ቀጥታ፡

የምክክር ጉባዔው ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ዕድል የፈጠረ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ዕድል የፈጠረ መሆኑን የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል።

በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪሎችም በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛል።

በብሪታንያ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የጋራና አካታች በመሆኑ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው።


 

በብሪታኒያ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባት ኡስታዝ ሙክታር ጀማል  እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ኢትዮጵያ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ያስፈልጋት የነበረ ታላቅ እርምጃ ነው።

ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ሂደት ነው ብለዋል።

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪ የሃይማኖት አባት ፓስተር አረጋ ሽፈራሁ በበኩላቸው፤ የምክክር ሂደቱ አካታችና አሳታፊ መሆኑንና እያንዳንዱ ተመካካሪ ሃሳቡን ያንፀባረቀበት ሁሉም በኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላምና ልማት እየመከረ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም