ቀጥታ፡

ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ሆነዋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6 /2018 (ኢዜአ)፦ ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።


 

ለዚህም ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ዝግጁ መደረጋቸውንም ገልጸዋል።

አረንጓዴ ለሆነች ነገ፤ ሁላችንም ተስፋን እንትከል በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም