ቀጥታ፡

በክልሉ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦በክልሉ ያለውን ሰላም በማጽናት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን  የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ መሠረት ማቲዎስ ገለፁ። 

የልማት ጥያቄያችን ምላሽ እያገኘ በመሆኑ ተደስተናል−የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች

የክልሉ  ምክር ቤት  9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በጋምቤላ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡


 

አፈ-ጉባኤዋ መሠረት ማቲዎስ ጉባኤው በተጀመረበት ወቅት እንዳሉት ፤ በክልሉ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ። 

ከዚህ ውስጥም የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የተከናወኑት ተግባራት ውጤት የታየባቸው እንደሆኑም ተናግረዋል።  

ነዋሪው በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በሌሎች የልማት መስኮች የሚያደርገውን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትም ስኬታማ ናቸው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም ምክር ቤቱ ህጎችን ከማውጣትና አተገባበራቸውን ከመከታተል ባለፈ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ በመከታተልና በመቆጣጠር የተሰጠውን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝም ገልፀዋል። 


 

ዘንድሮ የሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ያስፈልጋል ነው ያሉት አፈ-ጉባኤዋ።

በመሆኑም የክልሉ ነዋሪ  በህገ-መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመምረጥና የመመረጥ መብቱን ሊጠቀም እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ የክልሉን የ2018 የግማሽ በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ፣ የኦዲት ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጨምሮ የምክር ቤቱ ዕቅድ ክንውን ላይ እንደሚወያይም ነው የገለጹት።

በተጨማሪም ረቂቅ አዋጆችና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችም ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም