የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ሰኔ 6 /2018 (ኢዜአ) ፦በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ሰላምና የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዴሞክራሲያዊና ለሲቪል የፖለቲካ ባህል መጎልበት የፈጠርነውን ምቹ ምህዳርና ተቋማዊ አቅም ያሳየ ነው ብለዋል።
በዛሬው ዕለትም ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ጋር በመሆን፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱና በቁርጠኝነት ለተጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀውን የዕውቅና መርሃ ግብር መታደማቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጉልህ አሻራ ባሳረፈው በዚህ ምርጫ የሥልጣን ሽግግርና የፖለቲካ ፉክክር በሰላማዊ መንገድና በምርጫ ብቻ መሆኑን በማሳየት ረገድ የሲቪል ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የተጫወቱት ሚና የላቀ ነው ያሉት።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ሰላምና የዲሞክራሲ ባህል የጎለበተባት ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ አንግበን እየሠራን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ ሂደት የሲቪልና የፖለቲካ ድርጅቶችን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከርና ምህዳሩን ይበልጥ ለማስፋት መንግሥት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ጠቁመዋል።
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ