ቀጥታ፡

በተጠባቂው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ብራዚል እና ሞሮኮ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሶስት ተጠባቂ መርሐ ግብር ብራዚል እና ሞሮኮ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ከእኩለ ሌሊት በኋላ በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እስማኤል ሳይባሪ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሞሮኮ መሪ ሆናለች።

ቪኒሸስ ጁኒየር በ32ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ብራዚልን አቻ አድርጓል።

በጨዋታው ሞሮኮ ማራኪ እና ፍሰት ያለው የጨዋታ እንቅስቃሴ አድርጋለች።

ብራዚል በክንፍ መስመር ተጫዋቾቿ ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ስታደርግ ለመመልከት ተችሏል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።

ሁለቱ ሀገራት በምድቡ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።

ሞሮኮ ከስኮትላንድ፣ ብራዚል ከሀይቲ ቀጣይ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በምድብ ሶስት ሌላኛው መርሐ ግብር ሀይቲ ከስኮትላንድ ከሌሊቱ 10 ሰዓት በቦስተን ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም