ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ) 13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ማምሻውን በበፔሬ ጄጎ ስታዲየም ተካሄዷል።

አልጄሪያ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል በመፍጠር የነበራትን ብልጫ ወደ ውጤት መቀየር አልቻለችም።

መርሃ ግብሩ በአፍሪካ ዋንጫው ምንም ግብ ያልተቆጠረበት የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኗል።

ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ በአራት ነጥብ ምድቡን እየመራች ነው። ቱኒዚያ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

በምድብ ሶስት ቦትስዋና ከናይጄሪያ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ካሸነፈች የምድቡን መሪነት ከአልጄሪያ ትረክባለች።

ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ የያዘችው ቦትስዋና የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ ትጫወታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም