ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በተጠባቂው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ብራዚል እና ሞሮኮ አቻ ተለያዩ
Jun 14, 2026 191
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሶስት ተጠባቂ መርሐ ግብር ብራዚል እና ሞሮኮ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ከእኩለ ሌሊት በኋላ በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እስማኤል ሳይባሪ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሞሮኮ መሪ ሆናለች። ቪኒሸስ ጁኒየር በ32ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ብራዚልን አቻ አድርጓል። በጨዋታው ሞሮኮ ማራኪ እና ፍሰት ያለው የጨዋታ እንቅስቃሴ አድርጋለች። ብራዚል በክንፍ መስመር ተጫዋቾቿ ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ስታደርግ ለመመልከት ተችሏል። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል። ሁለቱ ሀገራት በምድቡ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። ሞሮኮ ከስኮትላንድ፣ ብራዚል ከሀይቲ ቀጣይ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ ሶስት ሌላኛው መርሐ ግብር ሀይቲ ከስኮትላንድ ከሌሊቱ 10 ሰዓት በቦስተን ስታዲየም ይጫወታሉ።
ስዊዘርላንድ እና ኳታር አቻ ተለያዩ
Jun 13, 2026 231
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት መርሐ ግብር ስዊዘርላንድ እና ኳታር ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሬል ኢምቦሎ በ17ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ጎሉን ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ስዊዘርላንድ መሪ ሆናለች። ይህም በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በፍጹም ቅጣት ምት የተቆጠረ የመጀመሪያ ግብ ሆኗል። ቦዓለም ኩኪ በ95ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ለኳታር ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝቷል። በጨዋታው ስዊዘርላንድ ብልጫ የወሰደች ቢሆንም ያገኘቻቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀም አልቻለችም። ውጤቱን ተከትሎ ስዊዘርላንድ እና ኳታር በውድድሩ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና አንድ አቻ ተለያይተዋል። ካናዳ ከኳታር፣ ስዊዘርላንድ ከቦሲኒያ ሄርዞጎቪና በቀጣይ በምድቡ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሀገርን ስም የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን የማፍራት ተግባሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ
Jun 13, 2026 291
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ እውቅ አትሌቶችንና ስፖርተኞችን የማፍራት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የስፖርት ክለብ እንዲሁም የሙዚቃና ቴአትር ቡድን የተመሠረቱበትን 40ኛ ዓመት በዓል ባከበሩበት መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ለታዋቂዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ የተሰጠ ሲሆን፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ በስፖርት ክለቡና በኪነ-ጥበብ ቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል። የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የኮሚሽኑ የስፖርት ክለብ ባለፉት 40 ዓመታት በሀገሪቱ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ማሳረፉን ገልጸዋል። የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ ያደረጉ እውቅ አትሌቶችንና ስፖርተኞችን በማፍራት በኩል ተቋሙ የተጫወተው ሚና የላቀ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኮሚሽኑ በስፖርትና በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የጀመራቸውን አበረታች ሥራዎች ይበልጥ ዘመናዊ በማድረግ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አስገንዝበዋል። የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚላኩ ታራሚዎችን አምራችና ሕግ አክባሪ ዜጋ አድርጎ የማውጣት ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም መሆኑን አስታውቀዋል። ይህን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት የስፖርት ክለቡ እንዲሁም የሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ የሕግ ማረም ሥራውን በጥበብና በማስረጽ፣ እንዲሁም በስፖርት የአካል ብቃት በማጎልበት ታራሚውን እያዝናኑና እያስተማሩ በመቅረጽ በኩል ሚናቸው የላቀ ነው ብለዋል። ሁለቱም ክፍሎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተለይም የስፖርት ክለቡ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረኮች የሀገርን ስም ያስጠሩ በርካታ ጀግና ስፖርተኞችን ያፈራ መሆኑን ገልጸዋል። በአትሌቲክሱ ዘርፍ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊትና ጥቁር ሴት የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነችውን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን፣ ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን፣ አትሌት ስለሺ ስህን እንዲሁም የማራቶን ጀግናዋን ፋጡማ ሮባን ማፍራቱን በኩራት አስታውሰዋል። በተመሳሳይ መልኩ የሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ደማቅ አሻራ ያሳረፉና ለሀገር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ በርካታ የጥበብ ባለሙያዎችን ለሀገር ማበርከቱን ጠቁመዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡበት ነው -አቶ አደም ፋራህ
Jun 13, 2026 667
አዲስ አበባ ፤ሰኔ 6 /2018 (ኢዜአ) ፦ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጡበት መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተሳተፉና አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሲቪል ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የዕውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ ምክር ቤቱ ምርጫው በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ላዘጋጀው የዕውቅና መርሐ ግብር ምስጋና ይገባዋል ብለዋል። የተቋም ግንባታ የሥልጣኔ መገለጫ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አደም ፋራህ፤ ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ አማራጭ የሌለው የሕልውና እና የብልፅግና መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል። ዴሞክራሲ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የምንገነባበት ምሰሶ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ያሉት አቶ አደም፤ ሀገራዊ ተቋማትን በጋራ ጥረትና መሥዋዕትነት መገንባት እንደሚገባም አሳስበዋል። በምርጫው ወቅት የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ፅኑ ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየበት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በምርጫው ወቅት የነበረውን ንቁ ተሳትፎ አድንቀው፤ በተለይም ዜጎች ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ድርጅቶቹ ገንቢ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የሲቪክ ማኅበራት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን ሚና እንዲያሳድጉ ሰፊ ሥራ መሠራቱን የጠቀሱት አቶ አደም፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የታየው ከፍተኛ ተሳትፎም ያለፈው ጥረታችን ውጤት ነው ብለዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ይበልጥ ለማጠናከርና አጋርነታቸውን ለማስቀጠል መንግሥት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። በፖለቲካው ምኅዳር በፉክክርና በትብብር መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ የመሄድ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤ ለማዘጋጀት ተመረጠች
Jun 13, 2026 300
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና ጉባኤ (Global Education Conference) እንድታስተናግድ መመረጧን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ ለስፖርት ልማት በተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን ዓለም አቀፍ የስፖርት ኩነቶች ለማዘጋጀት ጥረት እያደረገች ትገኛለች። እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና ጉባኤ (Global Education Conference) እንድታስተናግድ መመረጧን ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አዘጋጅነት በየጊዜው በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ አንድምታ ያለው ሁነት መሆኑ ተገልጿል። ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2018 በቻይና ቤጂንግ፣ በ2022 በአውስትራሊያ ሲድኒ እንዲሁም በ2024 በፈረንሳይ ሀገር መካሄዱ ይታወሳል። ይህ ጉባኤ በአፍሪካ ደረጃ ሲካሄድ የመጀመሪያው በመሆኑ ለኢትዮጵያ የገፅታ ግንባታ እና ለስፖርት ቱሪዝም እድገት ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ በተጨማሪ፣ በአህጉር አቀፍ ደረጃ የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴውን የበለጠ በማጎልበትና ንፁህ ስፖርትን በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል። ጉባኤው ኢትዮጵያ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመደበኛ የትምህርት ስርዓት ውስጥ አካትቶ መተግበርን፣ በቂ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ተግባራዊ ማድረግን፣ እንዲሁም ጠንካራ የምርመራና ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግን ጨምሮ ያስመዘገበቻቸውን በርካታ ውጤቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአግባቡ ለማስገንዘብ ተጨማሪ እድል እንደሚፈጥር የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ፖለቲካ

የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jun 13, 2026 450
አዲስ አበባ፤ሰኔ 6 /2018 (ኢዜአ) ፦በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ሰላምና የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዴሞክራሲያዊና ለሲቪል የፖለቲካ ባህል መጎልበት የፈጠርነውን ምቹ ምህዳርና ተቋማዊ አቅም ያሳየ ነው ብለዋል። በዛሬው ዕለትም ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ጋር በመሆን፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱና በቁርጠኝነት ለተጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀውን የዕውቅና መርሃ ግብር መታደማቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጉልህ አሻራ ባሳረፈው በዚህ ምርጫ የሥልጣን ሽግግርና የፖለቲካ ፉክክር በሰላማዊ መንገድና በምርጫ ብቻ መሆኑን በማሳየት ረገድ የሲቪል ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የተጫወቱት ሚና የላቀ ነው ያሉት። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ሰላምና የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል። በዚህ ሂደት የሲቪልና የፖለቲካ ድርጅቶችን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከርና ምህዳሩን ይበልጥ ለማስፋት መንግሥት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከሥጋት ቀጣና ወጥተው ወደ እውነተኛ የልማት አጋርነት ተሸጋግረዋል
Jun 13, 2026 404
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከቀድሞ የሥጋትና የጥርጣሬ ቀጣና ወጥተው ወደ እውነተኛ የመንግሥት የልማትና የዴሞክራሲ አጋርነት መሸጋገራቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተሳተፉና አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሲቪል ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የዕውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። "የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ያመሰግናሉ" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ፣ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ ሚኒስትሮች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሕዝብን ድምፅ የሚያሰሙና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል የመተማመን ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መሠረታዊ ዓላማቸው የሕዝብን ድምፅ ማስተጋባትና የሀገርን ጥቅም ማስጠበቅ ቢሆንም፤ ቀደም ሲል በነበሩ ሕጎች ምክንያት እንደ ሥጋት ታይተው መቆየታቸውን አስታውሰዋል። በተለይም የአዋጅ ቁጥር 621/2009 መውጣት መንግሥት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ከአጋዥ ይልቅ እንደ ሥጋት እንዲመለከታቸው አድርጎ እንደነበር ጠቅሰዋል። ሆኖም ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1113/2011 በመንግሥትና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት ከቁጥጥር ወደ አጋርነት፣ ከገደብ ወደ ትብብር እንዲሸጋገር መደረጉን አብራርተዋል። በዚህም ማህበራቱ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ መቻላቸውን ገልጸዋል። በሰብዓዊ መብትና በማኅበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ በርካታ ሥራዎችን መሥራታቸውን በመጥቀስ፤ ምርጫ የዴሞክራሲ ፅንሰ-ሐሳብ አንድ አካል መሆኑን ለኅብረተሰቡ ለማስገንዘብ ትልቅ ዕድል ማግኘታቸውንም ተናግረዋል። በዚህም ዜጎች በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ ተመልካች ሳይሆኑ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ስኬታማ ሥራ መሠራቱን ጠቁመዋል። የሲቪል ማኅበራት ስኬት የሚለካው ሰላም፣ ልማትና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እንዲገነባ በማድረግ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ለዚህ ስኬት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በገለልተኛ ተቋማዊ ብቃት ኃላፊነቱን በአግባቡ ተወጥቷል ብለዋል። ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ የጸጥታ አካላት የነበራቸው ሚና የጎላ እንደነበር በማንሳት፤ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም አማራጭ ሐሳቦችን በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎችን በማሰማራት አጋርነታቸውን በተግባር ማሳየታቸውን ጠቅሰው፤ የምስጋና መርሐ ግብሩ የተዘጋጀላቸው የሕግና የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲሁም ሚዲያዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ያለንን ፍቅርና የሰላም ቀናኢነት በተግባር አስመስክረናል - የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
Jun 13, 2026 507
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሚሊዮኖች በመመዝገብ በፅናት በመምረጥ ለሀገራችን ያለንን ፍቅርና የዘላቂ ሰላም ቀናኢነት በተግባር አስመስክረናል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ ይህንን የገለጹት የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተሳተፉና አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሲቪል ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የዕውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር ላይ ነው። "የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ያመሰግናሉ" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ፣ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ ሚኒስትሮች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከቅድመ ምርጫ እስከ ምርጫው ዕለት በኢትዮጵያዊ ስክነት በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያን ከራሳችን አልፎ ለዓለም ውህደትና ልማት መሠረት የሆኑ የጥንታዊ ሀገር በቀል እሴቶች ባለቤት ነን ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ፤ ይህ የኢትዮጵያ እሴት ግን ተገቢው የፖለቲካ ልምድ ታክሎበት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳይሸጋገር እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን አስገንዝበዋል። በዚህም በውይይት፣ በንግግርና በሀሳብ ልዕልና ሊፈቱ የሚችሉ ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት በመሞከሩ የዴሞክራሲ ሂደቱ ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰዋል። በመሆኑም ከታሪካዊ ሥልጣኔያችን አኳያ የተመኘነውን ያህል መራመድ ባንችል እንኳ፣ ያለፈውን ስህተት አርመን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ቁጭታችንን ስንቅ ልናደርግ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያውያን ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ባለው ሂደት ፍትሐዊና ሰላማዊ መንገድ በመከተል፣ ለዘመናዊ መንግሥት ግንባታ ፍትሐዊ ምርጫ ቁልፍ መሆኑን በተግባር አሳይተናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ተስፋ የሚለመልመው በሰለጠነ ምርጫ ነው በሚል በሚሊዮኖች በነቂስ ወጥተን በመምረጥ የነውጥ፣ የጥፋትና የሞት ድግስን ማክሰም ችለናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በትዕግሥት ድምፅ በመስጠት የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ በእጃችን መሆኑን በአሻራችን አትመናል ሲሉ ተናግረዋል። ለሕግ የበላይነት መገዛት፣ ውይይትና ንግግር የሰለጠነ ፖለቲካ መገለጫዎች መሆናቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፣ በምርጫው ሂደት ለሰለጠነ የሀሳብ የበላይነት ያለንን ዝግጁነት ያሳየንበት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ምርጫ በጥቂት ልሂቃን መካከል የሚደረግን ውድድር ለመታዘብ ሳይሆን ዘላቂ ሰላምን ለማፅናት የሚደረግ የዴሞክራሲ መንገድ መሆኑን አብራርተዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጎላ አበርክቶ ላደረገው ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለጸጥታ ኃይሎችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ፕሬዚዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት በማስቀጠል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የወጣቶች የነቃ ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
Jun 13, 2026 630
ባህርዳር፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት በማስቀጠል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የወጣቶች የነቃ ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። ''ባህር ዳርን ወደ ላቀ ከፋታ ለመውሰድ የወጣቶች ሚና የማይተካ ነው'' በሚል መሪ ሀሳብ ከወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት በማስቀጠል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። ወጣቱ የዘላቂ ሰላምና የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በማድረግ የጎላ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በዘርፉ በሚከናወኑ ተግባራት የወጣቱ የነቃ ትብብርና ተሳትፎ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተለይም በባህር ዳር ከተማ ሰፋፊ የልማት ስራዎች በተሻለ ጥራትና ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ የወጣቱ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት የበለጠ ይጠናከራል ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው፤ ከተማውን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከል ማድረግ ያስቻሉ ውጤታማ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉ ተናግረዋል። ለልማት ስራዎች ውጤታማነት ወጣቶች የከተማዋን ሰላም በማረጋገጥ አይተኬ ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል። ወጣቱ የሰላም ባለቤትነቱን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማረጋገጡን አንስተው፤ በከተማው ዘላቂ ሰላምና ልማት የማስቀጠል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል። በመድረኩ የከተማው ወጣቶች እየተሳተፉ ሲሆን በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ኢትዮጵያውያን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተረጋጋ ፖለቲካና ለዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ተነሳሽነት በተግባር አሳይተዋል
Jun 13, 2026 512
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በነቂስ በመሳተፍ ለተረጋጋ ፖለቲካና የዳበረ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያለውን ተነሳሽነት በተግባር ማሳየቱን ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሁራን ገለጹ፡፡ ከ54 ሚሊየን በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ የወሰዱበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምጽ መሰጠቱና ምርጫ መካሄዱ ይታወቃል። ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሁራን እንዳሉት፤ ዜጎች ከቅድመ ምርጫ እስከ ድምጽ መስጫው ዕለት ያሳዩት የነቃ ተሳትፎ የመንግስት ስልጣን መያዝ የሚገባው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ መሆኑን ያሳየና ትምህርት የሰጠ ነው። በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የተቋማት ልማትና አስተዳደር ተመራማሪው ዳንኤል አመንቴ (ዶ/ር)፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በድምጽ አሰጣጡ ዕለት በነቂስ በመውጣት ይበጀኛል የሚለውን ፓርቲ በነጻነት የመረጠበት ታሪካዊ ምርጫ መሆኑን አንስተዋል። አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ ጠንካራ የሕዝብ ተሳትፎ የታየበት፣ ዜጎች ምርጫን ለዴሞክራሲ ሥርዓት መዳበር ሁነኛ መሠረት መሆኑን በአግባቡ እንደተገነዘቡ ያስመሰከሩበት እንደሆነም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም እና አስተዳደር መምህርና ተመራማሪ ተስፋዬ ጂማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የምርጫው ሂደት የሃሳብና የፖሊሲ ልዩነቶችን በሕዝብ ድምጽ የመወሰን የዴሞክራሲ ባህል ልምምድ እያደገ መምጣቱን ያሳየ ነው ብለዋል። የሀገር ህልውና እና ልማት ቀጣይነት የሚረጋገጠው የዴሞክራሲ ተቋማት ሲጠናከሩ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ይበልጥ ጠንካራ ተቋማዊ አቅም ለመፍጠር የሁሉም እገዛና ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ለምርጫው ሂደት ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊነት ያደረጉት አበርክቶ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን አንስተዋል። የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የተረጋጋ ፖለቲካና የዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ዜጎች ያላቸውን ተነሳሽነት በተግባር ያሳዩበት ነው ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ የጀመረው ጉዞ ስኬታማ ሆኖ የተተለሙ ታላላቅ ሀገራዊ ግቦች እውን እንዲሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት
Jun 12, 2026 1715
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተጀመረው ጉዞ ስኬታማ ሆኖ የተተለሙ ታላላቅ ሀገራዊ ግቦች እውን እንዲሆኑ ሁሉም ዜጋ ለምክክሩ ውጤታማነት የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ኮሚሽኑ አስገነዘበ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ኮሚሽኑ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ በተለያዩ ምዕራፎች ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማካሄድ የሚያስችል አሳታፊና አካታች የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ አለመግባባቶችን በሰለጠነ ምክክር ብሔራዊ መግባባት መፍጠር የሚያስችል ምኅዳር መፈጠሩን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙ 1 ሺህ 234 ወረዳዎች፣ ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ዜጎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ የምክክር መድረክ መካሄዱን አንስተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ የእስካሁን ሂደትም ግልጽ፣ ገለልተኛ፣ አካታችና አሳታፊነቱን ጠብቆ የተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። ቀጣይም የኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በማካሄድ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በሰለጠነ ምክክር ዘላቂ መግባባት ላይ መድረስ መሆኑን አመላክተዋል። በዚህም ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ሳምንታት ያህል በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። ኢትዮጵውያንም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተደማምጠው በመመካከር የሚያቀርቧቸው ምክረ ሃሳቦችን በመተግበር ሀገርን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር የሁሉንም የጋራ ቁርጠኝነት እንደሚፈልግ አስገንዝበዋል። የጉባኤው ተሳታፊዎች ጉባኤው ከመጀመሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብለው ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ወደ ሚካሄድበት አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረድተዋል። የተተለሙ ታላላቅ የኢትዮጵያ የዕድገት ግቦች እንዲሳኩም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የተለመደውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ኮሚሽኑም ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ተስፋ የጣሉበትን ታሪካዊ የምክክር ሃላፊነት በከፍተኛ ታማኝነት፣ ገለልተኝነትና ቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሳተፉ ወደ ምክክሩ እንዲቀርቡ ጠይቀው ኮሚሽኑ ተቀብሎ ለማስተናገድ በሩ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያና ሩሲያ ፍሬያማ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ አጋርነት የበለጠ እየጎለበተ ነው -አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን
Jun 12, 2026 1463
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና ሩሲያ ፍሬያማ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ትብብር በሁሉም መስክ እየጎለበተ መሆኑን በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ገለጹ። አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያና ሩሲያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው። የሀገራቱ ፍሬያማ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ትብብርም በሁሉም መስክ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መምጣቱን ገልጸዋል። በተለይም የሀገራቱ የሁለትሽ የዲፕሎማሲ ትብብር በትምህርት፣ በንግድ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሳይንስና በሌሎች ስትራቴጂክ መስኮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል። ይህም የኢትዮ-ሩሲያ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እየተሻገረ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያና ሩሲያ ዜጎች መካከል እየጎለበተ የመጣው የባህል ልውውጥም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የበለጠ በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል። አምባሳደሩ በአዲስ አበባ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት በየዓመቱ የሚከበረው የሩሲያ ቋንቋ ቀንም በሀገራቱ መካከል ጠንካራ የባህል ዲፕሎማሲ እንዲጎለብት እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል የባህል ልውውጥን ለማሳደግ የሚከናወኑ የዲፕሎማሲ ተግባራትም የዕውቀት ሽግግርን ለማመቻቸት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በቀጣይም በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት በሁሉም መስክ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ማህበራዊ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት መጎልበትና ለቀጣናዊ ትስስር ትልቅ ሚና እያበረከተች ነው
Jun 13, 2026 549
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት መጎልበትና ለቀጣናዊ ትስስር ትልቅ ሚና እያበረከተች መሆኗን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ገለጹ። በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የነጻ ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊያ እና ሌሎች ጎረቤት ሀገራት የጤና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የጤና ዘርፍ አገልግሎቶችን፣ የጤና ተቋማትንና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ካደረጉት ጉብኝት መካከልም የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲቲዩት (AHRI) አንዱ ነው፡፡ የዚህ የመስክ ጉብኝት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነች ያለውን ተጨባጭ ሥራና ያላትን አቅም ለሰልጣኞቹ በተግባር ማሳየት እንደሆነ ተገልጿል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ እንደገለጹት፤ ጤና ድንበር የለውም፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ400 በላይ ለሚሆኑ የጎረቤት ሀገራት የጤና ባለሙያዎች ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት እያስተማረች ትገኛለች። ይህ ዓይነቱ የልምድ ልውውጥና የባለሙያዎቹ ጉብኝት በምሥራቅ አፍሪካና በአጠቃላይ በአህጉሪቱ በጤናው ዘርፍ በጋራ ለመሥራትና የቀጣናውን አቅም በጋራ ለማሳደግ ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምትሰጠው ነፃ የትምህርት ዕድል ቀጣናዊ ግንኙነትን እያጠናከረ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ድንበር የለሽ የሕክምና ዲፕሎማሲ ሚናዋን በተግባር እያሳየች ትገኛለች ብለዋል፡፡ በዚህም የአፍሪካ የጤና ሥርዓት እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኑን ጠቅሰው፣ በትምህርት ላይ የሚገኙት የውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ አጋርነትና ቀጣናዊ ሚና ዕውቅና እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኘው ዶክተር ሶቤክ ጆን በጉብኝቱ መደሰቱን ገልጾ፣ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ሥራዎችን መመልከት መቻሉን ገልጿል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጭ ዶክተር ሲሃም መሐመድ በበኩሏ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነችው ያለው ሥራ ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ብላለች። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያከናወነቻቸው ሥራዎች በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ያለችው ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጭ ዶክተር ኬጂ ጌርሚሊዮማ ናት።
በኦሮሚያ ክልል በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሠራር ይጠናከራል
Jun 13, 2026 404
አዳማ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሠራር እንደሚጠናከር የክልሉ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ገለጸ። የትራፊክ ደህንነትን ለማረጋገጥ ከክልሉ 21 ዞኖችና ከተሞች የተውጣጡ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት የምክክር መድረክ ተጠናቋል። የኦሮሚያ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ከማል ማሜ እንደገለጹት፤ በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ በቅንጅት ይሠራል ብለዋል። የትራንስፖርት አቅርቦቱን ቀልጣፋና የተሳለጠ ከማድረግ ባለፈ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት ተድርጎ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ኤጀንሲው የዘርፉን ችግሮች ለመቅረፍና አሠራሩን ወደ ዲጂታል ሥርዓት የማስገባት ሥራ በትኩረት እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በተጨማሪም የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የተቆጣጣሪዎችን አቅም መገንባት፣ የፍጥነት ገደብን መቆጣጠር፣ የተሽከርካሪዎችን የቴክኒክ ብቃት መፈተሽና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ለስኬታማነቱም ኅብረተሰቡ ስለ ትራፊክ ደህንነት ያለውን ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ፣ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። በኤጀንሲው የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ ሌችሳ ሃዩ በበኩላቸው፤ በዘርፉ የሚስተዋለውን የሥነ-ምግባር ጉድለት ለመቅረፍ በአመለካከትና በአቅም ግንባታ ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ለትራፊክ አደጋ መንስኤ የሆኑትን ሕገ-ወጥ አሠራሮች ለመግታት ከቴክኖሎጂ ጋር ራሱን የገነባና በሥነ-ምግባር የታነጸ የሰው ኃይል በመገንባት ረገድ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ራዳሮችና የአልኮል መጠን ልኬት ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ የማድረግና አጠቃቀማቸውን የማሳደግ ሥራ በስፋት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አሳምነው አብዲሳ በበኩላቸው፤ የትራፊክ ፖሊሶችና የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች ኃላፊነታቸውን በቅንጅት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በትራፊክ አደጋ ምክንያት እየደረሰ ያለውን የሕይወትና የንብረት ጉዳት ለመግታት፣ ኮሌጁ ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር በአቅም ግንባታ ላይ በስፋት እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በክልሉ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል - ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Jun 13, 2026 429
ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ተቋማትን ከማስፋፋት ባለፈ ለሰው ሀይል እና ለግብአት አቅርቦ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተገነቡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ከበቁት አዳዲስ ፕሮጀክቶች መካከል የኦክሲጂን ማምረቻ፣ የልዩ ቀዶ ሕክምና እና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል እንዲሁም የጡት ወተት ባንክ ይገኙበታል። ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በምረቃ መርሀ ግብሩ እንደተናገሩት በክልሉ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም በሀገራዊ የጤና አገልግሎት ሪፎርም መሰረት የጤና ተቋማትን የማስፋፋት፣ የውስጥ ግብአቶችን የማሟላትና የጤና ባለሙያዎችን በበቂ ሁኔታ የመመደብ ሥራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በነባርና አዳዲስ የሕክምና አገልግሎቶቹ ማህበረሰቡን በላቀ ደረጃ ለማገልገል እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ አገልግሎቶቹ ሰፍተውና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የክልሉ መንግስት ከሆስፒታሉ ጋር በቅርበት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው እንደ ሀገር የተቀመጠው የጤና ፖሊሲ በሽታን መከላከል ብቻ ሳይሆን አክሞ ለማዳንም የላቀ ትኩረት የሰጠ ነው ብለዋል። በዚህም በእናቶችና ሕፃናት ሞት መቀነስ እንዲሁም በሌሎች የጤና አገልግሎቶች ላይ በተሰሩ ስራዎች ስኬቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት። በሆስፒታሉ እውን የተደረገው የጡት ወተት ባንክ በተለይ ጨቅላ ሕፃናትን ለመንከባከብና ከሞት ለመታደግ ቁልፍ ሚና እንዳለውም አስረድተዋል። የኦክሲጅን እና የሕክምና ጋዝ ማምረቻ ለሆስፒታሉ እና በአጎራባች ለሚገኙ የጤና ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት አቅም ያለው ነው ብለዋል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) ዛሬ ለተመረቁት ፕሮጀክቶች ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉንና በጀቱም ከፌዴራል መንግስት የተገኘ መሆኑ ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በሲዳማ ክልልና በአጎራባች አካባቢዎች ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁመው የተመረቁት ፕሮጀክቶች ይህን አገልግሎቱን በተሻለ ጥራት መስጠት ያስችሉታል ነው ያሉት። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍፁም ወልደገብርኤል በበኩላቸው ሆስፒታሉ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት አሰራሮችን ከማሻሻል ባለፈ አዳዲስ አገልግሎቶችን እያሰፋ መሆኑን ተናግረዋል።
የጤና አገልግሎት ጥራትና ደህንነትን ይበልጥ ማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተተገበሩ ነው
Jun 13, 2026 283
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ የጤና አገልግሎት ጥራትና ደህንነትን ይበልጥ ማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተተገበሩ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በጤና ክብካቤ ጥራትና ደህንነት ሰርተፊኬሽንና አክሪዲቴሽን ፕሮግራም ትግበራ ዝግጁነት ላይ ያተኮረ በተግባር የተደገፈ የልምድ ልውውጥና የመማማሪያ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት በጤና ሚኒስቴር የጤና ሥርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አባስ ሐሰን እንደገለጹት፤ መንግሥት ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም ተደራሽነቱ የሰፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ባለፉት ዓመታትም የጤናውን ዘርፍ ውጤታማነት ማረጋገጥና የጤና አገልግሎት ጥራትና ደህንነትን ማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞችን ቀርጾ ወደ ተግባር ማስገባት መቻሉን ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት የተሻለ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡበትን አቅም ለመገንባት ከአጋርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የአክሪዲቴሽን ፕሮግራሙን በተመለከተም ከኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኢንስቲትዩትና ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን ስታንዳርዶችንና የትግበራ ማዕቀፎችን ሲያዘጋጁ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። የሀገሪቱን የጤና አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ፣ ተቋማቱ ወደ አክሪዲቴሽን ሥርዓት እንዲገቡ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀው ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ 32 የሚሆኑ የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት የአክሪዲቴሽን ሥርዓቱን ትግበራ እንዲጀምሩ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይ አምስት ዓመታት በርካታ የጤና ተቋማትን ወደዚህ ሥርዓት ለማስገባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሠራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያና ምሥራቅ አፍሪካ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ፣ መድረኩ የጤና ተቋማትን የአገልግሎት ጥራትና ደህንነት አቅም ለመገንባትና አፈጻጸማቸውን ገምግሞ ዕውቅና ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ፌዴሬሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወክላቸው 31 ሺህ የግል የጤና ተቋማት ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ ሕክምና እንዲሰጡ ከጤና ሚኒስቴርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ተቋማቱ ወደ አክሪዲቴሽን ትግበራ እንዲገቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ፣ በዘርፉ እውቅና ለሚያገኙ ተቋማት የሚሰጠውን ማበረታቻ የሚወስን ብሔራዊ የአክሪዲቴሽን ፍኖተ-ካርታ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ኢኮኖሚ
በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባለፈ የሥራ ባህል እያሳደገ ነው
Jun 13, 2026 359
ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባለፈ የሥራ ባህላቸው እንዲቀየር አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተጠቃሚዎች ገለጹ። በከተማዋ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው እየተፋጠነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት የተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎችን አካቶ እየተገነባ መሆኑም ተመላክቷል። በልማቱ በሥራ ዕድሉ ተጠቃሚ ከሆኑ ወጣቶች መካከል ኤርሚያስ ዳዊት እና ማለዳ ማቴዎስ በከተማው የተጀመረው የወንዝ ዳርቻ ልማት የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በልማቱ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው የተናገሩት ወጣቶቹ፣ በዚህም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ከማሳደግ ባለፈ ምሽት ጭምር በመስራት የሥራ ባህላቸው እየተቀየረ መምጣቱን ተናግረዋል። ሠርተው በሚያገኙት ገቢ ቤተሰቦቻቸውን እየደገፉና የራሳቸውን ጥሪት ለማፍራት እያገዛቸው መሆኑንም ገልጸዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማቱን እያከናወነ የ ሚገኘው ስራ ተቋራጭ ባለቤት አቶ ከበደ ተካ በበኩላቸው፣ የልማት ስራውን ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ቀንና ምሽት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በቅንጅት እየተከናወነ ባለው የመጀመሪያ ዙር የወንዝ ዳርቻ ልማት ለ70 ሰዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸው፣ ልማቱ ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማት የከተማውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የህብረተሰቡን የሥራ ባህል በማሻሻል ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ተናግረዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተቀናጀ መሠረተ ልማት አቅርቦት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አስራት ዳዊት በበኩላቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራውን በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ልማቱ በሁለት ሄክታር ላይ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው አምፊ ቴአትር፣ ፋውንቴኖች፣ ሰው ሰራሽ ሐይቅ፣ የተሽከርካሪ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ እንዲሁም የተለያዩ መዝናኛና ማረፊያ ቦታዎች እንደሚኖሩት አስረድተዋል። የሥራ ተቋራጩ በውሉ መሰረት ሥራውን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ ፈጥኖ ለማጠናቀቅም ቀንና ምሽት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ለልማት ሥራው ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተያዘ ሲሆን ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ የከተማዋን ገጽታ እንደሚቀይረው ተናግረዋል። በተጨማሪም የቱሪስት ፍሰትን ለማሳደግ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና የከተማዋን ገቢ ከማሳደግ አንጻር ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ ሥራው በልዩ ትኩረት እየተመራ ይገኛል ነው ያሉት።
የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ከትራንስፖርትም ባለፈ ለንግድና ኢንቨስትመንት ትልቅ አቅም ነው
Jun 13, 2026 215
ደብረ ማርቆስ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር ከትራንስፖርትም ባለፈ ለንግድና ኢንቨስትመንት ትልቅ እንደሚሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የክልል ኤርፖርቶች ፋሲሊቲ ኃላፊ ተወልደ ግርማይ ገለጹ። አየር መንገዱ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚያደርገውን የቅድመ ምረቃ በረራ በዛሬው እለት ጀምሯል። ኃላፊው ለኢዜአ እንደገለጹት የደብረ ማርቆስና አካባቢው ህብረተሰብ የቆየ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጥያቄ በመንግስት በተሰጠው ትኩረት ምላሽ አግኝቷል። በዛሬው እለትም የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩን ተናግረው በተለያዩ አካባቢዎች የዜጎችን የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት ፍላጎት የማሳለጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። አውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት መጀመሩ ለአካባቢው ከትራንስፖርትም ባሻገር ለንግድና ኢንቨትስመንት እንዲሁም ለቱሪዝም ሴክተሩ ትልቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ስለሺ ተመስገን፤ የደብረ ማርቆስና አካባቢው ህብረተሰብ የአየር ትራንስፖርት የረዥም ጊዜ ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ ትልቅ ደስታ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩም የከተማውንና የአካባቢውን የኢንቨስተመንት፣ የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማፋጠን የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል። የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ በበኩላቸው የአየር ትራንስፖርቱ ለዘመናት የነበረውን ፍትሃዊ የልማት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በበረራው ከተሳተፉት መካከል አቶ ባየ ገሰሰ እና ወይዘሮ ቃልኪዳን በረከት አየር መንገዱ በረራ በመጀመሩ መደሰታቸውን ተናግረዋል። የአካባቢውን ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ መሰረት አድርጎ መንግስት ፈጣን ተግባራዊ ምላሽ በመስጠቱም እናመሰግናለን ብለዋል።
በአማራ ክልል የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ኢንቨስትመንትና ቱሪዝምን እያነቃቃ ነው
Jun 13, 2026 221
ወልድያ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን የክልሉ ከተማና መሰረት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የአማራ ክልል ከተማና መሰረት ልማት ቢሮ ክልላዊ የኮሪደር ልማት ልምድ ልውውጥና የግምገማ መድረክ በወልድያ ከተማ ተካሂዷል። የቢሮ ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት የክልሉ ከተሞችን ለነዋሪዎች፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በተለይም የመኪና፣ የብስክሌትና የእግረኛ መንገድ እንዲሁም የመዝናኛ የአረንጓዴ ስፍራና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን አካቶ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማፋጠን መሰረት እየጣለ ነው ብለዋል። የኮሪደር ልማት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ጠንካራ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት ማዕከላት መፈጠራቸውን ገልጸው፤ ይህም ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት መነቃቃት ታላቅ ተስፋ ይዞ መጥቷል ብለዋል። ባዛሬው የልምድ ልውውጥና የግምገማ መድረክም የተሻለ የሰሩ ከተሞች ለሌሎች ልምዳቸውን በማካፈል በቀጣይ ከተሞች ተቀራራቢ እድገት እንዲያስመዘገቡ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርጫት ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ደሳለኝ በበኩላቸው ከተሞችን በኮሪደር ልማት ለማስዋብና ገጽታቸውን ለመቀየር የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል ብለዋል። ልማቱ የከተሞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቀስቃሴ ከማሳደግ ባለፈ የገጠሩን እድገት ለማፋጠን እንደሚያስችለም አመልክተዋል። የባህር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ በበኩላቸው፣ በባህር ዳር የተገነባው የኮሪደር ልማት የጣና ሐይቅን ጸጋ የገለጠና የከተማዋን ውበት ይበልጥ ያደመቀ መሆኑን ተናግረዋል። የኮሪደሩ ልማቱ የተሽከርካሪ፣ የሳይክልና የእግረኛ መንገድ፣ የመዝናኛ ስፍራ፣ የአረንጓዴ ሰፍራና ሌሎች ልማቶችን ማካተቱን ጠቁመው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል። በጎንደር ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረት ልማት መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ በጎንደር የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለቱሪዝም እንቅስቃሴና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል። በተለይ የፋሲል ግንብን፣ የሰሜን ተራሮችንና ሌሎች የመስህብ ስፍራዎችን ሊጎበኙ የሚመጡ የውጭና የአገር ውስጥ ቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም አዎንታዊ ለውጥ አምጥቷል ብለዋል። ልማቱ የቀጣዩን ትውልድ እድገት ጭምር መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው "መድረኩም ልምዳችንን ለሌሎች ከተሞች ለማጋራትና ክፍተታችን ለመሙላት ያስቻለ ነው" ብለዋል። በኮሪደር ልማት ደሴ ከተማን ማስዋብና ማሳመር ተችሏል ያሉት ደግሞ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ናቸው። በመድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል፣ የከተማና የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።
በክልሉ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል
Jun 13, 2026 231
ባህር ዳር፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ለመኸር ሰብል ልማት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሙሽራ ሲሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በክልሉ በ2018/2019 የምርት ዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ ግብዓትን ለአርሶ አደሩ በወቅቱ የማቅረብ ሥራ እየተሰራ ነው። ለምርት ዘመኑ 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን ከ4 ሚሊዮን 822 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያን ወደ ክልሉ በማጓጓዝ ለአርሶ አደሩ የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁንም ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚሆነው እንደተሰራጨ የገለጹት ዳይሬክተሯ፤ የማዳበሪያ አቅርቦቱ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪም በምርት ዘመኑ 220 ሺህ ኩንታል የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘር ለማቅረብ በታቀደው መሰረት እስካሁን 137 ሺህ 675 ኩንታል ለአርሶ አደሩ ደርሷል ብለዋል። የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦቱ በወቅቱ መካሄዱ አርሶ አደሩ ምርታማነቱን በማሳደግ የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባሻገር ለገበያ የሚተርፍ ምርት በአይነት፣ በብዛትና በጥራት እንዲያመርት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክተዋል። "በመኸር ምርቱ ምንም አይነት የግብዓት አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም እየተሰራ ነው" ያሉት ወይዘሮ ሙሽራ፣ አስፈላጊውን ግብአት ለማቅረብ በየደረጃው በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ ማይነት ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ንጋቴ ጎሸ እንደገለጹት ለዘር የሚያስፈልጋቸውን አምስት ኩንታል ማዳበሪያ ቀድሞ ማግኘታቸው የዘር ሥራቸውን ያለምንም ችግር ለማከናወን አግዟቸዋል። በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ እንጉቲ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ስሜነህ አበረ በበኩላቸው፤ የዘንድሮው የግብርና ግብዓት አቅርቦት ወቅቱን ጠብቆ መከናወኑን ተናግረዋል። ይህም የዘር ሥራቸውን ፈጥነው በማከናወን የተሻለ ምርት እንዲያገኙ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ነው ያስታወቁት። በአማራ ክልል በመኸር ወቅት 5 ነጥ 6 ሚሊየን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በማልማት ከ205 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደስራ መገባቱን ከቢሮው የተገ መረጃ ያስረዳል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
'’ብቃት'’ የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ በክህሎት የተቀረጹ፣ ተወዳደሪና በስራ ዓለም ብቁ የሆኑ ወጣቶችን ማፍራት ያስችላል
Jun 13, 2026 286
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ '’ብቃት'’ የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም በክህሎት የተቀረጹ፣ ተወዳደሪና በስራ ዓለም ብቁ የሆኑ ወጣቶችን ማፍራት እንደሚያስችል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰሎሞን ሶካ ገለጹ፡፡ ፕሮግራሙ ከዚህ ቀደም በ11 ከተሞች ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን ዛሬ ይፋ በሆነው ፕሮግራም 16 ተጨማሪ ከተሞች የተካተቱ ሲሆን በዚህም ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ለሁለት ዓመት የሚቆየው ይህ መርሐ ግብር የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍና ስትራቴጂያዊ ትብብሩን ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተመልክቷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰሎሞን ሶካ በመድረኩ እንደገለጹት፤ መንግሥት የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት በተሟላ መንገድ ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በተለይ ከለውጡ ወዲህ በርካታ ዜጎች በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውን በማገዝ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ በተለይም የወጣቶችን የሥራ ዕድል አማራጭ ለማስፋት በመደበኛነት ከሚከናወኑ ተግባራት በተጨማሪ፣ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር "ብቃት" የተሰኘውን የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይህ ፕሮግራም በከተሞች የሚኖሩ ወጣቶችን በተለያዩ ተቋማት በማሰማራት የሥራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው፤ ወጣቶቹ በቆይታቸው ከሚያገኙት የተግባር ዕውቀት ባሻገር የሥራ ልምድ እንዲያገኙና በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡ የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል። ይህ የሥራ ላይ ልምምድ መርሃ ግብር በቀጣይ በሚከናወነው የማስፋፊያ ሥራ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 29 የሆኑ፣ 12ኛ ክፍልና ከዚያ በታች የሆኑ ሴቶችንና ወጣቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡ ወደ ፕሮግራሙ የምትገቡ አዳዲስ ከተሞች ከነባር ከተሞች የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቅሰም ለላቀ ውጤት መዘጋጀት አለባችሁ ሲሉም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አስፋው ለገሰ፤ ''ብቃት'' የተሰኘው የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የስድስት ወር የሥራ ላይ ሥልጠና ቆይታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ፕሮግራሙ የከተማዋ ወጣቶች በመረጡት ዘርፍ ሥልጥነው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ትልቅ አቅም መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አወቀ ዘመነ በበኩላቸው፤ "ብቃት" የተሰኘው የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም በክልሉ ሰባት ከተሞች ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ ፕሮግራሙ በክልሉ 12ኛ ክፍል እና ከዚያ በታች የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ወጣቶች ተጠቃሚ ለማድረግ ጉልህ ሚና እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡
በክልሉ የፈጠራ ሥራዎችን በመደገፍ ለሁለንተናዊ ልማት ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ይጠናከራል
Jun 13, 2026 264
ቡታጅራ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን በመደገፍ ለሁለንተናዊ ልማት ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ። በክልሉ "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሳይንስ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የውይይት መድረክና አውደ ርዕይ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለጹት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ለሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ፋይዳቸው የጎላ ነው። በክልሉም ግብርናና ኢንዱስትሪን ጨምሮ በሌሎች የልማት መስኮች የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ የፈጠራ ሥራዎችን በመደገፍ ለሁለንተናዊ ልማት የሚኖራቸውን አበርክቶ ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በዘርፉ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት በትምህርት ተቋማት ላይ ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልጸዋል። የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው እንዳሉት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች የማህበረሰቡን ችግር በመፍታት በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው። የፈጠራ ባለቤቶችን በማበረታታትና ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ በዘርፉ እየተመዘገበ ያለውን ስኬት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የምርምር ሥራዎችን ለኢንዱስትሪዎች በማሸጋገር ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ማድረግ ይገባል ያሉት ደግሞ የክልሉ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ሙስጠፋ ኢሳ ናቸው። በክልሉ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን ከማፍለቅ በተጨማሪ ተኪ ምርት በማምረት በኩል የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢንተርፕራይዞቹ ለሌሎች ወጣቶችም የሥራ ዕድል እየፈጠሩ መሆኑን ጠቁመው፣ የዘርፉን ስኬቶች ለማጠናከር ቢሮው አበክሮ ይሰራል ብለዋል። ከዚህ ቀደም በምርምር ለከናወነው የተፈጥሮ ማዳበሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና እንደተሰጠው የተናገረው ወጣት ተመስገን በቀለ፣ በክልሉ በተደረገለት ድጋፍና ክትትል በእንሰት በሽታ መከላከል የሚያስችል ምርምር ማድረጉን ተናግሯል። በመድረኩ ማጠቃለያ በቡታጅራ ከተማ በተዘጋጀ 3ኛው ዙር ክልላዊ የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ ለእይታ ከቀረቡ 146 የፈጠራ ሥራዎች ለተሻሉት እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።
የኦዲት ሥራን ዲጂታላይዝ በማድረግ የኦዲት ውጤት ጥራት እንዲኖረው እየተሰራ ነው
Jun 13, 2026 225
አዳማ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የኦዲት ሥራን ዲጂታላይዝ በማድረግ ኦዲተሮች ሥራቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያከናውኑና የኦዲት ውጤት ጥራት እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ። መሥሪያ ቤቱ ከክልሉ ለተውጣጡ ከ300 በላይ ኦዲተሮችና አመራሮች በአዲሱ የክዋኔ ኦዲት እና የፋይናንሺያል ኦዲት ማንዋል ላይ ያዘጋጀው የአምስት ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በሥልጠናው ማጠቃለያ የተገኙት የክልሉ ምክትል ዋና ኦዲተር ቶሎሣ አቡማ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ የኦዲት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማስፋት ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ የዲጂታላይዜሽን አሠራር ሙሉ በሙሉ ይተገበራል። ለዚህም የክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኦዲተሮች ማኅበር ያወጣውን መሥፈርትና ደረጃ መሠረት ያደረገ አዲስ የክዋኔና የፋይናንሺያል ኦዲት ማንዋል ማዘጋጀቱን ጠቁመዋል። ሥልጠናውም የኦዲት አገልግሎቱን ዘመናዊ፣ ሙያዊ እና በዓለም አቀፍ መርሆች ላይ የተመሠረተ የለውጥ ጉዞ በክልሉ ለማስጀመር ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። የኦዲት አሠራርን ከወረቀት ንክኪ በማላቀቅ የኦዲት ሥነ-ምግባርን ለማክበርና ግልጽነትን ለመፍጠርም ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ኦዲት የሚደረጉ መሥሪያ ቤቶች ቁጥርና የመንግሥት በጀት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው፣ ይህንን ሊመጥን የሚችል የዲጂታላይዜሽን አሠራር መዘርጋቱን ምክትል ዋና ኦዲተሩ አስረድተዋል። ይህም ኦዲተሮች ሥራቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያከናውኑና የኦዲት ውጤት ጥራት እንዲኖረው ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል። የክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የፋይናንስ ኦዲት ዳይሬክተር እንዳልካቸው ታደሰ፤ ሥልጠናው በፍጥነት እየተለወጠ ካለው ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ሁኔታ ጋር ራስን ለማብቃት ገንቢ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ሌላው የሥልጠናው ተሳታፊ አቶ ጢቄ አብዲሳ በበኩላቸው፣ የኦዲተር ሙያ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትን ከብክነት መጠበቅ በመሆኑ ይህንን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሥልጠናው ዘመኑን የዋጀ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ገረመው አስፋ የተባሉ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው፣ አዲሱ ማንዋል የኦዲት ሥራን ከኋላ ቀር አሠራር ለመውጣትና የኦዲት ጥራትን ለማሻሻል ጠንካራ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንግልትንና አላስፈላጊ ወጪን በማስቀረት፣ ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል
Jun 13, 2026 201
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ መጀመሩ እንግልትንና አላስፈላጊ ወጪን በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ ተገልጋዮች ገለጹ። ዜጎች በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚገጥማቸውን እንግልትና ቅሬታ ለመፍታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ወደ ሥራ የገባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መንግስት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት በማላቅ ላይ ይገኛል፡፡ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በመንግሥት አገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ የተገልጋዮችን እርካታ እያሳደገ ይገኛል፡፡ ኢዜአ በመዲናዋ አገልግሎት መስጠት ላይ ከሚገኙት ማዕከላት መካከል በአዲስ ከተማ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የ"አዲስ መሶብ" ቅርንጫፎችን የአገልግሎት አሰጣጥ በመቃኘት ተገልጋዮችን አነጋግሯል፡፡ በማዕከሉ ያነጋገርናቸው አካል ጉዳተኛዋ ወይዘሮ ዘነበች አለኝታ፤ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቢሮ መመላለስ በራሱ ትልቅ ፈተና እንደነበር ገልጸዋል። ዛሬ ወደ ማዕከሉ ከገቡበት ሰዓት ጀምሮ ጉዳያቸውን ጨርሰው እስከሚወጡ ድረስ ያለው ሂደት እጅግ የተቀላጠፈ መሆኑንና በተለይም ለአካል ጉዳተኞችና ለአቅመ ደካሞች ልዩ ትኩረትና ቅድሚያ መስጠቱ ቀደም ሲል ይገጥማቸው የነበረውን እንግልት መቅረፉን ተናግረዋል። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአንድ ማዕከል ተገልጋይ ኢንስፔክተር የኔነሽ መርጋ የማዕከሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ግልጽነትን በመፍጠር መጉላላትን ማስቀረቱን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አቶ መኳንንት ይንገስ እና ወይዘሮ ዳቤልቱ ቲቻ የሰራተኞቹ መልካም መስተንግዶና ቅልጥፍና አገልግሎቱን በፍጥነት አግኝተው ያለምንም መስተጓጎል ወደ እለት ተእለት ስራቸው እንዲመለሱ በእጅጉ እንደረዳቸው ጠቁመዋል። የአገልግሎቱን አሰጣጥ በተመለከተ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ሰጪ ባለሙያ የሆኑት ይስሀቅ ተስፋዬ፤ ተገልጋዮች የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት መቻላቸው እንግልት ማስቀረቱን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአንድ ማዕከል ባለሙያዋ አቢጊያ ቁምላቸው፤ በማዕከሉ ያሉ አገልግሎቶች በሙሉ ዲጂታላይዝድ መደረጋቸውን ገልጻ ይህም ቀደም ሲል በወረቀት አሰራር ወቅት የነበረውን የፋይል መጥፋትና መዘግየት ችግር ሙሉ በሙሉ በመፍታት፣ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ አሰራር መዘርጋቱን አብራርታለች። የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ ማስረሻ፤ ተቋማቸው ፈጣንና ቀልጣፋ አሰራርን በማስፈን የህዝቡን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ከፍተኛ የህዝብ ፍላጎት ባለባቸው የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የአገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን በየጊዜው እያሻሻሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ስፖርት
በተጠባቂው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ብራዚል እና ሞሮኮ አቻ ተለያዩ
Jun 14, 2026 191
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሶስት ተጠባቂ መርሐ ግብር ብራዚል እና ሞሮኮ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ከእኩለ ሌሊት በኋላ በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እስማኤል ሳይባሪ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሞሮኮ መሪ ሆናለች። ቪኒሸስ ጁኒየር በ32ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ብራዚልን አቻ አድርጓል። በጨዋታው ሞሮኮ ማራኪ እና ፍሰት ያለው የጨዋታ እንቅስቃሴ አድርጋለች። ብራዚል በክንፍ መስመር ተጫዋቾቿ ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ስታደርግ ለመመልከት ተችሏል። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል። ሁለቱ ሀገራት በምድቡ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። ሞሮኮ ከስኮትላንድ፣ ብራዚል ከሀይቲ ቀጣይ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ ሶስት ሌላኛው መርሐ ግብር ሀይቲ ከስኮትላንድ ከሌሊቱ 10 ሰዓት በቦስተን ስታዲየም ይጫወታሉ።
ስዊዘርላንድ እና ኳታር አቻ ተለያዩ
Jun 13, 2026 231
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት መርሐ ግብር ስዊዘርላንድ እና ኳታር ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሬል ኢምቦሎ በ17ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ጎሉን ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ስዊዘርላንድ መሪ ሆናለች። ይህም በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በፍጹም ቅጣት ምት የተቆጠረ የመጀመሪያ ግብ ሆኗል። ቦዓለም ኩኪ በ95ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ለኳታር ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝቷል። በጨዋታው ስዊዘርላንድ ብልጫ የወሰደች ቢሆንም ያገኘቻቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀም አልቻለችም። ውጤቱን ተከትሎ ስዊዘርላንድ እና ኳታር በውድድሩ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና አንድ አቻ ተለያይተዋል። ካናዳ ከኳታር፣ ስዊዘርላንድ ከቦሲኒያ ሄርዞጎቪና በቀጣይ በምድቡ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሀገርን ስም የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን የማፍራት ተግባሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ
Jun 13, 2026 291
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ እውቅ አትሌቶችንና ስፖርተኞችን የማፍራት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የስፖርት ክለብ እንዲሁም የሙዚቃና ቴአትር ቡድን የተመሠረቱበትን 40ኛ ዓመት በዓል ባከበሩበት መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ለታዋቂዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ የተሰጠ ሲሆን፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ በስፖርት ክለቡና በኪነ-ጥበብ ቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል። የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የኮሚሽኑ የስፖርት ክለብ ባለፉት 40 ዓመታት በሀገሪቱ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ማሳረፉን ገልጸዋል። የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ ያደረጉ እውቅ አትሌቶችንና ስፖርተኞችን በማፍራት በኩል ተቋሙ የተጫወተው ሚና የላቀ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኮሚሽኑ በስፖርትና በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የጀመራቸውን አበረታች ሥራዎች ይበልጥ ዘመናዊ በማድረግ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አስገንዝበዋል። የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚላኩ ታራሚዎችን አምራችና ሕግ አክባሪ ዜጋ አድርጎ የማውጣት ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም መሆኑን አስታውቀዋል። ይህን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት የስፖርት ክለቡ እንዲሁም የሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ የሕግ ማረም ሥራውን በጥበብና በማስረጽ፣ እንዲሁም በስፖርት የአካል ብቃት በማጎልበት ታራሚውን እያዝናኑና እያስተማሩ በመቅረጽ በኩል ሚናቸው የላቀ ነው ብለዋል። ሁለቱም ክፍሎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተለይም የስፖርት ክለቡ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረኮች የሀገርን ስም ያስጠሩ በርካታ ጀግና ስፖርተኞችን ያፈራ መሆኑን ገልጸዋል። በአትሌቲክሱ ዘርፍ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊትና ጥቁር ሴት የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነችውን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን፣ ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን፣ አትሌት ስለሺ ስህን እንዲሁም የማራቶን ጀግናዋን ፋጡማ ሮባን ማፍራቱን በኩራት አስታውሰዋል። በተመሳሳይ መልኩ የሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ደማቅ አሻራ ያሳረፉና ለሀገር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ በርካታ የጥበብ ባለሙያዎችን ለሀገር ማበርከቱን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤ ለማዘጋጀት ተመረጠች
Jun 13, 2026 300
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና ጉባኤ (Global Education Conference) እንድታስተናግድ መመረጧን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ ለስፖርት ልማት በተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን ዓለም አቀፍ የስፖርት ኩነቶች ለማዘጋጀት ጥረት እያደረገች ትገኛለች። እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና ጉባኤ (Global Education Conference) እንድታስተናግድ መመረጧን ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አዘጋጅነት በየጊዜው በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ አንድምታ ያለው ሁነት መሆኑ ተገልጿል። ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2018 በቻይና ቤጂንግ፣ በ2022 በአውስትራሊያ ሲድኒ እንዲሁም በ2024 በፈረንሳይ ሀገር መካሄዱ ይታወሳል። ይህ ጉባኤ በአፍሪካ ደረጃ ሲካሄድ የመጀመሪያው በመሆኑ ለኢትዮጵያ የገፅታ ግንባታ እና ለስፖርት ቱሪዝም እድገት ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ በተጨማሪ፣ በአህጉር አቀፍ ደረጃ የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴውን የበለጠ በማጎልበትና ንፁህ ስፖርትን በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል። ጉባኤው ኢትዮጵያ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመደበኛ የትምህርት ስርዓት ውስጥ አካትቶ መተግበርን፣ በቂ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ተግባራዊ ማድረግን፣ እንዲሁም ጠንካራ የምርመራና ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግን ጨምሮ ያስመዘገበቻቸውን በርካታ ውጤቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአግባቡ ለማስገንዘብ ተጨማሪ እድል እንደሚፈጥር የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ስኬታማ ለማድረግ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ይጠናከራሉ
Jun 13, 2026 409
ጋምቤላ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በክልሉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ስኬታማ ለማድረግ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ይጠናከራሉ ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን በማስመልከት የዕውቅና መርሃ ግብር ዛሬ በአኙዋሃ ዞን አቦቦ ወረዳ ተካሂዷል። ርዕሰ መስተዳድሯ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ ዘላቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እውን ለማድረግ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ይጠናከራሉ። በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን አስታውሰዋል። በተለይም በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር በተከናወኑ ስራዎች የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ የተፈጥሮ ሚዛን በማስጠበቅበኩል ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ነባር የተፈጥሮ የደንና የብዝሃ ህይወት ሀብትን በመጠበቅ ለዘላቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲውል በማድረግም አበረታች ስኬተቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። ለዚህም ዋነኛ ማሳያው እውቅና የተሰጠው የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ ጨምሮ የማጃንግ የተፈጥሮ ደን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል። በክልሉ በሁለቱ ዞኖች በባዮስፌር ሪዘርቭነት የተመዘገቡት ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች የአየር ንብረት ሚዛንን ከመጠበቅ ባለፈ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ልማት የላቀ አብርክቶ ያላቸው መሆኑን አመልክተዋል። በመሆኑም የደን ሀብቶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለዘላቂ ልማት ለመዋል በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳደሯ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ አበራ ስዩም በበኩላቸው የአኙዋሃ ጥብቅ ደን በባዮስፌር ሪዘርቭ መመዝገቡ ኢትዮጵያ ለብዝሃ ህይወት ሀብት ጥበቃ ያላትን ቁጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። በዞኑ በባዮስፌር ሪዘርቭ የተመዘገበው ጥብቅ ደን የተፈጥሮ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን መገንበት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። የመልካ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክትር ሰለሞን ከበደ እንዳሉት የአኙዋሃ ጥብቅ ደን በባዮስፌር ሪዘርቭነት በዩኔስኮ ሊመዘገብ የቻለው በውስጡ በያዛቸው እምቅ የእንስሳትና የዕፅዋት ብዝሃ ህይወት ሀብቶች ነው ብለዋል። የተመዘገበው ጥብቅ ደን ለሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል። በዞኑ በባዮስፌር ሪዘርቭ የተመገበው ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ኢኮሚኖሚ ግንባታ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአኙዋሃ ዞን አስተዳደሪ አቶ ኝኬው ጊሎ ናቸው። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሲሆን በውስጡ ከአንድ ሺህ በላይ የዕፅዋት፣ 327 የአእዋፍ፣ 69 የአጥቢና 17 የተሳቢ እንስሳት ዝርያዎችን እንደያዘ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
የአረንጓዴ አሻራ ልማት አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትና መሠረት እየሆነ ነው
Jun 13, 2026 215
ጭሮ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ ልማት አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትና መሠረት እየሆነን ነው ሲሉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በዘርፉ ልማት ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች ተናገሩ። በምዕራብ ሐረርጌ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሐ ግብር ከ396 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። በዞኑ ባለፉት ዓመታት ለተለያዩ ጥቅሞች የሚውሉ ችግኞች ተተክለው ለስኬት በቅተው ዘርፈ ብዙ ጥቅም በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ከዚሁ ጋር በተገናኘ የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች በአረንጓዴ አሻራ ልማት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አርሶ አደር ዘሪሁን ከበደ እና አርሶ አደር መልካሙ ተስፋዬ፣ በአረንጓዴ አሻራ በየዓመቱ የተከሏቸው ችግኞች የተራቆቱ አካባቢዎችን ከመሸፈን ባለፈ የገቢ እና የምግብ ምንጭ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ መትከል ከጀመሩ ወዲህ የመሬት ለምነትና እርጥበት እንዲጠበቅ ማስቻሉን አንስተው፤ በፍራፍሬ ልማት የተተከሉ ችግኞችም ጥቅም እየሰጡ ነው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ አሻራ ልማት አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትና መሠረት እየሆነን ነው ሲሉ ተናግረዋል። በዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቡድን መሪ አቶ ዋሴ በቀለ፤ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራዎች በብዙ መልኩ ጥቅም እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል። አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትና መሠረት እና ጥሩ የገቢ ምንጭም እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። በመሆኑም ዘንድሮም ለችግኝ ተከላው የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን አንስተው፣ በመርሐ ግብሩ ከ396 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ለችግኝ ተከላውም ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ዝግጁ መሆኑን አንስተው፣ ዕቅዱን ለማሳካት የሁላችንም ዝግጁነት ሊኖር ይገባል ብለዋል። የዞኑ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊ ተወካይ አቶ ፍጹም አማረ፤ በዞኑ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያም የታየው ተሳትፎ የልማት ሥራውን ለውጤት አብቅቶታል ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ የደን ሀብት መጠንን ከመጨመር ባለፈ፣ ለምግብ ዋስትና መሠረት እያኖረ እና አይነተኛ የሥራ ዕድልም ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።
ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ሆነዋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Jun 13, 2026 204
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6 /2018 (ኢዜአ)፦ ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል። ለዚህም ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ዝግጁ መደረጋቸውንም ገልጸዋል። አረንጓዴ ለሆነች ነገ፤ ሁላችንም ተስፋን እንትከል በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
Jun 12, 2026 601
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ፣ እንዲሁም በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት አስታወቀ። ኢንስቲትዮቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይ በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል። በዚህም ምክንያት እርጥበታማ የአየር ሁኔታው በመጠንም ሆነ በስርጭት ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተስፋፋ ይሄዳል ብሏል። በዚህም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች የሚያመልክቱ ሲሆን በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። በሚቀጥሉት ቀናት ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎችና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ጠቁሟል። የሚኖረው እርጥበት ለመኸር እርሻ፣ የበልግ ሰብል አብቃይ ለሆኑ አካባቢዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብሏል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጽ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ብሏል። በዚህም አብዛኛው አባይ፣ ላይኛው እና መካከለኛ ባሮ አኮቦ፣ ኦሞ ጊቤ፣ ላይኛው ስምጥ ሸለቆ፣ በጥቂት የገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል ብሏል። አብዛኛው ተከዜ፣ በጥቂት የላይኛው እና ታችኛው አባይ፣ ላይኛውና መካከለኛው አዋሽ፣ ኦሞ ጊቤ፣ ባሮ አኮቦ፣ ገናሌ ዳዋ፣ ዋቤሸበሌ እና የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸውም ገልጿል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 7562
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 6402
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 5226
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 5132
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 1991
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም --
Jun 5, 2026 7772
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 24, 2026 5832
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የመደመር ማሳያ ከሳምንቱ አበይት ክስተቶች መካከል የኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች በአሶሳ ከተማ ያስገነቡት የጋራ ሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የህንፃ ምረቃ ይጠቀሳል። በክልሎቹ ትብብር የተከናወነው የህንፃ ግንባታ በመደመር እሳቤ የዜጎችን የጋራ ሰላም ለማስጠበቅና የልማት ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ ጥረት ማሳያ ነው። መርሃ ግብሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) የተገኙበት ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም ላይ ያተኮረው መድረክ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የተካሄደውና በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረው ፎረምም በእዚህ ሳምንት ዐበይት ጉዳይ ነበር። ፎረሙ የተካሄደው “ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን የተዘጋጀውም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በሰላም እና ፖለቲካዊ ምክክር ማዕከል (CRPP)፣ በሶማሌ ክልል መንግስት እና በሌሎች አጋር አካላት ነው። በፎረሙ መክፈቻ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፤ መድረኩ የውጭ ተዋናዮች ሳይገቡበት የቀጣናው አካላት በራሳቸው ጉዳይ፣ ፖሊሲና እርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ብቻ የሚመክሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል። እርስ በእርስ ለመተዋወቅ፣ ግልጽነትን ለመፍጠርና ጠንካራ ትስስርን ለመገንባት የሚያስችል በመሆኑም በቀጣናው ግጭቶች ለመቀነስ በእጅጉ እንደሚረዳ ነው ያነሱት። ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ምሁራን ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቀጣናው ፈተናዎች ተጨባጭ መፍትሄና አቅጣጫ እንዲያስቀምጡም ያግዛል ብለዋል። የጉባ ላይ ብስራቶች ተግባራዊ ልማት የሳምንቱ የበረራ ቅኝታችን የሚጀምረው ወደ ሶማሌ ክልል ጎዴ ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በስፍራው እየተገነባ ያለውን የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላም በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን ለማሳካት የመሬት፣ ውሃ እና የሚያለማ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ በቂ ሃብት ያላት መሆኑን ገልጸዋል። በምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እነዚህን ካሟላን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ ነገር ማድረግ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ የኒውክለር ሃይል ማመንጫ፣ የቢሾፍቱ አየር መንገድ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የቤቶች ልማት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጓቸው የጉባ ብስራቶች መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞጆ ከተማ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው ስራ ያስጀምሩትም በዚሁ ሳምንት ነበር። በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ፣ መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክና የፎርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ነው። የፋብሪካው መገንባት የውጭ ምርት ጥገኝነት ከመቀነስ ባለፈ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት መሆኑ ታውቋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ ጉብኝት በዚሁ ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ወደ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጓዝ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። በድሬዳዋ ቆይታቸው ብርቱካንና ሌሎች የፍራፍሬ ልማት ሥራዎች እንዲሁም የእንስሳት ሀብት ልማት ስራን ተመልክተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና የግብርና ልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላ ባስተላለፉት መልእክትም የጋራ ሙለታ ተፈጥሯዊ የልማት ፀጋና ከፍታም ታሪክን፣ ውብ መልክዓ ተፈጥሮን የታደለ፣ የኢትዮጵያን ሜዳና ተራሮች ምርት የሚታፈስባቸው የማድረግ ሀገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ማሳያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ ተገኝተው 142 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርቀው ሥራ ያስጀመሩትም በዚህ ሳምንት ነበር። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር በለውጡ ዓመታት ከልማት የራቁ አካባቢዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ መሰራቱን አንስተዋል። የኮንታ ኮይሻ ወረዳ የንጽህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶች ለዚሁ ማሳያ ናቸው ብለዋል። በተመሳሳይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የንጹህ መጠጥ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች መርቀው ለአገልግሎት አብቅተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በተለይ አርብቶ አደሮች ውሃ ለማግኘት ሩቅ አካባቢዎች ሲሄዱ ይደርስባቸው የነበረን እንግልት የሚያስቀር ነው። የመስኖ ፕሮጀክቱም የክልሉ አርብቶና አርሶ አደሮች በአካባቢው ያለውን ሰፊ መሬት በማልማት ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በፕሮጀክቶቹ ምረቃ ላይ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። በሲዳማ ክልልም በፌደራል መንግስት ድጋፍ በ460 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳዬ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታም ተመርቋል። ፕሮጀክቱ 75 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ነው። በሌላ በኩል የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ከ543 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 52 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መመረቃቸው ሌላው የሳምንቱ ክስተት ነበር። በዞኑ ለምረቃ ከበቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የውሃና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ቃሉ ወረዳ በ365 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የዲርማ ወንዝ መስኖ ፕሮጀክትንም መርቀዋል። ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚደረግበት የሃዋሳ ከተማ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም በዚህ ሳምንት ተካሂዳል። ለፕሮጀክቱ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የፕሮጀክቱ ግንበታ ሲጠናቀቀ ሀዋሳ ከተማዋን ጽዱ በማድረግ የቱሪዝምና የኢንቨስመንት ማዕከልነቷን ያሳድገዋል ተብሏል። አቶ ደስታ የፕሮጀክቱ ግንባታ መንግስት ለከተሞች እድገት የሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ሲሉም ነው የጠቀሱት። የከሰም መስኖ ግድብ የከሰም መስኖ ግድብ የጥገና ማሻሻያ ፕሮጀክትም በዚሁ ሳምንት ተመርቆ ሥራ ጀመሯል። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ነው። የማሻሻያ ግንባታ መጠናቀቅ ከሚሰጠው ዘላቂ የልማት አገልግሎት ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ለዓመታት ሲፈታተን የነበረውን የጎርፍ ስጋት ያስቀራል ተብሏል። በዚህ ወቅት ሚኒስትር አብርሃም (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የከሰም መስኖ ግድብ ቀደም ሲል በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ ትልቅ ስጋት ይታይ ነበር። የጥገና ማሻሻያው በአካባቢው ማህበረሰብ የነበረውን ይህን የአደጋ ስጋት በማስቀረት ግድቡን ለታለመለት የመስኖ ልማት ለማዋል የሚያስችል ነው። ለፕሮጀክቱም 2 ቢሊዮን ብር በጀት መውጣቱን ሚኒስትሩ አንስተዋል። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡን ከስጋት ያዳነ እና በርካታ ጥቅሞች ያሉት ነው ብለዋል። የግድቡ ጥገና መጠናቀቅ የሀዝቡን የቆየ ጥያቄ የፈታ መሆኑንም አንስተዋል። የግንቦት - ታላቁ ሁነት ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ድምጻቸውን ለመስጠት የተመዘገቡበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተውታል። የፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ሂደቱን ስኬታማ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አጠቃላይ ዜጎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በዚሁ ሳምንት "ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚ ና" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአዳማ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የዜጎች ጠንካራ ተሳትፎና የዳበረ የዴሞክራሲ ልምምድ የታየበት መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅም መገናኛ ብዙሃን የላቀ ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። ከተረጅነት የመውጣት ሀገራዊ ጥረት በድሬዳዋ "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የውይይት መድረክም ሌላው የእዚህ ሳምንት ዓቢይ ጉዳይ ነው። መድረኩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የግብርና ሚኒስቴር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። በመድረኩም በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተነስቷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቂና የተሟላ የውሃ ሀብት፣ የተማረና አምራች የሆነ ወጣት የሰው ኃይል እንዲሁም ለም የመሬት ፀጋዎች ያሉባት ሀገር በመሆኗ በማልማት እድገትና ማንሳራራትን ማስቀጠል ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። ለእዚህም ዋናው መሠረታዊ ጉዳይም ያሉ አቅሞችን በመለየትና ህዝብን ወደ ላቀ ምርታማነት ደረጃ በማሸጋገር በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጡን ሥራ በላቀ ደረጃ ማስቀጠል መቻል መሆኑን አንስተዋል። ለሰላም ጥሪ የተሰጠ ምላሽ የሠላም ጥሪን የተቀበሉ የአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የመረከብ፣ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማድረግና የመልሶ ማቋቋም (ዲዲአር) መርሀግብርም በዚህ ሳምንት ተከናውኗል። በብሔራዊ ተሀድሶ ማዕከል ጠዳ ጊዜያዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትሩ መሀመድ እድሪስ የቀድሞ ታጣቂዎች ከስልጠና በኋላ ከምንም በላይ የሰላም ዘብ ሆነው የበደሉትን ህዝብ ለመካስ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ታጣቂዎቹ ሠላምን አማራጭ በማድረግና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለሠላም ያደረጉት አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ መንግስት ለሠላም ባለው ጽኑ አቋምና ፍላጎት የሠላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና እንዲያልፉ በማድረግ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ እያደረገ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በኮምቦልቻ የስልጠና ማዕከል ስልጠና የጀመሩ መሆኑ ይታወቃል። ሐረር- ፕሮጀክቶች ምረቃ የሐረሪ ክለል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝትም ሌላው የእዚህ ሳምንት ኩነት ነበር። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት በተሻለ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ። በተለይም የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት የክልሉን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የበለጠ በማሳደግ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት። በዘመናዊ ትምህርት የታነፀና በእውቀት የበለፀገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም አንስተዋል። ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ለማስቻል በአስተዳደሩ በኩል ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት 672 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በይፋ የተመረቀውም በዚህ ሳምንት ነው። በምረቃው ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን፣ የክልሉ የመንገዶች ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢድሪስ ሙሴ እና ሌሎችም ተገኝተዋል። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እንደገለጹት ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት የከተማውን የንግድ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚያስችል ነው። የከተማውን ገፅታ በመለወጥ ረገድም የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ያነሱት። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው የመንገድ ፕሮጀክቱ የጂግጂጋ ከተማን ልማትና ዕድገት በማፋጠን በኩል ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የመንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን አስተዳደሩ ሀገራዊ የመንገድ መሰረተ ልማት ዕቅድን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ የመንገድ ፕሮጀክትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ 7 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 30 ሜትር ስፋት እንዳለውም ታውቋል።
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 5420
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
ትንታኔዎች
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 1991
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው?
Jun 12, 2026 897
የጤና ነገር … በዮሐንስ ደርበው የሰው ልጅ ሊሻሻሉ በሚችሉ እና በማይችሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለልብ ህመም ሊጋለጥ እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የአዋቂ የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሃኑ ሞገስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የልብ ህመም ከተወሳሰብ ዘላቂ የጤና እክል እስከ ድንገተኛ ኅልፈት ያደርሳል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ሰዎች ማሻሻል በሚችሏቸው (ሞዲፋይብል) እና ማሻሻል በማይችሏቸው (ነን ሞዲፋይብል ወይም ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች) ለልብ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዶክተር ብርሃኑ ይገልጻሉ። መሻሻል ከሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም (በአግባቡ መድኃኒቱ ካልተወሰደ)፣ተገቢ ያልሆነ የስብ ክምችት፣ ከፍተኛ ውፍረት (ክብደት)፣ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብ አለመኖር እንዲሁም አብዝቶ ስኳር፣ ጣፋጭና አልኮል መጠቀም የሚሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ እንዲሁም ሰዎች ማሻሻል ከማይችሏቸው (ተፈጥሯዊ) አጋላጮች መካከል፤ በቤተሰብ የሚተላለፍ መኖሩን፣ በዕድሜ መጨመር የሚከሰት መሆኑን (ለምሳሌ፡- ወንድ ከ45 ሴት ከ55 ዓመት በላይ ሲሆናቸው ለልብ ህመም ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን) እንዲሁም ወንዶ ከሴቶች በይበልጥ ለልብ ህመም ተጋላጭ የመሆናቸው አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም የልብ ህመም ምልክቶች የደረት ውጋት በግራ በኩል ወይም መሐል ላይ፣ ከወትሮው የተለየ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት መኖር፣ የሰውነት በተለይም እግር አካባቢ እብጠት፣ ራስን መሳት እና ሳል የልብና ተያያዥ ህመም ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ አብራርተዋል። የልብን ጤናን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ጤናማ አመጋገብን መከተል እንደሚገባ የሚመክሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ አትክልት ማዘውተር፣ ምግብ ሲዘጋጅም ፈሳሽ ዘይት መጠቀም፣ ስኳር፣ ጨው እና ጣፋጭ ነገሮችን መገደብ ከተቻለም ማስወገድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህም ብስክሌት መንዳት፣ በእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ዋና መዋኘት፣ እስከሚያልብ እና የልብ ምት እስከሚጨምር ብሎም እስከሚደክሙ የአካል ብቃት መሥራት የልብን ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽዖ አለው ነው ያሉት፡፡ ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ “ቦዲ ማስ ኢንዴክስ (ቢ ኤም አይ)” ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 እንዲሆን ይመከራል ብለዋል፡፡ ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠቀም፣ የስኳር ህመምና ከፍተኛ ደም ግፊት ካለም የመድኃኒት አወሳሰድን አለማስተጓጎል፣ አመጋገብ ላይ ስብ አለማብዛትና አብዝቶ አለመቀመጥ የልብ ህመምን ለመከላከል እንደሚያግዙ ነው ያስረዱት፡፡ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች የሆኑ ጤናማ ሰዎች ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ባሉ ጊዜያት አንድ ጊዜ፣ ዕድሜያቸው ከ45 በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም የልብ ህመም ያለባቸው እንደሁኔታው በየጊዜው ክትትል እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከልብ ህመም እንዲጠብቁ መክረው፤ ከዚህ ያለፈ ችግር ሲኖር ቶሎ የሕክምና ክትትል ማድረግ እና “ዛሬ ነገ” በማለት ጊዜ እያባከኑ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማይገባቸው አሳስበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ጤና #የልብ_ህመም
ባሳለፍነው ሳምንት …
Jun 7, 2026 2881
ባሳለፍነው ሳምንት … ከግንቦት 23 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ባሳለፍነው ሳምንት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለመራጮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምርጫው ወቅት ድምጽ ስለሰጡ መራጮች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል ብለዋል። ማገልገል መታደል መሆኑን ገልጸው፤ ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይህንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ ሲሉም አስገንዝበዋል። ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 22 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን ይሸፍናል። ይህ ፕሮጀክት የማይቆራረጥ የልማት ሥራችን ኅያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሀገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት ከያዘው የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል። ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፤ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን ሲሉም አመላክተዋል። የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳን የያዘ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ እንዲሁም ከእንጦጦ እስከ ቀበና ባለው መስመር የሚከናወነው መጠነ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽንም፤ ከወንዞቹ ባሻገር እስከ 50 ሜትር የሚዘልቅ መሆኑን አስረድተዋል። የአረንጓዴ ኮሪደሮችን፣ የሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን እና የንግድ ቦታዎችን ልማት ማካተቱን ጠቅሰው፤ ከተማዋን በእጅጉ የቀየረ ነው ብለዋል። የወንዝ ዳርቻዎችን ገጽታ እና አገልግሎት ከማሻሻል ባለፈ በኮንስትራክሽን፣ በኢንጂነሪንግ፣ በመልክዓ-ምድር ውበት ግንባታ፣ በሎጂስቲክስ እና በተያያዙ ዘርፎች ለብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም አብራርተዋል። አብዛኛው ሥራ በሀገር ውስጥ መሐንዲሶች መቀረጹና መተግበሩ፤ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በከተማ ልማት እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላቸው ዐቅም እያደገ መምጣቱን ያሳያል ነው ያሉት። ቀደም ሲል መርዛማ ኬሚካሎች እና ቆሻሻዎች የሚጣሉባቸው፣ በወንዝ ዳርቻዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች ላይ የጎርፍ አደጋ ይጋርጡ የነበሩት እነዚህ አካባቢዎች፤ አሁን ላይ ወደ አረንጓዴ፣ ጤናማ እና ለሕይወት ምቹ ወደሆነ የከተማ ቦታነት እየተቀየሩ መሆኑንም ገልጸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታም፤ የንግድ እና የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ተቀናጅተው መገንባታቸው፤ የአካባቢ ጥበቃ እና የኢኮኖሚ ዕድገት ከዚህ ቀደም ከነበረው ያልተናበበ ሥራ ተላቀው በጥናትና በጋራ ግብ ተባብሮ መሥራት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ስለመሆኑ አመላክተዋል። ይህ ፈጣን የልማት ሥራ አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ ይበልጥ የተሳሰረች፣ በኢኮኖሚ ንቁ እና ሰውን ማዕከል ያደረገች ከተማ የማድረግ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ ላይ መሰረት የተጣለበት የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ
በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ …
Jun 3, 2026 3257
በዮሐንስ ደርበው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር ሞላወርቅ አየለ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በዓለምም ሆነ በሀገራችን አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ ስለሆነው የደም ግፊት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቆይታቸውም፤ ለደም ግፊት አጋላጭ ስለሆኑ ምክንያቶችና ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄም እንዲሁም ከመድሃኒት አወሳሰድ ጋር በተያያዘ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን እና ምክረ ሐሳቦችን አቅርበዋል። · የደም ግፊት ምንድን ነው? ደም በደም ሥሮቻችን ሲያልፍ፤ የሚለካው መጠን “የደም ግፊት” እንደሚባል ዶክተር ሞላወርቅ ያስረዳሉ። የላይኛው (ሲስቶሊክ ወይም ከፍተኛው) የደም ግፊት መጠን ልብ በምትኮማተርበት ጊዜ ደም ወደ ደም ሥር ሲረጭ የሚለካው መሆኑንም ይገልጻሉ። የታችኛው (ዲያስቶሊክ ወይም ዝቅተኛው) የደም ግፊት መጠን ደግሞ ልብ ደም ለመቀበል ለአፍታ ዕረፍት በምታገኝበት ጊዜ የሚከሰት የግፊት ደረጃ መሆኑንም ይገልጻሉ። · የደም ግፊት ደረጃዎች እና ማስጠንቀቂያቸው ዶክተር ሞላወርቅ እንደሚሉት፤ የጤናማ ሰው የደም የግፊት መጠን 120 በ 80 እና በታች መሆን ይኖርበታል። በሌላ በኩል ግን ይላሉ፤ የላይኛው ከ120 እስከ 129 የታችኛው ደግሞ ከ80 በታች ከሆነ “ከፍ ያለ ወይም የጨመረ የደም ግፊት ደረጃ” ይባላል። የላይኛው ከ130 እስከ 139 ወይም የታችኛው ከ80 እስከ 90 ከሆነ ደግሞ “ደረጃ አንድ የደም ግፊት” እንደሚባል ያስረዳሉ። የላይኛው ከ140 በላይ ሲሆን እና የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ ደግሞ “ደረጃ ሁለት የደም ግፊት” እንደሚባል ነው የሚገልጹት። በሌላ በኩል “የከፋ የደም ግፊት ደረጃ” የሚባል እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም የላይኛው ከ180 በላይ እና የታችኛው ከ120 በላይ ሲሆን ነው በማለት ያብራራሉ። · ለደም ግፊት መጨመር መንስዔዎቹ ምንድን ናቸው? በዋናነት ሁለት ዓይነት የደም ግፊት መኖሩን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ ከፍተኛ የደም ግፊት እና መንስዔው የሚታወቅ የደም ግፊት መሆኑን አስረድተዋል። በዋናነት ወይም በአብዛኛው ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ ደም ግፊት የሚባለው መሆኑን ገልጸው፤ በርካታ መንስዔዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ቢገመትም ሁሉም በውል እንደማይታወቁ ያነሳሉ። ከበርካታ መንስዔዎቹ መካከልም፤ በቤተሰብ የሚወረስ (ተላላፊ)፣ አካባቢያዊ ምክንያቶች እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ የሚሉት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል። የአኗኗር ዘይቤ ሲባልም፤ የአመጋገብ ሥርዓት በተለይም ጨው የበዛበት ምግብ፣ ክብደት መጨመር፣ አካባቢያዊ ሁኔታዎች (አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ)፣ የስኳር ታማሚ መሆን የሚሉት ይጠቀሳሉ ይላሉ። · ለደም ግፊት በተለይም እነማን ተጋላጭ ናቸው? ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የደም ግፊት የመከሰት ዕድሉም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በዚህም መሠረት ባብዛኛው ዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። እንዲም በቤተሰብ የደም ግፊት ኬዝ ያለባቸው ሰዎች፣ የማንነት ሁኔታ (ኢትኒክ ግሩፕ) ለምሳሌ፡- በጥቁሮች (አፍሪካውያን)፣ በኤስያውያን፣ በደቡብ ኤስያውያን ላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ሊከሰት እንደሚችል ይገልጻሉ። እንደ ዶክተር ሞላወርቅ ማብራሪያ፤ በአጠቃላይ አጋላጭ ምክንያቶች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ። አንደኛው፡- ልንከላከላቸው (ልንቀንሳቸው) የምንችላቸው መሆናቸውን በመግለጽ ይህም የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል፣ ክብደት መቀነስ፣ አልኮልና ሲጋራ ማቆም እና መሰል መሆናቸውን አብራርተዋል። ሁለተኛው፡- ልንከላከላቸው የማንችላቸው መሆናቸውን ገልጸው ይህም፤ የዕድሜ መጨመር፣ የማንነት ሁኔታ (ኢትኒሲቲ) እና በቤተሰብ የሚተላለፍ የሚሉትን ጠቅሰዋል። · የደም ግፊትን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል? የደም ግፊ ከተከሰተ መቆጣጠር እንጅ ማዳን እንደማይቻል ገልጸው፤ ከላይ እንደተጠቀሰው አስቀድሞ መከላከል ወይም ማዘግየት የሚቻል እና መከላከል የማይቻል የደም ግፊት ደረጃ መኖሩን አስረድተዋል። · የደም ግፊት በውል የሚታወቅ ምልክት አለው? የደም ግፊት ሲከሰት ምልክት እንደሌለው በማንሳት፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ “ዝምተኛው ገዳይ” እስከመባል መድረሱን ዶክተር ሞላወርቅ ያነሳሉ። ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ግን፤ በአንድ ወይም በሁለት የሰውነት አካል ላይ ችግር ሊደርስ እንደሚችል ከዚህም ሲያልፍ እስከ ሞት እንደሚያደርስ ይጠቅሳሉ። በተያያዘም፤ የራስ ምታት፣ የዐይን ብዥ ብዥ ማለት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የድካም ስሜት፣ አንገት የመያዝ ዓይነት ስሜቶች የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ሊስተዋሉ የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል። አክለውም፤ በአብዛኛው በሕብረተሰቡ ላይ የደም ግፊት ምልክት ሳያሳይ ከፍተኛ ደረጃ ይደርስና ድንገት በጨመረ ጊዜ፤ ለሞት፣ ለአደጋ፣ ለልብ ድካም፣ አጣዳፊ ለሆነ የልብ ህመም፣ በጭንቅላት ላይ የደም መፍሰስ፣ የኩላሊት ድክመት፣ በደም ሥሮች በአግባቡ ደም እንዳይተላለፍ ማድረግ፣ ለዐይነ ስውርነት መዳረግን ጨምሮ መሰል ጉዳቶችን ሊያስከትል እንደሚችል አስገንዝበዋል። · መድኃኒት አወሳሰድ ላይ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ዶክተር ሞላወርቅ እንደገለጹት፤ አንድ ሰው ደም ግፊት እንዳለበት ከተነገረው በኋላ ሕክምናውም እንደ ደም ግፊቱ ደረጃ ይለያያል። ይህንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ የላይኛው ከ120 እስከ 129 ከሆነ “የጨመረ ግፊት” ይባላል፤ እዚህ ላይ ሰውየው ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አመጋገቡን እንዲያስተካክል፣ ስፖርት እንዲሠራ፣ ክብደት እንዲቀንስ፣ ሱስ (ሲጋራ፣ አልኮል) እንዲቀንስ ክትትል ይደረጋል ብለዋል። ስለዚህ መድኃኒት ሳይጀምር የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል የደም ግፊቱን ሊቀንሰው (ሊቆጣጠረው) ይችላል ማለት ነው ሲሉም ይገልጻሉ። “ደረጃ አንድ ግፊት” የሚለው ላይ ከደረሱ ግን ሕክምና የሚጀምሩም የማይጀምሩም እንዳሉ ተናግረዋል። ይህም ማለት የላይኛው ከ130 እስከ 139 የታችኛው ከ80 እስከ 90 ከደረሰ ሕክምና የሚጀምሩት የስኳር ህመም ያለባቸው፣ የስትሮክ ህመም ያለባቸው፣ ከልብና ደም ሥር የተገናኙ ህመሞች ያሉባቸው ከሆኑ ቢያንስ አንድ የግፊት መድኃኒት መጀመርና ክትትል ማድረግ አለባቸው ይላሉ። በሌላ በኩል ግን ይላሉ ዶክተር ሞላወርቅ፤ ሰዎች “ደረጃ ሁለት ግፊት” ላይ ከደረሱ (የላይኛው ከ140 የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ) ሁሉም መድኃኒት መጀመር እንዳለባቸው በአጽንዖት ገልጸዋል። የሚጀምሩት መድኃኒትም አሁን ባለው በተሻሻለው የሕክምና ዘይቤ ሁለት መድኃኒቶች የሚጀምሩበት ሁኔታ እንዳለ ነው የሚያስረዱት። የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ግን ለሁሉም የግፊት ዓይነቶች መሠረት (የሚመከር) መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ መድኃኒት ጀምሬያለሁ ብሎ የአኗኗር ዘይቤው ላይ ቸልተኝነት ሊኖር እንደማይገባም ነው የሚመከሩት። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከግፊት ጋር በተያያዘ ወደ ሆስፒታል መጥተው የሚታከሙ ታካሚዎች አብዛኞቹ፤ ጀምረው ያቋረጡ፣ ለመጀመር ፍላጎት የሌላቸው፣ ቅድመ ምርመራ ባለማድረግ ምክንያት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ የተጎዱ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። ስለዚህ የግፊት መድኃኒት ከተጀመረ ሊቋረጥ እንደማይችል አስጠንቅቀዋል። በየጊዜው ክትትል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አክለዋል። በሂደት እንደ ግፊቱ ሁኔታ መድኃኒቶች ሊቀነሱም ሊጨመሩም እንደሚችሉ አመላክተዋል። · የመስፋፋት ደረጃ የዓለም ጤና ድርጅት በ2024 ያወጣውን መረጃ ዋቢ አድርገው፤ 1/3ኛው የዓለም ሕዝቦች በደም ግፊት እንደሚጠቁ ዶክተር ሞላወርቅ አንስተዋል። ከእነዚህ መካከልም፤ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ገደማው በአንድም በሌላም ምክንያት ከደም ግፊት ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ጠቁመዋል። አብዛኞቹ የደም ግፊት ታማሚዎች ቁጥር የሚመዘገበው ደግሞ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ሀገራችንን ያካትታል ሲሉ ገልጸዋል። በሀገራችን ደረጃም ይላሉ ዶክተር ሞላወርቅ፤ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ባይኖሩም ከግፊት ጋር በተያያዘ በ2001 ላይ በ35 ሳይቶች የተጠኑ ጥናቶች ውጤቶች እንደሚያመላክቱት ከ21 እስከ 25 በመቶ ያህሉ ሕዝብ በደም ግፊት የሚጠቃ ነው ይላሉ። በአብዛኛው ደግሞ ከተማ ላይ እንደሚበዛ ጠቁመው፤ በተለይም አዲስ አበባ ላይ እስከ 30 በመቶ እንደሚደርስ የጥናቶቹ ውጤቶች ማመላከታቸውን ተናግረዋል። አብዛኞቹ ኬዞች ደግሞ ዕድሜያቸው ከፍ ያለ፣ ክብደታቸው የጨመረ፣ አልኮል እና ሲጋራ የሚጠቀሙ እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን አስረድተዋል። እንደ ዓለም አቀፍ ደረጃም ኬዙ ካለባቸው መካከል ግማሽ ያህሉ ግፊት እንዳለባቸው እንኳን እንደማያውቁ ነው የሚገልጹት። ለግፊት ሕክምና ትክክለኛ ክትትል አድርገው ግፊታቸውን በአግባቡ የሚቆጣጠሩት ከ 5 ሰዎች 1 መሆኑንም ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል። · ምክረ ሐሳብ በሀገራችን በሕብረተሰቡ ዘንድ ለደም ግፊት መለካት ኬዙ ከተገኘም የሕክምና ክትትል የማድረግ ሁኔታዎች ዝቅተኛ መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ሕብረተሰቡ የደም ግፊት ምልክት ሳያሳይ ከአካል ጉዳት እስከ ሞት ሊያደርስ እንደሚችል ተገንዝቦ፤ የደም ግፊቱን የመለካት ልምምዱን ሊያዳብር እንደሚገባ ዶክተር ሞላወርቅ መክረዋል። በሌላ በኩል እንደ ሀገራችን ባሉ ሆስፒታሎች በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም መቋረጥ (ስትሮክ) ካለባቸው ሰዎች ከ70 እስከ 85 በመቶው ከደም ግፊት ጋር በተያያዘ የሚከሰት መሆኑን ገልጸው፤ ድንገተኛ ግፊት መጨመር ከልብ እና ከደም ሥሮች ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዓለምም ሆነ እንደ ሀገር አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንደኛው ግፊት መሆኑንም አረጋግጠዋል። ስለዚህ የደም ግፊትን መለካት፣ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል፣ ከሱስ መራቅ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ለጤናማ ሕይወት ከፍተኛ ሚና እንዳለው መክረዋል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 14230
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 7870
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 13639
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 12100
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም --
Jun 5, 2026 7772
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 6796
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !