ቀጥታ፡

ኒውካስትል ዩናይትድ ብሩኖ ጉማሬሽን ለአርሰናል ለመሸጥ ተስማማ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የኒውካስትል ዩናይትዱ የአማካይ ተጫዋች ብሩኖ ጉማሬሽ ሻምፒዮኑ አርሰናልን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

ጣልያናዊው የስፖርት ጋዜጠኛና በእግር ኳስ የዝውውር ዜናዎቹ የሚታወቀው ፋብሪዚዮ ሮማኖ ኒውካስትል ተጫዋቹን ለመሸጥ መስማማቱን ገልጿል።’

የጉማሬሽ የዝውውር ዋጋ 75 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑንም አመልክቷል።

የ28 ዓመቱ ተጫዋች እ.አ.አ ጁላይ 2026 ላይ አርሰናልን ለመቀላቀል በግሉ ተስማምቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

አሁን ላይ ሁለቱ ክለቦች በዝውውሩ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የተንዛዛውን የዝውውር ጉዳይ እንዲቋጭ አድርጎታል።

ጉማሬሽ እ.አ.አ በ2022 ከሊዮን ወደ ኒውካስትል ዩናይትድ በመዘዋወር ሲጫወት ቆይቷል።

ተጫዋቹ መድፈኞቹን መቀላቀሉ የቡድኑን የአማካይ ክፍል ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።

ብሩኖ ጉማሬሽ ከክሪስቶስ ዞሊስ እና ኢላን ሜስሊዬር በመቀጠል አርሰናል በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የሚቀላቀል ሶስተኛ ተጫዋች ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም