ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
በዞኑ በመኸር ወቅት ከ264 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ይለማል
Jun 12, 2026 98
አፍጥር፣ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ):-በጉራጌ ዞን በተያዘው የመኸር ወቅት ከ264 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች እንደሚለማ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የዞኑ የ2018/19 የምርት ዘመን የመኸር ወቅት የሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ''የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልፅግና'' በሚል መሪ ሃሳብ በቸሃ ወረዳ ተካሂዷል፡፡   የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው በዚህ ወቅት እንዳሉት በዞኑ በመኸር እርሻ ከ264 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይለማል። ለመኸር እርሻ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመው፣ 56 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በመጠባበቂያነት መያዙንም ተናግረዋል፡፡ በመኸር ወቅቱ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ቦለቄ፣ የቢራ ገብስ እና ሌሎች ሰብሎች እንደሚለሙ ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅትም የእርሻ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ አበራ ገለጻ በመኸሩ ከሚለማው አጠቃላይ መሬት ውስጥ 41ሺህ 800 ሄክታሩ በኩታ ገጠም የሚለማ ነው።   የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሱ ድንቁ በበኩላቸው እንዳሉት በዓመት ከሦስት ጊዜ በላይ ለማምረት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋቱ በግብርና ምርት ላይ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው። የምርት ማሳደጊያ ግብዓት በወቅቱ ከማሰራጨት ባለፈ የአርሶ አደሩን ፍላጎት እና አቅም በሚገባ በመለየት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በተፋሰስ የለሙ አካባቢዎች ጭምር በተለያዩ ሰብሎች እየለሙ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የጌታ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙዘፋ የሱፍ ናቸው። የወረዳው አርሶ አደሮች በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ገቢ የሚያስገኙ ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩ በመደረጉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወታቸውን እየቀየሩ መጥተዋል ብለዋል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በዞኑ በሌማት ትሩፋት በተከናወኑ የዶሮ እርባታ፣ የወተት እና የእንስሳት ልማት ስራዎች እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።   በሰብል ልማትም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ያሉት አስተዳዳሪው በተያዘው የመኸር እርሻ አንድም መሬት ጾም እንዳያድር ልማቱን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። በበልግ ወቅት በዝናብ ስርጭት መዘግየት ምክንያት የጠፋውን የበቆሎ ሰብልን ለማካካስ አስፈላጊው የግብርና ግብዓት በመጠቀምና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበር ይሰራል ሲሉም አክለዋል። በመድረኩ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ ደህንነትና ብልፅግና ከጎረቤቶቿ የጋራ ተጠቃሚነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው
Jun 12, 2026 157
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ደህንነትና ብልፅግና ከጎረቤቶቿ የጋር ተጠቃሚነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያን የድንበር አስተዳደር ሥርዓት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማዘመን የሚያስችል ከፍተኛ ሀገራዊ የፖሊሲ ምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።   የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት እና ከአፍሪካ ህብረት የድንበር ፕሮግራም ጋር በመተባበር ላለፉት አምስት ወራት ''የኢትዮጵያን የድንበር አስተዳደር ማጠናከር'' በሚል መሪ ሀሳብ ሰፊ የምርምር ፕሮጀክት ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል። ኢኒስቲትዩቱ ጥናቱን መሰረት በማድረግም ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚያመላክት ፍኖተ ካርታ ዛሬ ይፋ አድርጓል። በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ድንበሮች ከወሰንነት ባሻገር የደኅንነት፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የሚንጸባረቅባቸው ስትራቴጂክ ቦታዎች ናቸው። የኢትዮጵያና ጎረቤቶቿ የድንበር አካባቢ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ቢሆኑም፤ በተለዋዋጭ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ውጤታማ የአስተዳደር መዋቅር የሚጠይቁ ተግዳሮቶችም እንደሚስተዋሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ደህንነትና ብልፅግና ከጎረቤቶቿ የጋር ተጠቃሚነት ጋር የተቆራኘ መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የድንበር አስተዳደር ማጠናከር ፖሊሲም ቀጣናዊ የጋራ ትብብርና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሁለገብ ይዘትን አካቶ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል።   'የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፤ በጥናት ላይ የተመሰረተው ፍኖተ ካርታ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ሕይወትና ነባራዊ ሁኔታ ያንጸባረቀ መሆኑን ተናግረዋል። በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችንም በድንበር ተሻጋሪ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አሰራር የሚዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የድንበር አካባቢዎችን ከፀጥታ ስጋት ጋር የሚያያዝ ዕሳቤ በመቀየር የንግድ፣ የፖሊስ፣ ጉምሩክ፣ ኢሚግሬሽንና የክልል መስተዳድር ተቋማትን ቅንጅት የሚያጠናክር አውድ የሚፈጥር ነው ብለዋል።   በአፍሪካ ሕብረት የጀርመን ምክትል ቋሚ ታዛቢ ዴቪድ ጉዲሽ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የድንበር ላይ አስተዳደር የፖሊሲ አቅጣጫ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። ለዚህም ጀርመን እ.አ.አ ከ2008 ጀምሮ ከአፍሪካ ህብረትና ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለድንበር አስተዳደር መጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን አስታውሰዋል። በቀጣይም የሀገራት ድንበሮች የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰብዓዊ ደኅንነትና የቀጣናዊ ብልፅግና ድልድዮች እንዲሆኑ ድጋፏ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የድንበር አስተዳደር ማጠናከር ፍኖተ ካርታም ድንበር አካባቢዎች የጋራ ሰላምና ደኅንነትን፣ ዕድገትና ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ድልድይ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።
የኢትዮጵያን የቡና ምርት ጥራትና ምርታማነት የሚያሻሽሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እየተደረጉ ነው
Jun 12, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የቡና ምርት ጥራትና ምርታማነት የሚያሻሽሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለቡና አምራች አርሶ አደሮች የሚውሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የግብርና ግብዓቶች አስረክቧል።   ለቡና አምራች አርሶ አደሮች የሚተላለፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የግብርና ግብዓቶችም የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ተረክበዋል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ በግብርና መስክ የተመዘገበው ስኬት ለቡና ምርት ጥራትና ምርታማነት ወሳኝ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። ባለስልጣኑ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን፣ የጥራት ቁጥጥር መሳሪያዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን ለክልል በማከፋፈል ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በቡና ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች በቴክኖሎጂ የተደገፉ ግብዓቶች በማቅረብ ጥራቱ የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱ በማስቻል የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ግብዓቶቹ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የቀረቡ ሲሆን ቡና አብቃይ በሆኑ ክልሎች የተመረጡ ወረዳዎች ለሞዴል አርሶ አደሮች ተደራሽ እንደሚሆኑ ገልፀዋል። ከዓመታት በፊት በሔክታር 6 ኩንታል ሲመረት የነበረ መሬት አሁን ላይ በሔክታር ከአስር ኩንታል በላይ ቡና ማምረት እየተቻለ መሆኑን አንስተዋል። በዛሬው እለትም 62 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የግብርና ግብዓቶች ለቡና አምራች አርሶ አደሮች መተላለፋቸውን አረጋግጠዋል። ግብዓቶቹ የቡና ምርታማነትንና ጥራትን በማሳደግ አርሶ አደሮችን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጋር እንደሚያላምዱ ጠቅሰዋል። ቴክኖሎጂዎቹም የቡና ምርታማነት ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ዓለም አፍ የገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንደሚያግዙ አስረድተዋል። የተሻለ ምርትና ምርታማነት በማረጋገጥ ምርቱ ጥራቱ ጠብቆ በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። በርክክቡ የተገኙት ኦሮሚያ ክልል ቡናና ሻይ ልማት ዳይሬክተር ታከለ ሃይለማርያም፤የክልሉ መንግስት የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የተሰጡት ግብዓቶችም የበዘርፉ የተሰማሩ እርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ በመሆናቸው አርሶ አደሩ በአግባቡ የሚጠቀምበት ይሆናል ብለዋል። የሲዳማ ክልልን ወክለው የመጡት ቡዙነህ ቡናዬ በበኩላቸው፤ ባለስልጣኑ ልዩ ልዩ ዘመናዊ የግብርና ግብአቶች ሲያቀርብ መቆየቱንና በዚህም የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከቫቲካን ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጄሮቲ እና ከኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጋር ተወያዩ
Jun 12, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የቫቲካን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ኃላፊ ብፁዕ ወቅዱስ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጄሮቲ እና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ጳጳሳቱ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።   በቫቲካን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ኃላፊ ብፁዕ ወቅዱስ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጄሮቲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እና የሞራል እሴቶች ለሀገሪቷ ትልቅ ሀብት መሆኑናቸውን ተገንዝበዋል። የሞራል እሴት ኢትዮጵያ በጀግኖች የተሞላች፣ የበለፀገ ሃይማኖታዊ ሥነ-ጽሑፍ፣ ምንኩስና እና ሥርዓተ-ቅዳሴ ያሏት ጥንታዊ ሀገር በመሆኗ ጉብኝታቸውን አስደሳች እንደሚያደርገው ገልጸዋል።   የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሀገሪቷ ውስጥ በትምህርት እና በጤና መስኮች ላይ በትብብር እንደምትሰራ ጠቅሰው፤ ይህም የሀገሪቷን ተስፋ ሊመጥኑ የሚችሉ የወደፊት ትውልዶችን ለመገንባት ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በስኬት ያጠናቀቀችውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክተውም፣ የኢትዮጵያ ጉዞ ሁልጊዜ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የማይመለስ በመሆኑ እየታየ ያለው የዲሞክራሲ ዕድገት ሊጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።   የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያና በቫቲካን መካከል ያለው የረዥም ዘመን ታሪካዊ ትስስር በተለያዩ ዘርፎች የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ከቫቲካን ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት በመጠቀም፣ የልማትና የበጎ አድራጎት ተግባራትን እንደምታከናውን ጠቁመዋል። በውይይቱ የሁለቱ ሀገራት ጳጳሳትን ጨምሮ የቫቲካን አምባሳደር ሊቀ ጳጳስ ብራያን አዳይግዌ ተገኝተዋል።
የሚታይ

ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 354
በኢዜአ አይን! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። ‎ የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድናቸው?
Jun 12, 2026 256
የጤና ነገር … በዮሐንስ ደርበው የሰው ልጅ ሊሻሻሉ በሚችሉ እና በማይችሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለልብ ህመም ሊጋለጥ እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የአዋቂ የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሃኑ ሞገስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የልብ ህመም ከተወሳሰብ ዘላቂ የጤና እክል እስከ ድንገተኛ ኅልፈት ያደርሳል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ሰዎች ማሻሻል በሚችሏቸው (ሞዲፋይብል) እና ማሻሻል በማይችሏቸው (ነን ሞዲፋይብል ወይም ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች) ለልብ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዶክተር ብርሃኑ ይገልጻሉ። መሻሻል ከሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም (በአግባቡ መድኃኒቱ ካልተወሰደ)፣ተገቢ ያልሆነ የስብ ክምችት፣ ከፍተኛ ውፍረት (ክብደት)፣ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብ አለመኖር እንዲሁም አብዝቶ ስኳር፣ ጣፋጭና አልኮል መጠቀም የሚሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ እንዲሁም ሰዎች ማሻሻል ከማይችሏቸው (ተፈጥሯዊ) አጋላጮች መካከል፤ በቤተሰብ የሚተላለፍ መኖሩን፣ በዕድሜ መጨመር የሚከሰት መሆኑን (ለምሳሌ፡- ወንድ ከ45 ሴት ከ55 ዓመት በላይ ሲሆናቸው ለልብ ህመም ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን) እንዲሁም ወንዶ ከሴቶች በይበልጥ ለልብ ህመም ተጋላጭ የመሆናቸው አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ የልብ ህመም ምልክቶች የደረት ውጋት በግራ በኩል ወይም መሐል ላይ፣ ከወትሮው የተለየ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት መኖር፣ የሰውነት በተለይም እግር አካባቢ እብጠት፣ ራስን መሳት እና ሳል የልብና ተያያዥ ህመም ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ አብራርተዋል። የልብን ጤናን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ጤናማ አመጋገብን መከተል እንደሚገባ የሚመክሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ አትክልት ማዘውተር፣ ምግብ ሲዘጋጅም ፈሳሽ ዘይት መጠቀም፣ ስኳር፣ ጨው እና ጣፋጭ ነገሮችን መገደብ ከተቻለም ማስወገድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህም ብስክሌት መንዳት፣ በእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ዋና መዋኘት፣ እስከሚያልብ እና የልብ ምት እስከሚጨምር ብሎም እስከሚደክሙ የአካል ብቃት መሥራት የልብን ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽዖ አለው ነው ያሉት፡፡ ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ “ቦዲ ማስ ኢንዴክስ (ቢ ኤም አይ)” ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 እንዲሆን ይመከራል ብለዋል፡፡ ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠቀም፣ የስኳር ህመምና ከፍተኛ ደም ግፊት ካለም የመድኃኒት አወሳሰድን አለማስተጓጎል፣ አመጋገብ ላይ ስብ አለማብዛትና አብዝቶ አለመቀመጥ የልብ ህመምን ለመከላከል እንደሚያግዙ ነው ያስረዱት፡፡ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች የሆኑ ጤናማ ሰዎች ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ባሉ ጊዜያት አንድ ጊዜ፣ ዕድሜያቸው ከ45 በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም የልብ ህመም ያለባቸው እንደሁኔታው በየጊዜው ክትትል እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከልብ ህመም እንዲጠብቁ መክረው፤ ከዚህ ያለፈ ችግር ሲኖር ቶሎ የሕክምና ክትትል ማድረግ እና “ዛሬ ነገ” በማለት ጊዜ እያባከኑ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማይገባቸው አሳስበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ጤና #የልብ_ህመም

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የኢትዮጵያ ደህንነትና ብልፅግና ከጎረቤቶቿ የጋራ ተጠቃሚነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው
Jun 12, 2026 157
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ደህንነትና ብልፅግና ከጎረቤቶቿ የጋር ተጠቃሚነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያን የድንበር አስተዳደር ሥርዓት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማዘመን የሚያስችል ከፍተኛ ሀገራዊ የፖሊሲ ምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።   የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት እና ከአፍሪካ ህብረት የድንበር ፕሮግራም ጋር በመተባበር ላለፉት አምስት ወራት ''የኢትዮጵያን የድንበር አስተዳደር ማጠናከር'' በሚል መሪ ሀሳብ ሰፊ የምርምር ፕሮጀክት ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል። ኢኒስቲትዩቱ ጥናቱን መሰረት በማድረግም ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚያመላክት ፍኖተ ካርታ ዛሬ ይፋ አድርጓል። በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ድንበሮች ከወሰንነት ባሻገር የደኅንነት፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የሚንጸባረቅባቸው ስትራቴጂክ ቦታዎች ናቸው። የኢትዮጵያና ጎረቤቶቿ የድንበር አካባቢ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ቢሆኑም፤ በተለዋዋጭ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ውጤታማ የአስተዳደር መዋቅር የሚጠይቁ ተግዳሮቶችም እንደሚስተዋሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ደህንነትና ብልፅግና ከጎረቤቶቿ የጋር ተጠቃሚነት ጋር የተቆራኘ መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የድንበር አስተዳደር ማጠናከር ፖሊሲም ቀጣናዊ የጋራ ትብብርና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሁለገብ ይዘትን አካቶ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል።   'የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፤ በጥናት ላይ የተመሰረተው ፍኖተ ካርታ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ሕይወትና ነባራዊ ሁኔታ ያንጸባረቀ መሆኑን ተናግረዋል። በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችንም በድንበር ተሻጋሪ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አሰራር የሚዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የድንበር አካባቢዎችን ከፀጥታ ስጋት ጋር የሚያያዝ ዕሳቤ በመቀየር የንግድ፣ የፖሊስ፣ ጉምሩክ፣ ኢሚግሬሽንና የክልል መስተዳድር ተቋማትን ቅንጅት የሚያጠናክር አውድ የሚፈጥር ነው ብለዋል።   በአፍሪካ ሕብረት የጀርመን ምክትል ቋሚ ታዛቢ ዴቪድ ጉዲሽ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የድንበር ላይ አስተዳደር የፖሊሲ አቅጣጫ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። ለዚህም ጀርመን እ.አ.አ ከ2008 ጀምሮ ከአፍሪካ ህብረትና ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለድንበር አስተዳደር መጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን አስታውሰዋል። በቀጣይም የሀገራት ድንበሮች የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰብዓዊ ደኅንነትና የቀጣናዊ ብልፅግና ድልድዮች እንዲሆኑ ድጋፏ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የድንበር አስተዳደር ማጠናከር ፍኖተ ካርታም ድንበር አካባቢዎች የጋራ ሰላምና ደኅንነትን፣ ዕድገትና ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ድልድይ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል
Jun 12, 2026 734
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ አስተማማኝ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና ለጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ወሳኝ ለሆነው ሀገራዊ ምክክር ስኬት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 የተቋቋመ ነፃ ተቋም ሲሆን፣ በሀገሪቱ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል። እስካሁን ባለው ሂደት ከወረዳ ጀምሮ መላውን የኅብረተሰብ ክፍል፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ሲቪክ ማኅበራትን፣ ምሁራንንና ሁሉም ባለድረሻ አካላትን ያሳተፈ ሰፊ የአጀንዳ ማሰባሰብ ተግባር አከናውኗል። ተቋሙ እነዚህን የተደራጁ አጀንዳዎች ይዞ ወደ ቀጣዩ ወሳኝ ምዕራፍ ለመሻገር፣ በቅርቡ ዋናውን ሀገራዊ ጉባኤ ለማካሄድ የመጨረሻ የዝግጅት ሥራዎቹን እያጠናቀቀ ይገኛል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠርና ልማትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ዓይነተኛ ሚና አለው፡፡ ሀገሪቱ ለዘመናት ከቆዩ ማነቆዎች ተላቃ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ እንድትሸጋገር ሀገራዊ ምክክር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም ትልቁና አስተማማኙ አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ በምክክር ሂደቱ ላይ በንቃት ከመሳተፍ ባለፈ፣ በሁለት ዙር ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰበሰቡትን ሀገራዊ አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን አስታውቀዋል። በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ዋናው ሀገራዊ የውይይት ጉባኤ ላይ፣ በኢትዮጵያውያን መካከል የቆዩና ለአለመግባባት ምክንያት የሆኑ ሥር የሰደዱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያገኝ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም አብራርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫና በሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ላይ በልዩ ዕቅድ መነሳቱን የገለጹት አቶ ሰለሞን፣ ኮሚሽኑ በከፍተኛ ኃላፊነት እዚህ ደረጃ ላይ በመድረሱ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ፓርቲዎች ከኮሚሽኑ ጋር ያላቸውን የቅርብ የሥራ ግንኙነትና ሀገራዊ ኃላፊነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመጠቆም፣ አሁን ባለው ወሳኝ ወቅት ለጋራ መግባባት መሠረት መጣል የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ ይህንን ታሪካዊና ትልቅ ተስፋ የተሰነቀበትን ሀገራዊ ሂደት በንቃት በመደገፍ፣ ሀገሪቱ ካለችበት የፖለቲካ ማነቆ ወጥታ ወደ አዲስ የመረጋጋትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ምዕራፍ እንድትሻገር የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
ቦርዱ የምርጫ ውጤቶችን ይፋ የሚያደርግበትን የድህረ-ምርጫ ተግባራት ለጋዜጠኞች አስጎበኘ  
Jun 11, 2026 1202
አዲስ አበባ፤ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችን ይፋ የሚያደርግበትን የድህረ-ምርጫ ተግባራት ለጋዜጠኞች አስጎበኘ። የምርጫ ቦርድ ውጤት ማረጋገጫ ክፍል አስተባባሪ ዶክተር ሽመልስ ሲሳይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በሁሉም ምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራ የተጠናቀቀላቸው ሙሉ ሰነዶች በቀጥታ ወደ ዋናው የቦርዱ ውጤት መረከቢያ ክፍል ይገባሉ። በመቀጠልም በማረጋገጫ ክፍሉ ውስጥ እያንዳንዱ ዕጩ ያገኘው ድምፅ ዋጋ ካላቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ እንዲሁም በዕለቱ በአካል ተገኝተው ከፈረሙ መራጮች ቁጥር ጋር የመጣጣሙ ጉዳይ በጥብቅ እንደሚፈተሽ ተናግረዋል።   አስተባባሪው ዶክተር ሽመልስ እንደገለጹት፤ ይህን የማጣራት ሂደት የሚያልፉ መረጃዎች ተገቢነትና ትክክለኛነታቸውን ወደ ሚያረጋግጠው የኦዲት ቡድን የሚመሩ ይሆናል። ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠው ደግሞ በቦርዱ የአይሲቲ (ICT) ሲስተም ውስጥ ገብተው በቦርዱ እንዲጸድቁ ይደረጋልም ነው ያሉት። በማረጋገጥ ሂደቱ ላይ ያልተጣጣሙና ግድፈት ያለባቸው መረጃዎች ሲገኙ የኦዲት ቡድኑ በሚገባ ከመረመረ በኋላ ለውሳኔ የሚያቀርብ ሲሆን፤ ቦርዱም እነዚህን ጥብቅ የአሠራር ሂደቶች በሙሉ ተከትሎ የመጨረሻውን ውጤት ይፋ ያደርጋል ብለዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የምርጫው አፈጻጸምና የድህረ ምርጫ ሥራዎችን ከነገ ጀምሮ በቀበሌ ደረጃ ይገመግማል
Jun 11, 2026 872
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸምና የድህረ ምርጫ ሥራዎች ግምገማ ከነገ ጀምሮ በቀበሌ ደረጃ ማካሄድ ይጀምራል። የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ የ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የፓርቲው አፈጻጸምና የድህረ ምርጫ ስራዎችን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ጌቱ በመግለጫቸው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ከሌሊት እስከ ሌሊት በመሰለፍ ድምፁን በመስጠት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ነው። በዚህም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ሰላማዊና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ በማካሄድ ኢትዮጵያውያን በፅናት አዲስ ታሪክ ጽፈዋል ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ ግቦችን አስቀምጦ የምርጫ ቦርድን ህጎች፣ አዋጅና መመሪያዎች ተከትሎ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እና በፉክክር በመንቀሳቀስ ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ ለምርጫው ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊነት የሚያስችሉ ስራዎች በቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል። ከቅድመ ምርጫ እስከ ምርጫው ዕለት የታየውን የአመራሮችና የአባላቱን የላቀ መናበብ፣ መቀናጀትና ቁርጠኝነት ግለቱን ጠብቆ ማስቀጠል አስፈላጊ ነው ብለዋል። የድህረ ምርጫ ሥራዎችን በስኬት በመፈፀምም የተጀመረውን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የብልጽግና ጉዞ ይበልጥ ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን ጨምሮ በሁሉም ወረዳ የሚገኙ የብልፅግና ህብረት አመራሮች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተያዙ መንትያ ግቦችን ለማሳካት የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ ተግባራት ላይ ተግባቦት መፈጠሩን ጠቅሰዋል። ከነገ ጀምሮም በክልሉ በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች በጠቅላላ ምርጫው አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ስራዎች እንደሚገመገም ጠቁመው፤ በዚህም በክልሉ በገጠር እና በከተማ የሚገኙ የፓርቲው አባላት እንደሚሳተፉ ነው የገለፁት። በመድረኩ ላይ ፓርቲው በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እቅዱ መሠረት በቅድመ ምርጫና በምርጫው ወቅት የነበረውን አፈጻጸም እንደሚገመገም አብራርተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በድህረ ምርጫ ወቅትም ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። በሚካሄደው ግምገማ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አባላት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑም ኃላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል።
በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኦብነግ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል
Jun 11, 2026 821
ጅግጅጋ፤ ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ምክትል ሊቀመንበር አሕመድ ያሲን፤ ከለውጡ በፊት በሶማሌ ክልል በነበረው አግላይና ፍትሃዊነት በጎደለው የፖለቲካ ስርዓት ኦብነግ የጫካ ትግል ውስጥ እንደነበር አስታውሰዋል። በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በተፈጠረው ምቹ የፖለቲካ ምህዳር የትጥቅ ትግሉን በመተው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። በዚህ የትግል ሂደት የሃሳብና የፖሊሲ ልዩነቶች እንደተጠበቁ መሆናቸውን አንስተው፤ በሀገር ሉአላዊነት፣ በብሄራዊ ጥቅምና በዜጎች ሰላምና ደህንነት ጉዳይ ላይ የተለየ አቋምና አመለካከት የለንም ሲሉ አስረድተዋል። በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት ለመጣው ዘላቂ ሰላም፣ የሚታዩና የሚጨበጡ የልማት ስራዎች ፓርቲያቸው አድናቆት እንዳለው አንስተው ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርቲያቸው የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በፓርቲው ስም ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር የባእድ ተልእኮ በመቀበል ለጥፋት የሚንቀሳቀሱ ባንዳዎች መኖራቸውን አስታውሰዋል። እንዲህ አይነት የጥፋት ተልእኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች በኦብነግ ውስጥ ምንም አይነት ስፍራ እንደሌላቸው አንስተው በጋራ እንታገላቸዋለን ሲሉም ገልጸዋል። ኦብነግ በሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ በመሳተፍ በክልሉ ያለውን ጠንካራ የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳየቱን ገልጸው በሰላማዊ ትግል ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት የበኩሉን መወጣቱን ይቀጥላል ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ሃይሎች በለውጡ የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ምህዳር በአግባቡ በመጠቀም ለሀገር ጥቅምና ለሁለንተናዊ እድገት አጋዥና ደጋፊ በመሆን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል።
ጽንፈኛ ቡድኑ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዳይሳካ ያደረገው ሙከራ በሰላም ወዳዱ ሕዝብ ህልም ሆኖ ቀርቷል-አቶ ጣሂር መሀመድ
Jun 11, 2026 1305
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ጽንፈኛ ቡድኑ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዳይሳካ ያደረገው ሙከራ በሰላም ወዳዱ ሕዝብ ህልም ሆኖ መቅረቱን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አባል አቶ ጣሂር መሀመድ ገለጹ። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብ ተሳትፎ ጎልቶ የታየበት ስኬታማ ሆኖ ተጠናቋል። ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ታዛቢዎች ምርጫው ዲሞክራሲያዊ፣ አካታችና ምሳሌነቱ የሚጠቀስ መሆኑን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አባል አቶ ጣሂር መሀመድ በምርጫውና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። አቶ ጣሂር እንዳሉት፤ የአማራ ክልል ሕዝብ በነጻነት የራሱን መሪዎች እንዳይመርጥ ጽንፈኛው ቡድን ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ጭምር በመቀናጀት ምርጫውን የማደናቀፍ ተግባራት ላይ ተጠምዶ መቆየቱን አንስተዋል። ጽንፈኛው ቡድን መራጩን ሕዝብ በዚህ ምርጫ ትሳተፍና፣ ይሄን ታደርግና የሚሉ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ጭምር በመጠቀም አደገኛ ቅስቀሳዎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ በመሰል እንቅስቃሴዎች ሕዝቡ ዋጋ ሲከፍል መቆየቱን ጠቅሰዋል። እንዲያም ሆኖ የአማራ ክልል ሕዝብ ጫናዎችን ተቋቁሞ ለሰላምና መረጋጋት ቅድሚያ በመስጠት ምርጫውን እንዲሳካ አድርጓል ያሉት አቶ ጣሂር፤ ለዚህ በሳል ውሳኔ ሕዝቡ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል። በዚህ ሁሉ ጫና ውስጥ ሕዝቡ ወጥቼ እመርጣለሁ፤ የምፈልገው መደበኛ የሆነ የመንግሥት አስተዳደር ነው በሚል መርህ በመመራት ምርጫውን ማሳካቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም በተጻጻሪው የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን የአማራን ሕዝብ እንደማይገልጸው ማሳያ መሆኑንም አስረድተዋል። በሕዝቡ ድምጽ የሚመሰረተው መንግሥት ዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ በከፍተኛ ኃላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ያመላከተ ነው ያሉት አቶ ጣሂር፤ ሕዝቡ በሰላም ዙሪያ በሚሰሩ ሥራዎች ተባባሪና ቁርጠኛ መሆኑን ያሳየበት ምርጫ መሆኑንም አብራርተዋል። በአማራ ክልል የተካሄደው ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ የጸጥታ ኃይልና ሚሊሻዎች በየደረጃው ካሉ አመራር ጋር በቅንጅት ያከናወኑት ተግባር ጉልህ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል። ይሄ ውጤት ደግሞ በመንግሥት እና በመደበኛ ሥርዓት ሕዝቡ እንዲተማመን ያስቻለ ነው ብለዋል። እንደ አቶ ጣሂር ገለጻ፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚጋፋ የኃይል አሰላለፍ ሕዝብንም ሀገርንም ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ሕዝቡ በዚህ ላይ ግንዛቤ ጨብጦ ለሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ የራሱን አሻራ እንዲያሳርፍ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ እየሰራ ነው። "ጥያቄዎች የሚመለሱት በኃይል ነው" የሚል አቋም ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት ሰላማዊ መንገድን በመምረጥ ችግሮች በውይይት የሚፈቱበት አውድ መፍጠር ላይ ሊሰሩ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። መንግሥት የሰላም ጥሪ አቅርቦ በሩን ክፍት ማድረጉ የሚበረታታ መሆኑን አመልክተው፤ ይሄ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመልክተዋል።

ማህበራዊ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከቫቲካን ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጄሮቲ እና ከኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጋር ተወያዩ
Jun 12, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የቫቲካን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ኃላፊ ብፁዕ ወቅዱስ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጄሮቲ እና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ጳጳሳቱ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።   በቫቲካን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ኃላፊ ብፁዕ ወቅዱስ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጄሮቲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እና የሞራል እሴቶች ለሀገሪቷ ትልቅ ሀብት መሆኑናቸውን ተገንዝበዋል። የሞራል እሴት ኢትዮጵያ በጀግኖች የተሞላች፣ የበለፀገ ሃይማኖታዊ ሥነ-ጽሑፍ፣ ምንኩስና እና ሥርዓተ-ቅዳሴ ያሏት ጥንታዊ ሀገር በመሆኗ ጉብኝታቸውን አስደሳች እንደሚያደርገው ገልጸዋል።   የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሀገሪቷ ውስጥ በትምህርት እና በጤና መስኮች ላይ በትብብር እንደምትሰራ ጠቅሰው፤ ይህም የሀገሪቷን ተስፋ ሊመጥኑ የሚችሉ የወደፊት ትውልዶችን ለመገንባት ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በስኬት ያጠናቀቀችውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክተውም፣ የኢትዮጵያ ጉዞ ሁልጊዜ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የማይመለስ በመሆኑ እየታየ ያለው የዲሞክራሲ ዕድገት ሊጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።   የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያና በቫቲካን መካከል ያለው የረዥም ዘመን ታሪካዊ ትስስር በተለያዩ ዘርፎች የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ከቫቲካን ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት በመጠቀም፣ የልማትና የበጎ አድራጎት ተግባራትን እንደምታከናውን ጠቁመዋል። በውይይቱ የሁለቱ ሀገራት ጳጳሳትን ጨምሮ የቫቲካን አምባሳደር ሊቀ ጳጳስ ብራያን አዳይግዌ ተገኝተዋል።
ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድናቸው?
Jun 12, 2026 256
የጤና ነገር … በዮሐንስ ደርበው የሰው ልጅ ሊሻሻሉ በሚችሉ እና በማይችሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለልብ ህመም ሊጋለጥ እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የአዋቂ የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሃኑ ሞገስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የልብ ህመም ከተወሳሰብ ዘላቂ የጤና እክል እስከ ድንገተኛ ኅልፈት ያደርሳል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ሰዎች ማሻሻል በሚችሏቸው (ሞዲፋይብል) እና ማሻሻል በማይችሏቸው (ነን ሞዲፋይብል ወይም ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች) ለልብ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዶክተር ብርሃኑ ይገልጻሉ። መሻሻል ከሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም (በአግባቡ መድኃኒቱ ካልተወሰደ)፣ተገቢ ያልሆነ የስብ ክምችት፣ ከፍተኛ ውፍረት (ክብደት)፣ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብ አለመኖር እንዲሁም አብዝቶ ስኳር፣ ጣፋጭና አልኮል መጠቀም የሚሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ እንዲሁም ሰዎች ማሻሻል ከማይችሏቸው (ተፈጥሯዊ) አጋላጮች መካከል፤ በቤተሰብ የሚተላለፍ መኖሩን፣ በዕድሜ መጨመር የሚከሰት መሆኑን (ለምሳሌ፡- ወንድ ከ45 ሴት ከ55 ዓመት በላይ ሲሆናቸው ለልብ ህመም ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን) እንዲሁም ወንዶ ከሴቶች በይበልጥ ለልብ ህመም ተጋላጭ የመሆናቸው አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ የልብ ህመም ምልክቶች የደረት ውጋት በግራ በኩል ወይም መሐል ላይ፣ ከወትሮው የተለየ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት መኖር፣ የሰውነት በተለይም እግር አካባቢ እብጠት፣ ራስን መሳት እና ሳል የልብና ተያያዥ ህመም ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ አብራርተዋል። የልብን ጤናን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ጤናማ አመጋገብን መከተል እንደሚገባ የሚመክሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ አትክልት ማዘውተር፣ ምግብ ሲዘጋጅም ፈሳሽ ዘይት መጠቀም፣ ስኳር፣ ጨው እና ጣፋጭ ነገሮችን መገደብ ከተቻለም ማስወገድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህም ብስክሌት መንዳት፣ በእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ዋና መዋኘት፣ እስከሚያልብ እና የልብ ምት እስከሚጨምር ብሎም እስከሚደክሙ የአካል ብቃት መሥራት የልብን ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽዖ አለው ነው ያሉት፡፡ ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ “ቦዲ ማስ ኢንዴክስ (ቢ ኤም አይ)” ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 እንዲሆን ይመከራል ብለዋል፡፡ ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠቀም፣ የስኳር ህመምና ከፍተኛ ደም ግፊት ካለም የመድኃኒት አወሳሰድን አለማስተጓጎል፣ አመጋገብ ላይ ስብ አለማብዛትና አብዝቶ አለመቀመጥ የልብ ህመምን ለመከላከል እንደሚያግዙ ነው ያስረዱት፡፡ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች የሆኑ ጤናማ ሰዎች ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ባሉ ጊዜያት አንድ ጊዜ፣ ዕድሜያቸው ከ45 በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም የልብ ህመም ያለባቸው እንደሁኔታው በየጊዜው ክትትል እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከልብ ህመም እንዲጠብቁ መክረው፤ ከዚህ ያለፈ ችግር ሲኖር ቶሎ የሕክምና ክትትል ማድረግ እና “ዛሬ ነገ” በማለት ጊዜ እያባከኑ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማይገባቸው አሳስበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ጤና #የልብ_ህመም
በዞኑ የባህላዊ ፍርድ ቤት ዳኞችን የህግ ግንዛቤ በማሳደግ ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ ነው
Jun 12, 2026 105
ገንዳውሃ፣ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ጎንደር ዞን የባህላዊ ፍርድ ቤት ዳኞችን የህግ ግንዛቤ በማሳደግ ህብረተሰቡ ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለጸ። በዞኑ በመተማ ወረዳና ገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ የቀበሌ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞችና ፀሐፊዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዛሬ ተሰጥቷል። ​የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኢብራሂም የሱፍ በስልጠናው ላይ እንደገለጹት፤ በዞኑ በአገር ሽማግሌ በመዳኘት በሰላም አብሮ የመኖር ባህላዊ እሴትን ከዘመናዊ የህግ እውቀት ጋር ለማጣመር የባህል ፍርድ ቤት ወሳኝ ነው። በዞኑም ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም ከዘመናዊው የፍትህ ዘርፍ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ፍትሀዊነትን ለማስፈን እየተሰራ ነው ብለዋል። ባህላዊ ዳኞች ጉዳዮችን ከህግ ድንጋጌዎች ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ባህል፣ ወግና አብሮ የመኖር እሴት በጠበቀ መልኩ እንዲከወን ማድረጋቸው በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ይህም በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚፈጠርን የክስ መዝገብ ክምችትና ህብረተሰቡ ፍትህን ለማግኘት ወደ ዞንና ክልል በመመላለስ የሚደርስበትን እንግልትን ለማስቀረት ያስችላል ብለዋል። የባህል ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙለትን ዓላማ እንዲያሳኩም ለዳኞችና ሌሎች ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናና ድጋፍ መስጠቱ እንደሚጠናከርም አረጋግጠዋል። ​በዞኑ ሽንፋ ቀበሌ የባህል ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አሰፋ ዋኘው እንደገለጹት በአካባቢያቸው የሚነሱ የመሬት፣ የቤተሰብና የተለያዩ የፍትሐ ብሄር ጉዳዮችን የበደለ ክሶ የተበደለ ተክሶ በዕርቅ እንዲቋጭ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ የተሰጣቸው ስልጠናም ከመደበኛ ህጎች ጋር የሚጣጣሙ አሰራሮችን ለይተው በማወቅ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። በገንዳ ውኃ ከተማ ቀበሌ 01 የባህል ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ረዳ ላቀው በበኩላቸው፤ በሚሰጡት የባህል የፍትህ አገልግሎት የህግ እውቀት ሲታከልበት የተበዳዮችን መብት ለማስከበር የሚያግዝ ነው ብለዋል። የባህል ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚመሰረተው በሁለቱም ባለጉዳዮች ፈቃደኝነት ላይ በመሆኑ በቀልን በማስቀረትና እርቅ በመፈጸም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። ይህም ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመመላለስ የሚባክነውን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ በመቆጠብ ለሌሎች የልማት ስራዎች ለማዋል ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር አመልክተዋል።
በሀገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማምጣት በቂ ዝግጅት አድርገናል- ተማሪዎች
Jun 12, 2026 114
ዲላ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- ዘንድሮ በሚሰጠው 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የዲላ ከተማ ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጹ። የከተማው አስተዳደር በበኩሉ በትምህርት ዘመኑ የማለፍ ምጣኔን ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት መደረጉን አስታውቋል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የዲላ ከተማ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር አቀፉ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በከተማው የቆፌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ቸርነት ዘነበ እንደገለጸው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሻለ ውጤት ለማለፍ አመቱን ሙሉ ከጓደኞቹ ጋር በቡድንና በተናጥል ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። በተለይ በትምህርት ቤቱ የሚሰጠውን ማጠናከሪያ ትምህርትና ተከታታይ ምዘና ከራሱ ጥረት ጋር ተዳምሮ ለፈተናው ዝግጁ እንዳደረገው አንስቷል።   በፈተናው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ዓመቱን ሙሉ በተለየ መልኩ ዝግጅት ስታደርግ መቆየቷን የገለጸችው ደግሞ የዲላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ዝናቧ ሚሊዮን ናት። በግል ጥረት ከማድረግ በተጓዳኝ በቡድን በማጥናትና ፈተናዎችን በመስራት እንዲሁም ማጠናከሪያ ትምህርት በመከታተል እራሷን ዝግጁ ማድረጓን ተናግራለች። የዲላ ዶንቦስኮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናርዶስ አዳነ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ደረጃ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስዳ ማጠናቀቋ ያለምንም ችግር ፈተናውን በበይነ መረብ ለመውሰድ ዝግጁ እንዳደረጋት ገልጻለች። በትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርት በመውሰድና ተከታታይ ምዘናዎችን በበይነ መረብ በመስራት ለፈተናው ዝግጁ መሆኗንም ገልጻለች። በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ በርትታ ስታጠና መቆየቷን ያነሳቸው ደግሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪ ፍርቱና የኔነህ ናት። በአሁኑ ወቅት የትምህርት ክፍለ ጊዜን በማጠናቀቅ ክለሳና የበይነ መረብ ፈተና ልምምድ እያረጉ መሆኑን አንስታ ይህም ለፈተናው በይበልጥ ዝግጁ እንዳደረጋት ተናግራለች።   የዲላ ከተማ ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ዮሴፍ ሆርዶፋ በበኩላቸው በከተማው ለ2 ሺህ 135 የ12 ክፍል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናውን በበይነ መረብ ለመስጠት የኮምፒዩተርና የኢንተርኔት ዝርጋታን ጨምሮ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። በትምህርት ዘመኑ የማለፍ ምጣኔን ለማሳደግ መምህራን፣ ተማሪዎችና የትምህርት አመራሩ በቅንጅት እየሰሩ መቆየቱን አንስተዋል። በተለይ የተማሪዎችን አቅም በማጠናከሪያ ትምህርትና ተከታታይ ምዘና ከማዳበር ባለፈ የበይነ መረብ ፈተና አሰጣጥ ጋር እንዲተዋወቁ በአራት ማዕከላት ተከታታይ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል። በዚህም በትምህርት ዘመኑ በሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ይመዘገባል ብለው እንደሚጠብቁ አመላክተዋል።
ኢኮኖሚ
በዞኑ በመኸር ወቅት ከ264 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ይለማል
Jun 12, 2026 98
አፍጥር፣ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ):-በጉራጌ ዞን በተያዘው የመኸር ወቅት ከ264 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች እንደሚለማ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የዞኑ የ2018/19 የምርት ዘመን የመኸር ወቅት የሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ''የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልፅግና'' በሚል መሪ ሃሳብ በቸሃ ወረዳ ተካሂዷል፡፡   የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው በዚህ ወቅት እንዳሉት በዞኑ በመኸር እርሻ ከ264 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይለማል። ለመኸር እርሻ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመው፣ 56 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በመጠባበቂያነት መያዙንም ተናግረዋል፡፡ በመኸር ወቅቱ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ቦለቄ፣ የቢራ ገብስ እና ሌሎች ሰብሎች እንደሚለሙ ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅትም የእርሻ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ አበራ ገለጻ በመኸሩ ከሚለማው አጠቃላይ መሬት ውስጥ 41ሺህ 800 ሄክታሩ በኩታ ገጠም የሚለማ ነው።   የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሱ ድንቁ በበኩላቸው እንዳሉት በዓመት ከሦስት ጊዜ በላይ ለማምረት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋቱ በግብርና ምርት ላይ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው። የምርት ማሳደጊያ ግብዓት በወቅቱ ከማሰራጨት ባለፈ የአርሶ አደሩን ፍላጎት እና አቅም በሚገባ በመለየት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በተፋሰስ የለሙ አካባቢዎች ጭምር በተለያዩ ሰብሎች እየለሙ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የጌታ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙዘፋ የሱፍ ናቸው። የወረዳው አርሶ አደሮች በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ገቢ የሚያስገኙ ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩ በመደረጉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወታቸውን እየቀየሩ መጥተዋል ብለዋል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በዞኑ በሌማት ትሩፋት በተከናወኑ የዶሮ እርባታ፣ የወተት እና የእንስሳት ልማት ስራዎች እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።   በሰብል ልማትም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ያሉት አስተዳዳሪው በተያዘው የመኸር እርሻ አንድም መሬት ጾም እንዳያድር ልማቱን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። በበልግ ወቅት በዝናብ ስርጭት መዘግየት ምክንያት የጠፋውን የበቆሎ ሰብልን ለማካካስ አስፈላጊው የግብርና ግብዓት በመጠቀምና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበር ይሰራል ሲሉም አክለዋል። በመድረኩ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያን የቡና ምርት ጥራትና ምርታማነት የሚያሻሽሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እየተደረጉ ነው
Jun 12, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የቡና ምርት ጥራትና ምርታማነት የሚያሻሽሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለቡና አምራች አርሶ አደሮች የሚውሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የግብርና ግብዓቶች አስረክቧል።   ለቡና አምራች አርሶ አደሮች የሚተላለፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የግብርና ግብዓቶችም የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ተረክበዋል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ በግብርና መስክ የተመዘገበው ስኬት ለቡና ምርት ጥራትና ምርታማነት ወሳኝ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። ባለስልጣኑ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን፣ የጥራት ቁጥጥር መሳሪያዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን ለክልል በማከፋፈል ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በቡና ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች በቴክኖሎጂ የተደገፉ ግብዓቶች በማቅረብ ጥራቱ የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱ በማስቻል የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ግብዓቶቹ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የቀረቡ ሲሆን ቡና አብቃይ በሆኑ ክልሎች የተመረጡ ወረዳዎች ለሞዴል አርሶ አደሮች ተደራሽ እንደሚሆኑ ገልፀዋል። ከዓመታት በፊት በሔክታር 6 ኩንታል ሲመረት የነበረ መሬት አሁን ላይ በሔክታር ከአስር ኩንታል በላይ ቡና ማምረት እየተቻለ መሆኑን አንስተዋል። በዛሬው እለትም 62 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የግብርና ግብዓቶች ለቡና አምራች አርሶ አደሮች መተላለፋቸውን አረጋግጠዋል። ግብዓቶቹ የቡና ምርታማነትንና ጥራትን በማሳደግ አርሶ አደሮችን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጋር እንደሚያላምዱ ጠቅሰዋል። ቴክኖሎጂዎቹም የቡና ምርታማነት ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ዓለም አፍ የገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንደሚያግዙ አስረድተዋል። የተሻለ ምርትና ምርታማነት በማረጋገጥ ምርቱ ጥራቱ ጠብቆ በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። በርክክቡ የተገኙት ኦሮሚያ ክልል ቡናና ሻይ ልማት ዳይሬክተር ታከለ ሃይለማርያም፤የክልሉ መንግስት የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የተሰጡት ግብዓቶችም የበዘርፉ የተሰማሩ እርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ በመሆናቸው አርሶ አደሩ በአግባቡ የሚጠቀምበት ይሆናል ብለዋል። የሲዳማ ክልልን ወክለው የመጡት ቡዙነህ ቡናዬ በበኩላቸው፤ ባለስልጣኑ ልዩ ልዩ ዘመናዊ የግብርና ግብአቶች ሲያቀርብ መቆየቱንና በዚህም የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 354
በኢዜአ አይን! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። ‎ የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለአርሶ አደሩ የብድር አገልግሎት በማቅረብ ተጠቃሚነቱን የማሳደግ ተግባር እየተከናወነ ነው
Jun 12, 2026 118
ሰቆጣ፤ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለአርሶ አደሩ የብድር አገልግሎት በማቅረብ ተጠቃሚ የሚሆንበት አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ። በመምሪያው የመሬት አስተዳደር ባለሙያ አቶ ቤተማርያም ሸጋው ለኢዜአ እንደገለፁት በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለ330 ሺህ አርሶ አደሮች የ2ኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቷል። ይህም አርሶ አደሩ ደብተሩን በማስያዣነት ተጠቅሞ ገንዘብ በመበደር ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም 624 አርሶ አደሮች በይዞታ ማረጋገጫ ደብተራቸው አማካኝነት የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ብድሩ መመቻቸቱም አርሶ አደሩ ከሰብል ልማቱ በተጨማሪ በእንስሳት ማድለብ፣ በወተት፣ በንብ ማነብና በሌሎች የገቢ ማስገኛ የልማት ስራዎች እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል። ይህም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር ተጨማሪ ሃብት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑንም አክለዋል። በጋዝጊብላ ወረዳ የ01 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዋጋው ካሴ እንደገለጹት ግማሽ ሄክታር የእርሻ ማሳቸውን በማስያዝ የ99 ሺህ ብር ብድር ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ለልማት እንዲተጉ እንደሚያደርጋቸው ጠቁመው በተበደሩት ገንዘብም በከብት ማድለብ ስራ መሰማራታቸውን ተናግረዋል። ሌላዋ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ራሄል ክንፈ በበኩላቸው ብድሩ መመቻቸቱ ከሰብል ልማት ባለፈ በከብት ማድለብና በሌሎች የስራ መስኮች ለመሰማራት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የዲጅታል ግብርና መስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Jun 12, 2026 150
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5 / 2018 (ኢዜአ)፦የዲጅታል ግብርና አሰራር በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑ ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ዲጅታል ግብርና ከልማዳዊ የእርሻ አሰራር ወደ እውቀትና ቴክኖሎጂ መር ኢንዱስትሪ በመቀየር፣ ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥና የግብርና ምርቶችን የውጭ ኤክስፖርት አቅም ማሳደግ የሚያስችል መፍትሄ ነው። በተጨማሪም ዲጅታል ግብርና ማለት ምርታማነትን ለመጨመርና ፈጣን ውሳኔዎችን ለማሳለፍ እንደ ኢንተርኔት፣ ድሮን እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በግብርናው ዘርፍ ውስጥ መጠቀም ነው። የግብርና ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዓመታዊ የዲጂታል ግብርና ኤክስቴንሽንና የምክር አገልግሎት ፎረም አካሂዷል።   የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ ፕሮፌሰር አሊ መሐመድ በዚሁ ጊዜ፤ የዘርፉ ክፍለ ኢኮኖሚ ለሥራ ዕድል፣ ለምግብ ሉዓላዊነትና እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት የላቀ ሚና ያለው የአገር ውስጥ የጀርባ አጥንት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዘርፉ ለዘመናት በዘመናዊ አሰራር ባለመደገፉ ምክንያት፣ አገሪቱ ካላት እምቅ ሀብት አንጻር የሚገባትን ጥቅም ሳታገኝ መቆየቷ ተናግረዋል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት መንግስት ዲጅታል የግብርና ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ጠቅሰው ስርዓቱ በተለይ በአርሶ አደሩና በባለሙያው መካከል የነበረውን የመረጃ ልውውጥ ክፍተት በመሙላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል፡፡ አርሶ አደሮች ሬዲዮና የእጅ ስልክን በመጠቀም ስለ አየር ንብረትና ግብዓቶች መረጃ በማግኘት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ምርታማነትን ማሳደግ መቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አርሶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግና ዘርፉን ለማላቅ የዲጅታል ግብርና ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡   በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን መሪ ስራ አስፈጻሚ የኔነሽ ኤጉ በበኩላቸው፤ ድጅታል ግብርና የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጅ አጠቃቀም ማሳደጉን ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ኋላ ቀር የግብርና አሰራር ስርዓት ወደ ዘመናዊ በማሸጋገር ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ማስቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡      
በክልሉ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎችን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል
Jun 12, 2026 119
ቡታጅራ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ችግር ፈቺ የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎችን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለጹ፡፡ "የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሳይንስ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ በቡታጅራ ከተማ 3ኛው ዙር ክልላዊ የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ ተከፍቷል።   የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎችን ለማሳደግ ትኩረት ተጥቷል፡፡ በክልሉ የሚካሄደው የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ አውደ ርዕይም በዘርፉ ተሰጥኦ ያላቸው የፈጠራ ባለቤቶችን በማበረታታት ከክልሉ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የመደመር መንግስት እሳቤ ለሳይንስ፣ ለቴክኖሎጂና ለፈጠራ ሥራዎች መስፋፋት መሰረት ጥሏል። በዚህም የዘርፉን አቅም ወደ ሀብት መቀየር የሚችሉ የፖሊሲና የህግ ማሻሻያዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ ሥራዎች ሁሉንም ዜጋ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የመሰረተ ልማት ዝርጋታ መከናወኑንም ጠቁመዋል።   ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ትግበራው ስኬታማነት ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ስርዓት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ናቸው። ለዚህም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ለሳይንስ፣ ለምርምር፣ ለእውቀት ሽግግር፣ ለቴክኖሎጂና ለኢንዱስትሪ ትስስር፣ ለኢንተፕራይዞች ልማት መስፋፋትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመዋል። የመማር ማስተማር ስራውን ከተለመደው አሰራር በማውጣት በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግም የዚሁ አስቻይ ሁኔታ አካል መሆኑንም ገልጸዋል። በአውደ ርዕዩ የአፈር ለምነትን በማሳደግ ምርትና ምርታማነት መጨመር የሚያስችል የተፈጥሮ ማዳበሪያ የምርምር ውጤት ይዘው መቅረባቸውን የተናገሩት ደግሞ መምህር ታምራት ተስፋዬ ናቸው። የአውደ ርዕዩ መዘጋጀት የምርምር ስራቸውን እንዲያስተዋውቁና ወደ ገበያ በማውጣት ለውጤታማነታቸው ተጨማሪ አቅም እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።   ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ክልል አቀፍ የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና የፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ የፈጠራ ሥራዎችን ከማስተዋወቅ ባለፈ ለተሻሉት እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ ታውቋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የፌዴራል፣ የክልሉና የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የፈጠራ ባለቤቶችና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።  
በስሉጥ ከተማ ስሉጥ አገልግሎት- አዲስ መሶብ
Jun 12, 2026 252
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5 / 2018 (ኢዜአ)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ከታየው አስደማሚ የከተሜነት ትራንስፎርሜሽን ጎን ለጎን የሕብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማዕከል ያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ሰው ተኮር ስራዎች ተሰርቷል፤ እየተሰሩም ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ የህዝቡ የዘመናት ጥያቄ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት ስር-ነቀል የሆነ ለውጥ ለማምጣትም መጠነ ሰፊ የሆነ የመሰረተ-ልማት እና የሰው ኃይል ልማት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ዕድገቷን እና ስሉጥ ከተማነቷን (Smart-city) የሚመጥን አገልግሎት ለማቅረብ ቴክኖሎጂን ተግባር ላይ የማዋል ሂደት አጠናክራ ይዛለች፡፡ ይኸውም የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ቀዳሚው ተጠቃሽ ነው፡፡   አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ በማድረግ የሕብረተሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ቀን ከሌሊት እየተሰራ ይገኛል፤ የላቀ ውጤትም ተመዝግቦበታል፡፡ እስካሁን በማዕከል እና በዘጠኝ ክፍለ-ከተሞች እንዲሁም በተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የተደራጀ፣ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግባቸው፣ የበቁ የሰው ኃይል የተሟላላቸው ማዕከሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በቴክኖሎጂ በታገዘ በተደረገ ዳሰሳ እንደሚያሳየው ተገልጋዩ ከ99 በመቶ በላይ እርካታ ያመላክታል፡፡ ቀሪ ሁለት ክፍለ ከተሞችም ግንባታቸው ተጠናቅቆ በጥቂት ቀናት አገልግሎት ይጀምራሉ፡፡   የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለትን ታሪክ ለማድረግ በቁርጠኝነት ተተግብሮ፣ የሕብተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ እንደሚሰራ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
በክልሉ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአገልግሎት አሰጣጥና በወጣቶች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ውጤት አምጥቷል
Jun 12, 2026 122
ሀዋሳ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ):-በሲዳማ ክልል የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአገልግሎት አሰጣጥና በወጣቶች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ውጤት ማምጣቱን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ በራሳ ለኢዜአ እንደተናገሩት የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ በክልሉ በመንግስታዊ አገልግሎትና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ውጤት አምጥቷል። በክልሉ ሰልጥነው ምስክር ወረቀት ካገኙት ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች፣ በተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ወጣቶች እንዲሁም ተማሪዎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል። በክልሉ ብዙ የመንግስት ሠራተኞች የዲጂታል ክህሎት ባለቤት መሆናቸው ውጤታማ መንግስታዊ አገልግሎት ለመስጠት ጉልህ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል። ሥልጠናውን የወሰዱ ወጣቶችም በአሁን ወቅት በዲጂታል ኢኮኖሚ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን በመጠቀም ገቢ የማግኘት ዕድላቸውን ማስፋታቸውንም አክለዋል።   በክልሉ ሥልጠናውን ወስደው ካጠናቀቁ ዜጎች መካከል በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ወይዘሮ ሙሉወርቅ መኳንት አንዷ ናቸው። በተለያዩ ኮርሶች የሚሰጡ የኮደርስ ስልጠናዎችን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት እንደወሰዱ ገልጸው በሥልጠናው የቴክኖሎጂ እውቀታቸው ያሳደጉና ለስራቸው አጋዥ የሆኑ ብዙ ክህሎቶችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል አሰራር በተለይ ለጤናው ዘርፍ አገልግሎት ቅልጥፍናና ተደራሽነት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረው፣ ስልጠናው በስራቸው አገልግሎቶችን በተሻለ መንገድ ለመስጠት አስችሎኛል ብለዋል።   ወጣት አብርሀም ጥላሁን በበኩሉ በሀዋሳ ከተማ በግል ድርጅት ውስጥ በመተግበሪያ አልሚነት ተቀጥሮ እየሰራ መሆኑን ገልጾ፣ የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ሁሉንም ኮርሶች መውሰዱን ተናግሯል፡፡ ድርጅቱ የተለያዩ መተግበሪያዎችን አልምቶ ለተጠቃሚዎች የማቅረብ እንዲሁም የኔትወርክ ዝርጋታ እና የኦንላይን ገበያ ላይ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል። በተቋሙ የሚለሙ መተግበሪያዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር አብረው እንዲሄዱ ለማድረግ ብሎም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታችን እንዲጨምር የኮደርስ ሥልጠና መውሰዴ ጠቅሞኛል ብሏል፡፡
ስፖርት
በዓለም ዋንጫው ሊታዩ የሚገባቸው 10 ተጫዋቾች
Jun 12, 2026 253
በሙሴ መለሰ በስተመጨረሻም ታላቁ የዓለም ዋንጫ ትናንት ተጀምሯል። በአሜሪካ ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት የተጀመረው የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ብሔራዊ ቡድኖችን በማሳተፍ 104 ጨዋታዎችን በ16 ስታዲየሞች ያካሂዳል። አዲሱ የውድድር ፎርማት አዳዲስ ኮከቦች ደምቀው እንዲወጡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል። መላው ዓለም ትኩረቱን ወደ ሰሜን አሜሪካ በሚያደርግበት በዚህ ወቅት፤ የእግር ኳስ ተንታኞች በልዩ ትኩረት ሊታዩ ይገባቸዋል ብለው የመረጧቸውን 10 ኮከብ ተጫዋቾች የተመለከቱ መረጃዎች ይዘን ቀርበናል። 1.ሊዮኔል ሜሲ (አርጀንቲና) ብዙዎች የወቅቱ ሻምፒዮን አርጀንቲና ጉዞዋ የሚወሰነው በሜሲ ብቃት ላይ ነው እያሉ ይገኛል። በ38 ዓመቱ ይህ ምናልባትም የመጨረሻው የዓለም ዋንጫው ሳይሆን አይቀርም። ሜሲ ጨዋታውን የሚያደርገውም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ሶከር ሊግ ኢንተር ማያሚን ወክሎ በፕሮፌሽናል ደረጃ በሚጫወትባት ሀገር ላይ ነው። አርጀንቲና አሁንም ዋንጫውን ለማንሳት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን፣ ሜሲ ለዚህ እንደ ትልቅ ምክንያት ይነሳል። የመጨረሻውን ስኬታማ ጉዞ የማድረግ ዕድሉ እና ምናልባትም ከረጅም ጊዜ ተቀናቃኙ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር በዓለም ዋንጫ መድረክ የመገናኘት አጋጣሚ፣ ይህንን ውድድር የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። 2.ክርስቲያኖ ሮናልዶ (ፖርቱጋል) ስለ ሮናልዶ ካነሳን አይቀር ልክ እንደ ሜሲ ሁሉ፣ ይህ በ41 ዓመቱ የሚጫወተው ስድስተኛው (ክብረ ወሰን የሆነ ተሳትፎ) እና ምናልባትም የመጨረሻው የዓለም ዋንጫው ይሆናል። በዚህ ዕድሜው በውድድሩ ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል የሚለው ጉዳይ ጥያቄ ቢያስነሳም፣ ፖርቱጋል እስካሁን የዓለም ዋንጫን አሸንፋ አታውቅም። ሮናልዶ በታሪክ የምንጊዜም ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ለመባል ይህንን ዋንጫ ማሸነፍ ይኖርበታል። ፖርቱጋል በውድድሩ ላይ እጅግ ጠንካራ እና ጥልቅ ስብስብ ያላት ቡድን ስትሆን፣ ዋንጫውን ካነሳች ሮናልዶ የሁሉ ነገር ማዕከል ይሆናል። 3. ላሚን ያማል (ስፔን) የዓለም ዋንጫው የትውልድ ቅብብሎሽ ወቅት ሊሆን ይችላል። ሜሲ እና ሮናልዶ ከመድረኩ ሲሰናበቱ፣ ተተኪነቱን ለመረከብ ዝግጁ የሆነው የ18 ዓመቱ ድንቅ ታዳጊ ብቅ ብሏል። ስፔን በውድድሩ ላይ ዋንጫውን ለማንሳት ቀዳሚ ግምት ባገኘችበት በዚህ ወቅት፣ ያማል በባርሴሎና ቤት 16 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማዘጋጀት የላሊጋው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ክብርን ተቀዳጅቷል። እንዲሁም የኮከብ ግብ አግቢነት (ጎልደን ቡት) ሽልማትን ለማግኘት ከሚጠበቁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ይህ ውድድር ያማል የዓለም እግር ኳስ ቁንጮ መሆኑን የሚያስመሰክርበት ትልቅ ዕድል ነው። 4. ኪሊያን ምባፔ (ፈረንሳይ) ከስፔን በመቀጠል ፈረንሳይ ውድድሩን የማሸነፍ ሰፊ ዕድል እንዳላት ይታመናል። ከአራት ዓመታት በፊት በአርጀንቲና በመለያ ምት ተሸንፋ ዋንጫውን ለማጣት ተገዳለች። ቢሆንም፣ ምባፔ ያንን ውድድር በስምንት ጎሎች እና በሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ ሽልማትን ወስዷል። አሁንም ያንን ክብር የመድገም ግምት ተሰጥቶታል ። በአሁኑ ወቅት የ27 ዓመቱ ወጣት ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት ከሪያል ማድሪድ ጋር 56 ጎሎችን አስቆጥሯል። ፈረንሳዮች የዓለም ዋንጫውን የሚያነሱ ከሆነ፣ ከድሉ ጀርባ የሚነሳው ምባፔ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። 5. ሃሪ ኬን (እንግሊዝ) ዋንጫው በመጨረሻ ወደ እንግሊዝ ይመለስ ይሆን? ሶስቱ አናብስቶች እ.አ.አ ከ1966 በኋላ የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ አልቻሉም፤ እንዲሁም እንደ ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ኮል ፓልመር፣ ፊል ፎደን እና ሃሪ ማጉዋየር ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾችን በዚህ ውድድር ላይ ሳይጠሩ ቀርተዋል። ነገር ግን ኬን አሁንም በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጥቂዎች አንዱ ሲሆን፣ እ.አ.አ በ2025/26 የውድድር ዓመት ለባየር ሙኒክ እና እንግሊዝ ባደረጋቸው 57 ጨዋታዎች ላይ 67 ጎሎችን አስቆጥሯል። እንግሊዝ የዓለም ዋንጫውን ለማንሳት እና ተፎካካሪ ለመሆን ከፈለገች ፣ የኬን ግቦች እጅጉን ያስፈልጓታል። 6. አርሊንግ ሃላንድ (ኖርዌይ) ኖርዌይ ማንም ዋንጫውን ታነሳለች ብሎ የማይጠብቃት፣ ነገር ግን ሳይጠበቁ አስገራሚ ነገር ሊሰሩ ይችላሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በምድብ ዘጠኝ ከፈረንሳይ፣ ሴኔጋል እና ኢራቅ ጋር ተደልድላለች። ኖርዌያውያን ያለ ጫና ሩቅ ርቀት መጓዝ የሚችሉ ሲሆን፣ ለዚህም የአንበሳውን ድርሻ ከሚወስዱ ተጫዋቾች መካከል የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተሰላፊ አርሊንግ ሃላንድ ይሆናል። ሃላንድ ለኮከብ ግብ አግቢነት ከሚጠበቁት ግንባር ቀደም ተጫዋቾች አንዱ የሆነበት የራሱ ምክንያት አለው። ለኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን በ50 ጨዋታዎች 55 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ዕድሜው ገና 25 ዓመት ብቻ ነው። 7. ቪኒሺየስ ጁኒየር (ብራዚል) ብራዚል ከማንኛውም ሀገር በላይ ብዙ ጊዜ (አምስት) የዓለም ዋንጫዎችን ያነሳች ሲሆን፣ ወደ እያንዳንዱ ውድድር የሚገቡትም ለማሸነፍ በማሰብ ነው። እንደ ኔይማር፣ ካሴሚሮ፣ ማርኪኒዮስስ እና ፋቢንሆ ያሉት አንጋፋ የብራዚል ከዋክብት የዕድሜ መግፋት፣ ወጣቱ ቪኒሺየስ ጁኒየር ወደ ፊት መጥቶ የሴሌሳኦ ወሳኝ ተጫዋች የመሆን ዕድል ይሰጠዋል። ቪኒ በዘንድሮው የውድድር ሪያል ማድሪድ 16 ጎሎችን አስቆጥሮ 5 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል፤ በ25 ዓመቱ የቀጣዩ ወርቃማ ትውልድ የእግር ኳስ ከዋክብት ተምሳሌት ሆኗል። ይህ ውድድር ቪኒሺየስ ከታላላቆቹ ተርታ ለመቀመጥ የሚመጥን የዓለም ቁንጮ ተጫዋች መሆኑን የሚያረጋግጥበት ትልቅ ዕድል ነው። 8. ኡስማን ዴምቤሌ (ፈረንሳይ) ዴምቤሌ እ.አ.አ በ2024/25 የውድድር ዓመት ከፒኤስጂ ባደረገው አስደናቂ ጉዞ በ49 ጨዋታዎች 33 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን 15 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም የባሎን ዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። ከበድኑ ጋር ለተከታታይ ዓመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አንስቷል። ትኩረቱ ሁሉ በምባፔ ላይ መሆኑ ባይካድም፣ የፈረንሳይ አደገኛነት ይበልጥ የሚያጎላው ሌላኛው አቅም የዴምቤሌ ፈጠራ እና ሁለገብነት ነው።በተሰጥኦ ረገድ በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ ተጫዋቾች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። 9. ያም ዲዮማንዴ (ኮትዲቯር) የዓለም ዋንጫ አንዱ መገለጫ ሁሌም አዳዲስ ኮከቦችን ይዞ ብቅ ማለቱ ነው። ዲዮማንዴ ደግሞ በዚኛው ዓለም ዋንጫ ትኩረት ከሳቡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ኮትዲቯር ከዋንጫ ተፎካካሪዎቹ መካከል ባትመደብም፣ ጀርመን፣ ኢኳዶር እና ኩራሳዎ በሚገኙበት ምድብ አምስት ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድል አላት። ዲዮማንዴ ገና የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ ባለፈው የውድድር ዓመት በጀርመኑ ቡንደስሊጋ አርቢ ላይፕዚግ በ28 ጨዋታዎች 12 ጎሎችን በማስቆጠር እና 8 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ደምቋል። ደጋፊዎች ስሙን ገና ላያውቁት ይችላሉ፣ ነገር ግን ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሁሉም ብቃቱን ሲመለከቱ ስለ እሱ ማውራታቸው የማይቀር ነው። 10. ቪቲንሃ (ፖርቱጋል) በፓርቹጋል የመሐል ሜዳ ክፍል ውስጥ ኳስን በመረዳት እና በመፍጠር አቅሙ ከሚነሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ቪቲንሃ ነው። በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የጨዋታ አቀጣጣዮች አንዱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ባለፈው ዓመት በባሎን ዶር ድምፅ አሰጣጥ ከዴምቤሌ እና ያማል በመቀጠል ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በቅርቡም ፒኤስጂ አርሰናልን አሸንፎ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ባነሳበት የፍጻሜ ጨዋታ የኮከብ ተጫዋች (Player of the Match) ክብርን አግኝቷል። ሮናልዶ የጋዜጣዎችን አርዕስተ ዜና ሊቆጣጠር ይችላል፣ ነገር ግን ፖርቱጋል በውድድሩ ላይ ምን ያህል ርቀት መጓዝ እንደምትችል የሚወስነው የቪቲንሃ የጨዋታ ፍሰት ነው።
የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች፦ ካናዳ ከቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና፣ አሜሪካ ከፓራጓይ
Jun 12, 2026 282
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5 /2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በሁለተኛ ቀን መርሃ ግብሩ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በምድብ ሁለት ካናዳ ከቦሲኒያ እና ሄርዞጎቪና ምሽት አራት ሰዓት ላይ በቶሮንቶ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ቡድኖች እርስ በእርስ ሲገናኙ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከጣምራ አዘጋጆቹ አንዷ የሆነችው ካናዳ በዓለም ዋንጫው ስትሳተፍ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የሰሜን አሜሪካዋ ሀገር እ.አ.አ በሜክሲኮ በተካሄደው 13ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እና ከአራት ዓመታት በፊት በኳታር በተደረገው 22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ካናዳ በውድድሩ ላይ እስከ አሁን ባደረጋቻቸው ስድስት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዳለች። ቦሲኒያ እና ሄርዞጎቪና እ.አ.አ በ1992 ነጻነቷን ካወጀች በኋላ በዓለም ዋንጫ ስትሳተፍ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የደቡብ ምስራቅ አውሮፓዋ ሀገር በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ጣልያንን በመለያ ምት በማሸነፍ ለውድድሩ ማለፏ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2014 በብራዚል በተካሄደው 20ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ነው። ቦሲኒያ በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ሶስት ጨዋታዎችን አድርጋ አንድ ጊዜ ስታሸንፍ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዳለች። ብቸኛ ድሏ የተመዘገበው ኢራንን 3 ለ 1 በማሸነፍ ነው። የዛሬው ጨዋታ ካናዳ በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ ፤ ተጋጣሚዋ ቦሲኒያ ሁለተኛ ድሏን ለማሳካት የሚያደርጉት ነው። ሁለቱ ሀገራት በዓለም ዋንጫው የሚኖራቸው ጉዞ የሰመረ እንዲሆን ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። በምድብ አራት አሜሪካ ከፓራጓይ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በሎስ አንጀለስ ስታዲየም ይጫወታሉ። ከዓለም ዋንጫው አዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ በውድድሩ ላይ ስትሳተፍ የአሁኑ ለ12ኛ ጊዜ ነው። አሜሪካ እ.አ.አ በ1930 በኡራጓይ በተካሄደው የመጀመሪያው ዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችበት አጋጣሚ ትልቁ ውጤቷ ነው። በውድድሩ ላይ ዘጠነኛ ተሳትፎዋን የምታደርገው ፓራጓይ እ.አ.አ በ2010 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 19ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ የደረሰችበት ውጤት የተሻለ ርቀት የሄደችበት ተሳትፎዋ ነው። ሁለቱ ሀገራት በዓለም ዋንጫው ሲገናኙ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ኡራጓይ እ.አ.አ በ1930 ባዘጋጀችው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ላይ ተገናኝተው አሜሪካ 3 ለ 0 አሸንፏል። አሜሪካ እና ፓራጓይ ከ96 ዓመታት በኋላ በድጋሚ በዓለም ዋንጫው ይገናኛሉ።
ሶስት ቀይ ካርዶች በታዩበት የዓለም ዋንጫው የመክፈቻ ጨዋታ  ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን አሸነፈች
Jun 12, 2026 218
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 ረታለች። ትናንት ማምሻውን በአዜቴካ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ አንድ ጨዋታ ጁሊያን ኪንዮኔስ በዘጠነኛው ደቂቃ ሜክሲኮን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል። የ29 ዓመቱ አጥቂ ኪንዮኔስ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ራውል ሂሜኔዝ በ67ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል። የደቡብ አፍሪካው ስፔፌሎ ሲቶሌ በ49ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። የውድድሩ የመጀመሪያ ቀይ ካርድ ሆኖ ተመዝግቧል። በ84ኛው ደቂቃ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካው ቴምባ ዝዋኔ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። በዚህም ደቡብ አፍሪካ ጨዋታውን በዘጠኝ ተጫዋች ለመጨረስ ተገዳለች። የሜክሲኮው ሴዛር ሞንቴስ በ92ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በመክፈቻው ጨዋታ ሶሶት ቀይ ካርዶች መመዘዛቸው አስገራሚ ሆኗል። በጨዋታው ሜክሲኮ ብልጫ የወሰደች ሲሆን ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር የምትችልባቸውን እድሎች አልተጠቀመችበትም። በጥልቀት የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት የጨዋታ ስልት ይዛ የገባችው ደቡብ አፍሪካ የግብ እድሎችን መፍጠር አልቻለችም። ከዓለም ዋንጫው አዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሜክሲኮ ውድድሩን በድል ጀምራለች። ደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ሽንፈት አስተናግዳለች። ከሜክሲኮ እና ደቡብ አፍሪካ ጨዋታ በፊት በአዜቴክ ስታዲየም ደማቅ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሄዷል። በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት መካሄድ የጀመረው 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አካባቢ ጥበቃ
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች  ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
Jun 12, 2026 169
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ፣ እንዲሁም በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት አስታወቀ። ኢንስቲትዮቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይ በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል። በዚህም ምክንያት እርጥበታማ የአየር ሁኔታው በመጠንም ሆነ በስርጭት ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተስፋፋ ይሄዳል ብሏል። በዚህም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች የሚያመልክቱ ሲሆን በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። በሚቀጥሉት ቀናት ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎችና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ጠቁሟል። የሚኖረው እርጥበት ለመኸር እርሻ፣ የበልግ ሰብል አብቃይ ለሆኑ አካባቢዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብሏል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጽ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ብሏል። በዚህም አብዛኛው አባይ፣ ላይኛው እና መካከለኛ ባሮ አኮቦ፣ ኦሞ ጊቤ፣ ላይኛው ስምጥ ሸለቆ፣ በጥቂት የገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል ብሏል። አብዛኛው ተከዜ፣ በጥቂት የላይኛው እና ታችኛው አባይ፣ ላይኛውና መካከለኛው አዋሽ፣ ኦሞ ጊቤ፣ ባሮ አኮቦ፣ ገናሌ ዳዋ፣ ዋቤሸበሌ እና የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸውም ገልጿል።  
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል-የኢሉአባቦር ዞን አርሶ አደሮች
Jun 12, 2026 246
መቱ ፤ ሰኔ 5 /2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ መራቆትን ከመከላከል ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን በኢሉአባቦር ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ። የኢሉአባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቋል። የዞኑ አርሶ አደሮች እንዳሉት ባለፉት ዓመታት የተካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ ልማቶች የአካባቢያቸውን ልምላሜ ከማሳደግ ባሻገር የኢኮኖሚ ምንጭም እየሆናቸው ነው። በዞኑ የሁሩሙ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር በላቸው ዓለማየሁ፣ በአረንጓዴ አሻራ ጥምር ጠቀሜታ ላላቸው ችግኞች የተሰጠው ትኩረት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዳሳደገው ተናግረዋል።   ባለፉት ዓመታት በግል ይዞታቸው ላይ የተከሏቸው የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች አሁን ላይ በሚገባ አፍርተው ለምግብነት ከማዋል ባለፈ ቋሚ የገቢ ምንጭ እንደሆናቸው አስረድተዋል። አቶ ተካልኝ ታደገ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪ በበኩላቸው፤ በልቅ ግጦሽና በጎርፍ ምክንያት ተጎድቶ የነበረው ይዞታቸው በአረንጓዴ አሻራ አገግሞና ለምነቱ ተመልሶ ለግብርና ልማት በማዋል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።   በግል ይዞታቸው ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በማልማት ከምርት ሽያጭ በዓመት እስከ 300 ሺህ ብር ገቢ በማግኘት ኑሯቸውን ማሻሻል እንደቻሉ አመልክተዋል። አቶ አይናለም ኪዳኑና አቶ ኢሳያስ አሰፋ የተባሉ የዞኑ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙና ልምላሜ እንዲላበሱ ከማድረግ በዘለለ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ምንጭ እየሆናቸው ይገኛል።   ተግባሩን ለማጠናከርም አሁን ላይ የችግኝ ጉድጓዶችን እያዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸውን ዕፅዋት ለመትከል ማቀዳቸውን አክለዋል። የኢሉአባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ለግብርና ሥራ ምቹ የአየር ሁኔታ ፈጥሯል። ለዜጎችም የምግብ ዋስትናና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።   ይህንን ለማስቀጠል እንዲቻልም ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ መትከያ ጉድጓድና የችግኝ ማጓጓዝ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነው ያስታወቁት። በዞኑ ከ254 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ያነሱት ኃላፊው በዚህም 54 ሺህ ሄክታር መሬት ይለማል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
ኮሌጁ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው የተሻሻሉ ችግኞችን በማዘጋጀት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው
Jun 11, 2026 552
ሚዛን አማን፣ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፡-የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚሆኑና የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው የተሻሻሉ ችግኞችን በማዘጋጀት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። ኮሌጁ የማኅበረሰብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን ለማስፋፋት በጥናትና ምርምር የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል።   የኮሌጁ ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን አለማየሁ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኮሌጁ በአረንጓዴ ልማት ሥራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ችግኞችን በማዘጋጀት ለማኅበረሰቡ እያሰራጨ ነው። በተለይ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ውጤታማነት ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዘንድሮ ተከላ ከ250 ሺህ በላይ በምርምር የተደገፉና የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን አዘጋጅቷል ብለዋል። ከተዘጋጁት ችግኞች መካከል ከዛፍ ጋር ትስስር ያላቸው ቁንዶ በርበሬ እና ቡናን ጨምሮ የሻይ ቅመም፣ የፍራፍሬ፣ የውበትና የጥላ ዛፎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። የችግኝ ዝርያዎቹ ፈጥነው እንዲደርሱ፣ በሽታ እንዲቋቋሙና ምርታማነታቸው የተሻለ እንዲሆን ኮሌጁ ከተለያዩ የግብርና ምርምር ማዕከላት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱንም አቶ ጥላሁን አክለዋል። የተዘጋጀውን ችግኝ ለማህበረሰቡ ከማሰራጨት ባሻገር ኮሌጁ በራሱ እንደሚተክል ገልጸው በዚህም የውስጥ ገቢውን ከማሳደግ ባለፈ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር በምግብ ራስን ለመቻልና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመልክተዋል።   በኮሌጁ ችግኝ ጣቢያ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው እየሰሩ ካሉ ወጣቶች መካከል መሠረት ታፈሰ በችግኝ ጣቢያው በዘርፉ ባለሙያዎች ታግዛ በመሥራት የቀሰመችው ሙያ በራሷ ችግኝ የማዘጋጀት አቅምን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላት ገልጻለች። የተዘጋጁ ችግኞችን የመከታተልና የመንከባከብ ሥራ በመሥራት ቤተሰባቸውን እያስተዳደሩ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ እልፍነሽ ተገኝ እና ታጋይነሽ ዘውዴ ናቸው።   የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ከተጀመረ ወዲህ ኮሌጁ ችግኞችን በብዛት እያዘጋጀ በመሆኑ ዓመቱን ሙሉ የሥራ ዕድል በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸወን ተናግረዋል።    
በክልሉ ከብክለት የፀዳ ከባቢን በመፍጠር ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት እየተደረገ ያለው ጥረት ይጠናከራል
Jun 10, 2026 747
ሆሳዕና ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከብክለት የፀዳ ከባቢን በመፍጠር ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ገለፀ። ቢሮው "ብክለትን እንቀንስ፣ እንከላከል" በሚል መሪ ሐሳብ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በህግ ተከባሪነት ዙሪያ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል።   የቢሮው ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ ከብክለት የፀዳ ከባቢን በመፍጠር ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት እየተደረገ ያለው ጥረት ይጠናከራል። ለዚህም ከኢንዱስትሪዎች የሚወገዱ ቆሻሻዎችን በአግባቡ የማስወገድ ስራ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ጠቁመው ይህንንም ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመንገባት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርና የፅዱ ኢትዮጵያ ኢንሼቲቮች ትግበራ መከናወኑን ጠቅሰዋል። በተለይም ከብክለት የጸዳ አካባቢን ለመፍጠር በተደረጉ ጥረቶች እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን ለማስፋት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።   ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል በሆሳዕና ከተማ የምስጋና ዱቄት ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ደመቀ በበኩላቸው ፋብሪካው ተረፈ ምርቶችን በአግባቡ በማስወገድ አካባቢውን ከብክለት ለመጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለስኬቱም የተረፈ ምርት ማስወገጃን የማዘጋጀትና ምድረ ግቢውን በአረንጓዴ ልማት የመሸፈን ተግባር መከናወኑን አስረድተዋል። ፋብሪካው በጤና ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ከብክለት የፀዳ አካባቢን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በወራቤ ከተማ የአበሩስ ዱቄት ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ ነስሬ ናቸው።   ፋብሪካው ለፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ሴፍቲ ታንክን በመጠቀም ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመዋል። በቀጣይም ፋብሪካው ንፅህናው የተጠበቀ ምርትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 7021
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 6132
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 4958
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 4863
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው።   የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 354
በኢዜአ አይን! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። ‎ የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም --
Jun 5, 2026 7017
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 24, 2026 5577
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የመደመር ማሳያ ከሳምንቱ አበይት ክስተቶች መካከል የኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች በአሶሳ ከተማ ያስገነቡት የጋራ ሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የህንፃ ምረቃ ይጠቀሳል። በክልሎቹ ትብብር የተከናወነው የህንፃ ግንባታ በመደመር እሳቤ የዜጎችን የጋራ ሰላም ለማስጠበቅና የልማት ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ ጥረት ማሳያ ነው።   መርሃ ግብሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) የተገኙበት ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም ላይ ያተኮረው መድረክ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የተካሄደውና በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረው ፎረምም በእዚህ ሳምንት ዐበይት ጉዳይ ነበር። ፎረሙ የተካሄደው “ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን የተዘጋጀውም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በሰላም እና ፖለቲካዊ ምክክር ማዕከል (CRPP)፣ በሶማሌ ክልል መንግስት እና በሌሎች አጋር አካላት ነው።   በፎረሙ መክፈቻ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፤ መድረኩ የውጭ ተዋናዮች ሳይገቡበት የቀጣናው አካላት በራሳቸው ጉዳይ፣ ፖሊሲና እርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ብቻ የሚመክሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል። እርስ በእርስ ለመተዋወቅ፣ ግልጽነትን ለመፍጠርና ጠንካራ ትስስርን ለመገንባት የሚያስችል በመሆኑም በቀጣናው ግጭቶች ለመቀነስ በእጅጉ እንደሚረዳ ነው ያነሱት። ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ምሁራን ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቀጣናው ፈተናዎች ተጨባጭ መፍትሄና አቅጣጫ እንዲያስቀምጡም ያግዛል ብለዋል። የጉባ ላይ ብስራቶች ተግባራዊ ልማት የሳምንቱ የበረራ ቅኝታችን የሚጀምረው ወደ ሶማሌ ክልል ጎዴ ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በስፍራው እየተገነባ ያለውን የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።   ከጉብኝታቸው በኋላም በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን ለማሳካት የመሬት፣ ውሃ እና የሚያለማ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ በቂ ሃብት ያላት መሆኑን ገልጸዋል። በምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እነዚህን ካሟላን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ ነገር ማድረግ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ የኒውክለር ሃይል ማመንጫ፣ የቢሾፍቱ አየር መንገድ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የቤቶች ልማት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጓቸው የጉባ ብስራቶች መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞጆ ከተማ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው ስራ ያስጀምሩትም በዚሁ ሳምንት ነበር።‎ ‎በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ፣ መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክና የፎርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ነው። የፋብሪካው መገንባት የውጭ ምርት ጥገኝነት ከመቀነስ ባለፈ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት መሆኑ ታውቋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ ጉብኝት በዚሁ ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ወደ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጓዝ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። በድሬዳዋ ቆይታቸው ብርቱካንና ሌሎች የፍራፍሬ ልማት ሥራዎች እንዲሁም የእንስሳት ሀብት ልማት ስራን ተመልክተዋል።   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና የግብርና ልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላ ባስተላለፉት መልእክትም የጋራ ሙለታ ተፈጥሯዊ የልማት ፀጋና ከፍታም ታሪክን፣ ውብ መልክዓ ተፈጥሮን የታደለ፣ የኢትዮጵያን ሜዳና ተራሮች ምርት የሚታፈስባቸው የማድረግ ሀገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።   የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ማሳያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ ተገኝተው 142 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርቀው ሥራ ያስጀመሩትም በዚህ ሳምንት ነበር። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር በለውጡ ዓመታት ከልማት የራቁ አካባቢዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ መሰራቱን አንስተዋል። የኮንታ ኮይሻ ወረዳ የንጽህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶች ለዚሁ ማሳያ ናቸው ብለዋል።   በተመሳሳይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የንጹህ መጠጥ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች መርቀው ለአገልግሎት አብቅተዋል።   የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በተለይ አርብቶ አደሮች ውሃ ለማግኘት ሩቅ አካባቢዎች ሲሄዱ ይደርስባቸው የነበረን እንግልት የሚያስቀር ነው። የመስኖ ፕሮጀክቱም የክልሉ አርብቶና አርሶ አደሮች በአካባቢው ያለውን ሰፊ መሬት በማልማት ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በፕሮጀክቶቹ ምረቃ ላይ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።   በሲዳማ ክልልም በፌደራል መንግስት ድጋፍ በ460 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳዬ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታም ተመርቋል። ፕሮጀክቱ 75 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ነው።   በሌላ በኩል የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ከ543 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 52 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መመረቃቸው ሌላው የሳምንቱ ክስተት ነበር። በዞኑ ለምረቃ ከበቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የውሃና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ቃሉ ወረዳ በ365 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የዲርማ ወንዝ መስኖ ፕሮጀክትንም መርቀዋል።   ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚደረግበት የሃዋሳ ከተማ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም በዚህ ሳምንት ተካሂዳል። ለፕሮጀክቱ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ናቸው፡፡   የፕሮጀክቱ ግንበታ ሲጠናቀቀ ሀዋሳ ከተማዋን ጽዱ በማድረግ የቱሪዝምና የኢንቨስመንት ማዕከልነቷን ያሳድገዋል ተብሏል። አቶ ደስታ የፕሮጀክቱ ግንባታ መንግስት ለከተሞች እድገት የሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ሲሉም ነው የጠቀሱት። የከሰም መስኖ ግድብ የከሰም መስኖ ግድብ የጥገና ማሻሻያ ፕሮጀክትም በዚሁ ሳምንት ተመርቆ ሥራ ጀመሯል። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ነው። የማሻሻያ ግንባታ መጠናቀቅ ከሚሰጠው ዘላቂ የልማት አገልግሎት ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ለዓመታት ሲፈታተን የነበረውን የጎርፍ ስጋት ያስቀራል ተብሏል።   በዚህ ወቅት ሚኒስትር አብርሃም (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የከሰም መስኖ ግድብ ቀደም ሲል በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ ትልቅ ስጋት ይታይ ነበር። የጥገና ማሻሻያው በአካባቢው ማህበረሰብ የነበረውን ይህን የአደጋ ስጋት በማስቀረት ግድቡን ለታለመለት የመስኖ ልማት ለማዋል የሚያስችል ነው። ለፕሮጀክቱም 2 ቢሊዮን ብር በጀት መውጣቱን ሚኒስትሩ አንስተዋል።   የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡን ከስጋት ያዳነ እና በርካታ ጥቅሞች ያሉት ነው ብለዋል። የግድቡ ጥገና መጠናቀቅ የሀዝቡን የቆየ ጥያቄ የፈታ መሆኑንም አንስተዋል። የግንቦት - ታላቁ ሁነት ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ድምጻቸውን ለመስጠት የተመዘገቡበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተውታል። የፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ሂደቱን ስኬታማ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አጠቃላይ ዜጎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።   በዚሁ ሳምንት "ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚ ና" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአዳማ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የዜጎች ጠንካራ ተሳትፎና የዳበረ የዴሞክራሲ ልምምድ የታየበት መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅም መገናኛ ብዙሃን የላቀ ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። ከተረጅነት የመውጣት ሀገራዊ ጥረት በድሬዳዋ "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የውይይት መድረክም ሌላው የእዚህ ሳምንት ዓቢይ ጉዳይ ነው። መድረኩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የግብርና ሚኒስቴር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። በመድረኩም በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተነስቷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቂና የተሟላ የውሃ ሀብት፣ የተማረና አምራች የሆነ ወጣት የሰው ኃይል እንዲሁም ለም የመሬት ፀጋዎች ያሉባት ሀገር በመሆኗ በማልማት እድገትና ማንሳራራትን ማስቀጠል ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል።   ለእዚህም ዋናው መሠረታዊ ጉዳይም ያሉ አቅሞችን በመለየትና ህዝብን ወደ ላቀ ምርታማነት ደረጃ በማሸጋገር በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጡን ሥራ በላቀ ደረጃ ማስቀጠል መቻል መሆኑን አንስተዋል። ለሰላም ጥሪ የተሰጠ ምላሽ የሠላም ጥሪን የተቀበሉ የአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የመረከብ፣ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማድረግና የመልሶ ማቋቋም (ዲዲአር) መርሀግብርም በዚህ ሳምንት ተከናውኗል። በብሔራዊ ተሀድሶ ማዕከል ጠዳ ጊዜያዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትሩ መሀመድ እድሪስ የቀድሞ ታጣቂዎች ከስልጠና በኋላ ከምንም በላይ የሰላም ዘብ ሆነው የበደሉትን ህዝብ ለመካስ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።   ታጣቂዎቹ ሠላምን አማራጭ በማድረግና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለሠላም ያደረጉት አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ መንግስት ለሠላም ባለው ጽኑ አቋምና ፍላጎት የሠላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና እንዲያልፉ በማድረግ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ እያደረገ ነው ብለዋል።   በተመሳሳይ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በኮምቦልቻ የስልጠና ማዕከል ስልጠና የጀመሩ መሆኑ ይታወቃል። ሐረር- ፕሮጀክቶች ምረቃ የሐረሪ ክለል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝትም ሌላው የእዚህ ሳምንት ኩነት ነበር። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት በተሻለ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ።   በተለይም የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት የክልሉን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የበለጠ በማሳደግ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት። በዘመናዊ ትምህርት የታነፀና በእውቀት የበለፀገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም አንስተዋል። ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ለማስቻል በአስተዳደሩ በኩል ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት 672 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በይፋ የተመረቀውም በዚህ ሳምንት ነው። በምረቃው ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን፣ የክልሉ የመንገዶች ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢድሪስ ሙሴ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።   የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እንደገለጹት ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት የከተማውን የንግድ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚያስችል ነው። የከተማውን ገፅታ በመለወጥ ረገድም የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ያነሱት። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው የመንገድ ፕሮጀክቱ የጂግጂጋ ከተማን ልማትና ዕድገት በማፋጠን በኩል ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የመንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን አስተዳደሩ ሀገራዊ የመንገድ መሰረተ ልማት ዕቅድን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ የመንገድ ፕሮጀክትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።   የመንገድ ፕሮጀክቱ 7 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 30 ሜትር ስፋት እንዳለውም ታውቋል።  
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 5163
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
ትንታኔዎች
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 354
በኢዜአ አይን! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። ‎ የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድናቸው?
Jun 12, 2026 256
የጤና ነገር … በዮሐንስ ደርበው የሰው ልጅ ሊሻሻሉ በሚችሉ እና በማይችሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለልብ ህመም ሊጋለጥ እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የአዋቂ የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሃኑ ሞገስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የልብ ህመም ከተወሳሰብ ዘላቂ የጤና እክል እስከ ድንገተኛ ኅልፈት ያደርሳል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ሰዎች ማሻሻል በሚችሏቸው (ሞዲፋይብል) እና ማሻሻል በማይችሏቸው (ነን ሞዲፋይብል ወይም ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች) ለልብ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዶክተር ብርሃኑ ይገልጻሉ። መሻሻል ከሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም (በአግባቡ መድኃኒቱ ካልተወሰደ)፣ተገቢ ያልሆነ የስብ ክምችት፣ ከፍተኛ ውፍረት (ክብደት)፣ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብ አለመኖር እንዲሁም አብዝቶ ስኳር፣ ጣፋጭና አልኮል መጠቀም የሚሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ እንዲሁም ሰዎች ማሻሻል ከማይችሏቸው (ተፈጥሯዊ) አጋላጮች መካከል፤ በቤተሰብ የሚተላለፍ መኖሩን፣ በዕድሜ መጨመር የሚከሰት መሆኑን (ለምሳሌ፡- ወንድ ከ45 ሴት ከ55 ዓመት በላይ ሲሆናቸው ለልብ ህመም ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን) እንዲሁም ወንዶ ከሴቶች በይበልጥ ለልብ ህመም ተጋላጭ የመሆናቸው አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ የልብ ህመም ምልክቶች የደረት ውጋት በግራ በኩል ወይም መሐል ላይ፣ ከወትሮው የተለየ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት መኖር፣ የሰውነት በተለይም እግር አካባቢ እብጠት፣ ራስን መሳት እና ሳል የልብና ተያያዥ ህመም ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ አብራርተዋል። የልብን ጤናን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ጤናማ አመጋገብን መከተል እንደሚገባ የሚመክሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ አትክልት ማዘውተር፣ ምግብ ሲዘጋጅም ፈሳሽ ዘይት መጠቀም፣ ስኳር፣ ጨው እና ጣፋጭ ነገሮችን መገደብ ከተቻለም ማስወገድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህም ብስክሌት መንዳት፣ በእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ዋና መዋኘት፣ እስከሚያልብ እና የልብ ምት እስከሚጨምር ብሎም እስከሚደክሙ የአካል ብቃት መሥራት የልብን ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽዖ አለው ነው ያሉት፡፡ ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ “ቦዲ ማስ ኢንዴክስ (ቢ ኤም አይ)” ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 እንዲሆን ይመከራል ብለዋል፡፡ ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠቀም፣ የስኳር ህመምና ከፍተኛ ደም ግፊት ካለም የመድኃኒት አወሳሰድን አለማስተጓጎል፣ አመጋገብ ላይ ስብ አለማብዛትና አብዝቶ አለመቀመጥ የልብ ህመምን ለመከላከል እንደሚያግዙ ነው ያስረዱት፡፡ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች የሆኑ ጤናማ ሰዎች ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ባሉ ጊዜያት አንድ ጊዜ፣ ዕድሜያቸው ከ45 በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም የልብ ህመም ያለባቸው እንደሁኔታው በየጊዜው ክትትል እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከልብ ህመም እንዲጠብቁ መክረው፤ ከዚህ ያለፈ ችግር ሲኖር ቶሎ የሕክምና ክትትል ማድረግ እና “ዛሬ ነገ” በማለት ጊዜ እያባከኑ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማይገባቸው አሳስበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ጤና #የልብ_ህመም
ባሳለፍነው ሳምንት …
Jun 7, 2026 2634
ባሳለፍነው ሳምንት … ከግንቦት 23 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ባሳለፍነው ሳምንት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለመራጮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምርጫው ወቅት ድምጽ ስለሰጡ መራጮች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል ብለዋል። ማገልገል መታደል መሆኑን ገልጸው፤ ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይህንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ ሲሉም አስገንዝበዋል። ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። ‎ ‎በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፕሮጀክቱ ‎በአጠቃላይ 22 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን ይሸፍናል። ይህ ፕሮጀክት የማይቆራረጥ የልማት ሥራችን ኅያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሀገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት ከያዘው የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል። ‎ ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፤ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን ሲሉም አመላክተዋል። የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳን የያዘ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ‎ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ እንዲሁም ከእንጦጦ እስከ ቀበና ባለው መስመር የሚከናወነው መጠነ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽንም፤ ከወንዞቹ ባሻገር እስከ 50 ሜትር የሚዘልቅ መሆኑን አስረድተዋል። የአረንጓዴ ኮሪደሮችን፣ የሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን እና የንግድ ቦታዎችን ልማት ማካተቱን ጠቅሰው፤ ከተማዋን በእጅጉ የቀየረ ነው ብለዋል። ‎ የወንዝ ዳርቻዎችን ገጽታ እና አገልግሎት ከማሻሻል ባለፈ በኮንስትራክሽን፣ በኢንጂነሪንግ፣ በመልክዓ-ምድር ውበት ግንባታ፣ በሎጂስቲክስ እና በተያያዙ ዘርፎች ለብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም አብራርተዋል። አብዛኛው ሥራ በሀገር ውስጥ መሐንዲሶች መቀረጹና መተግበሩ፤ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በከተማ ልማት እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላቸው ዐቅም እያደገ መምጣቱን ያሳያል ነው ያሉት። ‎ ቀደም ሲል መርዛማ ኬሚካሎች እና ቆሻሻዎች የሚጣሉባቸው፣ በወንዝ ዳርቻዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች ላይ የጎርፍ አደጋ ይጋርጡ የነበሩት እነዚህ አካባቢዎች፤ አሁን ላይ ወደ አረንጓዴ፣ ጤናማ እና ለሕይወት ምቹ ወደሆነ የከተማ ቦታነት እየተቀየሩ መሆኑንም ገልጸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታም፤ የንግድ እና የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ተቀናጅተው መገንባታቸው፤ የአካባቢ ጥበቃ እና የኢኮኖሚ ዕድገት ከዚህ ቀደም ከነበረው ያልተናበበ ሥራ ተላቀው በጥናትና በጋራ ግብ ተባብሮ መሥራት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ስለመሆኑ አመላክተዋል። ‎ይህ ፈጣን የልማት ሥራ አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ ይበልጥ የተሳሰረች፣ በኢኮኖሚ ንቁ እና ሰውን ማዕከል ያደረገች ከተማ የማድረግ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ ላይ መሰረት የተጣለበት የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ
በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ …
Jun 3, 2026 2998
በዮሐንስ ደርበው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር ሞላወርቅ አየለ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በዓለምም ሆነ በሀገራችን አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ ስለሆነው የደም ግፊት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቆይታቸውም፤ ለደም ግፊት አጋላጭ ስለሆኑ ምክንያቶችና ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄም እንዲሁም ከመድሃኒት አወሳሰድ ጋር በተያያዘ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን እና ምክረ ሐሳቦችን አቅርበዋል። · የደም ግፊት ምንድን ነው? ደም በደም ሥሮቻችን ሲያልፍ፤ የሚለካው መጠን “የደም ግፊት” እንደሚባል ዶክተር ሞላወርቅ ያስረዳሉ። የላይኛው (ሲስቶሊክ ወይም ከፍተኛው) የደም ግፊት መጠን ልብ በምትኮማተርበት ጊዜ ደም ወደ ደም ሥር ሲረጭ የሚለካው መሆኑንም ይገልጻሉ። የታችኛው (ዲያስቶሊክ ወይም ዝቅተኛው) የደም ግፊት መጠን ደግሞ ልብ ደም ለመቀበል ለአፍታ ዕረፍት በምታገኝበት ጊዜ የሚከሰት የግፊት ደረጃ መሆኑንም ይገልጻሉ። · የደም ግፊት ደረጃዎች እና ማስጠንቀቂያቸው ዶክተር ሞላወርቅ እንደሚሉት፤ የጤናማ ሰው የደም የግፊት መጠን 120 በ 80 እና በታች መሆን ይኖርበታል። በሌላ በኩል ግን ይላሉ፤ የላይኛው ከ120 እስከ 129 የታችኛው ደግሞ ከ80 በታች ከሆነ “ከፍ ያለ ወይም የጨመረ የደም ግፊት ደረጃ” ይባላል። የላይኛው ከ130 እስከ 139 ወይም የታችኛው ከ80 እስከ 90 ከሆነ ደግሞ “ደረጃ አንድ የደም ግፊት” እንደሚባል ያስረዳሉ። የላይኛው ከ140 በላይ ሲሆን እና የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ ደግሞ “ደረጃ ሁለት የደም ግፊት” እንደሚባል ነው የሚገልጹት። በሌላ በኩል “የከፋ የደም ግፊት ደረጃ” የሚባል እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም የላይኛው ከ180 በላይ እና የታችኛው ከ120 በላይ ሲሆን ነው በማለት ያብራራሉ። · ለደም ግፊት መጨመር መንስዔዎቹ ምንድን ናቸው? በዋናነት ሁለት ዓይነት የደም ግፊት መኖሩን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ ከፍተኛ የደም ግፊት እና መንስዔው የሚታወቅ የደም ግፊት መሆኑን አስረድተዋል። በዋናነት ወይም በአብዛኛው ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ ደም ግፊት የሚባለው መሆኑን ገልጸው፤ በርካታ መንስዔዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ቢገመትም ሁሉም በውል እንደማይታወቁ ያነሳሉ። ከበርካታ መንስዔዎቹ መካከልም፤ በቤተሰብ የሚወረስ (ተላላፊ)፣ አካባቢያዊ ምክንያቶች እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ የሚሉት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል። የአኗኗር ዘይቤ ሲባልም፤ የአመጋገብ ሥርዓት በተለይም ጨው የበዛበት ምግብ፣ ክብደት መጨመር፣ አካባቢያዊ ሁኔታዎች (አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ)፣ የስኳር ታማሚ መሆን የሚሉት ይጠቀሳሉ ይላሉ። · ለደም ግፊት በተለይም እነማን ተጋላጭ ናቸው? ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የደም ግፊት የመከሰት ዕድሉም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በዚህም መሠረት ባብዛኛው ዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። እንዲም በቤተሰብ የደም ግፊት ኬዝ ያለባቸው ሰዎች፣ የማንነት ሁኔታ (ኢትኒክ ግሩፕ) ለምሳሌ፡- በጥቁሮች (አፍሪካውያን)፣ በኤስያውያን፣ በደቡብ ኤስያውያን ላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ሊከሰት እንደሚችል ይገልጻሉ። እንደ ዶክተር ሞላወርቅ ማብራሪያ፤ በአጠቃላይ አጋላጭ ምክንያቶች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ። አንደኛው፡- ልንከላከላቸው (ልንቀንሳቸው) የምንችላቸው መሆናቸውን በመግለጽ ይህም የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል፣ ክብደት መቀነስ፣ አልኮልና ሲጋራ ማቆም እና መሰል መሆናቸውን አብራርተዋል። ሁለተኛው፡- ልንከላከላቸው የማንችላቸው መሆናቸውን ገልጸው ይህም፤ የዕድሜ መጨመር፣ የማንነት ሁኔታ (ኢትኒሲቲ) እና በቤተሰብ የሚተላለፍ የሚሉትን ጠቅሰዋል። · የደም ግፊትን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል? የደም ግፊ ከተከሰተ መቆጣጠር እንጅ ማዳን እንደማይቻል ገልጸው፤ ከላይ እንደተጠቀሰው አስቀድሞ መከላከል ወይም ማዘግየት የሚቻል እና መከላከል የማይቻል የደም ግፊት ደረጃ መኖሩን አስረድተዋል። · የደም ግፊት በውል የሚታወቅ ምልክት አለው? የደም ግፊት ሲከሰት ምልክት እንደሌለው በማንሳት፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ “ዝምተኛው ገዳይ” እስከመባል መድረሱን ዶክተር ሞላወርቅ ያነሳሉ። ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ግን፤ በአንድ ወይም በሁለት የሰውነት አካል ላይ ችግር ሊደርስ እንደሚችል ከዚህም ሲያልፍ እስከ ሞት እንደሚያደርስ ይጠቅሳሉ። በተያያዘም፤ የራስ ምታት፣ የዐይን ብዥ ብዥ ማለት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የድካም ስሜት፣ አንገት የመያዝ ዓይነት ስሜቶች የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ሊስተዋሉ የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል። አክለውም፤ በአብዛኛው በሕብረተሰቡ ላይ የደም ግፊት ምልክት ሳያሳይ ከፍተኛ ደረጃ ይደርስና ድንገት በጨመረ ጊዜ፤ ለሞት፣ ለአደጋ፣ ለልብ ድካም፣ አጣዳፊ ለሆነ የልብ ህመም፣ በጭንቅላት ላይ የደም መፍሰስ፣ የኩላሊት ድክመት፣ በደም ሥሮች በአግባቡ ደም እንዳይተላለፍ ማድረግ፣ ለዐይነ ስውርነት መዳረግን ጨምሮ መሰል ጉዳቶችን ሊያስከትል እንደሚችል አስገንዝበዋል። · መድኃኒት አወሳሰድ ላይ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ዶክተር ሞላወርቅ እንደገለጹት፤ አንድ ሰው ደም ግፊት እንዳለበት ከተነገረው በኋላ ሕክምናውም እንደ ደም ግፊቱ ደረጃ ይለያያል። ይህንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ የላይኛው ከ120 እስከ 129 ከሆነ “የጨመረ ግፊት” ይባላል፤ እዚህ ላይ ሰውየው ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አመጋገቡን እንዲያስተካክል፣ ስፖርት እንዲሠራ፣ ክብደት እንዲቀንስ፣ ሱስ (ሲጋራ፣ አልኮል) እንዲቀንስ ክትትል ይደረጋል ብለዋል። ስለዚህ መድኃኒት ሳይጀምር የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል የደም ግፊቱን ሊቀንሰው (ሊቆጣጠረው) ይችላል ማለት ነው ሲሉም ይገልጻሉ። “ደረጃ አንድ ግፊት” የሚለው ላይ ከደረሱ ግን ሕክምና የሚጀምሩም የማይጀምሩም እንዳሉ ተናግረዋል። ይህም ማለት የላይኛው ከ130 እስከ 139 የታችኛው ከ80 እስከ 90 ከደረሰ ሕክምና የሚጀምሩት የስኳር ህመም ያለባቸው፣ የስትሮክ ህመም ያለባቸው፣ ከልብና ደም ሥር የተገናኙ ህመሞች ያሉባቸው ከሆኑ ቢያንስ አንድ የግፊት መድኃኒት መጀመርና ክትትል ማድረግ አለባቸው ይላሉ። በሌላ በኩል ግን ይላሉ ዶክተር ሞላወርቅ፤ ሰዎች “ደረጃ ሁለት ግፊት” ላይ ከደረሱ (የላይኛው ከ140 የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ) ሁሉም መድኃኒት መጀመር እንዳለባቸው በአጽንዖት ገልጸዋል። የሚጀምሩት መድኃኒትም አሁን ባለው በተሻሻለው የሕክምና ዘይቤ ሁለት መድኃኒቶች የሚጀምሩበት ሁኔታ እንዳለ ነው የሚያስረዱት። የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ግን ለሁሉም የግፊት ዓይነቶች መሠረት (የሚመከር) መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ መድኃኒት ጀምሬያለሁ ብሎ የአኗኗር ዘይቤው ላይ ቸልተኝነት ሊኖር እንደማይገባም ነው የሚመከሩት። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከግፊት ጋር በተያያዘ ወደ ሆስፒታል መጥተው የሚታከሙ ታካሚዎች አብዛኞቹ፤ ጀምረው ያቋረጡ፣ ለመጀመር ፍላጎት የሌላቸው፣ ቅድመ ምርመራ ባለማድረግ ምክንያት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ የተጎዱ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። ስለዚህ የግፊት መድኃኒት ከተጀመረ ሊቋረጥ እንደማይችል አስጠንቅቀዋል። በየጊዜው ክትትል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አክለዋል። በሂደት እንደ ግፊቱ ሁኔታ መድኃኒቶች ሊቀነሱም ሊጨመሩም እንደሚችሉ አመላክተዋል። · የመስፋፋት ደረጃ የዓለም ጤና ድርጅት በ2024 ያወጣውን መረጃ ዋቢ አድርገው፤ 1/3ኛው የዓለም ሕዝቦች በደም ግፊት እንደሚጠቁ ዶክተር ሞላወርቅ አንስተዋል። ከእነዚህ መካከልም፤ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ገደማው በአንድም በሌላም ምክንያት ከደም ግፊት ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ጠቁመዋል። አብዛኞቹ የደም ግፊት ታማሚዎች ቁጥር የሚመዘገበው ደግሞ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ሀገራችንን ያካትታል ሲሉ ገልጸዋል። በሀገራችን ደረጃም ይላሉ ዶክተር ሞላወርቅ፤ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ባይኖሩም ከግፊት ጋር በተያያዘ በ2001 ላይ በ35 ሳይቶች የተጠኑ ጥናቶች ውጤቶች እንደሚያመላክቱት ከ21 እስከ 25 በመቶ ያህሉ ሕዝብ በደም ግፊት የሚጠቃ ነው ይላሉ። በአብዛኛው ደግሞ ከተማ ላይ እንደሚበዛ ጠቁመው፤ በተለይም አዲስ አበባ ላይ እስከ 30 በመቶ እንደሚደርስ የጥናቶቹ ውጤቶች ማመላከታቸውን ተናግረዋል። አብዛኞቹ ኬዞች ደግሞ ዕድሜያቸው ከፍ ያለ፣ ክብደታቸው የጨመረ፣ አልኮል እና ሲጋራ የሚጠቀሙ እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን አስረድተዋል። እንደ ዓለም አቀፍ ደረጃም ኬዙ ካለባቸው መካከል ግማሽ ያህሉ ግፊት እንዳለባቸው እንኳን እንደማያውቁ ነው የሚገልጹት። ለግፊት ሕክምና ትክክለኛ ክትትል አድርገው ግፊታቸውን በአግባቡ የሚቆጣጠሩት ከ 5 ሰዎች 1 መሆኑንም ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል። · ምክረ ሐሳብ በሀገራችን በሕብረተሰቡ ዘንድ ለደም ግፊት መለካት ኬዙ ከተገኘም የሕክምና ክትትል የማድረግ ሁኔታዎች ዝቅተኛ መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ሕብረተሰቡ የደም ግፊት ምልክት ሳያሳይ ከአካል ጉዳት እስከ ሞት ሊያደርስ እንደሚችል ተገንዝቦ፤ የደም ግፊቱን የመለካት ልምምዱን ሊያዳብር እንደሚገባ ዶክተር ሞላወርቅ መክረዋል። በሌላ በኩል እንደ ሀገራችን ባሉ ሆስፒታሎች በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም መቋረጥ (ስትሮክ) ካለባቸው ሰዎች ከ70 እስከ 85 በመቶው ከደም ግፊት ጋር በተያያዘ የሚከሰት መሆኑን ገልጸው፤ ድንገተኛ ግፊት መጨመር ከልብ እና ከደም ሥሮች ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዓለምም ሆነ እንደ ሀገር አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንደኛው ግፊት መሆኑንም አረጋግጠዋል። ስለዚህ የደም ግፊትን መለካት፣ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል፣ ከሱስ መራቅ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ለጤናማ ሕይወት ከፍተኛ ሚና እንዳለው መክረዋል።  
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 13739
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 7623
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 13397
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 11858
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 79524
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 64425
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 44790
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 42362
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 32752
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 32206
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 31677
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 30962
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 79524
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 64425
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 44790
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 42362
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም --
Jun 5, 2026 7017
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 6556
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም