የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ አድርጓል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አከናውኗል።
ብሔራዊ ቡድኑ ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቷል።
ቡድኑ ነገ ረፋድ 4 ሰዓት ከ40 ላይ ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሞሮኮ ጉዞ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
የመጀመሪያው ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ይካሄዳል።