ተቋማዊ ሪፎርሞች የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ተቋማዊ ሪፎርሞች የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ) ፦ተቋማዊ ሪፎርሞች የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተገኝተን በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ዐበይት የሪፎርም እና የማስፋፊያ ሥራዎችን ተመልክተዋል።
በዚህ ወቅት ቢሮው የሀገር አቀፍ ስማርት ሲቲና ስማርት ጤና አገልግሎት ራዕይን መነሻ በማድረግ ተቋሙን የማዘመን ሥራ በስኬት እያከናወነ ነው ብለዋል።
ለዲጂታላይዜሽን በተሰጠው ትኩረትም ተቋሙን ወረቀት አልባ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋት ላይ ይገኛል ነው ያሉት።
ከባሕር ዳር የኮሪደር ልማት ጋር የተናበበ ጽዱ የግቢ ማስዋብና ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀትም ጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን መመልከታቸውንም ጠቁመዋል።
ዘመናዊ የግንባታ አሠራርን በመጠቀም በነባሩ የቢሮው ሕንፃ ላይ ማራኪና ምቹ የሥራ ቦታዎች በጥራት ተገንብተዋል።
ተቋማዊ ሪፎርሞች የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥኑታል ሲሉ ነው የገለጹት።
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ