አርእስተ ዜና
ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ተችሏል
Jul 25, 2024 11
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ዘመን ጁነዲ፤ የ2016 በጀት ዓመትን አጠቃላይ ክንውን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱንና ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን ተናግረዋል። በአግሮ ፕሮሰሲንግና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ እመርታ መታየቱን የጠቀሱት ምክትል ሥራ አስፈጻሚው፤ በዚህ ረገድ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም የተሳካ እንደነበር አስረድተዋል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን ነው የተናገሩት። በጨርቃጨርቅ ምርትም የጸጥታ አካላት ዩኒፎርሞችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ማስቀረት ተችሏል ነው ያሉት። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለተሰማሩ ባለኃብቶች የማበረታቻ ድጋፎችን በማድረግ ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ትልቅ ለውጥ ስለመምጣቱም ጠቅሰዋል። የሀገር ውስጥ ባለኃብቱን ለማበረታታት መንግሥት ባደረገው ጥረት የባለኃብቶቹ ተሳትፎ ከነበረበት ከ10 ወደ 50 በመቶ ማደጉን ገልፀዋል። በመሆኑም በአግሮፕሮሰሲንግና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተገኘውን ስኬት በሌሎችም ለማስፋት በዚህ በጀት ዓመት ከፍተኛ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ አምራቾች ለማቅረብ ከ124 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብዓቶችን ማቅረብ መቻሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክረው  እንዲቀጥሉ የማህበራት ሚና ከፍተኛ ነው 
Jul 25, 2024 15
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የማህበራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ገለጹ፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር አካሂዷል፡፡ በመርኃ ግብሩ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት፣ የተለያዩ የስፖርት፣ የኪነ ጥበብና የስነ ጥበብ ማህበራት ተሳትፈዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ እንደተናገሩት ሚኒስቴሩ የሀገር ፍቅር በሚገለጽባቸው የበጎ ፍቃድ አገልግሎትና የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ በስፋት በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡   ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እነዚህ ተግባራት በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲቀጥሉ ከስፖርት ፣ከኪነ ጥበብ፣ ሥነ ጥበብና ሌሎች ማህበራት ጋር በስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ማካሄዱን ገልጸዋል፡፡ በመርኃ ግብሩ የችግኝ ተከላ፣ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የተቋሙ ሰራተኛ ልጆች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍና የደም ልገሳ ተከናውኗል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት አመት ዘርፈ ብዙ የአረንጓዴ አሻራና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡ በስፖርትና በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በቅርቡ በአማራ ክልል ማህበራቱን በማሳተፍ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች የማደስና ተግባር ይከናወናል ብለዋል፡፡   የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ምንያህል ጌታቸው በበኩሉ ፤ ማህበሩ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ከመሳተፍ ጎን ለጎን በስፖርቱ ድጋፍ ለሚፈልጉ ዜጎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በተለይም የሀገራቸውን ሠንደቅ አላማ ከፍ ያደረጉ ባለውለታዎች ችግር ባጋጠማቸው ወቅት ፈጥኖ በመድረስ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን በአብነት አንስቷል፡፡ እንደዚሁም አቅም ለሌላቸው ጀማሪ ስፖርተኞች የትጥቅና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጿል፡፡ ማህበሩ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአምስት አቅመ ደካማ ዜጎችን መኖሪያ ቤት የማደስ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍና በአዲስ አመት ለ 1 ሺህ 500 ዜጎች ማዕድ ለማጋራት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡   የተቋሙ ሰራተኛና የመርኃ ግብሩ አስተባባሪ የሆነው አቶ ተዋበ መኮንን ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራና የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ በንቃት መሳተፋቸውን በማስታወስ ዘንድሮም የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጧል፡፡
በጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ የልማት ዘርፎች የተሻለ የእቅድ አፈጻጸም ተመዝግቧል - አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
Jul 25, 2024 30
ጋምቤላ ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ የልማት ዘርፎች የተሻለ የእቅድ አፈጻጸም መመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ፡፡ የክልሉ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የ2016 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ክንውን ሪፖርት አዳምጦ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል ። ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ በበጀት ዓመቱ ሲከሰቱ የነበሩ የጸጥታ ችግሮችን በመቋቋም በግብርና፣ በትምህርት፣ በገቢ አሰባሰብና በሌሎች የልማት ዘርፎች የተሻሉ አፈፃፀሞች ተመዝግበዋል። በክልሉ በ2015/16 የምርት ዘመን በክረምትና በበጋ መስኖ ከለማው 158 ሺህ ሄክታር ሰብል 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት የተሰበሰበ ሲሆን፤ ከ42 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡንም በሪፖርታቸው አመላከተዋል። ይህም የሰብል ምርት ከቀዳሚው ዓመት የተሻለ መሆኑን አንስተው፤ በተለይም የቡና ምርት ካለፈው ዓመት በሰባት ሺህ ቶን ብልጫ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳዳግ በተከናወኑ ስራዎች በበጀት ዓመቱ ከተለየዩ የገቢ አርዕስት ከ2 ቢሊዮን 367 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ2 ቢሊዮን 164 ሚሊዮን በላይ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ይህም አፈጻጸሙ 91 ነጥብ 42 ከመቶ መሆኑን ገልጸዋል። የትምህርት ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎችም በትምህርት ዘመኑ ከ194 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የቅድመ መደበኛ፣ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሪፖርቱ ጠቁመዋል። በክልሉ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ አኳያም የወባ በሽታን ከመከላከልና የእናቶችንና የህፃናት ጤና በማሻሻል ረገድም አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። ግንባታቸው የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ በተደረገው ጥረትም የሚበረታታ ሥራ መሰራቱን ርዕሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።   በአንጻሩ በተደጋጋሚ ሲከሰት የነበረው የጸጥታ ችግር፣ የበጀት እጥረት፣ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋ ማሻቀብ፣ ህገ ወጥ የወርቅ ማዕድንና የጦር መሳሪያ ዝውውር በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙ ፈተናዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ከጉባዔው አባላት መካከል አቶ ፓል ቱት በሰጡት አስተያየት በክልሉ የነበረውን የጸጥታ ችግር በመቋቋም የተከናወኑት የልማት ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው ብለዋል። በቀጣይም በክልሉ አሁን ላይ ያለውን ሰላም በዘላቂነት በማጽናት ከህዝቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና ሌብነትን አምሮ መታገል እንደሚያስፈልግ አቶ ፓል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በክልሉ የተፈጥሮ ደን ሃብት ላይ እየደረሳ ያለውን ጉዳት በመከላከል በዘላቂነት ለመጠበቅና ለመጠቀም የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንደሚስፈልግ የገለጹት ደግሞ ሌላው የጉባዔው አባል አቶ ዩኒያስ ተኮምሳ ናቸው። ጉባዔው በዛሬው ውሎው የክልሉን የ2016 የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጦ ውይይት በማድረግ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።  
በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ብልጽግናን  ለማረጋገጥ  የሚደረገው ጥረት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው- በተ.መ.ድ የሞሮኮ አምባሳደር ኦማር ሂላሊ 
Jul 25, 2024 26
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ18/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይና ለሌሎች ተምሳሌት እንደሚሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሞሮኮ አምባሳደርና ቋሚ መልክተኛ ኦማር ሂላሊ ገለጹ። በመንግስታቱ ድርጅት የሞሮኮ አምባሳደርና ቋሚ መልዕክተኛ ኦማር ሂላሊ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን ጨምሮ በኢትዮጵያ የታዩት ለውጦች አስደናቂ መሆናቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲህ ፣ ባካሄደችው የኢኮኖሚና ሁሉን አቀፍ ማሻሻያ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን ማስመዝገብ እንደቻለች በማንሳት፣ ይህም ለሀገሪቷ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ተናግረዋል። በተለይ በኢኮኖሚው ዘርፍ መንግስት በወሰዳቸው ማሻሻያዎች የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን አድንቀዋል። የአንድን ሀገር ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የመሪ ሚና ቁልፍ ነው ያሉት አምባሳደሩ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላስመዘገበቻቸው ዘርፈ ብዙ ለውጦች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሚና የላቀ መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት ለሌሎች አፍሪካዊያን ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአካባቢ ምህዳርን ለማሻሻል በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እያከናወነች ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑንም ጠቁመዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ወሰን እንደሌለው ያነሱት አምባሳደሩ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት የሌሎችን እገዛ ከመጠበቅ ይልቅ ዛፍ በመትከል ወደ መፍትሄው መሄድ ከሁሉም ይጠበቃል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሀገራት በውስጣቸው የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ኢትዮጵያ ያሳካቻቸውን መሰል ለውጦች ለማምጣት ጥረት ማድረግ አለባቸው በማለት አሳስበዋል። ከአስር አመታት በፊት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ያነሱት አምባሳደሩ፣ አዲስ አበባ አሁን ላይ በእርግጥም ትልቅ ለውጥ አሳይታለች ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።        
የሚታይ

ከጠለምት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት ተወጥቷል - የታዛቢ ቡድኑ አባላት
Jul 25, 2024 29
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ ከጠለምት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት መወጣቱን የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የታዛቢ ቡድን አባላት ተናገሩ። ከሦስቱም የጠለምት ወረዳዎች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቀያቸው ሲመለሱ ማኅበረሰቡ በደስታ ተቀብሎ ሰላማዊ ኑሮ እንዲቀጥል መደረጉንም ተናግረዋል። የአማራ ክልል የጠለምት ወረዳዎች ተልዕኮ አፈፃጸም ታዛቢና ቅሬታ ሰሚ ዓባይ መንግስቴ፤ ከፌደራል መንግሥት እንዲሁም ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጣ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋሞ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ሥራ መሥራቱን ገልፀዋል። የሁለቱ ክልሎች ታዛቢዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በሕዝባዊ ውይይት በቀጥታ የስም ዝርዝር አስተችቶ በማረጋገጥ ተፈናቃዮችን የመመለስ ሥራው በተሳካ መልኩ ተከናውኗል ብለዋል። በተፈናቃይና በተቀባይ ማኅበረሰብ መካከል የተናበበና የመረጃ ትክክለኛነት ተረጋግጦ ከሦስቱም የጠለምት ወረዳዎች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። የተፈናቀሉ ዜጎችን በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት መወጣቱን አንስተው፤ በአካባቢው የሚነሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ በመመለስ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የተቀናጀ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ትዝብታቸውን አጋርተዋል። በአካባቢው የነበሩ ታጣቂዎችን በማስወጣት መከላከያ ሠራዊት የአካበቢውን ሠላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን መታዘባቸውንም አረጋግጠዋል። በትግራይ ክልል የጠለምት ወረዳዎች ተልዕኮ አፈፃጸም ታዛቢ ታዘዘ ገብረ-ስላሴ፤ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመመለስ መከላከያ ሠራዊት፣ የሁለቱ ክልሎች ተወካዮች፣ ከተፈናቃይና ተቀባዩ ማኅበረሰብ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት የጋራ መድረክ መካሄዱንአስታውሰዋል። በመድረኩ ላይ በተደረሰ የጋራ ስምምነት መሠረትም የመመለሱ ሂደት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል ብለዋል። በዚህም ነጋዴው ወደንግዱ አርሶ አደሩ ወደእርሻ ስራው እንዲገባ መደረጉን መታዘብ እንደቻሉ አስረድተዋል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተጠናከረ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግና ለዘላቂ ሰላም በጋራ በመሥራት ልማትን ማስቀጠል እንደሚገባ የታዛቢ ቡድኑ አባላት አስገንዝበዋል። መንግሥትም በአካባቢው የሕክምና፣ የግብርና ግብዓትን ጨምሮ ሌሎችም መሠረታዊ አገልግሎቶችን የማሟላት ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። በየአካባቢው ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥም ከኅብረተሰቡ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላደረገው የላቀ አስተዋጽዖ ታዛቢዎቹ አድናቆትና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በላቀ ክህሎት ሀገራቸውን የሚያስጠሩ በርካታ ባለተሰጥኦ ወጣቶች እየተፈጠሩ ነው
Jul 25, 2024 46
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ሀገራቸውን የሚያስጠሩ በርካታ ባለተሰጥኦ ወጣቶች እየተፈጠሩ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የታዳጊ ወጣቶችን የቴክኖሎጂና ፈጠራ አቅም ለማሳደግ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የክረምት ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። በዘንድሮው ዓመትም ለሶስተኛ ዙር የሰው ሰራሽ አስተውሎት የክረምት ሥልጠና ከመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 200 ተማሪዎችን አወዳድሮ ለይቷል፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር ኢ/ር)፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በትኩረት መስራት ለሀገር እድገት መሰረት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ ለዘርፉ እድገት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ለተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ባሻገር አዳዲስ እውቀት የሚያገኙበት የተደራጀ የክረምት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር ሥልጠና ተሰጥኦዎቻቸውን ወደ ውጤት በመቀየር ከግል ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት የሚችሉበት እድል ስለመፈጠሩም አስታውሰዋል። በመሆኑም የክረምት የታዳጊዎች ስልጠና ኢትዮጵያን በምርምርና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍ የሚያደርጉ ዓለምን የሚለውጡ ወጣቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የክረምት የታዳጊዎች ሥልጠና ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ዓለምን የሚያስጠሩ ባለተሰጥኦ ወጣቶች ባለቤት መሆኗን አሳይቶናል ነው ያሉት፡፡ ወጣቶች የላቀ እውቀትና ሀሳብ እንዳላቸው ገልጸው፤ አቅማቸውን አውጥተው መጠቀም የሚችሉበትን እድል ማመቻቸት ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ለሥልጠናው በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ ምቹ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች፣ ቤተ ሙከራዎች እና መሰል ግብዓቶች የተሟሉለት ማዕከል መገንባቱን ገልጸዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ሽግግር ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገለጸ
Jul 25, 2024 105
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ሽግግር እንዲሁም በአለም አቀፍ ጌትዌይ ስትራቴጂ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በ4ኛው ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤ (FfD) የዝግጅት ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከተገኙት የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ አጋርነት (INTPA) የዘላቂ ፋይናንስ ዳይሬክተር አንቲ ካርሁነን ጋር ተወያይተዋል።   በቅርቡ በጎፋ ዞን የደረሰው የመሬት ናዳ ባስከተለው አሰቃቂ የሰው ህይወት መጥፋት በአውሮፓ ህብረት ስም የተሰማቸውን ሀዘን ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል። የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና አሁን ላይ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ፌደራል የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ጋር እየሰራ በሚገኘው ቡድን በኩል እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በበኩላቸው ለአውሮፓ ህብረት ፈጣን ምላሽ አድናቆታቸውን ገልፀው ከአፋጣኝ ሰብአዊ ድጋፍ ጎን ለጎን ዘላቂ የአየር ንብረት መላመድ ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥተዋል። በሁለትዮሽ ውይይቱ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረትም ተመልክቷል። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ ማብራራታቸውም ተጠቁሟል። በመሆኑም የሽግግር የፍትህ ስርዓት የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ሊጠናቀቅ መቃረቡን ገልጸው በተጨማሪም የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወሳኝ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ማሻሻያ I ላይ ገለፃ በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት እና የኢንቨስትመንት መስህብነት በማጎልበት የተመዘገቡ ስኬቶችን አውስተዋል። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የሀገር ውስጥ ግጭቶች እና በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰቱ እንደ ድርቅ ያሉ የአየር ንብረት ነክ ጉዳዮች አንዳንድ የማሻሻያ ጥረቶች እንዲስተጓጎሉ እንዳረጉ አመላክተዋል፡፡ የሃገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ II ሌላኛው የውይይቱ ትኩረት እንደነበርም በመረጃው ተጠቅሷል። የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ አጋርነት (INTPA) የዘላቂ ፋይናንስ ዳይሬክተር አንቲ ካርሁነን የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ሽግግር እንዲሁም በአለም አቀፍ ጌትዌይ ስትራቴጂን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን መግለጻቸውም ተመላክቷል። በአውሮፓ ህብረት ሁለገብ አመታዊ አመላካች ፕሮግራም (MIP) ስር ለኢትዮጵያ የተመደበውን 650 ሚሊዮን ዩሮ አንዱ የድጋፉ አካል መሆኑን ማንሳታቸውም እንዲሁ። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ የኢትዮጵያን በሁለገብ አመታዊ አመላካች ፕሮግራም (MIP) በማቀድና ትግበራ ላይ ማሳተፍ በሀገሪቱ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ ረገድ ያለውን ጠቀሜታ አስገንዝበዋል። ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ወሳኝ የሆነው የአውሮፓ ህብረት የበጀት ድጋፍ እንደገና እንዲጀመርም ጥሪ አቅርበዋል። በአዲሱ የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ-ነጻ ደንብ (EUDR) ስጋት እንዳደረባቸው መግለጻቸውም ተጠቅሷል። የተጣደፈ ትግበራ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ቡና አምራቾችን ሊጎዳ እንደሚችል እና የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ-ነጻ ደንብ (EUDR) ከአለም አቀፍ የአየር ንብረት ስምምነቶች ትክክለኛ የሽግግር መርሆዎች ጋር ሙሉ በሙሉ መጣጣም እንዳለበትም አንስተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ የEUDR መስፈርቶችን ለማሟላት ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀው ለትግበራው የሚረዳ ተጨማሪ ግዜ እንደሚያስፈልግ ማመላከታቸውን በመረጃው ተመላክቷል፡፡
ፖለቲካ
በሀገረ-መንግሥት ግንባታም ሆነ በሀገራዊ ምክክሩ ሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ይሠራል-ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
Jul 25, 2024 82
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በሀገረ-መንግሥት ግንባታም ሆነ በሀገራዊ ምክክሩ ሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ይሠራል ሲሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) መንግስት ባለፉት አመታት ሲሰራበት የቆየውና ዜጎችም ሲጠየቁ የኖሩት በሀገራዊ ምክክር አማካኝነት መሰረታዊ ችግሮችን በውይይት የመፍታት እሳቤ አሁን ላይ ወሳኝ ሊባል በሚችል ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሀገረ-መንግስት ግንባታም ሆነ በሀገራዊ ምክክሩ ሴቶች የተሟላና ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ መድረኮችን ሲያመቻችና የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱን አንስተዋል፡፡   እንደ ሀገር በሚፈጠሩ አለመግባባቶች እና የሃሳብ ልዩነቶች ግንባር ቀደም ተጎጂዎች ሴቶች መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሯ አካታች ሀገራዊ ምክክር ማካሔድ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና ተቀራርቦ የመስራት ባህልን ለማጎልበት ጉልህ አስተዋፆ ስለሚያበረክት ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል። ጥምረት ለሴቶች ድምፅ ካለፈው መጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ጊዜያት በስምንት ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በመዘዋወር በሺዎች ለሚቆጠሩ ሴቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት አጀንዳዎቻቸውን የማሰባሰብ እና የማጠናቀር ተግባር ሲያከናውን መቆየቱን በመጠቆም ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።   የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አሸናፊ ሆነን እንውጣ ከተባለ መመካከር አለብን በምክክሩም ሴቶችን ይዘን መውጣት አለብን ብለዋል። የሴቶች አጀንዳ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ነው ሲሉም ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።   የጥምረት ለሴቶች ድምፅ ፕሬዝዳንት ሳባ ገ/መድህን በበኩላቸው በአገራዊ የምክክር መድረክ በሴቶች ተገቢውን ውክልና አግኝተው የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ መሆኑንም መግለጻቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በክልሉ ሠላምን በዘላቂነት ለማስፈን ህዝቡ ዋነኛ  ባለቤት ሆኖ መንቀሳቀስ አለበት 
Jul 25, 2024 77
ሰቆጣ፤ ሐምሌ 18/2016 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ዘላቂ ሠላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በየአካባቢው ያለው ህዝብ ዋነኛ የሠላም ባለቤት ሆኖ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተገለጸ። ''ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሠላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ነው።   በዚህ ወቅት የብሔረሰብ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃይሉ ግርማይ እንዳመለከቱት፤ በአካባቢው አጋጥሞ በነበረው ችግር ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ደርሷል። ችግሩን በሰለጠነ አግባብ በጠረጴዛ ዙሪያ በሠላም እንዲፈታ በህብረተሰቡ ዘንድ በተደጋጋሚ ሲጠየቅ እንደቆየ አውስተው፤ ለዚህም መንግስት ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ሠላምና መረጋጋት በዘላቂነት ለማስቀጠል የፀጥታ አካላት ከሚያከናወኑት ተግባራት ባለፈ በየአካባቢው ያለው ህዝብ ዋነኛ የሠላም ባለቤት ሆኖ መንቀሳቀስ እንዳለበት አመልክተዋል።    
በሀገራዊ የምክክር ሂደትና የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞች የሴቶች ትብብርና ተሳትፎ እያደገ ነው
Jul 25, 2024 296
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በሀገራዊ የምክክር ሂደትና የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞች የሴቶች ትብብር፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ዘሀራ ኡመድ ገለጹ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ኃብትና የማኅበራዊ ልማት ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እመርታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ባሉ ብሔራዊ ኢኒሼቲቮችና የልማት ሥራዎች ሴቶች በብዛትና በንቃት ከመሳተፍ ባለፈ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸው ይታወቃል። የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ዘሀራ ኡመድ፤ በዚህ ረገድ ለተገኘው ስኬት ሀገር እየመራ የሚገኘው ፓርቲ ሚናውን በመወጣቱ መሆኑን ተናግረዋል። በሀገራዊ የምክክር ሂደትና የተለያዩ ሀገራዊ የልማት ፕሮግራሞች የሴቶች ትብብርና ተሳትፎ በተጨባጭ እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል። በሀገራዊ ምክክር ሂደት የሴቶች ተሳትፎ 50 በመቶ እንዲሆን ኮሚሽኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተሳትፎው እንዲጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በሀገራዊ የምክክር ሂደትና የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞች የሴቶች ትብብር፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን ጨምሮ በሌማት ትሩፋት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ሌሎችም የልማት ተግባራትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሴቶች በንቃት እየተሳተፉና ተጠቃሚም እየሆኑ ነው ብለዋል። በዘንድሮው ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ6 ሚሊየን በላይ ሴቶች እየተሳተፉ መሆኑንም ወይዘሮ ዘሀራ ለአብነት ጠቅሰዋል። በብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አማካኝነት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው "ምግቤን ከጓሮዬ፤ ጤናዬን ከምግቤ'' የሚለው ንቅናቄም በሀገር አቀፍ ደረጃ በስኬት እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል። በአረንጓዴ አሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብሮችም የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቅሰዋል።      
በመዲናዋ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ህዝብን ያሳተፈ ስራ መሰራቱ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል
Jul 25, 2024 165
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመዲናዋ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ቢሮው ህዝብን ያሳተፈ ስራ መስራቱ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል ። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመዲናዋ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝብን ያሳተፈ ስራ መስራቱ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን ገልጿል። ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት አቅዶ ሲያከናውናቸው በነበሩ ተግባራት እና በ2017 የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አመራሮች ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል።   በዚሁ ወቅት የቢሮው ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተማዋ ያስተናገደቻቸው ሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ በዓላት ትውፊታቸውን ጠብቀው በሰላም ተከብረው ማለፋቸውን ገልፀዋል፡፡ ለዚህ ስኬት መሰረቱ ደግሞ ህዝቡ የሰላም ባለቤት በመሆን ያበረከተው አስተዋጽኦ መሆኑን ጠቅሰዋል። በከተማዋ የሚፈፀሙ ልዩ ልዩ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል እና ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ቢሮው ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡ በተለይም ህዝቡ ከሰላም ሰራዊት ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።   ለአብነትም በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፣ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም አዋኪ ድርጊቶችን መከላከል መቻሉን ገልፀዋል ። በአጠቃላይ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመዲናዋ የወንጀል ድርጊት የመፈፀም ምጣኔን ወደ 31 በመቶ ዝቅ ማድረግ የተቻለበት ነው ሲሉ አክለዋል ። በቀጣይም የከተማዋን ብሎም የማህበረሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ እና የወንጀል ድርጊትን ለመከላከል የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።  
በተያዘው በጀት አመት የክልሉን የውስጥ አቅሞችና ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም የህዝቡን ጉልህ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
Jul 25, 2024 217
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በተያዘው በጀት አመት የክልሉን የውስጥ አቅሞችና ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም የህዝቡን ጉልህ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ሲሆን በዛሬው እለት በክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት አመት እቅድ፣ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ በክልሉ በጀትና ሌሎች ቀሪ አጀንዳዎች ላይ በዝርዝር እየተወያየ ይገኛል።   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ለምክር ቤቱ የ2017 በጀት አመት እቅድ ባቀረቡበት ወቅት የክልሉን የውስጥ አቅሞችና ምቹ ሁኔታዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋልና የህዝቡን ጉልህ ተሳትፎና ድጋፍ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ይሰራል ብለዋል። በክልሉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረው ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት። በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት የሚተገበሩ እቅዶችን ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር ውይይቶች እና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ አጀንዳዎች መለየት መቻሉንም ጠቁመዋል። በበጀት ዓመቱ ከዚህ ቀደም የነበሩ መልካም ልምዶችን ማስቀጠል እንዲሁም መታረም የሚገባቸውን ጉድለቶች በመለየት ለላቀ የህዝብ ተጠቃሚነት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። የምክር ቤት አባላት በርዕሰ መስተዳድሩ በቀረበው የ2017 በጀት አመት እቅድ ላይ ውይይት እያካሔዱ እንደሚገኙ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በጋምቤላ ክልል ፈተናዎችን በጽናት በማለፍ ለህዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል - አፈ ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ
Jul 25, 2024 128
ጋምቤላ ፤ሐምሌ 18/2016 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ፈተናዎችን በጽናት በማለፍ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑት ስራዎች አበረታች እንደሆኑ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ባንቻየሁ ድንገታ ገለጹ። የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡   የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ ጉባዔውን ሲከፍቱ እንደገለጹት በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጋጥሞ የነበረው የጸጥታ ችግር በልማት ስራዎች ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ የነበረ መሆኑን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ የጸጥታ ችግሩ ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ በጽናት በማለፍ በበጀት ዓመቱ የታለሙ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን በመፈጸም ረገድ አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በርካታ ሰራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ሰሌዳ መፈጸማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል። እንዲሁም የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ አዳዲስ አዋጆችን ከማውጣት ባለፈ የወጡ ህጎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን እየተከታተለ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ በኩልም በምክር ቤቱ አጥጋቢ ስራዎች መከናወናቸውን አፈ ጉባኤዋ ገልጸዋል። ጉባዔው ከዛሬ ጀምሮ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታ የ2016 የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ ክንውን፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርት አድምጦ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ፣ በማስፈጸሚያ በጀትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ከወጣው የድርጊት መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። በጉባዔው ላይ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከ350 በላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።  

ማህበራዊ
የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክረው  እንዲቀጥሉ የማህበራት ሚና ከፍተኛ ነው 
Jul 25, 2024 15
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የማህበራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ገለጹ፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር አካሂዷል፡፡ በመርኃ ግብሩ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት፣ የተለያዩ የስፖርት፣ የኪነ ጥበብና የስነ ጥበብ ማህበራት ተሳትፈዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ እንደተናገሩት ሚኒስቴሩ የሀገር ፍቅር በሚገለጽባቸው የበጎ ፍቃድ አገልግሎትና የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ በስፋት በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡   ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እነዚህ ተግባራት በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲቀጥሉ ከስፖርት ፣ከኪነ ጥበብ፣ ሥነ ጥበብና ሌሎች ማህበራት ጋር በስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ማካሄዱን ገልጸዋል፡፡ በመርኃ ግብሩ የችግኝ ተከላ፣ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የተቋሙ ሰራተኛ ልጆች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍና የደም ልገሳ ተከናውኗል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት አመት ዘርፈ ብዙ የአረንጓዴ አሻራና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡ በስፖርትና በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በቅርቡ በአማራ ክልል ማህበራቱን በማሳተፍ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች የማደስና ተግባር ይከናወናል ብለዋል፡፡   የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ምንያህል ጌታቸው በበኩሉ ፤ ማህበሩ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ከመሳተፍ ጎን ለጎን በስፖርቱ ድጋፍ ለሚፈልጉ ዜጎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በተለይም የሀገራቸውን ሠንደቅ አላማ ከፍ ያደረጉ ባለውለታዎች ችግር ባጋጠማቸው ወቅት ፈጥኖ በመድረስ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን በአብነት አንስቷል፡፡ እንደዚሁም አቅም ለሌላቸው ጀማሪ ስፖርተኞች የትጥቅና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጿል፡፡ ማህበሩ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአምስት አቅመ ደካማ ዜጎችን መኖሪያ ቤት የማደስ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍና በአዲስ አመት ለ 1 ሺህ 500 ዜጎች ማዕድ ለማጋራት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡   የተቋሙ ሰራተኛና የመርኃ ግብሩ አስተባባሪ የሆነው አቶ ተዋበ መኮንን ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራና የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ በንቃት መሳተፋቸውን በማስታወስ ዘንድሮም የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጧል፡፡
ከጠለምት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት ተወጥቷል - የታዛቢ ቡድኑ አባላት
Jul 25, 2024 29
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ ከጠለምት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት መወጣቱን የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የታዛቢ ቡድን አባላት ተናገሩ። ከሦስቱም የጠለምት ወረዳዎች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቀያቸው ሲመለሱ ማኅበረሰቡ በደስታ ተቀብሎ ሰላማዊ ኑሮ እንዲቀጥል መደረጉንም ተናግረዋል። የአማራ ክልል የጠለምት ወረዳዎች ተልዕኮ አፈፃጸም ታዛቢና ቅሬታ ሰሚ ዓባይ መንግስቴ፤ ከፌደራል መንግሥት እንዲሁም ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጣ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋሞ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ሥራ መሥራቱን ገልፀዋል። የሁለቱ ክልሎች ታዛቢዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በሕዝባዊ ውይይት በቀጥታ የስም ዝርዝር አስተችቶ በማረጋገጥ ተፈናቃዮችን የመመለስ ሥራው በተሳካ መልኩ ተከናውኗል ብለዋል። በተፈናቃይና በተቀባይ ማኅበረሰብ መካከል የተናበበና የመረጃ ትክክለኛነት ተረጋግጦ ከሦስቱም የጠለምት ወረዳዎች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። የተፈናቀሉ ዜጎችን በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት መወጣቱን አንስተው፤ በአካባቢው የሚነሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ በመመለስ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የተቀናጀ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ትዝብታቸውን አጋርተዋል። በአካባቢው የነበሩ ታጣቂዎችን በማስወጣት መከላከያ ሠራዊት የአካበቢውን ሠላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን መታዘባቸውንም አረጋግጠዋል። በትግራይ ክልል የጠለምት ወረዳዎች ተልዕኮ አፈፃጸም ታዛቢ ታዘዘ ገብረ-ስላሴ፤ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመመለስ መከላከያ ሠራዊት፣ የሁለቱ ክልሎች ተወካዮች፣ ከተፈናቃይና ተቀባዩ ማኅበረሰብ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት የጋራ መድረክ መካሄዱንአስታውሰዋል። በመድረኩ ላይ በተደረሰ የጋራ ስምምነት መሠረትም የመመለሱ ሂደት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል ብለዋል። በዚህም ነጋዴው ወደንግዱ አርሶ አደሩ ወደእርሻ ስራው እንዲገባ መደረጉን መታዘብ እንደቻሉ አስረድተዋል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተጠናከረ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግና ለዘላቂ ሰላም በጋራ በመሥራት ልማትን ማስቀጠል እንደሚገባ የታዛቢ ቡድኑ አባላት አስገንዝበዋል። መንግሥትም በአካባቢው የሕክምና፣ የግብርና ግብዓትን ጨምሮ ሌሎችም መሠረታዊ አገልግሎቶችን የማሟላት ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። በየአካባቢው ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥም ከኅብረተሰቡ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ በመመለስ ሂደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላደረገው የላቀ አስተዋጽዖ ታዛቢዎቹ አድናቆትና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  
የክልሉን ሠላም ለማስጠበቅ  የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ድጋፋቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ
Jul 25, 2024 34
ወልዲያ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦የአማራ ክልልን ሠላም በማስጠበቅ ዘላቂ ለማድረግ በየአካባቢው የሚገኙ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ። ከሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የተሳተፉበትና በሠላም ማስከበር ዙሪያ የመከረ መድረክ በወልዲያ ከተማ ተካሄዷል። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤መንግስት የተሟላ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ህብረተሰቡን ባሳተፈ አግባብ ያለሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል።   መንግስት ለሠላም ያለው ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየ መሆኑን አመልክተው፤ ለዘላቂ ሠላም መስፈን በየአካባቢው የሚገኙ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የህዝብ ተሳትፎ አማካሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬ በበኩላቸው፤ ችግሩን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዚህ መድረክ ተሳታፊዎች "የሠላም አምባሳደር ልትሆኑ ይገባል'' ብለዋል። በምክክር መድረኩ የክልልና የዞን አመራር አባላት፣ ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተሳታፊ ሆነዋል።    
የሐረርጌ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በአሸዋ የገበያ ስፍራ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ደጋፍ አደረጉ
Jul 25, 2024 33
ድሬዳዋ ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ የሐረርጌ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፅህፈት ቤት ሠራተኞች በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ። በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት የማቋቋም ስራ እንደቀጠለ ነው። የሐረርጌ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር ጎሳ መንግስቱ (ዶ/ር) ዛሬ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ቤተክርስቲያኗ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖችን በመደገፍ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች። በድሬዳዋ አሸዋ የገበያ ስፍራ በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ከማፅናናት ባሻገር የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች ከሐምሌ ወር ደሞዛቸው በማወጣት ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት ሰራተኞቹ 571 ሺህ ብር በማዋጣት ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን በተግባር አረጋግጠዋል ብለዋል። በቀጣይም አጋር ድርጅቶችን እና ለጋሾችን በማስተባበር አንገብጋቢ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።   የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የገቢው አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ በበኩላቸው የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮቹ ከደሞዛቸው በማዋጣት ያደረጉት ድጋፍ በአርአያነት የሚጠቀስና የሚመሰገን በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚከናወኑ ስራዎች ስኬታማ እንዲሆን ኮሚቴው በአስተዳደሩ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በስፋት እየተነጋገረ መሆኑን ገልፀዋል። ሌሎቹም ተቋማት ይህንን መንገድ በመከተል ወገኖቹን ለማቋቋም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።      
ኢኮኖሚ
ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ተችሏል
Jul 25, 2024 11
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ዘመን ጁነዲ፤ የ2016 በጀት ዓመትን አጠቃላይ ክንውን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱንና ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን ተናግረዋል። በአግሮ ፕሮሰሲንግና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ እመርታ መታየቱን የጠቀሱት ምክትል ሥራ አስፈጻሚው፤ በዚህ ረገድ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም የተሳካ እንደነበር አስረድተዋል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን ነው የተናገሩት። በጨርቃጨርቅ ምርትም የጸጥታ አካላት ዩኒፎርሞችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ማስቀረት ተችሏል ነው ያሉት። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለተሰማሩ ባለኃብቶች የማበረታቻ ድጋፎችን በማድረግ ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ትልቅ ለውጥ ስለመምጣቱም ጠቅሰዋል። የሀገር ውስጥ ባለኃብቱን ለማበረታታት መንግሥት ባደረገው ጥረት የባለኃብቶቹ ተሳትፎ ከነበረበት ከ10 ወደ 50 በመቶ ማደጉን ገልፀዋል። በመሆኑም በአግሮፕሮሰሲንግና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተገኘውን ስኬት በሌሎችም ለማስፋት በዚህ በጀት ዓመት ከፍተኛ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ አምራቾች ለማቅረብ ከ124 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብዓቶችን ማቅረብ መቻሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
በጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ የልማት ዘርፎች የተሻለ የእቅድ አፈጻጸም ተመዝግቧል - አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
Jul 25, 2024 30
ጋምቤላ ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ የልማት ዘርፎች የተሻለ የእቅድ አፈጻጸም መመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ፡፡ የክልሉ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የ2016 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ክንውን ሪፖርት አዳምጦ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል ። ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ በበጀት ዓመቱ ሲከሰቱ የነበሩ የጸጥታ ችግሮችን በመቋቋም በግብርና፣ በትምህርት፣ በገቢ አሰባሰብና በሌሎች የልማት ዘርፎች የተሻሉ አፈፃፀሞች ተመዝግበዋል። በክልሉ በ2015/16 የምርት ዘመን በክረምትና በበጋ መስኖ ከለማው 158 ሺህ ሄክታር ሰብል 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት የተሰበሰበ ሲሆን፤ ከ42 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡንም በሪፖርታቸው አመላከተዋል። ይህም የሰብል ምርት ከቀዳሚው ዓመት የተሻለ መሆኑን አንስተው፤ በተለይም የቡና ምርት ካለፈው ዓመት በሰባት ሺህ ቶን ብልጫ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳዳግ በተከናወኑ ስራዎች በበጀት ዓመቱ ከተለየዩ የገቢ አርዕስት ከ2 ቢሊዮን 367 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ2 ቢሊዮን 164 ሚሊዮን በላይ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ይህም አፈጻጸሙ 91 ነጥብ 42 ከመቶ መሆኑን ገልጸዋል። የትምህርት ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎችም በትምህርት ዘመኑ ከ194 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የቅድመ መደበኛ፣ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሪፖርቱ ጠቁመዋል። በክልሉ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ አኳያም የወባ በሽታን ከመከላከልና የእናቶችንና የህፃናት ጤና በማሻሻል ረገድም አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። ግንባታቸው የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ በተደረገው ጥረትም የሚበረታታ ሥራ መሰራቱን ርዕሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።   በአንጻሩ በተደጋጋሚ ሲከሰት የነበረው የጸጥታ ችግር፣ የበጀት እጥረት፣ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋ ማሻቀብ፣ ህገ ወጥ የወርቅ ማዕድንና የጦር መሳሪያ ዝውውር በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙ ፈተናዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ከጉባዔው አባላት መካከል አቶ ፓል ቱት በሰጡት አስተያየት በክልሉ የነበረውን የጸጥታ ችግር በመቋቋም የተከናወኑት የልማት ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው ብለዋል። በቀጣይም በክልሉ አሁን ላይ ያለውን ሰላም በዘላቂነት በማጽናት ከህዝቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና ሌብነትን አምሮ መታገል እንደሚያስፈልግ አቶ ፓል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በክልሉ የተፈጥሮ ደን ሃብት ላይ እየደረሳ ያለውን ጉዳት በመከላከል በዘላቂነት ለመጠበቅና ለመጠቀም የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንደሚስፈልግ የገለጹት ደግሞ ሌላው የጉባዔው አባል አቶ ዩኒያስ ተኮምሳ ናቸው። ጉባዔው በዛሬው ውሎው የክልሉን የ2016 የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጦ ውይይት በማድረግ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።  
በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ብልጽግናን  ለማረጋገጥ  የሚደረገው ጥረት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው- በተ.መ.ድ የሞሮኮ አምባሳደር ኦማር ሂላሊ 
Jul 25, 2024 26
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ18/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይና ለሌሎች ተምሳሌት እንደሚሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሞሮኮ አምባሳደርና ቋሚ መልክተኛ ኦማር ሂላሊ ገለጹ። በመንግስታቱ ድርጅት የሞሮኮ አምባሳደርና ቋሚ መልዕክተኛ ኦማር ሂላሊ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን ጨምሮ በኢትዮጵያ የታዩት ለውጦች አስደናቂ መሆናቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲህ ፣ ባካሄደችው የኢኮኖሚና ሁሉን አቀፍ ማሻሻያ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን ማስመዝገብ እንደቻለች በማንሳት፣ ይህም ለሀገሪቷ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ተናግረዋል። በተለይ በኢኮኖሚው ዘርፍ መንግስት በወሰዳቸው ማሻሻያዎች የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን አድንቀዋል። የአንድን ሀገር ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የመሪ ሚና ቁልፍ ነው ያሉት አምባሳደሩ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላስመዘገበቻቸው ዘርፈ ብዙ ለውጦች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሚና የላቀ መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት ለሌሎች አፍሪካዊያን ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአካባቢ ምህዳርን ለማሻሻል በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እያከናወነች ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑንም ጠቁመዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ወሰን እንደሌለው ያነሱት አምባሳደሩ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት የሌሎችን እገዛ ከመጠበቅ ይልቅ ዛፍ በመትከል ወደ መፍትሄው መሄድ ከሁሉም ይጠበቃል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሀገራት በውስጣቸው የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ኢትዮጵያ ያሳካቻቸውን መሰል ለውጦች ለማምጣት ጥረት ማድረግ አለባቸው በማለት አሳስበዋል። ከአስር አመታት በፊት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ያነሱት አምባሳደሩ፣ አዲስ አበባ አሁን ላይ በእርግጥም ትልቅ ለውጥ አሳይታለች ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።        
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በላቀ ክህሎት ሀገራቸውን የሚያስጠሩ በርካታ ባለተሰጥኦ ወጣቶች እየተፈጠሩ ነው
Jul 25, 2024 46
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ሀገራቸውን የሚያስጠሩ በርካታ ባለተሰጥኦ ወጣቶች እየተፈጠሩ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የታዳጊ ወጣቶችን የቴክኖሎጂና ፈጠራ አቅም ለማሳደግ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የክረምት ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። በዘንድሮው ዓመትም ለሶስተኛ ዙር የሰው ሰራሽ አስተውሎት የክረምት ሥልጠና ከመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 200 ተማሪዎችን አወዳድሮ ለይቷል፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር ኢ/ር)፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በትኩረት መስራት ለሀገር እድገት መሰረት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ ለዘርፉ እድገት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ለተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ባሻገር አዳዲስ እውቀት የሚያገኙበት የተደራጀ የክረምት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር ሥልጠና ተሰጥኦዎቻቸውን ወደ ውጤት በመቀየር ከግል ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት የሚችሉበት እድል ስለመፈጠሩም አስታውሰዋል። በመሆኑም የክረምት የታዳጊዎች ስልጠና ኢትዮጵያን በምርምርና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍ የሚያደርጉ ዓለምን የሚለውጡ ወጣቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የክረምት የታዳጊዎች ሥልጠና ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ዓለምን የሚያስጠሩ ባለተሰጥኦ ወጣቶች ባለቤት መሆኗን አሳይቶናል ነው ያሉት፡፡ ወጣቶች የላቀ እውቀትና ሀሳብ እንዳላቸው ገልጸው፤ አቅማቸውን አውጥተው መጠቀም የሚችሉበትን እድል ማመቻቸት ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ለሥልጠናው በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ ምቹ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች፣ ቤተ ሙከራዎች እና መሰል ግብዓቶች የተሟሉለት ማዕከል መገንባቱን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያና የቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ የትብብር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
Jul 25, 2024 67
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና የቻይና ሦስተኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ የትብብር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በጉባዔው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሊበ ዢን እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንገዶች ተገኝተዋል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ በሚያስችል ጥረት ውስጥ መሆኗን ገልጸዋል። የኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲ በጠንካራ ግንኙነት መቀጠሉን ጠቅሰው፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ድጋፍና ትብብሩም ለድጅታል ትራንስፎርሜሸን እቅድ መሳካት የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል። ሁለቱ አገሮች በኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በመሠረተ-ልማትና ሌሎችም መስኮች ተቀራርበው መስራታቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የዛሬው መድረክም የዘርፉ ባለሙያዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል ነው ያሉት።  
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ  ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ ነው
Jul 23, 2024 448
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2016(ኢዜአ)፦የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡ ኢኒሼቲቩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና የኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 5 ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ነው፡፡ ስልጠናውም በዋናነት በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ከኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያው በተጓዳኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ኢኒሼቲቩ የትምህርት ዘርፉ ብቁ ትውልድ ለመገንባት በሚያከናውነው ስራ ላይ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል፡፡   በተለይ ትውልዱ በንድፈ ሃሳብ የሚያገኛቸውን እውቀቶች በቀላሉ ወደ ተግባር እንዲለውጥ ምቹ እድል በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላል ነው ያሉት፡፡ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው ቴክኖሎጂ ከስራ ፈጠራ ጋር የሚተሳሰር ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡   የወጣቶችን ዲጂታል አቅም ለመገንባት የተሰጠው ትኩረት ደግሞ ግብርናን ጨምሮ የተለያዩ መስኮችን ለማዘመን የተያዘውን ውጥን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው የተናገሩት፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስትን ወክለው በፓናሉ የተሳተፉት አብዱልአዚዝ አልጃዝሪ በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እውን በማደረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነት መኖሩን አንደታዘቡ ተናግረዋል፡፡   ይህ ደግሞ በኢኒሼቲቩ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ቴክኖሎጂ የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በእጅጉ እየቀየረ ስለመሆኑ አንስተው፤ ከዚህ አኳያ ለዘርፉ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡ የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት አቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያብራሩት ደግሞ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው፡፡   በእቅዱ ላይ ዲጂታል ክህሎትን መሰረት ያደረገ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት እንደተሰጠው ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም ይህን እውን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢኒሼቲቩ በኢትዮጵያ ክህሎት ያለው የሰው ሃይልን በመገንባት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአገልግሎቱ ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ዘመናዊና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እውን ማድረግ መንግስት እያከናወነ ያለው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡   ለዚህ ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች ዲጂታል ክህሎት ማደግ እንዳለበት ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያውን የሚያግዝ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡  
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያደርግ ነው - በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Jul 23, 2024 226
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2016 (ኢዜአ)፦የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያደርግ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡ ኢኒሼቲቩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 5 ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ነው፡፡ ስልጠናውም በዋናነት በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወሳኝ ከሆኑት መሰረቶች አንዱ የዲጂታል ስነ ምህዳሩን ማስፋት መሆኑን አንስተዋል፡፡ የዲጂታል ስነ ምህዳሩን ከሚያሰፉ ስራዎች መካከል ዋነኛው የክህሎት ግንባታ መሆኑን ገልጸው፤ በዘርፉ እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ማፍራት ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶች በዲጂታል ስነ ምህዳር ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን ክህሎት የሚያገኙበት መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው መስክ ወደ ፊት እንድትራመድ በር የሚከፍት መሆኑንም እንዲሁ፡፡ ኢኒሼቲቭ መንግስት ወጣቶች ለማብቃት፤ ፈጠራን ለማጎልበት እንዲሁም የዲጂታል አቅም ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እና አምራች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ክህሎት የሚያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል። አንድ ሰው የዲጂታል ክህሎት አለው የሚያስብለው ከቴክኖሎጂው ባሻገር ዘመኑን የሚዋጅ አስተሳሰብን ሲላበስ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመሆኑም ወጣቶች ከቴክኖሎጂ በተጨማሪ ህሊናዊና ባህሪያዊ የሆኑ የዲጂታል ዘመን ስብዕናን መገንባት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ለኢኒሼቲቩ ስኬታማነት የፌደራል እና የክልል የመንግስት መዋቅሮች፤ የግሉ ዘርፍ የልማት አጋሮች እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ እና ወላጆች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡   የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላ ናስር፤ ኢኒሼቲቭ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ያላቸውን አጋርነት ወደ አዲስ ምእራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ሁለቱን አገራት በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሌሎች የትብብር መስኮች ለማስተሳሰር በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡ በተያያዘ ዜናም የአስፈጻሚ አመራሮች ስልጠና መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል፡፡ ስልጠናው ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በትብብር የሚሰጡት ሲሆን፤ ከ15 የመንግስት ተቋማት የተወጣጡ አመራሮች ስልጠናውን የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ስልጠናው ስድስት ወራት የሚወስድ ሲሆን፤ በኦንላይና አካል እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡  
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የተጨዋቾች ዝውውርና የክለቦች የክፍያ አስተዳደር መመሪያ በማያከብሩ የሊጉ ክለቦች ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው
Jul 24, 2024 186
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የተጨዋቾች ዝውውርና የክለቦች የክፍያ አስተዳደር መመሪያን በሚጥሱ የሊጉ ክለቦች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳሰበ። የ2017 ዓ.ም.የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበርና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጨዋቾች ዝውውርና የክለቦች የክፍያ አስተዳደር መመሪያ አፈጻጸምን አስመልክቶ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግሮችን የተመለከተ ጥናት ከሁለት ዓመት በፊት ማስጠናቱ የሚታወስ ነው። ከጥናቱ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል አንዱ ክለቦች ያላቸው የፋይናንስ አስተዳደር እንዲሻሻል ምን መደረግ አለበት? የሚለው ላይ ሲሆን ጥናቱን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የክፍያ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ተዘጋጅቷል። ይህ መመሪያ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ማኅበሩ ባካሄደው 4ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ጸድቋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ዋና ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፤ መመሪያው ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከተጀመረው የ2017 ዓ.ም.የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ጀምሮ ተፈጻሚ መሆኑን ገልፀዋል። በመመሪያው አማካኝነት ክለቦች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዝውውር ውል ሳያጸድቅ ለተጨዋቾች አስቀድመው የቅድመ ክፍያ መፈጸምና በቼክ ገንዘብ መክፈል እንደማይችሉ አመልክተዋል። በተጨማሪም ክለቦች በዓመት ለተጨዋቾችና የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ደመወዝና ጥቅማጥቅም ከ57 ሚሊየን 750 ሺህ ብር በላይ ክፍያ መፈጸም አይችሉም ብለዋል። የሊጉ ክለቦች የተቀመጡትን አሠራሮች የሚጥሱ ከሆነ ከገንዘብ ቅጣት አንስቶ ውድድር መታገድ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ነው ሰብሳቢው የገለጹት። ክለቦች በመመሪያው ላይ ያላቸውን ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉበት የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱንም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው፤ በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ ክለቦች ተጨዋቾችን ሲያስፈርሙ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል። ክለቦች አንድ ተጨዋች ሲያስፈርሙ ፌዴሬሽኑ ዝውውሩ የተሟላ መሆኑን ይፋ የሚያደርገው የሕይወትና የአደጋ ጊዜ ኢንሹራንስ፣ የሕክምና ሰርቲፊኬት፣ የልደት ሰርቲፊኬትና በፊት ከሚጫወትበት ክለብ መልቀቂያ(ክሊራንስ) ሲያሟሉ ብቻ ነው ብለዋል። ፌዴሬሽኑ በመመሪያው አፈጻጸም ላይ ላይ ከሊጉ አክሲዮን ማኅበሩ ጋር በትብብር እንደሚሰራም አመልክተዋል። መመሪያው ለተጨዋቾችና ለአሰልጣኞች በግል የሚከፈላቸው ክፍያ ላይ ገደብ እንደማያስቀምጥና ዋንኛ ትኩረቱ ዓመታዊ ጥቅል የክለቦች ክፍያ ጣሪያ እንደሆነና ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ክፍያ ውጭ በሌሎች ወጪዎች ላይ ገደብ እንደማያስቀምጥ የአክሲዮን ማኅበሩ መረጃ ያመለክታል። ማኅበሩ የተጨዋቾችና አሰልጣኞችን አጠቃላይ ዓመታዊ ክፍያ የሚቆጣጠር ኮሚቴ ወደ ሥራ ማስገባቱ የሚታወስ ነው። የ2017 የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ እስከ መስከረም 26 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።  
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በምድብ 1 ተደለደለ
Jul 24, 2024 138
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በ2024/25 የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ዞን ማጣሪያ በምድብ 1 ተደልድሏል። ​​​​የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በተቋሙ ዋና መቀመጫ ግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ላይ አከናውኗል። ኢትዮጵያን በሴካፋ ዞን ወክሎ በማጣሪያ ውድድሩ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በምድብ 1 ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ ፣ከሩዋንዳው ራዮን ስፖርትስ፣ ከደቡብ ሱዳኑ ዬ ጆይንት ስታርስና ከዛንዚባሩ ዋሪየር ኩዊንስ ጋር ተደልድሏል።   የታንዛኒያው ሲምባ ኩዊንስ፣ የብሩንዲው ፒቪፒ ቡዬንዚ፣ የዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊምና የጅቡቲው ፋድ በምድብ 2 የተደለደሉ ክለቦች ናቸው። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከነሐሴ 11 እስከ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማጣሪያ ውድድሩ የሚሳተፈው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ነው። ንግድ ባንክ በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ሲሳተፍ የዘንድሮው ለአራተኛ ተከታታይ ዓመት ነው። ክለቡ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው ሶስት ተሳትፎዎች በሁለቱ ፍጻሜ ደርሶ ሲሸነፍ አንድ ጊዜ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ባስመዘገባቸው ውጤቶች ለካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ማለፍ አልቻለም። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአራተኛ ተሳትፎው የማጣሪያ ውድድሩን ካሸነፈ ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ ይሳተፋል። ካፍ በዘንድሮው የማጣሪያ ውድድር 38 ክለቦች በስድስት ዞኖች ተከፍለው ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ አስታውቋል።ክለቦቹ የካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ መስፈርቶችን ማሟላታቸውንም ገልጿል። በስድስቱ ዞኖች የሚያሸንፉ 6 ሀገራት፣ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሳንዳውንስና የውድድሩን የመጨረሻ ዙር የሚያዘጋጀው ሀገር ቡድን ጨምሮ 8 ክለቦች እ.አ.አ በ2025 ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማሉ። የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የተጀመረው እ.አ.አ በ2020 ነው። የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሳንዳውንስ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ያነሳ ሲሆን የሞሮኮው ኤኤስ ፋር ራባት ውድድሩን አንድ ጊዜ አሸንፏል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወንዶችም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ እንደሚሳተፍ ይታወቃል።
የ33ኛው ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ዛሬ ይጀመራል 
Jul 24, 2024 142
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2016(ኢዜአ)፦በፓሪስ የሚካሄደው 33ኛው ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ጅማሮውን ያገኛል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት 4 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ሁሉም ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች የመክፈቻ መርሐ ግብራቸውን ዛሬ ያከናውናሉ። በምድብ 3 ኡዝቤኪስታን ከስፔን እንዲሁም በምድብ 2 አርጀንቲና ከሞሮኮ በተመሳሳይ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ 1 ጊኒ ከኒውዝላንድ፣ በምድብ 3 ግብጽ ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ በተመሳሳይ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ከምሽቱ 2 ሰዓት በምድብ 2 ኢራቅ ከዩክሬንና በምድብ 4 ጃፓን ከፓራጓይ የሚጫወቱ ሲሆን በምድብ 1 አዘጋጇ ሀገር ፈረንሳይ ከአሜሪካና በምድብ 4 ማሊ ከእስራኤል በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ መርሐ ግብራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል። በተያያዘ ዜና የ33 ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ መርሐ ግብር ነገ ይጀመራል። በውድድሩ ላይ 12 ሀገራት በ3 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ 1 አዘጋጇ ሀገር ፈረንሳይ ፣ ኮሎምቢያ ፣ ካናዳና ኒውዝላንድ እንዲሁም በምድብ 2 አሜሪካ ፣ ጀርመን ፣ አውስትራሊያና ዛምቢያ ተደልድለዋል። ብራዚል ፣ ስፔን፣ ጃፓንና ናይጄሪያ በምድብ 3 የተደለደሉ ሀገራት ናቸው። የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል። በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የራግቢ ስፖርት ውድድር ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ከኦሊምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓት በፊት የእጅ ኳስና ኢላማ ተኩስ ውድድሮች እንደሚጀመሩ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መረጃ ያመለክታል። የ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስርዓት ከነገ በስቲያ ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ ከ206 ሀገራት የተውጣጡ እንዲሁም በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥላ ስር የሚወዳደሩ ገለልተኛ አትሌቶችና የኦሊምፒክ የስደተኞች ቡድን ጨምሮ 10 ሺህ 714 ስፖርተኞች በ32 የስፖርት ዓይነቶች ይሳተፋሉ። የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል።            
አካባቢ ጥበቃ
አካባቢን ጽዱና ማራኪ በማድረጉ እንቅስቃሴ የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎ ዘላቂ እንዲሆን ሊጉ አስገነዘበ
Jul 25, 2024 68
ሚዛን አማን ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ ከተሞችንና የመኖሪያ አካባቢን ጽዱና ማራኪ በማድረጉ እንቅስቃሴ ሴቶችና ወጣቶች ዘላቂ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የሴቶች ሊግ አስገነዘበ። የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ "በጎነት ለእህትማማችነት" በሚል በመሪ ቃል የክረምትና የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የጽዳት ዘመቻ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ ዛሬ አከናውኗል። በዚህ በወቅት የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የሴቶች ሊግ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አሰለፈች ታደሠ እንደተናገሩት፤ ውብና አረንጓዴ አካባቢን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ሴቶችና ወጣቶች ባህል አድርገው በዘላቂነት ሊሳተፉ ይገባል።   በዘመቻ መልክ ከሚደረገው የጽዳት መርሃ ግብር ባሻገር ሴቶችና ወጣቶች በየጊዜው ኃላፊነት ወስደው የማጽዳት ተግባሩን ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል። የመኖሪያ ቤት ዙሪያን በግል ከማስዋብ ጀምሮ ከጎረቤት ጋር ተቀናጅቶ አካባቢን ማጽዳት ለኑሮ ምቹ መንደርን ለመፍጠር የሚያስችል ተግባር በመሆኑ ሁሉም ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስበዋል። ''አሁን ላይ እንደ ሀገር በጋራ ከምንዘምትባቸው መልካም መስኮች አንዱ የአካባቢ ጽዳት ነው ያሉት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዋ ለዚህ ስኬታማነት በቁርጠኝነት ልንሳተፍ ያስፈልጋል'' ብለዋል። በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ጤንነቱ የተጠበቀ ማኅበረሰብን ለመገንባት ህብረተሰቡን ያሳተፈ ጠንካራ እንቅስቃሴ በፓርቲ ደረጃ እየተካሄደ እንደሚገኝም አመላክተዋል።   የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ብዙነሽ ዘብዴዎስ በበኩላቸው ሁሉም አካል ለቀጣይ ትውልድ ጽዱና አረንጓዴ አካባቢን ለማስረከብ ሊተጋ ይገባል ብለዋል። ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ የተነሳ የጎርፍ መፋሰሻ ቱቦዎች በቆሻሻ ሊደፈኑ እንደሚችሉ ጠቁመው ይህ እንዳይሆን አስቀድሞ ቆሻሻን በማስወገድ የከተማን ደህንነት መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል። በከተማዋ ከማኅበረሰቡ ጋር በሳምንታዊ የጽዳት መርሃ ግብር በመሳተፍ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡም ገልጸዋል። በከተማ የጽዳት መርሃ ግብሩ ላይም ከብልጽግና ፓርቲ ዋናው ጽህፈት ቤት፣ ከክልል፣ ከዞን ሴቶች ሊግ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።    
የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በዘላቂነት ለመቋቋም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ላይ በትኩረት መሠራት አለበት 
Jul 24, 2024 188
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2016 (ኢዜአ)፦ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በዘላቂነት ለመቋቋም የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን መሠረት ያደረጉ እርምጃዎች ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተጠቆመ። በዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት የአየር ንብረት ዘርፍ ተመራማሪ ተፈሪ ደጀኔ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዓለም በከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሥር ወድቃለች። ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጨመር፣ የዝናብ ሥርጭት መጠን ማነስ፣ ድርቅ፣ ጎርፍና ሌሎችም ተያያዥ ተግዳሮቶች በሰውና በእንስሳት ላይ የተለያዩ ተጽዕኖዎችን እያደረሱ መሆኑን ነው የገለጹት። በተለይም ኢንስቲትዩቱ ትኩረት አድርጎ በሚሰራው የቁም እንስሳት፣ ድርቅ በሚከሰትበት ጊዜ በውኃና በመኖ እጥረት እንዲሁም እንስሳቱ በቀላሉ ለበሽታ ተጋላጭ በመሆን ለከፍተኛ ጉዳት እየተዳረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህንንም ከፍተኛ ተጽዕኖ ለመቋቋም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ከሚረዱ ዋነኛ ጉዳዮች በቅድመ ማስጠንቀቂያ ላይ በቂ ሥራ መሥራት መሆኑን በማንሳት፤ በዚሁ ላይ የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው ምክረ-ኃሳብ ሰጥተዋል። ኢንስቲትዩቱ በዓለም ባንክ በኩል በሚደረግ ድጋፍ በስድስት የአፍሪካ አገራት በዝቅተኛ ሥፍራዎች በርካታ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና ሌሎች ተጓዳኝ የምርምር ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ከእነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን በማንሳት፤ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዋናነትም በአየር ንብረት መረጃዎች ላይ በቂ እውቀት ለመስጠትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህ ረገድ፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት መረጃን ተደራሽ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር የአየር ንብረት ተጽዕኖን ለመቋቋም እየወሰደች ያለው እርምጃም የሚበረታታ መሆኑንም ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (ኢልሪ) እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1974 አንስቶ በኢትዮጵያ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።    
በድሬዳዋ አስተዳደር በቤተሰብ ደረጃ የፍራፍሬ ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ
Jul 24, 2024 133
ድሬዳዋ፤ ሐምሌ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አስተዳደር የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነው በቤተሰብ ደረጃ የፍራፍሬ ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ተጀምሯል። የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የሆነው "አንድ ሎሚ ለአንድ ቤተሰብ" በሚል መሪ ሃሳብ የቤት ለቤት የፍራፍሬ ችግኞች ተከላው በአስተዳደሩ በወረዳ ሁለት ነው የተጀመረው። በመርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የአመራር አካላት የሎሚ፣ ፓፓያ፣ ማንጎ፣ ዘይቱን፣ ጊሽጣ፣ መንደሪን፣ ብርትኳን፣ አፕል እና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።   የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ድሬዳዋ ለከተማ ግብርና እና ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምቹና ተስማሚ ናት።   ነዋሪዎች ለዘመናት በግቢያቸው ውስጥ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በማብቀል ያከበቱትን ልምድ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ይበልጥ የማጠናከር ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻዎች የተተከሉት የፍራፍሬ ችግኞች ፍሬ መስጠት መጀመራቸውን ጠቅሰው፤ ይህም የቤተሰብ ፍጆታ ከመቻል በዘለለ ለተጨማሪ የገቢ ምንጭ እየዋለ ይገኛል ብለዋል። በአስተዳደሩ የገጠር ወረዳ ነዋሪዎችም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመሩትን ስራዎች ስኬታማ በማድረግ ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ መሆናቸውን አቶ ኑረዲን ገልጸዋል። ዛሬ "አንድ ሎሚ ለአንድ ቤተሰብ" በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው የፍራፍሬ ችግኞች ተከላ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ለማሳደግ እና የፍራፍሬ ዋጋን ለማረጋጋት ያስችላልም ብለዋል። ዘንድሮ በአረንጓዴ አሻራ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል ለምግብነት እና ለገቢ ምንጭነት የሚያገልግሉ የፍራፍሬ ችግኞች እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።   በተያያዘ ዜና በድሬዳዋ አስተዳደር ቃልቻ ገጠር ቀበሌ የተለያዩ የገጠር ማህበረሰብ እና የአመራር አካላት የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ የአስተዳደሩ ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐመድአሚን ኡመር ተገኝተዋል። አቶ መሐመድአሚን በዚሁ ወቅት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ለድሬዳዋ ጎርፍን በመከላከል፣ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመመከትና የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ዘንድሮም የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከር የተቀናጀ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን በማውሳት።  
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የትናንት፣ የዛሬ እና የነገን ትውልድ የሚያስተሳስር የእድገትና ብልጽግና መሠረት ነው - አቶ አደም ፋራህ
Jul 24, 2024 141
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2016(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የትናንት፣ የዛሬ እና የነገን ትውልድ የሚያስተሳስር የሀገር እድገትና ብልጽግና መሠረት መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ ምቹ ፕላኔት የመፍጠር ሚናዋን በብቃት እየተወጣችበት ያለ ግዙፍ ኢኒሼቲቭ መሆኑንም ተናግረዋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፤ የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ችግኞችን ተክለዋል።   በመርሃ-ግብሩ ላይ አቶ አደም ባደረጉት ንግግር፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የትናንት፣ የዛሬ እና የነገን ትውልድ የሚያስተሳስር የእድገትና ብልጽግና መሠረት መሆኑን ገልፀዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ ምቹ ፕላኔት የመፍጠር ሚናዋን በብቃት እየተወጣች ያለ ግዙፍ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ተናግረዋል። የልማት ሥራው ትላንት የተሰሩ ታሪኮችን የማስቀጠል፣ አደጋዎችን በዘላቂነት የመከላከልና ምድርን ከአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መጠበቅ የሚያስችል ነው ብለዋል። ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ገልፀዋል። ኢትዮጵያውያን በጋራ እየተገበሩት ያሉትን ሀገርን አረንጓዴ የማልበስ ሥራ ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጸው፤ ብልጽግና ፓርቲ ለመርሃ-ግብሩ መሳካት የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ይቀጥላል ብለዋል። በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ፤ አዲስ አበባን ምቹ፣ ውብና አረንጓዴ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።   በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለሰ ዓለሙ፤ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንትና የኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ ሆኗል ብለዋል።   በሁሉም የህይወት መስክ ጉልህ ፋይዳ ያለውን ይህን የአረንጓዴ ልማት ኢትዮጵያ በአርዓያነት እየከወነች ነው ያሉት ኃላፊው፤ ይህንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ተናግረዋል። የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሳዳት ነሻ፤ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ከመትከል በላይ ሀገርን አረንጓዴ የማልበስና ምርታማነትን የማሳደግ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።   ኢትዮጵያውያን ከሚያለያዩ ነገሮች ይልቅ የሚያሰባስቡና ሀገርን የሚያሻግሩ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በሁሉም መስክ የፀናች ሀገርን ለተተኪው ትውልድ የማስረከብ የጋራ ዓላማን ማሳካት አለባቸው ብለዋል። የፓርቲው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሙሳ አህመድ፤ ብልጽግና ፓርቲ የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልፀዋል። በዚህም በገጠርና ከተማ ሁለንተናዊ ፋይዳ እየሰጠ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተጠናክሮ መጠቀሉን ጠቅሰው፤ ችግኝ ከመትከል ባለፈ በመንከባከብ ለፍሬ ማብቃት የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታረቀኝ ገመቹ፤ በክፍለ ከተማው የአረንጓዴ ልማትና ውብ ከባቢን የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ሆኑ 
Jul 22, 2024 489
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ተደረጉ። የሩሰያ ዜና አገልግሎት ስፑትኒክ እንደዘገበው ናይጄሪያ ከሁሉም አገራት የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ከኬኒያና ታንዛኒያን ቀድማ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ታንዛኒያ በመጨረሻው በ10ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ዘገባው ያሳያል። የደረጃ አሰጣጡ መሰረት ያደረገው ከ80 ሺህ በላይ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተመርኩዞ መሆኑን ስፑትኒክ ጠቁሞ መስፈርቱ ከ22 ሺህ 500 በላይ የመረጃ ምንጮችን የሸፈነ እንደሆነም አመልክቷል። ለደረጃ አሰጣጡ ኦንላይን ስታትስቲክስ ፖርታል በመጠቀም መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ መከናወኑ ተገልጿል። በአፍሪካ አገራት በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት በተመጣጣኝ ዋጋ ባላቸው መሳሪያዎች ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት እያደገ መምጣቱን በዘገባው ተገልጿል። በተጨማሪም የተሻለ የቴሌኮም ግንኙነት በተለይም የዲጂታል አገልግሎቶች በመስፋፋታቸው ምክንያት የዓለም አቀፍ እና የአፍሪካ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ማሻቀቡን ቀጥሏል ብሏል ስፑትኒክ በዘገባው። በአፍሪካ ያለው የኢንተርኔት አጠቃቀም ምንም እንኳን ከሌሎች ክፍለ ዓለማት ጋር ሲነጻጸር አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አስደናቂ እድገት መታየቱን ዘገባው አስታውሷል። ዘገባው እ.ኤ.አ. በ2024 የኢንተርኔት አጠቃቀምን የሚመሩ አስር የአፍሪካ ሀገራትን ዝርዝር እንሚመለከተው አስቀምጧል፡- 1. ናይጄሪያ (103 ሚሊዮን ወይም 45 ነጥብ 2 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 2. ግብፅ (82 ሚሊዮን ወይም 76 በመቶው ህዝብ)፣ 3. ደቡብ አፍሪካ (45 ሚሊዮን ወይም ከህዝቡ 72 ነጥብ በመቶ)፣ 4. ሞሮኮ (34 ሚሊዮን ወይም 92 ነጥብ 2 በመቶው የህዝብ ብዛት)፣ 5. አልጄሪያ (33 ሚሊዮን ወይም 71 ነጥብ 8 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 6. ዲሞክራቲክ ኮንጎ (28 ሚሊዮን ወይም 27 ነጥብ 4 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 7. ጋና (24 ሚሊዮን ወይም 71 ነጥብ 3 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 8. ኢትዮጵያ (24 ሚሊዮን ወይም 21 ነጥጭብ 1 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 9. ኬንያ (22 ሚሊዮን ወይም 43 ነጥብ 3 በመቶው የህዝብ ብዛት)፣ 10. ታንዛኒያ (21 ሚሊዮን ወይም ከህዝቡ 33 ነጥብ 4 በመቶ
በአፍሪካ ቀንድ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከወትሮው የተለየ የሙቀት መጠን ሊኖር ይችላል  
Jul 21, 2024 452
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2016(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ቀንድ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከወትሮው የተለየ የሙቀት መጠን ሊኖር ይችላል። የኢጋድን በይነ መረብ ዋቢ አድርጎ ዥንዋ እንደዘገበው፤ በአፍሪካ ቀንድ ከነሐሴ እስከ ጥቅምት ወራት ባለሉት ጊዜያት ከወትሮው የበለጠ የሙቀት መጠን ይኖረዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ ኤጀንሲ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከነሀሴ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ከወትሮው የበለጠ ሙቀት እንደሚኖረው ትናንት ማስታወቁን ዘገበው አመልክቷል። የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማመልከቻ ማእከል ያስታወቀው፤ በአካባቢው በሚገኙ አንዳንድ ሀገራት የሙቀቱ መጠን እስከ 35 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ እንደሚችልም ነው የጠቆመው። ይሁን እንጂ ከሙቀቱ በተጋዳኝ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወትሮው የተለየ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ሊስተዋል እንደሚችል ድርጅቱ አስታውቋል። ሌሎች እንደ ጂቡቲ ፡ ኬንያ ፡ ደቡብ ሱዳን ፡ ሱማሊያና ኡጋንዳ በመሳሰሉት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚመዘገቡባቸው እንደሆኑም ዥንዋ በዘገባው አመላክቷል። በአካባቢው ከሚከሰተው ከፍተኛ ሙቀት በተጨማሪም ከነሀሴ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት የአፍሪካ ቀንድ ምስራቃዊ ክፍሎች ከወትሮው የበለጠ ደረቅ የአየር ንብረት እንደሚያጋጥማቸው የማዕከሉ ትንበያ ያመለክታል።
የተዛባ የእንቅልፍ ሰዓት ለስኳር በሽታ እንደሚያጋልጥ ተመላከተ
Jul 19, 2024 560
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2016(ኢዜአ)፡- መደበኛ ያልሆነ ወይም የተዛባ የእንቅልፍ ሰዓት በስኳር በሽታ የመያዝ እድልን እንደሚጨምር ተመላክቷል። የዩናይትድ ኪንግደም ባዮባንክ ያካሄደው ተከታታይ ጥናት መደበኛ ያልሆነ የመኝታ ሰዓት አጠቃቀም ለታይፕ 2 ስኳር በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች ሰፊ ድርሻ እንደሚኖረው አስገንዝቧል። የተለያየ የመኝታ ሰዓት የሚጠቀሙና መደበኛ የእንቅልፍ ቆይታ የሌላቸው ሰዎች ለስኳር በሽታ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ነው ጥናቱ ያመለከተው። ጥናቱ የተካሄደው በአማካይ 62 አመት የሞላቸው 84 ሺህ ስኳር ታማሚ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ሲሆን ለ7 ተከታታይ ቀናት የእንቅልፍ ሰዓታቸው ላይ ቁጥጥር ሲደረግ ነበር። በጥናቱ ውጤት መሰረት "መደበኛ ያልሆነ" የእንቅልፍ ሰዓት ተብሎ የተለየው በየቀኑ በአማካይ ከ1ሰዓት በላይ የሚለዋወጥ የእንቅልፍ ቆይታ መሆኑን ዩፒአይ ዘግቧል። በዚህም ከ60 ደቂቃ በላይ በየቀኑ የእንቅልፍ ሰዓታቸው የሚዛባ 34 በመቶው የጥናቱ ተሳታፊዎች ለስኳር ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቱ እንዳመለከተ ተገልጿል። በተጨማሪም የጥናቱ ተሳታፊዎች ባለፉት ሰባት ዓመታት ባጋጠማቸው የስኳር በሽታ ተጋላጭነት ላይ የዳሰሳ ጥናት መደረጉም ተመልክቷል። የጥናት ቡድኑ ለስኳር በሽታ ተጨማሪ አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶችን ከለየ በኋላ የተዛባ ወይም መደበኛ ያልሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ለታይፕ 2 ሰኳር በሽታ አጋላጭ ምክንያት መሆኑን አረጋግጧል። የጥናት ቡድኑ መሪ የሆኑት ሲና ኪያነርሲ ወጥነት ያለው የእንቅልፍ ሰዓት በታይፕ 2 ስኳር በሽታ የመያዝን እድል ለመቀነስ ጉልህ ድርሻ እንዳለው በጥናቱ መረጋገጡን ተናግረዋል።
ሐተታዎች
ከዛሬ ፈተና የነገ ተስፋ ገዝፎ የሚታያቸው ባለ ራዕይ ተማሪዎች
Jul 20, 2024 699
በርካታ ታዳጊዎች ገና በልጅነት ዕድሜያቸው ብዙ የህይወት ፈተና ለመጋፈጥ የሚገደዱባቸው የህይወት አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። አንዳንዶች በፈተናዎቹ በመረታት ህልማቸው ሲጨነግፍ ሌሎች ደግሞ ከትናንት ፈተናዎቻቸው በመማር፣ ዛሬን በጥንካሬ በመኖር እና ነገን ተስፋ በማድረግ በህይወታቸው ለውጥ ሲያመጡ ይስተዋላል። ሳምራዊት ሲሳይ፣ ምህረት ባዬ፣ አብርሃም ግዛቸው እና ኤፍሬም ሲሳይ ብዙ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች አሉ። ተማሪዎቹ ገና በልጅነት ዕድሜያቸው በግብአት እጥረት ትምህርት ለማቋረጥ እስከመገደድ እንዲሁም ቤተሰብን ለማገዝ የመኖሪያ ቀዬን ጥሎ ወደ ከተማ እስከመኮብለል የደረሰ የህይወት ፈተና ተጋፍጠዋል። ነገር ግን ለፈተናዎች ባለመረታት ዓመታትን ወደፊት አሻግረው በመመልከት የነገ የህይወት መንገዳቸውን በየራሳቸው አማራጭ እያበጁ መሆኑም ያመሳስላቸዋል። ሳምራዊት ሲሳይ የ16 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ትውልዷና እድገቷ አዲስ አበባ ነው። ሳምራዊት በእውቀት ለፍሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ትምህርቷን አጠናቃ በክረምት ወራት ለ10ኛ ክፍል የሚሆናትን ዝግጅት ከወዲሁ እያደረገች ትገኛለች። ትምህርት የሰው የሕይወት መስመር ነው የምትለው ሳምራዊት ወደፊት አዋላጅ ሀኪም በመሆን ሀገሯን የማገልገል ሕልም አላት።   ሌላኛዋ ባለ ሩቅ ህልም ታዳጊ ምህረት ባዬ ትውልዷ መቀሌ ሲሆን በልጅነቷ ወደ አዲስ አበበ መጥታ ትምህርቷን በሻምፒዮንስ አካዳሚ በመከታተል ላይ ትገኛለች። በጣም ጎበዝና የደረጃ ተማሪ ስትሆን በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ወደ 9ኛ ክፍል አልፋለች። መሐንዲስ (ኢንጂነር) የመሆን ራዕይ ያላት ታዳጊዋ እናትና አባቶቻችን ያስረከቡንን ሀገር እኔና አሁን ያለው ትውልድ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ለማሳደግ አደራ አለብን ብላለች።   በጅማ ከተማ የተወለደውና በልጅነት እድሜው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ኑሮን ለብቻው መግፋት የጀመረው አብርሃም ግዛቸው ትምህርትን የሕይወቱ ለውጥ ቁልፍ መሳሪያ በማድረግ በትጋት እየተማረ 10ኛ ክፍል ደርሷል። በምህንድስና ሙያ አገሩን ማገልገልን በማለም ዛሬ ላይ ነገውን እየሰራ ይገኛል። ገና በልጅነት እድሜው ኑሮን ለማሸነፍና ቤተሰቡን ለመደገፍ ከወሎ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ የሚናገረው ወጣት ኤፍሬም ሲሳይም በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ተመርቆ ኢትዮጵያን በሙያው የማገለልገል ሕልም አለው። ተማሪዎቹ ከራሳቸው አልፈው በክረምት ወራት ሌሎችን በበጎ ፈቃድ እያስተማሩና እያገዙ ይገኛሉ። እነዚህ ታዳጊዎችና ወጣቶች በፈተናዎች ሳይረቱ ትምህርታቸው ላይ በማተኮር የወደፊት ራዕያቸውን ዛሬ ላይ መቅረጽ ለመጀመራቸው ዋነኛ ምክንያቱ የውስጥ ብርታትና ጥንካሬያቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ዛሬ ላይ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በማሸነፍ የተሻለ ነገ እንደሚመጣ በማመን በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውስጥ ‘Sustainable East African Education and Development Society’ (ሲድስ) የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለያየ መንገድ እየደገፋቸው መሆኑንም ያነሳሉ።   የድርጅቱ የጋራ መስራች ምህረት ወርቁ ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ለ160 የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት ግብዓቶችና ሌሎችን ቁሳቁሶችን በመደገፍ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ውጤታማ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ዋንኛ ግቡ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎች በዘላቂነት ተቋቁመው ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ መሆኑን አመልክተዋል። የሲድስ ድርጅት የኢትዮጵያ አስተባባሪ ዓለም ዘለቀ ድርጅቱ ለተማሪዎች የጤና መድህን በመክፈልና ለወላጆች የመነሻ ገንዘብ በመስጠት ራሳቸውን እንዲያቋቁሙ እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል።   አብዛኞቹ ተማሪዎች በሚደረግላቸው ድጋፍ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ ነው ያሉት አስተባባሪዋ የተሻለ የትምህርት ደረጃ ላይ የደረሱ ተማሪዎች በመልካም ፈቃደኝነት ለተማሪዎች የትምህርት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችና ተቋማት በሕጻናት ትምህርት ላይ በመስራት ልጆች በችግር ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ይታይሽ ደነቀው ሲድስ በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 ቆሼ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የሚገኙ ልጆችና ወላጆችን በመደገፍ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ድርጅቱ የድጋፍ አድማሱን በማስፋት እንዲሁም ተማሪዎችና ወላጆች ከተረጂነት ተላቀው በዘላቂነት ሊቋቋሙ በሚችሉባቸው ሁኔታ ላይ ይበልጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።   የክፍለ ከተማው የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትልና ግምገማ ባለሙያ መስከረም ሙለታ ድርጅቱ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል። ትምህርት ለሕይወት ትልቅ መሰረት በመሆኑ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።  
ማትሪክ ተፈታኟ የ10 ልጆች እናት 
Jul 13, 2024 1374
ማትሪክ ተፈታኟ የ10 ልጆች እናት የ2016 ዓ.ም የ12ኛው ክፍል የመጀመሪያው ዙር የሆነው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በአገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከሐምሌ 3 ጀምሮ ለሶስት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል። ከእነዚህም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ሲሆን፤ በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከወሰዱት መካከል የ40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት ይገኙበታል። እኚህ እናት ፈተናው በሚሰጥበት የመጨረሻው ቀን ከክፍሉ ጥግ ይዘው ፈተናውን መስመር በመስመር እያነበቡ መልሱን ያከባሉ። በትኩረት ለተመለከታቸው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። እነሆ ተፈታኟ ከፈተና አዳራሽ ወጡ፤ መልካም ፍቃዳቸው ሆኖ ለቃለ ምልልስ ተቀመጥን። ወይዘሮ ኩመሌ ዳፋን ይባላሉ፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን የዛይ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፤ የ10 ልጆች እናት የሆኑት ተፈታኟ በልጅነታቸው ትዳር መመስረታቸውን አጫወቱኝ። ለልጆቼ አርአያ ለመሆን በማሰብ ያቋረጥኩትን የ12ኛ ክፍል ትምህርት ቀጥዬ ፈተና ለመውሰድ ወሰንኩ ሲሉ ገልጸውልኛል። አብረዋቸው ሲፈተኑ ከነበሩ የክፍሉ ተፈታኞች በበለጠ ተረጋግተው እና ጊዜያቸውን ተጠቅመው ፈተናውን ሰርተው እንደወጡ ነግረውናል። ወይዘሮ ኩመሌ "ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ባመጣ ትምህርቴን ከመቀጠል የሚከለክለኝ አንድም ነገር የለም" ሲሉ ይናገራሉ። "ሃገራችንን የምንቀይረው ራሳችን በመማር እና ልጆቻችንንም በማስተማር ነው" ብለው እንደሚያምኑ እኚሁ እናት አስረድተዋል። ከ10ሩ ልጆቻቸው መካከል የመጀመሪያዋ ልጃቸው በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እንደምትወስድ አመልክተው "ከልጄ ጋር በመፈተኔ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ ብለዋል። የአሶሳ የኒቨርሲቲ ተወካይ ዶክተር መልካሙ ደሬሳ የ12ኛ ክፍል ተፈታኟ የ10 ልጆች እናት ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ተጉዘው ወደ አሶሳ በመምጣት ፈተናውን መውሰዳቸው በአርአያነት የሚጠቀስ ሲሉ ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው 4 ሺህ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች የሰጠው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ሁለት ተማሪዎች ፈተና እየወሰዱ መውለዳቸውን ጠቅሰው፤ ህክምና አግኝተው ፈተናውን እንዲጨርሱ መደረጉን ተናግረዋል። ሌሎች 300 ያህል ተፈታኝ እናቶች ደግሞ የልጆቻቸው ሞግዚቶች በዩኒቨርሲቲው አልጋ ይዘው እንዲያግዟቸው በማድረግ ፈተናው እንዲወስዱ መደረጉን ዶክተር መልካሙ አስረድተዋል።  
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ እነማን ብዙ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀበሉ? 
Jun 28, 2024 2009
በእግር ኳስ ጨዋታ ከግብ አስቆጣሪዎች ጀርባ ኳስን ፍትፍት አርገው ጨርሰው የሚያቀብሉ ተጫዋቾች አሉ። አንድ ተጫዋች ግብ ሲያገባ ከማግባቱ ባልተናነሰ ማን ኳሱን አቀበለው? የሚለው ጥያቄ በተመልካቾች ይነሳል። በእግር ኳስ እድገት ውስጥ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለጎል ኳስ አመቻችተው የሚያቀብሉ ተጫዋቾች ትልቅ ዋጋ ይሰጣቸዋል። በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ወደ ጥሎ ማለፉ ተሸጋግረዋል። ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚገቡ ሀገራትን የሚለዩ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይካሄዳሉ። ከሰኔ 7 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረጉ የአውሮፓ ዋንጫ 36 የምድብ ጨዋታዎች 81 ግቦች ከመረብ ላይ አርፈዋል። ከተቆጠሩት ግቦች ውስጥ አብዛኛውን እነማን አቀበሉ? የሚለውን በዚህ ጽሁፍ ይዘን ቀርበናል። አራት ተጫዋቾች እስከ አሁን በውድድሩ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ለግብ አመቻችተው አቀብለዋል። አጓጊ ፉክክር በተደረገበት ምድብ 5 ሮማንያ 4 ነጥብ በመያዝ ምድቡን በበላይነት አጠናቃ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች። ቡድኑ በጨዋታዎቹ 4 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ሮማንያ ካስቆጠረቻቸው 4 ግቦች 2ቱን ለግብ አመቻችቶ ያቀበለው የ25 ዓመቱ የፓርማ የክንፍ ተጫዋች ዴኒስ ማን ነው። ማን ኳሶቹን አመቻችቶ ያቀበለው ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ነው። የክንፍ መስመር ተጫዋቹ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ የተጋጣሚ ተከላካዮችን በፍጥነት ኳስን በማንከባለል ፋታ እየነሱ ካሉ ተጫዋቾች መካከል ይገኝበታል። በተመሳሳይ በምድብ 5 ስሎቫኪያ በ4 ነጥብ ምርጥ ሶስተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏ የሚታወስ ነው። ስሎቫኪያ በሶስቱ የምድብ ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን አስቆጥራለች። ከነዚህም ውስጥ ሁለቱን ለግብ አመቻችቶ ያቀበለው ለሀገሩ ክለብ ስሎቫን ብራቲስላቫ የሚጫወተው ጁራጅ ኩችካ ነው። ኩችካ ስሎቫኪያ ቤልጂየምን 1 ለ 0 ባሸነፈችበትና ከሮማንያ አንድ አቻ በተለያየችበት ጨዋታ ኳሶቹን አመቻችቶ አቀብሏል። በምድብ 1 በ5 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዛ በመጨረስ 2ኛ ደረጃን ይዛ ያለፈቸው ስዊዘርላንድ በሶስቱ ጨዋታዎች 5 ግቦችን አስቆጥራለች። ከኖቲንግሃም ፎረስት በውሰት ለቦሎኛ የሚጫወተው የ32 ዓመቱ አማካይ ሬሞ ፍሩለር ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን 3 ለ 1 ስታሸንፍ እንዲሁም ከጀርመን አንድ አቻ ስትለያይ ለሁለቱ ግቦች መቆጠር የተጫዋቹ እጅ አለበት። ከዚሁ ጋር በተገናኘም ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን ባሸነፈችበት ተጫዋች ማርክ ኤቢሸር በጨዋታው ግብ በማስቆጠርና ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል። ይህም ኤቢሸርን በውድድሩ ታሪክ በአንድ ጨዋታ ጎል ያገባና ለግብ የሚሆን ኳስን አመቻችቶ ያቀበለ የመጀመሪያው ስዊዘርላንዳዊ ተጫዋች አድርጎታል። "የሞት ምድብ" በተባለው ምድብ 2 ክሮሺያ 2 ነጥብ ይዛ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ይታወቃል። የ32 ዓመቱ የኦሳሱና አጥቂ አንት ቡዲሚር ክሮሺያ በውድድሩ ተሳትፎ ካስቆጠረቻቸው 3 ግቦች 2ቱን ለግብ አመቻችቶ አቀብሏል። ቡዲሚር ኳሱን አመቻችቶ ያቀበለው ክሮሺያ ከአልባኒያ ሁለት እኩል እንዲሁም ከጣልያን ጋር ድራማዊና ልብ አንጠልጣይ በሆነ ሁኔታ አንድ አቻ በተለያየችበት ጨዋታዎች ላይ ነው። በተያያዘም ምድብ 2 ስፔን ክሮሺያን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ታዳጊው ስፔናዊ ላሚን ያማል በ16 ዓመት በ338 ቀናት ዳኒ ካርቫያል ያስቆጠረውን ግብ አመቻችቶ በመቀበል በውድድሩ ታሪክ በትንሽ እድሜው ለጎል የሚሆን ኳስ የሰጠ ተጫዋች የሚል ክብረ ወሰንን ጨብጧል። ያማል በዚህ ጨዋታ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ የተሰለፈ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ክብረ ወሰንንም ሰብሯል። በተጨማሪም በአውሮፓ ዋንጫው በሶስት ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ የሚገኘው የጆርጂያው አጥቂ ጆርጄስ ሚካውታድዛ ካገባቸው ግቦች በተጨማሪ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ማን ብዙ ለጎል የሚሆን ኳስ አቀበለ? ለሚለው ጉዳይ ትልቅ ግምት ሰጥቶታል። ማህበሩ በውድድሩ ሁለትና ከዚህ በላይ ተጫዋቾች በተመሳሳይ የግብ መጠን የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነው ቢያጠናቅቁ አንደኛ የሚወጣውን የሚለየው ከተጫዋቾቹ ማን የተሻለ ለግብ የሚሆን ኳስ አቀበለ? በሚለው መስፈርት ነው። የ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የግብ አግቢዎችና የኳስ አቀባዮቹ ፉክክር በያዘው ግለት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።                                                          
11 አገራት ያዘጋጁት ታሪካዊው የአውሮፓ ዋንጫ 
Jun 20, 2024 2216
አገራት ዓለም ዋንጫ፣ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችና ሌሎች ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ውድድሮች በጣምራ የማዘጋጀት ባህል ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ እየተለመደ መጥቷል። በተለይም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ይህ አዝማሚያ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። የስፖርት ሁነቶችን በጋራ የማዘጋጀት ሀሳብ የሚመነጫው አንድ አገር ግዙፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ሲያስተናግድ ለከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የሚዳርግና አላስፈላጊ ጫና ውስጥ የሚከት በመሆኑ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ስፖርታዊ ሁነት በትብብር ማዘጋጀት አገራት ኢኮኖሚን ጨምሮ ሌሎች ጥቅሞችንና የሚኖሩ ጉዳቶችን እንዲጋሩ በማድረግ የስፖርት ውድድር አስተዳደርን ውጤታማ እንደሚያደርግ ይናገራሉ። የዓለም የእግር ኳስ ቤተሰብ ቀልብ ከሳቡ ስፖርታዊ ውድድሮች አንዱ በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ነው። ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የአውሮፓ ዋንጫ የተጀመረው እ.አ.አ በ1960 ሲሆን የውድድሩ አዘጋጅ አገር የነበረችው ፈረንሳይ ነበረች። እንግሊዝ እ.አ.አ በ1996 እስካሰናዳችው 10ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ድረስ ውድድሩ ሲካሄድ የቆየው በአንድ አገር አዘጋጅነት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ አገር በላይ ውድድሩን ያዘጋጀው እ.አ.አ በ2000 በተካሄደው 11ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ነው። ውድድሩን ያዘጋጁት አገራት ደግሞ ቤልጂየምና ኔዘርላንድስ ናቸው። በጣምራ የተካሄደውን ታሪካዊ ሁነት ፈረንሳይ ጣልያንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች። እ.አ.አ በ2008 ኦስትሪያና ስዊዘርላንድ 13ኛው የአውሮፓ ዋንጫ እንዲሁም ፖላንድና ዩክሬን እ.አ.አ በ2012 የተካሄደውን 14ኛ የአውሮፓ ዋንጫ በጋራ አዘጋጅተዋል። ይሁንና እ.አ.አ በ2020 የተካሄደው 16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ከሁሉም የተለየና በጣም ያልተለመደ ነበር። በወቅቱ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት የነበሩት ሚሼል ፕላቲኒ የአውሮፓ ዋንጫ የተጀመረበትን 60ኛ ዓመት ለማክበር ውድድሩ በተለያዩ አገራት እንደሚካሄድ ይፋ አደረጉ። ፕላቲኒ ውድድሩን "የማይደገም የአንድ ጊዜ የአውሮፓውያውን የፍቅርና ወዳጅነት ሁነት" ሲሉም ገልጸውታል። 16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የተካሄደው በ11 የአውሮፓ አገራት በሚገኙ 11 ከተሞች ነው። አዘርባጃን፣ ዴንማርክ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ሀንጋሪ፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ሮማኒያ፣ ሩሲያ፣ ስኮትላንድና ስፔን ታሪካዊውን ውድድር በጋራ ያዘጋጁ አገራት ናቸው። ውድድሩ ከእ.አ.አ ሰኔ 12 እስከ ሐምሌ 12 2020 ይካሄዳል ተብሎ ቀን ቢቆረጥለትም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ 2021 ተዘዋውሯል። ውድድሩን 13 አገራት እንደሚያዘጋጁት ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ቤልጂየም ውድድሩን ለማስተናገድ ስትገነባው የነበረው ዩሮ ስታዲየም በጊዜው ባለመጠናቀቁና አየርላንድ ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ደጋፊዎች ስታዲየም ገብተው ጨዋታዎችን እንዲከታተሉ የማድረግ ዋስትናን ባለመስጠቷ ከአስተናጋጅነት ውጪ መሆናቸውን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በወቅቱ ገልጿል። እ.አ.አ በ2016 በፈረንሳይ በተካሄደው 15ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ የነበረችው ፖርቹጋል በጥሎ ማለፉ በቤልጂየም ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ መሆኗ ያልተጠበቀ ውጤት ነበር። 90 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን እንግሊዝን በመለያ ምት በማሸነፍ ታሪካዊውን ዋንጫ አንስታለች። በውድድሩ 24 አገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። 16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (ቫር) ጥቅም ላይ የዋለበት ነው። ከዚህ ቀደም ከሁለት አገራት በላይ በጣምራ ያዘጋጁት አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድር እ.አ.አ በ2007 የተካሄደው 14ኛው የእስያ ዋንጫ ነው። ኢንዶኔዢያ፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድና ቬትናም ውድድሩን ያዘጋጁ አገራት ናቸው። ከዚህ በኋላ በሚካሄዱ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች የ11 አጋራትን ጣምራ አዘጋጅነት ክብረ ወሰንን ያልፉ ይሆን? ለሚለው ጥያቄ ቀጣይ ጊዜያት ምላሽ ይሰጣሉ።                                    
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በምታደረገው ጥረት ያልተነገረ ታሪክ
Jul 24, 2024 207
ከሚዲያ ሞኒተሪንግና ትንተና ዳይሬክቶሬት ቀደም ባሉት ዘመናት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 40 በመቶ እንደነበረ፤ ቀስ በቀስ ይህ የደን ሀብት በተለያየ ምከንያት ተራቁቶ ወደ ሦስት በመቶ ያህል አሽቆልቁሎ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ከደን ሀብት መራቆት ጋር በተያያዘ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ተፅዕኖ የበረሃማነት መስፋፋት፣ በተደጋጋሚ የድርቅና ሌሎች ተጓዳኝ አደጋዎች መከሰት ያሳሰባት ኢትዮጵያ የደን ሀብት ልማት፣ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን አጠናክራ በመቀጠሏ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ የደን ሀብቷ ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ ወደ 17 ነጥብ 2 በመቶ ከፍ ማለቱንም መረጃዎቹ ይጠቁማሉ። በሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የመምራትና የማስተዳደር ሥልጣንን የተረከቡት ባለራዕይውና የለውጥ አራማጁ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2011 ዓ.ም ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውን እና አያሌ ትሩፋቶችን እያገናጸፈ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብርን ይፋ አደረጉ። መላው ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስድስት ዓመታት መርሃ ግብሩን እውን ለማድረግ በፅናት፣ በቁርጠኝነትና በኅብረት ባከናወኗቸው አያሌ ተግባራት በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከራሳቸው አልፎ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ያስደመመ ውጤት አስመዝግበዋል፤ እያስመዘገቡም ይገኛሉ። የዚህ ጽሑፍ አብይ ዓላማም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጨነት እውን የሆነውን፣ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውን እና አያሌ ትሩፋቶቹን እያቋደሰ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብርን ዘርዝሮ ማስረዳት አይደለም። ይልቁንም ተቀማጭነታቸውን በቱርክ አንካራ ያደረጉት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አፈወርቅ ሽመልስ “Untold story of Ethiopia's endeavor in combating climate change” በሚል ርዕስ ያሰናዱትን ጽሑፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ በመመለስ ስለኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ያልተነገረ ታሪክ ላይ የሰጡትን ህያው እማኝነት ለውድ ተደራሲያን በአጭሩ ማቋደስ ነው። የዲፕሎማቱን እማኝነት እነሆ ብለናልና አብራችሁን ዝለቁ። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ተጨባጭ ውጤቶችን እያሳየ ነው። ሆኖም ግን በሚገባው ልክ እንዳልተነገረለት ተቀማጭነታቸውን በቱርክ አንካራ ያደረጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አፈወርቅ ሽመልስ ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ ዴይሊሳባህ ለተባለው የቱርክ ድረገጽ በላኩት ጽሁፍ ከስድስት ዓመት በፊት አረንጓዴ አሻራ ማኖር በሚል የተጀመረው አገር አቀፍ ዘመቻ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዛፍ ችግኞች የመሸፈን ብሄራዊ መርሃግብር የደን ሽፋንን በማሳደግ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል። እንደ ዲፕሎማቱ ማብራሪያ አየር ንብረት ለውጥ በተደጋጋሚ መከሰቱ ለምድራችንና ለሰው ልጆ የማይታመን ከባድ ፈተና ፈጥሯል። በአሁኑ ጊዜ የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጅን ህልውና የሚፈታተን የማይቀር አደጋና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ሆኗል። እ.ኤ.አ. ከ1980ዎቹ ጀምሮ በዓለማችን የከፋ የአየር ሁኔታ መዛባት፣ ተደጋጋሚና ከባድ የሙቀት ማዕበል፣ በረሃማነት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የአርክቲክ በረዶ መቅለጥ፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋት፣ የመሬት መራቆት፣ የደን ሽፋን መመናመን፣ የለም አፈር መከላት፣ የምርታማነት ዕድገት መቀነስ እና ሌሎች በርካታ ፈተናዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየታዩ ነው። በዚህ ረገድ ያደጉ አገሮች በተለይም በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ የሚገኙ ከከባድ ኢንዱስትሪዎቻቸው በሚለቀቀው የሙቀት አማቂ ጋዞች ከባቢ አየርን በመበከል የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ። ለዓለም ሙቀት መጨመር እና ለካርቦን ልቀት እዚህ ግባ የሚባል አስተዋጽኦ የሌላት አፍሪካ በጣም የተጎዳችና እየተሰቃየች ትገኛለች። በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮች እየተለመዱ ከመምጣታቸው የተነሳ ድንጋጤ መፍጠር እያቆሙ መሆናቸውን ያተቱት ዲፕሎማቱ አፍሪካ ለችግሮቹ እዚህ ግባ የሚባል አበርክቶ ሳይኖራት የጉዳቱ ዋነኛ ሰለባ ከሆነች በርካታ አስርት ዓመታት እንደዋዛ መንጎዳቸውን ይገልጻሉ። የአፍሪካ ቀንድ ለዓለም ጠቃሚ የጂኦ ስትራቴጂክ አካባቢ ነው። በዚህ የዓለም ክፍል ውስጥ ያሉ ሀገራት ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለከፋ ችግሮች ተጋልጠዋል ይላሉ ዲፕሎማቱ። አገራቱ ካጋጠሟቸው ተግዳሮቶች መካከል በረሃማነት፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋት፣ተደጋጋሚ ድርቅ መከሰት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የመሬት መራቆትና የጎጂ ነፍሳት ክስተትና መስፋፋት ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ችግር ለከፍተኛ የምግብና የውሃ እጦት እና ለአዳዲስ የወረርሽኝ በሽታዎች መጨመርን አስከትሏል። የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ለረጅም ጊዜ ድርቅ ተጋላጭ አድርጎታል፤ ለሶስት ተከታታይ የምርት ወቅቶች ያጋጠመው የዝናብ እጥረት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖችን ለዘለቄታው የምግብ እጥረት፣ ለስቃይ እና መፈናቀል አጋልጧል፤ ድርቁ በከብቶች ህልውና ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን፤ በሦስት ዓመታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶች ሞተዋል ይላሉ ዲፕሎማት አፈወርቅ በጽሑፋቸው። ዲፕሎማት አፈወርቅ አያይዘውም የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ ቀንድ በምትገኘው ኢትዮጵያም በተደጋጋሚ ለድርቅ ተጋላጭ እንድትሆን፣ በአካባቢ መራቆት፣ በረሃማነት መጨመር ረገድ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። የአየር ንብረት ለውጥ በአከባቢው በተለይም በኢትዮጵያ ያለውን አደጋ የተረዱት የኢትዮጵያ የለውጥ አራማጅ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እ.ኤ.አ በ2019 አረንጓዴ ሌጋሲ ኢኒሼቲቭ በመባል የሚታወቀውን ዛፎች የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብር ይፋ ማድረጋቸውን ይገልጻሉ። ይህ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ​​ለመገንባት ያለመ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላ ሀገሪቱ የመትከል ታላቅ ዓላማ ያለው መርሃ ግብር ነው። መንግሥት በመጀመርያው ዓመት ከ4 ቢሊዮን በላይ የተለያዩ ችግኞችን በመትከል በአንድ ጀምበር ከ353 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሮታል ይላሉ። እንደ ዲፕሎማቱ ማብራሪያ መንግስት ለዚህ ዓለማ መሳካት በየዓመቱ ከ25 ሚሊዮን በላይ የሰው ኃይል በማነሳሳትና በመላ አገሪቱ በማሰባሰብ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ የጋራ የኃላፊነት ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል። መንግስት የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየዓመቱ ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የዝናብ ወቅት ችግኝ ተከላውን ቀጥሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተያዘው የክረምት ወራት 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የተለያዩ ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ተጀምሯል። በመላ ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ለየአካባቢው ስነምዕዳር ተስማሚ የሆኑ ከ32 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ እውን መሆን በመቻሉ የሀገሪቱ የደን ሽፋን እ.ኤ.አ በ2019 ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ በ2023 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል። በመላ አገሪቱ በመርሃግብሮቹ ከተተከሉት ችግኞች እንደ ወይራ፣ዋንዛ፣ኮሶና ጽድ የመሳሰሉት ለየአካባቢው ስንምዕዳር ተስማሚ የሆኑ የሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች ይገኙበታል። ከዚህም በሻገር በምግብ ራስን በመቻል ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው እንደ አቮካዶ፣ማንጎ፣ዘይቱን እና ኮክ የመሳሰሉ ለቆላማና ለከፊል ቆላማ አከባቢዎች ተስማሚ የሆኑ ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎች በአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው መሆናቸውን ዲፕሎማት አፈወርቅ አብራርተዋል። የአረንጓዴው አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝቦቿ የተቀናጀ ጥረት የኢትዮጵያን ተራሮች፣ ኮረብታዎች፣ ሜዳ ሸንተረሮች እና ከተሞችን አረንጓዴ በማልበስ በኢትዮጵያና በቀጣናው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ አስደንጋጭ ተግዳሮቶች ማስወገድ ነው። ዲፕሎማት አፈወርቅ በጽሑፋቸው እንዳስገነዘቡት የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር የሀገሪቱን የደን ሽፋን በማሳደግ፣ የመሬት መራቆትን በመከላከልና የደን ሀብትን በመጠበቅና በመንከባከብ ስነ-ምህዳሩን በማመጣጠን ለቀጣዩ ትውልድ ምቹና ዘላቂ አረንጓዴ አካባቢን ለማውረስ ይረዳል። እንዲሁም የዛፍ ችግኞችን በመትከል የተራቆተውን የደን ሀብት መልሶ በማልማት በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኘውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ሌሎች አደገኛ የሙቀት አማቂ ጋዞችን በመቀነስ ለኦዞን ሽፋን መሳሳትና ለዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተፅዕኖ ለመቋቋም የላቀ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ አፍስሶና በሀገሪቱ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብን ጨምሮ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎችን አንቀሳቅሶ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመግታት ብርቱ ጥረት አድርጓል ይላሉ። ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ቀጣናዊ ውህደት ለመፍጠር 1 ቢሊዮን ችግኞችን ለስድስት ጎረቤቶቿ በማከፋፈል በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ የቀጣናዊ ውህደቱ አካል እንዲሆኑ አድርጋለች ሲሉም ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ አያይዘውም በሌላ በኩል መንግሥት በክረምት ወራት አርሶ አደሩን በማንቀሳቀስ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራውን በመላ ሀገሪቱ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ሺህ ኪሎ ሜትር የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተከናውነዋል።በተለያየ ምክንያት በተራቆቱ ተራራማ፣ ዳገተማና ኮረብታማ አካባቢዎች እንዲሁም ተፋሰሶች መልሰው እንዲያገግሙና እንዲታደሱ የድንጋይና የአፈር እርኮኖችና ጋቢዮኖች ሥራ እንዲሁም ባህላዊ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ የውሃ መውረጃ ቦዮችና ማስተላለፊያ ቱቦች ግንባታ መካሄዱን በጽሑፋቸው አመላክተዋል። ፀሐፊው አክለውም የደን ​​ልማቱና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የመሬት መራቆትን፣ በጎርፍ የመጥለቅለቅ አደጋን፣ የለም አፈር መከላትን በመታደግ የከርሰና የገፀ ምድር የውሃ ሀብት እንዲጨምሩ የሚያስችሉና አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ውጥኖች የሆኑትን የውሃ ሼድ አያያዝ በኢትዮጵያ ሥነ-ምህዳራዊ ስርዓት መደበኛ በማድረግ በረሃማነትን በዘላቂነት በመከላከል ዓባይን በመሳሰሉት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን የውሃ ፍሰትን ለማስቀጠል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸውም ያስረዳሉ። በመሆኑም የታችኛው የተፋሰሱ አገራት ግብፅ እና ሱዳን፣ የዓባይን ውሃ በብቸኝነት ካልተቆጣጠርነው በሚል እሳቤ ያልተገባ ስሞታ ከማቀረብ ይልቅ፤ ለራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም ሲሉ አረንጓዴ ኢኒሼቲቭን በገንዘብ ጭምር በመደገፍ የውሃ ፍሰትን ዘላቂነት በማረጋገጥ ላይ በትብብር መንፈስ ቢሰሩ ይመራጣል ሲሉ ዲፕሎማት አፈወርቅ ይመክራሉ። ዲፕሎማት አፈወርቅ በጽሑፋቸው ማጠቃለያ አንኳር ሃሳብ እንዳስገነዘቡት ከዚህም ባሻገር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የፓርቲዎች ኮንፈረንስ (CoP) እና ሌሎች ማህበረሰቦች ተመሳሳይ መርሃ ግብር በሌሎች የቀጣናው አካባቢዎች እንዲደግሙ ለማነሳሳት ሰብዓዊነትን እንደ አንድ የጋራ ጥቅም እንዲያገለግል በተነሳሽነት መደገፍ አለባቸው። የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ የተራቆቱ አካባቢዎችን በማሻሻል ካስመዘገበው ስኬት ባለፈ ዋነኛ ዓላማው የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የአፍሪካ አረንጓዴ ቀበቶ ኢኒሼቲቭን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህም ባሻገር የካርቦን ልቀትን በ2030 ዜሮ ለማድረግ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት የኤሌክትሪክ ኃይልን ሙሉ በሙሉ ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከፀሐይና ከእንፏሎት ወዘተ. ለማመንጨት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። ኢትዮጵያ የቀጣናዊ ውህደቱ ዋና አንቀሳቃሽ እንደመሆኗ መጠን የኤሌክትሪክ የመሰረተ ልማት አውታርን ከጅቡቲ፣ ሱዳንና ኬንያ ጋር በማገናኘት ንፁህ ኃይሏን በማጋራት ከታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር እየሰራች ነው። እንዲሁም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን እና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ከብክለት የፀዳ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ አካል በማድረግ በኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሰራ አድርጓል።  
የሽግግር ፍትሕ - የአያሌ ችግሮች መፍቻ
May 11, 2024 3948
የሽግግር ፍትሕ - የአያሌ ችግሮች መፍቻ (ሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከስተዋል። የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገሪቱ ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። በደሎችን በማከም ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር መገንባትን ባለመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዝግጅት በጥር ወር 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ ያወጣው መግለጫ እንዳመላከተውም በኢትዮጵያ የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ሥልት ነው። ከአንድ ዓመት በላይ በዝግጅት ሂደት የቆየው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን ተከትሎ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብርም ተካሂዷል። የሽግግር ፍትሕ ታሪካዊ ዳራ የሽግግር ፍትሕ ዘርፍ ታሪካዊ መነሻ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1939 እስከ 1945 ከተደረገው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ ፍትሕን ለማስፈን የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1945 በጀርመን ኑረንበርግ የተሰየመ ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ችሎት የተቋቋመ ሲሆን፤ ችሎቱ የተቋቋመው ዋና የናዚ መሪዎችን የፍርድ ሂደት ለመከታተልና ውሳኔ ለመስጠት ነው። በወቅቱ የናዚ መሪዎች በጦር ወንጀል፣ በሰብዓዊ ጥፋት እንዲሁም ወንጀሎችን ለመፈጸም በማሴር ተከሰዋል። ለአንድ ዓመት የቆየው የፍርድ ሂደትም በናዚ ሰዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ “ታሪካዊ” እና “ታላቅ” የሚል አድናቆትን አግኝቶ ነበር። የጦርነቱም የፍርዱም ተሳታፊዎች “ጨርሶ አይደገምም፤ Never again” የሚል ቃል ገብተው ነበር። በወቅቱ የጃፓን ወታደሮች የፍርድ ሂደት የሚታይበት የቶኪዮ ወታደራዊ ችሎትም ተቋቁሞ ነበር። በኑረንበርግ እና በቶኪዮ የነበሩት ወታደራዊ ችሎቶች ለሽግግር ፍትሕ እሳቤ መጠንሰስ ቁንጮ ማሳያዎች እንደሆኑ ይነገራል። በግሪክ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1945 እና በአርጀንቲና እ.አ.አ በ1983 የቀድሞ ወታደራዊ መንግሥት አባላት የፍርድ ሥርዓትም እንደ ሽግግር ፍትሕ ማሳያ ይጠቀሳሉ። የሽግግር ፍትሕ ዘርፍ እ.አ.አ ከ1980 በኋላ ያለው እሳቤና ተፈጻሚነቱ እያደገ የመጣ ሲሆን፤ እ.አ.አ በ1970 እና 1980ዎቹ ትኩረቱን የሰብዓዊ መብቶች መከበርና መጠበቅ ላይ አድርጓል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽግግር ፍትሕ ተቀባይነት እንዲያገኝና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎችና ስምምነቶች እንዲቋቋሙ በር ከፍቷል። በወቅቱ የሽግግር ፍትሕ እሳቤ ማዕከል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በፖለቲካ ሽግግር እንዲሁም በሕግና ወንጀል ፍርዶች ወቅት እንዴት ይቃኛሉ? እንዴት ይታያሉ? የሚለው ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕን አስመልክቶ የነበሩ ክርክሮች “ፍትሕ” ለሚለው ዓለም አቀፍ ጽንሰ-ሀሳብ መዳበርና መስፋት አስተዋጽዖ እንደነበረውም ይጠቀሳል። በሂደት የሽግግር ፍትሕ እየሰፋ በተለይም እ.አ.አ በ1980ዎቹ መጨረሻና በ1990 መግቢያ ላይ ዴሞክራሲና የዴሞክራሲ እሳቤዎች ዓለምን እየተቆጣጠሩና ተጽዕኗቸው እየጨመረ ሲመጣ የሽግግር ፍትሕ ከዴሞክራሲ አንጻር መቃኘት ጀመረ። በዚህም የሽግግር ፍትሕ የዴሞክራሲ እሳቤ አንዱ የጥናት ዘርፍ መሆን የቻለ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕ “ጠባብ ከነበሩ የሕግ ጥያቄዎች ወደ የተረጋጉ የዴሞክራሲ ተቋማት መገንባትና የሲቪክ ተቋማት እንደገና ማደስ ወደሚል ሰፊ የፖለቲካ አመክንዮዎች አድማሱን አስፍቷል” ሲሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕን ማዕቀፍ ከፖለቲካዊ ሂደቶችና ዴሞክራሲያዊ ለውጦች ጋር ያቆራኙ አገራት ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር ምቹ መደላድል እንደፈጠረላቸው በዘርፉ ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ይጠቅሳሉ። በዴሞክራሲያዊ ሂደት ውስጥ ያሉ የሽግግር ፍትሕ ፈተናዎች በርካታ ናቸው የሚሉት ምሁራን የዴሞክራሲ ሂደቱ ሳይጓተት ላለፉ ቁርሾዎች መፍትሔ መስጠት፣ ግጭቶችን የሚፈታ የዳኝነት ወይም የሦስተኛ ወገን የፍትሕ ሥርዓት መዘርጋት፣ የካሳ ክፍያዎችን መፈጸም፣ ያልሻሩ ቁስሎች እንዲሽሩና የባህል እርቆችን የተሟላ ማድረግ ከፈተናዎቹ መካከል የሚጠቀሱ እንደሆኑ ያነሳሉ። ካናዳ፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አገራቱን የቆረቆሩ ነባር ዜጎች ይደርስባቸው ለነበረው ጭቆና ምላሽ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕን ተጠቅመውበታል። በአሜሪካም “የዘር ፍትሕ Racial justice” አስመልክቶ በሚደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች የሽግግር ፍትሕ ቋንቋና ሀሳብ ደጋግሞ ይነሳ ነበር። የሽግግር ፍትሕ አንድ የወለደው ሀሳብ ቢኖር የ”እውነት ፈላጊ” ኮሚሽኖች (Truth commissions) ማቋቋም ነው። በአርጀንቲና እ.አ.አ በ1983፣ በቺሊ እ.አ.አ በ1990 እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ እ.አ.አ በ1995 የ”እውነትን አፈላላጊ” ኮሚሽኖች ተቋቁመዋል። ኮሚሽኖቹ በላቲን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ እስያና ምስራቅ አውሮፓ እንደ ሽግግር ፍትሕ “ምልክት” ይታዩ የነበረ ሲሆን፤ ይሁንና በዩጎዝላቪያ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ቀጣናዊ የእውነት ፈላጊ ኮሚሽን ለማቋቋም ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም በፖለቲካ መሰናክሎች ምክንያት ሳይሳኩ መቅረታቸውን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። የዴሞክራሲ ምሁራንና ባለሙያዎች አገራት በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፎቻቸው ውስጥ ብሔራዊ ስትራቴጂዎቻቸውን ሲቀርጹ ያለፉ በደሎችንና ቁርሾዎችን እንደ አገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታና ባህርይ መፍታትን በዋናነት ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ እንደሚገባ ይመክራሉ። ይህ ቁርሾን የመፍታት ሂደት ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ከሕግ ተጠያቂነት የማምለጥ ዝንባሌን ለማስቀረት፣ በዜጎችና መንግሥታት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማደስና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባት አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕ ሰፊ የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ዜጎች ሁሌም ኋላቸውን እያዩ ወይም ካለፉ ክስተቶች ጋር ከመጋፈጥ ወደፊት የተሻለ ነገር ይመጣል ብለው ተስፋ እንዲሰንቁ እንደሚያደርግም ይጠቅሳሉ። እ.አ.አ በ2001 በሽግግር ፍትሕ፣ እርቅና ርትዕ ላይ የሚሰራ “ዓለም አቀፍ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል” የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም የተመሠረተ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ግብረ-ኃይል ተቋቁሟል። የሽግግር ፍትሕ በዘላቂ ልማት ግቦች መካከል ግብ 16 “የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አፋጣኝ የፍትሕ ጣልቃ-ገብነት እርምጃዎች በመውሰድ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት” የሚለውን ለማሳካት አጋዥ ነው። የሽግግር ፍትሕ ትርጓሜዎች እንደ ዓለም አቀፉ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል ከሆነ የሽግግር ፍትሕ “ከግጭት የወጡ አገራት በመደበኛ የፍትሕ ሥርዓት በቂ ምላሽ ሊሰጡባቸው የማይችሏቸውን ከፍተኛ፣ የተደራጁና በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምላሽ የሚሰጡባቸው መንገዶች ናቸው።” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሽግግር ፍትሕ ለፍትሕ ብቻ ትኩረት በማድረግ ፍትሃዊ የኃብትና አገልግሎት ክፍፍል ማድረግ ወይም ለኢ-ፍትሃዊነት ምላሽ መስጠት ሳይሆን “ከአቅም በላይ ለሆኑና ልዩ ባህርይ ላላቸው ፈተናዎች ምላሽ የሚሰጥበት አካሄድና መንገድ ነው” ሲል ይገልፀዋል። የወንጀል ቅጣቶች፣ የእውነት ፈላጊ ኮሚሽኖች መቋቋም፣ ካሳ መክፈል፣ ሰዎች በግጭት ወቅት ያጡትን ወይም የተሰረቁትን ንብረትና ኃብት መተካት፣ በጅምላ መቃብር ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች በክብር ለየብቻ እንዲቀበሩ ማድረግ፣ ይቅርታና ምህረት ማድረግ፣ መታሰቢያዎችን መገንባት፣ በግጭቶቹ ላይ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ ግጭቶችና በደሎች እንዳይደገሙ በሚያደርግ መልኩ ትምህርቶችን ማስተማርና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ምላሽ የሚሰጡ ተቋማዊ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ በሽግግር ፍትሕ ውስጥ ከሚካተቱ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። በሌላ በኩል በሽግግር ፍትሕ በፖለቲካዊ ሽግግር ውስጥ የሕግ የበላይነትን ማስፈን በዚህም ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት የሚደረግ ጉዞን ማፋጠን ያስፈልጋል የሚሉ ምሁራንም አሉ። የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት በደሎችን በማከም ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር መገንባትን ባለመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ያሉ አለመግባባትና ግጭቶችን ለመፍታት የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ትክክለኛ አማራጭ መሆኑ ይገለጻል። የሽግግር ፍትሕ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ሁሉንም የሚያሳትፍ፣ የሕግ ተጠያቂነት፣ ፍትሕ፣ እርቅና ካሳን ጭምር ታሳቢ የሚያደርግ እንደሆነ ተጠቅሷል። በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ መዘርጋት አስፈላጊነት ታምኖበት ሁሉን አቀፍ አካታችና ተመጋጋቢ የሆነ ፖሊሲ ለማዘጋጀት ላለፉት ጊዜያት ሰፊ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ያጋጠሟትን ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ታምኖበታል። የሽግግር ፍትሕ ሰላምና ፍትሕን አስተሳስሮ የመሄድ ጉዳይ እንደሆነና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የማይተካ ሚና እንዳለው እንዲሁም በሂደቱ የይቅርታና ምህረት ጉዳዮችን እንደሚያቅፍ የሕግ ምሁራን ይገልጻሉ። በጦርነት የተጎዱ አካላትን ማቋቋም በሽግግር ፍትሕ እንደሚታይና በዚህም ዘላቂ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ማምጣት እንደሚቻል ያስረዳሉ። የተለያዩ አገራት ከነበሩባቸው በርካታ ቀውሶች ወጥተው ወደ ሰላም የመጡበት ሂደት መሆኑን በማውሳት የዘርፉ ባለሙያዎችን ባካተተ መልኩ በቁርጠኝነት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ ምክረ-ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ። የሽግግር ፍትሕ ስልቶች ያለፉ በደሎችን፣ ቁርሾዎችን፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ አለመግባባትና ጥርጣሬን በአግባቡ በመፍታት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር ዋነኛ ዓላማው ነው። ቀደም ሲል ከነበረ አለመግባባት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲላቀቅ በማድረግ ቀጣይነት ያለው አብሮነትና መተማመን መፍጠር የሚያስችል የፍትሕ ማስገኛ ስልትም ነው። አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ አገራት በሽግግር ፍትሕ ስልቶች አልፈው ከነበሩበት ውስብስብ ችግር በመውጣት የተሻለ ሰላም፣ መረጋጋት እና የሕግ የበላይነት ማስፈን ችለዋል። ለአብነትም ኮሎምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩጋንዳና ሴራሊዮን ካለፉበት አስከፊ የእርስ በርስ ግጭትና አፓርታይድ ሥርዓት በሽግግር ፍትሕ መፍትሔ በመስጠት የተሻለ ሀገር መገንባት መቻላቸው በማሳያነት የሚቀርብ ነው። በኢትዮጵያም በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት ሊፈቱ የማይችሉ የረዥም ዓመታት ጥፋቶችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ታምኖ እየተሰራበት ይገኛል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት በኢትዮጵያ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዝግጅት በጥር ወር 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የሚያዘጋጅና ከተለያዩ ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ምህረት መስጠትን፣ የሕግና ተቋማት ማሻሻያ ማድረግን፣ ማካካሻ መስጠትን፣ እውነትን ማፈላለግን እና ተጠያቂነትን ማስፈንም የሽግግር ፍትሕ ሰነዱ ዓላማ አድርጎ የሽግግር ፍትሕ የደረሰበትን ደረጃ ባገናዘበ መልኩ ፖሊሲው ሲዘጋጅ ቆይቷል። ሰላምን በማረጋገጥ፤ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የማኅበረሰብን ትስስር መመለስ ያስፈልጋል የሚለው ጉዳይ ከፖሊሲው የትኩረት አቅጣጫ መካከል የሚጠቀስ ነው። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ከዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ውይይቶች ተደርገዋል። የፖሊሲው ዝግጅት የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ፣ ዓለም አቀፍ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው። በቅድመ-ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ ብቻ 60 የክልል እና 20 ሀገራዊ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮች እንደተካሄዱበት ተልጿል። በተጨማሪም መንግሥት የሽግግር ፍትሕ አማራጮችን አስመልክቶ ሕዝባዊ ውይይቶችን በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች አድርጓል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል። በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን አስታውሷል። ሆኖም እነዚህ አሠራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት፣ በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብዓዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም ብሏል። ስለሆነም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡንና ምክር ቤቱ ግብዓቶችን በማከል ፖሊሲው ከጸደቀበት ቀን እንስቶ ሥራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል። የባለድርሻ አካላት ሚና በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገበር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑ ዕሙን ነው። በፖሊሲው እንደተመላከተውም የሽግግር ፍትሕ ሥራዎችን ተግባራዊ የሚያደርጉ ተቋማት በርከት ያሉ ናቸው፡፡ በዚህ ሂደት የመንግሥት አካላት ሚናቸው ከፍተኛ ሲሆን ለአብነትም የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው። ለምሳሌ የፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓቱን በበላይነት የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈፀም ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር ትልቅ የቤት ሥራ አለበት፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴርም የአገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት የማስተዳደር፣ የፌዴራል መንግሥት በጀትን የማዘጋጀት፣ የተፈቀደ በጀትን ለሚመለከተው አካል የመላክ፣ አፈጻጸሙን የመገምገም እና የመሳሰሉት ተግባራት እና ኃላፊነቶች ያሉት መሥሪያ ቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ትግበራ ጋር በተያያዘ የሚኖሩት ተግባርና ኃላፊነቶች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር በሕዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማኅበረሰቡን የማሳወቅ እና የማንቃት ሥራ እንዲሰሩ እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ አተገባበር የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስተባበር ይጠበቅበታል። የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋማት የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቋቋሙ ተቋማት ወይም አደረጃጀቶች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ የሰላም እና የፀጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ረገድ ሚናቸው የጎላ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሕጎችን ቅድሚያ እና ትኩረት በመስጠት ከማጽደቅ፣ ለሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ ትግበራ የሚቋቋሙ ተቋማት ኮሚሽነሮች እና ዳኞች ሹመት ግልፅ በሆነ እና የሕዝብን ተሳትፎ በሚያረጋግጥ ሂደት እንዲከናወን ከማድረግ ወዘተ አኳያ ኃላፊነቱ ከፍተኛ ነው። የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ የሽግግር ፍትሕ አተገባበርን አስመልክቶ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር እና አዎንታዊ ሰላም እንዲገነባ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአቅም ግንባታ ሥራ በመሥራት፣ የሽግግር ፍትሕ ዘላቂ ሰላምን ሊያመጣ በሚችል አግባብ በሁሉም ክልሎች ወጥ በሆነ መንገድ እየተተገበረ ስለመሆኑ በመከታተልና አስፈላጊውንም ድጋፍ በማድረግ ረገድ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል። በአጠቃላይ ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት አተገባበር ጋር በተያያዘ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሚና የሚኖራቸው የመንግሥት ተቋማት ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎችም አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው። እነዚህ አካላት የሽግግር ፍትሕ ሂደት ትግበራው የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ያከበረ፣ ተጎጂን ማዕከል ያደረገ እና የፖሊሲውን መርሆዎች ያከበረ መሆኑን በመከታተልና በመደገፍ፤ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለ ሽግግር ፍትሕ ሥርዓት እና ሂደት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር በሕዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው በማድረግ፤ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። እንደ መውጫ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በቅርቡ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት እንደተገለጸውም መንግሥት የተሟላና ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚያስችል የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ለማዘጋጀት አስቀድሞ የገለልተኛ ሙያተኞች ቡድን በማዋቀር ሲሰራ ቆይቷል። ከ80 በላይ ሕዝባዊ የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ማኅበረሰቡ በስፋት ሃሳብ እንዲሰጥ በማድረግም የተገኙ ግብዓቶችን በፖሊሲው በማካተት እንዲፀድቅ መደረጉ ተገልጿል። የፖሊሲው አጠቃላይ ዓላማ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውድ መሠረት ያደረገ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር መሆኑ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል። የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲያመጣና ዜጎች ነገን በተስፋ እንዲጠብቁና በአገራቸው ላይ ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው በተሟላ መልኩ መተግበር አለበት። ለዚህም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው። የሽግግር ፍትሕ ሂደቱና አገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ችግር ወጥታ ወደ ቀጣዩ የእድገት ምዕራፍ እንድትሸጋገር ከማድረግ አኳያ እርስ በርስ የሚመጋገቡ ሲሆን፤ ከዚህ አንጻር ሁለቱ በሚጣጣሙባቸው አጀንዳዎችና ግቦች ላይ በጋራ በመሥራት ሁሉን አቀፍ ውጤት ማግኘትም ይቻላል።
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 3262
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 6974
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 17183
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 20298
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 11065
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 12517
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 36365
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 29183
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 20298
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 17183
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 15165
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 14295
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 13989
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 13193
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 36365
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 29183
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 20298
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 17183
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር ልዩ አጋጣሚ
Jul 2, 2024 2552
በይስሐቅ ቀለመወርቅ የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1916 በአርጀንቲና አስተናጋጅነት ተጀመረ። ዘንድሮ ደግሞ 48ተኛው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር በአሜሪካን አዘጋጅነት እየተደረገ ይገኛል። በውድድሩ 16 አሰልጣኞች የተለያየ ሀገራትን ብሔራዊ ቡድን ይዘው የሚያሰለጥኑ ሲሆን፤ ከነዚህ ሰባቱ አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች መሆናቸው የዘንድሮውን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር ልዩ ያደርገዋል። በራሳቸው ሀገር ተወላጆች እየሰለጠኑ በኮፓ አሜሪካው እየተሳተፉ የሚገኙ ሀገራትን ስንመለከት ብራዚል በብራዚላዊው አሰልጣኝ ዶሪቫል ሲልቬስትር፤ ሜክሲኮ በሜክሲኳዊው ጃሚን ሎዛኖ፣ አዘጋጇ ሀገር አሜሪካ ደግሞ በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ግሬግ ማቲውና አርጀንቲና ደግሞ በአርጀንቲናዊው ሊዮኔል ስካሎኒ እየሰለጠኑ ይገኛሉ። ፓናማ በዴንማርካዊው አሰልጣኝ ቶማስ ክርስቲያንሰን፤ ጃማይካ በአዬስላንዳዊው አሰልጣኝ ሂመር ሃልግሪምሰን፤ ካናዳ በአሜሪካዊው ጂሲ አለን፤ኢኳዶር በስፔናዊው ፍሊክስ ሳንቼዝ ፤ቦሊቪያ በብራዚላዊው አንቶኒዮ ካርሎስ እና ፔሩ በኡራጋዊው አሰልጣኝ በጆርጅ ፎሳቴ እየሰለጠኑ በኮፓ አሜሪካ በመሳተፍ ላይ ናቸው። በዘንድሮው ኮፓ አሜሪካ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝን ጨምሮ ሰባት አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች ሰባት ሀገራትን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። ለመሆኑ እነዚህ አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች እነማናቸው?   ሊዮኔል ስካሎኒ፡- ይህ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2018 እያሰለጠነ የሚገኝ ሲሆን በ2021 የኮፓ አሜሪካን፤ በ2022 ደግሞ የዓለም ዋንጫን ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር አሸንፏል። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ይዞ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን አርጀንቲና በምድብ ጨዋታዎቿ ካናዳ፣ ቺሊንና ፔሩን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍፃሜ እንድትገባ አስችሏታል። ማርሴሎ ቤልሳ፡- የ68 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋው አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የኡራጋይ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ይገኛሉ።   ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የኡራጋይ ብሔራዊ ቡድን የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ያገዙት ሲሆን ፓናማን፣ ቦሊቪያንና አዘጋጇ ሀገር አሜሪካንን አሸንፎ ሩብ ፍፃሜ እንዲቀላቀል አስችለውታል። ፈርናንዶ ባቲስታ፡- በ53 ዓመት ዕድሜው ላይ የሚገኘው ይህ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የቬንዙዌላ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ይገኛል።   ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የቬንዙዌላን ብሔራዊ ቡድንን ይዞ እየተሳተፈ ሲሆን፤ ቬንዙዌላ በምድብ ጨዋታዎቿ ኢኳዶርን፣ ሜክሲኮና ጃማይካን አሸንፋ ሩብ ፍፃሜ እንድትገባ አስችሏታል። ኔስተር ሎሬንዞ ፡- የ58 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2022 ጀምሮ እያሰለጠነ ይገኛል።   ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የኮሎምቢያን ብሔራዊ ቡድንን ይዞ ፓራጓይና ኮስታሪካን በምድብ ጨዋታ በማሸነፍ ኮሎምቢያ ሩብ ፍፃሜ እንድትገባ ያደረገ ሲሆን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከብራዚል ጋር ያደርጋል። ሪካርዶ ጋርሲያ፡- የ66 ዓመቱ አንጋፋ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ ሪካርዶ ጋርሲያ የቺሊ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2024 ጀምሮ እያሰለጠኑ ይገኛሉ።   ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የቺሊ ብሔራዊ ቡድንን ይዘው በሚፈልጉት ርቀት መጓዝ አልቻሉም። በምድብ ጨዋታቸው ከካናዳና ፔሩ ጋር በተመሳሳይ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀውና በአርጀንቲና 1 ለ 0 ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል። ዳንኤል ጋርኔሮ፡- የ55 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የፓራጓይ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2024 ጀምሮ እያሰለጠነ ይገኛል። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የፓራጓይ ብሔራዊ ቡድንን ይዞ እተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን፤ በሚፈለገው ርቀት መጓዝ አልቻለም።   ከኮሎምቢያና ብራዚል ጋር ባደረጋቸው ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈትን በማስተናገዱ፤ከኮስታሪካ ጋር የሚያደርገው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ እየቀረው ከውድድሩ ውጪ ሆኗል። ጉስታቮ አልፋሮ፡- የ61 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የኮስታሪካ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ይገኛሉ።   ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የኮስታሪካን ብሔራዊ ቡድንን ይዘው በምድብ ጨዋታቸው በኮሎምቢያ ተሸንፈው ከብራዚል ጋር አቻ ተለያይተዋል። ወደ ሩብ ፍፃሜው ለማለፍ ከፓራጓይ ጋር የሚደርጉትን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ማሸነፍና የኮሎምቢያና የብራዚልን የጨዋታ ውጤት መጠበቅ ግድ ይላቸዋል። በኮፓ አሜሪካ የዋንጫ ውድድር አርጀንቲና፣ ካናዳ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር፣ ኡራጋይ፣ ፓናማና ኮሎምቢያ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው። ኮሎምቢያ ከብራዚል፤ ኮስታሪካ ከፓራጓይ ከሌሊቱ 10 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ሩብ ፍፃሜ የሚገባው ቀሪ አንድ ቡድን የሚለይ ይሆናል። በዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር ሰባት አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች ሰባት ሀገራትን እያሰለጠኑ እየተፋለሙበት ያለ ልዩ አጋጣሚ ፈጥሯል።    
የአውሮፓ ዋንጫን ለበርካታ ጊዜ ያነሱት አገራት እነማን ናቸው?
Jul 2, 2024 1688
(በሙሴ መለስ) እ.አ.አ 1960 የመጀመሪያው የአውሮፓ ዋንጫ (በቀድሞ አጠራሩ ኢሮፒያን ኔሽንስ ካፕ) የጀመረበት ዓመት ነው። በፈረንሳይ አስተናጋጅነት እ.አ.አ ከሐምሌ 6 እስከ 10 1960 በተካሄደው ውድድር የያኔዎቹ ሶቪየት ሕብረት፣ ቼኮዝሎቫኪያና ዩጎዝላቪያ ተሳትፈዋል። ሶቪየት ሕብረት (በአሁኑ ስያሜዋ ሩሲያ) በፍጻሜው ጨዋታ ዩጎዝላቪያን ስላቫ ሜትሬቬሊና ቪክቶር ፖንዴልኒክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 1 በማሸነፍ ታሪካዊውን ዋንጫ አንስታለች። ከ64 ዓመት በፊት የተጀመረው የአውሮፓ ዋንጫ የዘንድሮውን ሳይጨምር 10 አገራት የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል። ጀርመንና ስፔን በተመሳሳይ ሶስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ስኬታማ የሆኑ አገራት ናቸው። ምዕራብ አውሮፓዊቷ ጀርመን እ.አ.አ በ1972፣ 1980 እና 1996 አህጉራዊውን ክብር ከፍ አድርጋ አንስታለች። ጀርመን ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ያነሳችው ምዕራብ ጀርመንና ምስራቅ ጀርመን ከመዋሃዳቸው በፊት ነበር። ብሔራዊ ቡድኑ ካነሳቻው ዋንጫዎች በተጨማሪ 3 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሶ ተሸንፏል። በደቡብ ምዕራብ አውሮፓ የምትገኘው ስፔን እ.አ.አ በ1964፣ 2008 እና 2012 በተካሄዱ ውድድሮች ዋንጫውን አንስታለች። 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሳ ሽንፈትን አስተናግዳለች። ስፔን በሁለት ተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫዎች ዋንጫ ያነሳች ብቸኛ አገር ናት። ጣልያንና ፈረንሳይ የአውሮፓ ዋንጫን ክብር ሁለቴ በመጎናጸፍ ይከተላሉ። የደቡብ ማዕከላዊ አውሮፓዊቷ አገር ጣልያን እ.አ.አ በ1968 እና 2020 ዋንጫውን አንስታለች። የ16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ባለቤት ጣልያን በጀርመን አስተናጋጅነት እየተደረገ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በጥሎ ማለፉ በስዊዘርላንድ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ የሚታወስ ነው። ሰማያዊዎቹ በሚል ቅጽል ስም በሚጠራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ በ1984 እና 2000 የአውሮፓ ዋንጫን ወስዷል። በተጨማሪም ጣልያን 2 ጊዜ እና ፈረንሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ሽንፈት አስተናግደዋል። ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድ፣ግሪክ፣ ሩሲያና በቀድሞ አጠራሯ ቼኮዝሎቫኪያ( በአሁኑ ሰዓት ቼክ ሪፐብሊክና ስሎቫኪያ የሚጠሩት አገራት) በተመሳሳይ አንድ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫን አንስተዋል። ሩሲያ 3 ጊዜ እንዲሁም ቼኮዝሎቫኪያና ፖርቹጋል በተመሳሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። ከዚህ ውጪ ዋንጫ ባያነሱም የቀድሞ ዩጎዝላቪያ 2፣ ቤልጂየምና እንግሊዝ በተመሳሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰዋል። በጀርመን እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አዲስ የዋንጫ ባለቤት ይገኝ ይሆን? ጥያቄው ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ምላሽ ያገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም