ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
Mar 23, 2026 60
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጋቸው የመጀመርያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል። ግብ ጠባቂዎች መቲ ረታ (ልደታ )፣ ኑዳ ሁሴን (አዲስ ከተማ ) እና ኢትዮጵያ ለማ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ማንጠግቦሽ አድማሱ (አርባምንጭ ከተማ )፣ ኤልሻዳይ ዮሴፍ ( ጉለሌ) ፣ ሴና ኤርሚያስ (ለሚኩራ )፣ ቤተልሄም ጌታቸው (ንፋስ ስልክ ላፍቶ)፣ መድሃኒት አለሙ (አርባምንጭ ከተማ) እና መሰረት ጌታቸው (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ) በተከላካይ መስመር የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው። በአማካይ ክፍል ኑአሚን ከበደ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ኢክራም ሚፍታህ (ደራርቱ ቱሉ አካዳሚ )፣ ትዕግስት ተሾመ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ሊያም ዳንኤል (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)፣ ቢታኒያ አስተረፍ (ሲዳማ ቡና) ፣ ሊዲያ ሰለሞን (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) እና ምህረት ወሰኑ (ሸገር ከተማ) በጥሪው ተካትተዋል። ሲርይ ተሾመ (ጉለሌ)፣ ኦጁሉ ኦዶንግ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ምህረት አየለ (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ማህሌት ደመቀ (ሐምሌ 19 ክለብ)፣ እመቤት ዘካሪያስ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ሙሉ አበራ (ለሚ ኩራ) እና ሰሊና ናግዋ (ጉለሌ) በአጥቂ መስመር ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። 10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዋን በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
ተቋማዊ ሪፎርሞች የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Mar 23, 2026 64
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ) ፦ተቋማዊ ሪፎርሞች የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተገኝተን በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ዐበይት የሪፎርም እና የማስፋፊያ ሥራዎችን ተመልክተዋል። በዚህ ወቅት ቢሮው የሀገር አቀፍ ስማርት ሲቲና ስማርት ጤና አገልግሎት ራዕይን መነሻ በማድረግ ተቋሙን የማዘመን ሥራ በስኬት እያከናወነ ነው ብለዋል። ለዲጂታላይዜሽን በተሰጠው ትኩረትም ተቋሙን ወረቀት አልባ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋት ላይ ይገኛል ነው ያሉት። ከባሕር ዳር የኮሪደር ልማት ጋር የተናበበ ጽዱ የግቢ ማስዋብና ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀትም ጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን መመልከታቸውንም ጠቁመዋል። ዘመናዊ የግንባታ አሠራርን በመጠቀም በነባሩ የቢሮው ሕንፃ ላይ ማራኪና ምቹ የሥራ ቦታዎች በጥራት ተገንብተዋል። ተቋማዊ ሪፎርሞች የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል ሲሉ ነው የገለጹት። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ አድርጓል
Mar 23, 2026 52
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አከናውኗል። ብሔራዊ ቡድኑ ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቷል። ቡድኑ ነገ ረፋድ 4 ሰዓት ከ40 ላይ ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሞሮኮ ጉዞ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች። የመጀመሪያው ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ይካሄዳል።
የግብርና ምርታማነትን ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የፋይናንስ አቅርቦት ምኅዳር እየተፈጠረ ነው
Mar 23, 2026 63
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የፋይናንስ አቅርቦት ምኅዳር እየተፈጠረ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ። የግብርና ሚኒስቴር ከክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የቢሮ ኃላፊዎችና በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከተሰማሩ ባለኃብቶች ጋር በግብርና ኢንቨስትመንት አፈጻጸም ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በዚሁ ወቅት የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፤ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የግብርና ምርታማነት በማስቀጠል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የግል ባለሃብቱ ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ 21 ሚሊየን ሔክታር የእርሻ መሬት እየለማ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በቀጣይም መታረስ የሚችል 38 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት የአነስተኛ ባለይዞታ አርሶ አደሮችንና ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት አቅምን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም አዳዲስ የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን የእርሻ ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ምኅዳር እየተፈጠረ መሆኑን አስገንዝበዋል። የእርሻ ኢንቨስትመንት የፋይናንስ ማነቆዎችን መፍትሔ ለመስጠት የግብርና ባንክ ማቋቋም የሚያስችል የመጨረሻ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ መደረሱን አስታውቀዋል። በቅርቡም በሙከራ ትግበራ ደረጃ በተለያዩ ወረዳዎች የአርሶ አደሮች የፋይናንስ ብድር አቅርቦት በይፋ እንደሚጀመር አንስተዋል። በተጨማሪም የልማት አጋሮችና የፋይናንስ ተቋማት ለኢትዮጵያ የግብርና ሥርዓት መሻሻል የገንዘብ ብድር የሚያቀርቡበትን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የፋይናንስ አቅርቦት ምኅዳር እየተፈጠረ እደሚገኝ አብራርተዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የእርሻ ኢንቨስትመንት አልሚ ባለሃብቶች የሚቀርብላቸውን የገንዘብ ብድር ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። ከተሳታፊዎች መካከል አቶ በለው ወንድም የእርሻ ኢንቨስትመንትን ለማሻሻል የሚደረገው የፋይናንስ አቅርቦት ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ጠቃሜታ አለው ብለዋል።
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት የሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል
Mar 23, 2026 96
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ከባለድርሻ አካላትጋር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ስም እንዲሁም የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተልን ለመወሰን የተዘጋጀውን የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የምርጫ ሂደቱን በስኬት ለመምራት ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበራትና ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው። በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የዕጩዎች ምዝገባ በማጠናቀቅ በየምርጫ ክልሉ ዕጩዎችን ይፋ በማድረግ ለሚቀርቡ አቤቱታዎች አፋጣኝ ምላሽ እየተሰጠ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በ'ምርጫዬ' የዲጂታልና ማኑዋል አማራጭ መራጮች ድምፅ መስጠት የሚያስችላቸውን ምዝገባ እያካሄዱ መሆኑን ጠቁመው፤ በ46 ሺህ 757 የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች መሰራጨቱን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በነፃ የአየር ሰዓት ድልድል፣ በፓርቲዎች የክርክር መድረክና በአስቻይ የፀጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል። ለመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለሚሰጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ተገቢውን የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በቦርዱ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ማስተባበሪያ ክፍል ኃላፊ ቀነኒ ኢንሰርሙ እንደገለጹት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ስም እንዲሁም የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ምርጥ ተሞክሮዎች የተቀመሩበት ነው ብለዋል። ቦርዱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ወቅት በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚሰፍረውን የዕጩዎች ቅደም ተከተል ለመወሰን በምርጫ ክልሎች ለ10 ቀናት የሚቆይ የዕጣ አወጣጥ ሥርዓት ያካሂዳል።
ፖለቲካ

የክልሉ ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
Mar 23, 2026 109
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት ሕዝቡ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር ሚናውን መወጣት አለበት። በክልሉ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። መንግሥት ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምርጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ ከወዲሁ የምርጫ ካርድ መውሰድ እንዳለበት አንስተዋል። ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የሀረሪ ብሔረሰብ ተወላጆች በሚመርጡባቸው የምርጫ ጣቢያዎች አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በኦሮሚያ ክልል (አዳማ፣ ጭሮ፣ ኮምቦልቻ ፣ ጉርሱም፣ ፈዲስ፣ ደደር እና ሃሮማያ)፣ ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ፣ እና በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙም መልዕክት አስተላልፈዋል። በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ምርጫው በታቀደለት የጊዜ ገደብ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።
ሀገራዊ ምክክር በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ ምን ፋይዳ አለው?
Mar 23, 2026 127
በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት መካከል ላለመግባባታችን ምክንያት የሆኑ እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት ምክክር እንዲደረግባቸው በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የሥነ-ምክክር መዛግብት የሚያስረዱት ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን ሀገራዊ ጉዳዮች በንግግር እንዲስተካከሉ እንደሚረዳ ነው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያስታወቀው፡፡ ከዚህ አኳያ እኛ ኢትዮጵያውያን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ሂደት በግለሰብ ደረጃ እንዴት ተጠቃሚ እንደሚያደርገን የሚከተሉት ሃሳቦች ከብዙ በጥቂቱ ያስረዳሉ፡፡ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት፡ ግጭቶች በንግግር የተፈቱበት ዓውድ ዜጎች ተገማች የሆነ ሕይወትን እንዲመሩ ያስችላቸዋል፡፡ ይህም ዜጎች በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ያለ ስጋት ለተለያዩ ዓላማዎች እንዲንቀሳቀሱ ትልቅ ነፃነትን ያጎናፅፋቸዋል፡፡ የሥራ ዕድሎችን ማስፋት፡ በንግግር መፈታት የሚገባቸው ግጭቶች እዚህም እዚያም መስተዋላቸው ትልልቅ የሥራ ዕድሎችን ሊፈጥሩ የሚችሉ የኢንቨስትመንት መስኮችን እንዲከስሙ አድርጓል፡፡ ይህም በሀገራችን ሙዓለ ንዋይ የሰለጠነ እጅግ ትኩስ እና አምራች የሰው ኃይል እውቀቱንና ልምዱን ለሀገሩ እንዳያበርክት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መጎልበት፡ ከሀገራዊ ምክክር ሂደት ተጠባቂ ውጤቶች እና ምክረ-ሀሳቦች አንዱ የተለያዩ ተቋማት የደንበኛ አያያዝ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ነው፡፡ ይህም ዜጎች በሀገራቸው ተቋሞች ላይ ባለቤትነትን በማዳበር ለጋራ ችግሮቻቸው የጋራ መፍትሔዎችን እንዲያበጁ መንገድ ይከፍታል፡፡ የፀጥታ ሥጋትን መቀነስ፡ ዜጎች በሀገራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈጠሩ ፖለቲካዊ ውጥንቅጦች የፀጥታ ሥጋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱም ዜጎች በዕለት ተዕለት ህይወታቸው የሚገጥማቸውን የፀጥታ ስጋቶችን ከሥር መሰረቱ ለመፍታት በመነጋገር የተለያዩ የመፍትሔ ሀሳቦች እንዲመነጩ ያስችላል፡፡ የሥነ-ልቦናዊ ጫናዎችን መቀነስ፡ ግጭቶች በባህሪያቸው ላልተፈለገ የሥነ-ልቦና ጠባሳ እና ጫና ይዳርጋሉ፡፡ በግጭት ዓውድ ውስጥ የሚኖሩም ሆነ ግጭት በሌለበት የሀገራችን አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የዚህ ገፈት ቀማሽ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ባሉን የሃሳብ ልዩነቶች ዙሪያ በግልፅ እና በእውነት ለመነጋገር መፍቀዳችን መሰል ችግሮቻችን እንዲቀረፉ በእጅጉ ይረዳናል ሲልም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩዎች ስም እና የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው
Mar 23, 2026 210
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የስም እና የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ምርጫ መሪዎች የሚመረጡበት ብቻ ሳይሆን የጸጥታ አካላት ሙያዊ ብቃታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ቦርዱ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ እያከናወነ ይገኛል። በሂደቱም ከሲቪክ ማህበራት፣ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙሃን እና ጸጥታ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች ምዝገባ ተጠናቅቆ በየምርጫ ክልሎች የእጩዎች ስም ዝርዝር በይፋ መለጠፉን የተናገሩት ሰብሳቢዋ፣ለሚቀርቡ ቅሬታዎችም ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን፣ ከአራት ቀን በፊት በተደራጀ መረጃ መሰረትም ከ18 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት መመዝገባቸውን አብራርተዋል። የምዝገባ ሂደቱ በዲጂታል እና በማኑዋል እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ሰብሳቢዋ፤ የሲስተም እና የኔትወርክ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ምዝገባው በማኑዋል እንዲካሄድ መደረጉን ገልጸዋል። በ46 ሺ 757 የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውንም ተናግረዋል። በቦርዱ ከተመዘገቡ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን 2 ሺህ 98 ዕጩዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆኑ 8 ሺህ 736 ደግሞ የክልል ተወካዮች መሆናቸው መገለጹ ይታወቃል። 73 እጩዎች ደግሞ በግል ለመወዳደር መመዘገባቸውም እንዲሁ።
ምርጫ መሪዎች የሚመረጡበት ብቻ ሳይሆን የጸጥታ አካላት ሙያዊ ብቃታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት ነው
Mar 23, 2026 186
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ምርጫ መሪዎች የሚመረጡበት ብቻ ሳይሆን የጸጥታ አካላት ሙያዊ ብቃታቸውንና ገለልተኝነታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት ወሳኝ መድረክ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ ገለጹ። መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ለአገር አንድነትና ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለፖሊስ መኮንኖች ያዘጋጀው የአመራር፣ የሰብአዊ መብቶች እና የምርጫ ደህንነት ስምሪት ላይ ያተኮረ ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ እንደገለጹት፤ ምርጫ መሪዎች የሚመረጡበት ብቻ ሳይሆን የጸጥታ አካላት ሙያዊ ብቃታቸውንና ገለልተኝነታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት ወሳኝ መድረክ ነው። በዚህም ቦርዱ በአሁን ወቅት ከፌዴራል፣ ከክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊሶችና የጸጥታ አካላት ጋር ተናቦ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል። የምርጫ ጣቢያዎች ደህንነት ጥበቃ፣ የምርጫ ቁሳቁሶች የሚገኙበት ቦታ ደህንነት፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ከዋና መስሪያ ቤት ወደ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በማጀብ የማሰራጨት ስራ በትብብር እየተሰራ እንዳለ ጠቅሰዋል። ምርጫው ፍትሐዊ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፖሊስ ድርሻ ቁልፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም በቂ ዝግጅት ሊኖረው እንደሚገባ ገልጸዋል። በተለይም ሰላማዊ የሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲኖር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ሚዛን ጠብቆ መሥራትና የዜጎችን መብቶች በሥርዓታዊ አግባብ እንዲከበሩ ማድረግ ከፖሊስ የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አንስተዋል። የፖሊስ መኮንኖች በነፃነትና በገለልተኝነት ሥራቸውን በማከናወን የሕዝብ ፍላጎት በሙሉነት እንዲንጸባረቅና የዴሞክራሲ ሂደቱ እንዲጎለብት የበኩላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሥልጠናው በምርጫ ወቅት የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን በብስለትና በብቃት ለመምራት ያግዛል ብለዋል። የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ታምራት ሙሉጌታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሥልጠናው በምርጫ ወቅት የጸጥታ አካላት ሊኖራቸው የሚገባውን ሙያዊ ስነ-ምግባር ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል። ፖሊስ የሕዝብ ደህንነት ጠባቂ በመሆኑ በምርጫ ሂደት ውስጥ የዜጎችን ሰላማዊ የመንቀሳቀስና የመምረጥ መብት አክብረው እንዲሰሩ ስልጠናው ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
በክልሉ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
Mar 23, 2026 170
ጋምቤላ ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦በክልሉ ያለውን ሰላም በማጽናት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ መሠረት ማቲዎስ ገለፁ። የልማት ጥያቄያችን ምላሽ እያገኘ በመሆኑ ተደስተናል−የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች የክልሉ ምክር ቤት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በጋምቤላ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ አፈ-ጉባኤዋ መሠረት ማቲዎስ ጉባኤው በተጀመረበት ወቅት እንዳሉት ፤ በክልሉ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ። ከዚህ ውስጥም የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የተከናወኑት ተግባራት ውጤት የታየባቸው እንደሆኑም ተናግረዋል። ነዋሪው በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በሌሎች የልማት መስኮች የሚያደርገውን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትም ስኬታማ ናቸው ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ምክር ቤቱ ህጎችን ከማውጣትና አተገባበራቸውን ከመከታተል ባለፈ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ በመከታተልና በመቆጣጠር የተሰጠውን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝም ገልፀዋል። ዘንድሮ የሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ያስፈልጋል ነው ያሉት አፈ-ጉባኤዋ። በመሆኑም የክልሉ ነዋሪ በህገ-መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመምረጥና የመመረጥ መብቱን ሊጠቀም እንደሚገባም ነው የተናገሩት። ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ የክልሉን የ2018 የግማሽ በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ፣ የኦዲት ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጨምሮ የምክር ቤቱ ዕቅድ ክንውን ላይ እንደሚወያይም ነው የገለጹት። በተጨማሪም ረቂቅ አዋጆችና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችም ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፓርቲው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየሰራ ነው
Mar 22, 2026 408
አሶሳ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱሰላም ሸንገል ተናገሩ። ፓርቲው የምርጫ ምልክቱን እና የምርጫ ማኒፌስቶውን ዛሬ ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ አስተዋውቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱሰላም ሸንገል በወቅቱ እንደተናገሩት፤ 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲያቸው በትኩረት እየሰራ ይገኛል። ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ መካሄድ እንዳለበት ለፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል። ፓርቲው ለክልል ምክር ቤት እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎችን በወቅቱ ማስመዝገቡን ጠቁመው፥ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ድምጽ ለመስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ በወቅቱ መውሰድ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በፓርቲው ማኒፌስቶ ላይ የክልሉን ጸጋዎች በመጠቀም ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን እና የህዝቦች ትስስርን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ መቀመጡንም ተናግረዋል። የፓርቲው የምርጫ ምልክት "የተጨባበጡ እጆች" እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
በምርጫው በንቃት በመሳተፍ የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮልናል -አካል ጉዳተኞች
Mar 22, 2026 291
ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮልናል ሲሉ የወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች ተናገሩ። በምርጫው ድምጻችንን ለፈለግነው ፓርቲ ለመስጠት የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል -የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ምርጫ ጣቢያዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ ከመሆናቸው በላይ በቅርበት መገኘታቸው የምርጫ ተሳትፏቸውን እንደሚያሳድገውም ተናግረዋል። በወላይታ ሶዶ ከተማ የምርጫ ካርድ ሲወስዱ ኢዜአ ያነጋገራቸው አካል ጉዳተኞች እንደገለጹት በዘንድሮ ምርጫ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱ በምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የወላይታ ሶዶ ከተማ አማኑኤል አካል ጉዳተኞች ማህበር መስራችና ሰብሳቢ አቶ መለሰ ኢዮብ የዘንድሮ ምርጫ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገና ያማከለ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ አካል ጉዳተኞች ካርድ ለመውሰድ እንዳይቸገሩ የምርጫ ጣቢያዎች በቅርበት መገኘታቸውና እነሱን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ብለዋል። በመጪው ጠቅላላ ምርጫ በመሳተፍ ይጠቅመኛል፤ ሀገርንም በተሻለ ያስተዳድራል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ከወዲሁ ተመዝግበው ካርድ እንደወሰዱም ተናግረዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ በላይ ጤቻ በበኩላቸው፤ የምርጫ ጣቢያዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ አድርገው መዘጋጀታቸውና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ የሚስተናገዱበት ሁኔታም መፈጠሩ የምርጫ ተሳትፏችንን ያሳድገዋል ብለዋል። በመሆኑም በተለይ ለአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት የተሻለ ሀሳብ ይዞ ለቀረበ ፓርቲ ድምጻቸውን በመስጠት በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ለአካል ጉዳተኞች ተገቢ ትኩረት ባለመስጠት፣ በአመለካከት ችግርና ምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ባለመሆኑ የምርጫ ተሳትፏችንን ገድቦት ነበር ያሉት ደግሞ አቶ ታረቀኝ ዛዛ ናቸው። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እነዚህ ችግሮች ተወግደው ለአካል ጉዳተኛው ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ አካል ጉዳተኛው መብቱን እንዲጠቀም ያደርጋል ያሉት አቶ ታረቀኝ፣ ለመራጭነት የሚያበቃ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውንም ተናግረዋል። በምርጫው ቀን የተሻለ የፖሊሲ ሀሳብ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥም ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሀን የሚያደርጉትን ክርክር በሚገባ እየተከታተሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ማህበራዊ
ተቋማዊ ሪፎርሞች የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Mar 23, 2026 64
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ) ፦ተቋማዊ ሪፎርሞች የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተገኝተን በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ዐበይት የሪፎርም እና የማስፋፊያ ሥራዎችን ተመልክተዋል። በዚህ ወቅት ቢሮው የሀገር አቀፍ ስማርት ሲቲና ስማርት ጤና አገልግሎት ራዕይን መነሻ በማድረግ ተቋሙን የማዘመን ሥራ በስኬት እያከናወነ ነው ብለዋል። ለዲጂታላይዜሽን በተሰጠው ትኩረትም ተቋሙን ወረቀት አልባ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋት ላይ ይገኛል ነው ያሉት። ከባሕር ዳር የኮሪደር ልማት ጋር የተናበበ ጽዱ የግቢ ማስዋብና ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀትም ጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን መመልከታቸውንም ጠቁመዋል። ዘመናዊ የግንባታ አሠራርን በመጠቀም በነባሩ የቢሮው ሕንፃ ላይ ማራኪና ምቹ የሥራ ቦታዎች በጥራት ተገንብተዋል። ተቋማዊ ሪፎርሞች የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል ሲሉ ነው የገለጹት። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግልጽና ትክክለኛ በመሆን አርዓያነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል
Mar 23, 2026 61
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፡- ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከማንኛውም ተቋም በበለጠ ግልጽና ትክክለኛ በመሆን አርዓያነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር አመዳደብ መመሪያ፣ የመንግስት ከፍተኛ ተቋማት የራስ ገዝነት ሽግግር መመሪያ፣ የራስ ገዝ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥቅል በጀት ድጋፍ ደንብ ዙሪያ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች እና የዘርፉ ተዋንያን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ ሰነዶቹ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1151/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሙያቸው የሰለጠኑ ብቃትና ችሎታ ያላቸው የትምህርት አመራር አባላትን ወደ ሥራ ማምጣት የሚያስችሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መንግሥት የትምህር ተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ አዋጆችን ለማስፈጸም የተዘጋጁት ደንብና መመሪያዎች ተቋማቱ የሚሰጣቸውን ሀብት በአግባቡ ማስተዳደርና ለታለመለት ዓላማ እንዲያውሉ ያስችላሉም ብለዋል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከማንኛውም ተቋም በበለጠ ግልጽ፣ ተዓማኒና እውነተኛ በመሆን አርዓያነታቸውን ማሳየት አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር አመዳደብ መመሪያ በተቋማት ላይ የነበረውን ስር የሰደደና ልማዳዊ አሰራሮቸን የሚያስቀር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው፤ የራስ ገዝ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥቅል የበጀት ደንብ ተቋማት የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡ መጠቀምና የፋይናንስ ምንጫቸውን ማስፋት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ የትምህርት ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት በፍትሐዊነት በመመደብ በዩኒቨርሲቲዎች ተጠያቂነትን ያሰፍናል ብለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር አመዳደብ መመሪያ ተቋማቱን ወደ ራስ ገዝነት የሚያሸጋገር ግልፅ አሰራር መሆኑን ጠቅሰው፤ የአካዳሚክ ነፃነትንም እንደሚያረጋገጥ ተናግረዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች የሚመረጡበት መመሪያ ዕውቀትና ልምድን መሰረት ያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። ደንብና መመሪያዎቹ ጥድፊያ የተሞላበትና ግልፅነት የጎደለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች አሰያየምን ያስቀራሉም ብለዋል፡፡
በክልሉ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለማከም በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የምርመራ ስራ እየተከናወነ ነው
Mar 23, 2026 57
ሀዋሳ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለማከም በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የምርመራ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ዓለም አቀፉ የቲቢ ቀን በክልል ደረጃ ''አዎ ቲቢን ማጥፋት እንችላለን'' በሚል መሪ ሀሳብ በወንዶገነት ወረዳ በምርመራና በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተከብሯል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል `ሀላፊ በላይነህ በቀለ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለማከም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ 12 ተንቀሳቃሽ የምርመራ ኤክስሬዎች ስራ ላይ ናቸው። በዚህም ጥራቱን የጠበቀ የምርመራ አገልግሎት ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በ47 የምርመራ ማዕከላትና በተለያዩ የጤና ተቋማት በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ የምርመራና ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በየመዋቅሩ ያሉ የጤና አደረጃጀቶችን በመጠቀም የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ትኩረት እንደተሰጠው አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ መድሃኒት የተላመደ ቲቢን ለማከም በሀዋሳ ከተማ ተጨማሪ የህክምና ማዕከል ተከፍቶ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዘርፉ የሚሰራው ሪች ኢትዮጵያ ሃዋሳ ማስተባበሪያ ቢሮ የክልሎች ክላስተር አስተባባሪ ጎሳ ግርማ በበኩላቸው ተቋሙ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመግታት በተለያዩ አካባቢዎች እየሰራ ነው ብለዋል። በዚህም በቴክኖሎጂ የታገዘ የቲቢ ህመምተኞችን የመለየት፣ የማከምና ስርጭቱን የመከላከል ስራን ከመንግስት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከፕሮግራሙ ተሳታፊዎች መካከል ተገቢውን ህክምና አግኝተው ከቲቢ ነጻ የሆኑ የወንዶ ገነት ወረዳ ነዋሪዎች ወይዘሮ ብርቱኳን ሹብሻ እና ወጣት ሳሙኤል ማቲዎስ የቲቢ ምርመራና ህክምና በጤና ተቋማት በነጻ ማግኝታቸውን ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የቲቢ ምርመራና የግንዛቤ ስራ የተሰራ ሲሆን የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
ሴቶች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል
Mar 23, 2026 70
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ ሴቶች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሀይሉ አዱኛ ገለጹ። 50ኛ ዙር የጉሚ በለል ውይይት መድረክ “በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የ50+ ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ተካሂዷል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሀይሉ አዱኛ እንደገለጹት ለሁሉም ዜጎቿ የምትመች ሀገር ለመገንባት የተጀመረው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህዝቡ የስልጣን ባለቤት መሆኑን የሚያረጋግጥ ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አንስተው፤ ያለፉ የፖለቲካ ችግሮችን በሀገራዊ ምክክር ለመፍታት የተጀመረው ጉዞ አዲስ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ሴቶች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ መብራት ባጫ እንዳሉት ሴቶች ያለባቸውን ድርብ ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ባለፈ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አበርክቷቸው የላቀ ነው። የለውጡ መንግስት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ አመርቂ ስኬት ማስመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል። በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ፋኖሴ መንግስቱ (ዶ/ር) ባቀረቡት የመወያያ ጥናት በሀገሪቱ የሴቶች ተሳትፎ እያደገ በመምጣቱ በወረዳ፣ በዞን፣ በከንቲባ፣ በሚኒስትርነትና በፓርቲም ደረጃ በተሻለ ሁኔታ በመምራት ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል። አክለውም በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ጠንካራ ስራ ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫን ለማሳካት የሁሉም አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ቢታመንም የሴቶች የተደራጀ ተሳትፎ ሚናው የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል። ከተሳታፊዎች መካከል ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የመጡ አቶ ሰለሞን ተፈራ፤ በአገሪቱ በሁለንተናዊ እድገት መስክ ለተገኘው ድል የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል። በቀጣይም ሴቶች በጠቅላላ ምርጫውና በሀገራዊ ምክክሩ ያላቸውን የነቃ ተሳትፎ ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።
ኢኮኖሚ
የግብርና ምርታማነትን ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የፋይናንስ አቅርቦት ምኅዳር እየተፈጠረ ነው
Mar 23, 2026 63
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የፋይናንስ አቅርቦት ምኅዳር እየተፈጠረ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ። የግብርና ሚኒስቴር ከክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የቢሮ ኃላፊዎችና በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከተሰማሩ ባለኃብቶች ጋር በግብርና ኢንቨስትመንት አፈጻጸም ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በዚሁ ወቅት የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፤ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የግብርና ምርታማነት በማስቀጠል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የግል ባለሃብቱ ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ 21 ሚሊየን ሔክታር የእርሻ መሬት እየለማ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በቀጣይም መታረስ የሚችል 38 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት የአነስተኛ ባለይዞታ አርሶ አደሮችንና ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት አቅምን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም አዳዲስ የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን የእርሻ ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ምኅዳር እየተፈጠረ መሆኑን አስገንዝበዋል። የእርሻ ኢንቨስትመንት የፋይናንስ ማነቆዎችን መፍትሔ ለመስጠት የግብርና ባንክ ማቋቋም የሚያስችል የመጨረሻ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ መደረሱን አስታውቀዋል። በቅርቡም በሙከራ ትግበራ ደረጃ በተለያዩ ወረዳዎች የአርሶ አደሮች የፋይናንስ ብድር አቅርቦት በይፋ እንደሚጀመር አንስተዋል። በተጨማሪም የልማት አጋሮችና የፋይናንስ ተቋማት ለኢትዮጵያ የግብርና ሥርዓት መሻሻል የገንዘብ ብድር የሚያቀርቡበትን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የፋይናንስ አቅርቦት ምኅዳር እየተፈጠረ እደሚገኝ አብራርተዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የእርሻ ኢንቨስትመንት አልሚ ባለሃብቶች የሚቀርብላቸውን የገንዘብ ብድር ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። ከተሳታፊዎች መካከል አቶ በለው ወንድም የእርሻ ኢንቨስትመንትን ለማሻሻል የሚደረገው የፋይናንስ አቅርቦት ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ጠቃሜታ አለው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊና ሕጋዊ መሰረት ያለው ለዘላቂ ልማትና ብልፅግና ወሳኝ መሰረት ነው
Mar 23, 2026 71
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊና ሕጋዊ መሰረት ያለው ለዘላቂ ልማትና ብልፅግና ወሳኝ መሰረት መሆኑን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ ገለፁ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ''የሃይድሮ ዲፕሎማሲና ቀጣናዊ ትብብር ለዘላቂ ውኃና ኢነርጂ ልማትና አስተዳደር'' በሚል መሪ ሃሳብ መጋቢት 14 እና 15 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጣናዊ ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው። በዚህ ወቅት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ፣ ሕጋዊ መሰረት ያለው መሆኑን አንስተዋል። ከ120 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያላት ሀገር የባህር በር ማጣቷ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ እንዳለው ጠቁመው፤ የባህር በር ጉዳይ የመልማት ጥያቄ መሆኑን አስረድተዋል። የባህር በር ለሀገር ብልጽግና ወሳኝ መሰረት መሆኑን አንስተው፤ በፍጥነት እድገት እያስመዘገበች ላለችው ኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ አሁን ላይ የባህር በር ባለቤትነቷን ለማስመለስ የምታደርገው ጥረት ቀደም ብሎ የተሰራውን ታሪካዊ ስህተት የማረም ተግባር ነው ብለዋል። ትውልዱ ለዘላቂ ልማትና ብልጽግና መረጋገጥ የባህር በር ሚና የማይተካ መሆኑን መገንዘብ እንዳለበት ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ህግ የሚደገፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በጉባዔው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና የአካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሕዳሴ ግድብ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ውህደት በማፋጠን ለጋራ ብልጽግና መሠረት እየጣለ ነው - ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
Mar 23, 2026 74
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ውህደት በማፋጠን ለጋራ ብልጽግና መሠረት እየጣለ እንደሚገኝ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ገለጹ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ''የሃይድሮ ዲፕሎማሲና ቀጣናዊ ትብብር ለዘላቂ ውኃና ኢነርጂ ልማትና አስተዳደር'' በሚል መሪ ሃሳብ መጋቢት 14 እና 15/2018 ዓ.ም ቀጣናዊ ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የዓባይ ተፋሰስ የጋራ ትብብር ለሀገራት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ወሳኝ ነው። የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትም ቀጣናዊ የኃይልና የመሰረተ ልማት ትስስር አቅም በመገንባት የጋራ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ትብብር ማጠናከር እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ውህደት በማፋጠን ለጋራ ብልጽግና መሠረት እየጣለ መሆኑንም አስረድተዋል። በቀጣይም የዓባይ ወንዝ ቀጣናዊ የጋራ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማሳለጥ በአካባቢ ጥበቃና መሰል የልማት መስኮች በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የውኃና መስኖ ሚኒስትር ጀምስ ማዊች በበኩላቸው፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የውሃና ኢነርጂ ፍላጎት በውሃ ሃብት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ብለዋል። የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ፍትሐዊ የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ደቡብ ሱዳን ለዘላቂ ቀጣናዊ ውሃ ሃብት አጠቃቀም ትብብር ቁርጠኛ ናት ብለዋል። የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የትብብር አቅምን ማጎልበት ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የዑጋንዳ ሪፐብሊክ የውሃና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ቢያትሪስ አቲም ናቸው። የተፋሰሱ ሀገራትም በትብብር ላይ የተመሰረተ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። በጉባዔው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖና ቆላማ አካባቢ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በጋምቤላ ክልል በግብርና፣ በማዕድንና በሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል
Mar 23, 2026 134
ጋምቤላ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በግብርና በማዕድንና በሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ። የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው መደበኛ ጉባኤ የክልሉን የግማሽ በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል። ርዕሰ መስተዳድሯ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ በሰላም ግንባታ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በገቢና በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በሕዝቡና በፀጥታ አካሉ የተደረገው የተቀናጀት ጥረት የተረጋጋ ሰላም ማምጣት አስችሏል ነው ያሉት። በ2017/18 የምርት ዘመን ከ186 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉንም ገልፀዋል። ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ እንዳለው በሪፖርቱ አመላክተዋል። በማዕድን ልማት ዘርፉም በመጀመሪዎቹ ስድስት ወራት 3 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ 3 ሺህ 860 ኪሎ ግራም መግባቱን ጠቅሰዋል። አፈፃፀሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1 ሺህ 057 ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለው ነው የገለጹት። የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራትም በግማሽ ዓመቱ ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን በሪፖርቱ አመላክቷል። በተጨማሪም በትምህርት፣ በጤና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በስራ ዕድል ፈጠራና በሌሎች የልማት መስኮች አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንሳዊ መረጃዎች ለማሀበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መሳለጥ ወሳኝ ደርሻ እየተወጡ ነው
Mar 23, 2026 56
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንሳዊ መረጃዎች ለማሀበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መሳለጥ ወሳኝ ደርሻ እየተወጡ እንደሚገኝ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዓለምአቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ቀንን በኢትዮጵያ ለ45ኛ ጊዜ "ዛሬን መመልከት፤ ነገን ለመጠበቅ" በሚል መሪ ሃሳብ አክብሯል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በዓለም አቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅህፈት ቤት ፕሬዝዳንት ፈጠነ ተሾመ፤ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መሳለጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል። የሚቲዎሮሎጂ መረጃ አገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ተቋሙ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚያከናውናቸው ስራዎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር እንዲሁም ዘመኑን የሚመጥኑ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። ኢንስቲትዩቱ የሚያቀርባቸው የአየር ትንቢያ መረጃዎች በተደራጀ፣ ትክክለኛና ተደራሽ በሆነ መንገድ በስፋት ለልማት ስራዎች አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከአየር ንብረ ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አደጋዎችን መከላከል የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ለ45ኛ ጊዜ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ቀን በቀጣይ በመስኩ የተሻሉ ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከርና ተደራሽነትን ለማስፋት አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። በኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ጣቢያዎች ኔትወርክ ፕሮጀክት አስተባባሪ ክንፈ ኃይለማሪያም በበኩላቸው፤ የተቋማትን ትብብር በማጠናከር የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ለማህበረሰቡ ተደራሽ እየተደረገ ነው ብለዋል። ኢኒስቲትዩቱ ለመረጃ ሥርጭት ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዕድገት አስመዝግቧል ያሉት ደግሞ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሳንታ በርበራ የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጸባይ ሳይንቲስት ድሪባ ቆሪቻ(ዶ/ር) ናቸው። የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎች በሚፈለገው ልክ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የዘርፉ ተዋናዮች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
አዳዲስና የተከለሱ 79 የኢትዮጵያ ደረጃዎች ጸድቀዋል
Mar 23, 2026 106
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት አዳዲስና የተከለሱ 79 ደረጃዎች መጽደቃቸውን ገለጸ። አኒስቲትዩቱ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የደረጃዎች ቦርድ ካጸደቃቸው ደረጃዎች መካከል 56 አዳዲስ ሲሆኑ፤ 23 ደግሞ የተከለሱ ናቸው። የደረጃዎች ቦርድ ደረጃዎችን ያጸደቀው በምግብና ግብርና ዘርፍ፣ በመሰረታዊና አጠቃላይ ዘርፍ እንዲሁም በኤሌክትሮ መካኒካል ዘርፍ መሆኑ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ ቦርዱ ካጸደቃቸው ደረጃዎች መካከል አስገዳጅ የህጻናት ምግብ ደረጃዎች፣ የተከለሱ የህጻናት ምግብ መፈተሻዎች፣ አስገዳጅ የማርና ማር ውጤቶች ደረጃዎች፣ የማርና የማር ውጤት መፈተሻዎች ይገኙበታል ብለዋል። የሳይበር ደህንነት አስገዳጅ ደረጃዎች እንዲሁም ሌሎች ደረጃዎች መጽደቃቸውንም ጨምረው ጠቅሰዋል። የህጻናት ወተትን ጨምሮ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ጥራትና ደህንነትን በተገቢው መልኩ ለመፈተሽ፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራትና ተወዳዳሪነት በማሳደግ በኩል የደረጃዎቹ መጽደቅ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ከ12ሺህ በላይ ደረጃዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ በደረጃዎች ቦርድ የጸደቁት ሥራ ላይ መዋል ተጨማሪ አቅም ይፈጥራሉ ብለዋል። የአገልግሎት ጥራትን ማሳደግ ሌላው ዓላማ መሆኑን ጠቁመው፤ እንደ ሀገር ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ሀብቴ በበኩላቸው፤ በቦርዱ ከጸደቁት 79 ደረጃዎች ውስጥ 28ቱ አስገዳጅ መሆናቸውን ተናግረዋል። በምግብና ግብርና ዘርፍ ስድስት የተከለሱ አስገዳጅ የግብርና ማዳበሪያ ደረጃዎች፣ ሁለት አስገዳጅ የህጻናት ምግብ ደረጃዎች፣ ሰባት የተከለሱ የህጻናት ምግብ መፈተሻዎች፣ አንድ የማርና ማር ውጤት ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ፣ ሁለት አዲስ የማርና ማር ውጤት መፈተሻዎች ከጸደቁት መካከል እንደሚገኙበት አብራርተዋል። በተመሳሳይም ሁለት አዲስ አጠቃላይ የምግብ ምርቶች አስገዳጅ ደረጃዎች፣ ሦስት አዲስ እና ዘጠኝ የተከለሱ በድምሩ 12 መፈተሻዎች መጽደቃቸውንም አንስተዋል። በመሰረታዊና አጠቃላይ ዘርፍ ደግሞ ሦስት ጂኦግራፊያዊ መረጃ አስገዳጅ ደረጃዎች፣ አምስት አዲስ የሳይበር ደህንነት አስገዳጅ ደረጃዎች፣ 30 አዲስ የሳይበር ደህንነት መፈተሻዎች፣ ሁለት አዲስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት አስገዳጅ ደረጃዎች በቦርዱ መጽደቃቸውን ተናግረዋል። በኤሌክትሮ መካኒካል ዘርፍ ደግሞ ስድስት አዲስ የትራንስፖርት አስገዳጅ ደረጃዎችና አንድ አዲስ የባቡር መንገድ የምህንድስና አስገዳጅ ደረጃ እንደሚገኙበትም አስረድተዋል።
የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያን የኢነርጂ አቅም በዘላቂነት ለማልማት የሰው ኃይል ማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥቷል
Mar 21, 2026 146
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያን የኢነርጂ አቅም በዘላቂነት ለማልማት የሚያስችል የሰው ኃይል ማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ራቢ (ኢ/ር) ገለጹ። የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ እና ጂ.ሲ.ኤል ኢነርጂ ኢንቨስትመንትስ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ የክህሎት ልማትን፣ ኢኖቬሽን እና ዘላቂ የኢነርጂ ልማትን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ስምምነቱ ለዩኒቨርሲቲው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ አለው። በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የንድፈ ሐሳብ ትምህርትን ከኢንዱስትሪው የተግባር ልምድ ጋር በማቀናጀት ለሀገር ግንባታ የሚሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ የሚያካሂዳቸው ጥናትና ምርምሮች ለጂ.ሲ.ኤል ኢነርጂ ፕሮጀክቶች ግብዓት ከመሆናቸው ባሻገር ከኩባንያው የሚገኘው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዕውቀት ለተማሪዎችና ለሀገር የኢነርጂ ዘርፍ ትልቅ አቅም ይፈጥራልም ነው ያሉት። ዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያን የኢነርጂ አቅም በዘላቂነት ለማልማት የሚያስችል የሰው ኃይል ማፍራት ላይ ትኩረት መስጠቱን እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል። የጂ.ሲ.ኤል ኢነርጂ ኢንቨስትመንትስ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ሱን ዦንግ እንዳሉት፤ ስምምነቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የኢንዱስትሪ እና የትምህርት ትስስር ለማሳደግ የሚያስችል ነው። በአካዳሚክ እና በኢንዱስትሪ መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ትብብር ለመፍጠር ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነም አስረድተዋል። ጂ.ሲ.ኤል በኢነርጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ በቴክኒክ፣ በትምህርት፣ በምርምርና ፈጠራ ዘርፍ ጠንካራ አቅም እንዲሁም ውጤታማ የሰው ኃይል ለማፍራት እንደ ቁልፍ ማዕከል እንደሚያገለግል አስገንዝበዋል።
ዩኒቨርስቲው ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በዘርፉ የተሻለ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ድርሻውን እየተወጣ ነው
Mar 21, 2026 307
ሮቤ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በዘርፉ የተሻለ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ ፈጠራና ኢንተርፕረነርሺፕ ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። ይህ ሥልጠና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግብ ስኬት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተመላክቷል። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት በዛብህ ወንድሙ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። በተለይም በባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖችና በምዕራብ አርሲ ዞን በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቴክኖሎጂ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመመልመል የክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። ከዚህም ባለፈ በተለያዩ ጊዜያት በሚሰጡ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የዜጎችን የሥራ ፈጣሪነት ባህል በሚያሳድግ መልኩ እንዲሰጡ መደረጉንም ገልጸዋል። በ2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ዩኒቨርሲቲውን ወክለው የቀረቡ ተማሪዎች አንደኛ ደረጃን በመያዝ ሽልማትና እውቅና ማግኘታቸው የዘርፉ ትኩረት ውጤት መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም አዲስ የፈጠራ ሀሳብና ግኝት ያላቸው ግለሰቦች በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑና ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ተግዳሮቶችን እንዲረዱ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን አክለዋል። ዩኒቨርሲቲው ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በዘርፉ ክህሎት የበለጸገ የሰው ኃይል ለማፍራት ድርሻውን መወጣቱን ይቀጥላል ነው ያሉት። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ ባለሙያ ወይዘሮ ራሄል ደበበ በበኩላቸው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ አገልግሎትን ከማዘመን ባለፈ የዜጎችን ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራትም ተቋማት አገልግሎታቸውን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር የዜጎችን ጊዜና ወጪ መቆጠብ መቻሉን አስታውሰዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሻለ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መድረክም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ስፖርት
በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
Mar 23, 2026 60
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጋቸው የመጀመርያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል። ግብ ጠባቂዎች መቲ ረታ (ልደታ )፣ ኑዳ ሁሴን (አዲስ ከተማ ) እና ኢትዮጵያ ለማ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ማንጠግቦሽ አድማሱ (አርባምንጭ ከተማ )፣ ኤልሻዳይ ዮሴፍ ( ጉለሌ) ፣ ሴና ኤርሚያስ (ለሚኩራ )፣ ቤተልሄም ጌታቸው (ንፋስ ስልክ ላፍቶ)፣ መድሃኒት አለሙ (አርባምንጭ ከተማ) እና መሰረት ጌታቸው (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ) በተከላካይ መስመር የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው። በአማካይ ክፍል ኑአሚን ከበደ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ኢክራም ሚፍታህ (ደራርቱ ቱሉ አካዳሚ )፣ ትዕግስት ተሾመ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ሊያም ዳንኤል (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)፣ ቢታኒያ አስተረፍ (ሲዳማ ቡና) ፣ ሊዲያ ሰለሞን (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) እና ምህረት ወሰኑ (ሸገር ከተማ) በጥሪው ተካትተዋል። ሲርይ ተሾመ (ጉለሌ)፣ ኦጁሉ ኦዶንግ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ምህረት አየለ (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ማህሌት ደመቀ (ሐምሌ 19 ክለብ)፣ እመቤት ዘካሪያስ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ሙሉ አበራ (ለሚ ኩራ) እና ሰሊና ናግዋ (ጉለሌ) በአጥቂ መስመር ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። 10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዋን በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ አድርጓል
Mar 23, 2026 52
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አከናውኗል። ብሔራዊ ቡድኑ ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቷል። ቡድኑ ነገ ረፋድ 4 ሰዓት ከ40 ላይ ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሞሮኮ ጉዞ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች። የመጀመሪያው ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ይካሄዳል።
የሀላባ ቁሊቶ ስታዲዮም ግንባታ የአካባቢውን የስፖርት እንቅስቃሴ እያነቃቃ ነው
Mar 23, 2026 62
ሀላባ ቁሊቶ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ) :- የሀላባ ቁሊቶ ስታዲዮም ግንባታ የአካባቢውን የስፖርት እንቅስቃሴ እያነቃቃ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በእግር ኳሱ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ስፖርተኞች መፍለቂያ በሆነው የሃላባ ዞን የስፖርት መሰረተ ልማት አለመኖር በርካታ ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል። አሁን ላይ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ደረጃውን የጠበቀ ስታዲዮም ግንባታ መጀመሩ ለአካባቢው የስፖርት እንቅስቃሴ መነቃቃት መፍጠሩን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ንጋቱ መለሰ እና አቶ ሳባቶ አህመድ እንደገለጹት ሀላባ ዞን በእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ስም የነበረው ቢሆንም በትኩረት ማነስና በመሰረተ ልማት እጦት ማደግ በሚገባውና ባለው አቅም ልክ ማደግ አልቻለም። በግንባታ ሂደት አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሀላባ ቁሊቶ ስታዲዮም በዘርፉ የተፈጠረውን መቀዛቀዝ በመቀየር አካባቢውን የስፖርት ልማት ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ ማነቃቃቱን ተናግረዋል። የስታዲዮሙ ግንባታ የእግር ኳስ አፍቃሪውን ዳግም ወደ ሜዳ የሚመልስና ሀገርን የሚወክሉ ስፖርተኞች እንዲፈልቁ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” ቡድኖች ጨዋታቸውን በስታዲዮሙ እያደረጉ ሲሆን አስተያየታቸውን የሰጡት የኤልቴክ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ይገረም ኤሊያስ በጥሩ ሜዳ መጫወት ውጤትን ይወስናል ብለዋል። ለስፖርት መሰረተ ልማት በተሰጠው ትኩረት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲዮሞች መገንባት ለሀገሪቱ የእግር ኳስ ስፖርት ዕድገት ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል። የሃላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታገል ጌታቸው በበኩላቸው፤ በህዝብ ተሳትፎ ግንባታው የተጀመረው የሀላባ ስታዲዮም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ሰው ሰራሽ የመጫወቻ ሜዳ፣ የተመልካች መቀመጫ፣ የፍሳሽ ማስወገጃና ሌሎችም በመጀመሪያው ምእራፍ ግንባታ መጠናቀቃቸውን የገለጹት ሃላፊው በስፖርት ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ የግንባታው ሁለተኛ ምዕራፍ አካል የሆኑት የመብራትና ዓለም አቀፍ መመዘኛ ያሟላ የክቡር ትሪቡን ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል። አካባቢው በእግር ኳስ ክህሎት የዳበረና የላቀ ብቃት ያላቸው ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩበት እንደሆነ ጠቅሰው ሜዳው አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚደግፍም አመልክተዋል። ግንባታው በሁለት ምዕራፍ እየተከናወነ የሚገኘው ስታዲዮሙ የካፍ ስታንዳርድን ባሟላ መልኩ እየተገነባ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሲጠናቀቅም ክልላዊም፣ ሀገር አቀፍና ሌሎች ውድድሮችን ለማስተናገድ እንደሚያስችልም ተናግረዋል።
አሜሪካ በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አንደኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች
Mar 23, 2026 146
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ አሜሪካ በ21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 18 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አሸናፊ ሆናለች። በፖላንድ ቶሩን ከተማ ከመጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ሲካሄድ የቆየው ሻምፒዮና ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል። በሻምፒዮናው ከ118 ሀገራት የተወጣጡ 674 አትሌቶች ተሳትፈዋል። አሜሪካ በአምስት ወርቅ፣ በሰባት ብር እና ስድስት ነሐስ በአጠቃላይ 18 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች። ታላቋ ብሪታኒያ (ሰሜን አየርላንድን ጨምሮ) በአራት ወርቅ ሁለተኛ ሆና ጨርሳለች። ጣልያን በሶስት የወርቅ እና ሁለት የብር በድምሩ አምስት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ዩክሬን እና ፖርቹጋል በተመሳሳይ ሁለት የወርቅ እና አንድ ብር በድምሩ ሶስት ሜዳሊያዎችን አግኝተው አራተኛ ወጥተዋል። በውድድሩ ላይ ከተሳተፉ አፍሪካ ሀገራት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘ ሀገር የለም። ሴኔጋል እና አልጄሪያ በተመሳሳይ አንድ አንድ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት 24ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሻምፒዮናው ላይ ከተሳተፉ 118 ሀገራት መካከል ሜዳሊያ ያገኙት 32ቱ ብቻ ናቸው። በሻምፒዮናው በስድስት አትሌቶች የተወከለችው ኢትዮጵያ ምንም ሜዳሊያ ሳታገኝ አጠናቃለች።
አካባቢ ጥበቃ
የሚቲዎሮሎጂ መረጃ አገልግሎትን በማዘመን የሚኖረውን ጠቀሜታ ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Mar 23, 2026 88
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦የሜቲዎሮሎጂ መረጃ አገልግሎትን ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የተፈጥሮ ሃብት አገልግሎት አቅራቢዎች ለሥነ-ምኅዳር ደኅንነት በይበልጥ ሊተጉ ይገባል ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ቀንን በኢትዮጵያ ለ45ኛ ጊዜ "ዛሬን መመልከት ፤ነገን ለመጠበቅ " በሚል መሪ ሀሳብ እያከበረ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም አቀፉ የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅህፈት ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደገለጹት፤ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ ያለ ጉዳይ ነው። በመሆኑም ተፅእኖውን መግታት የሚያስችል የሚቲዎሮሎጂ መረጃ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር ዋነኛው ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢኒስቲትዩቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም አጋር አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ማዋል እና የሰው ሀይል ልማት ዋና ዋናዎቹ ስለመሆናቸው አንስተዋል። በኢትዮጵያ ለ45ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ቀን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከርና ተደራሽነትን ለማስፋት አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጥር አክለዋል። በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በዘመናዊ የሚቲዎሮሎጂ ሳይንስ ላይ በመመስረት ዛሬ የተሻለ መረጃ በመያዝ የተሻለ ነገን ለመገንባት የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑን ገልጸዋል።
የትራንስፖርት ዘርፉን ከአካባቢ ብክለት የጸዳ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል
Mar 23, 2026 74
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፉን ከአካባቢ ብክለት የጸዳ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሐሰን ገለጹ፡፡ በባህር ዳር የአውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያን ጨምሮ ግዙፍ መሠረተ ልማቶች ግንባታ እየተፋጠነ ነው ኢትዮጵያ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት፣በከተማ ትራንስፖርት እና አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ዘላቂ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት እየሰራች ትገኛለች። ይህንን ለመደገፍ ታዳሽ የኃይል ምንጭ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ማስፋፋትና ዘርፉን ማበረታታት ከተሽከርካሪ የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ ያስችላል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሐሰን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘርፉ አካባቢን እንዳይበክል ከማድረግ አኳያ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለሚያስመጡና ለሚገጣጥሙ አካላት አተገባበርን በተመለከተ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ በዚህ ከቀረጥ ነጻን ጨምሮ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች እየተደረገላቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡ በነዳጅ የሚሰሩ ከሁለት እግር እስከ የከተማ ባስ እና የጭነት ተሽከርካሪዎች ድረስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ ይህ እርምጃ ኢትዮጵያ ለዓለም የአየር ንብረት መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ በአስር ዓመቱ ስትራቴጂ የልማት እቅድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ500 ሺህ በላይ ተሽካርካሪዎች የታዳሽ ኃይል አማራጭን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ታስቦ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታዳሽ የኃይል አማራጭን የሚጠቀሙ የተሽከርካሪዎች ቁጥር 115 ሺህ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የትራንስፖርት ዘርፉን ከአካባቢ ብክለት የጸዳ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አመላክተዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲ የትራንስፖርት ዘርፉ አካባቢን እንዳይበክል ከማድረግ ባሻገር ታዳሽ የኃይል አማራጭ ላይ ትኩረት እንዲደረግ እና የነዳጅ ጥገኝነትን ለመቀነስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ እንደ የነፋስ ኃይል፣ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና ሌሎች የታዳሽ ኃይል አማራጮች በስፋት መገኘት ከነዳጅ ተሽከርካሪዎች ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚደረገውን ሽግግር አስተማማኝ እንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው - አምባሳደር ዮሶን አርካዲዮ ሜኔስ ኮፔቴ
Mar 21, 2026 109
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሌሎች ሀገራት ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥርና ምሳሌ የሚሆን ፕሮጀክት ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የኮሎምቢያ አምባሳደር ዮሶን አርካዲዮ ሜኔስ ኮፔቴ ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። ይህም የአካባቢ ጥበቃን ከማጠናከር ባለፈ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው። ይህ መርሃ ግብር በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ግዙፍ የደን ልማትና የተፈጥሮ ጥበቃ ዘመቻ ሲሆን የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ረገድም በምሳሌነት ተጠቃሽ ነው። ሀገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የተፈጥሮ ሥርዓት እንድትገነባ እያገዘም ይገኛል። በኢትዮጵያ የኮሎምቢያ አምባሳደር ዮሶን አርካዲዮ ሜኔስ ኮፔቴ ለኢዜአ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሚመራው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲ እጅግ የሚደነቅ ጥረት ነው ብለዋል። አረንጓዴ አሻራ ለሌሎች ሀገራትና መሪዎች አርአያ የሚሆን ተሞክሮ እንደሚሆን ጠቁመው ይህ ተግባር ሁላችንም በጋራ እንድንሰራ ያበረታታናል ነው ያሉት። የሀገራት መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየመጡ ያሉ ተግዳሮቶችን ለዜጎች በግልጽ ማሳወቅ እንዳለባቸውና ይህም ዜጎች ለመፍትሄው እንዲሰሩ ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2027 የሚካሄደውን 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመረጧን አምባሳደሩ አድንቀዋል። ኮሎምቢያ እ.ኤ.አ. በ2024 የኮፕ 16 ጉባኤን ማስተናገዷን አውስተው ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን በምታዘጋጅበት ወቅት ሀገራቸው ያካበተችውን ልምድ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። አምባሳደሩ አክለውም የኮሎምቢያን ተሞክሮና የኢትዮጵያን የወደፊት ራዕይ በማጣመር፣ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ይሰራሉ ብለዋል።
የዜጎችን የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ለሚያሻሽሉ መመሪያዎች ተፈፃሚነት ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል
Mar 21, 2026 121
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የዜጎችን የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ የሚያሻሽሉ መመሪያዎችን በማውጣት ለተግባራዊነታቸው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና የአካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፋርም አፍሪካና ኤስ.ኦ.ኤስ ሳህል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ትግበራ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የባለድርሻ ተቋማትን ትብብር በማጠናከር በደንብ ቁጥር 545/2016 በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ሥርዓትን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን ዕምቅ የብዝኅ ህይወት ሃብት በሚገባት ልክ ጥቅም ላይ እያዋለች እንዳልሆነ ገልጸዋል። ለዚህም የውሃና የየብስ የሥነ-ምኅዳር ጸጋዎች ለሀገር የኢኮኖሚ ጥቅም ለማዋል የሚስችል "የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ ቁጥር 140/2018" ተግባራዊ መደረጉን አስታውቀዋል። ምክር ቤቱም ከመንግስተና የዘርፉ ተዋናዮች ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት ታክሎበት አዋጁን በማፅደቅ ሥራ ላይ እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም የዜጎችን የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ ለማሻሻል የሚረዱ የማስፈጸሚያ ደንቦችና መመሪያዎች መውጣታቸውንና ተፈፃሚነ መሆናቸውን ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ አንስተዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ንጉሱ ለማ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የሥነ-ምህዳር አገልግሎት የክፍያና የሕግ ማዕቀፍ እንዳለነበረ ገልጸዋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ሥርዓተ ምኅዳር ዘላቂነት ለማስጠበቅ የመንግስትና የባለድርሻ ተቋማትን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ ቁጥር 140/2018 መፅደቁን ተናግረዋል። የአገልግሎት ክፍያ የአሰራር ሥርዓቱም የኢኮኖሚ ዕድልን በመፍጠርና ለአገልግሎቱ አቅራቢዎች ዘላቂ ዋስትናን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ አዋጁን መነሻ በማድረግ የዘርፉን ተዋናዮች ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችል የማስተግበሪያ መመሪያ መዘጋጀቱን አስረድተዋል። የፋርም አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሸዊት አማኑኤል፤ ኢትዮጵያ ደኖችን በመንከባከብ የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ ለዓለም የከባቢ አየር ሥነ ምህዳር ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ደንን በመንከባከብ በአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ በሚበረክቱት አስተዋፅኦ ልክ ሳይንሳዊ ጥናትና ኦዲት ተካሂዶ ገቢ ማመንጨት መጀመሩን አንስተዋል። የሥርዓተ ምኅዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ በባሌ አካባቢ የተጀመረውን በሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት በር የሚከፍት መልካመ ዕድል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 89
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
የኢጋድ እና ጃፓን ትብብር መጠናከር ለቀጣናዊ ሰላም የጎላ ሚና አለው
Mar 9, 2026 219
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ጃፓን በቀጣናው ሰላም ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገለጹ። የኢጋድ ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዳይሬክተር ሂሮኒሪ ሱዙኪ ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በኢጋድ ቀጣና ስላለው የሰላም እና ደኅንነት ሁኔታ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ኢጋድ ሴክሬተሪያት መረጃ ጠቁሟል። ጃፓን ለኢጋድ እና አባል ሀገራት፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት መረጋገጥ ሥራ ዋና አጋር ሆና መቀጠሏም ተመላክቷል።
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 216
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ
Mar 8, 2026 204
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። "መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል። ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል። በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል። የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3224
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 333
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 384
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 366
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 21, 2026 568
ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት … ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም ጂ (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። #ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 21, 2026 159
በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ (በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት ስትወጥን የቀደመ ወረቷን፤ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን ይዛ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን ቀረጸች። ይህን ዕውን ለማድረግ ስትዘይድም የሕዝቧን የፋይናንስ፣ የዕውቀት እና የጉልበት ዐቅም በመደመር መጠቀምን ሻተች። በዚህም መሠረት በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶችን አስመዘገበች። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኢዜአ ዐይን …! ✍️ ገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻዎችና መናፈሻዎችን ለማልማት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ገበታ ለሸገር ኢኒሼቲቭ፤ ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን የሚሸፍን ነው። የሚሠራበትን ገንዘብ ለማሰባሰብም የገበታ ለሸገር የእራት ምሽት በዳግማዊ አጼ ምኒልክ የግብር አዳራሽ ተዘጋጀ፤ ባለሀብቶች፣ የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ድርጅቶችም ተሳትፈዋል። ኢኒሼቲቩ አንድነት ፓርክን ጨምሮ የእንጦጦ መናፈሻንና ሌሎች የተለያዩ መዲናዋን ያስዋቡ በረከቶችን ችሯል። ይህም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት በማልማት በርካታ ቱሪስቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ለምጣኔ ሃብት ዕድገት ጉልኅ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ለዚህ ሁሉ ስኬት መነሻ የሆኑትን ጉዳዮች ያስጀመሩትም ያስፈጸሙትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለሸገር የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ ገበታ ለሀገር የተሰኘውን ኢኒሼቲቭ አበሠሩ። ✍️ ገበታ ለሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻን ለማልማት ያለመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። ይህም በአዲስ አበባ ከተሠራው ገበታ ለሸገር ቀጥሎ የተከናወነ ነው። በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የገበታ ለሀገር ዓላማ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ የቱሪስት መስኅብ የሚሆኑና የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ አካባቢዎችን ማዘጋጀት መሆኑን አስገንዝበዋል። በገበታ ለሀገር መርሐ-ግብር ባለሀብቶችን ጨምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህን ለማሳካት የሀገሪቱን ባለሃብቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተለያዩ መርሐ-ግብሮች የተሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ውጤታማ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበታ ለሀገር ውጥን፤ እንደ ሀላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጉልተው በማሳየት ይበል ያሰኘ ውጤት አስመዝግቧል። ✍️ ገበታ ለትውልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2015 ዓ.ም ገበታ ለትውልድ የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ይህም ተጨማሪ መዳረሻዎች እንዲለሙ አስችሏል። በዚህ ኢኒሼቲቭ ሥር በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች የመዳረሻ ልማት ሥራዎች ተከናውነዋል፤ እየተከናወኑም ነው። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ አካባቢና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፕሮጀክቱ አካል የሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎች እየለሙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የሸበሌ ሪዞርት በይፋ መርቀዋል። እያንዳንዱ የሪዞርቱ ገጽታ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሐብት የሚያንፀባርቅ ነው። ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ትልቅ ታሪካዊ እጥፋት እንደሆነም ተገልጿል። ሎጎ ሐይቅ ሪዞርትም ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረቀ ሲሆን፤ ለጎብኚዎች የማይረሳ ትውስታን የሚሰጥ እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኖ ቀርቧል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክርም ነው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት። የቱሪዝም ልማቱን ከተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ፣ ከዘላቂነትና ከአካታችነት ጋር በማቀናጀት፤ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ጥልቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ዕሴት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅበት ሰፊ ገበታ ሆኖ ያገለግላል። ታሪካዊ ቦታዎችና የሀገር መገለጫ መሠረተ-ልማቶች ብሔራዊ ትርክቶችንም የሚገነቡ ናቸው። በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት ብሎም በየአካባቢው የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። የቱሪዝም ዘርፉን ለማጎልበት፣ ብዙ ጎብኚዎችን ለመሳብ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። እንዲሁም ነባር ቅርሶችን በማደስና በመጠገን ለትውልድ ለማሻገር ደማቅ ዐሻራ አሳርፈዋል። በሌላ በኩል የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት የመንግሥት ብቻ እንዳልሆነ ዐሳይተዋል። ባለሀብቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችም ሀገራቸውን የመሥራት ሚና እንደሚጠበቅባቸው አሥተምረዋል። ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ብሎም በርካታ የሥራ ዕድሎች በመፍጠር በኢኮኖሚው ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በኢትዮጵያም ቱሪዝም መንግሥት ላስጀመረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ ነው። ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎችም አንዱ የሆነው ለዚህ ነው። መሠረተ-ልማቶች ከሚገነቡባቸው ጡቦች ባለፈ የነገን ሀገራዊ ማንነት፣ ራዕይ እና መዳረሻን ይበይናሉ። ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ እንኳንም ታሰቡ፤ እንኳንም ተሳኩ። ይህ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መዳረሻ ባላገኘች ነበር።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 14, 2026 1369
ከየካቲት 29 - መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ኢትዮጵያ • ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተመልክተዋል። ማዕከሉ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል። ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል • በተመሳሳይ በድሬዳዋ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን በመከተል ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማትና ለሸማቹ ማኅበረሰብ የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። • የድሬዳዋ የኮሪደር ልማትንም የጎበኙ ሲሆን፤ የኮሪደር ልማቱ ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬዳዋ ዕውን እንዲሆኑ ማስቻሉን አስረድተዋል። • ከድሬዳዋ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር መርሐ-ግብር ያከናወኑት ባለፈው ሳምንት ነው። • በድሬዳዋ የሚገኘውን እመርታ ቤተ-መጻሕፍትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎብኝተዋል። ቤተ-መጻሕፍቱ በአንድ ጊዜ ለ1 ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። • በሳምንቱ መጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ሥራ ተመልክተዋል። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ፤ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ ዕቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል። • የቁንድዶ ተራሮችንም ጎብኝተዋል። • በሐረር ከተማ የተቋቋመውን መሶብ የአንድ ማዕከልም ተመልክተዋል። ማዕከሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር ዐቀፍ መርሐ-ግብር አካል መሆኑንም አስገንዝበዋል። • በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘውን ናሲኦል ዋሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ጎብኝተዋል። • ከሐረር ከተማ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር አካሂደዋል። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሹመት መስጠታቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሌ/ጄኔራል አሥራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድን እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች አድርገው የሾሙት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካቸው ጋር በጅቡቲ የቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጊሌ በተገኙበት ውይይት አድርገዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝታቸውን ቀጥለውም ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚሁ ወቅትም ከፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ✍️ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ጋር መምከራቸው • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ ታድመዋል። በዚሁ ወቅትም የሁሉም እምነት፣ ባህልና ሥርዓት የሚከበርባት ኢትዮጵያን መገንባት የመደመር መንግሥት ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል። • ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ዳይሬክተር ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) ጋር በዲጂታል ልማት ያለ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ያደረጉት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ እና ትብብራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይም የታደሙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምኅሮ፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ኅያው የሕይወት ስንቅ ነው ብለዋል። ✍️ የመሬት ናዳና ጎርፍ አደጋ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ • ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ የዜጎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል። ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የሐዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል። • ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ከፌደራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ያስታወቁት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። እስካሁንም በአደጋው ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስና መልሶ ለማቋቋም ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ በተቀናጀ መንገድ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለወገኑ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ✍ ምክር ቤቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ማወጁ • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወታቸው ያለፉትን ዜጎች በማስመልከት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ዐውጇል። በዚህም መሠረት ትናንት የጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀኑ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ ይሆናል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ዐበይት_ጉዳዮች #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 419
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3724
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2501
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8293
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6777
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ተከፍሎ የማያልቅ የኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ውለታ አለብን - የመናዊያን ፍልሰተኞች
Mar 19, 2026 2241
በዮሐንስ ደርበው ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለተገፉ፣ ጥላ ከለላ ለሚሹ፣ ለተከዙና ለታረዙ የሀገራት ዜጎች መጠጊያ ናት። የኢትዮጵያን ቸርነትም ከተጠለሉባት እንግዶቿ በላይ ምሥክር የለም። የኢትዮጵያን ደጅ የረገጡ ሁሉ በቆይታቸው ለተደረገላቸው ሁሉ ‘ውለታችንን በምን እንክፈል’ ሲሉ ይደመጣሉ። ከአያሌ ሀገራት በመልከ ብዙ ቀውሶች ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ የቆሰሉ ልባቸው ታክሞ፣ ዕንባቸው ታብሶና ሕይወታቸው ታድሶ ኑራቸውን አደላድለዋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በዚህም ከአፍሪካም ሆነ ከተቀረው ክፍላተ ዓለም የጦርነትና ግጭት ጥላ ያጠላባቸውና ሰላምን የተጠሙ የቀጣናው ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ሲሹ ማየት የተለመደ ነው። የየመን ዜጎች ለዚህ ማሳያ ናቸው። ኢብቲሳም ኻሊድ እና መሰል የመናዊያን ከየመን የእርስ በርስ ግጭት በኋላ የኢትዮጵያን ደጅ ረግጠው ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፍ የተድላ ኑሮ እየኖሩ ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረገችው ኢብቲሳም እንደምትለው፤ በየመን አለመረጋጋት በፈጠረው ጠባሳ እርሷና መሰሎቿ ለፍልሰት ተዳርገዋል። ለዚህ ደግሞ ምርጫቸው ኢትዮጵያ ሆነች። ወደ ኢትዮጵያም መጥተው የሀገሬው ፊት ሳይኮሰኩሳቸው በፍቅር እንደተቀበሏቸው ትናገራለች። በዚህም ዛሬ የመናዊያን ተስፋቸው ለምልሞ፣ ሕይወታቸው ሠምሮ ኢትዮጵያን እንደ እናት ቆጥረው እየኖሩ ስለመሆኑ ትናገራለች። ከ11 ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ኢብቲሳም፤ በወቅቱ ቀኑ እንደጨለመባት ታወሳለች። ሰው ከቤቱ፣ ከወገኑ…ከሀገሩ ወጥቶ ወዴት ይሄዳል? በወቅቱ የነበረውን ጭንቀት ማየልም ታስታውሳለች። አሁን ግን ስለ ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ በጎነት ዐውርታ አትጠግብም። “አሁን ፍልሰተኛ አይደለሁም፤ ያለሁት በሁለተኛዋ ሀገሬ ኢትዮጵያ ነውና” ትላለች። እንዲህ ባለው የረመዳን ወቅት ደግሞ የፍልሰተኞች ሁሉ ሰብሳቢ ናት። “ሁሉም ከእነ ቤተሰቡ ወደ ቤቷ እየመጣ ያፈጥራል። በዚህም በፍልሰት እንደመጡ ሳይሆን ቤተሰባዊነት ይሰማቸዋል። ከየመን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮንጎሊዝ (DRC) ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ ሰብሰብ ብለው የኢፍጣር መርሐ-ግብርን እንደሚያከናውኑም ታነሳለች። በዚህ ላይ ኢትዮጵያውያን ብርታት ናቸው ትላለች፤ ሁሌም ‘አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ነገ ጥሩ ይሆናል’ እያሉ ያበረቱናል፤ ክብርና ፍቅር ይሰጡናል ስትልም ታስረዳለች። የኢትዮጵያንና ሕዝቧን ውለታ እንዴት መክፈል ይቻላል? ኢትዮጵያን ሀገራችን ብለን ነው እየጠራን ያለነው። እንደ እንግዳ እንደ ፍልሰተኛ እራሳችንን አናስብም፤ እንደሀገሬው አንዱ እንጅ፤ የምትለው ኢብቲሳም፤ ኢትዮጵያን እንዴት ብዬ ነው የምገልጻት? እናትን መግለጽ ይቻላል? እናትን መግለጽ ከተቻለ ኢትዮጵያን በዚያ ልክ መግለጽ ይቻል ይሆናል፤ እኔ ግን አይቻለኝም በማለት ትናገራለች። “የዛሬ 11 ዓመት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት፤ የሰው ፊት አልገረፈኝም፤ ፊቱን ያዞረብኝም የለም። ኢትዮጵያውያን ደግ፣ ቅንና ደስ የምትሉ ሕዝቦች ናችሁ” ስትል ስሜቷን ትገልጻለች። ኢትዮጵያ እንደ ኒውዮርክ እያደገች ነው፤ እኛ ከመጣን በኋላ እንኳን በርካታ ለውጦች ዕያየን ነው ስትልም የኢትዮጵያን የለውጥ ሂደት አንስታለች። ለአብነትም ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በርካታ ነገሮች መስተካከላቸውን በመጠቆም፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግሥት እናመሠግናለን ብላለች። ከፍልሰተኞች ጋር በተያያዘ በርካታ ሕጎች በመሻሻላቸው፤ ዛሬ በራሴ ስም ንግድ ፈቃድ አውጥቼ እየሠራሁ ነው፤ በጨረታዎችም እወዳደራለሁ፤ የበጎ አድራጎት ማኅበር መመሥረትና መምራት ችያለሁ። እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያመጣቸው ለውጦች ናቸው ብላለች። በምድረ ኢትዮጵያ ያለን ሁሉ ለኢትዮጵያ ዕድገት እንተባበር ስትልም ጥሪ አቅርባለች። ህልማችን ከኢትዮጵያውያን ጎን ሆነን ኢትዮጵያን በማሳደግ ጥረት በንቃት መሳተፍ ነው፤ የኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ውለታ መመለስ አለብን ስትልም ትናገራለች። በኢብቲሳም ኻሊድ ቤት በተዘጋጀ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ የተሳተፈው አነስ አንዋር ለኢዜአ እንዳለው፤ ኢትዮጵያ በሯን ከፍታ አስጠልላዋለች። ከተለያዩ ሀገራት ብንመጣም ሰብሰብ ብለን ስናፈጥር፤ ማኅበራዊና ቤተሰባዊነታችን ይጠናክራል ብሏል። ብዙ ፈተናዎችን ዐይተናል፤ አልፈናቸው እዚህ ደርሰናል የሚለው አነስ፤ “ኢትዮጵያዊነት መልካምነት ነው” ሕዝቡ በክብር ነው የተቀበለን፤ ከምሥጋና ውጭ ምን ማለት እንችላለን? አመሥጋኞች ነን ሲል ገልጿል። እየተማርኩ ነው፤ ትምህርቴን አጠናቅቄ በሙያዬ በመሠማራት ኢትዮጵያን ማገዝ እፈልጋለሁ ብሏል። ራኪያ አሊ አብዱረዛቅ በበኩሏ በፈረንጆቹ 2011 ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷን ታወሳለች። ትምህርቷንም ተከታትላ መመረቋን ገልጻ፤ ቤተሰብ አፍርታ ሁለት ልጆችንም ወልዳ እየኖረች ነው። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሀገሬ ናት፤ ሰላም አላት፤ ሕዝቡም ሰው አክባሪ ነው። ለኢትዮጵያ የተሻለ ልማት ደግሞ መተባበር ወሳኝ ስለሆነ ለዚሁ እንትጋ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች። #ፍልሰተኞች #ኢዜአ
ከዛፍ የሚታለብ ወተት
Feb 27, 2026 625
በቀደሰ ተክሌ -(ከሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥበብ ከተፈጥሮ ጋር ስትገናኝ ሌላ እውነት ሌላ አዲስ ነገር ትፈጥራለች። የሰው ልጅ የመመራመርና የማወቅ ተፈጥሯዊ ባህርይው በተፈጥሮ ላይ ሁሉን የማድረግ ሥልጣንን ያስቸረ ነው። ሰው ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር ባይችልም፤ ከነበረው ሌላ ውጤት ማግኘት ወይም መፍጠር ይችላል። "ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በዓለማችን ሰውን እና እቃን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ትልቅ አገልግሎት ያለው ተሽከርካሪ ሕይወት ያለው መስሎ እንዲታይ የሚያደርገው የተገጠመለት ጎማ ነው። ታዲያ ይህ ጎማ ከዛፍ በተገኘ የወተት ጠብታ የሚሰራ መሆኑ አግራሞትን ከሚፈጥሩ የጥበብ ሥራ ውጤቶች መካከል እንዲሆን ያደርገዋል። የጎማ መስሪያ የሆነው ጥሬ ምርት ከዛፍ እንዴት እንደሚዘጋጅ ከስፍራው ኢዜአ የተመለከተውን ሊያስቃኛችሁ እነሆ ይላል፡- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጎማ ዛፍ ልማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የተባለው ይህ የጎማ ዛፍ ልማት በ3 ሺህ 884 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። አረንጓዴ ካባ የደረበውን የበበቃ ቀዬ እንደተሻገሩ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙ ዛፎች ቅርንጫፋቸውን ከመሬት ከፍ አድርገው ግንዱን ለሌላ ተግባር እየተዉ አድገው በአዲስ ብርሃን ቀበሌ ደምቀው ይታያሉ። እነዚህ ዛፎች ከወገብ በታች ባለው ክፍል ብዙ ሺህ ጅራፍ እንዳረፈበት ገላ ሰምበር በሰንበር ሆነዋል። ይህም ሌሊት ሌሊት በሚፈጸም ከዛፉ ወተት ለማምረት በተደረገ ጥረት ሳቢያ የተፈጠረ ነው። ጎማን ለመሥራት የሚያስችለውና ከዛፉ የሚገኘውን ወተት ማምረትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሌሊት ከ9 ሰዓት ጀምሮ የሚከውኑት ተግባር ነው። ይህን ሥራ ለማቀላጠፍም ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ላይና ታች ይላሉ። ሠራተኞቹም ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ በወዝ በላባቸው ለሀገር አዎንታዊ ተጠቃሚነት የሚውለውን ምርት ያቀርባሉ። የጎማ ዛፍ በተፈጥሮ ብዙ ወተት የሚይዘው ሌሊት ነው። ቀን የሰበሰበውን ወተት ሌሊት ያለ ስስት ይለግሳል። በዚህን ሰዓት ዛፉን አድምተው ወተት ሊያልቡ የተዘጋጁ ሠራተኞች በሰለጠኑት ሙያ መሠረት የፀሐይ መውጫና መግቢያ አቅጣጫን ቀድመው ይለያሉ። የፀሐዩን አቅጣጫ ከለዩ በኋላ በዛፉ ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ ጎን ላይ በስለታማ ቁስ በአንድ መስመር ቀጥ አድርገው በመፈቅፈቅ ለዛፉ ወተት መውረጃ ቦይ ያበጃሉ። በመቀጠል ሁለቱን መስመሮች ከፊት ለፊት የሚያገናኝ ሌላ መስመር በማበጀት የዛፉ ወተት መሰል ፈሳሽ ከስር ወደተቀመጠው ፈሳሽ መቀበያ ባልዲ ያለ ስስት ይፈሳል። የጎማ ዛፍ ወተት ጠብታ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር ተሰብስቦ በብዙ ሊትር ተመዝኖ በበርሜል ይከማቻል። በአግባቡ የማጣራትና አሲድ ጨምሮ የማርጋት ሥራ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይገባል። ወተቱ ከረጋ በኋላም ይታጠባል። ተድጦ የሚፈለገውን ያህል ቅርጽ ከያዘ በኋላ ጋቢ መስሎ ፀሐይ ላይ ይሰጣል። በፀሐይ ኃይል ጠፈፍ እንዲል የተሰጣው ምርት የተያዘለት ሰዓት ሲጠናቀቅ በባህላዊ መንገድ ወደ ተዘጋጀው ጭስ ቤት ይላካል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁ እሳት ማንደጃ ጉድጓዶች ይገኛሉ። ከፀሐይ ላይ ተሰጥቶ ወደ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ምርት በዚህ ክፍል ከ5 እስከ 6 ቀናት የተለያዩ የድርቀት ደረጃዎችን እየተሸጋገረ ይቆያል። በጥሩ ሁኔታ ቀይ ሆኖ ከደረቀ በኋላ ለጎማ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ሆኖ ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናል። ሁለት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረው የጎማ ልማትና ምርት ሥራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የጎማ ጥሬ ዕቃ በከፊል በመሸፈን በሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ እንደሚሉት፤ የጎማ ዛፍ አንድ ጊዜ ከተተከለ በኋላ ዓመቱን ሙሉ ምርት የሚሰጥ ዛፍ ነው። የወተት ምርት ለመስጠት ችግኙ ከተተከለ በኋላ ለሦስት ዓመታት ይቆያል። በጉራፈርዳ ወረዳ ለምቶ ምርት እየሰጠ ካለው ዛፍ በወር ከ37 እስከ 40 ቶን የጎማ ዛፍ ጥሬ ምርት በመመረት ላይ ሲሆን ዘንድሮ ከ560 ቶን በላይ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን የጥሬ ምርት ፍላጎት በከፊል ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ87 ሺህ ሄክታር በላይ ለጎማ ዛፍ ምቹ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በስፋት ወደዚህ ዘርፍ በመግባት የዘርፉን ኢኮኖሚ መጠቀም አልተቻለም። የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትን ለማስፋፋት አቅዶ በጥናት ከተለዩ ቦታዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቡር ዞን ከ2 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መሬት ተረክቦ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የሀገር ውስጥ የጥሬ ምርት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ በመሸፈን እና የተረፈውን ኤክስፖርት በማድረግ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን አቶ ዘማች ጠቁመዋል። ባለሃብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ሀገርን የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻልም አክለዋል። ኢትዮጵያ በየዘርፉ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የዕድገት ጉዞዋ አቅሞች ናቸው። በተለይ ለም አፈሯ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ምርቶችን በማብቀል ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀብት መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ እየተቻለ ነው። ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የጎማ ዛፍ ልማትም ከእነዚህ አቅሞች አንዱ ነው። ያሉንን ጸጋዎች ለይቶ ለማልማትና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሰጠውን ትኩረት መሠረት በማድረግ የጎማ ዛፍ ምቹ አጋጣሚዎችን ለይቶ መሥራት ከተቻለ ከዘርፉ በብዙ መጠቀም ይቻላል፡፡