ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቡርኪናፋሶ አቻው ተሸነፈ


አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ከቡርኪናፋሶ ጋር ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 1 ተሸንፏል።

ማምሻውን በኦገስት 4 ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ፒዬር ላንዲ ካቦሬ በ64ኛው፣ በ82ኛው እና በ96 ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

ቢኒያም አይተን በ84ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ቡርኪናፋሶ በ21 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ በጥሎ ለማለፍ ከሚሳተፉ አራት የአፍሪካ ሀገራት አንዷ የመሆን እድሏን አስፍታለች።


በዚሁ ምድብ ማምሻውን በተደረገው ጨዋታ ግብጽ ጊኒ ቢሳውን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ለዓለም ዋንጫ ያለፈው ቡድኑ በ26 ነጥብ ምድቡን በመሪነት አጠናቋል።

በዚሁ ምድብ በተደረገው ጨዋታ ሴራሊዮን ጅቡቲን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም