ቀጥታ፡

ቀሪ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ሊፈቱ የሚገባው በሁለቱ አገራት አቅም፣ የጋራ ጥረት እና ብልሃት ብቻ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ)፦ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የግብጽ አምባሳደር አባይዳ ኤ ኤል ዳንዳራዊን የሹመት ደብዳቤ ዛሬ ተቀብለዋል።

ኢዜአ ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፕሬዝዳንቱ ከአምባሳደሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አንስተዋል።


 

በሁለቱ አገራት መካከል ቀሪ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ቢኖሩም በሁለቱ ሃገራት አቅም፣ የጋራ ጥረት እና ብልሃት ብቻ የሚደረስባቸው መሆኑንም አስረድተዋል።


 

አገራቱ ግንኙነታቸውን ግብርናን ጨምሮ በኢንዱስትሪ፣ በማኑፋክቸሪንግና በሌሎች በርካታ ዘርፎች መቀጠል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም