ቀጥታ፡

በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጋቸው የመጀመርያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

ግብ ጠባቂዎች መቲ ረታ (ልደታ )፣  ኑዳ ሁሴን (አዲስ ከተማ ) እና ኢትዮጵያ ለማ  (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

ማንጠግቦሽ አድማሱ (አርባምንጭ ከተማ )፣ ኤልሻዳይ ዮሴፍ ( ጉለሌ) ፣ ሴና ኤርሚያስ (ለሚኩራ )፣ ቤተልሄም ጌታቸው (ንፋስ ስልክ ላፍቶ)፣ መድሃኒት አለሙ (አርባምንጭ ከተማ) እና መሰረት ጌታቸው (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ) በተከላካይ መስመር የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው።

በአማካይ ክፍል  ኑአሚን ከበደ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ኢክራም ሚፍታህ (ደራርቱ ቱሉ አካዳሚ )፣ ትዕግስት ተሾመ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ሊያም ዳንኤል (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)፣ ቢታኒያ አስተረፍ (ሲዳማ ቡና) ፣ ሊዲያ ሰለሞን (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) እና ምህረት ወሰኑ (ሸገር ከተማ) በጥሪው ተካትተዋል።

ሲርይ ተሾመ (ጉለሌ)፣ ኦጁሉ ኦዶንግ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ምህረት አየለ (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ማህሌት ደመቀ (ሐምሌ 19 ክለብ)፣ እመቤት ዘካሪያስ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ሙሉ አበራ (ለሚ ኩራ) እና ሰሊና ናግዋ (ጉለሌ) በአጥቂ መስመር ጥሪ ቀርቦላቸዋል።


ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።


10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።


ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዋን በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም