መጻኢ ጊዜ ፍትሃዊ እና ዘላቂነትን ላይ የተመረኮዘ እንዲሆን ያስችላል። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ 30) እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
72 የአጥቢ እንስሣት ዝርያዎች መገኛ ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ
Nov 9, 2025 150
ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ውድምቢ የተሰኘው የዱር እንስሣ ኢትዮጵያ ውስጥ በብቸኝነት መገኛ እንደሆነም ይነገራል። ማራኪ ዕይታና ድንቅ የተፈጥሮ አቀማመጥ የተቸረው ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ-ገባውን ሙርሲ፣ ቦዲ፣ ባጫ፣ ሙጉጂ፣ ኛንጋቶም፣ ሱርማ፣ ዲዚና ሚኒት ብሔረሰቦች አጅበውታል። ፓርኩ በ1959 ዓ.ም. ሲመሠረት 4 ሺህ 68 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት እንደነበረው የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ዋና ኃላፊ ኑሩ ይመር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። ይህ አሃዝ በ2012/13 ዳግም በተደረገ የመከለል ሥራ ወደ 5 ሺህ 149 ስኩየር ኪሎ ሜትር ከፍ ማለቱንም ጠቅሰዋል። 72 የአጥቢ እንስሣት ዝርያዎች በፓርኩ ውስጥ እንደሚኖሩ የጥናት ውጤቶች ማመላከታቸውን ጠቅሰዋል። ከእነዚህ መካከልም አምሥቱ ትላልቅ የአፍሪካ አጥቢ እንስሣት መሆናቸውን ጠቁመው፤ እነሱም ዝሆን፣ አንበሳ፣ ነብር፣ አውራሪስና ጎሽ እንደሆኑ አብራርተዋል። በተጨማሪም ከ325 በላይ የአዕዋፍ፣ ከ24 በላይ የተሳቢና ተራማጅ፣ ከ13 በላይ የዓሣ ዝርያዎች እንደሚገኙ አስረድተዋል። እንዲሁም ፓርኩ ከ600 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች መገኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። ብሔራዊ ፓርኩን ከተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባራት ለመጠበቅ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከመንግሥት መዋቅር ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ መሪዎች ብዝሃ ህይወትን ከብሄራዊ ፖሊሲዎቻቸው ጋር ማስተሳሰር ይገባቸዋል -አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ
Nov 6, 2025 290
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ መሪዎች የብዝሃ ህይወት አጀንዳን ከብሄራዊ ፖሊሲዎቻቸው ጋር በማቆራኘት ሊተገብሩ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ ገለጹ። ከጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በቦትስዋና ጋቦሮኒ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ በመሪዎች ደረጃ በተደረገ ስብስባ ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ የሀገራት መሪዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ መሪዎች እና ተመራማሪዎች፣ ሀገር በቀል የማህበረሰብ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። “የብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት በመጠቀም የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ ጉባኤው አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጠበቅ በጀመረችው ጉዞ ውስጥ ታሪካዊ ሁነት መሆኑን ገልጸዋል። ከኮንጎ ጥብቅ ደን እስከ ደቡብ አፍሪካው የኬፕ የአበባ ሀብት ቀጣና በአህጉሪቷ የሚገኙ ተፈጥሯዊ ምህዳሮች የህይወት፣ ባህል እና የኢኮኖሚ እድገት ምንጮች መሆናቸውን አመልክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ብክለት እና ዘላቂ ያልሆነ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም በአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ላይ ስጋቶችን እንደደቀኑ ተናግረዋል። የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ላይ የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ያስፈልጋል ያሉት አምባሳደሯ ለዘርፉ የሚያስፈልገውን መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከአባል ሀገራት፣ ከቀጣናዊ ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ ጋር በመሆን የአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ስትራቴጂ ከአጀንዳ 2063 እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር በተጣጠመ መልኩ እንዲተገበር በትብብር እንደሚሰራ ነው የገለጹት። ብዝሃ ህይወት እንደ ተጓዳኝ ጉዳይ ሳይሆን ለአፍሪካ ሰላም፣ አይበገሬነት እና ዘላቂ ልማት ባለው ቁልፍ ድርሻ ሊታይ እንደሚገባ ጠቅሰው በዚህ ረገድም የአፍሪካ መሪዎች ብዝሃ ህይወት ከብሄራዊ ፖሊሲዎች ጋር ማስተሳሰር እንዳለባቸው አሳስበዋል። ወጣቶች እና ሀገር በቀል ማህበረሰቦችን ማብቃት እንዲሁ በፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዓለም አቀፍ እኩልነት ለማስፈን መትጋት ትኩረት እንደሚያሻቸው ነው ያነሱት። የአፍሪካ ብልፅግና አረንጓዴ፣ ሁሉን አቀፍ እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። የጋቦሮኒው ጉባኤ የአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ድንጋጌ ቀጣይ ለሚመጡ ትውልዶች መሰረት የሚጥል እንደሚሆንም ገልጸዋል። ጉባኤው በአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ሀብቶች፣ እድሎች፣ ፈተናዎችና ቀጣይ እርምጃዎች በዋናነት መምከሩን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሄይቲ እና ጃማይካ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው ጎርፍ ሳቢያ የበርካቶች ሕይዎት አለፈ
Oct 31, 2025 471
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ)፡-በሄይቲ እና ጃማይካ የተከሰተው ‘ሃሪኬን ሜሊሳ’ የተሰኘው ወጀብና ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ እስካሁን የ49 ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል። በሄይቲ የ30 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን እና ከ20 በላይ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። እስካሁን ያሉበት ሁኔታ ያልታወቁ ሰዎችን የመፈለጉ ሥራም መቀጠሉን ባለሥልጣናቱ ለአልጄዚራ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመላክተዋል። እንዲሁም የአውሎ ነፋሱ ሰለባ በሆነችው ሌላኛው ሀገር ጃማይካ የ19 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል። እስካሁን ከተመዘገቡት በጣም ኃይለኛ የአትላንቲክ አውሎ ነፋሶች አንዱ እንደሆነ የተነገረለት ሃሪኬን ሜሊሳ በሠዓት 295 ኪሎ ሜትር እንደሚከንፍ ተገልጿል። አውሎ ነፋሱ የጃማይካን ምዕራባዊ ክልል በመምታት አስከፊ ጉዳት ማድረሱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ሃሪኬን ሜሊሳ በካሪቢያን ቀጣና ኩባ፣ሄይቲ እና ጃማይካ በሰው ሕይወት እንዲሁም በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል። ይህን ተከትሎም በካሪቢያን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ውጭ መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል። የኤሌክትሪክ አቅርቦቱን ለመመለስና አካባቢዎቹንም የማጽዳት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
የአፍሪካ ህብረት የ30 ቢሊዮን ዶላር የአቪዬሽን መሰረተ ልማት የኢንቨስትመንት እቅድ ይፋ አደረገ
Oct 31, 2025 385
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ):-የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷን የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ማዘመንን አላማ ያደረገ የ30 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ ዛሬ ይፋ አድርጓል። ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአንጎላ ሉዋንዳ ሲካሄድ የነበረው ሶስተኛው የአፍሪካ መሰረተ ልማት ፋይናንስ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአንጎላ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ጆአኦ ሎሬንቾ፣ የህብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የአየር መንገዶች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ከጉባኤው ጎን ለጎን በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት ገበያ አማካኝነት የአህጉሪቷን አቪዬሽን መሰረተ ልማት በፋይናንስ በመደገፍ እና በማዘመን የተቀናጀ የአየር አገልግሎት እና ነጻ እንቅስቃሴን መፍጠር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተከናውኗል። የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦጅ በመድረኩ ላይ በአየር ትራንስፖርት ገበያው አማካኝነት የአህጉሪቷን የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ለማዘመን የሚውል የ30 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ ዛሬ ይፋ አድርገዋል። እቅዱ አፍሪካ በቀጣይ 10 ዓመት የአቪዬሽን ዘርፉን ለማሻሻል የሚያስፈልጋትን ከ25 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በአፍሪካ እ.አ.አ በ2024 160 ሚሊዮን የነበረው የመንገደኞች መጠን እ.አ.አ በ2050 ወደ 500 ሚሊዮን ገደማ እንደሚደርስ የገለጸው ህብረቱ ኢንቨስትመንቱ የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እና አቅምን ለማጎልበት እንደሚያስችል አመልክቷል። በኢንቨስትመንት እቅዱ አማካኝነት ገንዘቡ ለአውሮፕላን ማረፊያ፣ አውሮፕላን ጣቢያ እና ጥገና ማዕከላት መሰረተ ልማት፣ የአቪዬሽን ስርዓቶች ማዘመን፣ ለሰው ኃይል ልማት፣ ለቁጥጥር ስራ፣ ለቴክኖሎጂ እና ተጓዳኝ ስራዎች እንደሚውል ተገልጿል። የአፍሪካ ህብረት 10 ቢሊዮን ዶላሩን ከአፍሪካ መንግስታት፣ ከቀጣናዊ የልማት ባንኮች እና ከባለቡዙ ወገን አጋሮች ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቋል። ቀሪው 20 ቢሊዮን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አጋሮች፣ የሉዓላዊ ሀብት ፈንዶች (sovereign wealth funds) እና የጡረታ ፈንዶችን ጨምሮ ከግል እና የተቋማት ኢንቨስተሮች ለማግኘት መታሰቡን ነው ያመለከተው። የሀብት ማሰባሰቡ የሚከናወነው በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ማዕቀፍ ሲሆን የ30 ቢሊዮን ዶላሩ ከእ.አ.አ 2025 እስከ 2035 ለሚተገበሩ ስራዎች የሚውል ነው። የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦጅ አቪዬሽን የትራንስፖርት አማራጭ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ትስስር ስትራቴጂካዊ ሞተር እንዲሁም የአጀንዳ 2063 እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ቁልፍ አቅም ነው ብለዋል። በኢንቨስትመንት እቅዱ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት መመዘኛዎችን ባሟላ እና ከካርቦን ልህቀት ነጻ በሆነ መልኩ እንደሚገነቡ አመልክተዋል። ህብረቱ ዘመናዊ፣ ውጤታማ እና ዘላቂ የአቪዬሽን ኔትወርክ በመፍጠር ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር፣ የአየር ትራንስፖርት ግንኙነት ስር እንዲሰድ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንዲያድግ በቁርጠኝነት ይሰራል ነው ያሉት።
ለአህጉሪቷ ለዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው
Oct 24, 2025 649
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ):-ለአህጉሪቷ አስተማማኝና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በስብሰባው ላይ የአባል አገራት በግብርና፣ በእንስሳት፣ በዓሳ ሀብት፣ በገጠር ልማት፣ በውሃ፣ በአካባቢ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው የሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም የማላቦ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2014 እስከ 2025) መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የሚተገበረው የካምፓላ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2026 እስከ 2035) ጸድቋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አባል ሀገራት የራሳቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም የግብርና ግብዓቶችንና ምርጥ ዘርን መጠበቀ እንዲሁም ብዝሃ ህይወትን ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የውሃ ኃብትን ከማሳደግ አኳያም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ - ኒፓድ የግብርና፣ የምግብ ዋስትና እና የአካባቢ ዘላቂነት ዳይሬክተር ኤስቴሪን ፎታቦንግ የካምፓላ አጀንዳ (2026–2035) በአፍሪካ የግብርና-ምግብ ሥርዓቶች ላይ የለውጥ ምዕራፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ ከአጀንዳው ግቦች መካከልም ዘላቂ የምግብ ምርትን፣ አግሮ-ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እና ንግድን ማጠናከር፣ ለግብርና-ምግብ ሥርዓት ለውጥ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስን ማሳደግ ብሎም የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚሉ እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ የካምፓላ አጀንዳ ስትራቴጂ እንዲሳከ ምቹ ሁኔታዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡ የዩጋንዳ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እና የአምስተኛው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካይ ፍሬድ ብዊኖ ክያኩላጋ የካምፓላ አጀንዳ የእንስሳት ሃብትን ማሳደግ ላይ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡ በዚህም ለእንስሳትና ለዓሳ እርባታ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የእንስሳት መኖ ማሳደግ፣ ለእንስሳት ጤና እንዲሁም የዘረመል መሻሻልም ከትኩረት መስኮች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ የካምፓላ አጀንዳ የአፍሪካ ግብርና ልማት መርሃ ግብር ታላላቅ ግቦች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ሐተታዎች
ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
Nov 7, 2025 229
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንገት በላይ ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ኦሊያድ ታረቀኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ስለ ጆሮ ህመም መንስዔ እና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል። የጆሮ ህመም ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ኦሊያድ ገለጻ፤ በጆሮ አካባቢ ያሉ የአካል ክፍሎችን የሚያጠቁ ህመሞች የጆሮ ህመም ሊባሉ ይችላሉ። በሳይንሱ የውጨኛው፣ የመካከለኛው እና የውስጠኛው የጆሮ ክፍል ህመም ተብለው እንደሚለዩ ጠቅሰው፤ እነዚህን ክፍሎች የሚያጠቁ የተለያዩ የህመም ዓይነቶች እንዳሉም አመላክተዋል። የጆሮ ህመም ዓይነቶች በተለያዩ መንስዔዎች የተለያዩ ህመሞች እንደሚከሰቱ ጠቁመው፤ ከእነዚህ መካከል በስፋት የሚከሰተው በኤንፌክሽን የሚከሰት የጆሮ ህመም መሆኑን ተናግረዋል። ከአደጋዎች፣ ህመሞችና ጉዳቶች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጆሮ ክፍሎች ህመሞች እንዳሉም በመጠቆም። እንዲሁም ከዕባጮች (ዕጢዎች) ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጆሮ ህመሞች እንዳሉ አመላክተዋል። በውጨኛው የጆሮ ክፍል የሚከሰቱ ከአጥንትና ከቆዳ የሚነሱ ዕባጭና ዕጢዎች፣ ከመካከለኛው የጆሮ ክፍል የሚነሱ በአብዛኛው ከደም ሥር ጋር የተያያዙ ዕጢዎች እንዲሁም ከውስጠኛው የጆሮ ክፍል ከነርቭ የሚነሱ የተለያዩ ዓይነት ዕጢዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም አብራርተዋል። ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች የጆሮ ህመም በሁሉም ጾታና የዕድሜ ክልል ሊከሰት እንደሚችል ገልጸው፤ በአብዛኛው አጋላጭ ምክንያቶች ተብለው ከሚነሱት መንስዔዎች መካከል ከታች የተጠቀሱት ዋነኞቹ መሆናቸውን ያብራራሉ። o ባብዛኛው ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች (ልጆች ባላቸው ያልዳበረ በሽታዎችን የመከላከል ዐቅም እንዲሁም አንዳንድ የሰውነት ክፍሎቻቸው በደንብ ባለመዳበራቸው ሊከሰት የሚችል ነው።) o ዕድሜ ሲጨምር የጆሮ መዳከም ችግር ሊኖር ስለሚችል የመስማት ዐቅም እየቀነሰ ሊሄድ ይችላል። o ለተለያየ ከባድ ድምጽ መጋለጥ ለጆሮ ህመም ወይም የተለያየ ደረጃ ላላቸው የመስማት ችግሮች ሊዳርግ ይችላል። o ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት ጭሶች መጋለጥ ለጆሮ ህመም ሊያጋልጥ ይችላል ተብሎ እንደሚታሰብ አስረድተዋል። የጆሮ ህመም ምልክቶች ምልክቶቹ እንደ ህመሙና ህመሙ እንደተከሰተበት ቦታ የተለያዩ መሆናቸውን ዶክተር ኦሊያድ ይገልጻሉ። ለምሳሌ በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት የጆሮ ህመም ከሆነ እንደተከሰተበት የጆሮ ክፍል ምልክቱ ይለያያል ይላሉ። ለአብነትም የውጨኛው የጆሮ ክፍል ላይ የሚከሰት የጆሮ ኢንፌክሽን ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል መጠዝጠዝ፣ ውጋትና ማሳከክ ዋናኞቹ ናቸው ብለዋል። ራሱ ይህ ህመም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ላይ ሲከሰት ደግሞ የመስማት ደረጃ መቀነስ፣ ትኩሳት፣ አልፎ አልፎ ከባድ የጆሮ ውጋት መኖር፣ የህመሙ ደረጃ እየጨመረ ሲሄድም የተለያዩ ፈሳሾችን ሊያሳይ ይችላል (ለምሳሌ እንደ ውኃ የቀጠነ ፈሳሽ፣ ወፍራም መግል የመሰለ ፈሳሽ፣ አንዳንድ ጊዜ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ሊሆን ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።) በተለያዩ ዕባጮችና ዕጢዎች የሚከሰት የጆሮ ህመም ሲሆን ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል፤ የጆሮ መደፈን ስሜት (ጆሮ ድፍን ብሎ ለመስማት መቸገር)፣ የተለያየ ዓይነት የጆሮ ውስጥ ድምጽና ጩኸቶች መኖር (አንዳንድ ጊዜ ከልብ ምት ጋር አብሮ ሊሰማ የሚችል የጆሮ ውስጥ ጩኸት ሊሆን ይችላል) ብለዋል። በውስጠኛው የጆሮ ክፍል ላይ የሚከሰት የዕጢ ዓይነት ደግሞ የመስማት ደረጃ መቀነስ፣ ማዞር እና ቫላንስ እስከ ማጣት (ሚዛንን ጠብቆ ለመንቀሳቀስ እስከመቸገር) የሚያደርሱ ምልክቶችን ሊያሳይ እንደሚችል ጠቁመዋል። ሰዎች ለጆሮ ህመም እንዳይጋለጡ ምን ያድርጉ? ሰዎች የተለያዩ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መክረው፤ ከእነዚህ ጥንቃቄዎች መካከልም፡- o በልማድ የሚደረጉ ጭራሽ ለጉዳት አጋላጭ የሆኑ ጆሮን የማጽዳት ተግባራት (‘የጆሮን ንጽህና እየጠበቅሁ ነው’ ብሎ በማሰብ ጆሮን ለማጽዳት የሚደረጉ ልማዶችን) ማስወገድ፤ o ጆሮ ለከባድ ድምጽ እንዳይጋለጥ ማድረግ። ለምሳሌ ለረጅም ሠዓት ‘ኤርፎን’ መጠቀም ለጆሮ ህመም እንደሚያጋልጥ በመገንዘብ የሠዓቱን እና የድምጹን መጠን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። ‘ኤርፎን’ በአንድ ጊዜ ለ60 ደቂቃ የድምጽ መጠኑ ከ60 በመቶ ባልበለጠ ጊዜ መጠቀም ይመከራል ያሉት ዶክተር ኦሊያድ፤ ከዚህ ደቂቃ በላይ በአንድ ጊዜ መጠቀም ሲያስፈልግ በየመሀሉ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ጆሮን ማሳረፍ እንደሚገባ ይመክራሉ። በሌላ በኩል ማሳከክን ጨምሮ የጆሮ ህመም ስሜት ሲኖር በወቅቱ ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ በማድረግ ህመሙ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ መታከም የጥንቃቄው አካል መሆኑን አስረድተዋል። የጆሮ ህመም ሕክምና ሕክምናው እንደ ህመሙ ዓይነት እንደሚለያይ አስገንዝበው፤ በአጠቃላይ በሚዋጡ፣ በመርፌ በሚሰጡ፣ በጆሮ ውስጥ በሚጨመሩ እንዲሁም በሚቀቡ አማራጮች ሕክምናው እንደሚሰጥ አብራርተዋል። ከላይ ከተጠቀሱት የሕክምና አማራጮች አልፎ የመስማት ደረጃ መቀነስና መቸገር ከተስተዋለ የቀዶ ሕክምና ማድረግ ብሎም የማዳመጫ ማገዣ መሣሪያ መጠቀም የሕክምናው አካል መሆናቸውን አስረድተዋል። የጆሮ ህመም በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ከ5 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ልጆች ላይ 8 በመቶ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ60 በላይ በሆኑ ሰዎች ደግሞ እስከ 73 በመቶ ድረስ የመስማት ችግር እንደሚያጋጥም ጥናት ማመላከቱን ጠቅሰዋል። ጆሮ ላይ የሚከሰቱ ህመሞች የመስማት ችግርን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረዋል።
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት አጋርነት
Nov 3, 2025 433
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት አጋርነት ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ያላቸው ታሪካዊ ወዳጅነት በርካታ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት በአራተኛው ክፍለ ዘመን እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ። በአክሱም ንጉስ ኢዛና ወቅት ኢትዮጵያ ከምስራቅ ሮም መንግስት ጋር ዲፕሎማሲያዊ እና ሃይማኖታዊ ግንኙነት እንደነበራት ይነገራል። 15ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው በሰነድ የተደገፈ የኢትዮጵያ እና አውሮፓ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ግንኙነቶች የተደረጉበት ወቅት ነው። እ.አ.አ በ1441 የኢትዮጵያ ልዑክ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምክር ቤት (The Council of Florence) ስብስባ ላይ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት እና አውሮፓ መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ግንኙነት እንደሆነ ታሪክ ያወሳል። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑካን ወደ ሮም፣ ቬኒስ እና ሊዝበን ጉብኝቶችን አድርገዋል። ከዛ በኋላ ባሉ ክፍለ ዘመናት በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ሀገራት መካከል በርካታ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ እንቅስቃሴዎች እና የጉብኝት ልውውጦች ተደርገዋል። እ.አ.አ 1975 ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ማህበረሰብ ጋር ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመረችበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት (በቀድሞ አጠራሩ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ) እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 28 1975 በቶጎ ሎሜ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ የሎሜ ድንጋጌ እየተባለ ይጠራል። ስምምነቱ ለኢትዮጵያ እና ለአውሮፓ ህብረት ትብብር መሰረት የጣለ ታሪካዊ ሁነት ነው። የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ ትብብር፣ የልማት ድጋፍ እና የወጪ ንግድ የስምምነቱ አበይት ማዕቀፎች ናቸው። የሎሜ ስምምነት አራት ጊዜ ማሻሻያ ተደርጎበታል። ማሻሻያዎቹ ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በፖለቲካ፣ ዴሞክራሲ፣ ኢንዱስትሪ፣ አካባቢ ጥበቃ እና ቀጣናዊ ትስስርን ጨምሮ ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ ማስፋትን ያለሙ ናቸው። እ.አ.አ በ2000 የሎሜ ስምምነት ወደ ኮቶኑ ስምምነት ተሸጋገረ። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በቤኒን ኮቶኑ አዲስ የትብብር ማዕቀፍ ተፈራረሙ። የኮቶኑ ስምምነት የሁለቱን ወገኖች አጋርነት ያስቀጠለ ነው። የፖለቲካ ምክክሮች፣ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶች አካቷል። ስምምነቱ ሁለት ጊዜ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ሲሆን እ.አ.አ በ2020 ማዕቀፉ እስከ እ.አ.አ 2024 እንዲቀጥል ተወስኗል። እ.አ.አ በ2023 በሶሞአ በተደረገ ውይይት የድህረ ኮቱኑ ስምምነት የተባለለት ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት እና አውሮፓ ህብረት መካከል ተፈርሟል።ኢትዮጵያ የዚህ ስምምነት ተጠቃሚ ናት። እ.አ.አ በ2016 የተፈረመው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ስትራቴጂካ ትስስር ማዕቀፍ ስምምነት የበለጠ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ያጸና ነው። የአውሮፓ ህብረት ያቋቋመው የአውሮፓ ቡድን በኢትዮጵያ (Team Europe in Ethiopia) ህብረቱን፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና 21 የህብረቱ አባል ሀገራትን አቅፎ የያዘ ነው። ከአውሮፓ ህብረት 27 አባል ሀገራት መካከል 21ዱ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ውክልና አላቸው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ሰላም እና ፀጥታ፣ የምግብ ስርዓት፣ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የግሉ ዘርፍ ልማት እና ትራንስፖርት ጨምሮ በሌሎች መስኮች ትብብር አላቸው። የአውሮፓ ህብረት በኮቶኑ ስምምነት የነበረውን የአውሮፓ የልማት ፈንድ ድጋፍ በመተካት ከእ.አ.አ 2021 እስከ 2027 የሚቆይ የፋይናንስ ማዕቀፍ እየተገበረ ይገኛል። 629 ሚሊዮን ዩሮ ፈሰስ የሚደረግበት ይህ ማዕቀፍ ከአውሮፓ ህብረት ተቋማት እና አባል ሀገራት አስተዋጽኦ የሚገኝ ሲሆን በየዓመቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለሚከናወኑ ስራዎች የሚውል ነው። ታዳሽ ኢነርጂ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ዘላቂ የስርዓተ ምግብ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ የሰው ሀብት ልማት፣ የፍልሰት አስተዳደር እና ሰላም ግንባታ ድጋፍ የሚደረግባቸአው መስኮች ናቸው። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ትብብር ውስጥ የሚጠቀሱ አንኳር ጉዳዮች አሉ። ከቅርቡ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ወደ ቤልጂየም ብራሰልስ በማምራት ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከርና ለማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ከውይይቱ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ" የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። "ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ" በአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን የሚመራ የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ ኢኒሼቲቭ ሲሆን ህብረቱ ከተለያዩ ሀገራት በዲጂታላይዜሽን፣ በታዳሽ ኃይል፣ በስርዓተ ምግብ፣ በጤና፣ በዘላቂ ግብርና፣ በሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በቁልፍ ዘርፎች ያለውን ትብብር እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው። ስምምነቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማሲ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ ገልጸዋል። በተጨማሪም ስምምነቱ ሁለቱ ወገኖች እ.አ.አ በ2016 ለተፈራረሙት የስትራቴጂክ ትስስር የጋራ ድንጋጌ አዲስ አቅም እንደሚፈጥርም ተመላክቷል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ሳምንት ለ2025 ዓመታዊ የድርጊት መርሃ ግብር የ90 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት በአዲስ አበባ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው። በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብስባ ላይ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከስበሰባው ጎን ለጎን ከአውሮፓ የኢንቨስትመንት ባንክ ከዓለም አቀፍ አጋርነት ዳይሬክተር ቱራያ ትሪኪ ጋር መክረው ነበር። በወቅቱ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም (RUFIP III) ሶስተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ የሚውል የ110 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱ የሚታወስ ነው። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢመስበርገር ተፈራርመውታል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የ240 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል። ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን ልማት በተለያዩ ወሳኝ ዘርፎች ለማጠናከር የሚውል ነው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም የጋራ ምክክር በአዲስ አበባ ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ የጋራ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል። ሁለቱ ወገኖች በህዳር ወር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተመሳሳይ የጋራ የምክክር መድረክ ማድረጋቸው አይዘነጋም። በ2011 ዓ.ም ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት በጤና ዘርፍ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ ያተኮረ የ20 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ዲፕሎማሲያዊ ትስስሩ ሁለቱ ወገኖች በሰኔ ወር 2008 ዓ.ም ከተፈራረሙት የስትራቴጂክ የጋራ ድንጋጌ በኋላ የበለጠ እየተጠናከረ መጥቷል። ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረሙ የሁለቱን አካላት ግንኙነት ለማጠናከር እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን የአፍሪካ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጌዛ ስትራመር፣ የፈረንሳይ የወጪ ንግድ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር መልዕክተኛ ኒኮላስ ፎርሲየር፣ የሜዴፍ ኢንተርናሽናል ምክትል ፕሬዝዳንት ፋብሪስ ላሳች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶች እና የንግድ መሪዎች ተገኝተዋል። ፎረሙ በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከርና አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በዝርዝር አስረድተዋል። ሪፎርሙ የግል ኢንቨስመንት መሳብ እና ኢትዮጵያ ከዓለም ኢኮኖሚ ጋር ያላትን ትስስር የበለጠ ማጠናከርን ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በፎረሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚ ትብብር እያደገ መምጣቱን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረም በኢትዮጵያ ተቋማትና በአውሮፓ ኩባንያዎች መካከል በኢኖቬሽን፣ በእሴት መጨመርና የጋራ ብልጽግናን መደገፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጎልበት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም ገልጿል። ፎረሙ የፈረንሳይ ድርጅቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚሰራ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በሚደግፈው ሜዴፍ ኢንተርናሽናል እና በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በአራት የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በአቪዬሽን፤ በታዳሽ ኃይል፤ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት እና በዲጂታል ቴሌኮሙኒኬሽን ላይ ያተኮረ ነው። የኢትዮጵያ- የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፎረምም ይህንን እያደገ ያለ ትብብር ያሳያልም ተብሏል። የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት ከግማሽ ክፍለ ዘመናት በላይ ጸንቶ የቆየ ወዳጅነት ነው። የሁለቱ ወገኖች ትብብር በአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት ላለው ግንኙነት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።
የብዙዎች ቤት…
Oct 27, 2025 582
እስካሁን በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት ከ81 በላይ የአጥቢ እንስሣት፣ ከ450 በላይ የአዕዋፍ እና ከ400 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች መኖሪያ ነው። ከእነዚህ መካከል አምስቱ የአዕዋፍ ዝርያዎች በዚህ ሥፍራ ብቻ ይገኛሉ፤ ከአምስቱ መካከል በተለይም የአንዷ ዝርያ ዓለም አቀፍ የዘርፉ ተመራማሪዎችንና ጎብኚዎች ቀልብ መሳቡ ይጠቀሳል። ከአካባቢው ተፈጥሯዊ አቀማመጥና የአየር ሁኔታ ጋር መጣጣም የቻሉ የቆላ እፅዋት (ዛፎች) በምቾት በስፋት እንደሚገኙበትም ይገለጻል። የተመሠረተው በ1958 ዓ.ም ሲሆን፤ ስፉቱም 591 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፤ በቁጥርም ሆነ በሥብጥር የብዙዎች መኖሪያ የሆነው ይህ ሥፍራ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ይሰኛል። መንግሥት በሰጠው ትኩረት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ እንስሣቱም ሆኑ እፅዋቱ እየኖሩ ነው፤ ከሕገ ወጥ ድርጊትም እንዲጠበቁ ማድረግ መቻሉን የፓርኩ ኃላፊ አደም መሐመድ ለኢዜአ አረጋግጠዋል። በፓርኩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁንም ለ247 ወገኖች ቋሚ እና ለ2 ሺህ 535 ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ዓመትም በ1 ሺህ 751 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች እንደተጎበኘ ኃላፊው ገልጸዋል።
የክህሎቶች ልማት፤ የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር
Oct 15, 2025 944
አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ። ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል። ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል። ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል። አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት። ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው። የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው። ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው። የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው። በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል። አህጉራዊ የንግድ ማዕቀፉ በሙሉ አቅሙ ሲተገበር የአፍሪካ ሀገራትን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ መጠን 50 በመቶ እንደሚጨምረው የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። ይህም ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን የሚያፋጥንና አህጉሪቷ ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ ልካ መልሳ ያለቀላቸውን ምርቶች በከፍተኛ ወጪ ከመግዛት ተላቃ ጥሬ ምርቶቿን በከፍተኛ ጥራት ወደ ማምረት ያሸጋግራታል። ይህ ትልቅ የኢኮኖሚ ትስስር እድል አፍሪካውያን በጋራ እንዲለሙ፣ የሙያ ክህሎት እንዲያሳድጉ እና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ እንዲሁም ጠንካራ እና የማይበገር ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። እነዚህ ሁላ ተስፋ ሰጪ አቅሞች የሚቃረን አንድ የማይካድ ሐቅ አፍሪካ ውስጥ አለ ይህ እውነት የአፍሪካን የእድገት አቅም በሚፈለገው መልኩ የሚመግብ የክህሎቶች እና የስራ ክፍተት ነው። በየዓመቱ በአፍሪካ ከ10 እስከ 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ። ይሁንና በአህጉሪቷ በዓመቱ የሚፈጠረው መደበኛ ስራ 3 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ከሆነ ከአፍሪካ ወጣቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ገደማው ስራ አጥ (Unemployment) ወይም ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) ውስጥ ነው። ይህ ስራ አለማግኘት ያለው በአፍሪካ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢነርጂ፣ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን እና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚገኙ ኩባንያዎች ክህሎት ያለው ሰው አጠረን እያሉበት ባሉበት ወቅት መሆኑ ትልቅ ጥያቄን ያስነሳል። በትምህርት ስርዓቱ እና በገበያው ፍላጎት መካከል እንዴት እንደዚህ አይነት አለመጣጣም ሊመጣ ቻለ? የሚል። በትምህርት እና በኢንዱስትሪው መካከል ባለው ያለመተሳሰር ችግር ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምርታማነት (productivity) ታጣላች። እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ ፈተናው የአቅም ሳይሆን ትምህርት እና ስራን፣ ፖሊሲ እና ተግባርን እና ስልጠናን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያስተሳሰር መስመር አለመዘርጋቱ ነው። በአፍሪካ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት እየሰሩ ያሉት ከኢንዱስትሪው ርቀው ነው ማለት ይቻላል ይህም ተመራቂዎች የስራ ገበያው የሚፈልገውን ክህሎት እና አቅም እንዳይታጠቁ አድርጓል። ሌላኛው ፈተና በአፍሪካ የተንሰራፋው ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ ነው። አንዳንድ ጥናቶች የአፍሪካን ኢ-መደበኛ የኢኮኖሚ ድርሻ እስከ 85 በመቶ ያደርሱታል። ይህም ዜጎች ክህሎታቸውን እንዳያሳድጉ እና የብቃት ማረጋገጫን እንዳያገኙ እክል ፈጥሯል። የአፍሪካን ክህሎት ምህዳር በመቀየር የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ላይ የጋራ ትብብርን ማጠናከር አበይት ትኩረቱ ያደረገ ሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። “አፍሪካውያንን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት የሚያፋጥኑበትን ክህሎቶች ማስታጠቅ” የሳምንቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሁነቱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው። በሁነቱ መክፈቻ ላይ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ እና የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የልማት ተቋማት አመራሮች፣ መምህራን፣ ኢኖቬተሮች፣ የወጣት ተወካዮች እና የልማት አጋሮች ተሳትፈውበታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክህሎቶች ለሀገራዊ ግቦችና ለአህጉራዊ የ2063 የልማት አጀንዳዎች መሳካት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ናቸው። ኢትዮጵያ ለክህሎት ልማት በሰጠችው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ነው ብለዋል። ክህሎት መር የፖሊሲ እርምጃችን ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ የስራ ፈጣሪነት ባህልን በንቃት እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እና እድገት እንዲያመጡ የሚያስፈልጋቸውን ስልጠና፣ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ እያመቻቸ መሆኑን አመላክተዋል። በስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትብብር የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው የህዝባችንን አቅም ወደ ውጤታማ፣ አሳታፊ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ የሥራ ኃይል መለወጥ አለብን ብለዋል። ክህሎት የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል። የክህሎት ልማት ለአሳታፊ ዕድገትና ለተገቢ የሥራ ዕድሎች ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዕቅድ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። አባል ሀገራት ሀገራዊ ለውጦችን ከአህጉራዊ ፍላጎቶች ጋር ለማጣጣም በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የተሻለ፣ ፈጣን እና ይበልጥ አሳታፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለውን የለውጥ አቅም መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። የፖሊሲ ወጥነትን እና ቀጠናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ክህሎት ክፍተትን መሙላት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለክህሎት ልማት መጠቀም እና በአጀንዳ 2063 አማካኝነት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ ላይ ውይይት ይደረጋል። በሳምንቱ የሚኒስትሮች እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች፣ የክህሎት አውደ ርዕዮች እና የገበያ ትስስር ሁነቶች እንዲሁም የወጣቶች እና የስራ ፈጣሪዎች ፎረም እንደሚካሄድ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፎረሙ የአፍሪካ ኢኖቬተሮች የስራ ውጤቶች ይቀርቡበታል። የክህሎቶች ሳምንት ተሳታፊዎቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና በኢኖሼሽን ማዕከላት ውስጥ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ይጎበኛሉ። ሳምንቱ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአፍሪካ ክህሎት ልማት አስመልክቶ የጋራ አቋም መገለጫ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ለአህጉሪቷ የኢንዱስትሪ እና ክህሎት አጀንዳ ተጨባጭ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል። የመጀመሪያው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት እ.አ.አ ኦክቶበር 2024 በጋና አክራ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ክህሎቶች ፈተናዎች ክፍተቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲሁም ምህዳሩን ለመቀየር አህጉሪቷ በዘርፉ አብዮት ያስፈልጋታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን የስነ ህዝብ ትሩፋት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ክህሎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል መቀየር ይገባል። ይህን ለማድረግ የተቀናጀ እና አህጉር አቀፍ ጥረት ያስፈልጋል። የሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ስኬት የሚለካው በንግግሮች እና በጋራ መግለጫዎች ሳይሆን ራዕዮቹን በአፍሪካ ትምህርት ተቋማት፣ ስልጠና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች በተጨባጭ በመቀየር እና ውጤት በማምጣት ነው። በዚህ ረገድም መንግስታት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች እና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የአፍሪካን የክህሎት ልማት መጻኢ ጊዜ በውድድር፣ በፈጠራ እና አሳታፊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊገነቡ ይገባል። አፍሪካ ወጣቶቿ በክህሎት እና በእውቀት ከታጠቁ አፍሪካ የተለመቻቸውን ግዙፍ እቅዶች እና ትላልቅ ውጥኖች ባጠረ ጊዜ እንዲሳኩ ያስችላል።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 1935
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2235
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3107
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 3201
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 1208
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 815
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 6656
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5127
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ባሕር በር -የታሪክና የእድገት ስብራት ወጌሻ
Nov 5, 2025 418
ባሕር በር የታሪክ እና የእድገት ስብራት ወጌሻ በቀደሰ ተክሌ የምሥራቅ አፍሪካዋ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ስሟ ገኖ እንዲነሳ ካደረጓት መካከል የሰው ዘር መገኛነት፣ የራሷ የሆነ የአስተዳደር ሥርዓት፣ የዘመን አቆጣጠር፣ ቋንቋና ፊደል ያላት ሉዓላዊት ሀገር መሆኗ ተጠቃሽ ነው ። የገናና የጥበብ ባለቤት መሆኗን አክሱም እና ላሊበላ ዛሬም ቆመው ይመሰክሩላታል። በጥንት ጊዜ ወደብ የስልጣኔ ተጽዕኖ ፈጣሪነት መገለጫ በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያም ስሟ ጎልቶ ይነሳ ነበር። ወደብ ዓለምን እርስ በእርስ ከማስተሳሰር ባለፈ የግብይት የጀርባ አጥንት ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፤ ዛሬም እያገለገለ ይገኛል። ሀገራት አዋጭ የንግድ ስትራቴጂ ቀይሰው የተለያዩ ወደቦችን የመጠቀም ልምዳቸው በታሪክ ውስጥ ጎልቶ የሚነሳ ነው። የንግድ ሥርዓታቸውን በወደብና በየብስ ከሚያከናውኑ የዓለም ሀገራት መካከል ደግሞ ኢትዮጵያ አንዷ ናት። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመነ መንግስታት የተለያዩ ወደቦችን በባለቤትነት አስተዳድራለች። ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስከ ደርግ መንግስት ድረስ አዱሊስ፣ አሰብ፣ ዘይላ፣ ምጽዋና ሌሎች ወደቦችን ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ትገለገል ነበር። ይሕ የኢትዮጵያ የወደብ ባለቤትነት ታሪክ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ የዘለቀ እንደነበር በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሰቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምሕርት ክፍል መምሕር አጥናፉ ምትኩ ይናገራሉ። ወደብ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ እንደሆነም አውስተዋል። በታሪክ ኩነት ውስጥ የተፈጠረ ሴራና ተንኮል ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። ይሕም ከሆነ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። በዚሕም ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ በየዓመቱ ብዙ ቢሊዮን ብር እየከፈለች የወጪ እና ገቢ ንግድን የማንቀሳቀስ እዳ ተጭኖባታል። ይሕም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ጉዳዮች አንዱ ሆኖ ዛሬ ድረስ ዘልቋል። የወደብ አገልግሎት ነጻነት ማጣት፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መጨመር፣ ማዳበሪያን ጨምሮ አስፈላጊ ግብአቶች መዘግየትና በወቅቱ አለመድረስ፣ በዚሕም የሰብል ልማት ስራዎች ላይ ችግሮች መስተዋል ከባሕር በር ባለቤትነት እጦት ጋር የመያያዝ እድላቸው ሰፊ ነው። እነዚሕ ችግሮች ደግሞ ተደማምረው ለኑሮ ውድነት መፈጠር አስተዋጾኦ ይኖራቸዋል ማለት ይቻላል። በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠረው ስብራት እያስከተለ ያለው ጉዳት አሁን ላይ ለኢትዮጵያ የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ በታሪካዊ ዳራ መሠረት መጠገን ያስፈልጋል። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ከ130 ሚሊዮን ያሻቀበ የሕዝብ ቁጥር፣ የኢኮኖሚ ዕድገትና ሀገራዊ የቆዳ ስፋት ገፊ ምክንያቶች ከሚባሉት ውስጥ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል ከዚሕ ቀደም የነበረው የሀገሪቱ ባሕር በር ባለቤትነት ማስረጃ ዛሬ ላይ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። መንግሥት የጀመረው የባሕር በር ባለቤት የመሆን ጥያቄ በመሬት ተዘግቶ የመኖር ታሪክ እንዲያበቃ የሚያደርግና በዓለም አቀፍ ሕግ ተፈጥሮን በጋራ ተጠቅሞ የመልማት መብትን የሚያስጠብቅ መሆኑ እውን ነው። ለሦስት አስርት ዓመታት ታፍኖ የቆየው የቀይ ባሕር ባለቤትነት ጥያቄ የመንግስት ቁርጠኝነት እንዳለ ሆኖ ዜጎችም አጥብቀው በመያዝ መልስ እስኪያገኝ ድረስ መስራት ይጠበቃል። የሀገርና የሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆነው የባሕር በር እስኪሳካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት ከሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚጠበቅ መምሕር አጥናፉ ይገልጻሉ። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆን የታሪኳና ዕድገቷ ወጌሻ ነው ያሉት መምሕር አጥናፉ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለመጠቀም የሚያስችላት ታሪካዊ መብት አላት። ይሕን ታሪካዊ መብቷን የምታረጋግጥበት ትልቁ መሣሪያ ደግሞ ያላት ጠንካራ የዲፕሎማቲክ አቅሟ ነው። ከዓለም ሀገራት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ተናግሮ ለማሳመን እውነታን ለመግለጽ የሚያስችላት ነው። ይሕንንም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓለም ፊት አረጋግጣለች። ይሕን የሕዳሴ ድል በቀይ ባሕር ላይ የማትደግምበት ምንም ምክንያት አይኖርም። በተለይ ኢትዮጵያ ያላት የጋራ ተጠቃሚነት መርሕ በዓለም ላይ ተቀባይነት ያለውን ሀሳብ ይዛ እንድትቀርብ እያስቻላት ይገኛል። ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጠው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ ተፈጥሮን ተባብሮ በማልማት እንጠቀም የሚል መሠረት ያለው ነው። መምሕር ይስሐቅ ንጉሤ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሰቲ የምጣኔ ሀብት መምሕር ሲሆኑ የባሕር በር ጉዳይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማጠንጠኛ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ የባሕር በር ማጣቷ በፈጣን ዕድገቷ ላይ መሰናክል ሆኖ መዝለቁን ተናግረዋል። በተለይ የዓለም ሀገራት ከፍተኛው የንግድ፣ የኢኮኖሚና ሀብት እንቅስቃሴ የሚታይበት እና የሀገራት የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት የቀይ ባሕር ቀጠና ላይ ያለውን አብሮ የመስራትና ከማደግ ዕድል ኢትዮጵያ ያለአግባብ መገለሏን ያነሳሉ።ይሕም በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገትና በሌሎች ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደሆነ ነው ያገለጹት። የባሕር በር ጥያቄ የምጣኔ ሀብት ዕድገትን በማሳለጥ ሀገሪቱ ከልመና ለመውጣት ያላትን ዕድል እንድትወስን ያስችላታል የሚሉት መምሕሩ ፤ለስኬቱም የተጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማጠናከር እንደሚገባም ነው የገለጹት። እንደ መምሕሩ ገለጻ ከዓለም አቀፍ መርሆችና ስምምነቶች እንዲሁም ካለን መልከአ ምድራዊ አቀማመጥና ታሪክ አንጻር ለኢትዮጵያ የባሕር በር ተገቢ ነው። ይሕ እንዲሳካም መንግስት ካሳየው ቁርጠኝነት በተጨማሪ ሁሉም በተቀናጀ መንገድ የሚያደርገውን ጥረት ማጠናከር ይኖርበታል። መንግስት የዘመናት የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የባሕር በር ጉዳይ በግልጽና በይፋ መረጃ በመስጠት ዓለም አቀፍ አጀንዳ እንዲሆንም ጭምር እያደረገ ያለውን ጥረትንም አድንቀዋል። ታሪክ በኩነቶች መካከል መጥፎም መልካም ሆኖ ያልፋል። በታሪክ የባሕር በር ባለቤትነታችን የገጠመውን ስብራት ለመጠገን የሚያስችል ወጌሻ ያስፈልጋል። በታሪክ ሂደት መልካሙ ወደ መጥፎ ሁኔታ እንደሚቀየር ሁሉ የተበላሸን ወደ መልካም የመቀየር ዕጣ ፈንታ ያለው የዛሬው ትውልድ ላይ ነው። ለእዚሕ ደግሞ ትውልዱ በሕዳሴው ግድብ ከመንግስት ጎን ሆኖ ያሳየውን አንድነትና ሕብረት በባሕር በርም መድገም አለበት። ታሪካዊ ዳራን፣ ዲፕሎማሲን፣ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታና ሕግን ተከትሎ በአብሮነት ከተሰራ ያኔ የተበላሸው ይቃናል፤ ያጣነውን እናገኛለን። "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" ዓይነት እንስሳዊ ግብር በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊሰማ አይገባም፤ መሰማትም አይኖርበትም። ኢትዮጵያ ብታደግ ለቀጣናው ኩራት፤ ለአፍሪካም ልዕልና እንጂ ጥፋት የሚያስከትል እንዳልሆነ መገንዘብና የትብብር ልማትና ዕድገትን ባሕል ማድረግ ሊለመድ ይገባል። ሰላም!
የዳሰነቾች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ''ጀለባ''
Oct 30, 2025 976
የዳሰነች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ''ጀለባ'' (በጣፋጩ ሰለሞን ከጂንካ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ዳሰነቾች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በአብሮነት ተጎዳኝተው ይኖራሉ። የብሔረሰቡ አባላት ዋነኛ መተዳደሪያ ከብት እርባታ ሲሆን፤ ከከብት እርባታው ጐን ለጐን በዝቅተኛ ደረጃ በግብርናና በዓሳ ማስገር ስራ ይተዳደራሉ፡፡ ዳሰነቾች በሰሜን ከሐመር፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ በምስራቅ ከቦረና በስተ ምዕራብ ደግሞ ከኛንጋቶም ማህበረሰብ ተጎራብተው ይኖራሉ። ዳሰነቾች ከኩሽቲክ የቋንቋ ነገድ የሚመዘዝ ''አፍ ዳሰነች'' የተሰኘ የመግባቢያ ቋንቋም አላቸው። ዳሰነቾች የተለየ የአለባበስ፣ የአጋጌጥ፣ የቤት አሰራር እና የባህላዊ የሙዚቃ ስልተ ምትን ጨምሮ አስደማሚ ባህሎች እና ማራኪ የመልክዓ ምድር አቀማመጥን የታደሉ ናቸው። ዳሰነቾች ከሚታወቁባቸው አስደማሚ ባህሎች ውስጥ አንዱ የሆነው አለመግባባቶችን በውይይት የሚፈቱበት የ''ጀለባ''ስርዓት ተጠቃሽ ነው። ይህ ስርዓት ግጭቱ ቂምና ቁርሾ በማይሻገርበት መልኩ በዘላቂነት የማስወገድ አቅም ያለው ሲሆን የማይናወጥ ሰላምና ወንድማዊ ትስስር እንዲጠናከርም ሚናው የጎላ ነው። ዕሴቱ የዳሰነቾች የአኗኗር ቁመና የሚለካበትና የሚመዘንበት መጻኢንም የሚተለምበትም ጭምር ነው። ስለሆነም በዳሰነቾች ዘንድ ቂም መያዝ አሎሎ ተሸክሞ እንደመዞር ይቆጠራል ነው የሚባለው። የባህሉ ተመራማሪ ሊዮን አርሎት 'ጀለባ'' የተሰኘው ባህላዊ ዳኝነት ከአካባቢው ሰላም አልፎ ለቀጠናው ወንድማማችነት መጠናከር ትልቅ ሚና ያለው የፍትህ ስርዓት መሆኑን ያነሳሉ። በ''በጀለባ'' ስርዓት ባህላዊ የዳኝነት አሰጣጥ እርከኖች እንዳሉ ጠቅሰው፥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ''ኖሞ'' የተሰኙ ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው በማቅናት የግጭቱን መንስኤ በማጣራት ''ቶሎል'' ለተሰኙ ሌሎች ሽማግሌዎች የሚያሳውቁበት አሰራርም አላቸው። እንደ ግጭቱ ቅለትና ክብደት ''ቶሎል'' በተሰኙ ሽማግሌዎች ተለይቶ ቀለል ያለው ''ካባና'' በተሰኙ ዳኞች ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን፥ ጉዳዩ ከበድ ያለ ከሆነ ደግሞ የመጨረሻው ውሳኔ ''አራ'' በተሰኙ ዳኞች ይሰጣል። ከነፍስ ማጥፋት በስተቀር ሁሉም ውሳኔዎች ''አራ'' በተሰኙ ዳኞች እልባት ያገኛሉ። የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሲከሰት ግን ጉዳዩን ለመንግሥት አሳልፎ በመስጠት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል ። ነፍስ ያጠፋው ሰው የእርምት ጊዜውን አጠናቆ ማህበረሰቡን ለመቀላቀል ሲወስን ባህላዊ የዕርቅ ስነ-ስርዓት ተዘጋጅቶ በዳይና ተበዳይ ይቅር የሚባባሉበትም ስርዓት እንዳለ የባህሉ ተመራማሪ ይናገራሉ። በዳሰነቾች ባህል ልዩነቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ በዘላቂነት መንገድ የመፍታት ዘመናትን የተሻገረ ድንቅ ዕሴት መኖሩን የሚያነሱት የብሔረሰቡ አባል አሸቴ ነካሲያ፤ “በዳሰነች ብሔረሰብ ቂም መያዝ አሎሎ ተሸክሞ እንደመዞር ይቆጠራል'' ይላሉ። በዳሰነቾች አለመግባባቶች በውይይት የሚፈቱበት ስርዓት እንዳለ ጠቅሰው፥ ''ናብ'' በተሰኘው የዳኝነት ስፍራ አለመግባባቶች ውለው ሳያድሩ እልባት ያገኛሉ ብለዋል። ሌላው የብሔረሰቡ አባል ሎቶያቡስ ሎኪሰሬሬ በበኩላቸው የባህል መሪዎች የተጣላን ማስታረቅ፣ ትውልዱን የመግራትና በስነ-ምግባር የማነፅ ኃላፊነት እንዳላቸው ጠቅሰዋል። ''ማንም ሰው ከባህል መሪዎች ትዕዛዝ አያፈነግጥም'' የሚሉት አቶ ሎቶያቡስ፥ ሁሉም እርስ በእርስ በመከባበር እና ችግሮች ሲኖሩ በውይይት በመፍታት አብሮነቱን ያጠናክራል ብለዋል። ወጣቱ ለባህል መሪዎች ታዛዥ ነው የሚሉት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ የብሔረሰቡ አባል ሎሲያ ሎብቻ ወጣቶች ለአካባቢው ሰላም ዘብ እንዲቆሙ፣ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በፍቅር እንዲኖሩ በማስተማር ወጣቱን በስነ-ምግባር የማነፅ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ በበኩላቸው የዳሰነች ህዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ከወረዳው አልፎ ለቀጠናው ሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። የብሔረሰቡ ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት ትውልዱን በመግራት በስነ- ምግባር የታነፀ ዜጋ እንዲፈጠር እንዳደረገም አስረድተዋል። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህርና ተመራማሪ አጎናፍር ሰለሞን፤ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቶች ለዘመናዊው የፍትህ ስርዓት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ቅጣት በመጣል ጥፋተኝነት እንዲሰማ የሚያደርጉ ሳይሆኑ፤ እውነተኛ ይቅርታን የሚያሰፍኑና ለአብሮነት የሚበጁ ዕንቁ ባህሎች እንደሆኑም አብራርተዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎቹ በግለሰብ ተጠቃሚነት ላይ ሳይሆን በማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ በመሆናቸው ከዘመናዊው የፍትህ ስርዓት በይበልጥ ለአብሮነት መጠናከር አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ገልጸዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎቹም ለሀገራዊ መግባባት ሚናቸው የላቀ በመሆኑ፥ እሴቶቹ ተጠብቀው፣ ለምተውና ጎልብተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ መስራት እንደሚገባም መክረዋል። ሀገራችን ቂምና ቁርሾን የወለዱ ያለመግባባቶች በዘላቂነት በሰለጠነና ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ሁሉንም ያሳተፈ ስራ እየሰራች እንደሆነ ያነሱት መምህርና ተመራማሪው አጎናፍር ሰለሞን ዕሴቶቹ በማህበረሰቡ ዘንድ ካላቸው ተቀባይነት እንዲሁም ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ከማገዝ አንጻር ጉልህ ሚና ስለሚኖራቸው መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።