ቀጥታ፡

በክልሉ የገበያ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በማጠናከር የኑሮ ጫናን ለማቃለል ትኩረት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፡-በክልሉ በተያዘው የበጀት ዓመት የገበያ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በማጠናከር እንዲሁም የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት እንዲሻሻል በማድረግ የኑሮ ጫናን ለማቃለል በትኩረት እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ በበጀት አመቱ በሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በያዝነው የበጀት አመት በክልሉ የኑሮ ጫናን ለማቃለል የሚያስችሉ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይከናወናሉ ብለዋል።

በተለይም የገበያ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በማጠናከር የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት እንዲሻሻል የማድረግ ስራዎች የላቀ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።

ሸማቹን ማህበረሰብ ለአላስፈላጊ ወጪና ለእንግልት የሚዳርጉ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪዎች የሚያደርጉ ነገዴዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ይሰራል ነው ያሉት።

የምርት አቅርቦትን በማሻሻል፣ የገበያ ሰንሰለት ማነቆዎችን በመፍታትና ህገ-ወጥ ንግድን የመቆጣጠር ስራዎችም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የቅዳሜና እሁድ ገበያን በማጠናከር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በቀጥታ ለሸማቹ በማቅረብ የኑሮ ጫናን ለማቃለል እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም