ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለአምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) የስራ መመሪያ ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለአምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) የስራ መመሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ)፦ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ለተመደቡት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ተመድበዋል።
አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በመቀበል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አማካኝነት ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለአምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ እና ጅቡቲን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ የሥራ መመሪያ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ተገኝተዋል።
አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል።