ስዊዘርላንድ እና ኳታር አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ስዊዘርላንድ እና ኳታር አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት መርሐ ግብር ስዊዘርላንድ እና ኳታር ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሬል ኢምቦሎ በ17ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ጎሉን ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ስዊዘርላንድ መሪ ሆናለች።
ይህም በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በፍጹም ቅጣት ምት የተቆጠረ የመጀመሪያ ግብ ሆኗል።
ቦዓለም ኩኪ በ95ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ለኳታር ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
በጨዋታው ስዊዘርላንድ ብልጫ የወሰደች ቢሆንም ያገኘቻቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀም አልቻለችም።
ውጤቱን ተከትሎ ስዊዘርላንድ እና ኳታር በውድድሩ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።
በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ካናዳ ከኳታር፣ ስዊዘርላንድ ከቦሲኒያ ሄርዞጎቪና በቀጣይ በምድቡ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።